cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

It is a platform for information on historical and contemporary architecture, urbanism, landscape, and the construction industry inside Ethiopia. It will also include similar issues from across the world.

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
11 667
Suscriptores
+4524 horas
+2067 días
+94530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

9ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ። ደጃዝማች ቢትወደድ ጠናጋሻው በሀብቴ። 9ኛው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሲሆኑ ጣልያን አዲስአበባ ሳይገባ ከ1926 እስከ 1928 ድረስ የመጨረሻው ከንቲባ ነበሩ። ምንጭ። ታሪካችን፣ ዊክፔድያ @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
6
ትልቁ ከተማ። ቶክዮ፣ ጃፓን ቶክዮ በአለም ላይ ትልቋ ከተማ ስትሆን 37.4 ሚልዮን ህዝብ አሏት። ስፋቷም 13,452 ካሬ ኪሎሜትር ነው። @ethiopianarchitectureandurbanism. Tokyo, Japan, is the largest city on Earth, with a population of 37.4 million people, which is over four times the population of New York City, USA. In total, the Japanese metropolis covers an area of 13,452km2. #tokyo #facts #factsdaily #geography #earthfacts #sciencelover
Mostrar todo...
👏 3👍 2 1😁 1
ኦሮሚያ ባንክ በገላን ለሚያስገነባዉ የልዕቀት ማዕከል ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ዉል መፈራረሙን አስታወቀ (ካፒታል : ግንቦት 07፤2016 ዓ.ም.) ባንኩ በኦሮሚያ ክልል በገላን ክፍለ ከተማ በ20 ሔክታር መሬት ላይ እያስገነባ የሚገኘዉ ሁለገብ የልህቀትና ኮይቬንሽን ማዕከል የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ተከትሎ ለሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ጥላሁን አበበ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የ 1.1 ቢሊየን ብር የግንባታ ዉል ከሰሞኑ መፈራረማቸውን ካፒታል ከባንኩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል ። በገላን የሚገነባው ማዕከል የባንክ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የማደሪያ ሕንፃዎችን ጨምሮ የመሰብሰብያ አዳራሾች፣ የገበያ ማዕከሎች የነዳጅ ማደያ፣ የመዋኛ ገንዳዎች ለተለያዩ ቢዝነሶችና አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎችን አካቶ የሚይዝ ነው፡፡ ከ1.1 ቢሊዮን በሚጠጋ ብር የሚገነባዉ ይህ ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉል ግዙፍ ባለ 9 ወለል ህንፃ በ1200 ካሬ መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል፡፡ ፊርማዉን የተፈራረሙት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈሪ መኰንን እና የጥላሁን አበበ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን አበበ መሆናቸው ተነግሯል? አማካሪው በዜናው ላይ አልተጠቀሰም። ምንጭ። Capital @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👍 7 1
የዝናብ መጥረጊያ ያላቸውና እስከ 10 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ የጠራ ምስል የሚያሳዩ የደህንነት ካሜራዎች። አዲስ ዋልታ ወደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቅናት በከተማው ውስጥ ስራ ስለጀመሩትና ለስማርት ሲቲ ግንባታ ያግዛሉ የተባሉትን የደህንነት ካሜራዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ካሜራዎች የህዝብ ደህንነትን በቴክኖሎጂ በታገዘ አማራጭ የሚጠብቁ፣ በተሽከርካሪ ፍሰት ውስጥ ስማርት የሆነ የትራፊክ ማኔጅመንት ሲስተምን የሚዘረጉ፣ የህግ አስከባሪ አካላትን የሚደግፉና ስራዎችን የሚያቀሉ፣  የስማርት  ከተማ ግንባታን እውን የሚያደርጉ ካሜራዎች ናቸው፡፡ ካሜራዎቹ እስከ 10 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ የሚደርሱ ሁነቶችን ጥርት ባለ ምስል መመልከት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ካሜራዎች የመኪናዎችን ታርጋ የሚለዩ ከመለየትም አልፎ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡ፣ በተሽከርካሪ ፍሰት ውስጥ ስማርት የሆነ የትራፊክ ማኔጅመንት ሲስተም እንዲኖር የሚያገለግሉ ካሜራዎች ናቸው፡፡ ማግኔቲክ በመሆናቸውም በየትኛውም ብረት ነክ ነገሮች ላይ ተለጣፊ ስለሆኑ ለመግጠም የማያስቸግሩና ተንቀሳቃሽ ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ሲኖር የራሳቸው የሆነ የዝናብ መጥረግያ አላቸው፡፡ ካሜራዎቹ በሁሉም ከተሞች ላይ እየተገጠሙ የሚገኝ ሲሆን ከተሞችን ስማርት በማድረጉ ሂደት ውስጥ የራሳቸውን ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡ ምንጭ። WMCC @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👍 4👏 1
ቢሮው ለ12 ማሕበራት ዕጣ አወጣ። የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማሕበራትን ለማብቃት የሚያስችል የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ዛሬም ለ12 ማሕበራት ዕጣ አውጥቷል። ማሕበራቱ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪዶር ልማት ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ የቢሮው የምሕንድስና ግዥ ዳይሬክተር ኢ/ር አለማየሁ ቱሊ በስነ-ስርዓቱ ላይ ገልፀው ማሕበራቱም ቢሮው በሚያስቀምጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት የሚሰጣቸውን ስራ በኃላፊነት ስሜት አከናውነው እንዲያስክቡ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል። ከዚህ ቀደም ዕጣ የወጣላቸው ማሕበራት በኮሪዶር ልማቱ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ይታወሳል። ምንጭ። አዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 06/2016 @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👍 1
ቢግ ፋይቭ ንግግሮች። በነብዩ ዮናስ ጋቦሬ (ፒኤችዲ) Introducing Nebyou Yonas Gabore, CEO of Founder and General Manager, JNK Consulting Architects and Engineers PLC, as a featured speaker at Big 5 Talks. During his informative session, he will elaborate on the “Role of architecture in urban planning and infrastructure development in the region” providing invaluable perspectives. Participants will gain practical expertise relevant to urban development and high-rise construction endeavors. Don't miss this chance to learn from a thought leader in the industry and earn CPD points. Register now for free: https://bit.ly/3VLdinH 🗓️ Date: 01 June 2024 ⏱️ Time: 11.00 - 11.30 AM ምንጭ። Big 5 Construct Ethiopia. @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👍 4 4
ታላቁ አል ነጃሺ ፕሮጀክት። ቦታ። ነጋሽ ከተማ (58.5ኪሜ ከ መቀሌ ሰሜን አቅጣጫ ርቀት ላይ ያለ) የግንባታ ቦታ ስፋት። 117,380ካሬ ሜ. አማካሪ። ዮሀንስ አባይ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች። አጠቃላይ የግንባታ ወለል ስፋት። 92,586.60 ካሬ ሜ. የፕሮጀክት ይዘት። 5 ኮከብ ሆቴል፣ ስብሰባ አዳራሽ፣ ቤተ መዘክር፣ የገበያ ቦታ፣ አል ነጃሺ ዩኒቨርስቲ፣ የመቻቻል ምርምር ማዕከል፣ መድረሳ፣ የአይን እንክብካቤ ማዕከል፣ መስጊድ፣ መኖርያ ቦታዎች፣ አረንጓዴ እንግዳ ማረፍያዎች፣ የቤት ውስጥና ውጭ ማረፍያና መዝናኛ፣ አምፊትያትር፣ አረንጓዴ ስፍራ ወዘተ ይኖሩታል። ንድፍ ደረጃ። ሀሳባዊ/ የመጀመርያ ደረጃ። @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👏 6👍 2😁 1
ድሮ እና ዘንድሮ ሰራተኛ ሰፈር። @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👍 3 1
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሊመረቅ ነው። መጋቢት 29/2007 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ የተጣለለት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊታችን ሰኔ 01/2016 ዓ/ም ተመርቆ ወደ አገልግሎት ይገባል። 600 የሕሙማን አልጋዎችን ይይዛል የተለያዩ ዘመናዊ የመመርመሪያና የሕክምና ቁሳቁሶች አሉት። ከሰባት ሚሊየን በላይ በሚሆኑ የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ነዋሪዎች ያገለግላል። ምንጭ። አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👏 8
መኪና መገጣጠምያ ፋብሪካ ጅግጅጋ። በ 250 ሚሊየን ብር ካፒታል በጅግጅጋ ከተማ የተገነባውና በቀን እስከ 10 መኪና የመገጣጠም አቅም እንዳለው የተገለጸው በዛሬው ዕለት የተመረቀው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ፡፡ ምንጭ። Somali Fast Info @ethiopianarchitectureandurbanism
Mostrar todo...
👍 4
Archivo de publicaciones