cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የሰለምቴዎች ቻናል

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 154
Suscriptores
+224 horas
+477 días
+28830 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
ምእመናን ግን በጀነት ስላሉ ከዚያ ቀን ስቃይ ተቤዥተዋል። ከእነዚያ ከካዱት ግን ቤዛ አይወሰድም፥ ለእነዚያም ለበደሉት ከሐድያን በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፦ 57፥15 «ዛሬም ከእናንተ ቤዛ አይወስድም፥ ከእነዚያ ከካዱትም አይወሰድም፡፡ መኖሪያችሁ እሳት ናት፥ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» ይሏቸዋል፡፡ فَالْيَوْمَ لَا يُؤْخَذُ مِنكُمْ فِدْيَةٌ وَلَا مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ مَأْوَاكُمُ النَّارُ ۖ هِيَ مَوْلَاكُمْ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ 39፥47 ለእነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፡፡ وَلَوْ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُ مَعَهُ لَافْتَدَوْا بِهِ مِن سُوءِ الْعَذَابِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ይህቺ የካፊር ነፍስ ከነፍስ ምንንም ቤዛ የማይያዝበትን ቀን ተጠንቀቁ! እንግዲህ ቤዛ፣ ምልጃ፣ ወዳጅነት የሌለበት ቀን የተባለው ከዐውድ እና አጠቃላይ ከቁርኣን መልእክት አንጻር ለከሓዲ በዳዮች ብቻ ነው። የፍርዱ ቀን ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ምልጃ ያረጋል፥ የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ሰው ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 402 አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው የአሏህ ነቢይም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ጸሎት ያረጋል፥ በትንሳኤ ቀን የእኔ ጸሎት ለኡመቴ ምልጃ ነው*። عَنْ قَتَادَةَ، حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ دَعَاهَا لأُمَّتِهِ وَإِنِّي اخْتَبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لأُمَّتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏”‏ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41 አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏ ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
1971Loading...
02
ምልጃ የሌለበት ቀን በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ "ምልጃ" ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፥ እነርሱም፦ ፨አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣ ፨ሁለተኛው የሚማልደው አማላጅ እና ፨ሦስተኛ የሚማለድለት ተመላጅ ናቸው። አሏህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፥ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱት አማላጆች ደግሞ መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው፦ 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ "ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም" የሚለው ይሰመርበት! ዐውደ ንባቡ ስለ መላእክት እያወራ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የሚማለድላቸው ተመላጆች ደግሞ አሏህ ዘንድ ቃል ኪዳን የያዙት አማንያን ናቸው፦ 34፥23 ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ 19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 20፥109 በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا "በዚያ ቀን" የሚለው የፍርዱ ቀን ሲሆን በዚያን ቀን አሏህ የፈቀደላቸው መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለምዕመናን ያማልዳሉ። ነገር ግን ለኩፋሮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፦ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع 2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ "ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን" የፍርዱ ቀን ሲሆን ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለው ለኩፋሮች ስለሆነ ዐውዱ ላይ "ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው" በማለት ይናገራል። ያ የፍርዱ ቀን እነርሱም ከአሏህ እርዳታ የማይረዱበትን እና ምልጃን የማይቀበሉባት ቀን ነው፦ 2፥48 ነፍስም ከነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፣ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፣ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝበትን፣ እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡ وَاتَّقُوا يَوْمًا لَّا تَجْزِي نَفْسٌ عَن نَّفْسٍ شَيْئًا وَلَا يُقْبَلُ مِنْهَا شَفَاعَةٌ وَلَا يُؤْخَذُ مِنْهَا عَدْلٌ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ "የማይቀበሉ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በግስ መደብ የተጠቀሱት እና "እነርሱ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በስም መደብ የተጠቀሱት በዳዮቹ ከሓዲዎች እንጂ ምእመናንን አይጨምርም፥ በፍርዱ ቀን አሏህ የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሙእሚን ቢኾን እንጅ ለከሓዲ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም። ኩፋሮች የትንሳኤ ቀን፦ "በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ? ተብለው ሲጠየቁ፦ "ከሰጋጆቹ አልነበርንም፣ ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፣ ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፣ በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን" ይላሉ። የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፦ 74፥48 የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" የተባለው አሁንም ለኩፋሮች እንጂ ለሙእሚን በፍጹም አይደለም። "ሑላህ" خُلَّة ማለት "ወዳጅነት" ማለት ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ማለት ደግሞ "ወዳጅ" ማለት ነው፥ በዚያ ቀን ኩፋሮች አንዱ ለሌላው ጠላት ነው፦ 43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ "ወዳጆች" ለሚለው የገባው ቃል "አኺላእ" أَخِلَّاء ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ" የሚለው ይሰመርበት! አሏህን ፈሪዎች ምእመናንማ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይወዳጃሉ፡፡ የእነዚያም ወዳጅነት አማረ፦ 4፥69 አላህን እና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَـٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَـٰئِكَ رَفِيقًا ስለዚህ "ምልጃም የሌለበት ቀን" የተባለው "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" በተባለበት ዐውድ ከሆነ እና ለምእመናን ምልጃ ሆነ ወዳጅነት ካላቸው ምልጃ እና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ለኩፋሮች ነው፥ የፍርዱ ቀን ለኩፋሮች ቤዛ የሌለበት ቀን ነው። ሙጅሪም ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፥ ቅሉ ግን ለእነርሱ ቤዛ የሌለበት ቀን ስለሆነ ከእሳት ቅጣት አይቤዥም፦ 70፥11 ዘመዶቻቸውን ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
1741Loading...
03
የአሏህ መታየት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ የትንሣኤ ቀን ምእመናን በጀነት ውስጥ ይሆናሉ፥ ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ በጀነት ውስጥ ያለው ተጨማሪ መንፈሳዊ ጸጋ አሏህን ማየት ነው፦ 50፥35 ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ”እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ”፡፡ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌۭ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 354 ሱሀይብ እንደተረከው፦ "ነቢዩም’ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነዚያ የጀናህ ባለቤቶች ጀናህ በሚገቡ ጊዜ የተከበረው እና ከፍ ያለው አሏህ፦ "ጭማሪ እንድሰጣችሁ ትፍልጋላችሁን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ ፊታችንን አላበራህምን? ጀናትንስ አላስገባከንምን? ከእሳትስ አላዳንከንምን? ይላሉ። ከዚያ እርሱ ግርዶሹን ያነሳል፥ ለእነርሱ የወደደው አሸናፊው እና ክብራማ የሆነውን ከጌታቸውን ፊት በስተቀር ለእነርሱ ምንም ነገር በእነርሱ ዘንድ የለም"። عَنْ صُهَيْبٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا دَخَلَ أَهْلُ الْجَنَّةِ الْجَنَّةَ - قَالَ - يَقُولُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى تُرِيدُونَ شَيْئًا أَزِيدُكُمْ فَيَقُولُونَ أَلَمْ تُبَيِّضْ وُجُوهَنَا أَلَمْ تُدْخِلْنَا الْجَنَّةَ وَتُنَجِّنَا مِنَ النَّارِ - قَالَ - فَيَكْشِفُ الْحِجَابَ فَمَا أُعْطُوا شَيْئًا أَحَبَّ إِلَيْهِمْ مِنَ النَّظَرِ إِلَى رَبِّهِمْ عَزَّ وَجَلَّ ‏"‏ ‏.‏ የምእመናን ፊቶች በትንሣኤ ቀን አብሪዎች ናቸው፥ ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፦ 75፥22 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ 75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ 10፥26 ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገር እና ”ጭማሪም አላቸው"። ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፥ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ ٱلْحُسْنَىٰ وَزِيَادَةٌۭ ۖ وَلَا يَرْهَقُ وُجُوهَهُمْ قَتَرٌۭ وَلَا ذِلَّةٌ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ በተቃራኒው የከሓዲያን ፊቶች በትንሣኤ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፥ ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። ምክንያቱም እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፦ 75፥24 ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ 80፥40 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አለባቸው። وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ 80፥41 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ 80፥42 እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ከእምነቸው በኋላ የካዱ እና ይክዱ በነበሩት ነገር ቅጣትን የሚቀምሱ ናቸው፥ እነርሱ በትንሣኤ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፦ 3፥106 ፊቶች የሚያበሩበትን ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን አስታውስ፡፡ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ» ይባላሉ፡፡ يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ اسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَانِكُمْ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ 84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ አምላካችን አሏህ በዛቱ ከፍጥረት ውጪ ቢሆንም ምእመናን በጀነት በዓይናቸው ሳያካብቡት እርሱ በሚፈልገው መልኩ ያዩታል። ፍጡራን እርሱን በማየት አያካብቡትም፥ እርሱ ግን ሁሉን ተመልካች ስለሆነ ሁሉንም ያካብባል፦ 6፥103 ዓይኖች አያካብቡትም፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያካብባል፡፡ እርሱም ርኅራኄው ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ "አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለት "ረቂቁ" ማለት ሲሆን አሏህ በፍጡራኑ ዓይን የማይከበብ ረቂቅ ነው፥ እኔ ለማወቅ የሚታወቅ ነገር፣ ለማየት ብርሃን፣ ለመስማት ድምፅ፣ ለመታየት አካል ያስፈልገኛል። አሏህ ግን ከማንም ከምንም ፍጥረት ጋር ስለማይመሳሰል ፍጥረት ሳይኖር ፍጥረቱን የሚያውቅ፣ በጨለማ ውስጥ ያሉትን የሚያይ፣ በልብ የሚንሾካሸኩትን የሚሰማ፣ ለምእመናን በትንሳኤ ቀን ስይካበብ በመገለጥ የሚታይ ነው፦ 42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ እሩቅ ሳንሄድ በባይብል አንዱን አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፥ እርሱም፦ "ፊቴን ማየት አይቻልህም" ብሏል፦ 1 ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው "ለማይታየውም" ለዘመናት ንጉሥ ምስጋና እና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን! አሜን። 1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም። ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ "ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም" አለ። አንዱን አምላክ አንድ ሰው እንኳ ባያየው እና ሊያይ ባይቻለው ባሮቹ ግን በትንሣኤ ቀን በትንሣኤያዊ ዓይን ፊቱን ያያሉ፦ ኢዮብ 19፥27 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል። ራእይ 22፥3 ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ። አምላካችን አሏህን በትንሳኤ ቀን እርሱን ከሚያዩት ምእመናን ያርገን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
2781Loading...
04
ሳትሳደቡ በማስረጃ መልሱ 1ኛ ነገሥት 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም። ⁵ ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ። ⁶ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። ደሞ ሌሎችንም ጣኦት ያስመልክ ነበር “በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ።” — 1ኛ ነገሥት 11፥7
1940Loading...
05
የታመማችሁ ሰዎች ብስራት🌹💧 አንድ ሙስሊም ቢታመም እሳት ከወርቅና ከብር ቆሻሻን እንደሚያስወግድ ሁሉ በበሽታው የተነሳ አላህ ኃጢአቱን ያስወግድለታል።” «አስ–ሲልሲለቱ አስ– ሰሒሃ –714» ◍እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
2240Loading...
06
የኢየሱስ እናት መርየም ለእናቷ አንድና የስለት ልጅ ብትሆንም በአባቷ ግን ወንድምና እህት እንዳላት ነገረ-ማርያም"Marylogy" ይነግረናል፣ ባይብልም ማርያም እህት እንዳላት ይናገራል፦ ዮሐንስ 19፥25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ፦ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ *የእናቱም እኅት*፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። በታሪክ፣ በፔንታተች ሆነ በታልሙድ መጻሕፍት የሙሴና የአሮን አባት "እንበረም" עַמְרָם ሲሆን እናታቸው ደግሞ "ዮከብድ" יוֹכֶ֤בֶד ናት፣ ይህን ከራሳችሁ መጽሐፍ ቅሪት ማየት ይቻላል፦ ዘጸአት 6፥20 *እንበረምም עַמְרָם የአጎቱን ልጅ ዮካብድን יוֹכֶ֤בֶד አገባ፥ “አሮንና ሙሴንም” ወለደችለት*፤ ነገር ግን የሙሴ እህት ማርያም እና የኢየሱስ እናት ማርያም ሁለት የተለያዩ ሴቶች ናቸው። ይህ በቀላለ እንድትረዱት አንድ ናሙና ከባይብል ልስጣችሁ፣ "የጌት ሰው ጎልያድን" የገደለው ማን ነው ዳዊት ወይስ ይሽቢብኖብ? እዚህ አንቀጽ ላይ የጌት ሰው ጎልያድን ዳዊት እንደገደለው ይናገራል፦ 1ኛ ሳሙኤል 17፥4 ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር *የጌት ሰው ጎልያድ*፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ። 1ኛ ሳሙኤል 17፥50 *ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ*፤ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም። እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ የጌት ሰው ጎልያድን ይሽቢብኖብ እንደገደለው ይናገራል፦ 2ኛ ሳሙኤል 21፥19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የቤተ ልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን *የጌት ሰው ጎልያድን* ገደለ። አንዱን ክርስቲያን ተወያይ ይህን ጥያቄ ሳቀርብለት "ወሒድ ምን ነካህ ደህና ሰው አልነበርክም እንዴ? ዳዊት የገደለው ጎልያድ እና ይሽቢብኖብ የገደለው ጎልያድ እኮ በተለያየ ዘመን የኖሩ ሁለት ግለሰቦች ናቸው" አለኝ፣ እውነት ነው የአይሁድ ሆነ የክርስቲያን ስመ-ጥርና ዝነኛ ኮሜንታተሮች በተለያዩ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ግን በአንድ ቦታ በጌት ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፣ ታዲያ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው ነገሩ፣ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ይሉሃል እንደዚህ ነው። ሲቀጥል ወንድምና እህት የግድ የአብራክ ክፋይ የሚለውን አያሲዝም። ሉጥ የኢብራሂም የወንሙ ልጅ ሲሆን ኢብራሂም ለሉጥ ደግሞ አጎት ነው፣ ነገር ግን ሉጥ ለኢብራሂም ወንድም ተብሏል፣ ያ ማለት የአንድ ቤተሰብ መሆንን ካሳየ የሙሳ ወንድም አሮንና መርየም የሌዊ ቤተሰብ ስለሆኑ ወንድም አሊያም እህት ቢባሉ ችግር የለውም፦ ዘፍጥረት14፥12 በሰዶም ይኖር የነበረውን *የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን* ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ። ዘፍጥረት14፥14 አብራምም *ወንድሙ* እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
2892Loading...
07
ነጥብ ሁለት "የሃሩን እኅት" አምላካችን አላህ በዒሣ እናት በመርየም ዘመን የነበሩት የመርየም ዘመዶች የዒሣን እናት መርየምን "የሃሩን እኅት" እንዳሏት ተርኮልናል፦ 19፥28 *«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት*፡፡ يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا "አሏት" የሚለው ይሰመርበት፤ ባዮቹ የመርየም ዘመዶች ቢሆኑም አላህ ይህንን ተርኮልናል። የኢሳን እናት መርየም የአባቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "ኢያቂም" יְהוֹיָקִים በቁርኣን ደግሞ "ዒምራን" عمران ነው፤ የእናቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "አና" חַנָּה በተፍሲር ደግሞ "ሐናህ" حنة ነው፣ ኢያቄም የማርያም አባት ስለመሆኑ ከቁርአን ማየት ይቻላል፦ 3፥35 *የዒምራን ባለቤት (ሐና)* «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን ፅንስ ከሥራ ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ 66፥12 *የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ*፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِين ቁርኣን ላይ የመርየም እናት ስሟ ባይጠቀስም ማንነቷ ተገልጻል። ነገር ግን ባይብል ላይ የመርየም እናት እና አባት ስም ሆነ ማንነት አልተገለጸም። ስለዚህ ከመነሻው በሌለ ነገር ሁለት የተለያዩ ታሪካትን አዛብቶ ግጭት መፍጠር አይቻልም፣ ታዲያ ዒሣ እናት የመርየም ወንድም ሃሩን ማነው? ስንል የስም ሞክሼ እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ይህንን ከነብያችን"ﷺ" መረዳት ይቻላል፦ ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 38, ሐዲስ 13 አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ እንደተረከው፦ *"ወደ ነጅራን በመጣው ጊዜ የነጅራን ክርስቲያኖች፦"የሃሩን እኅት ሆይ! የሚል ቀርተክልናል፤ ሙሳ ከዒሣ ብዙ ጊዜ በፊት የነበረ ነው" ብለው ጠየቁኝ። እኔም ወደ አላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስመለስ ስለዚህ ጉዳይ ጠየኳቸው፣ እሳቸውም አሉ፦ "የድሮ ሰዎች ከራሳቸው በፊት ከነበሩት የነቢያቶች ስሞች ከነቢያቱ ህልፈት በኋላ ይጠቀሙ ነበር*። عَنِ الْمُغِيرَةِ بْنِ شُعْبَةَ، قَالَ لَمَّا قَدِمْتُ نَجْرَانَ سَأَلُونِي فَقَالُوا إِنَّكُمْ تَقْرَءُونَ يَا أُخْتَ هَارُونَ وَمُوسَى قَبْلَ عِيسَى بِكَذَا وَكَذَا ‏.‏ فَلَمَّا قَدِمْتُ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سَأَلْتُهُ عَنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَمُّونَ بِأَنْبِيَائِهِمْ وَالصَّالِحِينَ قَبْلَهُمْ ከነቢያችን"ﷺ" ንግግር የምንረዳው የሙሳ ወንድም ሃሩን እና የዒሳ እናት የመርየም ወንድም ኃሩን የስም መመሳሰል እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ናቸው፣ የእሳቸው ዘመድና ባልደረባም ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." ይህን አንቀጽ ሲፈስረው፦ "አሮን የማርያም ግማሽ ወንድምና የአባቷ ልጅ ነው" በማለት አስቀምጦታል። ነጥብ ሦስት "ኢኽዋህ" “ኢኽዋህ” إِخْوَة ማለት “ወንድማማች እና እህትማማችነት" ማለት ነው፤ አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው፦ 49፥10 *ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው*፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ በነብያችን"ﷺ" ሐዲስ የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ ሁለት የስም ሞክሼ መሆኑ ተሰምሮበታል፤ ነገር ግን የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ አንድ ማንነት ናቸው ቢባል እንኳን አሁንም ችግር የለውም። ምክንያቱም አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው በሚል ቀመርና ስሌት መረዳት ይቻላል። በትውፊት መርየም የሌዊ ዘር ናት፤ ሃሩንም የሌዊ ዘር ነው፤ ስለዚህ ሁለቱም ወንድምና እህት መሆን ይችላሉ፤ "አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን እና "ኡኽት" أُخْت ማለት ደግሞ "እኅት" ማለት ነው፤ ቃሉ የግድ አብራካዊ ወንድምና እህት ብቻ አያመለክትም። ምክንያቱም "ኡኽት" أُخْت የሚለው ቃል "ሚስል" مِثْل ማለትም "ቢጤ" በሚል ይመጣል፦ 43፥48 ከተዓምርም አንዲትንም አናሳያቸውም እርሷ *ከብጤዋ* በጣም የበለጠች ብትኾን እንጅ፡፡ ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው፡፡ وَمَا نُرِيهِم مِّنْ آيَةٍ إِلَّا هِيَ أَكْبَرُ مِنْ أُخْتِهَا ۖ وَأَخَذْنَاهُم بِالْعَذَابِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ 7፥38 አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን *ብጤዋን* ትረግማለች፡፡ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا "ብጤዋ" ለሚለው የገባውን ቃል "ኡኽቲሃ" أُخْتِهَا አንዳንድ የኢንግሊሽ ትርጉም "እህትዋን"its sister" በማለት አስቀምጠውታል፦ 43፥48 And We showed them not a sign except that it was greater than *its sister*, and We seized them with affliction that perhaps they might return [to faith]. Sahih International ማጠቃለያ ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ በዐረቢኛ “መርየም” مَرْيَم‎ ፣ በዐረማይክ “ማርአም” ܡܪܝܡ‎ ፣ በግሪክ “ማርያ” mαρία ሲሆን የስሙ መሰረት የዕብራይስጡ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ነው፤ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “መር” מר ማለት “ጠብታ” ማለት ሲሆን “የም” ים ደግሞ “ባህር” ማለት ነው፤ በጥቅሉ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ማለት “የባህር ጠብታ” ማለት ነው። በባይብል ማርያም በሚል ስም የሚጠሩ ሴቶች ስምንት ሲሆኑ እነርሱም፦ 1ኛ. የሙሴ እህት፦ ዘጸአት 15፥21 2ኛ. የዕዝራ ልጅ፦ 1ኛ ዜና 4፥17 3ኛ. የኢየሱስ እናት፦ ማቴዎስ 1፥18 4ኛ. መቅደላዊት፦ ሉቃስ 8፥2 5ኛ. የአልዓዛር እህት፦ ዮሐንስ 11፥1 6ኛ. የቀለዮጳም ሚስት፦ ዮሐንስ 19፥25 7ኛ. የማርቆስ እናት፦ 12፥12 እና 8ኛ. የሮሜ ማርያም፦ ሮሜ 16፥6 ናቸው።
2612Loading...
08
ሃሩን ማን ነው? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا ሚሽነሪዎች፦ ቁርኣን ከባይብል ታሪክ ጋር ይጣረሳል" ብለው ሱሪ ባንገት ሊያስገቡ ሲቃጣቸው ይታያል፣ ከሚተቹበት መወዛገብ አንዱ፦ "ቁርአን የሙሴን ወንድ አሮንን የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም ያደርጋል" የሚል ግራጫ ውሸት ይዋሻሉ፥ ይለቃሉ። በኢስላም ላይ ስትቀጥፉ ህሊናን ከሚያሳድድ ጥያቄ አታመልጡም። ታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔው ሎሬትዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፦ "የሰው ልጅ ከሁለት ነገር ይማራል፦ አንዱ “ሀ” ብሎ “በሳር” ሲሆን ሁለተኛው “ዋ” ብሎ “በአሳር” ነው" ይለናል። ሚሽነሪ ሃያሲ ሂስ ከመስጠት በፊት “ሀ” ብሎ “በሳር” ከቁርአን መማር አሊያም “ዋ” ብሎ “በአሳር” ተነግሮ ከማያልቅ ታፍሶ ከማይዘለቅ ከዲነል ኢስላም ዕውቀት መማር ነው። መዋተቱና መቃተቱን ትታችሁ ጓዛችሁን ሸክፋችሁ ለመማር ኑ። መቆዘም አያዋጣም። ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተወዛገባችሁ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናያለን፣ "ሃሩን" هَارُونَ ማለት በአማርኛችን "አሮን" ተብሎ በቁርአን የተጠቀሱ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች አሉ፣ እነርሱም አንዱ የሙሴ ወንድም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም፣ ይህን ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦ ነጥብ አንድ "የሙሳ ወንድም ሃሩን" ሙሳ አንደበተ ኮልታፋ እና ተብታባ ስለነበር ወንድሙ በእርሱ ፋንታ እንዲናገር ወደ አላህ ዱዓ አደረገ፦ 20፥29 «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي 20፥30 *«ሃሩንን ወንድሜን*፡፡ هَارُونَ أَخِي 20፥32 *«በነገሬም አጋራው*፡፡ وَأَشْرِكْهُ فِي أَمْرِي 28፥34 *«ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና*፡፡» وَأَخِي هَارُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّي لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِيَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِي ۖ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ ሙሳ መልእክተኛ ነው፤ ሃሩን ደግሞ ነቢይ ነው፤ ነገር ግን "በነገሬም አጋራው" ብሎ በጠየቀው መሰረት ተውራት የተባለውን ሪሳላ ስለተጋራ መልእክተኛ ተባለ፤ "ከእኔ ጋር ላከው" የሚለው ይሰመርበት፤ ለዛ ነው አላህ ተውራትን ለሙሳ እና ለሃሩን ሰጠናቸው ያለው፦ 21፥48 *ለሙሳ እና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ ሃሩን በራሱ መልእክተኛ አይደለም፤ ግን ነቢይ ሆኖ ሙሳን በመልእክቱ በማስተላለፍ ይረዳዋል፤ አላህ ወደ ሕዝባቸው በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላካቸው፦ 19፥53 *ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ مِن رَّحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا 25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا 23፥45 *ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን*፡፡ ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَارُونَ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ ስለ ነቢዩ ሃሩን በጥቅሉ ይህንን ይመስላል። የሙሳ እና የሃሩን እናት እና አባት አሊያም የቤተሰብ ዝርዝር ስም ሆነ ማንነት ቁርኣን ላይ አልተጠቀሰም።
2333Loading...
09
በድብቅ አላህን ማመጽ💧 «ሰዎች እንዲያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህንም ስትሆን አትስራው !!» (አስሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 1055) ◍እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
2201Loading...
10
"ወንጀላችሁ እንድታበስለት የሚፈልግ ይችን ዚክር ይሐፍዝ" ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما على الأرضِ أحدٌ يقولُ لا إله إلا اللهُ واللهُ أكبرُ ولا حولَ ولا قوةِ إلا باللهِ إلا كفّرتْ عنهُ خطاياهُ ولو كانتْ مثلَ زبدِ البحرِ﴾ 📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል: 3460 እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
2472Loading...
11
من روائع سلسلة سورة الكهف | الشيخ الزين محمد أحمد | Al Zine MOhammed Ahmed | surat al kahf
1 3243Loading...
12
◆▮ውይይት▮◆ ◍ ወንድም ናይ ሐቅ ሚዛን ◍ ወንድም አቡ ሙሐመድ ◍ ወንድም ራስ ምታት 🆅🆂 ◍ ወገናችን Scorpio ◍ ወገናችን Nobi
3431Loading...
13
አህዛብ ማን ነው? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። አንዱ ክርስቲያን በውይይት ላይ ሲናደድ አህዛብ ብሎ ተናገረኝ፤ እኔም አህዛብ ምን ማለትና ምን እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ይቺን ቃል አትደፍራትም ነበር ብዬ ምላሽ ሰጠሁት፤ "አህዛብ" ተብሎ በግሪክ ብሉይ ሰፕቱአጀን እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ኤትኖስ" ἔθνος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤትኒኮስ" ἐθνικός ከሚለው ገላጭ የመጣ ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ "ጎይ" גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ አውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን "ህዝብ" "ብሔር" "አረማዊ" "ይሁዲ ያልሆነ" የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ "አህዛብ" ብለን የምንመለከተው "አረማዊ"pagan" የሚለው እሳቤ ነው፤ ሰዎች ይህ ስም የአብርሃምን አምላክ ለሚያመልኩ ለሙስሊሞች እንደ ቅፅል ስም ሲጠቀሙ እጅግ ስላስደመመኝ ይህ ስም ማንን እንደሚመለከትና ማንን አህዛብ እንደሚል ለመፅሐፍ ቅዱስ ቦታውን እንልቀቅ፦ ነጥብ አንድ "ርኵሰት" በመፅሐፍ ቅዱስ "የአሕዛብን ርኵሰት" ተብሎ የተቀመጠው ምዋርት፥ ሞራ ገላጭ፥ አስማት፥ መተተት፥ ድግምት፣ ጥንቆላ፥ መናፍስትንም መጥራት፥ ሙታን መሳብ ነው፦ ዘዳግም 18፥9-11 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ ""አሕዛብ"" የሚያደርጉትን "ርኵሰት" ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ታዲያ ይህ በኢስላም ትልቁ ሽርክ ነው፤ ከኢስላም አጥርስ የሚያስወጣ አይደለምን? ይህንን ድርጊትስ ማን ነው በዘመናዊ መልክ የሚያደርገው ሙስሊሙ ወይስ ስም ለጣፊው? ነጥብ ሁለት "ግብረ-ሰዶም" አላህ የፈጠረው ተቃራኒ ፃታ"hetro-sexual" እያለ ዛሬ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሆነው ግብረ-ሰዶም"homo-sexual" ማድረግ የአሕዛብን ርኵሰት ነው፦ 1ኛ ነገሥት 14፥24 በምድርም ውስጥ "ሰዶማውያን" ነበሩ፤ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን ""የአሕዛብን ርኵሰት" ሁሉ ያደርጉ ነበር። ታዲያ ይህ በኢስላም አይደለም መጋባት ይቅርና ድርጊቱ ሃራም ነው፤ ማን ነው ታዲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሚያጋባው ቤተክርስቲያን ወይስ መስኪድ? ህሊና ይፍረደዋ። ነጥብ ሶስት "የተቀረፀ ምስል" ነቢያት "የአሕዛብ ልማድ" ብለው ያስቀመጡት ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከብር እና ከወርቅ የተሰሩትን የተቀረፁ ምስሎች ነው፤ እነዚህ ምስሎች አፍ አላቸው አይናገሩም፤ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም፤ ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፣ አህዛብ ግን ወደ እነርሱ ይፀልያሉ፣ ይለማመናሉ፣ እጣን ያጨሳሉ፣ ይጎባደዳሉ፣ ያሸረግዳሉ፣ ይሰግዳሉ፣ -ያመልካሉ፦ 2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም "አሕዛብ" እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም "የተቀረጹ ምስሎቻቸውን" ያመልኩ ነበር፤ 2ኛ ዜና 16፥26 "የአሕዛብ አማልክት" ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች "የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ" ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም። ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ "ከአሕዛብ" ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ "የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት" የሚሸከሙና ያድን ዘንድ "ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ" እውቀት የላቸውም። ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። "የአሕዛብ ልማድ" ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው። ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስዕልና በሃውልት ፊት የሚለማመን፣ የሚያመልክ፣ እጣን የሚያጨስ፣ ስለት የሚሳል? ሙስሊሙ ወይስ እውነተኛው አህዛብ? ኅሊና እያለ ምን ይኮናል። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
3161Loading...
14
▪️ኢብኑ ረጀብ (رحمه الله) እንዲህ አሉ :- "አላህ ጭንቀትንና ትካዜን ከሚያስወግድበት ትልልቅ ምክንያቶች ውስጥ :- ① - አላህን አብዝቶ ማውሳት (ዚክር ማድረግ)። ② - በመልክተኛው (ﷺ( ላይ ሰለዋት ማውረድ። ③ - ቁርአን መቅራትን ማብዛት ናቸው።" اللهم صل على نببينا محمد وعلى آله وصحه أجمعين. ✍️ እኅት ዛህራ ሙስጠፋ
2333Loading...
15
Media files
3380Loading...
16
Media files
3480Loading...
17
ትክክለኛ የአላህ ባርያ ናችሁ? ◍እኅት ዝሀራ ሙሥጠፍ🎤📜
2932Loading...
18
◆▮ውይይት▮◆ ◍ ወንድም ናይ ሐቅ ሚዛን ◍ ወንድም አቡ ሙሐመድ ◍ ወንድም ራስ ምታት 🆅🆂 ◍ ወገናችን Scorpio ◍ ወገናችን Nobi
6111Loading...
19
ይመሰክራሉ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 36፥65 ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን እንዲመሰክሩ የሚያደርጋቸው ፍጡራን በዱንያህ ውስጥ መናገር የማይችሉ ፍጥረታትን ነው፥ ለምሳሌ የሰው ምላስ፣ ጆሮ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር እና ቆዳ አሁን ላይ የማይናገር ሲሆን የትንሳኤ ቀን ግን አሏህ እንዲናገሩ በማድረግ ይመሰክራሉ፦ 24፥24 በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡ يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ 41፥20 በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸው እና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል፡፡ حَتَّىٰ إِذَا مَا جَاءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَارُهُمْ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ 36፥65 ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ በእርግጥም ሰው በራሱ ላይ አስረጅ ነው፥ ከሓዲ መሆኑን በራሱ ላይ በራሱ ምላስ፣ ጆሮ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር እና ቆዳ ይመሰክራል፦ 75፥14 በእርግጥም ሰው በራሱ ላይ አስረጅ ነው። بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ 6፥130 "በራሳቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ"፡፡ وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِينَ 7፥37 "እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ"፡፡ وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ በትንሳኤ ቀን የአንገት ቅርፅ ከእሳት ይወጣል፥ ለእርሱ የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና የሚናገርበት አንደበት ይኖረዋል፦ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 2775 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "በትንሳኤ ቀን የአንገት ቅርፅ ከእሳት ይወጣል፥ ለእርሱ የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና በሦስት ሰዎች ላይ ተወክያለው፥ እነርሱም፦ በእያንዳንዱ አረመኔ አንባገነን ላይ፣ ከአሏህ ሌላ አምላክን የሚጣራ ሁሉ እና ቀራፆች ናቸው" ብሎ የሚናገርበት አንደበት ይኖረዋል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَخْرُجُ عُنُقٌ مِنَ النَّارِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ لَهُ عَيْنَانِ تُبْصِرَانِ وَأُذُنَانِ تَسْمَعَانِ وَلِسَانٌ يَنْطِقُ يَقُولُ إِنِّي وُكِّلْتُ بِثَلاَثَةٍ بِكُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ وَبِكُلِّ مَنْ دَعَا مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ وَبِالْمُصَوِّرِينَ ‏"‏ ‏ “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት” ማለት ነው። የአላህ ቤት የሚጎበኝ ተባዕት “ሓጅ” حَاجّ ሲባል የአላህ ቤት የሚምትጎበኝ እንስት ደግሞ “ሓጃህ” حَاجَّة‎ ትባላለች፥ የሓጅ ወይም የሓጃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሑጇጅ” حُجَّاج‎ ይባላሉ። እሳት ለቅጣት የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና የሚናገርበት አንደበት እንደሚኖረው ሁሉ በሐጅ ሥርዓት ላይ ሐጀሩል አሥወድ በነኩት ሑጇጅ ላይ መልካም ምስክር ይመሰክራል፦ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 155 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስለ ሐጀሩል አሥወድ እንዲህ አሉ፦ "ወሏሂ! አሏህ በትንሳኤ ቀን ሐጀሩል አሥወድ ከሚያይበት ዓይኖች እና በሐቅ በሚነካው ላይ ለመመስከር ከሚናገርበት አንደበት ጋር ያስነሳዋል"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فِي الْحَجَرِ ‏"‏ وَاللَّهِ لَيَبْعَثَنَّهُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ لَهُ عَيْنَانِ يُبْصِرُ بِهِمَا وَلِسَانٌ يَنْطِقُ بِهِ يَشْهَدُ عَلَى مَنِ اسْتَلَمَهُ بِحَقٍّ ‏"‏ ‏ አንድ የማይናገርን ግዑዝ ነገር አሏህ እንዲናገር ማድረግ ምንም አይሳነውም፥ ምክንያቱም አሏህ ከግዑዝ አፈር ሰውን ፈጥሮ እንዲናገር ማረጉ በራሱ የእርሱ ችሎታ ነው። እሩቅ ስንሄድ በባይብል ኢያሱ ታላቁን ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው፥ ከዚያም ለሕዝቡ፦ "እነሆ፥ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ "ሰምቶአልና" ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል" አላቸው፦ ኢያሱ 24፥26-27 ኢያሱም ይህን ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው። ኢያሱም ለሕዝቡ፦ እነሆ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ "ሰምቶአልና" ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል" አላቸው። "ሰምቶአልና" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ታላቁ ድንጋይ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ የሚሰማበት ጆሮ አለውን? ሰምቶስ የሚመሰክርበት አንበት አለውን? ምን ያስደንቃል? ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል እኮ፥ የሚያጅበው ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ሲጮኽ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ሰምቶ ይመልስለታል፦ ዕንባቆም 2፥11 ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል። የድንጋይ እና የእንጨት መናገር እና መስማት ለመቀበል ፍልስፍና ካላስፈለገ አሏህ በትንሳኤ ቀን ሐጀሩል አሥወድ ከሚያይበት ዓይኖች እና በሐቅ በሚነካው ላይ ለመመስከር ከሚናገርበት አንደበት መኖሩን ለመቀበል ፍልስፍና መስፈርት አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
3940Loading...
20
ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል https://t.me/path_of_the_prophets?livestream=c21133ab6a58434a42
2980Loading...
21
Media files
1 3577Loading...
22
▯▩ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ▩▯ "የሐዲስ አሰባሰብ" ◍ ወንድም ሳላህ ◍ ወንድም ሳላህ 🆅🆂 ◍ ወገናችን 🅄🄶🄸🅈
6431Loading...
23
ጠባቂዎች በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ ማመናፈስ እና ማመቻመች የሚወዱ ሚሽነሪዎች ቀን ከሌሊት ወቃሽና ነቃሽ በመሆን ማኮሰስ እና ማራከስ ተያይዘውታል፥ የሃይማኖት ንጽጽር ላይ ያሉት ዐቃቢያነ እሥልምና ደግሞ የሚሽነሪዎችን የቆላ ሀሩር የደጋ ቁር ኢምንት እና ቀቢጽ ያክል ሳይቆጥሩ መልስ ይሰጣሉ። ከሚያንኳስሱትና ከሚያራክሱት ነገር መካከል፦ "ከአሏህ በቀር ጠባቂ የለም" ተብሎ በሌሎች አናቅጽ "መላእክት ጠባቂዎች ናቸው" መባላቸውን ነው። ይህንን የተውረግረገረገ መረዳት በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንየው፦ አምላካችን አሏህ ለአማንያን ጠባቂ ነው፥ ከእርሱ በቀር ጠባቂ የለም። ከእሳት ቅጣት የሚጠብቅ እርሱ ብቻ ነው፦ 9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ 11፥113 ወደ እነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረዱም፡፡ وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ "ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እሳት እንዳይነካን ከአሏህ ሌላ ጠባቂዎች የሉም። ቅሉ ግን አምላካችን አሏህ ለሰው ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አድርጓል፦ 13፥11 *"ለሰው ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አሉት"*፡፡ لَهُ مُعَقِّبَاتٌ مِّن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ يَحْفَظُونَهُ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ 86፥4 *"ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም"*፡፡ إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ 6፥61 እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸናፊ ነው፥ በእናንተም ላይ ጠባቂዎችን ይልካል፡፡ وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ ۖ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ምክንያቱም “መልአክ” مَلْأَك የሚለው ቃል “ለአከ” لَأَكَ ማለትም “ላከ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ተላላኪ” ማለት ነው፥ የመለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “መላኢክ” مَلَائِك‎ ወይም “መላኢካህ” مَلَائِكَة‎ ነው። እነዚህ የአሏህ መላእክት የተለያየ የሥራ ድርሻ ተሰቷቸው ይጠብቃሉ፦ 72፥8 ‹እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችን እና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡ وَأَنَّا لَمَسْنَا السَّمَاءَ فَوَجَدْنَاهَا مُلِئَتْ حَرَسًا شَدِيدًا وَشُهُبًا 72፥27 ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡ إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا ስለዚህ አሏህ "ጠባቂ" የተባለው በራሱ የተብቃቃ እና የባሕርይ ገንዘቡ"ontological term" ሲሆን መላእክት "ጠባቂዎች" የተባሉት የጸጋ እና የሹመት ጉዳይ"functional term" ነው። አንድ ስም ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር እና ስሙር ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙን ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው። ይህ እንዲገባችሁ ከባይብል አንድ ናሙና እንመልከት! ፈጣሪ ብዙ ቦታ፦ "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይላል፦ ኢሳይያስ 45፥22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና፥ "ከእኔም በቀር ሌላ የለም"። פְּנוּ־אֵלַ֥י וְהִוָּשְׁע֖וּ כָּל־אַפְסֵי־אָ֑רֶץ כִּ֥י אֲנִי־אֵ֖ל וְאֵ֥ין עֹֽוד ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ "ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ" እዩ!። רְא֣וּ ׀ עַתָּ֗ה כִּ֣י אֲנִ֤י אֲנִי֙ ה֔וּא וְאֵ֥ין אֱלֹהִ֖ים עִמָּדִ֑י אֲנִ֧י אָמִ֣ית וַאֲחַיֶּ֗ה מָחַ֙צְתִּי֙ וַאֲנִ֣י אֶרְפָּ֔א וְאֵ֥ין מִיָּדִ֖י מַצִּֽיל ኢሳይያስ 45፥5 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። "ከእኔም በቀር አምላክ የለም"። אֲנִ֤י יְהוָה֙ וְאֵ֣ין עֹ֔וד זוּלָתִ֖י אֵ֣ין אֱלֹהִ֑ים אֲאַזֶּרְךָ֖ וְלֹ֥א יְדַעְתָּֽנִי ኢሳይያስ 45፥22 ላይ "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤል" אֵ֖ל ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፥ ዘዳግም 32፥39 እና ኢሳይያስ 45፥5 ላይ "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤሎሂም" אלהים ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ብዜት ነው። ከእርሱ በቀር ኤሎሂም ከሌለ መላእክት "ኤሎሂም" אלהים ተብለዋል፦ መዝሙር 97፥7 "አማልክትም" ሁሉ ስገዱለት። הִשְׁתַּחֲווּ־לֹ֝ו כָּל־אֱלֹהִֽים መዝሙር 8፥5 "ከአማልክትን" እጅግ ጥቂት አሳነስኸው። וַתְּחַסְּרֵ֣הוּ מְּ֭עַט מֵאֱלֹהִ֑ים መዝሙር 138፥1 በአማልክት" ፊት እዘምርልሃለሁ። נגד אלהים אזמרך እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ "ኤሎሂም" כֵּֽאלֹהִ֔ים የተባሉት መላክእት ስለሆኑ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ፦ "መላእክት" ብለው በግልጽ አስቀምጠዋል። ጥያቄአችን፦ "ያህዌህ ከእኔ ሌላ ኤሎሂም የለም" ካለ ዘንዳ በሌሎች ጥቅሶች መላእክት ለምን ኤሎሂም ተባሉ? አዎ መልሱ፦ "መላእክት "አማልክት" የተባሉት ፈጣሪ "አምላክ" በተባለበት ስሌት እና ቀመር አይደለም" ከሆነ እንግዲያውስ መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም አይደለም። ተግባባን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
4061Loading...
24

10Loading...
25
• من سورة ق .. 🌸 ..° } ..• @slmatawahi
1 3305Loading...
26
"የሰውን ሥጋ መብላት በእስልምና እና በክርስትና አስተምህሮ" ◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቤ ኢሥላም ◍ ወንድም ዒምራን ◍ ወንድም ሳላህ ◍ ወንድም አሕመድ
4946Loading...
27
ነጥብ ሁለት "ቀውል" “ቀውል” قَوْل የሚለው ቃል “ቀወለ” قَوَّلَ “ማለትም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የንግግር ክህሎት"articulate speech" ማለት ነው፥ ሰው ስሜቱን እና አሳቡ በቃላት የሚገልጽበት እና የሚያስረዳበት ጥበብ "በያን" بَيَان ይባላል፦ 55፥4 መናገርን አስተማረው፡፡ عَلَّمَهُ الْبَيَانَ እዚህ አንቀጽ ላይ "መናገር" ለሚለው የገባው ቃል "በያን" بَيَان መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰው ከእንስሳ በተለየ መልኩ በተለያየ አገር ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች ጋር በስም፣ በተውላጠ-ስም፣ በገላጭ ቅጽል፣ በግስ፣ በተውሳከ ግስ፣ በመስተዋድድ፣ በመስተጻምር የሚግባባው አሏህ ቀውል የሚባል የመናገር ቅኝት እና ተውህቦ"faculty" ስለሰጠው ነው። ቋንቋ መግባቢያ ነው፥ መግባቢያ ሁሉ ቋንቋ አይደለም። እንስሳት እርስ በእርሳቸው ቢግባቡም ቋንቋ የላቸውም፥ እንስሳ በቋንቋ አይናገሩም እንዲሁ በቋንቋ አይረዱም። ሰው ግን አእምሮው ጤነኛ ከሆነ ከእናት ቋንቋው በተጨማሪ የሌላ አገር ቋንቋ ተረድቶ ማስረዳት ይችላል። ነጥብ ሦስት "መሥኡሉል ዐደብ" "መሥዑል" مَسْؤُول ማለት "ተጠያቂነት" ማለት ሲሆን "ዐደብ" اَدَب‎ ማለት ደግሞ "ግብረገብ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "መሥኡሉል ዐደብ" مَسْؤُول الاَدَب‎ ማለት "ግብረገባዊ ተጠያቂነት"moral accountability" ማለት ነው። አንድ እንስሳት ከእናቱ፣ ከእኅቱ፣ ከሴት ልጁ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ አይጠየቅም አይቀጣም፥ ሰው ግን በሚሠራው ሥራ ይጠየቃል፦ 16፥93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون 102፥8 ከዚያም ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ “ነዒም” نَّعِيم ማለት “ጸጋ” ማለት ሲሆን ይህ የተሰጠን ጸጋ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ነጻ ፈቃድ”free will” ነው። ሰው በሚሠራው ሰናይ ሆነ እኩይ ሥራ ግብረገባዊ ተጠያቂነት ስላለው በፍርዱ ቀን ይጠየቃል። አሏህ በሠራው እና በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም፥ ሰዎች ግን በሚሠሩት ሥራ ይጠየቃሉ፦ 21፥23 ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ግን ይጠየቃሉ፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ ሰዎች በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ይሠሩት የነበሩትን መልካም ነገር ይመነዳሉ፥ በተቃራኒው ይሠሩት የነበሩትን መጥፎ ነገር ይቀጣሉ፦ 18፥180 “ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ”፡፡ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ 6፥120 “እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣሉ”፡፡ نَّ الَّذِينَ يَكْسِبُونَ الْإِثْمَ سَيُجْزَوْنَ بِمَا كَانُوا يَقْتَرِفُونَ አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረበት ጸጋ የሚደንቅ ነው። አሏህ የሰጠንን ጸጋ በአግባብ የምንጠቀም ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
3911Loading...
28
ሰው በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 35፥3 እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ ያለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ!፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ አምላካችን አሏህ የአደምንም ልጆች በእርግጥ አክብሯል፥ ከፈጠራቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 17፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው። وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 17፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا ሰው አሏህ ያከበረው ክቡር ፍጡር ነው፥ ሰው ከእንስሳ የበለጠ ፍጡር ነው። በሰው ላይ ያለው የአሏህ ጸጋ ብዙ ነው፦ 35፥3 እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ ያለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ!፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ ሰው ከእንስሳ በልደት፣ በሞት፣ በመተኛት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተራክቦ በማድረግ የጋራ ተፈጥሮ ቢኖረውም የሚለይበት ሦስት ዐበይት ነገራት ዐቅል፣ ቀውል እና መሥኡሉል ዐደብ አሉት። እነዚህን ሦስት ነገራት ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦ ነጥብ አንድ "ዐቅል" “ዐቅል” عَقْل የሚለው ቃል “ዐቀለ”عَقَلَ ማለትም "ተገነዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አእምሮ" "አመክንዮ" "መረዳት" "ግንባዜ"metacognition" ማለት ነው። ሰው የማሰብ፣ የማስተንተን፣ የመረዳት ተውህቦ"faculty" ያለው ውሳጣዊ ተፈጥሮ የሆነ አእምሮ ስላለው ነው፥ ሰው ከእንስሳ በዐቅል ይለያል። እንስሳ ሰናይ እና እኩይ የሚያመዛዝኑበት አእምሮ የላቸውም፥ ሰው “መንጢቅ” مَنْطِق ማለትም “ሥነ-አመክንዮ”logic" የሚጠቀመው የዐቅል ባለቤት ስለሆነ ነው። አንድ ሰው ወፈፌ ከሆነ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ የሚሠራውን እኩይ ሥራ መላእክት አይመዘግቡበትም፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48 ዓኢሻህ “ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል፥ እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ እና ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ”። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏ ባለማወቅ የሚሠራ መጥፎ ሥራ "ስህተት" ሲባል በመርሳት የማይሠራ መልካም ሥራ "ግድፈት" ይባላል፥ ስህተት ሆነ ግድፈት አያስቀጣም፦ 2፥286 “ጌታችን ሆይ! ”ብንረሳ ወይም ብንስት አትቅጣን” በሉ፡፡ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَ 33፥5 በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ”። አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا "ብንረሳ" ማለት መሥራቱ ግዴታ የሆነ መልካም ሥራ በመርሳት መግደፍ ሲሆን "ብንስት" ማለት መሥራቱ ክልክል የሆነ መጥፎ ሥራ ባለማወቅ መሳሳት ነው። በተሳሳትንበት ነገር በእኛ ላይ ኃጢአት የለብንም፥ ቅሉ ግን ልባችን እያወቀው በሠራነው መጥፎ ሥራ ኃጢአት አለበት፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ
3231Loading...
29
◆▮ነቢያት በባይብል▮◆ "የአላህ መልእክተኛﷺ አባት ጣኦት አምላኪ ከነበሩ ለምን አብደላህ ተባሉ?" ◍እኅት ዘሐራ ሙስጥፋ
1 1184Loading...
30
◆▮ውይይት▮◆ "የነብዩ ሱለይማን(ሰለሞን" በቁርአን እና በባይብል ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ኤሊያስ (ጉድ አይድያ)
3932Loading...
31
◆▮ውይይት▮◆ "የነብዩ ሱለይማን(ሰለሞን" በቁርአን እና በባይብል ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ኤሊያስ (ጉድ አይድያ)
4210Loading...
32
ኤክሌሲያ ገቢር ሦስት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ በማረበብ ከካቶሊክ ኤክሌሲያ በ 1517 ድኅረ-ልደት የሉተር ተሐድሶ፣ በ 1527 ድኅረ-ልደት የአናፓፕቲዝም ተሐድሶ፣ በ 1530 ድኅረ-ልደት የአንግሊካን ተሐድሶ፣ በ 1790 ድኅረ-ልደት የሬስቶሬሽን ተሐድሶ ወጥተው የየራሳቸው ቤተክርስቲያን በመመሥረት፦ "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" በማለት ይስብካሉ፣ ይዘምራሉ፣ ያውጃሉ፥ እነዚህ የተሐድሶ አንጃዎች ሰባቱንም አጠቃላይ ጉባኤ"ecumenical council" ይቀበላሉ። የሉተር ተሐድሶ አምስት ሶላዎችን ያካተተ ሲሆን በካልቪን እርምደተ ሒደት እየሰፋ የመጣ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ዛሬ ላይ እንደ አሸን የሚፈላ የተለያየ ጎጥ ይዟል። ከፕሮቴስታንት ደግሞ አድቬንቲስት፣ ሞርሞር፣ የይሆዋ ምስክሮች፣ የሐዋርያት ቤተ እምነት እና ስፍር ቁጥር የሌላቸው የክርስትና አንጃዎች ወጥተዋል። ዛሬ በዓለማችን ላይ 2.5 ቢሊዮን ክርስቲያን አለ፥ ከዚያ ውስጥ፦ 1ኛ. 1.3 ቢሊዮን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት፣ 2ኛ. 920 ሚልዮን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ናት፣ 3ኛ. 230 ሚልዮን የምስራቋ ቤተክርስቲያን ናት፣ 4ኛ. 62 ሚሊዮን የኦሬንታል ቤተክርስቲያን ናት። እንግዲህ ትልቋ እና የጥንቷ ኤክሌሲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስትሆን ይህቺ ቤተክርስቲያን ከሐዋርያው ህልፈት በኃላ አምላክን ሦስት በማለት ሦስት አካላት ማምለክ፣ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ሳለ ሰው ማምለክ፣ የማርያምን ድንግልና፣ የማርያምን የአምላክ እናት መሆን፣ የማርያምን እርገት፣ ወደ ማርያም መጸለይ፣ ፍጡራን የሆኑትን መላእክት እና ሰዎች መለማመን፣ የሕፃናት ጥምቀት፣ ሰንበትን እሑድ ማድረግ፣ መስቀልን ለምልክትነት መጠቀምና መስገድ፣ ስዕልና ሐውልት ለአምልኮ መጠቀም እንዲሁ ምንኩስናን ደንግጋለች፥ ከላይ የተዘረዘሩትን ሐዋርያት አላስተማሩም። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እነዚህን ድንጋጌዎች ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን እስከ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ደንግጋለች፥ ፕሮቴስታንት የቤተክርስቲያን አበው ስለ ሥላሴ እና ስለ ኢየሱስ የተናገሩትን በመቀበል ስለ ማርያም፣ ስለ መላእክት፣ ስለ መስቀል፣ ስለ ስዕል እና ስለ ምንኩስና ያስተማሩትን ዓይናቸውን በጨው አጥበው "አላየንም" ጆሮራቸውን በጥጥ ደፍነው "አልሰማንም" ብለዋል። የካቶሊክ ኤክሌሲያ እነዚህን ከመስመር የወጡ ትምህርታት የሚያርማትን ሰው የጴጥሮስን መንበር እና የመፍታትና የማሰር ቁልፍ ተቀብያለው በማለት "መናፍቅ" እያለች በግዝት እና በግዞት ስታሰቃይ ነበር፥ ይህቺ ተቋም ሲያሰኛት በጉልበት፣ በበባርነት እና በቅኝ ግዛት ሰዎች ክርስትናን እንዲቀበሉ አርጋለች። ባይብልን ወደ ሌላ ቋንቋ የሚተረጉሙ ሰዎችን ሰቅላለች በእሳት አቃጥላለች። የኢየሱስ ሐዋርያት እንዲህ አላደረጉም፥ ቅሉ ግን እነርሱ አንዱን አምላክ በብቸኝነት የሚያመልኩ ሙሥሊሞች ነበሩ፦ 3፥52 ዒሣ ከእነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፦ «ወደ አላህ ረዳቶቼ እነማን ናቸው» አለ፥ ሐዋርያት፡- «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፣ በአላህ አምነናል፣ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዜት ነው። "ረዳቶች" ለሚለው የገባው ቃል "አንሷር" أَنصَار ነው፥ "ነስራኒይ" نَصْرَانِيّ የሚለው ቃል "ነሰረ" نَصَرَ ማለትም "ረዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ረጂ" ማለት ነው። የነስራኒይ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ነሷራ" نَصَارَىٰ ነው፥ አምላካችን አሏህ፦ "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ይዞ ነበር፥ ይህም ኪዳን፦ "በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ" የሚል ትእዛዝ ነው፦ 5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ» በማለት "ባዘዝኩ" ጊዜ አስታውስ፡፡ «አመንን፤ እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ 5፥14 ከእነዚያም፦ "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም "ከታዘዙበት" ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ አሏህ አንድ አምላክ እንደሆነ እና መሢሑ መልእክተኛ እንደሆነ እንዲያምኑ ያዘዘውን ትእዛዝ ከሐዋርያት ህልፈት በኃላ ያሉት የኤክሌሲያ አበው ፈጣሪ፦ "በአካል ሦስት ነው" በማለት ከታዘዙበት ነገር ፈንታን በመተው ወሰን አለፉ፦ 4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ 4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉም! ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ይህንን ተከታታይ መጣጥፍ የምታነቡ ክርስቲያኖች አንዱን አምላክ በብቸኝነት እንድታመልኩ ወደ ኢሥላም እንጠራችኃለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦ 1.Louis Berkhof(1949)Systematic Theology. 2. Henry Chadwick (2001). The church in ancient society: from Galilee to Gregory the Great. 3. Justo L. González(2010) The Early Church to the Dawn of the Reformation. ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
4992Loading...
33
Media files
8513Loading...
34
◆▮ከውይይት ቡኃላ▮◆ "የመጽሐፍት መጠበቅ"   ቁርአን ወይስ ባይብል ◍ ወንድም ዒምራን ◍ ወንድም ሳለህ ◍ ወንድም ዊስፐር ◍ ኡስታዝ ኤሊያህ ◍ ኡስታዝ አረብ
5173Loading...
35
◆▮ከውይይት ቡኃላ▮◆ "የመጽሐፍት መጠበቅ"   ቁርአን ወይስ ባይብል ◍ ወንድም ዒምራን ◍ ወንድም ሳለህ ◍ ወንድም ዊስፐር ◍ ኡስታዝ ኤሊያህ ◍ ኡስታዝ አረብ
20Loading...
36
Media files
2 4258Loading...
37
ኤክሌሲያ ገቢር ሁለት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ "ሲኖዶስ" σύνοδος ማለት "ስብሰባ" ማለት ሲሆን ኤክሌሲያ ካደረገቻው መደበኛ ስብሰባ አንዱ በ 397 ድኅረ-ልደት የካርቴጁ ጉባኤ ነው፥ በካርቴጅ ጉባኤ የቀኖና መጻሕፍት ብለው የፈጣሪ ንግግር ያለበትን ከሰው ንግግር ጋር ቀላቅለዋል፥ ይህ ሒደት “ስይነርጎስ” ይባላል፥ “ስይነርጎስ” συνεργός ማለት “ቅልቅል” ማለት ነው። በተጨማሪም ከወንጌል ላይ የማይፈልጓቸው የወንጌል ክፍሎች በመቀነስ “አፓክሪፋ” አድርገዋል፥ “አፓክሪፋ” የሚለው ቃል “አፓክርፎስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፦ 3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን "ትቀላቅላላችሁ" እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን "ትደብቃላችሁ"? يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ በመጀመር በ431 ድኅረ-ልደት በሮሙ ንጉሥ በትንሹ እና በሁለተኛው ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የኤፌሶን ጉባኤ 200 ኤጲስ ቆጶሳት በተሰበሰቡበት የሶሪያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ንስጥሮስን አውግዘዋል፥ በዚህም ምክንያት የሶርያን ቤተክርስቲያን፦ "የቶማስን መንበር በመያዝ የሐዋርያዊ ተተኪ"apostolic succession" ይዤአለው" በማለት የራሷን ቤተክርስቲያን "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" በማለት ትሰብካለች፣ ትዘምራለች፣ ታውጃለች። የኒቂያ እና የቆስጠንጥኒያ አጠቃላይ ጉባኤ"ecumenical council" ስትቀበል የተቀሩትን አጠቃላይ ጉባኤያት አትቀበልም። በመቀጠል በ451 ድኅረ-ልደት የሮሙ ሁለተኛው ቴዎዶስዮስ እኅት በብርክልያ ጠሪነት የተዘጋጀው የኬልቄዶን ጉባኤ 130 ኤጲስ ቆጶሳት በተሰበሰቡበት የአሌክሳንድርያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ዲዮስቆርዮስን አውግዘዋል፥ በዚህም ምክንያት የኦሬንታል ቤተክርስቲያን ከካቶሊኳ ኤክሌሺአ ተለይታለች። የኦሬንታል ቤተክርስቲያን የሚባሉት የአሌክሳንድሪያ፣ የኢትዮጵያ፣ የሕንድ፣ የአርመንያ አብያተክርስቲያናት ናቸው፥ የኦሬንታል ቤተክርስቲያን፦ "የማርቆስን መንበር በመያዝ የሐዋርያዊ ተተኪ ይዤአለው" በማለት የራሷን ቤተክርስቲያን "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" በማለት ትሰብካለች፣ ትዘምራለች፣ ታውጃለች። የኒቂያ፣ የቆስጠንጥኒያ እና የኤፌሶን አጠቃላይ ጉባኤ"ecumenical council" ስትቀበል የተቀሩትን አጠቃላይ ጉባኤያት አትቀበልም፥ የኦሬንታል ቤተክርስቲያን የኬልቄዶን ጉባኤን፦ "የውሾች ጉባኤ"ጉባኤ ከለባት" ትላለች። የካቶሊክ ቤተክርስትያን ደግሞ የሶርያ ቤተክርስቲያንን እና የኦሬንታል ቤተክርስቲያንን "አውግዤአቸዋለው፣ መናፍቅ ናቸው፣ በአንብሮተ እድ(እጅ በመጫን) የተቀበሉት ምንም ዓይነት ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የለም" በማለት ትቃወማለች። ፨የባይዛንታይን ቤተክርስቲያን የሮም፣ የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ የሰርቢያ፣ የሩሲያ፣ የቡልጋሪያ፣ የግሪክ አብያተክርስቲያናት ሲሆኑ የጴጥሮስ መንበር ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሆነ የራሳቸው ትውፊት"tradition" አላቸው። ፨የሶርያም ቤተክርስቲያን የቶማስ መንበር ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሆነ የራሳቸው ትውፊት"tradition" አላቸው። ፨የኦሬንታል ቤተክርስቲያን የማርቆስ መንበር ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሆነ የራሳቸው ትውፊት"tradition" አላቸው። በመሠለስ በ 1054 ድኅረ-ልደት "መንፈስ ቅዱስ የሰረጸው ከማን ነው? በሚል የሥነ-መለኮት ውዝግብ እና በኤክሌሲያ አስተዳደር ጉዳይ ለሁለት ተሰነጠቁ፥ ይህ ታልቁ ክፍልል"great Schism" ይባላል። ይህም ክፍፍል ሮም የጴጥሮስ መንበር ያላት በካቶሊክ ኤክሌሲያ እና በተቀሩት የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ የሰርቢያ፣ የሩሲያ፣ የቡልጋሪያ፣ የግሪክ አብያተክርስቲያናት መካከል ነው፥ የጴጥሮስ መንበር መቀመጫ አላት የምትባለው የሮም ኤክሌሲያ ምሥራቃዊ አብያተክርስቲያን የሚባሉትን የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ የሰርቢያ፣ የሩሲያ፣ የቡልጋሪያ፣ የግሪክ አብያተክርስቲያን አወገዘች። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተወገዘችው ምሥራቃዊ ቤተክርስቲያን ከኦሬንታል ቤተክርስቲያን ጋር፦ "መንፈስ ቅዱስ የሰረጸው ከአብ ብቻ ነው" በሚለው በሚያግባባት የጋራ ነጥብ ላይ "ኦርቶዶክስ" የሚል አቋም ያዙ። "ኦርቶዶክስ" ὀρθόδοξος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኦርቶ" ὀρθός ማለትም "ትክክለኛ" እና "ዶክሳ" δόξα ማለትም "አመለካከት" ከሚል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "ትክክለኛ አመለካከት" ማለት ነው፥ "ኦርቶዶክስ"የሚለውን ቃል ከጥንት ጀምረው የካቶሊክ ኤክሌሲያ፣ የሶርያ፣ የኦሬንታል እና የምሥራቃዊ ቤተክርስቲያን ለዶግማ የሚጠቀሙበት ስም ነው። ኢንሻሏህ የኤክሌሲያ ታሪክ በክፍል ሦስት እንቋጫለን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
4261Loading...
38
◆▮ውይይት▮◆ "የመጽሐፍት መጠበቅ" ቁርአን ወይስ ባይብል ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ሙሐመድ አበባው
3983Loading...
39
◆▮ውይይት▮◆ "የመጽሐፍት መጠበቅ"   ቁርአን ወይስ ባይብል ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ሙሐመድ አበባው
2 3268Loading...
40
ውይይቱ ጀምሮል https://vt.tiktok.com/ZSY8BWVvM/ ቲክቶክ የማትጠቀሙ https://t.me/path_of_the_prophets
3691Loading...
ምእመናን ግን በጀነት ስላሉ ከዚያ ቀን ስቃይ ተቤዥተዋል። ከእነዚያ ከካዱት ግን ቤዛ አይወሰድም፥ ለእነዚያም ለበደሉት ከሐድያን በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፦ 57፥15 «ዛሬም ከእናንተ ቤዛ አይወስድም፥ ከእነዚያ ከካዱትም አይወሰድም፡፡ መኖሪያችሁ እሳት ናት፥ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» ይሏቸዋል፡፡ فَالْيَوْمَ لَا يُؤْخَذُ مِنكُمْ فِدْيَةٌ وَلَا مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ مَأْوَاكُمُ النَّارُ ۖ هِيَ مَوْلَاكُمْ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ 39፥47 ለእነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፡፡ وَلَوْ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُ مَعَهُ لَافْتَدَوْا بِهِ مِن سُوءِ الْعَذَابِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ይህቺ የካፊር ነፍስ ከነፍስ ምንንም ቤዛ የማይያዝበትን ቀን ተጠንቀቁ! እንግዲህ ቤዛ፣ ምልጃ፣ ወዳጅነት የሌለበት ቀን የተባለው ከዐውድ እና አጠቃላይ ከቁርኣን መልእክት አንጻር ለከሓዲ በዳዮች ብቻ ነው። የፍርዱ ቀን ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ምልጃ ያረጋል፥ የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ሰው ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 402 አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው የአሏህ ነቢይም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ጸሎት ያረጋል፥ በትንሳኤ ቀን የእኔ ጸሎት ለኡመቴ ምልጃ ነው*። عَنْ قَتَادَةَ، حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ دَعَاهَا لأُمَّتِهِ وَإِنِّي اخْتَبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لأُمَّتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏”‏ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41 አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏ ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
👍 2
ምልጃ የሌለበት ቀን በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ "ምልጃ" ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፥ እነርሱም፦ ፨አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣ ፨ሁለተኛው የሚማልደው አማላጅ እና ፨ሦስተኛ የሚማለድለት ተመላጅ ናቸው። አሏህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፥ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱት አማላጆች ደግሞ መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው፦ 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ "ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም" የሚለው ይሰመርበት! ዐውደ ንባቡ ስለ መላእክት እያወራ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የሚማለድላቸው ተመላጆች ደግሞ አሏህ ዘንድ ቃል ኪዳን የያዙት አማንያን ናቸው፦ 34፥23 ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ 19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 20፥109 በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا "በዚያ ቀን" የሚለው የፍርዱ ቀን ሲሆን በዚያን ቀን አሏህ የፈቀደላቸው መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለምዕመናን ያማልዳሉ። ነገር ግን ለኩፋሮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፦ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع 2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ "ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን" የፍርዱ ቀን ሲሆን ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለው ለኩፋሮች ስለሆነ ዐውዱ ላይ "ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው" በማለት ይናገራል። ያ የፍርዱ ቀን እነርሱም ከአሏህ እርዳታ የማይረዱበትን እና ምልጃን የማይቀበሉባት ቀን ነው፦ 2፥48 ነፍስም ከነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፣ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፣ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝበትን፣ እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡ وَاتَّقُوا يَوْمًا لَّا تَجْزِي نَفْسٌ عَن نَّفْسٍ شَيْئًا وَلَا يُقْبَلُ مِنْهَا شَفَاعَةٌ وَلَا يُؤْخَذُ مِنْهَا عَدْلٌ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ "የማይቀበሉ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በግስ መደብ የተጠቀሱት እና "እነርሱ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በስም መደብ የተጠቀሱት በዳዮቹ ከሓዲዎች እንጂ ምእመናንን አይጨምርም፥ በፍርዱ ቀን አሏህ የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሙእሚን ቢኾን እንጅ ለከሓዲ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም። ኩፋሮች የትንሳኤ ቀን፦ "በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ? ተብለው ሲጠየቁ፦ "ከሰጋጆቹ አልነበርንም፣ ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፣ ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፣ በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን" ይላሉ። የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፦ 74፥48 የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" የተባለው አሁንም ለኩፋሮች እንጂ ለሙእሚን በፍጹም አይደለም። "ሑላህ" خُلَّة ማለት "ወዳጅነት" ማለት ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ማለት ደግሞ "ወዳጅ" ማለት ነው፥ በዚያ ቀን ኩፋሮች አንዱ ለሌላው ጠላት ነው፦ 43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ "ወዳጆች" ለሚለው የገባው ቃል "አኺላእ" أَخِلَّاء ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ" የሚለው ይሰመርበት! አሏህን ፈሪዎች ምእመናንማ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይወዳጃሉ፡፡ የእነዚያም ወዳጅነት አማረ፦ 4፥69 አላህን እና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَـٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَـٰئِكَ رَفِيقًا ስለዚህ "ምልጃም የሌለበት ቀን" የተባለው "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" በተባለበት ዐውድ ከሆነ እና ለምእመናን ምልጃ ሆነ ወዳጅነት ካላቸው ምልጃ እና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ለኩፋሮች ነው፥ የፍርዱ ቀን ለኩፋሮች ቤዛ የሌለበት ቀን ነው። ሙጅሪም ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፥ ቅሉ ግን ለእነርሱ ቤዛ የሌለበት ቀን ስለሆነ ከእሳት ቅጣት አይቤዥም፦ 70፥11 ዘመዶቻቸውን ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
Mostrar todo...
የአሏህ መታየት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ የትንሣኤ ቀን ምእመናን በጀነት ውስጥ ይሆናሉ፥ ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ በጀነት ውስጥ ያለው ተጨማሪ መንፈሳዊ ጸጋ አሏህን ማየት ነው፦ 50፥35 ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ”እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ”፡፡ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌۭ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 354 ሱሀይብ እንደተረከው፦ "ነቢዩም’ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነዚያ የጀናህ ባለቤቶች ጀናህ በሚገቡ ጊዜ የተከበረው እና ከፍ ያለው አሏህ፦ "ጭማሪ እንድሰጣችሁ ትፍልጋላችሁን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ ፊታችንን አላበራህምን? ጀናትንስ አላስገባከንምን? ከእሳትስ አላዳንከንምን? ይላሉ። ከዚያ እርሱ ግርዶሹን ያነሳል፥ ለእነርሱ የወደደው አሸናፊው እና ክብራማ የሆነውን ከጌታቸውን ፊት በስተቀር ለእነርሱ ምንም ነገር በእነርሱ ዘንድ የለም"። عَنْ صُهَيْبٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا دَخَلَ أَهْلُ الْجَنَّةِ الْجَنَّةَ - قَالَ - يَقُولُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى تُرِيدُونَ شَيْئًا أَزِيدُكُمْ فَيَقُولُونَ أَلَمْ تُبَيِّضْ وُجُوهَنَا أَلَمْ تُدْخِلْنَا الْجَنَّةَ وَتُنَجِّنَا مِنَ النَّارِ - قَالَ - فَيَكْشِفُ الْحِجَابَ فَمَا أُعْطُوا شَيْئًا أَحَبَّ إِلَيْهِمْ مِنَ النَّظَرِ إِلَى رَبِّهِمْ عَزَّ وَجَلَّ ‏"‏ ‏.‏ የምእመናን ፊቶች በትንሣኤ ቀን አብሪዎች ናቸው፥ ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፦ 75፥22 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ 75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ 10፥26 ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገር እና ”ጭማሪም አላቸው"። ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፥ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ ٱلْحُسْنَىٰ وَزِيَادَةٌۭ ۖ وَلَا يَرْهَقُ وُجُوهَهُمْ قَتَرٌۭ وَلَا ذِلَّةٌ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ በተቃራኒው የከሓዲያን ፊቶች በትንሣኤ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፥ ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። ምክንያቱም እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፦ 75፥24 ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ 80፥40 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አለባቸው። وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ 80፥41 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ 80፥42 እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ከእምነቸው በኋላ የካዱ እና ይክዱ በነበሩት ነገር ቅጣትን የሚቀምሱ ናቸው፥ እነርሱ በትንሣኤ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፦ 3፥106 ፊቶች የሚያበሩበትን ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን አስታውስ፡፡ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ» ይባላሉ፡፡ يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ اسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَانِكُمْ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ 84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ አምላካችን አሏህ በዛቱ ከፍጥረት ውጪ ቢሆንም ምእመናን በጀነት በዓይናቸው ሳያካብቡት እርሱ በሚፈልገው መልኩ ያዩታል። ፍጡራን እርሱን በማየት አያካብቡትም፥ እርሱ ግን ሁሉን ተመልካች ስለሆነ ሁሉንም ያካብባል፦ 6፥103 ዓይኖች አያካብቡትም፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያካብባል፡፡ እርሱም ርኅራኄው ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ "አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለት "ረቂቁ" ማለት ሲሆን አሏህ በፍጡራኑ ዓይን የማይከበብ ረቂቅ ነው፥ እኔ ለማወቅ የሚታወቅ ነገር፣ ለማየት ብርሃን፣ ለመስማት ድምፅ፣ ለመታየት አካል ያስፈልገኛል። አሏህ ግን ከማንም ከምንም ፍጥረት ጋር ስለማይመሳሰል ፍጥረት ሳይኖር ፍጥረቱን የሚያውቅ፣ በጨለማ ውስጥ ያሉትን የሚያይ፣ በልብ የሚንሾካሸኩትን የሚሰማ፣ ለምእመናን በትንሳኤ ቀን ስይካበብ በመገለጥ የሚታይ ነው፦ 42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ እሩቅ ሳንሄድ በባይብል አንዱን አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፥ እርሱም፦ "ፊቴን ማየት አይቻልህም" ብሏል፦ 1 ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው "ለማይታየውም" ለዘመናት ንጉሥ ምስጋና እና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን! አሜን። 1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም። ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ "ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም" አለ። አንዱን አምላክ አንድ ሰው እንኳ ባያየው እና ሊያይ ባይቻለው ባሮቹ ግን በትንሣኤ ቀን በትንሣኤያዊ ዓይን ፊቱን ያያሉ፦ ኢዮብ 19፥27 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል። ራእይ 22፥3 ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ። አምላካችን አሏህን በትንሳኤ ቀን እርሱን ከሚያዩት ምእመናን ያርገን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ሳትሳደቡ በማስረጃ መልሱ 1ኛ ነገሥት 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም። ⁵ ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ። ⁶ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። ደሞ ሌሎችንም ጣኦት ያስመልክ ነበር “በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ።” — 1ኛ ነገሥት 11፥7
Mostrar todo...
04:04
Video unavailableShow in Telegram
የታመማችሁ ሰዎች ብስራት🌹💧 አንድ ሙስሊም ቢታመም እሳት ከወርቅና ከብር ቆሻሻን እንደሚያስወግድ ሁሉ በበሽታው የተነሳ አላህ ኃጢአቱን ያስወግድለታል።” «አስ–ሲልሲለቱ አስ– ሰሒሃ –714» ◍እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
Mostrar todo...
👍 3
የኢየሱስ እናት መርየም ለእናቷ አንድና የስለት ልጅ ብትሆንም በአባቷ ግን ወንድምና እህት እንዳላት ነገረ-ማርያም"Marylogy" ይነግረናል፣ ባይብልም ማርያም እህት እንዳላት ይናገራል፦ ዮሐንስ 19፥25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ፦ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ *የእናቱም እኅት*፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። በታሪክ፣ በፔንታተች ሆነ በታልሙድ መጻሕፍት የሙሴና የአሮን አባት "እንበረም" עַמְרָם ሲሆን እናታቸው ደግሞ "ዮከብድ" יוֹכֶ֤בֶד ናት፣ ይህን ከራሳችሁ መጽሐፍ ቅሪት ማየት ይቻላል፦ ዘጸአት 6፥20 *እንበረምም עַמְרָם የአጎቱን ልጅ ዮካብድን יוֹכֶ֤בֶד አገባ፥ “አሮንና ሙሴንም” ወለደችለት*፤ ነገር ግን የሙሴ እህት ማርያም እና የኢየሱስ እናት ማርያም ሁለት የተለያዩ ሴቶች ናቸው። ይህ በቀላለ እንድትረዱት አንድ ናሙና ከባይብል ልስጣችሁ፣ "የጌት ሰው ጎልያድን" የገደለው ማን ነው ዳዊት ወይስ ይሽቢብኖብ? እዚህ አንቀጽ ላይ የጌት ሰው ጎልያድን ዳዊት እንደገደለው ይናገራል፦ 1ኛ ሳሙኤል 17፥4 ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር *የጌት ሰው ጎልያድ*፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ። 1ኛ ሳሙኤል 17፥50 *ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ*፤ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም። እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ የጌት ሰው ጎልያድን ይሽቢብኖብ እንደገደለው ይናገራል፦ 2ኛ ሳሙኤል 21፥19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የቤተ ልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን *የጌት ሰው ጎልያድን* ገደለ። አንዱን ክርስቲያን ተወያይ ይህን ጥያቄ ሳቀርብለት "ወሒድ ምን ነካህ ደህና ሰው አልነበርክም እንዴ? ዳዊት የገደለው ጎልያድ እና ይሽቢብኖብ የገደለው ጎልያድ እኮ በተለያየ ዘመን የኖሩ ሁለት ግለሰቦች ናቸው" አለኝ፣ እውነት ነው የአይሁድ ሆነ የክርስቲያን ስመ-ጥርና ዝነኛ ኮሜንታተሮች በተለያዩ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ግን በአንድ ቦታ በጌት ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፣ ታዲያ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው ነገሩ፣ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ይሉሃል እንደዚህ ነው። ሲቀጥል ወንድምና እህት የግድ የአብራክ ክፋይ የሚለውን አያሲዝም። ሉጥ የኢብራሂም የወንሙ ልጅ ሲሆን ኢብራሂም ለሉጥ ደግሞ አጎት ነው፣ ነገር ግን ሉጥ ለኢብራሂም ወንድም ተብሏል፣ ያ ማለት የአንድ ቤተሰብ መሆንን ካሳየ የሙሳ ወንድም አሮንና መርየም የሌዊ ቤተሰብ ስለሆኑ ወንድም አሊያም እህት ቢባሉ ችግር የለውም፦ ዘፍጥረት14፥12 በሰዶም ይኖር የነበረውን *የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን* ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ። ዘፍጥረት14፥14 አብራምም *ወንድሙ* እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
👍 3
ነጥብ ሁለት "የሃሩን እኅት" አምላካችን አላህ በዒሣ እናት በመርየም ዘመን የነበሩት የመርየም ዘመዶች የዒሣን እናት መርየምን "የሃሩን እኅት" እንዳሏት ተርኮልናል፦ 19፥28 *«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት*፡፡ يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا "አሏት" የሚለው ይሰመርበት፤ ባዮቹ የመርየም ዘመዶች ቢሆኑም አላህ ይህንን ተርኮልናል። የኢሳን እናት መርየም የአባቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "ኢያቂም" יְהוֹיָקִים በቁርኣን ደግሞ "ዒምራን" عمران ነው፤ የእናቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "አና" חַנָּה በተፍሲር ደግሞ "ሐናህ" حنة ነው፣ ኢያቄም የማርያም አባት ስለመሆኑ ከቁርአን ማየት ይቻላል፦ 3፥35 *የዒምራን ባለቤት (ሐና)* «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን ፅንስ ከሥራ ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ 66፥12 *የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ*፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِين ቁርኣን ላይ የመርየም እናት ስሟ ባይጠቀስም ማንነቷ ተገልጻል። ነገር ግን ባይብል ላይ የመርየም እናት እና አባት ስም ሆነ ማንነት አልተገለጸም። ስለዚህ ከመነሻው በሌለ ነገር ሁለት የተለያዩ ታሪካትን አዛብቶ ግጭት መፍጠር አይቻልም፣ ታዲያ ዒሣ እናት የመርየም ወንድም ሃሩን ማነው? ስንል የስም ሞክሼ እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ይህንን ከነብያችን"ﷺ" መረዳት ይቻላል፦ ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 38, ሐዲስ 13 አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ እንደተረከው፦ *"ወደ ነጅራን በመጣው ጊዜ የነጅራን ክርስቲያኖች፦"የሃሩን እኅት ሆይ! የሚል ቀርተክልናል፤ ሙሳ ከዒሣ ብዙ ጊዜ በፊት የነበረ ነው" ብለው ጠየቁኝ። እኔም ወደ አላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስመለስ ስለዚህ ጉዳይ ጠየኳቸው፣ እሳቸውም አሉ፦ "የድሮ ሰዎች ከራሳቸው በፊት ከነበሩት የነቢያቶች ስሞች ከነቢያቱ ህልፈት በኋላ ይጠቀሙ ነበር*። عَنِ الْمُغِيرَةِ بْنِ شُعْبَةَ، قَالَ لَمَّا قَدِمْتُ نَجْرَانَ سَأَلُونِي فَقَالُوا إِنَّكُمْ تَقْرَءُونَ يَا أُخْتَ هَارُونَ وَمُوسَى قَبْلَ عِيسَى بِكَذَا وَكَذَا ‏.‏ فَلَمَّا قَدِمْتُ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سَأَلْتُهُ عَنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَمُّونَ بِأَنْبِيَائِهِمْ وَالصَّالِحِينَ قَبْلَهُمْ ከነቢያችን"ﷺ" ንግግር የምንረዳው የሙሳ ወንድም ሃሩን እና የዒሳ እናት የመርየም ወንድም ኃሩን የስም መመሳሰል እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ናቸው፣ የእሳቸው ዘመድና ባልደረባም ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." ይህን አንቀጽ ሲፈስረው፦ "አሮን የማርያም ግማሽ ወንድምና የአባቷ ልጅ ነው" በማለት አስቀምጦታል። ነጥብ ሦስት "ኢኽዋህ" “ኢኽዋህ” إِخْوَة ማለት “ወንድማማች እና እህትማማችነት" ማለት ነው፤ አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው፦ 49፥10 *ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው*፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ በነብያችን"ﷺ" ሐዲስ የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ ሁለት የስም ሞክሼ መሆኑ ተሰምሮበታል፤ ነገር ግን የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ አንድ ማንነት ናቸው ቢባል እንኳን አሁንም ችግር የለውም። ምክንያቱም አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው በሚል ቀመርና ስሌት መረዳት ይቻላል። በትውፊት መርየም የሌዊ ዘር ናት፤ ሃሩንም የሌዊ ዘር ነው፤ ስለዚህ ሁለቱም ወንድምና እህት መሆን ይችላሉ፤ "አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን እና "ኡኽት" أُخْت ማለት ደግሞ "እኅት" ማለት ነው፤ ቃሉ የግድ አብራካዊ ወንድምና እህት ብቻ አያመለክትም። ምክንያቱም "ኡኽት" أُخْت የሚለው ቃል "ሚስል" مِثْل ማለትም "ቢጤ" በሚል ይመጣል፦ 43፥48 ከተዓምርም አንዲትንም አናሳያቸውም እርሷ *ከብጤዋ* በጣም የበለጠች ብትኾን እንጅ፡፡ ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው፡፡ وَمَا نُرِيهِم مِّنْ آيَةٍ إِلَّا هِيَ أَكْبَرُ مِنْ أُخْتِهَا ۖ وَأَخَذْنَاهُم بِالْعَذَابِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ 7፥38 አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን *ብጤዋን* ትረግማለች፡፡ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا "ብጤዋ" ለሚለው የገባውን ቃል "ኡኽቲሃ" أُخْتِهَا አንዳንድ የኢንግሊሽ ትርጉም "እህትዋን"its sister" በማለት አስቀምጠውታል፦ 43፥48 And We showed them not a sign except that it was greater than *its sister*, and We seized them with affliction that perhaps they might return [to faith]. Sahih International ማጠቃለያ ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ በዐረቢኛ “መርየም” مَرْيَم‎ ፣ በዐረማይክ “ማርአም” ܡܪܝܡ‎ ፣ በግሪክ “ማርያ” mαρία ሲሆን የስሙ መሰረት የዕብራይስጡ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ነው፤ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “መር” מר ማለት “ጠብታ” ማለት ሲሆን “የም” ים ደግሞ “ባህር” ማለት ነው፤ በጥቅሉ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ማለት “የባህር ጠብታ” ማለት ነው። በባይብል ማርያም በሚል ስም የሚጠሩ ሴቶች ስምንት ሲሆኑ እነርሱም፦ 1ኛ. የሙሴ እህት፦ ዘጸአት 15፥21 2ኛ. የዕዝራ ልጅ፦ 1ኛ ዜና 4፥17 3ኛ. የኢየሱስ እናት፦ ማቴዎስ 1፥18 4ኛ. መቅደላዊት፦ ሉቃስ 8፥2 5ኛ. የአልዓዛር እህት፦ ዮሐንስ 11፥1 6ኛ. የቀለዮጳም ሚስት፦ ዮሐንስ 19፥25 7ኛ. የማርቆስ እናት፦ 12፥12 እና 8ኛ. የሮሜ ማርያም፦ ሮሜ 16፥6 ናቸው።
Mostrar todo...
👍 3
ሃሩን ማን ነው? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا ሚሽነሪዎች፦ ቁርኣን ከባይብል ታሪክ ጋር ይጣረሳል" ብለው ሱሪ ባንገት ሊያስገቡ ሲቃጣቸው ይታያል፣ ከሚተቹበት መወዛገብ አንዱ፦ "ቁርአን የሙሴን ወንድ አሮንን የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም ያደርጋል" የሚል ግራጫ ውሸት ይዋሻሉ፥ ይለቃሉ። በኢስላም ላይ ስትቀጥፉ ህሊናን ከሚያሳድድ ጥያቄ አታመልጡም። ታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔው ሎሬትዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፦ "የሰው ልጅ ከሁለት ነገር ይማራል፦ አንዱ “ሀ” ብሎ “በሳር” ሲሆን ሁለተኛው “ዋ” ብሎ “በአሳር” ነው" ይለናል። ሚሽነሪ ሃያሲ ሂስ ከመስጠት በፊት “ሀ” ብሎ “በሳር” ከቁርአን መማር አሊያም “ዋ” ብሎ “በአሳር” ተነግሮ ከማያልቅ ታፍሶ ከማይዘለቅ ከዲነል ኢስላም ዕውቀት መማር ነው። መዋተቱና መቃተቱን ትታችሁ ጓዛችሁን ሸክፋችሁ ለመማር ኑ። መቆዘም አያዋጣም። ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተወዛገባችሁ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናያለን፣ "ሃሩን" هَارُونَ ማለት በአማርኛችን "አሮን" ተብሎ በቁርአን የተጠቀሱ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች አሉ፣ እነርሱም አንዱ የሙሴ ወንድም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም፣ ይህን ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦ ነጥብ አንድ "የሙሳ ወንድም ሃሩን" ሙሳ አንደበተ ኮልታፋ እና ተብታባ ስለነበር ወንድሙ በእርሱ ፋንታ እንዲናገር ወደ አላህ ዱዓ አደረገ፦ 20፥29 «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي 20፥30 *«ሃሩንን ወንድሜን*፡፡ هَارُونَ أَخِي 20፥32 *«በነገሬም አጋራው*፡፡ وَأَشْرِكْهُ فِي أَمْرِي 28፥34 *«ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና*፡፡» وَأَخِي هَارُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّي لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِيَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِي ۖ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ ሙሳ መልእክተኛ ነው፤ ሃሩን ደግሞ ነቢይ ነው፤ ነገር ግን "በነገሬም አጋራው" ብሎ በጠየቀው መሰረት ተውራት የተባለውን ሪሳላ ስለተጋራ መልእክተኛ ተባለ፤ "ከእኔ ጋር ላከው" የሚለው ይሰመርበት፤ ለዛ ነው አላህ ተውራትን ለሙሳ እና ለሃሩን ሰጠናቸው ያለው፦ 21፥48 *ለሙሳ እና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ ሃሩን በራሱ መልእክተኛ አይደለም፤ ግን ነቢይ ሆኖ ሙሳን በመልእክቱ በማስተላለፍ ይረዳዋል፤ አላህ ወደ ሕዝባቸው በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላካቸው፦ 19፥53 *ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ مِن رَّحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا 25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا 23፥45 *ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን*፡፡ ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَارُونَ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ ስለ ነቢዩ ሃሩን በጥቅሉ ይህንን ይመስላል። የሙሳ እና የሃሩን እናት እና አባት አሊያም የቤተሰብ ዝርዝር ስም ሆነ ማንነት ቁርኣን ላይ አልተጠቀሰም።
Mostrar todo...
02:48
Video unavailableShow in Telegram
በድብቅ አላህን ማመጽ💧 «ሰዎች እንዲያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህንም ስትሆን አትስራው !!» (አስሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 1055) ◍እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
Mostrar todo...
👍 1
02:15