es
Feedback
የኔ' ማስታወሻ ..🧚

የኔ' ማስታወሻ ..🧚

Ir al canal en Telegram

በዚህ ቻናል የማይዳሰስ ጉዳይ የለም የተለያዩ አስገራሚ ታሪኮችን፣ ግጥሞችን፣ መጣጥፎችን፣ ወጎችን እንዲሁም በጥበባዊ እይታ የተቃኙ ሁሉ አይነት ጉዳዮችን እናይበታለን ሼር በማድረግ ቤተሰብ እናብዛ... እወዳችኋለሁ❤️ for any comment :- 👉 @Hamy_Hamy Subscribe 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Yenemastawosha

Mostrar más
1 930
Suscriptores
+624 horas
+347 días
+10330 días

Carga de datos en curso...

Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
julio '26
julio '26
+46
en 1 canales
junio '26
+114
en 0 canales
Get PRO
mayo '26
+84
en 2 canales
Get PRO
abril '26
+56
en 1 canales
Get PRO
marzo '26
+39
en 1 canales
Get PRO
febrero '26
+34
en 1 canales
Get PRO
enero '26
+46
en 1 canales
Get PRO
diciembre '25
+37
en 0 canales
Get PRO
noviembre '25
+34
en 0 canales
Get PRO
octubre '25
+71
en 2 canales
Get PRO
septiembre '25
+42
en 0 canales
Get PRO
agosto '25
+50
en 0 canales
Get PRO
julio '25
+63
en 0 canales
Get PRO
junio '25
+62
en 1 canales
Get PRO
mayo '25
+374
en 9 canales
Get PRO
abril '25
+116
en 4 canales
Get PRO
marzo '25
+360
en 1 canales
Get PRO
febrero '25
+323
en 4 canales
Get PRO
enero '25
+13
en 0 canales
Get PRO
diciembre '24
+24
en 0 canales
Get PRO
noviembre '24
+35
en 2 canales
Get PRO
octubre '24
+24
en 1 canales
Get PRO
septiembre '24
+19
en 0 canales
Get PRO
agosto '24
+33
en 0 canales
Get PRO
julio '24
+29
en 0 canales
Get PRO
junio '24
+17
en 0 canales
Get PRO
mayo '24
+14
en 1 canales
Get PRO
abril '24
+10
en 1 canales
Get PRO
marzo '24
+12
en 0 canales
Get PRO
febrero '24
+10
en 0 canales
Get PRO
enero '24
+8
en 0 canales
Get PRO
diciembre '23
+11
en 0 canales
Get PRO
noviembre '23
+3
en 0 canales
Get PRO
octubre '23
+5
en 0 canales
Get PRO
septiembre '23
+16
en 0 canales
Get PRO
agosto '23
+16
en 0 canales
Get PRO
julio '23
+36
en 0 canales
Get PRO
junio '23
+24
en 0 canales
Get PRO
mayo '23
+320
en 0 canales
Get PRO
abril '23
+24
en 0 canales
Get PRO
marzo '23
+20
en 0 canales
Get PRO
febrero '23
+17
en 0 canales
Get PRO
enero '23
+44
en 0 canales
Get PRO
diciembre '22
+24
en 0 canales
Get PRO
noviembre '22
+33
en 0 canales
Get PRO
octubre '22
+31
en 0 canales
Get PRO
septiembre '22
+36
en 0 canales
Get PRO
agosto '22
+27
en 0 canales
Get PRO
julio '22
+47
en 0 canales
Get PRO
junio '22
+102
en 0 canales
Get PRO
mayo '22
+39
en 0 canales
Get PRO
abril '22
+47
en 0 canales
Get PRO
marzo '22
+21
en 0 canales
Get PRO
febrero '22
+17
en 0 canales
Get PRO
enero '22
+26
en 0 canales
Get PRO
diciembre '21
+49
en 0 canales
Get PRO
noviembre '21
+26
en 0 canales
Get PRO
octubre '21
+79
en 0 canales
Get PRO
septiembre '21
+202
en 0 canales
Get PRO
agosto '21
+294
en 0 canales
Get PRO
julio '21
+438
en 0 canales
Get PRO
junio '21
+296
en 0 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
08 julio+1
07 julio+6
06 julio+3
05 julio+1
04 julio+7
03 julio+9
02 julio+5
01 julio+14
Publicaciones del Canal
፪ ✅ታውቃለህ ? ሕይወት ለሴት ሌላ ናት… ጨካኝ ናት። ስነቃ ዙሪያዬ በእርጉዝ፣ ዙሪያዬ በሰርግ፣ ዙሪያዬ በ“ቆመሽ ቀረሽ” ምክር ታጅቦአል። አንተ እንደ መጀመሪያው አፍላ ፍቅር፣ አፍላ ጭቅጭቅ፣ አፍ
፪ ✅ታውቃለህ ? ሕይወት ለሴት ሌላ ናት… ጨካኝ ናት። ስነቃ ዙሪያዬ በእርጉዝ፣ ዙሪያዬ በሰርግ፣ ዙሪያዬ በ“ቆመሽ ቀረሽ” ምክር ታጅቦአል። አንተ እንደ መጀመሪያው አፍላ ፍቅር፣ አፍላ ጭቅጭቅ፣ አፍላ መውደድ ላይ ነህ። ✅ኩርፌያዬ፣ ስጋቴ፣ ጭቅጭቄ ውስጥህ አልዘልቅም አለ። ቁም ነገር የሌለው ፍቅር፣ ያልበሰለ ፍቅር፣ ነገ የሌለው ፍቅር፤ 'አቤት እዚ ጋ ነኝ' የማይሉት ፍቅር ከወንድ በላይ ለሴት ምቾት አይሰጥም። የማይታገል ወንድ፣ ሃላፊነት የማይሸከም ወንድ፣ “እከለልበታለሁ” የማይሉትን ወንድ፣ “አለልኝ” የማይባል ወንድን ባል ማድረግ ያስፈራል። አስቴር አወቀ “ጠይም ዘለግ ያለ፣ የሰፋው ደረቱ ፍቅር ሃላፊ ነው ባረገኝ እህቱ…” እንዳለችው ነው። ፍቅር ሃላፊ እንደሆነ አስተዳደጌ ነግሮኛል ... አያያዛችን ... ✅ፍቅሩ ሲያልፍ፣ የኑሮን ቀንበር ስንሸከም፣ ሲያንገዳግደን፣ ሃላፊነት ሲወጥረን፣ ልጆች ሲመጡ ....... ጫንቃችን “አልተዘጋጀም” አልኩኝ። እንዳላጠናክርህ የምለው አይገባህም፤ እንዳታጠናክረኝ አልጠነከርክም። ልቤ እየወደደህ አልረጋ አለ… “የት ነሽ?” ስባል “እዚ ጋ” ማለት ተሳነኝ፤ ልቤ ሸሸክ… ሄድኩኝ። የተለየውህ እንደ ዋዛ አልነበረም፤ ሌት ቀን አስቤ "ያልበሰለ ሰው ፍቅር አያሻግረም ብዬ እያዘንኩኝ ነው " © Adhanom @poethaymi @poethaymi

2
፩ ✅ታውቂለሽ ..... ? ተኩሰሽ ብትገይኝ ይታረድ ስለተባለ ስቃይ እንዳይበዛብኝ ነው የተኮሰችብኝ ነው የምለው.... አንቺ ለኔ እንደህልሜ ከልቤ ጠፍተሽ አታቂም ። ሌላ ቦታ ያለዉ ቸልታዬ አንቺ ጋ
፩ ✅ታውቂለሽ ..... ? ተኩሰሽ ብትገይኝ ይታረድ ስለተባለ ስቃይ እንዳይበዛብኝ ነው የተኮሰችብኝ ነው የምለው.... አንቺ ለኔ እንደህልሜ ከልቤ ጠፍተሽ አታቂም ። ሌላ ቦታ ያለዉ ቸልታዬ አንቺ ጋ ሲደርስ አቅም አንሶት ይተጋል ተጎድቼ እምጨነቀው ጉዳቴን የምነገርሽ መንገድ ነው.... ድንገት ተለያየን እንደዋዛ ታውቂኝ የለ ስቃይን መሸከም ፣ የተሰማኝን አምእሮዬ ውስጥ ማስቀመጥ እችላለሁ .... እንዳልናፈቀ፣ እንዳልተጎዳ መሆን መንገዴ አስተምሮኝ የለ? ብንለያይም ልቤ አልተለየሽም ነበር . .... ልቤ ያላዜመሽ ያላወሳሽ ያልተረከሽ ቀን የለም ..... ✅ሲሳካልኝ ፣ስወድቅ ፣ ሲደብረኝ ፣ የልቤን ሳወራ ከትውስታ ከትዝታዬ መሀል እየወጣሁ የማወሳሽ ሚስጥሬ ነሽ ታሪኬ ነሽ .....ትዝታዬም አንቺ ግን ሶስት ወር የምታቂውን ሰው ልታገቢ ነው??! ታድለሻል .....! እኔ የዘገየሁት እራሴን እየጠረብኩ፣ እየቀረፅኩ ፣ እያበጃጀሁት ነበር፣ ...... ✅ያልመጣሁት መቀየሬን ላሳይሽ ፣ ማደጌን ላስዳስስሽ ነበር... ስደርስ ግን በሌላ መንገድ እየሄድሽ ነው.... የውነት ግን ደስተኛ ነሽ ?? ይሁን..... የኔን ግን እንዳልኩሽ ነው ✍️Adhanom Mitiku @poethaymi @poethaymi @poethaymi
118
3
አንድ ልጅ እናቱን በጣም ይጠላት ነበር። ለምን ቢባል እናቱ አንድ አይኗ የለም ነበር። "የአንድ አይን ባለቤት ልጅ" እየተባለ በትምህርት ቤት ስለሚሳለቁበት፣ እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ስትመጣበት ይሸማቀቅና ይቆጣ ነበር። "ለምንድነው እንዲህ ሆነሽ የምታሳፍሪኝ? ብትሞቺ ይሻል ነበር!" ብሎ ይጮህባት ነበር። ልጁ አድጎ፣ ተምሮና ሀብታም ሆኖ ትልቅ ከተማ ውስጥ መኖር ጀመረ። ትዳር ይዞ ልጆች ወለደ። አንድ ቀን እናቱ ልጇን ናፍቃ ልትጠይቀው ቤቱ መጣች። ልጆቹ ግን አያታቸውን አይተው ደነገጡ፤ እርሱም "ለምን መጥተሽ ልጆቼን ታስፈራሪያለሽ? ውጪልኝ!" ብሎ አባረራት። ከወራት በኋላ እናቱ መሞቷን ሰማ። ወደ ቤቷ ሲሄድ እናቱ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ትታለት ነበር፦ "ልጄ ሆይ፣ ሁልጊዜ ስላሳፈርኩህ ይቅርታ። ግን አንድ ሚስጥር ልንገርህ... ትንሽ ህፃን ሳለህ አደጋ ደርሶብህ አንድ አይንህን አጥተህ ነበር። እኔ ግን ልጄ በአንድ አይን እንዲያድግ ስላልፈለኩ፣ የራሴን አንድ አይን አውጥቼ ሰጠሁህ። ዛሬ አንተ በአይኔ እያየህ ስላለህ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ።" በአለም ላይ ትልቁ ስቃይ ለአንድ ሰው ሙሉ ህይወትህን ሰጥተህ፣ ያ ሰው ግን እንደ ውርደት ሲቆጥርህ ነው። እናትና አባት የሰጡንን ብርሃን ረስተን፣ በራሳችን ብርሃን የፈጠርን ይመስለንና ስንኮራ ነፍሳችን በቁም ትሞታለች። 📕 ርዕስ፦የተሰበሩ ክንፎች ✍🏻 ደራሲ፦ካህሊል ጂብራን 📚 @poethaymi
250
4
«በእኔ እይታ ለራሴ ታላቅ ነኝ፤ ምክንያቱም ትግሎቼን፣ መከራዬን እና መሰቃየቴን የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። እንዲሁም ሊያሸንፉኝ ቀርበው ያልተሸነፍኩላቸውን እያንዳንዱን ቅጽበት የማውቅ ብቸኛ ምስክር እ
«በእኔ እይታ ለራሴ ታላቅ ነኝ፤ ምክንያቱም ትግሎቼን፣ መከራዬን እና መሰቃየቴን የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። እንዲሁም ሊያሸንፉኝ ቀርበው ያልተሸነፍኩላቸውን እያንዳንዱን ቅጽበት የማውቅ ብቸኛ ምስክር እኔ ነኝ!።»      ፦The Gambler-ዶስቶይቭስኪ        Imagination_officially @poethaymi
321
5
ሁለት ነገሮች በምድር ላይ እጅግ በጣም ያስፈሩኛል :- ታዋቂነትና አላዋቂነት። በተለይ ታዋቂ ስትሆን (በሰዎች ፊት ከፍ እያልክ ስትሄድ) ልክ እንደ ዝንጀሮ ከስር ያለው መላጣህ ይገለጣል። በዚህ ጊዜ
ሁለት ነገሮች በምድር ላይ እጅግ በጣም ያስፈሩኛል :- ታዋቂነትና አላዋቂነት። በተለይ ታዋቂ ስትሆን (በሰዎች ፊት ከፍ እያልክ ስትሄድ) ልክ እንደ ዝንጀሮ ከስር ያለው መላጣህ ይገለጣል። በዚህ ጊዜ ሁለቱም ያላቸው ሰዎች እየበዙ ነው። እና አንድ ያላዋቂ ታዋቂ ሰው ከሰፈር ሽማግሌዎች ጋር ባልና ሚስት ለማስታረቅ ይቀመጣል። አንቺም ተይ አንተም ተው እያሉ በብዙ ልፋት ወደ ገደለው ጉዳይ ሳይገቡ ሽማግሌዎቹ እንደምንም ከአንገት በላይ ያስታርቋቸዋል። (ይሄ ከENT ሰርጀሪ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም) በመጨረሻ ያ ያላዋቂ ታዋቂ ሰው የመዝጊያ ንግግር እንዲያደርግ ይጋበዛል። እሱም ተነስቶ በመታረቃቸው የተሰማውን ደስታ ገልፆ "በሉ ይሄን የመሰለ ደስታ ብቻችንን መካፈል የለብንም፤ አንቺም ውሽማሽን አንተም ጎሮቤት ያለውን ልጅህን ይዛችሁ መደሰት አለብን" በሚል ንግግሩን ይዘጋል። 🙄 እናላችሁ አላዋቂ ታዋቂዎችን እናክማለን ገባ ገባ በሉ🤗🥰 👇👇👇 @poethaymi @poethaymi
425
6
የህይወት ወርቃማ ህግ:- መቀየር ባልቻልከው ነገር አትበሳጭ ነገሩን እንዳለ ተቀበለው። የአየሩን ሁኔታ ለመቀየር አንሞክርም ነገርግን በቀላሉ እንዳየሩ ሁኔታ እንለብሳለን። ምርጡ ወንድ 🕴 ➱ ዘወትር ሌሊት 11:30 ይነሳል ➱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደርጋል ➱ አልጋውን ያነጥፋል ➱ ቤቱን ያፀዳል ➱ በትጋት ይሰራል ➱ አልኮል ንክች አያደርግም ➱ ከኩሽና  አይጠፋም ➱ በየቀኑ ይጸልያል ➱ ያነባል ➱ ምሽት 9:00 አልጋው ላይ ያርፋል ጥያቄ:- እንደዚህ ያለ ምርጥ ወንድ የት ነው የሚገኘው? መልስ:- ማረሚያ ቤት @poethaymi
420
7
✔️የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። +++ ✔️እድሜ ጊዜ ነው። ሰው ሞተ የሚባለውኮ ጊዜው ሲያልቅ ነው። ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደግሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ሕመም አይሆንብንም? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው። የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው "ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው።" እንዴት? የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የተቀንሰ ነውና። #ሰበዝ -ገፅ 156 በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ** @poethaymi
457
8
​🎭 POCKET HISTORIES | እውቀትን በዘመናዊ መንገድ ​እውቀት ኃይል ነው። ከእለት ተዕለት ህይወትዎ አልፈው እራስዎን ለማሻሻል የሚያስፈልጉዎትን መረጃዎች በትክክለኛው ቦታ ያግኙ። 🔴 ​ቻ
​🎭 POCKET HISTORIES | እውቀትን በዘመናዊ መንገድ ​እውቀት ኃይል ነው። ከእለት ተዕለት ህይወትዎ አልፈው እራስዎን ለማሻሻል የሚያስፈልጉዎትን መረጃዎች በትክክለኛው ቦታ ያግኙ። 🔴 ​ቻናላችን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፦ 📖 የግል እድገት: ስነ-ልቦና (Dark Psychology) እና የህይወት ክህሎት። 📈 ፋይናንስ: የ Forex Trading እና የቢዝነስ ስልቶች። 🧬 ጤና እና አካል: ቁመት መጨመሪያ እና የሰውነት ግንባታ መረጃዎች። 📚 ስነ-ጽሁፍ: ያልተለመዱ ልቦለዶች እና የፍልስፍና መፅሐፍትን ጨምሮ። ​የእውቀት ባለቤት ይሁኑ። አሁኑኑ ይቀላቀሉ! https://t.me/pockethistoriess https://t.me/pockethistoriess https://t.me/pockethistoriess
247
9
መጨረሻውን አውቃለሁ .. ግን መንገዱን ወደድኩት...😊 @poethaymi
መጨረሻውን አውቃለሁ .. ግን መንገዱን ወደድኩት...😊 @poethaymi
788
10
ያስታመመ ሲቀብር ብዙ አያለቅስም @poethaymi
919
11
✅‹‹እናም በድንገት ከረጅም ጊዜ በኋላ በዚህ ሕይወት "የተሻለ ሰው" ብለን የምናስበው ነገር በጠቅላላ ጠቃሚ ነገር አለመሆኑን  እንረዳለን። ያምራሉ የተባሉትን ነገሮች በሙላ ከፍ ከፍ ማድረግ እናቆማለን። በዛ ፈንታ በጸጥታ ውስጥ ተቀምጠን መንፈሳዊ እንሆናለን።  ምንም ነገር ባለመፈለጋችን በሁሉም ነገር እረካለን።››     ―ዶ/ር አሕመድ ካሊድ ታውፊቅ @poethaymi
927
12
ሰው በውስጡ ይዞት የሚኖረው ቁስል የእድሜ ልክ ህመም ነው:: @poethaymi
ሰው በውስጡ ይዞት የሚኖረው ቁስል የእድሜ ልክ ህመም ነው:: @poethaymi
1 068
13
ልማድን መስበር ትችላለህ ፤ የመርሳት እድልህ ግን ዝቅተኛ ነው ። @poethaymi
868
14
ቀድመህ ማወቅ ያለብህ 10 እውነቶች 👌 ♻️መዝናናት ማለት መጠጣት፣ ፓርቲ ማድረግ እና ከሰው ጋር መዋል ብቻ አይደለም። መዝናናት ማለት ብቻህን የምታሳልፋት ምሽት፣ መጽሐፍ ውስጥ ሰምጦ ማንበብ፣ ጥልቅ ውይይት ማድረግ、እርምጃ መውሰድ፣ ስነ-ጥበብ መፍጠር፣ ሙዚቃ መጫወት ወይም ስራህን መስራት ሊሆን ይችላል። መዝናናት ያንተ ነው፤ ትርጉሙን የምትሰጠው አንተው ራስህ ነህ። ♻️"እምቢ" ለማለት ብዙ ማብራሪያ መስጠት እንደሌለብህ እወቅና ልማድህ አድርገው። ♻️ለግል ድንበርህ/ወሰንህ ክብር የማይሰጥና የሚቀየምህ ሰው ካለ ችግሩ የራሱ ነው። በህይወትህ ውስጥ ልታስወግዳቸው ከምትችላቸው ሸክሞች ሁሉ ትልቁ ሸክም፣ ሌሎች ሰዎች ስለአንተ ያላቸው አስተያየት ነው። ♻️ጓደኛ ታፈራለህ፤ ታጣቸዋለህም። ስህተት ትሰራለህ፤ ታርማለህም። ትወድቃለህ፣ ትከሽፋለህ፣ ትማራለህ፣ ትገነዘባለህ፣ ከእውነታው ጋር ትጋጫለህ፣ በፍቅር ትወድቃለህ፣ ትጎዳለህም። ራስህን ታጣለህ፤ በመጨረሻም ትጠነክራለህ። ♻️99% የሚሆነው ጉዳት በአዕምሮህ ውስጥ በአንተና በአስተሳሰብህ የሚፈጠር ነው። 1% የሚሆነው ጉዳት ብቻ ነው በእውነተኛው ሁኔታና በውጤቱ የሚከሰተው። ♻️የአዕምሮ ምግብህን አሻሽል። የአኗኗር ስርአትህ የምትመገበው ብቻ እንዳልሆነ ስትገነዘብ ሁሉም ነገር ይለወጣል። የአኗኗር ስርአትህ የምታየው፣ የምታነበው፣ የምትከታተላቸው ሰዎች እና አብረሃቸው ጊዜ የምታሳልፋቸው ጭምር ነው። ግብህ ጤናማ አዕምሮ እንዲኖርህ ከሆነ፣ ከአዕምሮ ምግብህ ላይ "ቆሻሻ ምግቦችን" ማስወገድ ጀምር። ♻️የምትወደውን ሰው ለመማረክ ብቻ አካላዊ ውበትህ ላይ ብዙ ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ አዕምሮአዊ ውበትህን በማሳደግ ላይ አተኩር። ራስህን አስተምር፣ ተደጋጋሚ መርዛማ አስተሳሰቦችህን ተጋፈጣቸው፣ የበታችነት ስሜትህን አስተካክል እና በራስህ ደስተኛ መሆንን ተማር። ♻️ብዙውን ጊዜ ችግሩ ራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ ስለ ችግሩ የምታስብበት መንገድ ነው። አብዛኛውን ችግሮችህን አስተሳሰብህን በማስተካከል ብቻ መፍታት ትችላለህ። ♻️ከማግባትህ በፊት፣ ስለ ገንዘብ አጠቃቀም፣ ስለ ልጅ አስተዳደግ፣ ልጆቻችሁ በምን አይነት እምነት ማደግ እንዳለባቸው፣ ስለ ልጅነት የስነ-ልቦና ጠባሳዎች፣ ስለ ወሲብ ያላችሁ ምልከታ、ስለ ገንዘብ ነክ ምልከታዎች፣ ስለ ቤተሰብ የጤና ታሪክ፣ ስለ ህልም ቤት፣ ስራና ትምህርት እንዲሁም አዕምሮአችሁ ውስጥ ስለሚመጡ ማናቸውም ነገሮች ተወያዩ። ፍቅር ብቻውን በቂ አይደለም። ልጆችህ አንተን ወላጅ በማግኘታቸው ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመፈወስ እንዳይገደዱ፣ ልጆች ከመውለድህ በፊት አንተ ከውስጥ ቁስሎችህ ተፈወስ። ♻️ራስህን ታጣለህ፤ በመጨረሻም ትጠነክራለህ። አስታውስ! እነዚህ የህይወትህ ምርጥ ዓመታት ናቸው። በነዚህ ዓመታት በመደሰት እና እነሱን በማበላሸት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት አለብህ። #ውብ #ቀን ❤ @poethaymi
983
15
....20ዎቹ ወይም 30ዎቹ እድሜ ውስጥ ነህ? ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ “ህይወቴ ዘግይታለች” የሚል ስሜት ይሰማሀል? ዙሪያህን ስትመለከት ሁሉም ሰው የህይወቱን መንገድ ያገኘ ይመስልሃል… አንዱ ቢዝነስ ከፍቷል… አንዱ ተጋብቷል… ሌላው አለምን ይዞራል… ሁሉም ደስተኛ፣ ውጤታማ፣ የተሳካላቸው ይመስሉሀል… አንተ ግን እዛው ቆመህ ራስህን “ገና ጊዜ አለኝ…” እደርስባቸዋለህ ብለህ ለማሳመን ትሞክራለህ። ግን ውስጥህ አይቀበልህም… ውስጥህ አልፎብሀል የሚል ጩሀት ያስተጋባል ..... ወንድሜ… ችግሩ ከአንተ አይደለህም። ችግሩ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርህ ነው። Social media ላይ የምታየው ሙሉ ህይወት አይደለም… ሰዎች የሚያሳዩህ ድሎቻቸውን....ስኬታቸውን ብቻ ነው… እንባቸውን፣ ውድቀታቸውን፣ ጭንቀታቸውን አያሳዩህም። በ 23 አመቱ ድርጅት የከፈተውን ወጣት ታያለህ… ከ6 ወር በኋላ መክሰሩን ግን አታይም። በ25 አመቷ አለምን ስትዞር ታያታለህ… በእዳ እንደምትኖር ግን አታውቅም። በ27 አመታቸው በደማቅ ሰርግ የተጋቡትን ጥንዶች ታያለህ… እርስ በእርስ ቀስ ብለው ያለ ጭቅጭቅ መነጋገር እንደማይችሉ ግን አታይም። ወዳጄ… አንተ ዘግይተህ አይደለህም። ህይወት ውድድር አይደለችም። 20ዎቹና 30ዎች “ሁሉን ነገር መጨረሻ” ሳይሆን ሁሉን ነገር የመጀመሪያ ፣ የመሞከሪያ ፣ የመውደቅ፣ የመነሳት ዘመን ናቸው። 20ዎቹን አልፈህ .... በ30ዎቹ መጨረሻ ስራህን ልታገኝ ትችላለህ… በ40ዎቹ ደሞ ራስህን ልታገኝ ራሰህን ልታውቅ ትችላለህ… በ50ዎቹ ፍቅር ውስጥ ልታገባ ትችላለህ… ምንም “ትክክለኛ የህይወት ሰዓት” የሚባል የለም። ላንዱ ቀድሞ የተሳካለት ላንዱ በእስተርጅናው ሊሳካለት ይችላል። ማምሻም እድሜ ነው....የማታ እንጀራ ይስጠኝ የሚባለው ፀሎት የሚፀለየው ለዚህ ነው። ስለዚህ… ዛሬ ከሌሎች ህይወት ይልቅ የራስህን ጉዞ አክብር። ቀስ ብለህ ብትሄድም እየተራመድክ ነው። ውድቀትህ መጨረሻህ አይደለም… የዛሬ ውድቀትህ ለነገ ስኬትህ ምክንያት ነው። አንተ የማትረባ ሰው አይደለህም… አንተ በሂደት ላይ ያለህ ጠንካራ ብርቱ ሰው ነህ!! ፈጣሪ ሀሳብህን በሙሉ ያሳካልህ፣አግኝቶ ከማጣት ይሰውርህ.. ሰላም አዳር🙏 @poethaymi
1 051
16
አንዳንዴ ሁሉም ነገር ይደክማል😟 @poethaymi
878
17
#ጠያቂ - መርዝ ምንድነው? #ሩሚ- ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣ ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ ጉ
#ጠያቂ - መርዝ ምንድነው? #ሩሚ- ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣ ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ ጉጉት፣ ወይንም ሌላ ማንኛውንም ነገር ሊሆን ይችላል። . #ጠያቂ - ፍርሃት ምንድነው? #ሩሚ- እርግጠኛ አለመሆንን አለመቀበል ነው። እርግጠኛ አለመሆናችንን ብንቀበል ፣ ፍርሃትገድል ይሆናል። . #ጠያቂ - ቅናት ምንድነው? #ሩሚ- የሌሎችን በጎ ነገር አለመቀበል ነው። የሌሎችን በጎነት ብንቀበል ፣ መነሳሳት ይፈጥርልናል። . #ጠያቂ - ንዴት ምንድነው? #ሩሚ - ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል ነው። ያንን ብንቀበል ትእግሥት ይሆነናል። . #ጠያቂ - ጥላቻ ምንድነው? #ሩሚ - ጥላቻ አንድን ሰው እንዳለ በሰውነቱ መቀበል አለመቻል ነው። አንድን ሰው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ብንችል ግን፣ ያ ጥላቻ ፍቅር ይሆናል። "አንድን ነገር በጥሞና እና በጥልቅ ከተረዳህ፣ በዛ ውስጥ ሁሉንም ነገር ትረዳለህ" @poethaymi
991
18
በራስ መተማመን በአንድ ጀምበር አይገነባም፤ ልክ እንደ ጡንቻ በልምምድ የሚያድግ ክህሎት ነው! ✔️ታላቁ የሥነ-ልቦና ጠቢብ ዴል ካርኔጌ "በራስ መተማመን" በተሰኘው ድንቅ መጽሐፉ ፍርሃትን አሸንፈን የስኬት ማማ ላይ የምንወጣባቸውን 3 ወርቃማ ምስጢሮች እንዲህ ያስቀምጣል፡ ✅ ፍርሃትን ፊት ለፊት መጋፈጥ፦ ፍርሃት የሚጠፋው በመሸሽ ሳይሆን ውስጥ ገብተው ሲለማመዱት ነው። ✅ በቂ ዝግጅት፦ የምታደርገውን ነገር በሚገባ ስታውቀው፣ ልብህ ሙሉ ይሆናል፤ ፍርሃትህ ይበናል! ✅ ራስህን ሁን፦ ሌላውን ለመምሰል አትጣር፤ ያንተ ትልቁ ውበትና ጥንካሬ "ራስህን መሆን" ላይ ነው። ✔️"ማንም ሰው ተደብቆ እንዲኖር አልተፈጠረም። ተለማመድ፣ ተዘጋጅ፣ ፍርሃትህን ሰብረህ ውጣ!" #በራስመተማመን #ዴል ካርኔጌ @poethaymi
860
19
በዚህ ዓለም ላይ ያለህ ዋጋ የሚለካው በምትሰጠው አገልግሎትና በምታመጣው ውጤት እንጂ በአንተ ሰብዕና ወይም በልብህ ንፅህና አይደለም። ሰዎች ጓደኛዬ ወይም ወዳጄ የሚሉህ የአንተ መኖር ለኑሯቸው ምቾት እስከሰጠ ወይም የሆነ ፍላጎታቸውን እስካሟላህ ድረስ ብቻ ነው። ልክ እንደ ባትሪ፣ ኃይልህ ሲያልቅና ጥቅም መስጠት ስታቆም ያለምንም ርህራሄ ተጥለህ በሌላ ትተካለህ። ማንም ሰው "ስለ ወደድኩህ አጠገብህ እቆያለሁ" ቢልህ አትመን፤ እውነቱ ግን "ካንተ የምፈልገው ነገር እስካለ ድረስ አጠገብህ ነኝ" የሚል ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮው ራስ ወዳድ ነው፤ የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሲል አንተን እንደ መሰላል ተጠቅሞብህ ሊሄድ ይችላል። ይህን መራራ እውነታ ተረድተህ ካልኖርክ፣ በሰዎች  ጥቅመኝነት ዘወትር እየተሰበርክ ትኖራለህ። ዓለም የምታከብረው ጠቃሚ እቃን እንጂ መልካም ሰውን አይደለም። 📕 ርዕስ፦ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ህጎች ✍️ ደራሲ፦ ሮበርት ግሪን @Bemnet_Library @poethaymi
870
20
⭐ ሰዎች አንዳንዴ ህመማቸውን መጥተው ሲነግሯችሁ በተቻለ መጠን ትሁት መሆን እና ከእነርሱ በላይ አንገት መስበር ያስፈልጋል 🤗❤️🙌🏼 ⭐ችግራቸውን ስትሰሙ እና ስታማክሯቸው ቤተመቅደስ እንደሚገባ ሰው ጫማ አውልቃችሁ የመግባት ያህል ትሁት ሁኑ!! ትሁት ሁኑ ሰው ችግሩን እና ጉዳቱን ለመናገር አመናችሁ ማለት በዙሪያው የገነባውን አጥር እና ግድግዳ አፍርሶ ነው ወደ ህይወቱ ያስገባችሁ ማለት ነው:: ጋሻ በሌለው ሰው ላይ ደግሞ ጦር አይሰበቅም !! ✍@poethaymi
871