es
Feedback
GLOW KG AND PRIMARY SCHOOL ADDIS ABABA ETHIOPIA.

GLOW KG AND PRIMARY SCHOOL ADDIS ABABA ETHIOPIA.

Ir al canal en Telegram

Always strive for Excellence❤!!

Mostrar más
1 431
Suscriptores
+824 horas
+127 días
+730 días
Archivo de publicaciones
ዉድ ወላጆች በሙሉ ከላይ በተገለፀዉ የፈተና ኘሮግራሙን ተከትላችሁ ልጆቻችሁን እንድትረዷቸዉ እናሳስባለን::

የተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል? 12 ወሳኝ ነጥቦች 1. ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ። ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ። 2. መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ።  መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ... የተሳሳተውን እያስተካከሉ ይጓዛሉ። 3. ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ። 4.:አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ.... 5. ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም። 6. ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ:: 7. በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡ 8. ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡ 9. ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡ 10. ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡ 11. ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡ 12. እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉመምህር አማንስስ አብይ

ዉድ ወላጆች እንኳን ደስ አለችሁ / አለን። Congratulations to Glow School Admin ,Teachers , Students and Our parent’s . Baga Gammadaa / gammanne maatiin , Bulchitoonni, Barsiisistonni fi barattoota mana barumsaa Glow hundaaf. Glow school.

አዲስ የተማሪዎች ዝውውር መመሪያ ረቂቅ 2016 ዓ.ም አዲስ የተማሪዎች ዝውውር መመሪያ ረቂቅ 2016ዓም ዋና ዋና ነጥቦች ከዚህ በፊት በተለያዩ ክልሎች ወጥነት ያልነበረው የተከታታይ ምዘና አያያዝ  ማለትም 60% ተከታታይ ምዘና 40% ማጠቃለያ ፈተና አሁን ወደ 40% ተከታታይ ምዘና 60% ማጠቃለያ ፈተና ተሰጥቶ ከ100% ይያዛል ከ9-11ኛ ክፍል Maths and English ከ50% በታች ያመጣ ተማሪ እንዲሁም 1-7ኛ ክፍል 6ኛን ሳይጨምር Maths እና የማስተማሪያ ቋንቋውን ከ50% በታች ካመጣ ወደቀጣይ ክፍል መዛወር አይችልም አንድ ክፍል ደረጃ ከአንዴ በላይ ከደገመ ከትምህርት ይሰናበታል። @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library

በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!🥰🥰 ======================== 👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:- ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን 🥰:- ------------------------------------------------ ☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ 👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።  ☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

የፈተና ፕሮግራም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ነዉ።

የ6ኛና 8ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና ፕሮግራም

ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተናን ለመስጠት የጊዜ ሰሌዳ አዉጥቷል። በመሆኑም ወላጆች ልጆቻችሁ በቤት ዉስጥ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተገቢዉን ጊዜና ቦታ በማመቻቸት እገዛ እንድታደርጉላቸዉ ለማሳሰብ እንወዳለን። ፈተናው ጥር 1 እና 2/2016 የሚሰጥ ሲሆን የጊዜ ሰሌዳዉ ከዚህ በታች አያይዘን ልከናል።