cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ

ይህ የቴሌግራም ቻናል በኢትዮጽያ ሙሉ ወንጌል አማኛች ቤተክርያን የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ፣የሚከናወኑና የሚተገበሩ ፕሮግራምዎችን መከታተያ page ነው፡፡ this is official page of goro sefera full gospel believers church... If you have any question Contact: @Kirubel76 @pastor_sisay

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
324
Suscriptores
Sin datos24 horas
+67 días
+1630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሁለቱ ወሳኝ ጉዳዮች ቴልስ (Thales/546 B.C.) የተሰኘው ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ በአንድ ወቅት፣ “በዓለም ላይ በጣም አስቸጋሪው ነገር ምንድን ነው?” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ፣ “ራስን ማወቅ” በማለት እንደመለሰ ይነገራል፡፡ ከዚያም ጠያቂዎቹ ጥያቄውን በመገልበጥ፣ “በዓለም ላይ በጣም ቀላሉ ነገርስ ምንድን ነው?” ብለው ሲጠይቁት፣ “ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት” በማለት እንደመለሰም ይነገራል፡፡ ወደ አዲሱ አመት ለመግባት እየቀረብን ስንሄድ፣ በእነዚህ በሁለት ከባድና ቀላል በተሰኙት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንስራ፡፡ 1.  ከባዱ ነገር - ራስን ማወቅ ራእዬን፣ ፍላጎቴን፣ ዝንባሌዬን፣ የሚቀናኝንና የማይነቀኝን፣ የቤተሰብ አስተዳደጌ በእኔ ላይ ያመጣውን ተጽእኖ፣ ከሕብረተሰቡ የወረስኩትን መልካምና አጉል ተጽእኖና የመሳሰሉትን ማሰብ፣ መለየትና ተገቢውን የጥበብ እርምጃ መውሰድ በሚቀጥለው ዓመት የሚኖረኝን ስኬታማነት ይወስናል፡፡ 2.  ቀላሉ ነገር - ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት ለቅርብ ሰዎችም ሆነ በአካባቢያችን ለሚኖሩ የሕብረተሰቡ አካሎች በማያገባን ነገር ሁሉ ጥልቅ እያልን ሃሳብ ሰንዛሪዎች መሆን በመጀመሪያ በራሳችን ላይ እንዳንሰራ ትኩረታችንን የመስረቅ ጉልበት ሲኖረው፣ ሲቀጥል ደግሞ ያለንን የማሕበራዊ ግንኑነት የማበላሽት አቅም አለው፡፡ ለመደገፍና ለመፍትሄ ራስን ለማቅረብ ፈቃደኞች ባልሆንበት ጉዳይ ላይ የሩቅ ሃሳብ-ሰጪዎች እንደመሆን ቀላልና ቀላልነትንም የሚስከትል የሕይወት ዘይቤ የለም፡፡ በፊታችን ወዳለው አዲስ አመት ለመግባት ስንዘጋጅ እጅግ ቀላል የሆነውን የሃሳብ ሰንዛሪነት ልማድ ቀነስ በማድረግ ከበድ ያለውንና  እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ራስን የማወቅን ጎዳና በመጀመር በዚያ የመመራትን ልምምድ እንድትጀመሩ ላነሳሳችሁ፡፡  ራስን የማወቅ ጎዳናን ለመጀመር . . .  •  የግል ራእያችንን ለይተን እንወቅና እንከተል •  ብርቱና ደካማ ጎናችንን በመለየት በብርታታችን ላይ እንገንባ •  በልጅነታችን አመታት ያሳለፍናቸው ሁኔታዎች በእኛ ላይ ያስከተሉትን ተጽእኖዎች በሚገባ በመለየት ትክክለኛውን ምላሽ እንስጥ •  ፈጣሪ የሰጠንን ማንነት ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንቀበል ምንጭ ዶክተር ኢዮብ
Mostrar todo...
ሁለቱ ወሳኝ ጉዳዮች ቴልስ (Thales/546 B.C.) የተሰኘው ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ በአንድ ወቅት፣ “በዓለም ላይ በጣም አስቸጋሪው ነገር ምንድን ነው?” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ፣ “ራስን ማወቅ” በማለት እንደመለሰ ይነገራል፡፡ ከዚያም ጠያቂዎቹ ጥያቄውን በመገልበጥ፣ “በዓለም ላይ በጣም ቀላሉ ነገርስ ምንድን ነው?” ብለው ሲጠይቁት፣ “ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት” በማለት እንደመለሰም ይነገራል፡፡ ወደ አዲሱ አመት ለመግባት እየቀረብን ስንሄድ፣ በእነዚህ በሁለት ከባድና ቀላል በተሰኙት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንስራ፡፡ 1.  ከባዱ ነገር - ራስን ማወቅ ራእዬን፣ ፍላጎቴን፣ ዝንባሌዬን፣ የሚቀናኝንና የማይነቀኝን፣ የቤተሰብ አስተዳደጌ በእኔ ላይ ያመጣውን ተጽእኖ፣ ከሕብረተሰቡ የወረስኩትን መልካምና አጉል ተጽእኖና የመሳሰሉትን ማሰብ፣ መለየትና ተገቢውን የጥበብ እርምጃ መውሰድ በሚቀጥለው ዓመት የሚኖረኝን ስኬታማነት ይወስናል፡፡ 2.  ቀላሉ ነገር - ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት ለቅርብ ሰዎችም ሆነ በአካባቢያችን ለሚኖሩ የሕብረተሰቡ አካሎች በማያገባን ነገር ሁሉ ጥልቅ እያልን ሃሳብ ሰንዛሪዎች መሆን በመጀመሪያ በራሳችን ላይ እንዳንሰራ ትኩረታችንን የመስረቅ ጉልበት ሲኖረው፣ ሲቀጥል ደግሞ ያለንን የማሕበራዊ ግንኑነት የማበላሽት አቅም አለው፡፡ ለመደገፍና ለመፍትሄ ራስን ለማቅረብ ፈቃደኞች ባልሆንበት ጉዳይ ላይ የሩቅ ሃሳብ-ሰጪዎች እንደመሆን ቀላልና ቀላልነትንም የሚስከትል የሕይወት ዘይቤ የለም፡፡ በፊታችን ወዳለው አዲስ አመት ለመግባት ስንዘጋጅ እጅግ ቀላል የሆነውን የሃሳብ ሰንዛሪነት ልማድ ቀነስ በማድረግ ከበድ ያለውንና  እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ራስን የማወቅን ጎዳና በመጀመር በዚያ የመመራትን ልምምድ እንድትጀመሩ ላነሳሳችሁ፡፡  ራስን የማወቅ ጎዳናን ለመጀመር . . .  •  የግል ራእያችንን ለይተን እንወቅና እንከተል •  ብርቱና ደካማ ጎናችንን በመለየት በብርታታችን ላይ እንገንባ •  በልጅነታችን አመታት ያሳለፍናቸው ሁኔታዎች በእኛ ላይ ያስከተሉትን ተጽእኖዎች በሚገባ በመለየት ትክክለኛውን ምላሽ እንስጥ •  ፈጣሪ የሰጠንን ማንነት ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንቀበል ምንጭ ዶክተር ኢዮብ
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

ወደ ቤተክርስቲያን የምንሄደው ፕሮግራም ለመካፈል ሳይሆን ህይወት ለመካፈል እኛ ፕሮግራም መር ሳንሆን ህይወት መር ነን
Mostrar todo...
Mostrar todo...
2#Mamusha_Fenta /Dr/“መንፈሳዊ ግልሙትና አለ!!” “የመጪው ትውልድ ነገር በጣም ያስጨንቀኛል!” Nikodimos Show - Tigist Ejigu

የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇

https://www.facebook.com/nikodimosshow/

ፕሮግራማችንን እየተከታተላችሁ ገንቢ አስተያየታችሁን ሁል ጊዜ ስለምትለግሱን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አዳዲስ ቪዲዮ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ፡፡ This Video Clip is Dedicated Only to Nikodimos Show Channel /Tigist Ejigu/! Subscribe today for latest Videos Here:- www.youtube.com/NikodimosShow Facebook:-

https://www.facebook.com/nikodimosshow

Instagram:-

https://www.instagram.com/tigisttg/

Awtaru Kebede,Ethiopia,Ethiopian Gospel Song,Amharic Gospel © Copyright:- #Tigist Ejigu /Nikodimos Show/ 2024

ከምክንያት ወደ ውጤት! ስላላችሁበት ሁኔታ ምክንያት እየሰጣችሁ ባላችሁበት ከመርገጥ ይልቅ ለውጤት ወደመስራት አለፋችሁ እንድትሄዱ . . . 1.  በዚህ አመት የሚሰራ ስራ ካጣችሁ በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኮረን ክህሎት ያለማዳበራችሁን ጉዳይ አስቡብ፡፡ በተቃራኒው፣ መስራት የምታስቡት ነገር በዝቶባችሁ ከየትኛው እንደምትጀምሩ ግራ ከገባችሁ የትኩረት ችግር አለባችሁና እሱ ላይ ስሩ፡፡ 2.  በዚህ አመት ጊዜያችሁን የምታሳልፉበት ነገር ካጣችሁ ራእይና ዓላማ እንደሌላችሁ ጠቋሚ ነውና እሱ ላይ ስሩ፡፡ በተቃራኒው፣ የማሕበራዊው ግንኙነትና የስራው ብዛት ጊዜ ካሳጣችሁ ነገሮችን ቅደም-ተከተል የማስያዝ ብቃተችሁን አስቡበት፡፡  3.  በዚህ አመት ጓደኛ ካጣችሁና ብቸኝነት ከተሰማችሁ የባህሪያችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡ በተቃራኒው፣ ጓደኛ በዝቶ ለራሳችሁ ጊዜ እስከማጣት ድረስ ከደረሳችሁ እንደዚህ የሚያጦዛችሁ የብቸኝነት ስሜት እንዳይሆን ሁኔታውን ለማጤን ሞክሩ፡፡ 4.  በዚህ አመት ገንዘብ ካጣችሁ የሰዎችን ችግር የመፍታት ብቃታችሁን አስቡበት፤ ገንዘብ የምናገኘው ለፈታነው የሰዎች ችግር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ገንዘብ በዝቶ በምን ላይ እንደምታውሉት አጠቃቀሙን ግራ ከገባችሁ የፈጠራ ብቃታችሁ ላይ ስሩ፡፡ ዝም ብላችሁ የመጣውን እየተቀበላችሁ፣ የሚሄደውን ደግሞ እየሸኛችሁ አትኑሩ! አስቡ! ጠይቁ! መልስ እስከምታገኙ አትረፉ! ሞክሩ! ተንቀሳቀሱ ምንጭ ዶክተር ኢዮብ
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

የብርጭቆ ውኃው ነገር ሶስት አመለካከቶች አሉ፡- 1.  ግማሽ ድረስ ውኃ ያለበትን ብርጭቆ በማየት ግማሽ ሙሉ መሆኑ ላይ በማተኮር የሚያመሰግኑ፡፡ የሞላው ነገራችን ላይ በማተኮር ፈጣሪን ስናመሰግንና ለዚያ ነገር መዋጮ ያደረጉትን ሰዎች እውቅና ስንሰጥ ብሩህና የጠራ ምልከታ ስለሚኖረን የጎደለውን የመሙላት አቅም እናገኛን፡፡ 2.  ግማሽ ድረስ ውኃ ያለበትን ብርጭቆ በማየት ግማሽ ጎዶሎ መሆኑ ላይ በማተኮር የሚነጫነጩ፡፡ የጎደለው ነገራችን ላይ በማተኮር ፈጣሪን ስናማርርና ለዚያ እንደዳረጉን ያሰብናቸውን ሰዎች ስንወቅስ ያለንን ጋማሹን እንኳን መጠቀም እስከማንችል ድረስ ጨለምተኞች እንሆናለን፡፡  3.  ሙሉ ውኃ ያለው ብርጭ ቢያዩም እንኳን ድንገት አንድ ሰው ይደፋዋል ብለው የሚጨናነቁ፡፡ ሁሉ ነገር ሞልቶልን እንኳን ገና ለገና ይሆንብናል እና ይደርስብናል ብለን ስለምናስባቸው ነገሮች የመጨናነቅ ልማድ ካለን አንዱንም ነገር ሳናጣጥመው እንደፈራንና እንደሰጋን ዘመናችንን እናቃጥላለን፡፡ ዋናው ቁም ነገር ያለንና የሌን ነገር ሳይሆን ባለንም ሆነ በሌለን ነገር ላይ ያለን አመለካከት መሆኑን አትዘንጉ ምንጭ ዶክተር ኢዮብ
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

አድልዎ አታድርጉ ያዕ 2:1-7   ያዕቆብ በምዕራፍ አንድ መጨረሻ ላይ ስለ ንጹህና ነውር ስለ ሌለው አምልኮ እየተናገረ ወላጅ የሌላቸውን ልጆችና ባልቴቶችን በችግራቸው መርዳት አስፈላጊ ስለ መሆኑ አስተምሯል ይሁን እንጂ ሰወችን ከመርዳት በፊት ስለ ሰው የተስተካከለ እይታ ሊኖር ይገባል ። ጳውሎስ ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ እንዳለ ከሁሉ በፊት ክርስቶስ ሰውን እንዴት እንደሚያየውና በክርስቶስም ማን እንዳደረገው መረዳት ያስፈልጋል ። እነዚህ ቅዱሳን በየስፍራው ተበታትነው በፈተና ውስጥ እያለፉ የሚገኙ ናቸው ይሁን እንጂ በመከራ ማለፍ በራሱ ቅድስናን አያመጣም ነገር ግን እውነትን መማርና ማወቅ አርነትንና ቅድስና እንዲገለጥ ያደርጋል ። ሰውን በቀለሙ ፣ በውጫዊ ልብሱ ፣ በገንዘቡ ፣ በብሄሩ ፣ በእውቀቱ ፣ በስልጣኑ ወዘተ ... ማሰብ በመጀመሪያ ኃጢአት ነው ሲቀጥልም ይህ የዓለም እይታ እንጂ የክርስቶስ አይደለም ። ይህ የክርስቶስን አካል ምንነትን በሚገባ አለመረዳት የፈጠረው ቀውስ ሰወች በክርስቶስ ሆነው በቀለማቸው መሰባሰብን ፣ በብሄራቸውና በቋንቋቸው ህብረት ማድረግን እንደ መልካም ነገር እንዲቆጥሩት አድርጓል እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ግን የክርስቶስን አካል አይወክልም ። ችግሩ በቀለምና በቋንቋ መሰባሰብ ሳይሆን የተሰባጠረ ህዝብ ባለበት ለሌላው ስፍራ / room / ሳይኖረን ሲቀር ነው ። መጽሐፍ ቅዱስ በተለይ አዲስ ኪዳንን የጻፉት የአይሁድ ክርስቲያኖች ናቸው ይሁን እንጃ የጻፉት በራሳቸው ቋንቋ ሳይሆን በግሪክ ቋንቋ ነበር ምክንያቱም በዚያ ዘመን ሰወች በጋራ የሚናገሩት የነበረው የግሪክ ቋንቋ ስለ ነበር ነው ። ይህ ማለት በየቋንቋው መጻፉ ትክክል አይደለም ማለት ሳይሆን ሀልጊዜ የጋራ በሆነ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረግ ጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት ነው ። 1. የክርስቶስን መርህ አትጣሱ   “ ወንድሞቼ ሆይ ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ ” ያዕ 2፥1   ኢየሱስ አድልዎ የለበትም ለሰው ልጆች ካለው ፍቅር የተነሳ ለሰው ሁሉ በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎአል ። እኛ እያንዳዳችን በክርስቶስ ወንድማማቾች ነን ስለዚህ ነው ያዕቆብ ወንድሞች ሆይ የሚለው ጳውሎስ ሲናገር " ... እናንተ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጋ ፣ የእግዚአብሔርም ቤተ ሰብ አባል ናችሁ እንጂ ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም " ኤፌ 2:19 ይላል ። በክርስቶስ አድልዎ የለም ። ስለዚህ ይህንን መርህ ልንከተል ይገባል እንጂ አድልዎ በማድረግ የክርስቶስን የፍቅር ህግና መርህ  መጣል አይገባንም ። በክርስቶስ የሆነው ምንም የሌለው ወንድም ከማንም ይልቅ በእምነት ባለጠጋ በመሆኑ በክርስቶስ ጸጋ ከክርስቶስ ጋር በአብ ቀኝ መቀመጡን መዘንጋት አይገባም ። ምንም ጊዜ ከሚታየው ነገር ይልቅ የማይታየው ይበልጣል ያዕቆብ ስለዚህ ዓለም ቁስ ሲናገር " ... እንደ ሣር አበባ ይረግፋልና ።  ፀሓይ በነዲድ ሙቀቷ ወጥታ ሣሩን ታጠወልጋለችና ፤ አበባው ይረግፋል ፤ ውበቱም ይጠፋል " ያዕ 1:10 2. ለሰወች መሰናከል አትሁኑ   " የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ ፦ አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት ፥ ድሀውንም ፦ አንተስ ወደዚያ ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት ፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን ? ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን ? " ያዕ 2:3,4   በቤተክርስቲያን በክርስቶስ ያመኑ ሰወች ህብረት ስትሆን እንደ ማግኔት ሰውን ሁሉ ከየአቅጣጫው ወደዚህ ማዕከል የሚስበው የክርስቶስ ፍቅር ነው ። ክርስቶስ የሰው ልጆች ሁሉ ነው ። እኛም በዚሁ የፍቅር መንፈስ ወደ ህብረታች የሚመጡትን ሁሉ ለመቀበል የተዘጋጀን ካልሆንንና በተለያየ አስተሳሰብ ልዩነትን የምንፈጥር ከሆን ሰወችን እናሰናክላለን እኛም  ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ህብረት ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ እናደርጋለን “ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው ፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልም  ' 1ኛ ዮሐ 4:20 ሰውን በውጫዊ ልብስ ስንመዝን የኛን ግብዝነት ከማሳየቱ ሌላ በማንነቱ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ልቡን እንሰብራለን ። ሰይጣን ይህንን እንደመሳሪያ በመጠቀም ሰወች ከክርስቶስ ማለትም ከህይወት እንዲወጡ በማድረገ ይጠቀምበታል ። ሰወችን መርጠን ሰላም ስንል ሰወችን እናሰናክላለን ፣ እንጎዳቸዋለን ፣ ክርስቶስ ግን ከነ ቆሻሻችን ጠርቶ አጠበን " በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ ፣ እንዲሁም ጒድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር አልባ የሆነች ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው " ኤፌ 5:26-27 3. የዓለምን መንገድ አትከተሉ   " እናንተ ግን ድሆችን አዋረዳችሁ ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን ? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን ? የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን ? " ያዕ 2:6,7     ዓለም ሰወችን የምትመዝነው በውጫዊ ነገር ነው ፣ ዓለም ሽር ጉድ የምትለው ለክፉዎች ፣ ለሌቦች ፣ ለሚያስጨንቁ ፣ በላያቸው ለሚሰለጥኑ ፣ ኃጢአትን ለሚጨልጡ ወዘተ ... ነው ። እኛ ግን የዓለምን መንገድ እንዳንከተል ታዘናል " መልካም ፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ " ሮሜ 12:2 ጌታ ኢየሱስ ስለዚህ ዓለም ሰወች ሲናገር " ... የአሕዛብ አለቆች ተብለው የሚታሰቡት እንደሚገዟቸው ፤ ሹሞቻቸውም በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን እንደሚያሳዩ ታውቃላችሁ ፤ በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም ፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋይ ይሁን ” ማር 10:42-43 ምንጭ ወዊ ምንተሰኖት
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.