es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 337 suscriptores, ocupando la posición 5 643 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 190 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 337 suscriptores.

Según los últimos datos del 13 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -75, y en las últimas 24 horas de 2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 22.35%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.54% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 428 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 616 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 25.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 14 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 337
Suscriptores
+224 horas
-47 días
-7530 días
Archivo de publicaciones
✤ ሥርዓተ ማኅሌት ዘበዓለ ሆሣዕና ወዘመጋቢት መድኀኔዓለም ✤ ✤ እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና እንዲሁም ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ ✤ ዘንድሮ ፳፻፲፰ ዓ.ም ሁለቱ ታላላቅ የጌታችን በዓላት አንድ ቀን ገጥመዋል። ጥንተ ስቅለቱ እና በዓለ ሆሳዕና። ፩) ጥንተ ስቅለት፦ መጋቢት ፳፯ ቀን የመድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉም በዓለ መድኀኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ #በመድኀኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል። ፪) ሆሣዕና፦ (#በዓለ_ተፂዕኖ) (#የፀበርት_እሑድ) ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው። የሰሞነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን፤ የዐቢይ ጾም ስምንተኛውና የመጨረሻው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል። መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተጭኖ፤ ሕጻናት እና አዕሩግ፥ እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፤  "ሆሣዕና በአርያም" እያሉ እየዘመሩለት ወደ ኢየሩሳሌም ሀገር የገባበት በዓል መታሰቢያ ነው። ሥርዓተ ማኅሌቱ ምን ይመስላል? በሁሉም የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት የሆሣዕና ቀለም የሚቆም ሲሆን፥ የመድኀኔዓለም ታቦታት ባሉባቸው አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ አስቀድሞ መልክዐ ኢየሱስ፤ በማስቀጠልም መልክዐ መድኀኔዓለም፥ ለበዓሉ ተስማሚ የሆኑት ቀለሞች በሊቃውንት አባቶች እየተመረጡ የሚቆም ይሆናል። የየአድባራቱ የቀለም ምርጫ እንደ ሊቃውንቱ እና እንደየቦታው ይትበሀል ሊለያይ ስለሚችል፥ እኛ ሁለቱንም ሥርዓተ ማኅሌቶች አስቀምጠንላችኋል። እንደየቦታው ማኅሌታቱን እየተከተላችሁ እና አባቶችን እየጠየቃችሁ ተጠቀሙባቸው። ✤ መልካም በዓል ✤

ሥርዐተ ማኅሌት ወዑደት ዘበዓለ ሆሣዕና ልዩ ማስታወሻ፤ የማኅሌቱን ሥርዐት በበዓታ(በታች ቤት)ና በዐቢየ እግዚእ(በላይ ቤት) አብነት የምትቆሙ አድባራት እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትቆሙበት ዘንድ፤ የሚ
+5
ሥርዐተ ማኅሌት ወዑደት ዘበዓለ ሆሣዕና ልዩ ማስታወሻ፤ የማኅሌቱን ሥርዐት በበዓታ(በታች ቤት)ና በዐቢየ እግዚእ(በላይ ቤት) አብነት የምትቆሙ አድባራት እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትቆሙበት ዘንድ፤ የሚለያዩባቸውን ዘበዐታና ዘዐቢየ እግዚእ በሚል አስቀምጠንላችኋል፡፡ ✤ መልካም በዓል ይሁንላችሁ ✤ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

ሆሣዕና የሰሞነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን ሆሣዕና ይባላል፤ ትርጉሙም ‹‹እባክህ አሁን አድን አንድም መድኃኒት›› ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን የማዳን ሥራውን ወደሚፈጽምባት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ ቤተ ፋጌ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ‹‹ያስፈልጉኛልና የታሠሩትን አህያና ውርንጫ ይዛችሁልኝ ኑ፡፡›› ብሎ ላካቸው፡፡ በምስጢሩም የአዳምን ልጆች ከዲያብሎስ ቁራኝነት ሊፈታ እንደ መጣ ለማጠየቅ ነው፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት መጡ፤ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲሆን 14ቱን በእግሩ፣ 2ቱን በአህያ ሄዶ፣ ቤተ መቅደሱን 3 ጊዜ በውርንጭላዋ ከዞረ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ ቀድሞ በነቢያት ዘመን ጸብዕ (ጥል) በሆነ ጊዜ በፈረስ ተቀምጠው የጦር ዕቃ ይዘው ይታዩ ነበር፤ ዘመነ ሰላም በሆነ ጊዜ ደግሞ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉ፤ እርሱም ‹‹ዘመነ ሰላም ይዤላችሁ›› መጣሁ ሲል በአህያ ተቀምጦ መጣ፡፡ (ስለ ሰላምሽ የሚሆነውን አንቺስ ብታውቂ … /ሉቃ. 19፥24/) ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስም በትንቢቱ በአህያ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር /ዘካ. 9፥9/፡፡ በግራና በቀኝ የነበሩትም ‹‹እንኳን አንተ የተቀመጥክባትም አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም›› እያሉ ግማሹ ልብሱን ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ አነጠፉለት፡፡ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፣ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ዮዲት ሆሎፎርኒስን በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው አመስግነው ነበር፤ በዚያ ልማድ ጌታችንንም ዘንባባ ይዘው ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ሆሣዕና በአርያም›› እያሉ አመሰገኑት፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በዚያ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ በመቆጣት የለዋጮችን ገበታ እየገለበጠ አስወጣቸው፡፡ አይሁድም ሕፃናት ሲያመሰግኑ ሰምተው በቅንአት በታወረ ልቦናቸው ‹‹ዝም አስብላቸው እንጂ›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ አፍ ምስጋና ለራስህ አዘጋጀህ›› /መዝ. 8፥2/ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ጠቅሶ አሳፍሯቸዋል፡፡ በሌላም አንቀጽ እነሱ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ሲያመሰግኑ አይተው አፍረዋል፡፡ይህ በዓል ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

በኢትዮጵያ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርበት ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡ የሕማማትህንና የሞትህን ዜና ስለሰማች ዋልድባ ቅድስት ከዓመት እስከ ዓመት ታለቅሳለች፤ ፈጣሪ
በኢትዮጵያ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርበት ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡ የሕማማትህንና የሞትህን ዜና ስለሰማች ዋልድባ ቅድስት ከዓመት እስከ ዓመት ታለቅሳለች፤ ፈጣሪዋ አምላኳ ስለሆንክ፥ በስደትህ ጊዜ የባረካትና የመሠረትሃት፥ ኋላም እንደ ተሰቀልክ ሆነህ የተገለጽክባትና የቀደስካት በመሆኗ ዓመት እስከ ዓመት በሱባዔ ታስብሃለች፡፡ መጋቢት 27 ግን እንባዋን በቅዳሴ ጭምር የምታብስበት የደስታዋ ቀን ነው፤ ሰብዐ ዓለም ወሰብአ ኢትዮጵያ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ ተሰብስበው በኢትዮጵያ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓልህን ያስባሉ፤ ማዕከላዊና ደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዋልድባ ገዳም በመራቃቸው ብዙሃን ሕዝብ ለክብረ በዓሉ ወደ ዋልድባ ባይሄድም፤ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በተለይም ከጎንደርና ከትግራይ የ7 ዓመት ሕፃናት ሳይቀር ያን በረሐ አቋርጠው ወደ ገዳሙ ይተማሉ ፤ መነኰሳቱም እንደ አሸን ለበዓሉ የሚመጣውን ምዕመን በቋርፍና በጭልቃ፣ በሰሊጥና በሻይ ይቀበሉታል፡፡ ቅዳሴው እንዳበቃም ነፋስ እንደበተነው አሸዋ ባንዴ ሕዝቡ ወደ መንደሩ ይተምማል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ #ጥንተ_ስቀለት #ክርስቶስ_የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን #ከሆነ _እንደገና_በሌላ_ጊዜ_በዓለ_ስቅለትን_ማክበር_ለምን_አስፈለገ?       #ጥንተ_ስቀለት የጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ፳፯ ቀን ሰማያዊ አምላክ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው #በገዛ_ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ #በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል ፡፡ የመጋቢት ጽንሰት ( ብሥራት ) ታሕሣስ 22  እንደሚከብረሁ ሁሉ ማለት ነው ፡፡    ፠#ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ከሆነ እንደገና በሌላ ጊዜ በዓለ ስቅለትን ማክበር ለምን አስፈለገ?   ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ ሲሆን ከመቃብር የተነሣውም በዕለተ እሑድ በመሆኑ #ስቅለት ከዕለተ ዓርብ፣ #ትንሣኤም  ከዕለተ እሑድ፣ #ዕርገት ደግሞ ከዕለተ ሐሙስ እንዳይወጡ፤ ሌሎቹም በዓላትና አጽዋማት በተወሰነላቸው ቀን እንዲውሉ ማድረግ ይቻል ዘንድ የቀድሞ አባቶችና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሰባት አዕዋዳት አዘጋጅተው እና ቀምረው ሁሉም ሥርዓቱን ጠብቆ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቀን እንዲከበር የወሰኑ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት ጥንተ ስቅለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በየዓመቱ እየታሰበ በዓለ ስቅለቱ ደግሞ ከሰሙነ ሕማማቱ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በዕለተ ዓርብ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በአክፍሎትና በስግደት እንዲከበር በማድረግ ሕግና ሥርዓት ስለሠሩ በዚሁ መሠረት ይፈጻማል::    #ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጌታችን #የጽንሰቱ_በዓል በታላቅ ድምቀት የሚከበርበት ቀን ከመሆኑ የተነሣ በዓሉን በዓል ተጭኖት ነው እንጂ ፫ኛው ቀን መጋቢት ፳፱ኝም ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት #ጥንተ_ትንሣኤ በመሆኑ እንደ ጥንተ ስቅለቱ ሁሉ ጥንተ ትንሣኤውም ከበዓለ ጽንሰቱ ጋር አብሮ የሚታሰብ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡ #በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤    ✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤ ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ. ✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም ✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም ✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና ✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ ✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ ✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (ቦሌ የመድኀኔዓለም ታቦት ) ✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም ✤9.#ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም   ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ 110 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡  ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡) 10 #መናገሻ_ጋራ_መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡ 11.  #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡ 12.  #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል) #በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርባችው ፪ቱ ታላላቅ ገዳማት ፩ኛ. ኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ዜና_ዕረፍት 😭😭😭 በደብራችን ለበቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ለበርካታ ዓመታት በጥበቃ ሲያገለግሉ የነበሩ ከሁሉ ጋር በመግባባት እና በመስማማት ሁሉ
#ዜና_ዕረፍት 😭😭😭     በደብራችን ለበቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ለበርካታ ዓመታት በጥበቃ ሲያገለግሉ የነበሩ ከሁሉ ጋር በመግባባት እና በመስማማት ሁሉን በእኩል በማክበር በመልካም ጸባያቸው የሚታወቁት 10 ዐለቃ ሙሉጌታ አረፉ ።   ስርዐተ ቀብራቸው ሐሙስ ከ 5-6 በ ደብረዘይት ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ  ይፈጸማል ። ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን :: በቀብሩ መገኘት የምትችሉ ሁሉ በስልክ ቁጥሮች 0911972909/ / +251940801867 በመደወል በመመዝገብ መሄድ ትችላላችሁ  ነፍሳቸውን ከደጋጎቹ እቅፍ ያሳርፍልን ።

#ኒቆዲሞስ፤ #ሰባተኛው_ሳምንት ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፤ በዚህ ሳምንትም ይህ ይታሰብበታል፡፡ ‹‹ኒቆዲሞስ››፤ * አይሁዳዊ ሲሆን ከፈሪሳውያን ወገን የነበረ ነው    * በኢየሩሳሌም በሀብት ቢሉ በዕውቀት እንዲሁም በሥልጣን የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡    * ማታ ማታ ጌታችን ዘንድ እየተገኘ ይማር ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ አስቀምጦልናል፦ ፨ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ ‹‹መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህ ተዓምራቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ⊚ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ፨ ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ⊚ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።›› /ዮሐ. ፫፥ ዘ፩-፲፭/ ፨ ለምን በሌሊት ይመጣ ነበር? ⊚ አይሁድ ‹‹ማንም ከእኛ ወገን የሆነ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሆነ ሀብት ንብረቱ ይወሰድ፣ በቤተመቅደስ አይግባ፣ መሥዋዕት አይሥዋ›› ብለው ነበርና አይሁድን ፈርቶ፥ ሀብት ንብረቱን ወዶ እንዳይታወቅበት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ⊚ በሌላ በኩል ደግሞ የቀን ልብ ባካና ነው፤ ዓይን ብዙ ያያል፥ ሐሳብ ይበታተናል፡፡ በተሰበሰበ ልብ ለመማር፤ በተጨማሪ ‹‹ሊቅ ነኝ›› እያለ ‹‹እስከ ዛሬ ትምህርት አልጨረሰም›› እንዳይሉት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ⊚ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን ለመማር የመጣውን እራሱ እየሄደ ያስተምር ነበርና ኒቆዲሞስ ምንም በሌሊት ቢመጣም ማወቅን ፈልጎ ነውና ስለዳግም መወለድ /ስለጥምቀት/ በእግዚአብሔር ልጅ ስለማመንና ስለ ጽድቅ ስራ በዝርዝር አስተምሮታል፡፡ ⊚ ኒቆዲሞስ በመጨረሻው ቀን በዕለተ ዐርብ በስቅለቱ ጊዜ፤ ከመስቀል ላይ ሥጋውን ለማውረድና ገንዞ ለመቅበር ቀድሞ ተገኝቷል፡፡ /ዮሐ. ፲፱፥፴፰/ ፨ከኒቆዲሞስ ሕይወት የምንማረው፡- ፩. ትሕትና፦ ኒቆዲሞስ በትምህርት፣ በሹመት፣ በባለጸግነት የአይሁድ አለቃ ሲሆን አለቅነቱ ግን ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ እርሱ ተገኝቶ ለመማር አልከለከለውም፡፡ /በጽሑፉ መጨረሻ ያለውን ቅኔ ተመልከቱ/ ፪. አለማመካኘት፦ ከመጀመሪያ ሰዎች ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ ሰዎች በምክንያተኝነት በአመፅ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ ኒቆዲሞስም ወደ ጌታ በመቅረቡ የጸሐፍት ፈሪሳውያን አድማና ግርግር ታላቅ እንቅፋትና ምክንያት መሆን እንደሚችል ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት እንደማያዋጣ አውቆ የሚያወጣውን አደረገ፡፡ ፫. ጥበብ፦ በክርስትና ጉዞ ውስጥ ጥበብ የመጀመሪያ ቦታ ትይዛለች፡፡ ኒቆዲሞስም ጕዞውን በጥበብ አደረገ፡፡ በሌሊት ያደረገበት ምክንያት፡- ራሱ መምህር ሆኖ ሌላ ትምህርት አስፈለገው ብለው ሌሎች እንዳይሰናከሉበት፣ የመዓልት ልቦና ስለሚሰበሰብ በቂ ዕውቀት ለማግኘት፣ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት በመዓልትም በሌሊትም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብን ለማጠየቅ፣ ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ያሉ ነፍሳት በሲዖል ይገኛሉ ሲል፣ በመዓልትም በሌሊትም ብትፈልጉ ትገኛለች ሲል ነው፡፡ በእውነት ግሩም ጥበብ! ፬. የተነገረውን አምኖ በመቀበሉ፡- ጸሐፍት ፈሪሳውያን ብዙ ምክንያቶች እየደረደሩ የጌታን አምላክነት አምኖ መቀበል ሲያቅታቸው እርሱ ግን ጌትነቱን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ፭. ለእውነት መመስከር፡- እነርሱ ሲክዱ ጌታ ላይም ትርፍ ቃል ሲናገሩ፤ በድፍረት መክሰሳቸውን እየነገራቸው የጌታችን አምላክነቱን በግልጽ ይመሰክር ነበር፡፡ ፮. ጽንዓት፡- ብዙዎች በመከራ ጊዜ ላይለዩት ቃል ቢገቡም መጨረሻ ላይ ያኔ በመከራ ሰዓት ከመስቀሉ ሥር ሊገኙ የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስም በዚች ሰዓት ያንን መከራ ታግሶ በጽነዓት ከዮሴፍ ጋር የጌታን ሥጋ ከመስቀል አውርደው በአዲስ መቃብር ቀብረውታል፡፡ ምንጭ፤ የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዐቢ ፠፨፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠፨፠ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958