cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethio Legal Hub

እንኳን ወደ Ethio Legal Hub በሰላም መጣችሁ። በዚህ ቻናል ጠቃሚ የህግ ፅሁፎች፣ አዋጆች፣ መመሪያዎች፣ደንቦች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ታገኛላችሁ። የቻናላችን ቤተሰብ በመሆን ይከታተሉን፡፡ሌሎችንም ወደ ቻናሉ በመጋበዝ ስለ ህግ ይወቁ! ለ ጥያቄ እና አስተያየት Contact us @https://t.me/the_Legalhub @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 918
Suscriptores
Sin datos24 horas
+47 días
+630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ቁም ኑዛዜ ስጦታ ========== ሟች ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆች ወይም ወራሾች ቢኖሩትና ከነዚያ መካከል ለአንደኛው የኑዛዜ ስጦታ ቢያደርግ የሌሎችን ወራሾች ከሟች ውርስ መነቀል አያስከትልም፡፡ ይህንንም የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 913 የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሀሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት አንድ ድርሻ ወይም አንድ ንብረት ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ ከአንቀጽ 1117 ጀምሮ ያሉት ድንጋጌዎች አግባብነት አላቸው አንቀጽ 1117 አባትና እናት ወይም ሌሎች ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ለልጆቻቸው እና ሌሎች ተወላጆች ሀብታቸውን ለመስጠትና ለማከፋፈል እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ ይህ ክፍፍል ሥርዓት አንድን ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 1123 ተደንግጓል፡፡ አንቀጽ 1123/1/ ሲነበብ “በስጦታ አከፋፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር ወደታች ከሚቆጠሩ ተወላጆች አንዱ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላል” ሰ/መ/ቁ 32337 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 882፣ 913፣ 2428፣ 2443 ©️Lawyer_Henok_Taye ======= Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
የሰራተኛ ደመወዝ ቅነሳ ======== የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 53 እና ተከታዮቹን ድንጋጌ ስንመለከት ደመወዝ አንድ ሰራተኛ በስራ ውሉ መሰረት ለሚያከናውነው ስራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ሲሆን አሰሪው ለሰራተኛው የሚከፍለው የትርፍ ሰአት ክፍያ፣ የተለያዩ አበሎች፣ ጉርሻ( ቦነስ)፣ ኮሚሽን፣ የማትጊያ ክፍያዎች እና ከደንበኛ የሚሰበሰቡ የአገልግሎት ክፍያዎች እንደ ደመወዝ እንደማይቆጠሩ ይደነግጋል፡፡ የሰራተኛ ደመወዝ በምን አግባብ መቀነስ ይቻላል የሚለውን በአዋጁ አንቀፅ 59 ስር የተቀመጠ ሲሆን ይህም በህግ፣ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ ደንብ በተወሰነ ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ካልሆነ ወይም ሰራተኛው በፅሁፍ ካልተስማማ በስተቀር አሰሪው ከሰራተኛው ደመወዝ ሊቀንስ እንደማይችል ወይም በእዳ ሊይዝ ወይም ሊያቻችል አይችልም በማለት በግልፅ የሚደነግግ በመሆኑ ይህንን በመተላለፍ የሚደረጉ የደመወዝ ቅነሳዎች ህግን መሰረት ያደረጉ አይደሉም፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 59666 ላይ ከደመወዝም በተጨማሪ አሰሪ ለሰራተኛው ለትምህርት ቤት የከፈልኩት ክፍያ ነው በማለት ሰራተኛው ስራ በሚለቅበት ጊዜ ከሚያገኘው የአገልግሎት ካሳም ላይ ቢሆን እንኳን አሰሪ በራሱ ውሳኔ ሊቀንስ ወይም ሊይዝ ወይም ለእዳ እንዲቻቻል ማድረግ እንደማይችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ አሰሪው ከሰራተኛ እዳ እንዳለበት ካመነ እዳውን ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ማስመለስ ይችላል እንጂ ሰራተኛው ሳይፈቅድ በራሱ ተነሳሽነት የሰራተኛውን ደመወዝ ወይም ሌሎች ጥቅሞቹን መቁረጥ አይችልም፡፡ በተጨማሪነትም በሰራተኛው ፈቃድ፣ በህብረት ስምምነት፣ በስራ ደንብ ወይም በህግ በተቀመጠው አግባብ የሚቀነሰውን የደመወዝ መጠን በተመለከተ በአዋጁ አንቀፅ 59(2) ላይ የተገለፀ ሲሆን ሰራተኛው በፅሁፍ ስምምነቱን ካልገለፀ በቀር በአንድ ጊዜ ከሰራተኛው ደመወዝ ላይ በአጠቃላይ ሊቆረጥ የሚችለው የገንዘብ መጠን በምንም አኳኃን ከወር ደመወዙ አንድ ሶስተኛ( 1/3) መብለጥ እንዳሌለበት አስገዳጅ ህግ ተቀምጧል፡፡ በመሆኑም አሰሪዎች ከሰራተኛው ላይ ደመወዝ ሲቀንሱ ወይም ሲቆርጡ ይህንኑ ታሳቢ ማድረግ አለባቸው። ======= Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
3👏 1😱 1
በጋብቻ ወቅት የተቀላቀሉ የግል ንብረቶችን በተመለከተ (የሰበር መ/ቁ 231592) በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 እንዲሁም በአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/1995 ድንጋጌዎች ይዘት ማየት እንደሚቻለው ባል እና ሚስት የንብረት ግንኙነታቸው አስመልከተው የጋብቻ ውል ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ከተጋቡ በኃላ አንዱ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ የሚያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሸጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ሀብቱ የሚሆን ሲሆን ይህ ግን የሚሆነው የግል ይባልልኝ ብሎ አንደኛው ወገን ጥያቄ አቅርቦ ፍ/ቤት(የፍትህ አካል) ሲያፀድቀው ነው፡፡ በመሆኑም ተጋቢዎች ስለ ንብረቱ ስምምነት ከሌላቸው እና ንብረቱ የግል ይባልልኝ ተብሎ በፍ/ቤት ካልፀደቀ ገዢ የሚሆነው የቤተሰብ ህጉ በመሆኑ የግል ንብረት ተሸጦ ወይም ተለውጦ የሚገኘው ንብረት የጋራ ንብረት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ መጋቢት 28 ቀን 2015ዓ.ም፡ ======= Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
👍 2
የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የስጦታ ውል ፎርም (የሰበር መ/ቁ 222326) ============ የስጦታ ውል አዋዋይ ፊት የተደረገ እና ተረጋግጦ የተመዘገበ ከሆነ በልዩ ሁኔታ ፍርድቤቱ በበቂ ምክንያት እንዲስተባበል ካልፈቀደ በስተቀር ውሉ ሙሉ እምነት የሚጣልበት ነው፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ሲተላለፍ ውሉ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር ካልተደረገ ፈራሽ እንደሚሆን በፍ/ህ/ቁ 2443 ስር በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ግልፅ ኑዛዜን በተመለከተ የፍ/ህ/ቁ 881 እና ተከታዮቹ ላይ እንደተቀመጠው በፅሁፍ መደረግ እንዳለበት፣ ኑዛዜ አድራጊው እና ምስክሮች ባሉበት መነበብ እንዳለበት እንዲሁም በፊርማ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን ይህንን ያላሟላ ኑዛዜም ሆነ የስጦታ ውል ፈራሽ እንደሆነ ህጉ ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን በሠ/መ/ቁ 193067 ላይ በተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ኑዛዜው ወይም የስጦታ ውል በህግ ስልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት የተደረገ እንደሆነ ኑዛዜው ወይም የስጦታ ውሉ በኑዛዜ/ስጦታ አድራጊው እና ምስክሮች ፊት መነበብ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይሀው የማንበብ ስርአት ስለመፈፀሙ በሰነዱ ላይ በግልፅ ባይፃፍም ኑዛዜው ወይም ስጦታ ውሉ ህጋዊ ውጤት ሊኖረው ይገባል በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የስጦታ ውሉ ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት የተደረገ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በስጦታ ውሉ ላይ ሁለት ምስክሮች ከፈረሙ በቂ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 882 ላይ ተደንግጎ እያለ በስጦታ ውል ሰነዱ ላይ አራት ምስክሮች አልፈረሙም በሚል ፈራሽ ሊሆን አይገባም ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ======= Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
👍 2
የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የስጦታ ውል ፎርም (የሰበር መ/ቁ 222326) ======= የስጦታ ውል አዋዋይ ፊት የተደረገ እና ተረጋግጦ የተመዘገበ ከሆነ በልዩ ሁኔታ ፍርድቤቱ በበቂ ምክንያት እንዲስተባበል ካልፈቀደ በስተቀር ውሉ ሙሉ እምነት የሚጣልበት ነው፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ሲተላለፍ ውሉ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር ካልተደረገ ፈራሽ እንደሚሆን በፍ/ህ/ቁ 2443 ስር በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ግልፅ ኑዛዜን በተመለከተ የፍ/ህ/ቁ 881 እና ተከታዮቹ ላይ እንደተቀመጠው በፅሁፍ መደረግ እንዳለበት፣ ኑዛዜ አድራጊው እና ምስክሮች ባሉበት መነበብ እንዳለበት እንዲሁም በፊርማ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን ይህንን ያላሟላ ኑዛዜም ሆነ የስጦታ ውል ፈራሽ እንደሆነ ህጉ ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን በሠ/መ/ቁ 193067 ላይ በተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ኑዛዜው ወይም የስጦታ ውል በህግ ስልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት የተደረገ እንደሆነ ኑዛዜው ወይም የስጦታ ውሉ በኑዛዜ/ስጦታ አድራጊው እና ምስክሮች ፊት መነበብ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይሀው የማንበብ ስርአት ስለመፈፀሙ በሰነዱ ላይ በግልፅ ባይፃፍም ኑዛዜው ወይም ስጦታ ውሉ ህጋዊ ውጤት ሊኖረው ይገባል በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የስጦታ ውሉ ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት የተደረገ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በስጦታ ውሉ ላይ ሁለት ምስክሮች ከፈረሙ በቂ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 882 ላይ ተደንግጎ እያለ በስጦታ ውል ሰነዱ ላይ አራት ምስክሮች አልፈረሙም በሚል ፈራሽ ሊሆን አይገባም ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ===== join our 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W
Mostrar todo...
photo1717412877 (1).jpg0.58 KB
ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። ምንጭ:- ethiopiainsider.com
Mostrar todo...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
ችሎት መድፈር (የሰበር መ/ቁ 48237) ተከራካሪ ወገን ገና መዝገቡ እልባት አግኝቶ ሳይዘጋ በምርመራ ሂደት ላይ እያለ  ጉዳዩ አልቋል፣ አስጨርሼዋለሁ፣ የተፈረደላችሁን ገንዘብ አታገኙም፣ ጉዳዩን ለማስጨረስ ከዳኞች ጋር ተነጋግሬ ገንዘብ ከፍያለሁ እያለ ማስወራቱን በሚገባ በማስረጃ የተረጋገጠ እንደሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 480 መሰረት ጉዳዩን የሚከታተለው ችሎት ድርጊቱ የዳኝነትን ክብር፣ የዳኝነት አስተዳደርን የሚነካ እና ህብረተሰቡ በፍ/ቤት ላይ እምነት እንዳይኖረው ስለሚያደርግ በተያዘው መዘገብ ወዲያውኑ በቀጥታ የጥፋተኝነትና የገንዘብ መቀጮ እንዲደረግ ውሳኔ መስጠት ይችላል፡፡ ===== Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
👍 8 1
ጣልቃገብ እና የመቃወም አመልካቾች ✍️✍️✍️ ====================== ከሳሽ እና ተከሳሽ በሚከራከሩበት ክርክር/ክስ/ መብት እና ጥቅማቸው የሚነካባቸው ቢሆንም ክሱ ውስጥ ያልተካተቱ ወይም ያልተጠሩ ግለሰቦች በህጉ መሰረት ወደ ክርክር ገብተው መብት እና ጥቅማቸውን የሚያስከብሩበት የህግ ስርአት ተቀምጧል፡፡ 1. ሶስተኛ ወገን ጣልቃገብ (የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 41 እና 43) በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል ያለው ክርክር ያገባኛል መብቴን እና ጥቅሜን ይነካል የሚል የክርክሩ አካል ያልሆነ ሶስተኛ ወገን በራሱ ተነሳሽነት ፍርድ ወይም ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 41 መሰረት ጉዳዩን ለሚያየው ፍ/ቤት ጣልቃ ገብቼ ልከራከር ይገባል በማለት ከማስረጃ ጋር አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ አቤቱታ አቅራቢው ሌሎች ሰዎች በሚከራከሩበት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በቀጥታ መብቱን እና ጥቅሙን የሚነካ መሆኑን ይህም አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን ማስረዳት መቻል አለበት፡፡ በሌላ በኩል ከሳሽ ላቀረበብኝ ክስ ኃላፊነት ያለበት ወይም ኃላፊነቱን የሚጋራ በክሱ ውስጥ ያልተካተተ ሶስተኛ ወገን ወደ ክሱ ሊካተት ይገባል የሚል ተከሳሽ ይህ መሆኑን በማስረጃ በማስደገፍ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 43 መሰረት አቤቱታ በማቅረብ ሶስተኛ ወገን ወደ ክርክሩ ገብቶ እንዲከራከር ማድረግ ይቻላል፡: 2. የመቃወም አመልካች/ፍርድ ላይ የሚቀርብ ተቃውሞ/ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 ባለጉዳዩ ስለ ክርክሩ የማያውቅ በከሳሽም እና በተከሳሽ በኩል ያልተጠራ፣ የክርክሩ አካል ያልነበረ፣ ስለ ክሱ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ፍርድ መሰጠቱን የማያውቅ እንደሆነ ነገር ግን ፍ/ቤት ጉዳዩን አከራክሮ ፍርድ በሰጠበት ጉዳይ መብቱ እና ጥቅሙ የተነካበት ግለሰብ በውሳኔው መብቴ ስለተነካ ፍርዱ ቀሪ እንዲሆን በማለት የመቃወም አመልካች ሆኖ ወደ ክርክሩ ለመግባት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነው ፍርዱ በሌላ ፍ/ቤት ያልተሻረ እንደሆነ ወይም እንደ ፍርዱ ያልተፈፀመ ከሆነ የመቃወም አመልካች በመሆን የክርክሩ አካል ባልሆንም በውሳኔው መብቴ ተነክቷል በማለት ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ ወደ ክርክር ገብቼ ልከራከር በሚል አቤቱታ ሲያቀርብ ነው፡፡ ፍ/ቤትም በትክክል መብቱ መናካቱን በማስረጃ ካረጋገጠ በኃላ የሰጠውን ውሳኔ በመተው አመልካችን ወደ ክርክሩ ጣልቃ በማስገባት የሚያከራከርበት የህግ ስርአት ነው፡፡ የመቃወም አቤቱታ ተቀብሎ የማየት እና የቀደመውን ውሳኔ መለወጥ የሚችለው ፍርዱን የሰጠው ፍ/ቤት ነው፡፡ 3. ንብረት እንዳይያዝ ወይም እንዳይከበር የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ (የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 418) ፍርድ ተሰጥቶ ጉዳዩ አፈፃፀም ላይ ደርሶ ለፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲሆን የተያዘ ወይም የተከበረ ንብረት የፍርድ ባለእዳ ንብረት አይደለም የራሴ ንብረት ነው የሚል ወገን ወይም የቅድሚያ መብት አለኝ የሚል ወገን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 418 መሰረት ለአፈፃፀም ችሎቱ የሚያቀርበው የመቃወም አቤቱታ ነው፡፡ አቤቱታ አቅራቢው በዋናው ፍርድ ላይ ምንም አይነት ክርክር የሌለው እና በፍርዱ መብቱ ያልተነካ፣ ንብረቱም የክርክር አካል ያልነበረ ነገር ግን አፈፃፀም እንዲቀጥል ትዕዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም ከላይ በተጠቀሰው የህግ አግባብ የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገን ነገር ግን በአንድም ይሁን በሌላም መልኩ የፍ/ቤቱ ውሳኔም ሆነ ትዕዛዝ መብት እና ጥቅሙን የሚነካበት እንደሆነ ወደ ክርክሩ ለመግባት አቤቱታ አቅርቦ በመግባት መብት እና ጥቅሙን ማስከበር ይችላል፡፡ ======= Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
👍 5 1🙏 1
የኮንዶሚንየም ቤት ሽያጭ ውል /የሰበር መ/ቁ 158899/ ============== የኮንዶሚንየም ቤት የደረሰው ሰው ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ሊያስተላልፍ የሚችለው ቤቱን ከገዛ በ5 አመት ሲሞላው ብቻ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 19/97 ላይ የተቀመጠ ሲሆን ይህ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው እጣው ከወጣ በኃላ ነው ወይስ እጣውን ተከትሎ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጋር ውል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚለው ሲያከራክር የነበረ ሲሆን በአዋጁ ላይ በግልፅ ባይቀመጥም ከጠቅላላ ድንጋጌዎቹ ይዘት የምንረዳው የኮንዶሚንየም ቤት እጣ ከከተማው አስተዳደር ጋር የቤት ግዢ ውል ለማድረግ መብት የሚሰጥ እንጂ እራሱ የቤት ግዢ ውል አይደለም፡፡ ስለዚህም የኮንዲሚንየሙ ባለቤት ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለው ቤቱን በገዛ 5 አመት ሲሞላው ነው የሚለው ጊዜ የሚቆጠረው እጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን የሚቆጠረው የቤት ሽያጭ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ======= Join us👇👇 https://t.me/ET_Legalhub join our discussion group👇👇 https://t.me/the_Legalhub 👉Facebook👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556230857972 👉 Tiktok 👇 https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/ --------------- ለበለጠ፡ contact us @Lawyer_eleni @Lawyer_elsa @Lawyer_hawi
Mostrar todo...
6👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
🙏 2