cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኮሜድያን ሻጠማ እድሮች

ይህ ትክክለኛው የኮሜድያን ሻጠማ እድሮች ( ኮሜዲያን አሞራው ና ኮሜዲያን ዶጊሶ ) የቴሌግራም ቻናል ነው። ለወዳጅ ጓደኛዎ ሼር በማድረግ ቀን በቀን ይዝናኑ። ለማንኛውም አስተያየት @comedian_amoraw

Mostrar más
Etiopía8 750Amárico7 969La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
473
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from N/a
#የፈጣሪ_ድርሰት 🖊sinex ፈጣሪም በህይወት መዝገብ ላይ ሊያሰፍረን ብዕሩን አነሳ። እኔን ቸክቻኪ ከሚለው ምዕራፍ ላይ አኖረኝ። እቺን ውብ ደግሞ ለቆነጃጅት ምሳሌ ትሆን ዘንድ በውበት ምዕራፍ ላይ ርዕስ አድርጎ ጻፋት። ለኔም ውበቷን አደንቅ ዘንድ ጥቂት ቃላትን በተን አደረገልኝ። በእርግጥ ውብ ናት ስል ውጪያዊ ውበቷን ብቻ አይቼ አይደለም፤ ወጀብ አልባ ውቅያኖስን የሚያስቀናው እርጋታዋ፣ የንጋት አዕዋፋት ዝማሬን የሚያስንቀው ድምጿ(በእርግጥ ድምጿን ሰምቼው አላውቅም ግን ቢሆንም ከአዕዋፋት ዝማሬ እንደማይተናነስ ምንም ጥርጥር የለኝም)፣ ከክዋክብት ተቀድተው የተሰሩ እሚመስሉ አይኖቿ…. (እህ? ድምጽ እና አይን ውጪያዊ ውበቶች አይደሉ እንዴ? እና ስቀባጥር ምን ዝም ትሉኛላችሁ?) ከእርጋታዋ ባሻገር ቁጥብነትዋ ሙሉ ሴት ያደርጋታል። አንዳንዴ ጥላሁን ድሮ ድሮ ሞናሊዛዬ ነሽ ብሎ የዘፈነው ለሷ ይመስለኛል። ምናልባት በራዕይ ታይታው… ምናልባትም ከሱ በፊት ሌላ ባለ ትንቢት እነሆ አንድ ታላቅ ድምጻዊ ቃላቶች ያጥሩኛል ብሎ ለአንዲት ውብ እንስት ትንቢታዊ ሙዚቃ ያቀነቅናል፤ ከአመታት በኋላም ይህች ውብ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ትታያለች፤ ለውበቷም ቃላት አይገኝም…. (ሌላም ሌላም ተብሎ ይሆናል ማን ያውቃል)። በርግጥ የሞናሊዛ ውበት ምኑ ጋር እንደሆነ አይገባኝም(ድሮስ አንተ ምን ገብቶህ ያውቃል እንዳትሉኝ) ስለዚች ሴት ውበት ግን በሙሉ ልቤ መከራከር እችላለው። የአባይ ፏፏቴን በጥቁር የመሠለው ፀጉሯ ትከሻዋ ላይ ዘንፈል ብሎ ወደ ወገቧ ቁልቁል ሲጋልብ ማየት በራሱ እፎይታን ይሰጣል። (ጥሎብኝ ደግሞ ፀጉር ስወድ በርግጥ የአይንም አድናቂ ነኝ። ቅድም ስለ አይን ለምንእንደቀባጠርኩ ገባችሁ አይደል)። ያለ አንዳች ቃል ብዙ ሚናገረው ዝምታዋ በእርግጥም ዝምታ ወርቅ ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው። መለስ ብዬ የጻፍኩትን ሳየው ትንሽ በራሴ እናደዳለው። እቶን ለሆነው ውበቷ፣ ማዕበል ለሆነው ዝምታዋ፣ ድንቅ ለሆነው ቁጥብነቷ ከነዚህ የተሻሉ ቃላትን ባለማግኘቴ በራሴ እናደዳለው። እኔን ብሎ ደራሲ… ምናልባት ፈጣሪ ቃላቱን ሲበትንልኝ ስለ ውበቷ ለመጻፍ ተጣድፌ አንዳንድ ቃላትን ረስቼ ይሆን እላለው። በርግጥ ከእብደቴ ቀጥሎ የተመረቀልኝ ትልቁ ስጦታዬ ዝርክርክነቴ ይመስለኛል። እናም ሳስበው ያኔ የተዝረከረኩ ይመስለኛል፤ ይህችን ድንቅ ጥበበኛ ሰዓሊ የሳላት ስዕል የመሰለች እንስት ለመግለጽ ቃላት ካጣው ምናልባትም ተዝረክርኬ ይሆናል ይሄ ልጅ ዝም ብለን ከሰማነው ብ…ዙ…. ሊያወራብን ነው ማለት ሳጀምሩ አትቀሩም። (ብትጀምሩስ እኔ ምን አገባኝ፤ ያላትን እንጂ ያልሰጣትን አላወራው።) ፈጣሪም ቀጠለና ትንሽ ኩርፊያ ጣል አደረገባት፤ ስታድግ ኩርፊያዋም አብሮ አደገና ይኸው ውሃ ቀጠነ እያለች ማኩረፍ ነው፤ እኔ ደሞ ጥሎብኝ ኩርፊያ ስፈራ(ኤጭ! አንተ ደግሞ ስንቱን ነገር ነው ሚጥልብህ እንዳትሉኝ)። በነገራችን ላይ ስንፍናዋ አያድርስ ነው። እናቴ ስንፍና ቤቱን ሰርቶብሃል ትለኝ ነበር፤ እሷን ብታይ ሰባት ኮንዶሚንየም እና 3 አፓርታማ ነበር ምትገነባላት ። ድሮ ተፈጥራ ቢሆን ማርፈድ የስንፍና ምልክት ነው ሳይሆን መቲ የስንፍና ምልክት ናት እያልን ነበር (ኦው ለካ ስሟን አልነገርኳችሁም። መቲ ማለት እሷ ናት፤ መታሰቢያ)። ብዙ ስለሷ መጻፍ አስብና ሃሳቦቼን መሰብሰብ እየከበደኝ ቁጭ ብዬ ቀራለው። አለ አይደል አንዳንዴ ከቃላት በላይ የሚሆንባቹን ሰው መግለጽ ይከብዳል። ፍልስፍናዬን ሳልጀምር አንድ ሙዚቃ ልጋብዛችሁና ላብቃ፤ የሚካኤል በላይነህ… “ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ….” ጨርሱት። Join for more https://t.me/ahava_creatives @ahava_creatives
Mostrar todo...
Repost from Arada style
ለአሼ ታለንት የሬዲዮ ዝግጅት አድማጮች በሙሉ ? አሁን በቀጥታ የምንገኘው በአንጋፋው fm አዲስ 97.1 ላይ ነዉ ። አሼ ታለንቶች ነን ! አሼ ታለንት በfm አዲስ 97.1 ይጠብቆታል ። በነጻ ፍላጎትዎ ከልብዎ የሚያዳምጡት ! ዘመኑ ከልብ የመግባባት ነዉ ። ተወዳጁ አሼ ታለንት ፕሮፋይል የቀጥታ ስርጭት የመረጃና የመዝናኛ ልዩ ዝግጅት መጋቢት 6 /2014 በአዲስ አቀራረብ በ fm አዲስ 97.1 ላይ ይጀምራል : ቀጣዩ ጉዞም ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ዘዉትር ማክሰኞ ከምሽቱ 2-3 እና ሃሙስ ከምሽቱ 2-3 በfm አዲስ 97.1 ብቻ በአራዳ style ይጠብቆታል ። ሳይቅሙ መንቃት : ሳይጠጡ / ሳያቦኑ መዝናናት አሊያም ፈታ ማለት በአራዳ style ዛሬም ይቻላል ። ጋዜጠኛ : የጸረ -ሱስ አክቲቪስት እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር አሼ ታለንት ( አሸናፊ ግዛው መሸሻ ) ከ13 ዓመት በላይ ልምድ ያለዉ ።
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.