cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የሰለምቴዎች ቻናል

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 027
Suscriptores
+1424 horas
+707 días
+23230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

📣       📢      📣       📢       📣       📢 አሰላሙዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ ሙስሊሞች ሆይ! እነሆ የአል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ "አል ሙኒር በገጠር" ለተሰኘው ፕሮጀክት አለም-አቀፍ  የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በ MAY 18/2024 በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት (ከኢሻ ሰላት በኋላ) እንደሚከናወን እያበሰርን ለፕሮግራሙ መሳካት በያላችሁበት ዱዐ እንድታደርጉና ከዚህ በታች የምንለጥፋቸዉን ማስታወቂያዎች እና በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶች ለዘመድ ወዳጆቻችሁ ታጋሩ ዘንድ በአላህ (ሱ.ወ) ስም እንጠይቃለን። የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ( Facebook, Telegram, WhatsApp, ወዘተ) በመጠቀም በርካታ እህትና ወንድሞች በዚህ ኸይር ስራ ላይ እንዲሳተፉ ሰበብ እንሁን። ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን! አል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ። ዋትስ አፕ ግሩፕ 👇👇👇 https://chat.whatsapp.com/BeWTXzCakK8C7A1BKaQqAr ቴሌግራም ሊንክ 👇👇👇 https://t.me/almuniracademy1 የዞም ሊንክ 👇👇👇 Zoom Meeting https://us02web.zoom.us/j/6138373158?pwd=bFo5ZVFrcUpWbFV5YVNZMDlwZ2piQT09 ሜይ 18 እንገናኝ ሼር ሼር ሼር አድርጉ ባረከላሁ ፊኩም አዳል ለልኸይር ከፋኢሊሂ ነው
Mostrar todo...
Ismail Annuri
Mostrar todo...
◆▮ነቢያት በባይብል▮◆ "ዳዊት (ዳውድ) ጨፋሪ ነበርን?" ◍እኅት ዘሐራ ሙስጥፋ
Mostrar todo...
"ግድያ በባይብል" ◁ አቅራቢ ◍ ወንድም ሳላህ
Mostrar todo...
የአሳማ ሥጋ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ "ኺንዚር" خِنزِير ማለት "አሳማ" ማለት ሲሆን የአሳማ አስተኔ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ ጉንደ እንስሳ "እሪያ" እና "ከርከሮ" ናቸው፥ አሳማ ሴረም ፕሮቲኖችን ስለያዘ ሥጋው በሰውነት ውስጥ የአለርጂን ሂደት የሚያነቃቁ አልቡሚን እና ኢሚውኖ ግሎቡሊን አላቸው። በዚህም ግልጽ ምክንያት አካላችንን በጣም ብዙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ይይዛል፥ በአሳማ የጡንቻ ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ሰው የአሳማ ሥጋ ሲበላ ወደ ልቡ ጡንቻ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ይራቡና በዚህም ለሕይወቱ አስጊ ሁኔታን ያስከትላል። አምላካችን አሏህም ሰውን የሚጎዳው ይህንን የአሳማ ሥጋ መብላት ክልክሏል፦ 2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ 16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋን እና ያንን በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ 6፥145 በላቸው፡- «ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ ወይም ፈሳሽ ደምን፣ ወይም የአሳማ ሥጋን እርሱ ርኩስ ነውና፣ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ قُل لَّا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ "ሐርረመ" حَرَّمَ ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ይህ ክልከላ እኛን ስለሚጎዳን እንጂ አንድ ሰው በረሃብ ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ቢሆን መብላቱ ሙባሕ ነው። ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን"ﷺ ኡማህ ካነሳው ሦስት ነገሮች አንዱ የገተደዱበትን ነገር ነው፦ 2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ 16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ 6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውጪ ያሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች የአሳማ ሥጋ መብላትን ሐላል አርገዋል፥ ቅሉ ግን በባይብልም ቢሆን የአሳማ ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ ዘሌዋውያን 11፥7 እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። ዘዳግም 14፥8 እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፥ ሥጋውን አትብሉ! በድኑንም አትንኩ። "ሥጋውን አትብሉ" የሚለው ክልከላ ይሰመርበት! የእሪያን ሥጋ የሚበሉ ግን በጀሃነም በአንድነት ይጠፋሉ፦ ኢሳይያስ 66፥17 "የእሪያን ሥጋ፣ አስጸያፊ ነገርን፣ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ" ይላል ያህዌህ። የክርስትና እምነት ተከታዮች እነዚህን አናቅጽ ስንሰጣቸው፦ "የእሪያን ሥጋ በአዲስ ኪዳን ተፈቅዷል" ይላሉ፥ ነገር ግን መፈቀዱን የሚያሳይ አንድም ጥቅስ አያመጡም፦ ማቴዎስ 15፥11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው" አላቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥4 እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም"። እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ አንጻራዊ ንግግር እንጂ ወደ አፍ የሚገባ የሚያረክሱ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ ሐራም ናቸው፦ 1 ቆሮ 10፥28 ማንም ግን፦ "ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው" ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ"። ራእይ 2፥14 ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ። የሐዋርያት ሥራ 15፥20 ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰት፣ ከዝሙት ከታነቀም፣ ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ። የሐዋርያት ሥራ 21፥25 አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ነፍሳቸውን እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል። ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ አያካትትምን? ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ የሚጣል የለምን? አይ፦ "ኢየሱስ አያረክስም ያለው እጅ ሳይታጠቡ መብላትን እንጂ እርኩስ ነው የተባሉትን ምግብ አይደለም፥ ጳውሎስ የሚጣል የለም ያለው መልካም ምግብን ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ የአሳማ ሥጋ የተፈቀደበት አንድም ጥቅስ መቼም ልታመጡ አትችሉም። የማታውቁትን ነገር መናገር ዳፋው እና ጦሱ ለራስ ነው፥ ስለዚህ ጨርቄን እና ማቄን ሳትሉ የአሳማ ሥጋ ሐራም መሆኑን ብትቀበሉ ይሻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
ሌላን አትገዙ! በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ ሚሽነሪዎች ኢየሱስ እንደሚመለክ ለማስመሰል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም፥ "በ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" የሚለውን ሐረግ "ለ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" በሚል እያንሸዋረሩ ይረዳሉ ያስረዳሉ። ነገር ግን ጳውሎስ ያስቀመጠው በዚህ መልኩ አይደለም፥ እስቲ ከኢሳይያስ ኃይለ-ቃል እንጀምር! ፈጣሪ፦ "ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል" እያለ ይናገራል፦ ኢሳይያስ 45፥23 ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል። "ለእኔ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ለ" እና "በ" ሁለት የተለያዩ መስተዋድዶች ናቸው፦ ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ። "በ" የሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ ያለ መስተዋድድ በኢየሱስ ስም ለአብ መንበርከክን ያሳያል እንጂ ለኢየሱስ መንበርከክን አያሳይም። ለምሳሌ፦ ኤፌሶን 5፥20 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን እና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ። አምላክና አባት የተባለው እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ይመሰገናል፥ አሁንም ኢየሱስ "በ" በሚል መስተዋድድ አስመላኪ እንጂ "ለ" በሚል መስተዋድድ ተመላኪ አይደለም፦ ቆላስይስ 3፥17 እግዚአብሔር አብን "በ"-እርሱ እያመሰገናችሁ። የሚመሰገነው አብ በማን ነው? ስንል "በ"-ኢየሱስ ነው። "በ" የሚለው መስተዋድድ አስምሩበት! እግዚአብሔር አብ "በ"-ኢየሱስ ይመሰገናል፦ ሮሜ 1፥8 አምላኬን "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ። ጳውሎስ አምላኩን እግዚአብሔርን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመሰግናል። ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ የምስጋናን መሥዋዕት የሚቀርበው "ለ"እግዚአብሔር "በ"ክርስቶስ እንደሆነ ይናገራል፦ ዕብራውያን 13፥15 እንግዲህ ዘወትር "ለ"-እግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ "በ"-እርሱ እናቅርብለት። "በ" አስመላኪ ሲሆን "ለ" ደግሞ ተመላኪ ነው። ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር ክብር የሚሰጠው "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፦ ሮሜ 7፥25 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን "ለ"-እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። "በ" የሚለውን "ለ" ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ "በ"-ጽዮን" የሚለውን "ለ"-ጽዮን" ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦ መዝሙር 65፥1 አቤቱ "በ"-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון ዋናው ነጥብ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክ ለኢየሱስ ስም ሳይሆን በኢየሱስ ስም ለፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አስመላኪ እንጂ ተመላኪ አይደለም፥ ለፈጣሪው ተንበርክኮ የሚያመልክ አካል ተመልሶ ተመላኪ አይሆንም። ኢየሱስ እራሱ በጉልበቱ ተንበርክኮ እና በፊቱ ተደፍቶ ወደ ፈጣሪ ይጸልይ ነበር፦ ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀ እና ሲጸልይ። ሉቃስ 22፥41 ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም። ሸብረክ እና ብርክክ ብሎ ለፈጣሪው ሡጁድ የሚወርድ ኢየሱስ እራሱ አምላኪ መሆኑን ይህ ጥቅስ ጉልኅ ማሳያ ነው። እናንተም እንደ ኢየሱስ አሏህን እንጂ ሌላን አትገዙ፦ 11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
👍 2
◁▮ወይይት▮▷ "ቃልም ሥጋ ሆነ?" ◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም 🅅🅂 ◍ ወገናችን መሰሞ
Mostrar todo...
👍 2
ኢልቲፋት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 11፥1 አሊፍ ላም ራ! ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት በዓረፍተ ነገር በማዋቀር ረገድ “ነሕው” نَحْو ጉልኅ ሚና ሲኖረው “በላጋህ” بَلَاغَة ደግሞ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት የዓረፍተ ነገሩን መልእክት በመግለጽ ጉልኅ ሚና አለው፥ “በላጋህ” بَلَاغَة ማለት “የንግግር ስልት”rhetoric” ማለት ነው። ቅዱስ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፥ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው አሏህ ዘንድ የተወረደ ነው፦ 11፥1 አሊፍ ላም ራ! ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ በበላጋህ ደርሥ ውስጥ ኢልቲፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። "ኢልቲፋት" اِلتِفَت የሚለው ቃል "ለፈተ" لَفَتَ ማለትም "ዞረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መዞር" ማለት ነው፥ በቁርኣን ውስጥ ያሉት ሰዋሰዋዊ ዙረት"grammatical shift" በጥቅሉ "ኢልቲፋት" اِلتِفَت ይባላሉ። አምላካችን አሏህ ሰዋሰዋዊ ዙረት የሚጠቀመው የቁርኣንን መልእክት ትኩረት እንድንሰጥ እና በቃላቱ እንድናሰላስል ነው፥ ለምሳሌ በሙተከለም ደረጃ ከሙፍረድ አነጋገር ወደ ተዐዚም አነጋገር ይዞራል፦ 70፥40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ "እምላለው" በሚል ነጠላ ንግግር ጀምሮ "እኛ" በሚል የግነት እኛነት ይዞራል፥ በተመሳሳይ "አርሠልና" أَرْسَلْنَا በሚል ተዐዚም አነጋገር ጀምሮ "አና" أَنَا በሚል ሙፍረድ አነጋገር ይዞራል፦ 21፥25 ከአንተ በፊትም፦ "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ በተጨማሪም በሦስተኛ መደብ "አርሠለ" أَرْسَلَ ብሎ ተናግሮ በሦስተኛ መደብ የሚናገርለት ማንነት እራሱ እንደሆነ ለማሳየት በመጀመርያ መደብ "ሡቅና" سُقْنَا በማለት ያዞረዋል፦ 35፥9 አላህም ያ ነፋሶችን የላከ ነው፥ ደመናዎችንም ትቀሰቅሳለች፤ ወደ ሙት አገርም እንነዳዋለን፡፡ وَاللَّهُ الَّذِي أَرْسَلَ الرِّيَاحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَسُقْنَاهُ إِلَىٰ بَلَدٍ مَّيِّتٍ እንዲሁ በመጀመሪያ መደብ "ቁልና" قُلْنَا ብሎ ተናግሮ በመጀመሪያ መደብ የሚናገርለት ማንነት እራሱ እንደሆነ ለማሳየት በሦስተኛ መደብ "አሏህ" اللَّهُ በማለት ያዞረዋል፦ 2፥73 «በድኑን በከፊሏም ምቱት» አልን፥ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል፡፡ فَقُلْنَا اضْرِبُوهُ بِبَعْضِهَا ۚ كَذَٰلِكَ يُحْيِي اللَّهُ الْمَوْتَىٰ وَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" "በል" በሚል ትእዛዛዊ ቃል ሲልካቸው፦ "እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ" በሚል በመጀመሪያ መደብ እንዲናገሩ በተናገረበት አንቀጽ ላይ "የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ" በማለት በሦስተኛ መደብ ያዞረዋል፦ 7፥158 በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ በአላህ እና በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡» قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ እንደዚህ የማዞር ሰዋስው በባይብል ውስጥም በጥቂቱ አለ፥ ለምሳሌ ያህዌህ በመጀመሪያ መደብ፦ "ያህዌህ አምላክህ እኔ ነኝ" ካለ በኃላ እራሱን በሦስተኛ መደብ፦ "የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ! ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና" ብሎ ይናገራል፦ ዘጸአት 20፥2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ያህዌህ አምላክህ እኔ ነኝ። ዘጸአት 20፥7 የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ! ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። ያዕቆብ በመጀመሪያ መደብ፦ "እንድነግራችሁ" ካለ በኃላ እራሱን በሦስተኛ መደብ፦ "አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ" ብሎ ይናገራል፦ ዘፍጥረት 49፥1 ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ "በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። ዘፍጥረት 49፥2 እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ፥ ስሙም፤ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። ኢየሱስ በመጀመሪያ መደብ፦ "በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ" ካለ በኃላ እራሱን በሦስተኛ መደብ፦ "የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል" ብሎ ይናገራል፦ ሉቃስ 12፥8 እላችሁማለሁ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል። ትልም እና ሕልም ለይተው የማያውቁ ሚሽነሪዎች ቁርኣንን የጦስ ዶሮ ለማድረግ ከመቸኮል መጽሐፋቸውን በቅጡ ቢያነቡ መልካም ነው፥ እንዲህ ሲነጻጸር "የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ" ማለታቸው አይቀሬ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...