es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 045 suscriptores, ocupando la posición 5 280 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 240 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 045 suscriptores.

Según los últimos datos del 29 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 518, y en las últimas 24 horas de 1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.50%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.35% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 090 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 660 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 33.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 30 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 045
Suscriptores
+124 horas
+917 días
+51830 días
Archivo de publicaciones
እንኳን ደስ አለን፡፡ (በሰንበት ትምህርት ቤታችን ታሪክ 5ት አባላት በአንድ ቀን ጋብቻቸውን የፈጸሙበት ቀን፤ 7ት ተጋቢዎች ደግሞ በደብራችን በአንድ ቀን ሥርዐተ ጋብቻቸውን የፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡) /በዕለተ መድኀኔ ዓለም ወበዓለ ዳግም ትንሣኤ ጋብቻችሁን የፈጸማችሁ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በዳግም ምጽአት በቀኝ ያቁማችሁ፡፡/ ‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሚያዝያ ፳፯/፳፻፲፩ ዓ.ም. (በዕለተ መድኀኔ ዓለምና በዳግም ትንሣኤ ቀን) ጋብቻችሁን የፈጸማችሁ የደብራችን አገልጋይና ፭ት የሰ/ት/ቤታችን አባላት፤ * #መሪጌታ_ኃይሉ_ለገሠ_ከፍሬሕይወት ጋር #ይደነቁ_ዘነበ_ከከበደ ጋር #ዳንኤል_ንጉሤ_ከሠናይት_አበበ ጋር #ገነት_ዳንኤል_ከቢንያም ኤርምያስ ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

/በዕለተ መድኀኔ ዓለም ወበዓለ ዳግም ትንሣኤ ጋብቻሽን የፈጸመሽው እኅታችን ትርሲት ጉልላት ከእነባለቤትሽ፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በዳግም ምጽአት በቀኝ ያቁማችሁ፡፡/ ‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሚያዝያ ፳፯/፳፻፲፩ ዓ.ም. (በዕለተ መድኀኔ ዓለምና በዳግም ትንሣኤ ቀን) ጋብቻሽን የፈጸመሽው የሰ/ት/ቤታችን አባል፤ * #ትርሲት_ጉልላት_ከግርማ ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#ዜና_ዕረፍት ታሪካዊ ነክ በሆኑ ስብከታዊ ትምህርቶቻቸውና ጽሑፎቻቸው እጅጉን የሚታወቁት፤ #ብፁዕ_አቡነ_ገሪማ_(ዶ.ር.) #ሚያዝያ_27_በዕለተ_መድኀኔ_ዓለም_ዐረፉ፤ #የግብዓተ_መሬት_ሥነ_ሥርዐቱም_ረቡዕ_ሚያዝያ_30/2011ዓ.ም. #በቅድስት_ሥላሴ_ቤ/ክ ይካሄዳል፡፡ ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከልም፤ *የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የሚል መጽሐፍ *ከ30 በላይ የትምህርታዊ ጽሑፎች ያካተተ ስብስብ በ2006 ዓ.ም. የሳተሙት መጽሐፍ *የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻ በሚለው ድንቅ እስትጉቡእ (ስብስብ) መጽሐፍ ላይ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና መንግሥት በየዘመናቱ›› የሚል ጽሑፍ አዘጋጅተዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ የተወለዱት በሰሜን ሸዋ በ1937 ዓ.ም. ሲሆን፤ ማዕርገ ዲቁናን ከግብጻዊው አቡነ ቄርሎስ፣ ማዕርገ ምንኵስናን ደግሞ መጋቢት 1973 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ በመንፈሳዊ ትምህርት ዜማ፥ ቅኔ፥ አቋቋም ከተለያዩ መምህራን ቀስመዋል፡፡ ዘመናዊ ትምህርታቸውን፤ በሐረር የራስ መኰንን አዳሪ ትምህርት ቤትና የከፍተኛ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት ተምረው አጠናቀዋል፡፡ በ1958 ዓ.ም. ለከፍተኛ ትምህርት ከሌሎች አራት የቤተ ክርስቲያን ወጣቶች ጋራ ወደ ሩማንያ ተልከው በታሪክ ትምህርት የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም በነገረ መለኰት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ ከጵጵስና በፊት ስማቸው ዶ/ር ግርማ ወልደ ቂርቆስ ነው፡፡ በሓላፊነትና በአገልግሎት ከሠሩባቸው መካከል፣ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪና ዋና ጸሐፊ፣ የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ሓላፊ፣ በብሥራተ ወንጌል ራዲዮ ጣቢያ በመምህርነት ይገኙባቸዋል፡፡ #ጵጵስናን በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ሐምሌ 9 ቀን 1973 ዓ.ም. ተቀብለው፤ በሰሜን ሱዳን ካርቱም ኤጲስ ቆጶስነት የተሾሙት ብፁዕ ዶር. አቡነ ገሪማ፣ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት፣ ወደ ኋላም የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው አገልግለዋል፡፡ #በተለይ በአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ክህነት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤቱንም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቱንም (የአመራሩንም የአስፈጻሚውንም) ሓላፊነቶችን ደርበው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የቅድስት ሥላሴ እና የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጆች ዲን፣ በመንበረ ፓትርያርኩ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ቢሮ ዋና ጸሐፊ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ እንዲሁም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊ ሆነው ያገለገሉበበት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው ካላቸው መንፈሳዊነትና የዓላማ ጽናት የተነሣ በዕርግና ምክንያት ያጋጠማቸውን ሕመም ተቋቁመው እስከ ማዕዶት ሰኞ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ከቆዩ በኋላ፤ ሕመሙ እያየለባቸው ስለመጣ በቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ ሰጭነት ሚያዝያ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተው ሕክምና እየተከታተሉ ሳለ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም አንቀላፍተዋል፡፡ የብፁዕ አባታችን ቡራኬ ይድረሰን፨

#የትንሣኤ_ልዩ_ዝግጅት፤ #የዐርብ_ጕባኤ_፻፳፯ኛ_ሳምንት #ሚያዝያ_፳፭/፳፻፲፩ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ #በሰዐቱ_ይገኙ!!!!!!!! እንዳያመልጥዎ!! በእለቱ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮችና ውዳሴ ማርያም በዜማ ይካሄዳል:: ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት::

አስቸኳይ ማስተካከያ፤ ሚያዝያ 23 ሰሙነ ፋሲካ ላይ ስለዋለ፤ ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ደግሞ የሚውሉ በዓላት ማኅሌታቸው የጌታችን የሰሙነ ፋሲካን እንጂ የቅዱሳንና የቅዱሳት መልክእ ማኅሌት ስለማይቆም፤ ቀን ላይ ለጥፈነው የነበረው ሥርዐተ ማኅሌት በዚህኛው እንዲስተካከልና፤ ላላስተካከሉ እንዲያስተካክሉ ታደርሱ ዘንድ እናሳስባለን፡፡ ... በነገራችን ላይ በጎንደርና በአዲስ አበባ ባሉ ታላላቅ አድባራት (ለምሳሌ እንደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም፤ መናገሻ ገነተ ጽጌ፤ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም፤ መካነ ሥላሴ /መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ/ ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ማኅሌት ይቆማሉ፡፡ የጎንደር አድባራት ደግሞ ከዳግም ትንሣኤ በኋላ ያለውን ተጨማሪ አንድ ሳምንትን ‹‹ጠፈረ ጽድቅ›› የሚለውን ማኅሌት በልዩ ሁኔታ ይቆማሉ፡፡ /ለዚህ ሥርዐተ ማኅሌት አስተዋጽዖ ላደረጉት፤ ለሊቀ ጠበብት ይልማ (የደብራችን ሊቀ ጠበብት)ና ለሊቀ ጠበብት ፀጋዬ (የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሊቀ ጠበብት) አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይስጥልን፡፡

ዛሬ ሚያዝያ 22/2011ዓ.ም. ወንድማችንና መምህራችን ስለሺ ብርሃኑ (ብርሃነ መስቀል) በሥጋ ከተለየን 6ኛ ዓመቱ ኾነ፤ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጋር ይደምርልን፥ ነፍስ ይማርልን፡፡ #መሐራ_እግዚኦ_ለነፍሰ_እኁነ_ብርሃነ_መስቀል፡፡ ያረፈበት ቀንም ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ7506 ዓመት(በፀሐይ)፤ በ2006 ዓመተ ምሕረት (በፀሐይ)፤ በ58 ዐውደ ቀመር፤ በወንጌላዊ ማርቆስ፤ በ1 ጥንተ ዮን፥ በ6 እንድክትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፤ በሚያዝያ ወር በ22ኛ ቀን (በፀሐይ)፤ በ26 ሠርቀ ሌሊት፤ በ1730 ዓመተ ሰማዕታት ነው፡፡ በዕለቱ ከቀረቡ ግጥሞችና ቅኔዎች የተወሰኑትን እነሆ ብለናችኋል፡፡ (ግጥሞቹና ቅኔዎቹ ከሕይወቱ ታሪክ ጋር /በፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት አገልጋይ ከመኾኑ ጋር፣ 2ት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ከማሠራቱ ጋር፣ በዳግማዊት ስሪንቃ ቅድስት አርሴማ ጠበል ቦታ ከማገልገሉ ጋር ….. የተመሳጠሩ ድንቅ የሆኑ ግጥምና ቅኔዎች ናቸው)፡፡ #ስለሺ ወንድሜ በነበረህ ለዛ፣ በሚጥመው ቃልህ በስብከት መዐዛ፣ ቀና በል ተናገር ዝምታ አታብዛ፣ ሁሉም ያልፋልና ድንገት እንደዋዛ፡፡ #ክፉ ሰው ሞት በሰው ላይ ነገረ ሠሪ፣ ለምድር አሽከርካሪ ለሰማይ አብራሪ፣ ደኅና ሰውን መስሎ የቅርብ ዘመድ መካሪ፣ ደርሶ የሚያጣላ ፍጡርን ከፈጣሪ፣ ክፉ ሰው ሞት በሰው ላይ ነገረ ሠሪ፣ ዛሬ ምን በደለው ስለሺ የብዙዎች(የብዙኃን) አስተማሪ፡፡ #በነገረ ሠሪ ኅልፈት ክፉ መሃለኛ፣ ከፊትህ ብትርቅ ድንገት ሕይወት ወረተኛ፣ የነበረው ቀርቶ ብትሆንም ብቸኛ፣ ብቸኛ ነኝ አትበል ስለሺ በሠራኸው ሥራ ነህና ዝነኛ፡፡ #ስለሺ ለብዙዎች ብሎ የጸለየው ጸሎት ተግቶ፣ በማርያም ምልጃ ከእግዚአብሔር ተሰምቶ፣ ሲሻው የነበረ እንዲሰጥ ጽዋ ሞት ተቀድቶ፣ ተቀበለ ዛሬ ከቅዱስ ዑራኤል እጅ ነስቶ፡፡ #ሥጋም በምድር ላይ መከራን ታገሺ ነፍስም በሰማይ ላይ በገነት ንገሺ፣ ክርስቶስ በዳግም ትንሣኤ እስኪነግስ ስለሺ፡፡ #ጕባኤ_ቃና_ቅኔ ……. ቃልየ አጽምዕ እግዚኦ ወለቡ ጽራሕየ ……. በሕማም ወጸዕር ሶበ ወጽአት ለብርሃነ መስቀል ነፍሱ፤ እጼ ወዝኅር አዝማዱ ንብረተ ሥጋሁ ወረሱ፡፡ #ሥላሴ_ቅኔ …….. ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ …….. ብርሃነ መስቀል በአዕይንቲሁ ወኢይርዓይ መልክዐ ብእሲት ዓለም አበሳ ዘብዙሃነ ፈተነ፤ ሥጋ ሰብእ ዓይነ እንቲአሁ በልብሱ ከደነ፤ በቃለ ሐዲስ ወንጌል እምንእሱ እስመ አእመረ ወኮነ፤ ወበዝ ዓለም እስከ ሀለውነ፤ ኢርዕዮተ ዓለም ብእሲት ዘገብሮ እኁነ፣ ለኵልነ ትምህርተ ይኵነነ፡፡ #መወድስ_ቅኔ ……. ፍትሃ ሊተ እግዚኦ ወተበቀል በቀልየ ………. እንበለ ኢምንት ፍጥረተ ኀበ ተኀሰበ በዓይነ አብዕልት ሕዝብ ወበእግረ ንዑስ ወዐቢይ፤ ዘይትከየድ ዘልፈ መቃብረ ሥጋ ነዳይ፤ ሞተ አቤል ወርኅ ጊዜ አንገሦ፤ በዓለም ተፈጥሮተ ሥጋ ዘብዙኅ ጌጋይ፤ ይቀውም ከመ ቆሙ ዲበ ዘገፍዕዎ ቅድመ ገበርተ ዓመጻ ወእከይ፤ ንሕነኒ ይደልወነ ከመ ንጸልይ፤ ጸሎተ ንስሓ መንገሌሁ ለአምላከ ምድር ወሰማይ፤ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ እምነ አእላፍ ኅሩይ፤ በኢያእምሮ ዘአበስናሁ ወዘጌገይ ናሁ ከመ ይሥረይ፡፡

፨፨#ጽሑፎቻችን ለሌሎችም እንዲዳረሱ #የቴሌግራም_አድራሻችንን_ለሌሎችም_ያስተዋውቁ፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት) ወይም https://t.me/medihanaelem ፨፨#የፌስቡክ_ገጻችንን_ለምትፈልጉ፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት) ወይም https://www.facebook.com/%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8C%A8%E1%8A%94-%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%88%A8-%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%88%98%E1%8B%B5%E1%8A%80%E1%8A%94%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%93-%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%88%A8-%E1%89%B5%E1%8C%89%E1%88%83%E1%8A%95-%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5-%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%89%A4%E1%89%B0-%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8D%8D%E1%8A%96%E1%89%B0-%E1%88%95%E1%8B%AD%E1%8B%88%E1%89%B5-%E1%88%B0%E1%8A%95%E1%89%A0%E1%89%B5-%E1%89%B5%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%89%A4%E1%89%B5-1620932764891482/

#ሚያዝያ_23_በዓለ_ክላሌሁ_ለሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፡፡ ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ #ኮከበ ክብር፥ *ሊቀ ሰማዕታት፥ *መክብበ ሰማዕታት፥ *የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥ *የልዳ ፀሐይ፥ *የኢትዮጵያ ገበዝ፥ *ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥ *፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥ *በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ በዕረፍቱ ክርስቶስን የሰበከ፥ ከዕረፍቱ በኋላ ዛሬን ጨምሮ ፈትኖ የሚራዳ፥ *፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥ *፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤ *እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤ #.... የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን በዓለ ክላሌ (ሚያዝያ 23) ከዋይዜማው ጀምሮ በመላው ሃገራችን የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡ #አማን በአማን፥ አማን በአማን፤ ኮከበ ልዳ፥ ፀሐየ ፋርስ፡፡ #በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ዘአንበሩ ብየ አክሊለ ሞገስ፤ መዘምረ እኩን ለጊዮርጊስ፡፡ #ኀያል መስተጋድል ኀያል ኮከበ ክብር፤ ኀያል ገባሬ ተአምር፤ ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር፡፡ #በእንተ ጊዮርጊስ ፍቁርከ(ሰማዕትከ፥ ምዕመንከ)፤ ምህላነ ስማዕ በዕዝንከ፡፡ #ሥርዐተ ማኅሌቱን ሌሎችም እንዲደርሳቸው ከዚህ በታች የሰፈረውን ገጻችንን LIKE LIKE እንዲያደርጉ ያስተዋውቁ፤ INVITE INVITE INVITE ያድርጉ፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት)

ለአባላት በሙሉ፤ #የኪዳነ_ምሕረት_ማኅበራችን ሰሙነ ሕማማት ላይ ውሎ ስለነበረ፤ የሚደረገው ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ ፳፩ በመኾኑ፤ በሰዐቱ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ሰሙነ ፋሲካ (ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ) ከትንሣኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታት ሰሙነ ፋሲካ ወይም ትንሣኤ እየተባሉ የየራሳቸው ምስጢራዊ ስያሜ አላቸው፡፡ ይኸውም፡- ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ጌታችን በሞትና ትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ሆና «ፀአተ ሲኦል ማዕዶት» ትባላለች፡፡ ዮሐ. 19-18 ሮሜ. 5-10-17 የዳግም ትንሣኤው ማግሥት ያለችው ግን ገበሬው፤ ወንዶቹ እርሻ ቁፋሮውን፣ ንግዱን፣ ተግባረ እዱን ሁሉ ሴቶቹ ወፍጮውን፣ ፈትሉን፣ ስፌቱን የሚጀምሩባት ዕለት ስለሆነች «እጅ ማሟሻ» ሰኞ ትባላለች፡፡ ✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ሐዋርያ አልነበረም ኋላ ከሔደበት ሲመጣ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት እኔ ሳላይ አላምንም በማለቱ በዚህ ጥያቄው መሠረት በሳምንቱ ጌታችን በድጋሚ ስለተገለጸ ለዚህ መገለጹ መታሰቢያ ሆና ዕለቲቱ «በቶማስ» ተሰየመች፡፡ ዮሐ. 20-24-30 ✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ከሞተና ከተቀበረ አራት ቀን በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላሥነሣው፣ አላዓዛር መታሰቢያ የእርሱንም ተነሥቶ በማየት በጌታችን ብዙ ሕዝብ ስለአመነበት ቀኒቱ «አላዓዛር» ተብላ ትታሰባለች፡፡ ዮሐ. 11-38-46 ✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ የአዳም ተስፋው ተፈጽሞለት ከነልጅ ልጆቹ ወደቀደመ የገነት ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ሆና «የአዳም ኀሙስ» ተብላ ይኸው ትከበራለች፡፡ ሉቃ. 24-25-49 ✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በክርስቶስ ደም ተዋጅታ በተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዐርብ «ቤተ ክርስቲያን» ተብላ ትጠራለች፡፡ ማቴ. 26-26-29 የሐ. ሥራ. 20-28 በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በስተቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበይባት «የቁራ ገበያ» የገበያ ጥፊያ ስትባል በቤተ ክርስቲያን ግን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጉልበታቸው ለአገለገሉት በስቅለቱ ዋይ ዋይ እያሉ እስከ ቀራንዮ ለተከተሉት፣ የትንሣኤው ዕለት ገና ከሌሊቱ ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው በመገሥገሣቸው ትንሣኤው ከሁሉ ቀድሞ ለተገለጸላቸው ቅዱሳት አእንስት መልካም መታሰቢያ ሆና «አእንስት» ተብላ ትጠራለች፡፡ ሉቃ. 23-27-33፣ 24-1-01፣ ማቴ. 25-1-11 ✞ እሑድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት) + + + መልካም በዓል!!! + + +

፠በሕማሙ በከይነ፤ ወበትንሣኤሁ ተፈሣሕነ። (#በሕማሙ_አዘንን፤ #በትንሣኤው_ደግሞ_ተደሰትን) ቅዱስ ያሬድ፨ /እንኳን አደረሳችሁ፤ ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፨/