1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
ክፉውን ያርቀውና ድንገት የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ምን ያደርጋሉ?
******************
ከአስፈሪ የተፈጥሮ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ርዕደ መሬት ነው፡፡ በእርግጥ በመሬት ከመከዳት በላይ ምን ሊያስፈራ ይችላል፡፡
ዓለማችን በርዕደ መሬት መለኪያ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦችን በየጊዜው ታስተናግዳለች፡፡
በእኛም ሀገር ባሳለፍነው ሳምንት እሑድ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ አካባቢ፣ በዛሬው ዕለትም ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ገደማ በአዋሽ ፈንታሌ መካከለኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፡፡
የተከሰቱት ርዕደ መሬቶች ንዝረታቸው እስከ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱ ለመሰል ክስተቶች እንግዳ የሆነውን ህዝብ ያስደነገጠውም ይመስላል፡፡
ምንም እንኳን በስምጥ ሸለቆ እና አካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ንዝረት የተለመደ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ቢናገሩም ፤ ክፉውን ያርቀው እንጂ አደጋው ቢያጋጥም ምን ማድረግ ይኖርብናል የሚሉ ጥያቄዎች ከብዙዎች ተነስተዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ ባለንበት ሥፍራ ቢከሰት ድንጋጤን ውጦ እኚህን ነገሮች ለማድረግ መሞከር የራስንም ሆነ የወዳጅን ህይወት ለመታደግ ያግዛል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ የሚሰጥ አደጋ ባለመሆኑ እራስን ለማዳን ከቦታ ቦታ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ባሉበት ቦታ ከታች ያሉትን የአደጋ መከላከያ ነጥቦች ይተግብሩ፡፡
• የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተሰማዎ አንገትዎን በሁለት እጅዎ አጥብቀው በመያዝ በጉልበትዎ ይንበርከኩ
• በቀላሉ የማይንቀሳቀሱ ጠንካራ ነገሮችን አጥብቀው ይያዙ
• እንደ ጠረጴዛ ያሉ ከላይ መከለያ ያላቸው ዕቃዎች ሥር መግባት በሚወድቅ ዕቃ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ይቀንሳል፡፡
- የሚይዙት ዕቃ እንዳይንቀሳቀስ ከጠንካራ ነገር ጋር በደምብ ያስጠጉት (ለምሳሌ ከቤት ምሰሶ ጋር)
• እንደ መስታውት ያሉ በቀላሉ ረግፈው ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ነገሮች ይራቁ
• ቤት ውስጥ ከሆኑ ሲሊንደር ጋዝ፣ የተለኮሰ ሻማ አሊያም ሌላ እሳት ሊፈጥር የሚችል ነገር ካለ ያጥፉ
• አሳንሰር ከመጠቀም ይቆጠቡ
• ወጪ ከሆኑ ኤሌክትሪክ የተሸከሙ ፖሎች፣ ዛፎች አሊያም ሌሎች የተተከሉ ነገሮች እንዳይወድቁብዎ መራቅ እና በተቻለ መጠን ሜዳማ በሆነ ግልጽ ቦታ ላይ መገኘት እራስን ከአደጋው ለመጠበቅ ያግዛሉ፡፡
Ethiopian Broadcasting Corporation
ከሁለተኛ ዙር “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!” ሰልጣኝ አመራሮች ጋር በመሆን በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች፣ በተለይም በፌደራል ፖሊስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመገኘት በተቋም ግንባታና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የተሰሩ አስደማሚ እና ዘመኑን የዋጁ ስራዎችን ጎብኝተናል።
እንደነዚህ ያሉ በቴክኖሎጂ የተደራጁ ተቋማትን መገንባት የበለጸገችና ተወዳዳሪ የሆነች ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ፣ ከተማችንን ስማርት ስቲ ለማድረግ እንዲሁም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በኩል ትልቅ አቅም የሚሆኑ ሲሆን እያበረከታችሁት ላለው አስተዋፅዖ ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ከከተማ አስተዳደር እና የፌዴራል ተቋማት የተወጣጡ የሁለተኛ ዙር "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!!" ሰልጣኝ አመራሮች በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው ።
በጉብኝታቸውም የሜክሲኮ ፣ሳር ቤት፣ ወሎ ሰፈር፣ ቦሌ እና ሌሎች በኮሊደሩ የለሙ ቦታዎችን እና የአቃቂ የግብርና ማቀነባበርያ ፣ የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ ማዕከል ፣ የልበ ብርሀን ማዕከል ፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ፣ የእንጀራ ፋብሪካዎች ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ እና መረጃ ማዕከል፣ የከተማችን የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣ እና ሌሎች የፌዴራል ተቋማትን ተመልክተዋል።
በተለይም ባለፉት ጥቂት ወራት የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የተናገሩት የጉብኝቱ ተሳታፊ አመራሮቹ ይህም ገፅታን ከመቀየሩ በተጨማሪም የህብረተሰቡን ህይወት ያቃለሉ ስለመሆናቸውም ገልፀዋል።
አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ከመሆኗም ባሻገር የብዙ ዲፕሎማቶች መዳረሻ ናት ያሉት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አሁን የተሰሩ ስራዎች ከተማዋን የሚመጥኑ ስለመሆናቸውም አንስተዋል።
በፕሮጀክቶቹ ግንባታ በሳል አመራር የታየ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ለዚህ እውን መሆን ድርሻቸው ለጎላው የከተማዋ አመራሮች ምሰጋናም አቅርበዋል።
በተጨማሪም ስልጠናው የአመራር ብቃትን እንድናዳብር እና በቀጣይ የስራ ዘመን ተሞክሮ እንድንወስድ ያደረገ ነው ያሉት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የዛሬው ጉብኝት ደግሞ ይህን በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
በመዲናዋ የታየው ፈጣን ለውጥ የአመራሩን ቁርጠኝነት እና የማህበረሰቡን ተሳትፎ የሚያሳይ ነው ያሉን አመራሮቹ ይህም በቀጣይ ስራችን ተሞክሮ እና ስንቅ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ ተናግረዋል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ የቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቶኒ ብሌር ኢንስቲቲዩት ዋና ሊቀመንበር የሆኑትን ቶኒ ብሌርን ተቀብያለሁ።
መጠነ ርዕይ ባላቸው አለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ያደረግን ሲሆን ተቋማቸው በኢትዮዽያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተም ተነጋግረናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ባለችው እመርታየአፍሪካ ምርምር እና ኢንተለጀንስ አገልግሎቶች ተቋም (IOA/አይኦኤ) የምግብ ዋስትና ካረጋገጡ ምርጥ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ መያዟን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ደቡብ አፍሪካ 94 ነጥብ 22 በመቶ የምግብ ዋስትናዋን በማረጋገጥ ቀዳሚ ሀገር ስትሆን ኢትዮጵያ 91 ነጥብ 31 በመቶ በማሳካት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ሞሮኮ፣ አልጀሪያ፣ ናይጀሪያ፣ ጋቦን፣ ርዋንዳ፣ ጋና፣ ሴኔጋል እና ናሚቢያ ደግሞ በቅደም ተከተል ደረጃ መያዛቸውም የተቋሙ ሪፖርት ያረጋግጣል።
ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ባለችው እመርታየአፍሪካ ምርምር እና ኢንተለጀንስ አገልግሎቶች ተቋም (IOA/አይኦኤ) የምግብ ዋስትና ካረጋገጡ ምርጥ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ መያዟን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ደቡብ አፍሪካ 94 ነጥብ 22 በመቶ የምግብ ዋስትናዋን በማረጋገጥ ቀዳሚ ሀገር ስትሆን ኢትዮጵያ 91 ነጥብ 31 በመቶ በማሳካት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ሞሮኮ፣ አልጀሪያ፣ ናይጀሪያ፣ ጋቦን፣ ርዋንዳ፣ ጋና፣ ሴኔጋል እና ናሚቢያ ደግሞ በቅደም ተከተል ደረጃ መያዛቸውም የተቋሙ ሪፖርት ያረጋግጣል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የ'ሴኡል ስማርት ሲቲ 2024' ምርጥ አመራር ሽልማት አሸናፊ የሆኑበት የእውቅና ስነ ስርዓት::
በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን
እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ,!
በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ የ2024 ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ ሽልማት ከ72 ሀገሮችን እና ከ115 አቻ ከተሞች አስተዳደር ከንቲባዎች መካከል ምርጥ የአመራር ሸልማት በማግኘታችን በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።
ይህ ያስመዘገብነው ውጤት በከተማችን በተሰሩ እና በህዝባችን ተሳትፎ እና ቅንጅት የተገኘ ውጤት በመሆኑ ለዚህ ወጤት መገኘት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን ሁሉ እያመሰገንኩ፣ በደቡብ ኮሪያ 2024 ሴኡል ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ የእውቅና ሸልማት ስለተበረከተልንም እናመሰግናለን።
ለህዝባችን ሰርተን በምናገኘው እውቅና ሁሉ ተመስጋኙ ሁሌም ከጎናችን በመሆን የልማቱ ዘዋሪ እና ተጠቃሚ የሆናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች መሆናችሁን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባረክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
10000000_586479193708949_7041193215104992809_n.mp4.crdownload19.97 MB
በ2ኛው ምእራፍ የኮሪደር ልማት ዙሪያ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሰጡት ማብራሪያ
Mayor Adanech Abeibei’s briefing on the 2nd round Corridor development
#AddisAbaba #AbiyAhimed #AdanechAbeibei #Corridor
AMN - መስከረም 29/2017 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የአደባባይ በዓላት በድምቀት ተከብረው እንዲጠናቀቁ አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል::
ከንቲባ አዳነች በተለይም ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በአዲስ አበባ የተከበሩት በዓላት ፍጹም ሰላማዊ፣ የተረጋጋ፣ ደማቅ፣ ህዝቡን ባከበረ እና ላቅ ባለ ዲስፒሊን በተሞላበት መንገድ ኃላፊነታቸውን የተወጡ የጸጥታ አካላትን፣ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩን አመራሮችን እንዲሁም መላው የከተማውን ህብረተሰብ አመስግነዋል::
የአደባባይ በዓላት ለከተማችን ተጨማሪ ውበት እና የቱሪስት መስህብ ናቸው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ነዋሪውን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ ከተማችን አዲስ አበባን ሰላማዊ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል::
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የአደባባይ በዓላቱ በድምቀት ተከብረው ለመጠናቀቃቸው የከተማ አስተዳደሩ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለሰራው ስራና ለተገኘው ውጤት አመስግነው ይበልጥ ውጤታማ ስለሚያደርገን በጋራ መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል::
