es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 123 suscriptores, ocupando la posición 5 232 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 221 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 123 suscriptores.

Según los últimos datos del 01 noviembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 598, y en las últimas 24 horas de 74, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 23.12%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.46% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 729 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 686 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 29.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 02 noviembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 123
Suscriptores
+7424 horas
+847 días
+59830 días
Archivo de publicaciones
ለተዝካረ አበው /ኅዳር ፰/ (በታላቁ ገዳም በዋልድባ/ዋሊ/ ብቻ በዛሬው ዕለት ለሚደረገው የአበው መታሰቢያ አደረሳችሁ፨ በኢትዮጵያ በብቸኝነት ጌታችን በመሠረተው በዚህ በታላቁ ገዳም በዋልድባ ብቻ ከሚደረጉ ሥርዐቶች መካከል አንዱና ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው መካከል፤ የወጣ ሳይገባ፥ የገባ ሳይወጣ (መርፌም ቢኾን ከሱባዔው በፊት ወደ ገዳሙ ካልገባ ሱባዔው እስኪያልቅ ጥቅም ላይ አይውልም)፨ የ158 ቀናት ሱባዔ ይደረጋል፤ (ከ143 ቀናት በኃዋላ ዛሬ ኅዳር ፰ በተዝካረ አበው ቀን በማኅበር ደረጃ ቢሰባሰቡም መልሰው እስከ ኅዳር ፳፬ ወደ ሱባዔ ገብተው በ፳ወ፬ቱ ካህናተ ሰማይ ትልቁ ሱባዔ ያበቃል፨ በእነዚህ ቀናት ከቀባሪ በስተቀር ወደ ገዳሙ መግባትም አይቻልም፨ ፠፠ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ከአበው አንድነት፥ ከአቡነ ሳሙኤል ልጅነት፥ ከገዳመ ዋሊ ረድኤት በረከት ይክፈለን፨ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/

ኅዳር ፯ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ተዓምራትን የሚሠሩት (እንጨቱ ጸበላቸው ውስጥ ሲገባ መቁጠሪያ የሚያደርጉት፤ በፎቶ የምታዩት)፤ ፻ ትውልድ የሚያስምሩት፤ በደንጊያ ሠረገላነት የሚጓጓዙት ከ፯ቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ አንዱ የኾኑት አባ ገብረ እንድርያስ በዓለ ዕረፍታቸው ነው፨ ቦታቸውን ክርስቲያን የኾነ ኹሉ ሊያየው የሚገባም ነው፤ እንዲሁም የሊቀ ስማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ ነው፨ ✤✣✤ ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ፤ ✤አባታቸው ተንስአ ክርስቶስ፥ እናታቸው አርሴማ ሲባሉ፥ የትውልድ ሀገራቸው ወሎ፥ ቦረና፥ ጋሥጫ ሲኾን የቀድሞ ስማቸው ንፍታሊም ይባል ነበር። ✤ ለትምህርት ሲሄዱ መምህራቸው ብዙሃኑን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ ብለው ትንቢት የተናገሩላቸው ሲኾን፤ የጻሕፍትን ትርጓሜ በደንብ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሊም ይባል የነበረውን የቀድሞ ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አላቸው። ✤ ጻድቁ በአቡነ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፤ ብዙ አባቶች ሱባኤ በሚይዙበት በስኮሩ ስላሴ ቤተክርስትያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ኡራኤል በወርቅ ጽዋ ማየ ሕይወት አጠጥቷቸዋል። ✤ ጻድቁ አባታችን ሙታንን በማስነሳት ና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል። ✤ ጻድቁ ዐርብ ዐርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን ና ክቡር ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በአየር ላይ ድንጋዩን እንደ ሰረገላ ዋርካውን እንደ ጥላ ይጠቀሙበት ነበር። ይህ ሰረገላ የሆነው ድንጋይ በገዳማቸው ይገኛል። ✤ ጻድቁ አባታችን እግዚአብሄር ኀጥአንን እንዲምርላቸው ርቀት ወንዝ ከተሰኘው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሽከሙ ይጸልዩ ነበር። በዚህም ይጸልዩበት በነበረው ወንዝ ውስጥ በተአምራት መቁጠርያ የሚሰራ ጸበል ፈለቀላቸው፤ ጠበላቸው ውስጥም እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፤ ይኸውም መቁጠሪያ ለብዙ ሕመሞች መድኀኒት ነው፡፡ ✤ ✤ ✤ ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሃገራችን ሰላም የ፩ ሱባዔ ምሕላ እንዲደረግ ያወጀው ማብቂያው ነው፤ አቡነ ገብረ እንድርያስና ሊቀ ሰማዕቱ ስለ ሃገራችን በተቀበሉት ቃል ኪዳን ሰላምና ጤና ያውርዱልን፤ ጠላታችንን ከሃገራችን ያባርሩልን፨ ✤ እባካችሁ ዝም አትበሉን እናንት ገዳማት! ዕድሜ ጠገቦቹ የዘመን አዝማናት፡፡ እነ አባ ያዕቆብ እነ ደብረ ጽጌ፤ እነ ቦሎ ዋሻ እነ ደብረ ሐይጌ፤ እነ ፍልፍሌ ጸዓዳ እነ ጅቦ ዋሻ፤ እነ ደብረ ቆዘት እነ ጊዮርጊስ ዋሻ፤ ታሪካችሁን ንገሩን እንያዝ ማሰታወሻ፤ ድንገት ብትጠፉብን እንዲሆን ማልቀሻ፡፡ ደብረ ቆዘት ጠርተን ገብረክረስቶስ አልን፤ የገዛዛን ታሪክ ለላሊበላ ሰጠን ፤ ደበረ ከረቤ ብለን አባ ያዕቆብ አልን፤ የወለቃ ጉዳይ ለዘካርያስ ሰጠን፡፡ እነ ደብረ ሐይጌ እነ ጅቦ ዋሻ፤ የያጌ ጌጦች የታሪክ መናገሻ፤ የጎለሌው ዋሻ የተባለከው ፍልፍሌ፤ የቦሎ ቤቴክስያን የጉርባው ቀበሌ፤ የጊዮርጊስ ዋሻ ነአኩቶ ድድምቱ ፤ እስኪ ተናገሩ የታሪክ እውነቱ፡፡ ማን እንበላችሁ የመጠርያ ስማችሁ፤ እነማን ነበራችሁ የታለ ገድላችሁ? ያሁኑ ስማችሁስ ማን ሰየመላችሁ? * (በደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ ለሚገኙ ከዘመናት ብዛት በመፈራረስ እና በመጥፋት ያሉ ታሪካቸው በአግባቡ ያልታወቁ 13 ጥንታዊያን ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት፡፡ 2001 ዓ.ም) /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/

ኅዳር 5፤ አባ ዮሐኒ ወአሞኒ፤ ዘገዳመ ዓሣይ፤ ቆላ ተንቤን (ከአስቴር ማስታወሻ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ/ የተወሰደ) አባ ዮሐኒ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ በትግራይ ተንቤን አውራጃ በሀገረ ሰላም ቀበሌ የተወለደ ቅዱስ ነው፡፡ በዚያን ዘመን ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም አበው በምናኔ በበረሃ ይኖሩ ነበር፡፡ ከ4ኛው መ/ክ/ዘ በፊት (ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ሀገራችን የገባው በኢትዮጵያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ /ከአባ መቃርስ ወደ አባ ጳኵሚስ፤ ከአባ ጳኵሚስ ወደ አባ ቴዎድሮስ፤ ከአባ ቴዎድሮስ ወደ አባ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ) ቢሆንም የብሕትውና ኑሮ ግን በሀገራችን ከዚያም ቀድሞ እንደነበረ ከሚጠቁሙን ዋነኛ ነገሮች አንዱ የገዳመ ዓሣ/ይ/ ታላላቅቆች የኾኑ ቅዱሳን አባቶቻችን ቅዱሳን አባ አሞኒ እና አባ ዮሐኒ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ገዳሙ ከ1600-1800ዓመታትን ያስቈጠረ ውቅር(ፍልፍል) ቤተክርስቲያኝ ሲኾን፤ ገዳሙ ያለበት ተራረ ብቻውን ከ20ደቂቃ በላይ ያስጕዛል፤ እንደ ደረጃ ያሉ፥ ሠርጥ የኾኑና አንድ ድልድይን ካለፉ በኋላ ገዳመ ዓሣን እንዲኹም ወደ ላይ ተጨማሪ የ5 ደቂቃ ተራራ ሲወጡ አባ ዮሐኒ በሕፃንነታቸው (ከተወለዱባት እለት ጀምሮ እስከ 3 ዓመት እስከሚሞላቸው) ያደጉባን ትንሽ ዋሻ ያገኛሉ፤ የአባ አሞኒና የአባ ዮሐኒ ታሪክም ከአባ መሪና ጋር በተወሰነ መልኩ ይመሳሰላል፤ ………. ለማንኛውም ከዚህ በታች ታሪኩ ይተረካል………፡፡ አባ ዮሐኒ ከመወለዱ በፊት፤ የእናቱ ባል የተንቤን ሹም ስለበር ለዘመቻም /ለንግድም/ ይላሉ ኖባ ወደሚባል አገር ሔዶ ለሰባት ወር ያህል ዘገየ፤ ታናሽ ወንድሙም ወንድሜ ዘገየ ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስም /ሞቷልም ይላሉ/ ስለዚህ ሚስት ትሆኚኝ ዘንድ ነዪ ቃል ኪዳን እንግባ አላት፤ እሷም የባሏ ታናሽ ወንድምና በቤቷ ውስጥ ያሳደገችው ነበረና እንዴት ደፈርከኝ ብላ ተቆጣች፤ እርሱም ተቆጥቶ ደረሰባትና ጸነሳ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ በወለደችበት ቀንም ከብዙ ምርኮ ጋር ባሏ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ሚስቱ ከቤት የለችም ነበርና ሚስቴ ወዴት ሔደች ብሎ ጠየቀ፡፡በቤቱ ውስጥ ያለ አንድ ሕፃን ባለቤትህ ታማለች አለው፤ ባለቤቷም በሽታዋ ምንድን ነው አለው? ያ ሕፃንም ዛሬ ልጅ ወለደች ብሎ መለሰለት፡፡ ይህንንም በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ተቆጣ፤ ያ ሐፃንም እየመራው ሚስቱ ወዳለችበት ገባ ይደበድባት ጀመር፡፡ ደብረ ዓሣይ (በቆላ ተንቤን የሚገኝ) በሚባል ገዳም ስሙ አባ አሞኒ ዘናሕሶ የተባለ ገዳማዊ ነበር፤ በዚያ ገዳምም ለሃያ ዓመታት ያህል የቆየ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም አባ አሞኒን ተነስተህ የተንቤን ሹም ወደ ሆነው ሰው ቤት ሂድ ከዚያም እግዚአብሔር የወደደውን ነገር ታገኛለህ አለው፤ አባ አሞኒም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ከተራራው(ከገዳሙ) ወርዶ ወደ ተንቤን ሹም ቤት ደረሰ፤ ሚስቱም በቤቷ በር ፊት ለፊት አባ አሞኒን ባየችው ጊዜ ውስጡ ጥበበ እግዚአብሔር ነውና፤ ለባሏ የጸነስኩት ከዚህ መነኵሴ ነው አለችው፡፡ ያን ጊዜም ባሏ በቁጣ ወጥቶ አባ አሞኒን መታው፥ ደበደበው፤ ልጅህን ይዘህ ሒድ ብሎ ሕፃኑን ለአባ አሞኒ ሰጠው፡፡ አባ አሞኒም ሕፃኑ በተወለደበት ቀን በልብሱ አቀፈው፤ ወደ ገዳሙ (ደብረ ዓሣይ) ወስዶ እኔ ጡት የለኝ! ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከገደሉ ጀርባ እንደ መቃብር አስመስሎ ምድርን ቆፈረና፤ ለሕፃኑ የሰሌን ቅጠልን አንጥፎ በዚያ አስቀመጠው፥ ድንጋይም ከደነ፤ እግዚአብሔር ከወደደ ያድንህ፣ ይህቺ ጉድጓድ እናትህ ትሁን ብሎ ከዚያ ትቶት ወደ በዓቱ ሔደ፡፡ በነጋውም ማልዶ ወደዚያ ሕፃን ገሠገሠ፤ ፌቆ/ሚዳቋ የምትመስል/ ከጉድጓዱ ድንጋዩን አስወግዳ ተንበርክካ ስታጠባው አያት፤ ፌቆዋም አባ አሞኒን ባየችው ጊዜ ከጉድጓዱ ውስጥ ሸሸች፤ አባ አሞኒም ያን ሕፃን ደስተኛ ሆኖ ዓይኖቹን ባየ ጊዜ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት፤ ትርጕሙም ወላጆችህ ወይም አሳዳጊዎችህ አራዊት ናቸው እንደ ማለት ነው:: አባ አሞኒም ይህን ዕፁብ ድንቅ ሥራ ..................... ቀሪውን ታሪክ ሳምንት ይጠብቁ ........

አክሊለ በረከቱ ለጊዮርጊስ፥ ወትምክህተ ቤቱ ለክፍለ ያዕቆብ፨ (የተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌን የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያምና የደብራችን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ፍቅረ ማርያም ምሕረቱ እየመሩት፨

እንኳን ለእመቤታችን ከነልጇ ከ፫ ዓመት ከ፮ ወር ከስደት በኃዋላ ተመልሰው በደብረ ቁስቋም ላረፋበት ለበዓለ ቁስቋም ማርያም አደረሰን፨ ከሚከበርባቸው ቦታዎች ዐበይቶቹ፤ ፠ ረጠደብረ ቁስቋም (ግብፅ) ፠ ገዳመ ጽጌ ድንግል (ደቡብ ወሎ፥ ወግዲ ወረዳ) ፠ ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም (ጎንደር ከተማ) ፠ እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም (እንጦጦ፥ አዲስ አበባ) ፠ ቃሊቲ ቁስቋም ማርያም (ቃሊቲ፥ አዲስ አበባ) ፠ ሸጎሌ ኪዳነ ምሕረት /የቁስቋም ማርያም ታቦት በድርብነት አለ፤ (ጉለሌ፥ ጎጃም በር፥ አዲስ አበባ)

ንግሥተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል፤ (ኅብረ ሐመልሚል ቀይህ ወፀዓድዒድ) ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ፡፡ (የብር ዝንጕርጕር፣ የነጭና የቀይ ድብልቅ መልክ ያለው ንጹሕ ተዓምርሽ በወርቅ አምሳል የተዘጋጀ ነው፤ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል /ጽጌ ብርሃን/ የደረሰው እነሆ ያማረ የተወደደ ማኅሌተ ጽጌ የተባለ ምሥጋና መላ፥ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወዳጅሽ በእቅፍሽ ውስጥ እንዳለ ይህንንም የማኅሌተ ጽጌ ምሥጋናን ተቀበዪ፥ ወደ ሰማይ አሳርጊ፡፡)

ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ፤ ወለሊቃውንቲከ ይዜንዉከ፡፡ (አባትህን ጠይቅ ይነግርሃል፤ ሊቃውንትን ጠይቅ ያስታውቁህማል፡፡) የኹሉንም ሳምንታት ማኅሌተ ጽጌ ቀድሞ ከአባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ዚቁን፤ ታላቁ ሊቅና ቅዱስ አባ ጽጌ ድንግል ከደረሰው ማኅሌተ ጽጌ ጋር እያስማሙ አቀናብረው ያቀረቡልን ዐበይት የላይ ቤትና የታች መምህራን፡፡ እነርሱም፤ ✤✤ የላይ ቤቱን፤ መምህር ተክለማርያምና ሊቀ ማዕምራን ወመጋቤ ሐዲስ ወ/ሰንበት ባይነሳኝ፤ (ሁለቱም የቀለም ቀንድ የኾኑ ሊቃውንት የመጻሕፍተ ሐዲሳት ዋና ምስክርና የመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ ናቸው፡፡) ✤✤ የታች ቤቱን፤ መምህር ክፍሌ ወልደ ጻድቅ ና መጋቤ አእላፍ ሄኖክ ወልደሚካኤል /ሁለቱም ሊቃውንት የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓታ የአቋቋም ዋና ምስክርና የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩ ናቸው፡/

ታላቁ ገዳማችን አሰቦት ደብረ ወገግንና ደብረ ኪሩብን ለመሠረቱት ለአባታችን ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ በዓለ ዕረፍት (ጥቅምት 29) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ አቡነ ሳሙኤል ዘደደብረ ወገግ፡ ፠ በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት ‹እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ጣዖታትን የሚሰብር፣ የሚያጠፋ፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኀጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ› ተብሎ በተነገረለት ትንቢታዊ ብሥራት ከደጋግና ከበቁ አባታቸው እንድርያስና ከእናታቸው አርሶንያ ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም. በቡልጋ ተወለዱ፤ ሲወለዱም መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡ ፠ስማቸውን ሳሙኤል በብለው የሰየሟቸውና ክርስትናም ያነሷቸው፤ ኋላም መዓርገ ምንኵስናን የሰጧቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡ ፠ ብዙ ጻድቃንን (አቡነ ተክለሃይማኖትን፣ ታዴዎስ ዘደብረ ድኁኃን፣ ሮማኖስ ዘደብረ ዋምን፣ አቡነ አኖሬዎስ ዕንቈ ባሕርይ ዘመረግድ ወመስተጋድል ወምግባር ንጹሕን) በሥጋ የሚዛመዱ ናቸው፡፡ ፠ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና አባቱ ዓምደ ጽዮን ለሠራው ክፉ ሥራ ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ ፠፠ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል፤ * በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ * ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡ * ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፥ * ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፥ * በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፥ * ይህን ኀላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፥ * በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፥ * በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ፤ * ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግም ይታወቃሉ፤ ከእነዚህም ጥቂቶቹ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት (በጥቅምት 29) በኦጋዴን ዘርዘር በተባለ ቦታ በሰላም አርፈዋል፤ ከ7 ወራት በኋላ ሠምረ ክርስቶስ የተባለ ልጃቸው ሥጋቸውን አፍልሶ በደብረ ወገግ በክብር አሳርፎታል፡፡ ፠ የአሰቦት ደብረ ወገግን (ምስራቅ ሐረርጌ) ና ደብረ ኪሩብ (አፋር) ገዳምን የመሠረቱ፥ ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና፤ የመሠረቱት ገዳም የምሥጢርና የብዙ ስውራን መኖሪያ የኾነላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ፠ ከአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ ከተሾሙት 12ቱ ንቡራነ ዕድ አንዱ ናቸው፤ ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነው፡፡ ፠ ‹‹ደብረ ወገግ›› ከ2-5 ዓ.ም. እመቤታችን ከነልጇ ስተሰደድ ለ6 ወር የተቀመጠችበት ሲኾን፤ ደብረ ወገግ የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል በ34ዓ.ም. የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ ወገግ ላይ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ ወገግን የብርሃን ውጋገን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም ቦታውን ‹‹ደብረ ወገግ›› (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት›› ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት አርጓል፡፡ ✤✤ ደብረ ወገግ፤ ፠ በደብረ ወገግ ቦታ ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡ ፠ ገዳሙ በግራኝ ወረራ ወቅት ከጠፋ በኋላ እንደገና መልሶ የቀናው በ1911ዓ.ም. በታላቁ ሊቅና መናኝ በአለቃ ገብረ መድኅን ነው፡፡ በ1912 ዓ.ም. የአቡነ ሳሙኤልን ቤተ ክርስቲያንን በሣር ክዳን ሠሩ፤ በዓመቱ በ1918 ዓ.ም. ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሥራት ጀምረው ፍጻሜውን ሳያዩ እርሳቸው ቢያርፉም፤ በ1919 ዓ.ም. የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተጠናቋል፡፡ በ1929 ዓ.ም. በሶማልያ በኩል በገባው የፋሽስት ኢጣልያ ጦር ገዳሙ ተዘርፏል፥ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንም ፈርሷል፡፡ በወቅቱ በገዳሙ ከነበሩት ከ500 በላይ መነኰሳት መካከል ከፊሉ ታቦቱን ይዘው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲሸሹ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ተወስደው ታስረዋል፡፡ ከጣሊያን ወረራ በኋላ መነኰሳቱ በ1936 ዓ.ም. ተሰባስበው ወደ አሰቦት መጡ፡፡ ከ22 ዓመት በኋላ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ በ1952 ዓ.ም. ተሠራ፡፡ በደርግ ዘመነ መንግሥት ሶማሊያ ኢትጵያን ስትወርር ገዳሙ ላይ አደጋ ለመጣል የመጡ ጠላቶች በተአምራት ያለቁበት ነበር፤ የጃራ ጦር የሚባሉ ገዳሙን ለማጥፋትም መጡ ጠላቶች እንዲሁ በተአምራት አብደው የተመለሱበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡ ግንቦት 16 ቀን 1984 ዓ.ም. በአክራሪ ኃይል የገዳሙን መነኰሳትና የአካባቢው ምዕመናን ላይ የከፋ አደጋ ጥሏል፤ ብዙዎችም ሰማዕት ሁነዋል፡፡ በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ እጅግ በርካታ ቅዱሳን ስለመኖራቸው በገድለ አቡነ ሳሙኤል መቅድም ውስጥ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት በቦታው ላይ የተሰወሩት ቅዱሳን ለገዳማውያኑም ሆነ በዓለም ለሚኖሩ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ለያዙ ሰዎች እየተገለጡላቸው ይታዩዋቸዋል፣ መልእክትም ይነግሯቸዋል፡፡ እንዲሁም ስውራኑ ባሉበት ቦታ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ዕጣን ይሸታል፣ ቀንና ሌሊት አራዊት ሲሰግዱበትና ሲጠብቁት ይታያል፡፡ ለአብነትም በ1972ዓ.ም. ሐምሌ 7 ብዙ ሰው እያያቸው አባ መዘምር የተሠወሩበት ታለቅ ገዳም ነው፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘፍቅዳቲሁ ራብዕ፤ ውእቱ ልኩእ ዲበ ረቀ ሰማይ ሳብዕ፡፡ ሊቀ ካህናት ሳሙኤል ዘደብተራ ሐዲ ምሥዋዕ፤ አስተስሪ ኀጣውእየ በደመ ነቢብ በግዕ፤ ለቤዛ ሙታን ዘሞተ በግፍዕ፡፡ (ሳሙኤል ሆይ ቊጥሩ ዐራት ለኾነ በሰባተኛው የሰማይ ብራና(ወረቀት) ለተጻፈ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፤ የሐዲስ መሠዊያ አገልጋይ፥ የካህናት አለቃ ሳሙኤል ሆይ፤ ለሰዎች ቤዛ ለመኾን በግፍ በሞተ በነባቢ ክርስቶስ ደም ኀጢአቴን አስተሥርይ፡፡) /ታሪኩን ለዘገበልን ወንድማችን አምላከ አቡነ ሳሙኤል በረድኤት በበረከት በጤና ይጠብቅልን፡፡/