es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 129 suscriptores, ocupando la posición 5 230 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 226 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 129 suscriptores.

Según los últimos datos del 31 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 520, y en las últimas 24 horas de 7, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 22.41%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.30% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 597 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 653 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 28.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 01 noviembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 129
Suscriptores
+724 horas
+197 días
+52030 días
Archivo de publicaciones
#ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ_ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3_ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡ #በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን ("ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ እናቴ ሆይ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ "እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ..." ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤ * በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡ * ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡ * አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡ * በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው * የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡ * በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡ (ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡) ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ (ምንጭ፤ የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት፣ ከገድላት አንደበትና ዝክረ ቅዱሳን) /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ከቃና ዘገሊላ በዓል ትውስታ፤ (በመንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም)

#ወጽአ_ወገብአ_ በሰላም_፡፡ ከጥምቀት ትውስታ፤ #ቂርቆሶች በዓሉን ስዕላዊ(ድራማዊ) በማድረግ ተክነውበታል፤ (ፎቶዎቹን ይመልከቱ) #መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊዮሶች እንደ አድዋ ባንዲራ የቅዱስ ጊዮርጊስ ምልክት ባላበት ባንዲራ በማሸብረቅ የሚደርስባቸው አልተገኘም፤ #የደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖትና የጽርሐ ጽዮን ጰራቅሊጦስ ወጎላ ሚካኤል ከሕፃን እስከ ጎልማሰ የሰ/ት/ቤቶችን ስብጥር በማሰለፍ ቀዳሚ ነበሩ #የኮተቤ ደብረ ጽባሕ (ሲምሲ) ሚካኤሎች በባህላዊ አከባበር የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ የጥምቀት አከባበሮች በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው የታዩበት ነበር፤ #ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለሞች በአጥቢያቸው ከሚገኙ ማኅበራት ጋራ በመተባበር በሀዲያና በስልጤ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ለሌላውም ልምድ የሚሆን ነው (በሌላ ዘገባ ሰሞኑን እንመለስበታለን)፡፡ #ጎንደሮች 17ት አውሮፕላን ተጓዥ በቀጥታ የተሳተፈበትን በዓል በልዩ ሁኔታ አክብረውታል፡፡ # በጥምቀት ሌሊት በጨረቃ ላይ የጌታን መጠመቅ የሚያሳይ ስዕል ታየ # በዐረብ ሃገራት በባሕሬን የጥምቀተ ባህሩ ታቦታት ሲጠጉት እንደ ዮርዳኖስ ሲሸሽ ታየ /እኛ ይህንን ጻፍን፤ ሌሎችንም በዘንድሮ ጥምቀት የተመለከታችሁትንና ያሰማችሁትን ልዩ ልዩ ነገሮች ጻፉ)

በቃና ዘገሊላ፤ ዘገሊላ ከብካብ ኮነ፨ ሥርዐተ ማኅሌት ዘጥር ፲፪፥ ዘቃና ገሊላ (የምትመለከቱት ፎቶ ጌታችን በቃና ዘገሊላ ተዓምራት ያደረገበት የዶኪማስ ቤት ነው።) በኔትወርክ ም/ት ዘግየታችን በመለጠፋችን ይቅርታ እንጠይቀለን፨

#ጾመ_ገሃድ/#የገናና_የጥምቀት_ጾም/ (በብዙዎች ዘንድ የተጠየቀ) #አስቸኳይ_ለሌሎችም_ማድረስን_አትርሱ_shareeeeee_ #ገሃድ_ ማለት አግሀደ (ገለጠ፥ አሳየ) ካለው የተገኘ ሲሆን መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። ጾመ ገሀድ በልደትና በጥምቀት ዋዜማ የሚጾም ጾም ሲሆን ከ፯ቱ አጽዋማት አንዱ ነው። #ጋድ_ ማለት ደግሞ እጅ መንሻ፣ ስጦታ አንደማለት ነው። ጋዳ ካለው የተወሰደ ሲሆን ይህም ማለት ማክሰኞ ተጹሞ ለረቡዕ፥ ረቡዕ ተጹሞ ለኀሙስ፥ .... የሚሰጥ ስጦታ እንደማለት ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም (ጋዳ ዖፍ/ድጓ/፥ ጋዳ ያበውኡ ቁርባን- ቁርባንን እጅ መንሻ ይመጣሉ/ዝማሬ/) እንዲል፨ #አንድም_ ለልማዱ ጾም የሚጾመው በእለቱ ሲሆን የጋድ ጾም ግን በዋዜማው ያለው እለት ተጹሞ የእለቱ አለት የሚበለበት ስለሆነ ተውላጠ ጾም እንደማለት ጋድ ተባለ። #አንድም_ ጋድ_ የጠፍር ሰም ነው፤ ይኸውም ቁመቱ ከሁለት ክንድ የማይበልጥ የጠፍር ዐይነት ሲሆን አገልግሎቱም ላም ሲታለብ እግሮቿን ወድሮ ማሰሪያ ነው፤ ጋዱን ስጭን አንዲሉ፤ ታዲያ ከገሃድ ጾም ጋራ ምን ያመሳስለዋል ቢሉ ለምሳሌ ረቡዕ ቢውል ማክሰኞ ተጹሞ ለረቡዕ ተውላጥ(ለውጥ) በመስጠቱ ጾም ያልነበረ ማክሰኞን ልክ እንደላሟ እግር ከረቡዕ ጋራ አጣምሮ፥ ወድሮ፥ አንድ የሚያደርግ የጾም ዕለት ስለሆነ ጋድ ተባለ። #አንድም_ጋድ_ ማለት የማይዳሰስ፥ የማይታይ፣ ረቂቅ፥ ስውር አምላክ ከሚታይ ከሚዳሰስ ሥጋ ጋራ አንድ ሆነ፥ ተሳሰረ (እግዚአብሔር ቃል ከትስብዕት ጋራ ተሳሰረ፥ ተዋሐደ) ሲሉ ጋድ ብለውታል። /እንደ ላይ ቤት ትርጓሜ/፨ ይኸውም፤ ጥምቀት ማክሰኞ ሲውል ዋይዜማው ሰኞ እስከ ምሽት 12 ሰዐት ይጾማል፤ ጥምቀት ረቡዕ ሲውል ዋይዜማው ማክሰኞ እስከ ምሽት 12 ሰዐት ይጾማል፤ ጥምቀት ኀሙስ ሲውል ዋይዜማው ረቡዕ እስከ ምሽት 12 ሰዐት፤ ማክሰኞ እስከ 6(9) ሰዐት ይጾማል፤ ጥምቀት ዐርብ ሲውል ዋይዜማው ኀሙስ እስከ ምሽት 12 ሰዐት ይጾማል፤ #ጥምቀት_ቅዳሜ_ሲውል_ዋይዜማው_ዐርብ_እስከ_ምሽት_12_ሰዐት_ኀሙስ_እስከ_6(9)_ሰዐት ይጾማል፤ ጥምቀት እሑድ ሲውል ዋይዜማው ቅዳሜ እስከ 6 ሰዐት፤ ዐርብ እስከ ምሽት 12 ሰዐት ይጾማል፤ **ጥምቀት ሰኞ ሲውል ዋይዜማው እሑድ እስከ ምሽት ጠዋት 3 ሰዐት፤ ቅዳሜ እስከ 6 ሰዐት ይጾማል፤ #የጾሙ_ቀመር፤ ለጥምቀት ቀን ስጦታ(ልዋጭ) የሚሆን 12 ሰዐት መጾም ነው። ዋይዜማው ረቡዕና ዐርብ ላይ ሲውል ረቡዕና ዐርብ ራሳቸው እስከ 9 ሰዐት ጾም ስለሆኑ እስከ ምሽቱ 12 ሰዐት ተጹመው ዋይዜማቸው ማክሰኞና ኀሙስ እስከ 6(9) ሰዐት ይጾማል። ጥምቀት የሚውልበት ቀን ጥምቀተ ባሕሩ እስኪባረክ እስከ 3 ሰዐት ድረስ ይጾማል፤ ድምሩ 12 ሰዐት ይሆናል፨ #በባሕረ ሐሳብ ቀመርም ጥምቀት የዋለበትን ቀን ደግሞ የሚውለው ከ8 ዓመታት በኃዋላ ነው፨ (ማብራሪያውን ለሰጡን ለአራቱ ጉባኤያት መምህርና ለቅኔው ማዕበል፥ ለቅኔው ፈጣሪ ለሊቁ ከሃሊ በቃሉ መድኀኔ ዓለም ይስጥልን)

#ጌታ_ለምን_በሠላሳ_ዘመኑ_ተጠመቀ? 1. በሕገ ኦሪት መሠረት ለካህናት አገልግሎት መመረጥ የሚቻለው በ፴ ዘመን እንደነበረ ሁሉ እርሱም የሊቀ ካህናትን ተግባር፣የመምህርነቱንና የአዳኝነቱን ሥራ በ፴ ዘመኑ በጥምቀት ጀመረ፡፡ 2. አዳም እንደ ሠላሳ ዘመን ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በአርባ ቀኑ ልጅነትን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያጣውን ልጅነት ይመልስለት ዘንድ ነው፡፡ #የጥምቀት_ጥቅም_በጥምቀት_የሚገኝ_ጸጋ) ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ እንወለዳለን፡- ድህነትን እናገኛለን፡- የኃጢአት ሥርየትን እናገኛለን፡- ….. ፪...፫…፬…፭…. #በጥር_11_በጥምቀት_በዓል_የምንረጨውና_የምንጠመቀው_ጥምቀት_ለቡራኬ_ነው፡፡

(ሥርዐተ ማኅሌቱን ሁላችሁም ትጠቀሙበት ዘንድ በሁሉም አድባራት/ጥምቀተ ባሕር/ የሚቆመውን የየአድባራቱን ይትበሃል አዘጋጅተነዋል፤ መልካም በዓል፡፡ #ዘመነ_አስተርእዮ “አስተርእዮ” ቃሉ የግእዝ ሲሆን ተርእየ (ታየ፣ ተገለጠ) ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጕሙም በገሀድ መታየት በይፋ መገለጥ ማለት ነው፡፡ በጽርዕ ቋንቋም ኤጲፋኒ(Epiphany) ይባላል፡፡ ዘመነ አስተርእዮ ከጥምቀት በዓል (ጥር 11) አንስቶ አስከ ጾመ ነነዌ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ አስተርእዮ የተባለበት ምክንያትም የማይታየው የአምላክ አካልና ባሕርይ ከሚታየው የሰው አካልና ባሕርይ ጋር ተዋሕዶ የተገለጠበትና ማንነቱ በገሀድ (በዮርዳኖስ ባሕር) የታወቀበት፥ ምሥጢረ ሥላሴም የተገለጠበት ወቅት ስለሆነ ዘመነ አስተርእዮ ተባለ፡፡ በዚህ ዘመን የሚውሉ ማንኛውም በዓላት የአስተርእዮ በዓል ይባላሉ፤ ለምሳሌ ጥር 21 እመቤታችን በዓለ ዕረፍቷ ሆኖ ሳለ ‹‹የአስተርእዮ ማርያም›› ይባላል፡፡ #በዓለ_ጥምቀት_የጥምቀት_በዓል የጥምቀት በዓል በየዓመቱ ጥር 11 ዕለት ይውላል በዓሉ የሚጀምረውም ከጥር 10 ዕለት ጀምሮ ሲሆን፤ ኦሪት ለወንጌል አምሳል፣ መርገፍ እንደሆነች፤ በዘመነ ብሉይ የተሠሩ አጽዋማትና በዓላትም በዘመነ ሐዲስ ለተሠሩ አጽዋማትና በዓላተ አምሳል መርገፍ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያተ በብሉይ ይከበር በነበረው በበዓለ መጸለት(ዳስ በዓል) በዓለ ጥምቀት ገብቶበታል፡፡ ይኸውም እንደምን ነው ቢሉ በመጸለት ቀድሞ ካህናተ ኦሪት ለ7ት ቀናት ታቦት ይዘው ወንዝ ወርደው ድንኳን ተክለው ድባብ አጥልተው ጃንጥላ ጥለው ሕዝቡ እህል አከማችተው አባቶቻችን በኢያሱ መሪነት ውኃውን አቁሞ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻገራቸው እያሉ ያስቡበት ነበር፤ በዘመነ ሐዲስ በጥምቀተ በዓልም ካህናተ ወንጌል ታቦት ይዘው፤ ወንዝ ወርደው /ውሃ ከትረው/ ድንኳን ተክለው ድባብ አጥልተው ጃንጥላ ጥለው ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ሄዶ በእደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ ተጠመቀ እያው ያስቡበታልና፡፡ /ዘሌ.23÷39-43፣ ኢያ. 3÷16/ #ለጥምቀት_በዓል_ምዕመናን_የምንይዘው_ዥንጉርጉር_በትር_ምሳሌው፣ ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳው ሸሽቶ በአጐቱ በላባ ቤት ብዙ ዓመታት ስላገለገለ ለአገልግሎቱ ዥንጉርጉር ሆነው የሚወለዱት በጐች ለያዕቆብ እንዲደረግና ምልክት የሌለባቸውን ለላባ እንዲሰጠው አዘዘው፡፡ ያዕቆብም በጐቹ ምልክት ያለባቸው ሆነው እንዲወለዱ ዥንጉርጉር እንጨት ውኃ በሚጠጡበት ውስጥ ጨምሮ በጐቹም እንደበትሩ ዥንጉርጉር እንደወለዱ እናያለን፡፡ /ዘፍ. 30÷31/ ይህ ምሳሌ ነው፡፡ በጐቹ የምዕመናን ውኃው የጥምቀት አውራዎቹ የመምህራን አንድም የቀሳውስት የሚጸነሱት በትሩን እንጂ አውራውን እንደማይመስሉ ምዕመናንም ሥላሴን ይመስላሉ እንጂ ያስተማራቸውን መምህራንን ቀሳውስትን አይመስሉምና፤ እንጨቱ ዥንጉርጉር መሆኑ ጌታችን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው /አምላክ ወሰብእ/ ለመሆኑ ምሳሌ፤ ያዕቆብ የጌታ ላባ የዲያብሎስ ምሳሌ ነው፡፡ ምልክት ያላቸው ለያዕቆብ ምልክት የሌላቸው ለላባ እንደሆኑ ሀብተ ወልድ፥ ሕይወተ ልቡና ያላቸው ለጌታ፤ ሀብተ ወልድና ሕይወተ ልቡና የሌላቸው ለዲያብሎስ የመሆናቸው ምሳሌ ነው፡፡ ምዕመናን ዥንጉርጉር በትር መያዛቸው ሰው የሆነ አምላክ /አምላከ ወሰብእ/ ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ በመሠረተልን ጥምቀት ተጠምቀን ሀብተ ወልድና ሕይወተ ልቡናን አግኝተን የሥላሴ ልጆች መሆናችንን ለማሳየት ነው፡፡ #ጥምቀት_ አጥመቀ /አጠመቀ/ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣መዝፈቅ፣ማጥመቅ፣ሲሆን በተገብሮ ደግሞ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጠመቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪም አጠማመቅ፣ ጠመቃ፣ የማጥመቅና የመጠመቅ ሥራ፣ኀጽበት በጥሩ ውሃ የሚፈፀም፣ የበዓል ስም፤ ጌታችን የተጠመቀበት ዕለት ማለትም ነው፡፡ በብሉይና በሐዲስ ኪዳን የተለያዩ የጥምቀት ዓይነቶች አሉ እነርሱም፡- #ጥምቀት_በብሉይ_ኪዳን_ (የአይሁድ ጥምቀ፣ የኤሲያንስ ጥምቀትና የዮሐንስ ጥምቀት ነበሩ) #ጥምቀት_በሐዲስ_ኪዳን፤ ፩. #የጌታችን_ጥምቀት፤ #የጥምቀት_መሥራች_ማነው_በምንስ_ተመሠረተ? የጥምቀት መስራቹ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን አመሠራረቱም በትምህርት /ዮሐ.351/፣ በተግባር /ማር.19፣ ማቴ.313/ እና በትዕዛዝ /ማቴ.2813/ ነው፡፡ #ጥንተ_ጥምቀት_ጌታችን_መቼ_ተጠመቀ? ጥንተ ጥምቀት ማለት ጌታችን የተጠመቀበት ዕለት ማለት ሲሆን ጌታችን የተጠመቀውም ዓለም በተፈጠረ በ5531 ዓመተ ዓለም(በ31 ዓመተ ምሕረት)፤ በዘመነ ሉቃስ፤ በዕለተ ማክሰኞ፤ ጥር 11 ዕለት፤ ሌሊት በ10 ሰዓት ነው፡፡ በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ፍት.ነገሥ.አን.19፣ ድስቅ.29፣ ተረፈ.ቄርሎስ፣ ሉቃ.323/ #ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ_? ሀ. ምሥጢረ ሥላሴን ለመግለጥ ለ. ሰው /አዳም/ በበደል ምክንያት ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ሐ. የአዳምና የሔዋንን ዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ ‹‹የዕዳችንን ደብዳቤ ደመሰሰልን›› /ቆላ. 2$14/፣ ወሠጠጠ መጽሐፈ እዳሆሙ ለአዳም ወለሔዋን (ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸውን ቀደደላቸው) /ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ቊ.9/ ሠ. ትንቢተ ነቢያትን ለመፈፀም /መዝ.76$16/ ረ. በእርሱ ጥምቀት የእኛን ለመባረክ ሰ. የእግዚአብሔር ልጅ እንድንሆን /ገላ.3$26፣ገላ.4$4፣ሮሜ.8$14፣ዮሐ.1÷13፣1ኛ.ዮሐ.3÷1/ #ጌታችን_ለምን_በዮርዳኖስ_ተጠመቀ? ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፤ ትንቢቱን(/መዝ.113$1-8/)፣ ምሳሌውን(ዮርዳኖስ ከላይ ነቅዑ /ምንጩ/ አንድ ነው ዝቅ ብሎ ለሁለት ‹‹ዮር›› እና ‹‹ዳኖስ›› ተብሎ ይከፈላ….፣ ፣ዘፍ.14$14-20፣ መጽሐፈ ነገስት ካልእ 6$1 አንድምታ ና መጽ.ነገሥት ካልዕ 5$16 ምሥጢሩን (በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የአዳምንና የልጆቹን ደብዳቤ ለመደምሰስ/ቆላ.2$14፣ ኤፌ.2$15፣ ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ቊ.1/፡፡) ለመፈጸም ነው፡፡ #ጌታችን_ለምን_በውኃ_ተጠመቀ?  ትንቢቱ፡- ሀ. ‹‹ጥሩ ውሃንም እረጫችኋለሁ እናንተም ከርኵሰታችሁ ትነፃላችሁ›› ጥሩ ውሃ የተባለ የጥምቀት ውሃ ነው፡፡ /ት.ሕዝ.36$25/ ለ. ‹‹አቤቱ ውኖች አዩህ ውኖች አይተው ፈሩ›› /መዝ.76$16/ ሐ. ድሆችና ምስኪኖች ውኃ ይሻሉ /ኢሳ.41$17/ መ. ‹‹ወይቤ ኩሎሙ እለ ጸምዑ ይሑር ኀበ ማይ፣ እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውኃ ሂዱ›› /ት.ኢሳ. 55$1/  ምሳሌው፡- ዘፍ.1$2፣ አክሲማሮስ ዘሐሙስ #ጌታችን_ለምን_ወደ_ዮሐንስ_ሄደ_ለምንስ_በዮሐንስ_እጅ_ተጠመቀ? 1. ትህትናን ለማስተማር፡ 2. ለአብነትና ሥርዐትን ሊደነግልልን፡- #ጌታችን_በማን_ስም_ተጠመቀ? ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሌላውን ሰው በአንተ ስም፣ በባሕርይ አባትህ በአብ፣ በባሕርይ ሕይወትህ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለሁ አንተን ግን በማን ስም /ምን እያልኩ/ አጠምቅሃለሁ አለው›› ጌታችንም ‹‹ወልዱ ለብሩክ ከሳቴ ብርሃን ተሣሀለነ …፣ እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለን$ ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም፣ እነሆ የዓለምን ሀጢአት የምታስወግድ የእግዚአብሔር በግ /መስዋዕቱ/ እያልክ አጥምቀኝ›› አለው፡፡ /ዮሐ. 1÷30/

#የእግዚአብሔርን_የቃል_ኪዳን_ታቦት_ሌዋውያን_ካህናት_ተሸክመውት_ባያችሁት_ጊዜ_ከስፍራችሁ_ተነስታችሁ_ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ ‹‹#አነ_ውእቱ_ኖላዊ_ሔር_ (እውነተኛ ጠባቂ እኔ ነኝ)፡፡››፤ #መድኀኔ_ዓለም_ዘደብረ_ሰላም፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መለያ ዓርማ:: መድኀኔ ዓለም ዘደብረ ሰላም፤ ታላቁ ደብር ከዓመት ዓመት ውዳሴና ማኀሌት የማይቋረጥበት (የጥምቀት በዓል ተረኛ በሚሆንበት እንኳን ሳይቀር በጃንሜዳና በቤተክርስቲያንችን በ2ቱም ቦታ ላይ ማኅሌት የሚቆምበት ቅዳሴ የሚቀደስበት)፤ ውዳሴ ማርያም፣ ከስተተ አርያምና መስተጋብዕ በዜማ ከዓመት ዓመት የሚደርስበት........ ኦ ደብረ ሰላም ኢይተዓፀዉ አናቅጽኪ፤ ኢይጸልም ፀሐይኪ፤ ወኢየዓርብ ወርኅኪ፤ ....... ይበራህ ውዳሴኪ ወማኅሌትኪ፥ ወያፍርሁ ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር ምዕመንኪ፥ ይብዝሁ ወይተግሁ በሰላም ወበጥዒና ማኅበረ ካህናትኪ ....... -ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀ ኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኅ ኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡) -አብርሂ አብርሂ ደብረ ሰላም፤ ብርሃንኪ መድኀኔ ዓለም፡፡ (ብርሃንሽ መድኀኔ ዓለም ነውና ደብረ ሰላም ሆይ አብሪ ድመቂ፡፡)

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቀሳውስትና ዲያቆናት (አስተዳዳሪዎቹ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ፍቅረማርያም ምሕረቱ የደብረ ሰላም አስተዳዳሪና መልአከ ሰላም/ኋላ ሊቀ ሥልጣናት/ ቆሞስ ወልደ ሳሙኤል የመንበረ ጸባዖት አስተዳዳሪ ና መልአከ ገነት የመናገሻ ሀነተ ጽጌ አስተዳዳሪ/ (መስቀል ሲያሳልሙ የሚታዩት መነኰስ አባት የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም መጋቤ/ (ጥቁር ሰናፊር የለበሱት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች)

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ዲያቆናትና ደባትር መዘምራን