es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 369 suscriptores, ocupando la posición 5 633 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 187 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 369 suscriptores.

Según los últimos datos del 19 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -46, y en las últimas 24 horas de 37, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 22.37%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 7.87% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 438 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 210 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 22.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 20 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 369
Suscriptores
+3724 horas
+367 días
-4630 días
Archivo de publicaciones
በዓለ ጥንተ ስቅለተ መድኀኔዓለም መጋቢት 2016 ዓ.ም  ፎቶ ማስታወሻ  + ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ፥ በዕምርት ዕለት በዓልነ፡፡ (#በከፍተኛው_በዓላችን_ቀን_መለከትን_ንፉ፡፡) መዝሙረ ዳዊት ፹፥፫ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት  ::/    #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem .      www.finotehiwotsundayschool.com #ቀጨኔ_መድኀኔዓለም

እንኳን ለጥንተ ትንሣኤ እና ለጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ፅንሰት  በሰላም አደረሳቹህ #እግዚአብሔር_ዓለምን_ከፈጠረበት_ጥበቡ_ይልቅ_ከድንግል_ማርያም_ሰው_ሆኖ_ዓለምን_ያዳነበት_ጥበቡ_ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም፤ ፠ እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበት ጥበቡ፤ 7ቱ ዕለታትን፣ 20ው ዓለማትን፣ 22ት ሥነ ፍጥረታትን ካለመኖር ወደ መኖር፤ ከፈጠራቸውም ላይ አሻሽሎ አስገኘ ፠ ዓለምን ያዳነበት ጥበብ፤ሰማይና ምድር የማይወስኑት፤ ከጽርሐ አርያም በላይ ጠፈሩ፥ ከበርባሮስ በታች መሠረቱ፥ ለአድማስና ለናጌብ ዳርቻቸው የኾነ አምላክ  በአጭር ቁመትና በጠባብ ደረት ለሰው ልጅ ቤዛ ለመሆን ወደ ፈጠረው ምድር በፈጠረው አካል ላይ የሰማይ ዙፋኑን ሳይለይ መጥታል #ብስራትና  ፅንሰት በአንድ ዕለት ነው የተከናወኑት፡፡ #ኢየሱስ ክርስቶስ በማህፀነ #ማርያም የተፀነሰው ልክ ቅዱስ #ገብርኤል ‹‹ ትፀንሺያለሽ ›› ሲላት እርሷም “ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ” ‹‹ እንደቃልህ ይደረግልኝ ›› ብላ በተቀበለች ጊዜ የእግዚአበሔር ቃል በማህፀነ ድንግል ማርያም ተፀነሰ፡፡  አብ አፀናት መንፈስቅዱስ አነፃት ወልድ በተለየ አካሉ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ተዋሐደ (ሉቃ 1፤33)፡: እመቤታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕት መቅደሱ ናትና ፤ ነገሩን አስቀድማ ጠንቅቃ ትወቅ ሲል ቅዱስ ገብርኤልን ልኮታል ( ሉቃ ፩፥፳፮ -፳፷) ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡:ቅዱስ ገብርኤልም  ብርሃናዊ መልአክ መሆኑን ለማጠየቅ እና የሥላሴ ማደርያ መኾኗን ለማስረዳት  3 ጊዜ ተመላልሷል ፡፡  ሉቃ 1 ፥33  ማቴ 18፥ 16 #ሊቀ_መላእክት ቅዱስ ገብርኤልም በደስታ ተውጦ ለመላእክት ጉባኤ “በቅድስት ድንግል ማርያም የይሁንታ ቃል ምክንያት ዓለም ዳነች” ብሎ የምስራች አላቸው፡፡ ነቢዩ ሕዝቅኤል “… በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ” (ሕዝ.1፡26) ብሎ እንደገለጠው እግዚአብሔር አምላክ ለመላእክት በሰው ምሳሌ ተገልጦ ይታያቸው ነበር እንጂ እርሱን ገጽ በገጽ አያዩም ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ገብርኤል የፀንሰቱን ነገር ለመላእክት በነገራቸው ጊዜ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ቃል ሰው በመሆን በአካል ሊያዩት  እንደተቃረቡ ተረድተው ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማያውቅ ታላቅ የሆነ የደስታ ዝማሬ ዘመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ደስታቸው ድርብ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ደስታቸው የሰው ልጆች መዳን ሲሆን ሁለተኛው ግን አምላካቸውን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ለማየት በመብቃታቸው ነበር፡፡ #_1 ቅዱስ ገብርኤል ለማብሰር የተመረጠውም #በማብሠር የታወቀ ስለሆነ(መሳ 13) ሊቃ 1  #_2 #የስሙ ትርጓሜ ሥራውን ስለሚገልጽ ፡፡ ገብር ሰው ማለት ሲሆን ኤል ደሞ አምላክ ማለት ነው ስለዚህ  አምላክ ወሰብእ ማለት ነው (አምላክም ሰውም) ስለዚህ የአምላክ ሰው የመሆንን ምሥጢር እንዲያበስር ተልኳል ፡፡ #_3.#ሳጥናኤል አምላክ እኔ ነኝ ብሎ መላእክትን ባሸበራቸውጊዜ ‹‹ነቁም በበህላዌነ እስከ ነአምሮ ለአምላክነ (የፈጠረን ይህ አይደለምና ፈጣሪያችንን እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንጽና )   ብሏል፡፡ ይህን ያለበት አንደበቱ የአምላክን ሥጋዌ ለእመቤታቸን ለመንገር አብቅቶታል :: ይህ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት አምላክ በማኅፀነ ማርያም ያደረበትን የፅንሰቱን በዓል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት በማኅሌት፣ በቅዳሴ፣ በትምህርት መጋቢት ፳፱ ቀን ስታስብ ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት ውስጥ አንደኛውና የመጀመሪያው አድርጋ ታስበዋለች፡፡ ይህ በዓል በፆም ወቅት ሰለሚውል  መጋቢት 29 ቅዱስ አበው በሰሩልን ሥርዓት መሠረት ልዋጭ በዓሉን ታኀሣሥ 22 ብሥራቱን በድምቀት እናከብረዋለን ፡፡ ፍትሐ ነ አነድምታ አ.15 #ጥንተ ትንሣኤ «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግስ ሲሆን፡፡ «ትንሣኤ» ማለት = መነሣት፥ አነሣሥ፥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡ ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቆል  በሥጋ ከሞተበት ቀን መጋቢት 27 ፤ ሦስተኛው ቀን መጋቢት 29 ነውና ይህች ዕለት ቅድስት ትንሣኤው ውሎባታል  በከበረች ልዩ የሆነች ትንሣኤው የዓለም ድኀነት ሆነ ፡፡ በረቀቀ ጥበቡ በዚህች ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል ፡ያመ የጽንሰቱ በዓል ተደርቦባት ነው እንጂ ልናስበው የሚገባ ትልቅ ዕለት ነው :: /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

#ምስባክ #መጻጕዕ ዘመጋቢት ፳፮ ፣ ፳፯ ፣ ፳፰ የምስባኩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ https://terakiapp.page.link/ScsMfBfsWRAaw6i6A
#ምስባክ #መጻጕዕ ዘመጋቢት ፳፮ ፣ ፳፯ ፣ ፳፰ የምስባኩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ https://terakiapp.page.link/ScsMfBfsWRAaw6i6A

እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ #የቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም    ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ 112 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡  ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡) የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡ ✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡) www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

☆ እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን ☆ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ
+8
☆ እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን ☆ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ #ጥንተ_ስቀለት #ክርስቶስ_የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን #ከሆነ _እንደገና_በሌላ_ጊዜ_በዓለ_ስቅለትን_ማክበር_ለምን_አስፈለገ? #ጥንተ_ትንሣኤ #ጥንተ_ስቀለት የጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ፳፯ ቀን ሰማያዊ አምላክ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው #በገዛ_ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ #በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል ፡፡ የመጋቢት ጽንሰት ( ብሥራት ) ታሕሣስ 22 እንደሚከብረሁ ሁሉ ማለት ነው ፡፡ ፠#ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ከሆነ እንደገና በሌላ ጊዜ በዓለ ስቅለትን ማክበር ለምን አስፈለገ? ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ ሲሆን ከመቃብር የተነሣውም በዕለተ እሑድ በመሆኑ #ስቅለት ከዕለተ ዓርብ፣ #ትንሣኤም ከዕለተ እሑድ፣ #ዕርገት ደግሞ ከዕለተ ሐሙስ እንዳይወጡ፤ ሌሎቹም በዓላትና አጽዋማት በተወሰነላቸው ቀን እንዲውሉ ማድረግ ይቻል ዘንድ የቀድሞ አባቶችና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሰባት አዕዋዳት አዘጋጅተው እና ቀምረው ሁሉም ሥርዓቱን ጠብቆ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቀን እንዲከበር የወሰኑ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት ጥንተ ስቅለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በየዓመቱ እየታሰበ በዓለ ስቅለቱ ደግሞ ከሰሙነ ሕማማቱ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በዕለተ ዓርብ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በአክፍሎትና በስግደት እንዲከበር በማድረግ ሕግና ሥርዓት ስለሠሩ በዚሁ መሠረት ይፈጻማል:: #ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጌታችን #የጽንሰቱ_በዓል በታላቅ ድምቀት የሚከበርበት ቀን ከመሆኑ የተነሣ በዓሉን በዓል ተጭኖት ነው እንጂ ፫ኛው ቀን መጋቢት ፳፱ኝም ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት #ጥንተ_ትንሣኤ በመሆኑ እንደ ጥንተ ስቅለቱ ሁሉ ጥንተ ትንሣኤውም ከበዓለ ጽንሰቱ ጋር አብሮ የሚታሰብ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡ #በኢትዮጵያ_በዋነኛነትና_በግንባር_ቀደምትነት_የስቅለት_በዓል_የሚከበርበት #ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡ #142 ዓመታትን ያስቈጠረው ጥንታዊው የጮቢ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም፡፡ በ1868ዓ.ም. የተመሠረተ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን በጀልዱ ወረዳ በጮቢ የሚገኝ፡፡ #በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤ ፤ ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳምና ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ. ፠ አንድ ላይ ያሉት፤ ✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤ ✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም ✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም ✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና ✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ ✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ ✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (ቦሌ የመድኀኔዓለም ታቦት ) ✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም ✤9.#ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ 110 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡) 10 #መናገሻ_ጋራ_መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡ 11. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡ 12. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል) #በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርባችው ፪ቱ ታላላቅ ገዳማት ፩ኛ. ኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን ፪ኛ. #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤትየተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/finotehiwotte http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

ሞተ አሐዱ ቤዛ ኩሉ ፥ ልዩ የበዓለ ንግሥ ጉባኤ በቀጨኔ ደብረ ሰላም ፥ መድኀኔዓለም ፥ መጋቢት 25 ፣ 26 ፣ 27 ።
ሞተ አሐዱ ቤዛ ኩሉ ፥ ልዩ የበዓለ ንግሥ ጉባኤ በቀጨኔ ደብረ ሰላም ፥ መድኀኔዓለም ፥ መጋቢት 25 ፣ 26 ፣ 27 ።

ሞተ አሐዱ ቤዛ ኩሉ ፥ ልዩ የበዓለ ንግሥ ጉባኤ በቀጨኔ ደብረ ሰላም ፥ መድኀኔዓለም ፥ መጋቢት 25 ፣ 26 ፣ 27 ።
ሞተ አሐዱ ቤዛ ኩሉ ፥ ልዩ የበዓለ ንግሥ ጉባኤ በቀጨኔ ደብረ ሰላም ፥ መድኀኔዓለም ፥ መጋቢት 25 ፣ 26 ፣ 27 ።