cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዝማሬዎች

ማንኛውንም ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬዎችን በዚህ ግሩፕ ማግኘት ይችላሉ እንዲሁም ወቅታዊ አዳዲስ ዝማሬዎችን ጨምሮ የምትፈልጉት ዝማሬ ይጠይቁን.....ማንኛውም ሰው ወደ ግሩፑ ሲገባ....20 ሰው Add እንዲያደርግ በ እእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ፡፡+

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
569
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል። #ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና። #ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ። #ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል። #ምልጃሽ #ኢትዮጵያን #ይታደግ። ለአለም ምህረት ይሁን ። #Memhr_Abunu_Mamo
Mostrar todo...
«ወንድምህን አትናቀው» ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል። "እንዴት?" ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የከደርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @beteafework @beteafework @beteafework @beteafework @beteafework @beteafework
Mostrar todo...
#ምጽዋት በአበው አንደበት "አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው።" #ቅዱስ_ባስልዮስ "አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ "ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ "ወንድምህ ዕርቃኑን ወድቆ እያለቀሰ ነው ፣ አንተ ግን የሚያምር የወለል ንጣፍ ለመምረጥ ተቸግረህ ቆመሃል።" #ቅዱስ_አምብሮስ "አባት ሆይ ወጪውን ሳናሰላ እንድንመጸውት አስተምረን።" #ቅዱስ_አግናጥዮስ
Mostrar todo...
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል? "ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡ እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው? አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
Mostrar todo...
ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ? ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል ጅራፍ በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል ችቦ ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ሙልሙል በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡ ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው @Menfesawitarikochachn @Menfesawitarikochachn
Mostrar todo...
ቀን ያስጎነብሳል.mp38.19 MB
#ከንስሐ_ርቀን_ይቅርታን_አናገኝም ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት፡፡ ይህንንም የሚያስረዳ ነገር በጥምቀት ከእግዚአብሔር ከምትገኝ ልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት፡፡ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግስተ ሰማይ መያዣ ከናት፡፡ በንስሐ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን፡፡ ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት፡፡ በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን፡፡ መከላከያ ከሚሆን ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፡፡ አምላክ የጻፈው መጽሐፍ እንደተናገረ ሁላችን በድለናልና ያለ ዋጋ በይቅርታው ከኃጢአት እንነጻለን፡፡ ንስሐ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በሃይማኖትና በልቡና የምትገኝ ሁለተኛ ጸጋ ናት፡፡ ሀብታተ ምስጢራት ከሚገኙበት ከመንፈሳዊ ፍቅር እስክንደርስ ድረስ የሚጠብቀን መንፈሳዊ ዕውቀት ነው፡፡ (ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ)
Mostrar todo...
አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ኀዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፡14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡ ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን? እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Mostrar todo...
ዘማሪ ብርሃኑ ጫኔ ክራር ኢዮሲያስ አበራ @krarnadmtsi
Mostrar todo...
ግሩም_ዝማሬ_አንደበቴም_ያውጣና_ሌሎችም_.mp35.66 MB
እንዴት ወጣሁ ብዬ.mp34.10 MB
“አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡ አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!” #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ገጽ 178)
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.