es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 389 suscriptores, ocupando la posición 5 582 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 199 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 389 suscriptores.

Según los últimos datos del 02 julio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 23, y en las últimas 24 horas de -3, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 21.38%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.20% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 290 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 569 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 17.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 03 julio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 389
Suscriptores
-324 horas
+207 días
+2330 días
Archivo de publicaciones
#መልክአ_ሕማማት፤ (የ፯ቱ ጊዜያት ጸሎት) *መልክአ ሕማማት ማለት ስለ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ መምህር #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ ነው፡፡ *መልክአ ሕማማት በባለ 3ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤ የተደረሰውም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹#ጸሎት_ዘሰባዐቱ_ጊዜያት›› በሚል መጠሪያም ይጠራል፡፡ የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3ት ክፍሎችን የያዘ ነው፤ እነርሱም፤ 1ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/ 2ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/ 3ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/ **በ7ቱ ጊዜያት ጸሎት ማድረስ እንደሚገባን ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 118 ላይ ‹‹ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ ይላል››፤ አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህንኑ ደንግገዋል፡፡ /ዲድስቅልያ 37፣ ቀሌምንጦስ 1ና 7፣ አቡሊዲስ 25ኛና 27ኛ፣ ባስልዮስ 28ኛ አንቀጽ፣ ፍትሐ ነገሥት ገጽ 21/፡፡ ፠ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መልክአ ሕማማትን ሲደርስም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት የተፈጸሙትን ድጊቶች ከ3ቱ የየጊዜያቱ የድርሰቱ ክፍሎች ምስጋና (የማርያም፣ የጌታ፣ የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና) ጋር እያመሠጠረና እያራቀቀ፥ እያስዋበና ምሥጢር እያመጣ፤ እንደ ወርቅ እያንከባለለ፥ እንደ ሸማ እየጠቀለለ፥ በግጥም እያስጌጠ፥ በቃላት እየሰደረ፥ በዜማ እያሸበረቀ፥ መንፈስን እየመሰጠ፤ ነው የደረሰው፡፡ #የ7ቱ_የጸሎት_ጊዜያት_የሚባሉትም፤ ፠1ኛ) መንፈቀ ሌሊት(ሌሊት 6 ሰዐት)፤ ጌታችን የተወለደበት፥ የተጠመቀበት፥ የተነሣበትና ዳግመኛ የሚመጣበት ፥ … ሰዐት ነው፡፡ ፠2ኛ) ነግህ (ማለዳ፥ ጧት)፤ ጨለማን አርቆ ብርሃንን የሚያመጣበት፥ አባታችን ቅዱስ አዳም የተፈጠረበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጲላጦስ አደባባይ ፊት ቁሞ የተመረመረበት፥ …. ሰዐት ነው፡፡ ፠3ኛ) ሠለስት (ጠዋት ሦስት ሰዐት)፤ እናታችን ሔዋን የተፈጠረችበት፥ ነቢዩ ዳንኤል ጸሎት ያደረሰበት፥ እመቤታችን ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን ሰምታ የጸነሰችበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠4ኛ) ቀትር (6 ሰዐት)፤ አጋንንት የሚሰለጥኑበት ሰዐት ስለሆነ እንዳይሰለጥኑብን፥ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሳተበት ስለሆነ እንዳንስት እንጸልያለን፡፡ በተጨማሪም ነቢዩ ሄኖክ ቤተ መቅደስን ያጠነበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠5ኛ) ተስዓት (ዘጠኝ ሰዐት)፤ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ የወጡበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው የለየበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠6ኛ) ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዐት)፤ ነቢዩ ኤልያስ መሥዋዕት የሰዋበት፥ ዕዝራ ጸሎትን ያቀረበበት፥ ሕዝቅያስ ጸልዮ ፀሐይን ወደ ዐሥር ደረጃዎች የመለሰበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደ በፈቃዱ ወደ አዲስ መቃብር የወረደበት፥ …… ሰዐት ነው፡፡ ፠7ኛ) ንዋም (የመኝታ ሰዐት)፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጌቴሴማኒ የጸሎትን ሥርዐት ያስተማረበት ፥ እንዲሁም ሌሊቱን በመላእክት ጥበቃ ከርኵሳን አጋንንት እንዲጠብቀን የምንጸለይበት …… ሰዐት ነው፡፡ #ለቡ(ልዩ ማስታወሻ)!! ይህ ታላቅ ጸሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስር ባሉ በሁሉም ገዳማትና አድባራት በሰሙነ ሕማማት የሚደርስ ሲሆን፤ በአንዳንድ ትላልቅ ገዳማት (እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ወደብረ ጎል አቡነ በጸሎተ ሚካኤል) ያሉ መነኰሳትና መናንያን ግን ከዓመት እስከ ዓመት ጸሎቱን በዜማ /በንባብ/ ያደርሱታል፡፡ #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem Finotehiwotsundayschool.com

👉 #የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች (#ሥርዐተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት፡፡) 👉 #፬ቱ #ስግደታ 👉መልክአ ሕማማት #የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች † #ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ:: † #ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን:: † #ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን:: † #ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ:: † #ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ:: † #ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡ መሉውን ፌስቡክ ገጻችን ላይ ያግኙ መሉውን ፌስቡክ ገጻችን ላይ ያግኙ መሉውን ፌስቡክ ገጻችን ላይ ያግኙ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/posts/2887543898230356

የሆሣዕና በዓል፤ የፎቶ ማስታወሻዎች :: የሆሣዕና አቅራቢ ደብረ ተረኛ በነበርንበት ሰዓት ፤ የ2010 E.C 2001 ዓ.ም ፤ እንዲሁም የተለያዩ ዓመተ ምህረቶች የፎቶ ማስታወሻ ከፎቶ ማኀደራችን ፡፡
የሆሣዕና በዓል፤ የፎቶ ማስታወሻዎች :: የሆሣዕና አቅራቢ ደብረ ተረኛ በነበርንበት ሰዓት ፤ የ2010 E.C 2001 ዓ.ም ፤ እንዲሁም የተለያዩ ዓመተ ምህረቶች የፎቶ ማስታወሻ ከፎቶ ማኀደራችን ፡፡