cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መዝሙረ ዳዊት

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ ☞ @mezmurochh ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Mostrar más
Advertising posts
42 778Suscriptores
-1124 hours
+1887 days
+73030 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
♦️ቀጥታ♦️በካራ ቆሬ ደብረ ገነት ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን

#ethiopia​ #orthodox​  #natanimtube ተዋህዶ #ethiopian​ orthodox mezmur #Tinsae​ #Fasika​ #Easter​ Ethiopia #ዘኪ​ ቲዩብ #ethiopian​ mezmur #የትንሳኤ​ መዝሙር #ከትንሳኤ​ እስከ ዳግም ትንሳኤ #Dagim​ Tinsae #ከትንሣኤ​ ስብስብ ►የትንሳኤ መዝሙሮች ስብስብ #Mezmur​ ምርጥ መዝሙር , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ►Ethiopian Easter 2021 ►Easter mezmur collection ►Yilma Hailu ►Marta Hailesilasie ►Nebiyu samuel ►Chernet Senai ►Hiwot Teferi #ፅዋ_ቲዩብ​​ #TsiwaTube​​ #newmezmur2020​​ #tewahdomezmur​ #orthodoxmezmur​​ #mahtottube​​ #omegatube​​ #aryam​​ #mihretab​​ #mehreteab​ #sibket​​ #gubae​​ #Lideta​​#Bata​​#Yohannis​​#Abuye​​#Abune​​ gebremenfes kidus#Arsema​​#Eyesus​​#silase​​#sositu​​ silasochi# #Aba​​ kiros#estinfase​​ kirstos#hana​​ mariam#abunehara​​# dingil# kidus mikael#mikael​​#melaku​​ mikael#egizhaber​​ abe#ab​​#welde​​#menfes​​ kidus#abune​​ aregawi#qirqos​​#hitsahu​​ kirqos#kidanemihret​​#enate​​#kidane​​ mihret#semaetu​​ estifanos#estifanos​​#kidus​​ gebrial#gebrial​​#melaku​​ gebrial#mariam​​#dingil​​ mariam#deginesh​​#tsiyon​​#tsige​​#soliyan​​#tsadikane​​#urael​​#kidus​​ urael#kidus​​ giorgis#giorgis​​#teklehaimanot​​#aba​​ tekilehaimanot#cherqos​​#kidus​​ qirkos#medihaniyalem​​#amilak​​#eyesus​​#hosahina​​#lemariam​​#amanual​​#bale​​ egizhabiher#yohannis​​#markos​​#ልደታ​​ #ባታ​​ #ዮሃኒስ​​ #አቡዬ​​ #አቡነ​​ ገብረመንፈስ ቅዱስ#አርሴማ​​#ቅድስት​​ አርሴማ#እየሱስ​​#ስላሴ​​#ስላሶች​​፣ሶስቱ ስላሴ#አባ​​ ኪሮስ#እስትንፋሰ​​ ክርስቶስ#ሃና​​ ማርያም#ማርያም​​#አቡነሃራ​​ ድንግል#አቡነ​​ ሐራ#ሚካኤል​​#ቅዱስ​​ ሚካኤል#መላዕኩ​​ ሚካኤል#እግዚሃብሔር​​ አብ#አብ​​#አቡነ​​ አረጋዊ#ኪዳነምህረት​​#እናቴ​​#ኪዳነ​​ ምህረት#ሰማዕቱ​​ እስቲፋኖስ#እስቲፋኖስ​​#መላዕኩ​​ ገብርኤል#ገብርኤል​​#ቅዱስ​​ ገብርኤል#ቅድስት​​ ማርያም#ድንግል​​ ማርያም፣ፂዮን#ሶልያና​​#ፃድቃኔ​​ ማርያም#ዑራኤል​​#ቅዱስ​​ ዑራኤል#መዕላኩ​​ ዑራኤል#ቅዱስ​​ ጊዎርጊስ#ጊዮርጊስ​​#ተክለ​​ ሃይማኖት#አቡነ​​ ተክለሃይማኖት#ቂርቆስ​​#ጨርቆስ​​#መድሃኒያለም​​#አማኑኤል​​#አምላክ​​#ባለእግዚሃብሔር​​#ማርቆስ​​#ዮሐንስ​​#መጥምቀ​​ ዮሐንስ #መስቀል​ አደባባይ #Abel​ Birhanu #Rama​ Tube #Rama​ Media #Rama​ tube # ll ራማ ቲዩብ Zemari Tadewos

🙏 ቅዱስ እስጢፋኖስ 🙏 • “ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ዲያቆናት አንዱ ነው ። ይህ ብቻ አይደለም ቅዱሳን ሐዋርያት አገልግሎታቸው ከቀጠለ በኋላ በክርስቶስ ምክንያት ከቤተልሔም ሕጻናት ቀጥሎ የመጀመሪያው ቅዱስ ሰማዕት ነው። ሰማዕት ማለት ትርጉሙ ምስክር ማለት ነው። ከመጨረሻው በሞት ከሚፈጸመው ምስክርነት አስቀድሞ እያንዳንዱ ክርስቲያን በቃልም ሆነ በተግባር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመሰክር ለሕይወት ተጠርቷል። ምን አልባት ሁሉም ክርስቲያን ስለ ጌታ ኢየሱስ ደሙን በማፍሰስ ሰማዕትነት ላይቀበል ይችላል የተቀደሰ የሕይወት ምስክርነት ግን ግዴታው ነው : : በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ባለ እምነት ደማቸውን በማፍሰስ ፍቅራቸውን የገለጡ ሁሉ ከሁሉ የሚበልጡ ነፍሳችን የምትወዳቸው ድንቆች ናቸው : : ክርስትና ዕድሜ ያገኘው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በርትተው ሰማዕትነት በተቀበሉ የጌታ ኢየሱስ ሙሽሮች ነው : : ከእኒህም አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን በተቀደሰ ሕይወት ከጌታ ኢየሱስ ጋር በመጣበቅ ኑሮ በመጨረሻም በሰማዕትነቱም ለጌታ ያለው ፍቅር ጥልቅ መሆኑን አሳይቷል : : የጥንቶቹ አማኞች ስለ ክርስቶስ አሰቃቂ ስደትንና ስቃይን በመጋፈጥ ቀዳሚ ሆነው አብነት ትተውልናል :: እግዚአብሔር ይመስገን ! ! ! • በክርስትና ምክንያት የሚደርሰው የመከራ ዓይነት ልዩ ልዩ ነው :: በመጋዝ መሰንጠቅ ፣ በወኅኒ መጣል ፣ በእሳት ውስጥ መንደድ ... :: በድንጋይ መወገርን ደግሞ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተቀብሏል ። ቅዱሱ በድንጋይ የሚያስወግር በደልን ባይፈጽምም በእንዲህ ሁኔታ የሚገድሉትን ይቅር ማለቱ ክርስቲያናዊ ምግባሩ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝና ተግባር ጋር ምን ያህል እንደተስማማ የሚያሳይ ውብ ነጸብራቅ [ምልክት] ነው ። እኛ ባልፈጸምነው በደል አይደለም በኃጢአታችን እንዲህ ብንሰቃይ ልባችን በይቅርታ ብርሃን የተመላ ይሆን ይሆን ?! አዎ በእውነት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ በፊት እንዳነሳነው ከተመረጠበት ዓላማ በላይ የኖረ ነው :: ኖኅ የመዳኛ መርከብን እየሠራ ሰባኪ እንደነበር ቅዱስ እስጢፋኖስም ማዕድ እያስተናገደ ግን ድንቅ ሰባኪ ነበር : : ዝቅ ያሉ ሰዎች ውስጥ ትልቅ በረከት ፥ ጥልቅ ዕውቀት አለ : : ከተመረጡት ዲያቆናት በዕድሜ ከፍ ያለው እርሱ ሊሆን ይችላል ግን የቅዱስ እስጢፋኖስ ይህ ሁሉ ክብሩ በዕድሜው ሳይሆን እስከ ሞት በደረሰ ምስክርነቱ ፣ በመንፈስ ቅዱስ በሚመራ ሕይወቱ ነው : : • ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅ ያደርግ ነበር ነገር ግን ተቃውሞ ተነሣበት ። ቅድስናና እውነተኛነትን ከዕውቀት ጋር ብንይዝም ተቃዋሚ ላለመነሳቱ ደጀን አይደለም እንደውም የመነሻ ምክንያት ነው እንጂ : : የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ክስረት አልነበረም ለእርሱ አክሊልን ሲያገኝበት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በነፋስ እየተበተነ ስፍራን ሁሉ እንደሚያነድ የብዙ የእሳት ፍንጣሪ ሆነች ። አንድ ክርስቲያን በደረሰበት ሁሉ ስፍራን በክርስቶስ እምነት የሚያበራ የእሳት ጉማጅ ነው : : ተቃውሞን ሰው ለመቀነስ ይነሳበታል እግዚአብሔር ደግሞ ለመብዛት ያደርገዋል :: የሆነው ሁሉ መነሻ ደግሞ የሀሰት ክስ ነው የሀሰት ክስ ዛሬ የጀመረ አይደለም በጌታ አንድ የተባለና በደቀ መዛሙርቱ ሁሉ የቀጠለ እንጂ ። ሰይጣን ምንጊዜም በማሳበል ነው የሚሠራው የሥላሴ መንግሥት ደግሞ በእውነት ፥ ሰማዕታት የዚህ እውነት ድምፆች ናቸው : : • እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ ተሞላ በዚህም የእስራኤልን ታሪክ በዝርዝር በመግለጥና እግዚአብሔር ለተመረጡት ሕዝቦቹ የሰጣቸውን በረከቶች በመዘርዘር ለክሱ መንፈሳዊ ምላሽ ሰጥቷል ። እኛ መንፈሳዊውን ነገር በሥጋ እንዳንዋጋ መንፈስ ቅዱስ እያስተማረን ነው : : በቅዱስ እስጢፋኖስ ትምህርት ውስጥ የጌታ ቸርነትና ምሕረት ቢበዛላቸውም እስራኤላውያን ግን የማይታዘዙና አንገተ ደንዳና እንደሆኑ አብራርቷል። ወገኖቼ ዛሬ አለመታዘዝና ለእግዚአብሔር ፍቅር ምቹ አለመሆን በእኔና በእናንተ ሕይወት ውስጥም አለ : : ውጤቱ የሕይወት ጌታ ኢየሱስን መግፋት ስለሆነ መመለስ ይገባናል : : ውኃና የሕይወት ስህተት እያሳሳቀ ወስዶ ከማይወጣበት አዘቅት ውስጥ የሚጨምር ነውና መጠንቀቅ ይገባል : : • ቅዱስ እስጢፋኖስ ከላይ እንደ ገለጽነው መንፈሳዊ መከላከያውን ሲያጠናቅቅ የቀጠለው ቀና ነገር ቀና ብሎ ወደ ላይ በተመለከተ ጊዜ በራዕይ ጌታ ኢየሱስን በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ ማየቱ ነው ። ሕይወትን በኃይል የሚመላት ወደ እግዚአብሔር ቀና ማለት ነው ፥ ስብከትንም ለሰባኪና ተሰባኪ ውጤት እንዲያመጣ የሚያደርገው ቀና ማለት ነው ። በዘመናት ሁሉ የክርስቶስ ምስክሮች ድልን የተጎናጸፉበት ምክንያት ወደ ጌታ ኢየሱስ ማየታቸው ነው : : አንድ ሰማዕት በመስቀል ላይ ሰቅለውት እንደገና በስሩ እሳት ያነዱበታል ታዲያ ይህ ምስክር ድንገት ፍልቅልቅ ብሎ በደስታ ሳቀ ። በዚህ ጊዜ የሚያሰቃዩት “ መከራው አልጠቀምህ ብሎ ነው የምትስቀው ?” አሉት ፥ እሱም “ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን በዕለተ ዐርብ መልኩ በሰማዩ ደመና ላይ አይቼው ነው ” አለና በክብር ሰማዕትነቱን ፈጸመ ::ወገኖቼ የክርስትና ክብሩ ክርስቶስ ቀና ብሎ እያዩ በመኖር ውስጥ ያለ ነው : : • ሰማይ ተከፍቶ በእግዚአብሔር ቀኝ ጌታ ኢየሱስን ማየቱን በተናገረ ጊዜ ጌታ ኢየሱስን “መሲሕ ወይም የእግዚአብሔር ልጅ ነው” ብለው ያላመኑ አይሁዶች ትልቅ ስድብን እንደመናገር ቆጠሩት ። እነሱ ባይቀበሉትም እውነት ከእውነትነቱ አይለወጥም እውነት እውነት የሚሆነው በእኛ መቀበል አይደለም እኛ ብንቀበለው እውነታውያን እንሆናለን እንጂ የምንጨምረው ነገር የለም : : ይህ ራዕይ ከቃሉ ጋር ተዳምሮ ሕዝቡ እስጢፋኖስን በድንጋይ ለመውገር እንዲፈጥኑ አደረጋቸው : : ሁሉም ሰው እኛ ያየነውን ጌታ ኢየሱስን ላያይ ይችላል ። እርሱን ያላዩ አቅማቸውና መገለጫቸው ወጋሪነትና ከሳሽነት ብቻ ነው ። ወገኖቼ የቅዱስ እስጢፋኖስ ልጆች አዲስ ነገር እንደሆነባችሁ አታድንቁ ይህ ነገር ጠባዩ ነውና : : • ቅዱስ እስጢፋኖስ በአሰቃቂ ሁኔታ በድንጋይ እየተወገረ ሳለ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” ሲል የመጨረሻ ቃሉን አሰማ : : ጌታ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተናገረውን ቃል የሚያስተጋባ ድምፅ ነበረ ። ከዚህ ቃል በኋላ እስጢፋኖስ በጌታ አንቀላፋ ። እግዚአብሔር በእኛ ላይ ማየት የሚፈልገው የሕይወት መልክና መስማት የሚሻው ቃል እንደ ልጁ የሆነውን ነው : : ° ዘንባባው የድል ምልክት ፣ ድንጋዩ የተወገረበት ፣ መጽሐፍ ደግሞ የሰባኪነቱ ምልክት እንዲሆን ዘንባባ ድንጋይ መጽሐፍ ይዞ ይሳላል : : ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋ ተወግሮ በሰማዕትነት አንቀላፋ ፥ እኛንም ለክርስቶስ ምስክር መሆነን አደፋፈረን ። ቅዱስ ጊዮርጊስም ነገሥታትን የመቃወም መምህራችን ነው ። ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ለእውነት አለመመለስን ያስተማረን ነው ። የሕይወት ምስክርነት በቀጥታ መስማት ትወዳላችሁ ? ገድለ ሰማዕታትን ስሙ ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት ይባርከን ! ! ! ለመቀላቀል   👇       ┏━━° •❈• ° ━━┓     💚 @mezmurochh 💚     💛 @mezmurochh 💛     ❤ @mezmurochh ♥       ┗━━° •❈• ° ━━┛
Mostrar todo...
እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።             ሐዋ 7 ÷ 56 ለ ቀዳሚ ሰማዕት ለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወርሀዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሳቹ ። ቅዱስ አስጢፋኖስ ከችግራቹ ከበሽታቹ ከህመማቹ አውጥቶ በእለተ ቀኑ መልካምን ያሰማቹ መልካሙን ይስጣቹ መልካሙን ያርግላቹ ከክፋት በስተቀር የልባችሁን መሻት ይፈፅምላቹ አለው ይበላቹ 🙏 መልካም እለተ ሐሙስ።
Mostrar todo...
❤️
😍
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔      ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሀይሉ          ሥላሴን ከሰማይ   ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥               |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:             💚@mezmurochh💚                💛@mezmurochh💛                ❤@mezmurochh❤                  |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|: ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Mostrar todo...
ሥላሴን ከሰማይ ሥላሴን ከሰማይ እስጢፋኖስ አይቶ ዓይኑ በመገረም ቀረ ተሰክቶ የድንጋዩ ናዳ ቢወርድበት እንኳ ሥላሴን በማየት እረስቶታል ለካ    ስብሐት ለእግዚአብሔር የሰው ልጅ በቀኙ ተቀምጦ ነበር እስጢፋኖስ ሲያየው በሚያስፈራ ክብር ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን ከበውት ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ስብሐት ስብሐት    ስብሐት ለእግዚአብሔር ምሥጢረ ሥጋዌ ተገልጾለት በአካል ሥጋው ቢታመምም ሐዘኑን ሽሮታል ነፍሱ ከጸባኦት ስታመሰጥር ድንጋይ ይለቅማሉ ያልታደሉ በምድር    ስብሐት ለእግዚአብሔር ለፈሪሳውያን ተሰውሮባቸው የሥላሴ ምሥጢር ድንጋይ ሰበሰቡ ጻድቁን ለመውገር እርሱ ግን ከሰማይ ፈጣሪውን አይቶ ድንጋዩን እረሳው ህሊናው ተነክቶ    ስብሐት ለእግዚአብሔር የሰማዩ ሥርዓት ልዩ ስለነበር ምንም አልመሰለው የድንጋዩ ክምር የፍጥረታ ሁሉ ፈጣሪ ተገልጠው ስቃዩን አስረሱት ህሊናውን ፍቀው    ስብሐት ለእግዚአብሔር ልባችሁ ጆሮአችሁ መቼ ተገረዘ የጠነከረ ነው ለአምላክ ያልታዘዘ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ እንደገዛ ፍቃድ እየተመራችሁ    ስብሐት ለእግዚአብሔር ሥላሴን ከሰማይ እስጢፋኖስ አይቶ አይኑ በመገረም ቀረ ተሰክቶ የድንጋይ ናዳ ቢወርድበት እንኳ ሥላሴን በማየት እረስቶታል ለካ    ስብሐት ለእግዚአብሔር                 መዝሙር     ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥    ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮    ✥     💚 @mezmurochh 💚    ✥    ✥     💛 @mezmurochh 💛    ✥    ✥     ❤ @mezmurochh ❤    ✥    ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Mostrar todo...
💚💛❤️ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን እንወቅ💚💛❤️
Mostrar todo...
❤️ ትምህርቶች ❤️
❤️ ኦርቶዶክስ ❤️
❤️ ስብከቶሽ ❤️
💛 ስንክሳር 💛
💚 መዝሙራት 💚
💚 ምክረ አበው 💚
💚 እኚህንና የተለያዩ መንፈሳዊ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን💚
💚💛❤️ ይቀቀላቀሉን 💚💛❤️
Mostrar todo...
🎤ድምፀ ተዋህዶ💒
📚ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት📚
የክርስትና ስም ለምን ያስፈልጋል⁉️
የመጀመሪያው ነብይ ማነው⁉️
የመጨረሻው ነብይ ማነው⁉️
📖የሁሉም መልስ እዚህ ይገኛሉ📖