es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 042 suscriptores, ocupando la posición 5 280 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 240 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 042 suscriptores.

Según los últimos datos del 29 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 518, y en las últimas 24 horas de 1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.50%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.35% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 090 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 660 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 33.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 30 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 042
Suscriptores
+124 horas
+917 días
+51830 días
Archivo de publicaciones
#_ግንቦት_26_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተ_ማርያም_ልደታቸው_ነው፡፡ ፠፠በማዕጠንታቸው የታወቁ፤ ፠፠በጽድቅ ሥራቸው የተደነቁ፤ ፠፠5ት መቅሰፍቶችን የሚያርቁ፨ ፠በመራ ውዕይ (ሸዋ ፥ ቡልጋ) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክና ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መንና ነበር፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡ ፠አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡ ፠ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡ ለአብነትም፤ *ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤ *በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤ *በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤ *ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤ *በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርል፤ *ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤ *በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡ *የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡ *"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም" የተባለለት ታላቅ አባት ነው፡፡ ፠ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡ ፠ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡ *የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡ ፠ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው:: "*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው:: +ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::  ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤ 1. #_መብረቅ፣ 2. #_ቸነፈር፣ 3. #_ረሃብ፣ 4.#_ወረርሽኝ፣ 5.#_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡ ፨በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡ (ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡) #ሰላም_ለጽንሰትከ_እማኅፀነ_ቅድስት_ዮስቴና፤ #በብሥራተ_ጻድቅ_ባሕታዊ_ሠናየ_ዜና፡፡ #ሀብተማርያም_ጴጥሮስ_ሐዋርያ_ወልደ_ዮና፤ #መሐረኒ_ምግባረ_ጽድቅ_ወጸግወኒ_ልቡና፤ #አፍቅሮ_ቢጽ_እኅሥሥ_ዘምስለ_ፍጽመት_ትሕትና፡፡ ፎቶ ላይ የሚታዩት ገዳሞቹ፤ ፨ብሔረ ብፁዓን ድበረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ ፨ቃሌ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተማርያም ገዳም፤ አዲስ አበባ ከዊንጌት ትምህርት ቤት አጠገብ፡፡

‹‹ከእግዚአብሔር የኾነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፡፡››፤ በልዩ አቀራረብና በአዲስ የሥርዐተ ትምህርት ዝግጅት፡፡ /ለትምህርቱ የምትመዘገቡ ካሁኑ ዝጅት አድርጉ፤ እንደ አስፈላጊነቱ የመግቢያ ፈተና ሊኖር ይችላል!!፡፡/

#ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ_፤ እመቤታችን እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ለ3 ዓመት ከ6 ወር ከተሰደዱ በኋላ ወደ ግብጽ ሃገር ገብታ በሰላም ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫ *በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤ ፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (365ት ቀናት ሙሉ ዝክር በማኅበረ መድኀኔ ዓለም አዳራሽ የሚዘከርባት ቤ/ክ) ፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ)

#የ100ኛ_ዓመት_መዝጊያ_መርሐ_ግብር_በደብረ_ናዝሬት_ቅዱስ_ዮሴፍ_ቤተ_ክርስቲያን፡፡ ፠እድሳት የተደገለት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ (ከ፻ ዓመት ዓመታት በፊት በ፲፻፱፲ ዓ.ም. በሰብዮን ኀይለ ማርያም የተመሠረተው) ዐርብ ግንቦት 23 በ9 ሰዐት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይመረቃል፡፡ ፠ግንቦት 24/2011 ታቦቱ ወጥቶ ይነግሳል፡፡ ፠ከግንቦት 23-27፤ ከ10፡30 ጀምሮ ልዩ የዐውደ ምሕረት ጕባኤ ይካሄዳል፡፡ #ጻድቁ_ዮሴፍ_፤ **የጌታችን ከእመቤታችን መጸነስ በመንፈስ ቅዱስ ግብር መሆኑን በመልአክ የተገለጸለት **የእመቤታችን የድንግል ማርያም ጠባቂዋ፤ **ከእመቤታችንና ከልጇ ከአምላካችን ጋር ለ3 ዓመት ከ6 ወር አብሮ በበረሃ የተሰደደ **በድንግልና ለወለደችው መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ አባት ተብሎ የተጠራ **በእረፍቱ ጊዜ አባት ተብሎ በተጠራለት በመድኀኔ በክርስቶስ እጅ የገነዘ ✤#_ሊቁ_አባ_ጽጌ_ድንግል_በሰቈቃወ_ድንግል ድርሰቱ እንዲህ ብሎ ያመሰገነው፡፡ ጐየ ዮሴፍ ብሔረ ግብጽ ተንሢኦ እምንዋሙ፤ መልአከ እግዚአብሔር ሌሊተ በከመ ነገሮ በሕልሙ፡፡ ነሢኦ ሕፃነ ዘምስለ ማርያም እሙ፤ ይእቲ ትበኪ ወትቤ ቀቲሎትየ ይቅድሙ፤ እምእርአይ ለወልድየ ዘይትከዐው ደሙ፡፡ (የእግዚአብሔር መልእክተኛ የኾነ ቅዱስ ገብርኤል ሌሊት በሕልሙ እንደነገረው ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቅቶ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ ይዞ ወደ ግብፅ ሃገር ሸሸ፤ ድንግል ማርያምም የልጄ ደም ሲፈስ ከማይ ይልቅ የሄሮድስ ሠራዊት እኔን አስቀድመው ይግደሉኝ እያለች አለቀሰች፡፡ / ሰቈቃወ ድንግል፣ ማቴ.2፥13/ ፠ደብሩ፤ ደብረ ናዝሬት ተብሎ የተሠየመው ጌታ በቤተ ልሔም ተወልዶ ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ ተሰዶ ሲመለስ ወደ ቤተ ልሔም ሳይኾን ናዝሬት ገብቶ ነው ያደገው፤ እንዲሁም ናዝሬት አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ የተቀመጠባትና ብዙ ምሥጢራት ያየባት በመኾኗ ደብረ ናዝሬት ተብሎ ደብሩ ተሰይመሟል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በደጃዝማች መርዕድ መንገድ ላይ፤ ከቦሌ ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው ቀለበት መንገዱ ዳር ላይ ይገኛል፡፡ (የታክሲ ትራንስፖርት፤ ከላጋር፣ ከፒያሣ፣ ከ4ኪሎ ቃሊቲ መናኸሪያ በቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ብለው በሚጭኑት በቶሎ ቤተ ክርስቲያኑ በር ድረስ ያደርስዎታል፡፡)

#ዐርብ_ግንቦት_23_2011 ዓ.ም.#131ኛ_ሳምንት_የዐርብ_ጕባኤ_ከ12-2ሰዓት፤ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል:: ትምህርት ይሰጣል::
#ዐርብ_ግንቦት_23_2011 ዓ.ም.#131ኛ_ሳምንት_የዐርብ_ጕባኤ_ከ12-2ሰዓት፤ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል:: ትምህርት ይሰጣል::

አርእይኒ ገጸ ዚአኪ ማርያም ምዕረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ፡፡ #ማርያም_ሆይ_ለሌላ_የማልነግረው_( #_ሌላ_የማይሰማው)#ነገርን_እነግርሽ_ዘንድ_አንድ_ጊዜ_ፊትሽን_ግለጪልኝ_፡፡

እንኳን አደረሳችሁ፡፡ #ግንቦት_21_ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም_የምናከብርበት_ምክንያቱና_ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_21፡፡ ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከግንቦት 21 እስከ 25 የእመቤታችንን በዓል (አጎበር ጥለው፥ ድንኳን ተክለው፥ ድባብ ዘርግተው ያከብራሉ፤ እመቤታችንም ከቅዱሳን ጋር በመገኘት ትባርካቸዋለች፡፡) እነዚህ 5ት ቀናትም ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት 5ቱን ከተ.ቊ 25ኛ እስከ 29ኛ ያለውን ይይዛሉ፡፡ እነርሱም፤ ፠25ኛ. ግንቦት 21 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ ፠26ኛ. ግንቦት 22 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ ፠27ኛ. ግንቦት 23 ቀን ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ የታየችበት ነው፡፡ ፠28ኛ. ግንቦት 24 ተሰዳ ግብጽ የገባችበት ነው፤ /ኢሣ.1 9፥11፣ ማቴ.2፥13-15/ ፠29ኛ. ግንቦት 25 ልጇ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የደረቁ በትሮችን ተክሎ ያለመለመበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸውን የደብረ ምጥማቅ በዓላት (ከግንቦት 21-25) በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተነሥቶ የነበረው የግብፁ ንጉሥ እንዳያከብሩ በመከልከሉ፤ ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ለማክበር ይሄዱ ነበርና አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለመጽናኛ እንዲሆን በሃገራችን የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያምን መሠረተ፤ እመቤታችንም ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠችው፤ ይኸው ቃል ኪዳኗ ሳይታጠፍ በጻድቃኔ ማርያም ዛሬ ድረስ ስፍር ቊጥር የሌለው ብዙ ተዓምራትና የምሕረት ሥራ የሚፈጸምባት ቅዱስ ቦታ ኾና ትገኛለች፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ በሃገራችንም ግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ ክብረ በዓል በዋነኛነት!!! (በዋነኛነት!!!) የሚከበርባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤ *1ኛ) #ደብረ_ምጥማቅ_ጻድቃኔ_ማርያም_ገዳም፡፡ /ሰሜን ሸዋ/ *2ኛ) ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን /ጎንደር ከተማ/ *3ኛ) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም /አዲስ አበባ/ (ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በ Facebook, Telegram, Email, Viber, Xender, Bluetooth በማድረስ ይተባበሩ፡፡) ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡

አዲስ ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ (ቅዳሴ ቤት ሲከበር) ወይም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ሲመረቅ የሚባለውን #ሥርዐተ_ማኅሌት እነሆ አቅርበንላችኋል፡፡ (ቤተ ክርስቲያኑ የቅዱስ ገብርኤል ከሆነ የሚቆመው ማኅሌት ከሌሎቹ ሁሉ ስለሚለይ የማኅሌቱን ጽሑፍ ያለ ሐረግ አዘጋጅተነዋል፡፡) #ግንቦት_21_2011_ዓም_የሚመረቁ_አብያተ_ክርስቲያናትን_እንጠቁማችሁ #እናንተም_ጨምሩባቸው፤ #ደቡብ_ወሎ_ደሴ_ወረኢሉ_ካቤን_ሰኞ_ገበያ_ወይብላ_ማርያም (በ8 ወር ተሰርታ የተጠናቀቀች) /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ. ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት/

ኢትዮጵያን አይርሱ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአምላክ ጳጳሱ፣ በሰማዩ መቅደስ ሰዓታት ሊያደርሱ፣ ከርክበ ካህናት አቋርጠው ተነሡ፤ በሞት ሠረገላ የሕይወት ፈረሱ፣ እንደ አባ ገሪማ ሔዱ ገሰገሱ። በስብሐተ ፍቁር በዘይነግሡ፣ አባ ኤልሳዕ አደራ ኢትዮጵያን አይርሱ፤ እኛም እንዳንጠፋ ዘወትር ያስታውሱ። ©ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

፠በሃገራችን ብቸኛ የኾነውንና በድርቡሽ ጠፍ ሁኖ ለ126ዓመታት የቆየውን የሠለስቱ ምዕት ቤ/ክን ያስከፈቱ፤ ፠ለ41 ዓመታት ከኤጲስ ቆጶስነት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ያገለገሉ፤ ፠በኹለት ቅዱሳን ፓትርያርኮች ምርጫ በዕጩነት የቀረቡ፤ ፠በእግራቸውና በበቅሎ ገጠር ከመንደር እየዘዋወሩ ያስተማሩ ሕንፃ ቤ/ክን የባረኩ (ፎቶውን ይመልከቱ)፤ ፠ለበርካታ ሺህ ካህናትና ዲያቆናት የክህነት አባት የኾኑ፤ ፠ቤተ ክርስቲያን፣ ምዕመናንና ሊቃውንት ሲበደሉ ማንንም (መንግሥትም) ቢኾን የማይፈሩ፤ በዚህም እስከ እስር የተዳረጉ፡፡ ፠የፍቅርና የትሕትና አባት፤ የዋሁና ደጉ፤ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ፡፡ ፠በጎንደር ክፍለ ሀገር፣ ደብረ ታቦር አውራጃ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ደብር፣ ከአባታቸው አቶ ፈንታ ወልድየ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ወለተ ተክለ ሃይማኖት፣ ግንቦት 29 ቀን በ1927 ዓ.ም. ተወለዱ #የትምህርት_ሁኔታቸው_፤ *ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ፣ በተወለዱበት ደብር በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ የድጓ መምህር ከነበሩት መምህር ሙሉጌታ ኀይሉ የቃል ትምህርት እና ጾመ ድጓ ተምረዋል፡፡ *ከዚያም ወደ ሸዋ ክፍለ ሀገር መጥተው በደብረ ብርሃን አውራጃ በናስ ማርያም ከአለቃ ቤተ ማርያም ድጓ፣ በምግልዋሻ ገብርኤል ከአለቃ ኀይለ ጊዮርጊስ ቅኔ ተምረዋል፤ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ልዩ ልዩ መምህራን ዘንድ እየተዘዋወሩ አቋቋም እና ቅኔ ተምረዋል፡፡ ድጓውንና ዝማሬ መዋስዕቱን ጽፈው አመልክተው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ *ቀጥሎም በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም ከመምህር ገብረ ሕይወት ሐዲስ፥ ፍትሐ ነገሥት፣ ትርጓሜ ዳዊት፣ ኪዳን፣ ትምህርተ ኅቡአት፣ ባሕረ ሐሳብ፣ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ ተምረዋል፡፡ እንዲሁም ከአለቃ መርዓዊ ዝማሬ መዋሥዕት፣ ከአለቃ አፈ ወርቅ ዜማን በማሻሻል፣ ከመሪጌታ ልዑል ቅዳሴ፣ ከመሪጌታ ቀለም ወርቅ ተምረዋል፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን እንደ ንህብ የቀሰሙ፤ ቢዘምሩ ቢቀድሱ፣ ቢሰብኩ ቢናገሩ፣ ቢተቹ ቢፈርዱ የሚያምርባቸው፤ ሊቅነት ከደግነት የተባበረላቸው ሙሉ አባት ናቸው፡፡ #ክህነት_፤ *በ1945 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዲቁና፣ *በ1964 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ገዳም ምንኩስናን ተቀብለዋል፡፡ *በ1965 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቅስና፣ *በ1969 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡ #አገልግሎት_፤ *በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም፣ በትምህርት ላይ እንዳሉ፥ በቅዳሴ፣ በመዘምርነትና በልዩ ልዩ የገዳም ሥርዓቶች፣ ለዐሥራ አምስት ዓመታት ያኽል አገልግለዋል፡፡ *በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በመምህርነት በማገልገል እንዳሉ ለኤጲስ ቆጶስነት ማዕርግ ተመረጡት፡፡ ጥር 8 ቀን 1971 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርኩ የተካሔደው ምርጫ፣ ከ14ቱም ክፍለ ሀገር እና ከአዲስ አበባ፣ ከቀረቡት 21 ቆሞሳት 12ቱ በድምፅ ብልጫ ማለፋቸውንና በሰሜን አሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በከፍተኛ ድምፅ የተመረጡት አባ ላዕከ ማርያም ማንደፍሮ በኋላ ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ተጨምረው በጠቅላላ 13 አባቶች ለሢመተ ጵጵስና ቀርበው በጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. በሦስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ሥርዐተ ጵጵስና ተከናወኖላቸዋል፡፡ ይህም በአንድ ጊዜ 13 ጳጳሳት ሲሾሙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከፍተኛውና የመጀመሪያው ነው፤” የእኒህ 13 ኤጲስ ቆጶሳት መመረጥም ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት፣ ስለ ሰበካ ጉባኤ መጠናከር፣ ቤተ ክርስቲያን ለወጣቶች ማድረግ ስላለባት መልካም አቀባበልና ስለ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነትና ስለሌላው የቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ይዘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ #በጵጵስና_አገልግሎት፤ በቀድሞው ስማቸው መምህር ቆሞስ አባ ኅሩይ ፈንታ ይባሉ የነበሩ አቡነ ኤልሳዕ ጵጵስና ከተቀበሉ በኋላ ለ41 ዓመታት በሚከተሉት አህጉረ ስብከቶችና ኃላፊነቶች በትጋትና በንቃት፥ በብርታትና በታማኝነት፤ ገጠር ከተማ ሳይለዩ፤ በበቅሎና በአግራቸው አቀበት ዳገቱን እየወጡ እየወረዱ አገልግለዋል፡፡ ፠ ከ1971 እስከ 1976 ዓ.ም. የጅማ፣ ፠ ከ1976 እስከ 1978 ዓ.ም. የካፋ፣ ፠ ከ1978 እስከ 1981 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ፠ ከ1981 እስከ 2001 ዓ.ም. የደቡብ ጎንደር፣ ፠ ከ2001 እስከ 2011 ዓ.ም. የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመኾን፣ ቤተ ክርስቲያንን ለ41 ዓመታት በትጋት አገልግለዋል፡፡ ፠ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመነ ክህነት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የካህናት የበላይ ጠባቂ ኾነው ሠርተዋል፡፡ ፠የራብዓይ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና የስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የፕትርክና ምርጫ በተከናወነበት ወቅት፣ በዕጩነት ከቀረቡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም አንዱና ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ በተለይም ከ1986 ዓ.ም. አንሥቶ፣ በግፍ እስር ታፍነው የሚገኙትን ሊቁን እንደሥራቸው አግማሴን ለማስፈታት ቅዱስ ሲኖዶስንና መንግሥትን ሳይሰለቹ በመወትወትና በሀገረ ስብከታቸው የሚፈጸሙ ኢሰብአዊ ተግባራትን በመቃወማቸው ምክንያት፣ በኮማንድ ፖስት እስከ መታሰርና በተለያየ መልክ የሚገለጽ መገፋት የደረሰባቸው መኾኑ የሚታወስ ነው፡፡ በታኅሣሥ ወር 2006 ዓ.ም.፣ “አራቱ ኀያላን” የተሰኘውን መጽሐፉን በጎንደር ባስመረቀበት መርሐ ግብር ላይ፥ “ሙሐዘ ጥበባት” የሚለው ስመ ማዕርግ ለጸሐፊና የነገረ ቤተ ክርስቲያን ተመራማሪ ዲን. ዳንኤል ክብረት ሰጥተውታል፡፡ ገጠር ሳይመረጡ በትጋት፣ በደግነትና በሰላማዊነት አባታዊ ሓላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ (ፎቶው ይሄንኑ ይመሰክራል) የብፁዕ አቡነ ገሪማ ሐዘን ሳይረሳ ሌላ ደግ አባታችንን ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ሠርክ ላይ በተወለዱ በ84 ዓመት ዕድሜያቸው አጣን፤ ሰኞ ግንቦት 19 በጎንደር መስቀል ዐደባባይ የስንብትና የሽኝት መርሐ ግብር ተደርጎ፤ ሥርዓተ ቀብራቸው፥ ማክሰኞ ግንቦት 20 በኑዛዜ ቃላቸው መሠረት በታላቁ ደብር በደራ ወረዳ አፈር ውኃ እናት በመካነ ሰማዕት ቅ/ገላውዴዎስ በ7፡00 ሰዐት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይፈጸማል፡፡ ከ40 ዓመት በኋላ ዛሬ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት ካሉን 70 ያኽል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ፣ በሹመት ቀዳሚዎቹ በ1971 ዓ.ም. የተቀቡቱ ሲኾኑ፣ ዓረፍተ ዘመን እየገታቸው እየተለዩን ናቸው፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ በዐጸደ ሥጋ የቀሩን የዘመኑ ተሿሚ አባቶች ከሦስት አይበልጡም፡፡ ካረፉት አባቶች በረከት ይክፈለን፤ ያሉትንም በጤናና በዕድሜ፤ በብርታትና በኀያል ጠብቆ የአበው አምላክ መድኀኔ ዓለም ያቆይልን፡፡ የብፁዕነታቸው በረከት ይድረሰን፤ አሜን፡፡ (ፎቶዎቹ፤ ፠ በሰሜን ተራሮች ታስ ደጀን አጠገብ የታላቁን ገዳም የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ ቤ.ክና የቅዱስ ያሬድ የዜማ ትምህርቶችን በአንድ ላይ ይዞ እንዲሠራ ለታሰበው የመሠረት ድንጋይ ለመጣል ሲጓዙ፤ ፠ በጵጵስና ቀደምት ተሽዋሚ በመሆናቸው ከአቡነ ናትናኤል ጋር በመሆን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ሲሾሙ፡፡ ፠ ሆስፒታል ተገኝተው ሕሙማንን ሲጠይቁ፤ ፠ በሃገር አቀፍ የሰበካ ጕባኤ ስብሰባ ላይ፡፡ ፠ በጎንደር ለሚገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችን የምስከር ወረቅት ሲያበረክቱ፡፡)