የጥበብ ማዕድ
📈 Análisis del canal de Telegram የጥበብ ማዕድ
El canal የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 880 suscriptores, ocupando la posición 5 407 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 116 en la región Etiopía.
📊 Métricas de audiencia y dinámica
Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 880 suscriptores.
Según los últimos datos del 24 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 628, y en las últimas 24 horas de 31, conservando un alto alcance.
- Estado de verificación: No verificado
- Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 2.61%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 2.09% de reacciones respecto al total de suscriptores.
- Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 415 visualizaciones. En el primer día suele acumular 332 visualizaciones.
- Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.
📝 Descripción y política de contenido
El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 25 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.
በ20ኛዉ ክፍለዘመን ላይ በ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰናዳ ታዋቂ የፍልስፍና ፅሁፋዊ ሲምፖዚየም ነበር፤ ይህ ሲምፖዚየም ርዕሱን "Theology and Falsification"ላይ አርጎ ሶስት ፈላስፋዎች ምልልስ ያደረጉበት የፅሁፍ ሙግት ነዉ።
የመጀመሪያዉ አንቶኒ ፍሊዉ ሲሆን ሙግቱን ጆን ዊዝደም "አማልክት" በሚሰኘዉ ትረካዉ ላይ ካለዉ ምስሌያዊ ፅሁፍ በመነሳት ይጀምራል።
ምሳሌዉም እንዲህ እያለ የሚቀጥል ነዉ፦ ሁለት ተጓዦች ጫካ ውስጥ ብዙ አበቦችና አረሞች ያሉበት ቦታ ያገኛሉ። አንደኛው "ይህንን የሚንከባከብ አትክልተኛ አለ" ሲል፣ ሌላኛው ግን "አትክልተኛ የለም" ይላል። አትክልተኛውን ለማግኘት ቢጠባበቁም፣ በኤሌክትሪክ የታጠረ አጥር ቢሰሩም፣ አልፎ ተርፎም አነፍናፊ ውሾችን ቢጠቀሙም ምንም አይነት ሰው አያገኙም።
ነገር ግን አማኙ አሁንም አልተረታም፤ "አትክልተኛው የማይታይ፣ የማይዳሰስ፣ ሽታ የሌለውና በድብቅ የሚመጣ ነው" ይላል። በዚህ ጊዜ ተጠራጣሪው እንዲህ ሲል ይጠይቃል፦ "ይህ አንተ የምትለው የማይታይና የማይዳሰስ አትክልተኛ፣ በጭራሽ ከሌለ (ምናባዊ) አትክልተኛ በምን ይለያል?"።
በዚህም ፍሊዉ አንድ እምነት ማስረጃዎች በሚቃወሙት ቁጥር "እንዲህ ቢሆንስ" እያለ ማስተባበያዎችን እና ማለሳለሻዎችን እየተካ ከሄደ መጨረሻ ላይ የተነሳበት ነጥብ ትርጉም አልባ የሚሆንበት ደረጃ ላይ ይደርሳል የሚል ነዉ፤ለምሳሌ ፈጣሪ ሰዎችን ይወዳል ለሚለዉ ነጥብ ምድር ላይ ያሉ ክፋቶች እንደ ማስረጃነት ሲቀርቡ፣ "አይ የፈጣሪ ፍቅር እንደ ሰዉ አይደለም"፣"ፈጣሪ የሚወደዉን ይፈትናል"፣"ፈጣሪ የተሻለ እቅድ አለዉ" እያሉ የሚሰጡ ማለሳለሻዎች በመዉደድ እና ባለመዉደድ መሃል ያለዉን መስመር ሙሉ ለሙሉ የሚያደበዝዙ እና መዉደድ የሚለዉ ቃል ምንም አይነት የሚወክለዉ ምድራዊ ሁኔታ እስከማይኖር ድረስ ትርጉም አልባ ያረጉታል ይህንንም ፍሊዉ "በሺህ ማስተባበያዎች የሚሞት አንድምታ" ወይም "Death by thousand qualifications" ይለዋል።
ሌላኛዉ ደሞ መስፈርት የግድ ሊኖር ይገባል የሚል ነዉ፤አንድ ነገር እዉነት ነዉ ሲባል ተቃራኒዉ ዉሸት ነዉ እየተባለ ነዉ በዚህም አንድ አባባል እዉነት መሆኑን ለማወቅ ዉሸት መሆኑን የሚያረጋግጥ ምን አይነት ድርጊት ቢፈጠር ነዉ? የሚለዉን ጥያቄ መመለስ አለበት፤ አያይዞም "እግዘብሔር ይወደናል" ለሚሉ ሃይማኖተኛ ሰዎች ምን አይነት መጥፎ አጋጣሚ ቢፈጠር ነዉ እምነታቹ ዉሸት መሆኑን የምትቀበሉት ሲል ይጠይቃል።
በመቀጠል ሪቻርድ ሄር የፍሊዉን አምክንዮአዊ ልክነት በመቀበል ሃይማኖትን ተምርምሮ ፉርሽ ከሚደረጉ ነጥቦች ዘንዳ ማሰለፉ ግን ልክ እንዳልሆነ ይሞግታል።
ሄርም ለዚህ የአንድ እብድ እና የዩንቨርስቲ አስተማሪዎቹን ምሳሌ ይሰጣል፤ምሳሌዉም እንዲህ የሚል ነዉ፦
አንድ እብድ ሰው "የዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ሁሉ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ" ብሎ ያምናል። ጓደኞቹ በጣም ደግ የሆኑ አስተማሪዎችን
ቢያስተዋውቁትም፣ እሱ ግን "ይህ ተንኮላቸውን ለመሸፈን ያደረጉት ነው" በማለት እምነቱን አይቀይርም። እንደ ፍሉ መመዘኛ ይህ ሰው ምንም አይነት መረጃ እምነቱን ስለማይቀይረው አባባሉ "ትርጉም የለውም" ሊባል ይችላል፤ ነገር ግን በእሱና በጤነኛ ሰው መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።
ሄርም በዚህ ሙግቱ ላይ አንድ "ብሊክ" የሚለዉን ፅንሰሃሳብ ያስተዋዉቃል፤ ይህም ይህን አለም የምናይበት መሰረታዊ፣ኢምክንያታዊ፣ ስሁት መሆኑ ሊረጋገጥ የማይችል እና ሌላ እዉነታዎችን ልንተረጉምበት የምንነሳበት አመለካከት ነዉ ይላል።
ሁሉም ሰዉ ብሊክ አለዉ ለምሳሌ መኪና ስንነዳ መሪዉ አይገነጣጠልም ብለን የምናምነዉ በሳይንሳዊ ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን አለም አስተማማኝ ነች የሚለዉን ቅድመ እሳቤ(ብሊክ) ይዘን ነዉ።በዚህም ሃይማኖት እንደ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ሊቆጠር የሚገባ ሳይሆን አለምን የምንመለከትበት መሰረታዊ መነፅር ነዉ፤ሳይንቲስትም ሆነ አማኝ የየራሳቸዉ ብሊክ አላቸዉ በማለት ያትታል።
ባሲል ሚችል ደሞ ከሁለቱም የተለየ ሃሳብ ያቀርባል፤ እሱንም በተዋጊዉ እና እንግዳዉ መሪ ምሳሌ ለመግለጥ ይሞክራል።ምሳሌዉ እንዲህ ሲል ይቀጥላል፦
በጦርነት ወቅት አንድ ተዋጊ ከአንድ እንግዳ ሰው ጋር ይገናኛል። እንግዳው "እኔ የነፃነት ታጋዮች መሪ ነኝ፣ ምንም ቢፈጠር እመነኝ" ይለዋል። ተዋጊው በእንግዳው ማንነት ይረካል። በኋላ ላይ ግን እንግዳው አንዳንዴ ጠላትን ሲረዳ፣ እሱንም ድጋፍ ሳይሰጠዉ ሲቀር ይመለከታል። ታዲያ ተዋጊው በእንግዳው ድርጊት ቢጨነቅም፣ በመጀመሪያው ግንኙነታቸው ላይ በመመስረት "እንግዳው ከእኛ ጋር ነው" ብሎ ማመኑን ይቀጥላል።
ሚችል በመቀጠል እንደ ሄር አባባል ሃይማኖት በጭፍን የሚታመን "ብሊክ" ብቻ አይደለም። አማኙ መከራና ስቃይ በእምነቱ ላይ ተቃራኒ ማስረጃ መሆናቸውን ይገነዘባል በተጨማሪም የሚያረጋቸዉ ገለፃዎች እንዲሁ በደፈናዉ ምናባዊ ብቻ ሳይሆኑ ገሃዳዊም ናቸዉ፤ ፈጣሪ ይወደኛል ሲል መዉደድ በገሃዱ አለም ላይ የሚወክላቸዉን ነገር እሳቤ ዉስጥ በማስገባት ነዉ የሚለዉ፤ ሆኖም አንድ አማኝ በእምነቱና በሚያየው መከራ መካከል ያለው ግጭት በውስጡ ሊሰማው ይገባል፤ ካልሆነ ግን እምነቱ ትርጉም አልባ ይሆናል። እምነት ማለት መረጃን በቸልታ ማለፍ ሳይሆን፣ ምንም እንኳ ተቃራኒ ሁኔታዎች ቢኖሩም በመጀመሪያው እውነት ላይ መጽናት ማለት ነው።
ከ Abdisa defar
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
