1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
“የህልም ጉልበት ለዕመርታዊ እድገት!” በሚል መሪ ቃል ለፓርቲያችን አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀናል ።
ስልጠናዉ የአመራራችንን አቅም የሚያጎለብት ሲሆን የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎት እና ልምድ በማዳበር ጠንካራ የተደራጀ ብቁ ተቋም እየገነባ ሁሉንም በእኩልነት የሚያገለግል መሪ ለመሆን እና የኢትዮዽያን የመበልፀግ ህልም ለማሳካት ጠንክሮ የሚሰራ እንዲሆን የሚያግዝ ነው።
በስልጠናው ላይ የተሳተፋችሁ የከተማችን አመራሮች በቆይታችሁ ያገኛችሁትን እውቀት እና ልምድ ህብረብሄራዊ አንድነትን በሚያጎላ መልኩ ህብረተሰባችሁን በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት አገልግሉበት።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት ዙሪያ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ከተለያዩ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ያደረጉት ውይይት::
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን
የመጀመሪያ ሩብ አመት የመቶ ቀን ግምገማችን በተለያዩ ዘርፎች ላቅ ያሉ እድገቶች መመዝገባቸውን አሳይቶናል። ይሁንና የእድገት አቅጣጫችን ከፊታችን የበለጠ ሥራ እንደሚቀረን ያመለክተናል። ስንተገብራቸው የቆየነው የተቋም እና የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ሥራዎች የእድገት ጥረታችንን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ። የሕዝብ አገልግሎቱ ዘርፍ አዲሱን የማብቃት ባሕል እንዲያሳድግ እና ሌሎችም ውጤታማ እንዲሆኑ እንዲደግፍ እጠይቃለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ ከከተማችን ነዋሪዎችና ከልማት ተነሺዎች ተወካዮች፣ ከታዋቂ ሰዎች እና ከሐይማኖት አባቶች ጋር በኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገናል።
በውይይቱ ከኮሪደር ልማት አስፈላጊነት ጋር ተያይዞ ያሉ ጥንካሬዎች፤ እጥረቶች፣ ሃሜቶች ሳይቀሩ የተለያዩ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች በዝርዝር ተነስተዋል።
እኛም ከልማት እና የህዝብን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ዉጪ ምንም ድብቅ አጀንዳ ስለሌለን ሁሉንም መረጃ እና አሰራር በዝርዝር አቅርበን ግንዛቤያቸውን የሚጨምሩ እና የመረጃ ክፍተቶችን የሚሞሉ እንዲሁም ላነሱዋቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሚሆኑ ማብራሪያዎች ሰጥተናል።
ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ በሚነሡ የተዛቡ መረጃዎች ላይም ግልፅነት ፈጥረናል። ካዋረደን የድህነት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ቆርጠን እየሰራን እና ያረጁ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ቤቶችን እየቀየርን የዜግነት ክብርን ማረጋገጥ ላይ ስለመሆናችን የግንዛቤ ችግር ባይኖርም፣ የልማት ፍላጎቱ ግን ዕለት በዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን መገንዘብ ችለናል።
የለዉጥ መንገድ አልጋ በአልጋ ስለማይሆን ጊዜያዊ ችግሮችን ተቋቁመን መሰረታዊ ለወጥ ለማምጣት በጋራ መትጋት እንዳለብን ተግባብተናል።
ከምንም በላይ የከተማችንን ነዋሪዎች ልናመስግናቸው ይገባል። አስፈላጊነቱን በመገዘብ ለልማት የሚያስፈልገውን ትብብር ሁሉ በማድረግ ከጎናችን መሆናቸውን አይተናል። እኛም ለማገልገል ቆርጠን ነው የገባንበት።
ለዚህም ለከተማችን ብልፅግና ያለ እረፍት በፍጥነት መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆናችንን ለማረጋግጥ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ ማለዳ የቢሾፍቱ የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ከከተማው አመራሮች ጋር በመሆን ገምግመናል።
የተጀመረውን ይበልጥ ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ጋር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ስራን ጎብኝተናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅድሚያ ትኩረት የሰጣቸውን 16 ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለይቶ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ የሪፎርም እና የተቋም ግንባታ ስራ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል። ከነዚህ ተቋማት መካከል የመሬት ልማት አገልግሎትን ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እንዲሁም ዲጂታላይዝ በማድረግ በኩል የጀመርነዉ ስራ ውጤታማ መሆኑን አይተናል።
በተለይም እስከ ዛሬ ድረስ የተፈጠሩ መብቶችን ወደ ዲጂታል የመቀየር፣ አዳዲስ የተፈጠሩ መብቶችን በግልፅነትና በታወቀ ውሳኔ ብቻ መብት እዲፈጠር የማድረግ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ፋይል በፎርጂድ ተደራጅቶ ሲመጣ ወደ ሲስተም እንዳይገባ የመከላከል፣ በተጭበረበረ እና በህገወጥ መንገድ መብት ፈጠራን የመለየት፣ በህገ ወጥ መንገድ መብት ቢፈጠር እንኳን በቀላሉ ውድቅ የሚሆንበት፣ ለጀርባ ማህተም ተገልጋይ የማይንገላታበት፣ የደብዳቤዎች ስወራን እንዲሁም ከሰው ማህደር ውስጥ ፋይል ማጥፋትና በህገወጥ መንገድ ፋይል የመጨመር እና ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን በሚያስቀር ደረጃ የተሟላ የዲጂታል ስራ እየተተገበረ ይገኛል።
ስለዚህ ውድ ተገልጋዮቻችን ይህ ከፍተኛ እንግልት የነበረበት አገልግሎት፣ እንግልቱ ቀንሶ ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ ካልሆነ በስተቀር በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መገልገል የምትችሉበትን ስርዓት የዘረጋን ሲሆን አገልግሎቱን በመረዳት በህጋዊ መንገድ መገልገል የምትችሉ መሆኑን እገልጻለሁ።
አገልግሎቱን ከዚህ በላይ የላቀ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሲስተሙን እኩል መጠቀም እንዲችሉ እነሱንም የማናበብ ስራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን አሁን የሊዝና የመሬት አገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ሁሉም ክፍያዎች ግለሰብ ጋር ሳይደርስ በባንክ እና ቴሌብር በኩል እንዲከፈል ማድረግ ስለተቻለ ተገልገሉበት።
ይህንን መልካም ጅማሮ ተደራሽ ለማድረግ ይበልጥ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ትላንት ማማሻዉን ለልማት የተነሱ የከተማችን ነዋሪዎች አዲስ ወደ ገቡበት አቃቂ ገላን ጉራ እና ቦሌ አራብሳ ቤቶች ሄደን ቤት ለንቦሳ ብለን ጎብኝተናቸዋል።
ከዚህ ቀደም ከነዋሪዎቻችን ጋር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ማድረጋችን ይታወሳል። በውይይት መድረኮቹ ላይ በመነጋገርና በመግባባት በጋራ ባሳለፍነው ውሳኔ መሰረት ተነሺ ነዋሪዎቻችን አዲስ የገቡባቸው አካባቢዎች ለኑሮ የሚስማማ ጥሩ አየር፣ የጋራ መጠቀሚያዎች ያላቸውና ንጹህ፣ ጽዱና ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች የተሟሉላቸዉ የመኖሪያ ቤቶች ያገኙ ሲሆን አካባቢዎቹ ለተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማትና ፋርማሲ እንዲሁምም የሸማቾች ሱቆች የተሟሉላቸው ናቸዉ።
በተጨማሪም ለእናቶች እና ወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሼዶች ከውሃ እና መብራት አቅርቦት ጭምር ተዘጋጅቷል ።
በሌላ በኩል በገላን ጉራ መኖሪያ መንደር እስከ መንደሩ ድረስ የሚዘልቀዉን መንገድ ደረጃ ወደ አስፋልት በማሻሻል የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት በፍጥነት ለመዘርጋት እየሰራን ነዉ። እንዲሁም የተማሪዎች የክፍል ጥበት በማጋጠሙ በ2 ወር የሚጠናቅ ትምህርት ቤት፣ የልጆች መጫዎቻዎች ግንባታ እና የእንጀራ ማምረቻ ማእከልም አስጀምረናል።
ማምሻውን ባካሄድነው የቤት ለንቦሳ ጉብኝት መርሃ ግብር ለነዋሪዎች ማዕድ በማጋራት እና ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማበርከት አብሮነታችንን ገልጸናል።
የምንሰራዉ ለሀገራችን ብልፅግና ሲሆን የሀገራችን ብልፅግና ደግሞ የዛሬ እና የነገዉን ትዉልድ ታሳቢ ያደረገ ነው።
ስለዚህ በፍታዊነት እንሰራለን፤ ጊዜያዊ ችግሮችን ጨከን ብለን በትብብር ሰርተን በፍጥነት እናልፋቸዋለን።
ይህ ካልሆነ ለዉጥ አይኖርም። ለዉጥ ካላመጣን ደግሞ ጉስቁልና ይቀጥላል። ትጋታችን ከልማታችን ተቋዳሽ ሳይሆን ማንም ወደኋላ እንዳይቀር ነው።
ለከተማችን ልማት በሙሉ ልባችሁ ትብብር አድርጋችሁ የከተማውን የልማት ስትራቴጂ የደገፋችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ለተዛባ መረጃዎችን ቦታ ሳትሰጡ ከጎናችን ሆናችሁ ስላበረታታችሁን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ያለኝን አክብሮት እየገለጽኩ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
17ተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ- ዓላማ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከበረ፡፡
17ተኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን፤ለሉአላዊነትነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ወ/ሮ ፋይዛ መሐመድ፣ የከተማችን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ወ/ሮ ፋይዛ መሐመድ :- የህዝባዊ አንድነታችንና የህብረ -ብሔራዊነታችን መገለጫ የሆነውን የሰንደቅ ዓላማችን ቀን ስናከብር በብልጽግናችን የጋራ መግባበት በመፍጠር ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን እና ሀገራዊ አንድነትን በማጽናት መሆን አለበት ብለዋል።
ሰንደቅ ዓላማ ከምልክትነትም ባሻገር ህልውናችን ነው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ የአሁኑ ትውልድ መንግሥት የጀመራቸውን የላቀ ሀገራዊ ትርጉም ያላቸውን ስራዎች በሚችለው በመደገፍና የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በማስቀጠል በልማቱ መስክ አዲስ የጋራ ታሪክ በመጻፍ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
04/02/2017
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በመላ ሀገሪቱ ለ17ኛ ጊዜ “ ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል ሀሳብ እየተከበረ የሚገኘውን የባንዴራ ቀን በፓናል ውይይት አከበሩ
በመድረኩም ሰለ ባንዴራ ቀን የህግ ድንጋጌዎች፣ የቀለማት ትርጉምና በባንዴራ አጠቃቀም ላይ የተመለከቱ ሀሳች በሰንድ ቀርበው ሰራኛው ውይይት በማድረግ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዝ የተሰራ ሲሆን
በአሉ ሲከበር ሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አክብራ የኖረችና ብዝሀነት መገለጫዋ መሆኑን መረዳት እና ለሀገርና ለሰንደቅ ዓላማ ያለንን እውነተኛ ክብርና ፍቅር ሁላችንም የምንገልፅበት በአል መሆኑን ማወቅና መተግበር እንደሚገባ ግንዛቤ ተይዞባታል
ጽዳት የዘመናዊነት እና የስልጣኔ መገለጫ ነው!
ይህ የምትመለከቱት ቪዲዮ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ታግዞ የሚከናወን የከተማ ጽዳት አገልግሎትን ያሳያል።
መዲናችን አዲስ አበባም እጅግ ውብ፣ ጽዱ እና ሳቢ ከተማ እየሆነች ትገኛለች።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
