cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Some stories now

This is the channel where u could find some notes on controversial issues. In addition we also post some short novels, narratives, poems and many many more. So stay with us if you want to see more.

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
195
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አፈቅርሻለሁ በላት! አንድ ቀን ጎረቤታችን እንቅፋት እስኪደፋት እየተንደረደረች መጣችና "እስኪ ወደሀይልየ ስልክ ደውሉልኝ፤ ስልኩን ሳይሰርቁት አይቀሩም" አለች ተጨናንቃ ነበር! ባለቤቷ ነው! በኋላ ስናረጋግጥ እውነትም የባለቤቷ ስልክ ተሰርቆ ነበር! የሚገርመው የስልኩን መሰረቅ ባለቤቷ ራሱ ከእርሷ በኋላ ነበር ያወቀው! ደውሎ "ያንን ሱሪ እጠቢልኝ" ሊል ኪሱ ሲገባ ስልኩ ኢንጅሩ! ነገሩ ገርሞኝ " እንች ግን ስልኩ እንደተሰረቀ በምን አወቅሽ ?" አልኳት! "የተላከልኝ ቴክስት አታየውም?" ብላ ስልኳን ፊቴ ላይ አስጠጋችልኝ! "I love you ! ይላል! እና ይሄ.... ከማለቴ! "ከተጋባን 17 ዓመታችን አንድም ቀን እንዲህ ብሎኝ አያውቅም" አለች በቅሬታ! ብራዘር፤ ስልክህ ብቻ ሳይሆን ነፍስህም መቸ እንደሚነጠቅ አታውቅም! ዋናው ልብ ነው ምናምን አትበል! አሁኑኑ "አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ" በላት! አልካት? ድ ገ ማ ት! ... አይከፈልበት😀
Mostrar todo...
የነገ ሟች..የዛሬ ሟችን ይቀብራል። በቤተክርስቲያን ዙርያ ጭር ያሉ የመቃብር ቦታዎችን ስትመለከቱ ምን ይሰማችኃል? እኛም ወደእናንተው ነን እያላችሁ ነው የምታልፉት? ወይስ ዝም ብላችሁ ወደቤታችሁ ትገሰግሳላችሁ? ነገ ሀውልታቱ ላይ የኛም ስም ተፅፎ እንደሚታይ የትኛው ልብ ያስባል? ሁሉ ነገር ሩጫ በሆነበት ዓለም ዉስጥ ሁልጊዜ ስለሰው ልጅ ዉድቀት የማያቆም ጭፈራ ወይም የነውር ነገር መስማት አይሰለችም?ለምንድነው የምኖረው?ለሚለው ጥያቄያችን መልስ ማግኘት ካልተቻለ ሁሉ ነገር ድግምግሞሽ ነው። ሕይወት ባዶ ሆኖባቸው ሰሞኑን ብዙ የምናውቃቸው ሰዎች  ጓደኞቻችን ወይም ብዙዎች በተለያየ ምክንያት እየተለዩን ነው አዝነን ብንረሳውም ተራችንን የምንጠብቅ የነገ ተረኞች መሆናችን ግን ታሳቢ አናደርገውም። ሞት የሚባል ነገር እንዳለ መረሳቱ ደግሞ ጥሩ ሕይወት መኖርን እንዳናስብ ያደረገ ይመስለኛል ምክንያቱም መኖር ማለት መሰንበት ማለት ብቻ ስላልሆነ ሕይወትና ሞት እነኚህ ሁለቱ ተቃራኒ ብቻ ሳይሆኑ የማይነጣጠሉም ናቸው አንዱን ማሰብ ሌላውንም ማሰብ ነው ሞትህን ማሰብ ከአስፈሪነቱ በላይ ሕይወትህን በአግባቡ እንድትኖር የሚያደርግህ ልዩ technique ነው። ማለቂያ ለሌለው ከንቱ ፍላጎታችን ገደብ ያበጅልናል ሥጋችንን ብቻ በማጥገብ ብንኖር የተጠማ እና የደከመ መንፈስ ግን እንዲሁ እንደማይረካና እንደማያርፍ ባለፉት ሰዎች በኩል ይተርክልናል... ዛሬ ቆመን የምንረማመድበት መሬት ስር ነገ  ተጠጋግተን እንደምንቀበርበት ብናስብ ኖሮ የሚያከባብር እንጂ የሚያጣላ መሬት አለመኖሩን እንረዳ ነበር አፈር ነንና ወደ አፈር እንመለሳለን እስክንነሳ ይህቺን ባንረሳ! @somestoriesnow
Mostrar todo...
አንዳንድ ቤት ግን ሲጨንቅ! የሆነ በቁሙ የሞተ! ግድንግድ ሶፋ ፣ ውድ ቲቪ በሸክላ ሰሀን የተሞላ ቡፌ ፣ ውድ መጋረጃ ለመርገጥ የሚያስፈራ ምንጣፍ .... ስልክ ቁጥር ለመፃፍ ቁራጭ ወረቀት ብትጠይቁ ግን የወረቀት ዘር በቤቱ የለም! መፅሐፍማ እርሱት! "ወይ እዚህ ጋ ትፅፈው?" ብለው ናብኪን ያመጡላችኋል! እና እዚህ መቃብር ውስጥ ልጆች ያድጋሉ! እናንተ በቤት እቃ የተገነዛችሁ ሰዎች እባካችሁ ልጆቻችሁን እንኳን ከእናተ የቁም ሞት አትርፏቸው! ለናሙና እቤታችሁ የሚነበብ ነገር ለልጆቻችሁ አስቀምጡ! ወረቀት ሲንኮሻኮሽ ይስሙ! ያንብቡ በእድሚያቸው ልክ መፅሐፍት ግዙላቸው! ምን አይነት ጨካኝ ወላጆች ብትሆኑ ነው ግን? ይሄን ኮተት እንደትልቅ ነገር አትቁጠሩት! ልጆቻችሁ ያንብቡ ማለት የመፅሐፍ ሻጭ ተራ ማስታወቂያ አይደለም! ነገ ልጀ እንዲህ ሆን እንደዛ እያላችሁ ከመነፋረቅ ያድናችኋል! ልጆቻችሁ ነገ ወደዚች አለም የእናተን ሶፋና ምንጣፍ ተሸክመው አይሄዱም! ባዶ ልጆች ለዓለም አታዋጡ!
Mostrar todo...
By the way, women who stand against what women think and say about men and say "we are caring for men" etc. are traitors to me 😀 Many of them are Indian movies! They think everything can be fixed by calculating and coloring! You will find them on police news when they cut their husband with a knife and their hair stood up! I'm some kind of an angel and some kind of polite painting! They think there's a way to love a man they created who hasn't tried! My sisters, I tell you... If you want to shake, shake; if you want to say ooh, say ooh... Just be yourself! Life is like a river, it has its own flow, enjoy it to take you, don't get tired swimm… See more
Mostrar todo...
ከይስሙላ አንድነት ፣በእምነት ካልተዋቀረ ህብረት፣ በግርግር ከተሞላ መንጋነት ይልቅ ጥርት ያለ ልዩነት ለመፍትሄ ያበቃል። @somestoriesnow
Mostrar todo...
ናፍቀኸኛል........
Mostrar todo...
6.69 MB
❤️
የሆነ ቀን ላይ ወደ ኋላ መልስ ብላችሁ ራሳችሁን የምታዩበት ቀን ይመጣል። የሆነ ቀን ላይ መስኮቶቻችሁን ከፍታችሁ፤ሰማዩን እየተመለከታችሁ ወደ ትናንትናው ህይወታችሁ መልስ ብላችሁ ራሳችሁን የምታዩበት ቀን ይመጣል። ጓደኛዬ ትናንቴን ሳይ ያመኛል ይለኛል።እኔ ደግሞ ልጅነቴ ይናፍቀኛል እለዋለው።ምናልባት አንዳንዶቻችን ትናንትናችን ስንመለከት በእንባ እንሞላ ይሆናል።አንዳንዶቻችን ደግሞ ያቦካናቸውን ጭቃዎች፤የሰራናቸውን ጎጆዎችና የተጣላንባቸውን ቀናቶች እያስታወሰን ፈገግ ማለት እንጀምር ይሆናል። ይሄ ነገር ወዴት እንደሚወስደኝ አላውቅም።ነገር ግን በትናንትነትና በአሁንነት ውስጥ ያለው ለውጥ ምንድን ነው? ብዬ ራሴን ስጠይቅ "አሁን የምንሰራት ነገር ትናንትና ተብላ ትተረካለች" የሚል መልስ አገኘው!
Mostrar todo...
በዘመናት ውስጥ የአራዳነት ማሳያ ተደርገው የቀረቡ ብዙ ነገሮች አሉ። ከሁሉም የሚልቅ አንድ የአራዳነት ምልክት ግን አለ - እርሱም ማንበብ ነው! አራዳ ወጣት አንባቢ ነው። በአጓጉል ሱሶች ሳይሆን፥ በንባብ ሱስ የተጠመደ ነው። ያነባል፥ ያስነብባልም! ብዙዎች ጎራ ብለው እየሸመቱ ነው። እርስዎስ ታዲያ መቼ ብቅ ያላሉ? #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #ደስተኛ_ደንበኞች #reading_addicts
Mostrar todo...
2.76 MB
❤️
👍
አንዳንድ ቀኖች ልክ አስተውለን እንዳልሰማነው ወሬ ይሆኑብናል ፣በብርቱ የህይዉት ሰልፍ ላይ ፈድፍችንን አጥተን እንየተንከላውስን አይነት ፣አንኳኩ ይከፈታል የባሉት በሮች ተከፍተውልን እንኳን ያልገባን ወይም ያልወጣን መሀል ሰፋሪዋች አይነት ፤ ደስተኛ ናችሁ ብንባል "አልቅሼ አላውቅም "አይነት መልስ ያለን ፣መቼ እዚህ እንደደረስን የማናውቅ ፣ብቻ በሚመጣው የቀን መንጋ መሀል ብ..ር.....ት.....ር የምትል ነፍስ ። @somestoriesnow
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.