cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

"ቃለ እግዚአብሔር "

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16 "ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
8 308
Suscriptores
+424 horas
+47 días
-1430 días
Archivo de publicaciones
የያዘውን በትር ከእጁ ተቀብለው ራሱን መቱት፤ ነገር ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን፤ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እ ባብ ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን ቀንዶቹን አጠፋልን) በማለት አስተምረዋል፡፡ ክብር ይግባውና ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ ጌታችንን በመኻከል አድርገው ሰቅለውታል (ማቴ ፳፯፥፴፰፤ ማር ፲፭፥፳፯፤ ሉቃ ፳፪፥፴፫፤ ዮሐ ፲፱፥፲፰)፡፡ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት ነው በተጨማሪም ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕ ፶፫፥፲፪ ላይ “ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምስጢሩ ግን በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር (ማቴ ፳፭፥፴፫፤ ራእ ፩፥፯)፡፡ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ውስጥ የኸኑት ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳና በርዜዳ ስለዚኽ ነገር ሲገልጹ “ወሰቀልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ገጹ መንገለ ምሥራቅ ወእዴሁ ዘየማን መንገለ ደቡብ ወእዴሁ ዘፀጋም መንገለ ሰሜን…” (ጌታችን ኢየሱስንም በዕንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት፤ ፊቱን ወደ ምሥራቅ ቀኝ እጁን ወደ ደቡብ፤ ግራ እጁን ወደ ሰሜን አድርገው ሰቀሉት…ከርሱም ጋር ኹለቱን ወንበዴዎች አንዱን በቀኝ አንዱን በግራው በመኻከላቸው ጌታችን ኢየሱስን አድርገው ሰቀሉ፤ ሕዝቡም ርሱም እንደነርሱ ወንበዴ ነው ይሉት ዘንድ ሰቀሉት፤ ርሱ ግን ወድዶ ከወንበዴዎች ጋር በዕንጨት መስቀል ተሰቀለ፤ ልዑላን መላእክት ፈርተው በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉለት ርሱ በሚሰቅሉት ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ (ፊልጵ ፪፥፲፤ ራእ ፬፥፲-፲፩)፤ በከሃሊነቱ ሰማይና ምድርን ያጸና ከግርማውም የተነሣ ሰማያትና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ርሱን ደካማ ዕንጨት ተሸከመው (ምሳ ፴፥፬፤ ኢሳ ፵፪፥፭)፤ ርሱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱ ያስታርቀን ዘንድ ከሰማይ ዝቅ ብሎ ከምድር ከፍ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ርሱም ስለእኛ በሥጋው በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ከኀጢአታችን ይለየን ዘንድ በቸርነቱ ያድነን ዘንድ ተሰቀለ (፩ጴጥ ፪፥፳፬)፤ ርሱ ግን ሰማያትን ይቀድስ ዘንድ በአየር ያሉ አጋንንትን ያወርዳቸው ዘንድ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ሙሴ አርዌ ብርትን በገዳም እንደ ሰቀለው ርሱም በዕንጨት ላይ ተሰቀለ ፤ በርሱ ያመነ ኹሉ ይድናል እንጂ እንዳይጐዳ የክብር ባለቤት ርሱ ግን ስለ እኛ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ (ዮሐ ፫፥፲፬-፲፭)፤ አውቀውስ ቢኾን የክብር ባለቤት ጌታን ባልሰቀሉት ነበር (፩ቆሮ ፪፥፰)፤ ሰማይ ዙፋኑ ሲኾን ምድርም በእግሮቹ የተረገጠች ስትኾን ስለኛ በዕንጨት ተሰቀለ (ኢሳ ፷፮፥፩)፤ ርሱ ግን ተጠብቆለት ስላለ ስለ ደስታው የመስቀልን መከራ ንቆ አቃልሎ ተቀበለ ኀፍረትንም ናቃት፤ ለተሰቀለው ለርሱ የማይሰግድ ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይኹን (ፊልጵ ፪፥፰-፲፩)፤ ርሱ ግን ስለ ዓለሙ ደኅንነት በማእዝነ ምድር ወደ ላይ ወደ ታች ወደ ግራ ወደ ቀኝ ኾኖ እንደ መጋረጃ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ፤ እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ) በማለት በስፋት የነገረ ስቅለቱን ምስጢር አስተምረዋል፡፡ በመስቀል ሲሰቀልም በቀኙ የተሰቀለው ጥጦስ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ይባላል፤ በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ ፀሓይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትኾን፣ ከዋክብት ከብርሃናቸው ሲራቈቱ፣ ድንጋዮች ሲሠነጠቁ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ የምኩራቡ መጋረጃ ወደ ኹለት ወደ ሦስት ሲቀደድ ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ አይቶ አምላክነቱን ተረድቶ ወደ ርሱ ሲለምን በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ሰምቶ “አንተስ ክርስቶስ አይደለኽምን? ራስኽንም እኛንም አድን” ይል ዠመር (ሉቃ ፳፫፥፴፱)፡፡ ያን ጊዜ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ጌታችን ለቤዛ ዓለም የተሰቀለ እውነተኛ የባሕርይ አምላክነቱን ስለተረዳ በግራ የተሰቀለውን “አንተ እንደዚኽ ባለ ፍርድ ሳለኽ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይኽ ግን ምንም ክፋት አላደረገም” ብሎ ከገሠጸው በኋላ ኀጢአት ሳይኖርበት የተሰቀለውን ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን “ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ” (ጌታ ሆይ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ) እያለ ሲለምነው ጌታችንም “እውነት እልኻለኊ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኾናለኽ” ብሎት ደመ ማኅተሙን ሰጥቶታልና ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚኽ መጽሐፉ ላይ፡- “ምስጋና ለአንተ ይገባል፤ የሞትን ፃዕረኝነት (ችንካር) ትሽር ዘንድ ክፋትን የሠራኽ ሳትኾን (ሳትሠራ) በኹለት ሽፍቶች (ወንበዶች) መኻከል የተቸነከርኽ እውነተኛ ኢየሱስ ምስጋና ለአንተ ይገባል” በማለት ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን አመስግኗል (ሉቃ ፳፫፥፴፱-፵፫)፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ . . . .
Mostrar todo...
👍 2
መንፈሳዊ ጉባኤ: Henok: 💦💦የሚገርም ፍቅር💦💦💦 ♥የጌታችን ሕማማት በሊቃውንት♥ : ☞በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት በማዳኑ፣ ዕዉራነ ሥጋን በተአምራት ዕዉራነ ነፍስን በትምህርት በማብራቱ፣ ልሙጻነ ሥጋን በተአምራት ልሙጻነ ነፍስን በትምህርት በማንጻቱ፣ አጋንንትን በማውጣቱ፣ ሙታንን በማንሣቱና ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ መኾኑን በማስተማሩ አይሁድ ከፍተኛ ቅንአት ዐድሮባቸው ጌታን ይዘው የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ይዘውት በመኼድ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ኹሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሐሰት ምስክር ቢፈልጉም ምንም ዐይነት በደል ሊያገኙበት አልቻሉም ነበር፤ በኋላም ሊቀ ካህናቱ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የኾንኽ እንደ ኾነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልኻለኊ” ብሎ ሲጠይቀው፤ ጌታም “አንተ አልኽ፤ ነገር ግን እላችኋለኊ፤ ከእንግዲኽ ወዲኽ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችኊ” በማለት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው በአብ ቀኝ ያለው የአብ የባሕርይ ልጅ የኾነው ርሱን በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ማለት፡- ዓለምን በማሳለፍ ኀይል ባለው ዕሪና በባሕርይ ክብሩ መጥቶ ታዩታላችኊ በማለት ተናገረው (ማቴ 26፡63-64)፡፡ ያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ በንዴት ልብሱን ቀደደ፤ በዘሌ 21፡10 ላይ “በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ ልብሱንም አይቅደድ” በማለት እንዳዘዘው በኦሪት ሥርዐት ካህን በሐዘን ምክንያት ልብሱን ከቀደደና ፊቱን ከነጨ ከሹመቱ የሚሻር ነውና በዚኽም የሊቀ ካህናቱ ኦሪታዊ ክህነት ማለፉን አጠይቋል፡፡ ከዚያ በኋላ ጌታን “ሞት ይገባዋል” በማለት በደረቅ ግንባር ላይ ዐይንን በፈጠረ በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፡- ጌታ በኢሳይያስ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ወኢይትሀከዩ ወሪቀ ውስተ ገጽየ ወኢሜጥኩ ገጽየ እምኀፍረተ ምራቅ” (ዠርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠኊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም) ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ምራቃቸውን ተፍተውበታል፡፡ አንድም አዳምን ዲያብሎስ በገጸ ልቡናው ምራቀ ምክሩን እየተፋ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ካሳ ሊኾን ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፍቶበታል፡፡ ከዚያም ራሱን በዘንግ መቱት “ወኲሉ ርእስ ለሕማም” (ራስ ኹሉ ለሕመም ኾኗል) ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ይደርስ ይፈጸም ዘንድ የሕይወት ራስ ርሱን በዘንግ መቱት (ኢሳ ፩፥፭)፤ አንድም ዲያብሎስ የአዳምን ርእሰ ልቡናውን በበትረ ምክሩ እየመታ ሲኦል አውርዶት ነበርና ካሳ ሊኾን ነበር፤ ከዚያም ፊቱን በሻሽ ሸፍነው “መኑ ውእቱ ክርስቶስ ዘጸፍዐከ” (ክርስቶስ በጥፊ የመታኽ ማነው? ንገረን እስቲ ዕወቀን) እያሉ ዘብተውበታል፤ ይኸውም መተርጒማን እንዳመሰጠሩት አዳምና ሔዋን የአምላክነትን ዕውቀት ዕንወቅ ብለው ሲኦል ወርደው ነበርና ልቡና ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን ኹሉን የሚያውቅ ርሱ ላይ በዚኽ ቃል መዘበታቸው ለአዳምና ለሔዋን ሊክስላቸው ነው፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት የሚያድሩ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የኾኑት ኤልሳቤጥ፣ ቤርዜሊ፣ መልቴዳ በዕለተ ዐርብ በዐይናቸው ያዩትን የጌታን ሕማማት በተናገሩበት ድርሳን ላይ ይኽነን ሲገልጹ፡- “ወሶበ ዘበጥዎ አፉሁ ለእግዚእ ኢየሱስ ሐሙ ከናፍሪሁ ወአስናኒሁ፤ ወውሒዘ ደም ብዙኅ እምአፉሁ…” (ጌታችን ኢየሱስን አፉን በመቱት ጊዜ ከንፈሮቹ ጥርሶቹም ታመሙ፤ ከጌታችንም ከኢየሱስ አፍ ብዙ ደም ፈሰሰ፤ አሕዛብን በሚያጠፋበት ስለቱ (ሥልጣኑ) በኹለት ፊት የኾነ የተሳለ ሰይፍ ከአንደበቱ የሚወጣ ሲኾን (ወደ እኔ ኑ፣ ከእኔ ኺዱ የሚልበት ሥልጣን ገንዘቡ ሲኾን) (ማቴ ፳፭፥፴፩-፵፮)፤ ዳግመኛ አይሁድ ጌታችን ኢየሱስን ፊቱን ፳ ጊዜ በጡጫ መቱት ይኸውም እግዚአብሔር አብን መንፈስ ቅዱስንም በመልክ የሚመስል በባሕርይ የሚተካከል ነው (ዮሐ 10፡30)፤ በጌትነት ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸ ጊዜ ተለውጦ እንደ ፀሓይ ያበራ መልኩ ፊቱ ነው (ማቴ ፲፯፥፪)፤ ርሱ የማይጠልቅ ፀሓይ የማይጠፋ ፋና ነውና፤ በወዳጆቹም ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሓይ ነውና (ራእ ፳፪፥፭)፤ ሰነፎች አይሁድም ከምድር ነገሥታት ይልቅ የሚያስፈራ ፊቱን ሲመቱት የጌታችን የኢየሱስ የፊቱ ግርማ ሦስት ጊዜ ወደ ምድር የኋሊት የጣላቸው መኾኑን አላሰቡትም) በማለት በቅንአት የሰከሩ የዝንጉኣን የአይሁድን ነገር አስምረዋል፡፡ ዓለምን ለማዳን ሲል አካላዊ ቃል ክርስቶስ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም በቅዳሴው ላይ ሲተነትናቸው፡- “በይእቲ ሌሊት እንተ ባቲ ረፈቀ ምስለ አርዳኢሁ መጠወ ነፍሶ ለሞት በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ ርእሱ…” (ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በተመጠባት በዚያች ሌሊት በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ ሰውነቱን ለሞት ሰጠ፤ ኹሉን የያዘውን ያዙት ኹሉን የሚገዛውን አሰሩት የሕያው የአምላክን ልጅ አሰሩት፤ በቊጣ ጐተቱት በፍቅር ተከተላቸው፤ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተላቸው ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በዐደባባይ አቆሙት ኀጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን ርሱን (ኢሳ ፮፥፪፤ ራእ ፭፥፭-፲፬)፤ ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው (ዮሐ ፲፰፥፳፪) የመላእክት ሰራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ (ፊልጵ ፪፥፲) ይኽን ያኽል ትሕትና እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው?፤ ይኽን ያኽል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው?፤ ይኽን ያኽል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው?፤ ይኽን ያኽል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው?፤ ኀያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው፤ በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት፤ ሕይወት የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቈጠሩት፤ አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በአዳም ላይ የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋራ የተቀላቀለ የኾመጠጠ መጻጻን ጠጣ ወዮ፤ የወልድ መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ኅሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል፤ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ) በማለት ሕማማቱን በስፋት አስተምሮታል፡፡ ወንጌላውያንም እንደጻፉት ጌታችንን አይሁድ ኀሙስ ማታ ከያዙት በኋላ “ወወሰድዎ ለእግዚእ ኢየሱስ እምኀበ ቀያፋ ኀበ ዐውድ ወጎሕ ውእቱ” ይላል በማለዳ ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወደ ፍርድ ዐደባባይ አስረው በማለዳ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ወስደውታል (ማቴ ፳፯፥፲፩፤ ማር ፲፭፥፩፤ ሉቃ ፳፫፥፩፤ዮሐ ፲፰፥፳፰) ይኸውም አዳምን ከመልአከ ገሀነም ፊት አስረው ወስደው አቁመውት ነበርና ለካሣ ሊኾን ነበር፡፡ .
Mostrar todo...
👍 2
ይኽ የጌታችን ትሕትና ብዙዎችን አስደንቋል፤ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንትም በቅዳሴያቸው ላይ “በይእቲ ሌሊት አኀዝዎ ወጸቢሖ ረበናተ አይሁድ ወሊቃነ ካህናት ምስለ ጲላጦስ መስፍን ወነበሩ ዐውደ ለኰ ንኖቱ…” (በዚያች ሌ ሊት ያዙት. በነጋም ጊዜ የአይሁድ መምህሮችና የካህናት አለቆች ከገዢው ከጲላጦስ ጋራ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፤ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ የመላእክት ሰራዊት በመፍራት የሚቆሙለትን በፊታቸው አቆሙት፤ ክፉ ባሪያ ርሱን ያልበደለውን ፊቱን በጥፊ ይመታው ዘንድ እጁን አጸና፤ የመላእክት አለቆች በፍጹም ድንጋፄ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት ይሰግዱ ዘንድ አጐነበሱለት) በማለት ዐርብ ጠዋት አይሁድ ጌታን ወደ ፍርድ ዐደባባይ እንዴት እንዳቀረቡት በስፋት አስተምረዋል፡፡ ጌታ ከመወለዱ አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድሞ ጌታችን በንጉሥ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፰ ላይ “ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጭፍሮች ጌታን ከሰቀሉት በኋላ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ኾኖ በአራት ሲከፋፍሉት ከላይ ዠምሮ ወጥ ኾኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ ያልነበረው እጀ ጠባቡን ደግሞ በመውሰድ ርስ በርሳቸው ለማን እንዲኾን በርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባለዋል፤ ይኽቺውም ቀሚሱ ሰብአ ሰገል ያመጡለት ሲያድግ የምታድግ ዐሥራ ኹለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የነበረችው ሴት የተፈወሰችበት ገባሪተ ተአምራት ነበረች (ማቴ ፪፥፲፩፤ ፱፥፳)፡፡ አይሁድ ይኽነን ማድረጋቸው ለጊዜው “ኹለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል” (ማቴ ፭፥፵) በማለት ኹለት ልብስ አታኑሩ በማለት የሚያስተምረው የርሱ ልብስ ለአራት ቤት ጭፍራ በቃ ለማለት ለመዘበት ሲኾን ፍጻሜው ግን ልብስ የወንጌል ምሳሌ አራት ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ወገን ኹና ለመጻፏ፤ አለመቅደዳቸው በምስጢር አንድ የመኾኗ፤ አንድም አራቱ ኹሉ ባንዲቱ ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ክፍል ስትኾን አንድ ሕግ ለመኾኗ ምሳሌ፤ አንድም “አንቅደድ” ማለታቸው ትስብእቱን ከመለኮቱ ሳንለይ እንመን ሲያሰኛቸው ነው በማለት መተርጒማነ ሐዲስ ያመሰጥራሉ (ማቴ ፳፯፥፴፭፤ ማር ፲፭፥፳፬፤ ሉቃ ፳፫፥፴፬፤ ዮሐ ፲፱፥፳፫)፡፡ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነን ሲገልጹ “ወእምዝ አዕተቱ አልባሲሁ ወአልበስዎ ሜላተ ልብስ…” (ከዚያም ልብሶቹን ገፍፈው የመንግሥት ልብስ የሚኾን ነጭ ሐር የካህናት ልብስ የሚኾን ቀይ ሐር ሕብራቸው ቀይና ጥቁር የሚኾን ልብስ አለበሱት፤ የአጣቢ ሳሙና ማንጻት የማይቻለው እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ እንደ በረድ የኾነ ነጭ ልብስ የሚለብስ ሲኾን፤ ለኪሩቤል የመብረቅ ልብስን ለሱራፌል ግርማ ያለው ልብስን የሚያለብሳቸው ርሱን እንደዚኽ በምድር በመዘባበት ቀይ ሐርና ነጭ ልብስ አለበሱት) በማለት አስተምረዋል፡፡ ልዑል አምላክ ዘመኑ ሲፈጸም ስለሚቀበላቸው ሕማማተ መስቀል አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፮ ላይ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ዳግመኛም ከ፯፻ ዓመት አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስም ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጌታችንን አይሁድ ገርፈውታል፡፡ አንድም ንጹሐ ባሕርይ ጌታችን መገረፉ ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ወደ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ሊክስለት ሲኾን ዳግመኛም በጌታ ላይ አይሁድ የግፍ ድርብ አድርገውበታል በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም ነበር በተጨማሪም በኦሪት ልምድ ከአርባ አትርፎ መግረፍ የተከለከለ ሲኾን እነርሱ ግን ፴፱ ጊዜ ከገረፉ በኋላ ቊጥር ተሳሳትን እያሉ ሥጋው ዐልቆ ዐጥንቱ እንደ በረድ ነጭ እስከሚኾን ድረስ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ግርፋትን ገርፈው እንደ ብራና ወደዚያና ወደዚኽ ወጥረው ሲሰቅሉት ዐጥንቱ ታይቶ የሚቈጠር ኹኗል፡፡ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነኑ ሲያብራሩ “ወእምድኅረ አሠርዎ ቀሠፍዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ጲላጦስ ወአርባዕቱ ሐራ በሐብል ወበአስዋጥ መጠነ ፷፻ ወ፮፻፷፮ … ” (ጌታችን ኢየሱስንም ካሠሩት በኋላ አራት ቤት ጭፍሮችና ጲላጦስ በገመድና ባለንጋ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ጊዜ ገረፉት፤ ዐምስት እልፍ ነው የሚሉም አሉ፤ የግርፋቱን ቊጥር እያሳሳቱ ገርፈውታልና፤ የሚሞት እንዳይገረፍ የማይሞት እንዲገረፍ እያወቁ፤ በግፍ ገርፈው በግፍ ገደሉት የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ፤ ከግርፋቱም ጽናት የተነሣ ሥጋው ኹሉ ዐለቀ፤ ሺሕ ከ፮፻ ከሚኾኑ ቊስሎቹም ወገን ዐጥንቶች ታዩ፤ ጥቁርና ሰማይ የሚመስሉ ቊስሎቹ ግን ሺሕ አንድ መቶ ከዘጠና ናቸው፤ የማይገረፍ አምላክ በዚኽ ሥጋ ተገረፈ፤ ጲላጦስ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችንን የገረፈው በዦሮ ለሚሰማው በዐይን ለሚያየው ሰው ዕጹብ ድንቅ ነው፤ በመገረፉም አይሁድን ደስ አሰኛቸው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን በመገረፉ ሰው ኹሉ ከተገረፈባት ኀጢአት ፍዳ አዳነን፤ ስለ ልጆቹና ስለ አዳም መገረፍን መታሠርን ከፍሏልና) በማለት ለኹላችን ካሳ ስለተገረፈው ግርፋት አስተምረዋል፡፡ በነቢዩ ኢሳይያስ ላይ ጌታ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” ብሎ ያናገረው ሊደርስ ሊፈጸም ክብር ይግባውና በአምላካችን ፊት ላይ አይሁድ ምራቃቸውን ተፍተውበታል፤ ዳግመኛም ዲያብሎስ ምራቀ ምክሩን እየተፋ ወደ ሲኦል ላወረደው ለአዳም ሊክስለት የማኅበረ አይሁድን ምራቅ ክብር ይግባውና አምላካችን በትዕግሥት ተቀብሎታል፡፡ ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል ሲያብራሩ “አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ…” (የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና፤ በቀኝ እጁ ዘንግ አስያዙት፤ ሲያሽሟጥጡ በፊቱ እየወደቁ እጅ ነሡለት፤ የመላእክት ሰራዊት እየደነገፁ የሚሰግዱለትን የአይሁድ ንጉሥ ቸር ውለኻል አሉት፤ ሥልጣናትና ሊቃናት እየፈሩ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት እጅ ነሡት፤ ዐምስት የሚኾኑ መዘባበቻቸውን ከጨረሱ በኋላ በምራቁ ኹለተኛ ዐይኖችን በሚፈጥር በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዳግመኛም ፊቱን በጥፊ መቱት፤ ኪሩቤል ፊቱን ከማየት የተነሣ በእሳት አክናፍ የሚሰወሩት ያልበደላቸውን ርሱን አይሁድ በጥፊ መቱት፤ ፊቱ እንደ መንፈስ ቅዱስና እንደ አባቱ ሲኾን በተዋሐደው ሥጋ ፊቱን ጸፉት ከፊቱ ግርማ የተነሣ ፍጥረቱ ኹሉ የሚርዱለት የሚንቀጠቀጡለት የፈጣሪያቸውን ፊቱን ጸፉት፤ መዠመሪያ በመመታቱና የሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ራሱ የቈሰለ ከመኾኑም በላይ
Mostrar todo...
👍 1
👍 6
መንፈሳዊ ጉባኤ: Henok: ❖ ❖ ❖ ጸሎተ ሐሙስ ❖ ❖ ❖ ጸሎተ ሐሙስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ስያሜ ያለው ነው፡፡ ይህም ምክንያቱ በዕለቱ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የተገለጠበት ስለሆነ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህን በሚዘክር ሁኔታ ታስበዋለች፡፡        ❖ በዚህ ዕለት ምን ተፈጸመ? ❖ √ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ እለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ ሌላው በዚህ ዕለት የተፈጸመው ተገባር ሕጽበተ እግር ነው፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ሐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” � /ዮሐ.13፥1-10/ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው” /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም” በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ደቀ መዛሙርቱን ሥርዓተ ጥምቀት ፈጸመ ሁለተኛ በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ. 11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አላየውም፡፡    √ ሌላው በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር ለይቶ ነገራቸው፡፡ እንዲህም ብሎ “እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው” በዚህ ዕለትም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ የተቀበለልን የእኛን ሥጋ የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/     ❖ የዚህ ዕለት ስያሜዎች፦ ❖       ☞  ጸሎተ ሐሙስ ፦ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17/ በዚህም ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ ይጠራል፡፡        ☞  ሕጽበተ እግር ፦ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ወንጌሉ እንደሚል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡”/ማቴ.26፥27/            ☞  የምሥጢር ቀን ፦ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ የምሥጢር ቀን ይባላል፡፡       ☞  የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ፦ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ የሆነውን የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተበት ነው፡፡ ቀድሞ የነበረውን መስዋዕተ ኦሪት ሽሮ የሐዲስ ኪዳን ደምና ሥጋውን ፈትቶ ስላቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ /ሉቃ.22፥20/      ☞  የነጻነት ሐሙስ ፦ በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የመለሰበት ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡         ❖ሥርዓተ ጸሎተ ሐሙስ ❖ ☞ በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ እንደተለመደው ይከናወናሉ ለየት ያለው ሥርዓት መንበሩ /ታቦት/ ጥቁር ልብስ ይለብሳል ጸሎተ ዕጣን ይጸለያል ቤተ ክርስቲያኑ በማዕጠንት ይታጠናል፡፡ በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኰስኰስቶችን ውኃ ሞልቶ ያቀርባል አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ መታጠቢያ፡፡ ጸሎተ አኮቴት የተባለ የጸሎት ዐይነት ተጸልዮ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ /በሊቀ ጳጳሱ/ እጅ ተባርኮ የሕጽበተ እግር ሥርዓት ከካህናት እስከ ምእመናን ከወንዶች እስከ ሴቶች በካህኑ አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡ ሥርዓተ ኅጽበቱ የሚከናወነውም በውኃ ብቻ ሳይሆን የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓቱ ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ምስጢሩም ወይራ ጸኑዕ ነው ክርስቶስ ጽኑ መከራ መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም /የሚያጥበውና የሚታጠበው ክርስቲያን/ መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ነው፡፡ የወይኑ ቅጠል በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን የሕይወት መጠጥ ይሆናቸው ዘንድ መስጠቱን ለማዘከር ነው፡፡ ማቴ 26.26 ይህም ሥርዓት ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለምእመናን ለማሳየት ነው ዮሐ. 13፤14፡፡ በቀኝና በግራ የቆሙ ሊቃውንትም ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ እያሉ ይዘምራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን ይቀበላሉ፡፡ የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴው የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ነው፡፡ ደወሉ የጸናጽል ድምጽ ሲሆን በቀስታ ስለሚጮህ ነው፡፡ የድምጽ ማጉያ አይጠቀሙም፡፡ ምክንያቱም ዲያቆኑና ካህኑ ዜማውን በቀስታ የሚሉት ይሁዳ በምስጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም ሲሆን በሌላ በኩል የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማስታወስ ነው፡፡ በመቀጠል ክቡር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡             ❖  ጉልባን  ❖ ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ
Mostrar todo...
እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !!! ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለጥምና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !!! የዘመኑን ወረርሽኝ በቸርነቱ ያስታግስልን አሜን!!! ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
Mostrar todo...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል? ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው። እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም። "ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1 ዲያቆን አቤል ካሳሁን @KaleEgziabeher
Mostrar todo...
👍 4
01:27
Video unavailableShow in Telegram
ከማግሥተ ሆሣዕና በኃላ ዕለተ ረቡዕ ሰሞነ ህማማት እለተ ረቡዕ በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላት እንደ ተገለጸው በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ተግባራት ተፈጽመዋል፤ አንደኛ የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤ ሁለተኛ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡ ሦስተኛ ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹‹ሲኒሃ ድርየም›› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለ ነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡ ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ ‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ ቅቤ አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ይሁዳ፣ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም ነበረ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ (ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮)፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡ ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን
Mostrar todo...
👍 12
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4
#የሰሙነ_ሕማማት_ማክሰኞ #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡ #የትምህርት_ቀንም_ይባላል፡- በማቴ. 21፥28፣ ማቴ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ማር.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ሉቃ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱም መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡          "እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም              አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ    እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሓ ወበሰላም!"
Mostrar todo...
👍 5
👍 9
#ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) #የዘንባባ_ዝንጣፊ፡- ☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ #የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡
Mostrar todo...
👍 24
ተጨማሪ
Mostrar todo...
👍 7
Henok: መንፈሳዊ ጉባኤ: ❖ ❖ ❖ የዐቢይ ፆም ስምንተኛ ሳምንት። 💦💦💦💦💦"ሆሣዕና" ❖ ❖ ❖ ሆሣዕና ማለት በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ መድኃኒት ማለትም ነው፡፡ ከጌታችን ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ሆሣዕና፡-- የተባለበት ምክንያት ጌታ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት የሚታሰብበትና የሚዘመርበት በመሆኑ ነው፡፡ የሆሣዕና ሥርዓት ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዕለቱ ፍጻሜ ድረስ የተለየ አገልግሎት አለው፡፡ ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ“ አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡ አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸው፡፡ የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች- ዘሁል22+28 ፤ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል ፣ የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል፡፡ ለምን የተዋረዱትን አህያዎች መረጠ ? 1. ትሕትናን ለማስተማር የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው ለሰው ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ 2. ትንቢቱን ለመፈጸም ትንቢት- ‹‹ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ በእህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል›› ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው ዘካ 9+1 3. ምሳሌውን ለመግለጽ ምሳሌ- ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል፡፡ 4. ምሥጢሩን ለመግለጽ ምሥጢር- በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል √ አህያ የእስራኤል ምሳሌ ፤ ውርንጫላይቱ የአሕዛብ ምሳሌ አህያይቱ ቀንበር መሸከም የለመደች ናት እስራኤልም ሕግ መጠበቅ ለምደዋልና ፤ ውርንጫላይቱ መሸከም አለመደችም አሕዛብም ሕግ መጠበቅ አለመዱምና √ አህያ የኦሪት ምሳሌ ፤ ውርንጫይቱ የወንጌል ምሳሌ አህያ ቀንበር መሸከም እንደለመደች ኦሪትም የተለመደች ሕግናትና ውርንጫላይቱ ቀንበር መሸከም አለመደችም ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና √ በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው √ በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል:: ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ √ በአህያዋ ላይ ኳርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ሕግ ሠራህልን ሲሉ ነው። √ ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ ልማድ ነው፡፡ እዩ የተባለው ሰው በእስራኤል ላይ ሲነግሥ እስራኤል ልብሳቸውን አንጥፈውለት ነበረና በዚያ ልማድ አንጥፈውለታል √ እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ። * ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፦ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤ አንድም ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡ * የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦ ቴምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ ቴምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የቴምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አንተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡ * የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡ * ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፦ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ “የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡ ኢየሱስ ኢየሩሳሌምን ሲያያት አለቀሰላት፡፡ “አንቺ ኢየሩሳሌም ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው አውቀሽ ቢሆን ኖሮ አሁን ግን ይህ ነገር ከዓይንሽ ተሰውሮብሻል ጠላቶችሽ በዙሪያሽ እንደ አጥር ከብበው በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል… ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽና ሊጐበኝሽ የመጣበትን ጊዜ
Mostrar todo...
👍 4
ባለማወቅሽ ነው” እያለ ረገማት፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ሰለ ደኅንተቷ ሊያሳስባት ፈልጐ ነው፡፡ በማያወላዳ መንገድ ንጉሧና መድኃኒቷ እንደሆነ ገለጸላት፡፡ ወደ ራሷ ተመልሳ ጸጋዋን እንድትቀበል የልቧን ድንዳኔ ትታ እርሱን እንድትሰማ አስጠነጠቃት፡፡ ግን አልተጠነቀቀችም፡፡ ለጊዜው በክብር ተቀበለችው፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ግን ተወችው፤ በመስቀል ላይ ሰቀለችው፡፡ የደኅንነቷን ቀን ማወቅ ተሳናት፡፡ በዚህም ደግሞ ከብዙ ዓመታት በኋላ መዓት ወረደባት፡፡ ይህ የሚያሳዝን የኢየሩሳሌም ሥራ የእኛም ሥራ ነው፡፡ ኢየሱስን መድኃኒታችንን መቀበል አንፈልግም ወይም ተቀብለን በኃጢአታችን ከእኛ እንዲርቅ እናደርገዋለን፡፡ በቅዱስ ቁርባን ወደ እኛ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ትንሽ ቆየት ብለን ደግሞ እናዋርደዋለን፡፡ ከእርሱ ጋር እንጣላለን፡፡ ከኃጢአት ጋር ጓደኝነት እንይዛለን፡፡ በኃጢአት ስንወድቅ እርሱን እንደገና እንሰቅለዋለን፡፡ ኢየሱስ እኛን “አቤት በዚህ ቀን ለደኅንነትህ የሚደረገውን ብታውቅ ኖሮ …፣ ይህ ሁሉ ከዓይንህ ተሰውሮብሃል ማወቅን አልፈለግህም፡፡ ይህን እወቅ ግን አንድ ቀን …” እያለ አዝኖ ይፈርድብናል፡፡ ይህንን በማሰብ ሲመጣና ሲናገረን እምቢ አንበለው አናባርረው፡፡ በኋላ እርሱ ቂም ይዞ እምቢ እንዳይለና እንዳያባርረን ደኅንነታችንን ራሳችን አናጥፋት፡፡ በዚህ ዕለት ፀበርት /ዘንባባ/ እየተባረከ ለሕዝብ ይታደላል ይኽንን በመያዝ ዕለቱ የፀበርት እሑድ ይባላል፡፡ታሪኩ በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡ √ማቴ.21፡4 √ ማር.11፡1-10 √ሉቃ.19፡28-40 √ዮሐ.12፤15 • የሆሣዕና መዝሙር፡- - ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ • የሆሳዕና የቅዳሴ ምንባባት ( ዕብ.8÷1-ፍጻ. ) ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (1ኛ ጴጥ.1÷13 ) ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ ( ሐዋ.8÷26-ፍጻ. ) የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡ • የሆሣዕና ምስባክ የቅዳሴ ( መዝ.80÷3 ) ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ“ ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡ (ወይም መዝ.80÷2 ) እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡“ ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡ • የሆሣዕና ወንጌል የቅዳሴ ( ዮሐ.12÷1-11 ) ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ...... • የሆሣዕና ቅዳሴ - ቅዳሴ ዘጐርጐርዮስ
Mostrar todo...
👍 6
ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለበዓለ ትንሣኤ የነድያን ማስፈሰኪያ መርሐ ግብርን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል።" ምሳሌ 19፦17 የሰንበት ት/ቤቶች ላለፉት ረጅም ዓመታት ዋነኛ የሆነውን ህጻናት እና ወጣቶች የተምሮ ማስተማር ሥራ በተጨማሪ ህጻናት ወጣቶች እና ጎልማሶች የተማሩትን በሕይወት እንዲተገብሩ የተለያዩ ክፍላትን በማደራጀት ወንጌልን በተግባር እንዲተረጉሙ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህን አገልግሎት ከሚያከናውኑባቸው አበይት ክፍሎች አንድ የበጎ አድራጎት ክፍል ተጠቃሽ ነው። ዛሬ ይህን መግለጫ ለመስጠት ያነሳሳን በአዲስ አበባ ብቻ የሚገኙ ከ250 በላይ ሰንበት ት/ቤቶች በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እና ትንሳኤ በዓል ሰንበት ት/ቤቶች በተናጠል በየ አጥቢያቸው ከ 200 እስከ 3000 ነደያንን በአንድ ቀን በመመገብ በድምር በአንድ በዓል በአማካይ 125,000 በላይ ነደያንን እና አቅመ ደካሞችን የመመገብ አገልግሎት ላለፉት አሥርት ዓመታት ሲተገብሩ ቆይተዋል ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎታቸውን በማስፋት የአበይት በዓላት የነበረውን አገልገሎት ወደ nሚነት በመቀየር ላይ ይገኛሉ ከአገልገሎቶቹም መሃል ምሳሌ ለመጥቀስ 1. የነደያን የሳምንታዊ እና ወርሃዊ ምገባ እና ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩ ማድረግ እና ለስጋ ወደሙ እነዲበቁ ማድረግ 2. የነደያን ልጆችን ከመዋዕለ ህጻናት ከፍቶ ከማስተማር ጀምሮ ዘላቂ ድጋፍ በመስጠት እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ እና በዘላቂ ፕሮጀቸቶች ራስን የማስቻል ተግባራት 3. መድኃኒት መግዣ ያጡ ህሙማንን የመድኃኒት መግዣ በመደገፍ ከሥጋዊ መከራ በመታደግ 4. የጎዳና ተዳዳሪ ወንድሞች እና እኅቶችን በምገባ እና ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማር 5. ደጋፊ የሌላቸውን ጸበልተኞች በመደገፍ 6. ለአለአስፈላጊ ሥራ የተደረጉ እህቶችን ካሉበት ሕይወት በማውጣት ቃለ እግዚአብሔር በማስተማር እና በመደገፍ 7. በቤታቸው ሆነው ዝቅተኛ ገቢ ኖሯቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች እና ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው ቤተሰቦች ከወር የቤት ወጪ ጀምሮ እስከ በዓላት ማስፈሰክ እነዚህ እና እነዚህን የመሰሉ አያሌ ሥራዎች በሰንበት ት/ቤቶች እየተሠሩ ይገኛሉ። በመሆኑም ዛሬ ከፊታችን በሚከበረው የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ሰንበት ት/ቤቶች ምዕመናንን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ በማስተባበር እና በማሳተፍ ከዚህ ቀድሞ ከምታደርጉት የበጎ አድራጎት አገልግሎት በስፋት በማስተባበር የድርሻችንን እንድንወጣ እያሳሰብን ተርቤ አብልታችሁኛል ፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል ታርዤ አልብሳችሁኛል ታምሜ ጠይቃችሁኛል የሚለውን የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ጥያቄ ሁላችንም ለመፈጸም እንችል ዘንድ ሀ- ምእመናን በጉልበታችሁ በገንዘባችሁ በእውቀታችሁ በቅርባችሁ በሚገኙ አድባራት እና ገዳማት ሰንበት ት/ቤቶች ጋር በመገኘት ከበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ እና የዘላቂ በጎ አድራጎት ስራቸውንም በመረዳት ከጎናችው በመሆን እነድትደግፉ፡፡ ለ- የዚህን በጎ አድራጎት ስራ ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆናችው የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በቀሪዎቹ ቀናት ውስጥ ሀሳቡ ብዙሃን ጋር እንዲደረስ የበኩላችሁን በቅስቀሳ እነድታግዙን ሐ- የሰንበት ት/ቤትን ፍሬ በህይወታችሁ የቀመሳችሁ ቀደምት አባላት እንዲሁም አሁንም በማገልገል ላይ የምትገኙ ካህናት ፤ መምህራነ ወንጌል ፤የኪነ ጥብብ ባለሙያዎች፤ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ፤ በየሙያ ዘርፉ የምትገኙ ሁላችሁም ምእመናን የበጎ አድራጎቱ በረከት ተሳታፊ እንዲሆኑ እግዚአብሔር የሰጣችውን ፀጋ በመጠቀም በቅስቀሳ እንድታግዙ፡፡ እናንተም በጉለበታችሁ ፤በገንዘባችሁ እና በእውቀታችሁ ያሳደገቻችሁ ሰንበት ት/ቤት በመገኘት በአገልገሎት ላይ ያሉ ወንዲሞች እና እህቶችን በማገዝ እንድታበረቱ ሰንበት ት/ቤታችሁ ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡ መ- የገዳማት እና አድባራት አስተዳደር አካላት የሰበካ ጉባኤ እንዲሁም የምግባረ ሠናይ ክፍሎች ይህን የተቀደሰ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሰንበት ት/ቤቶቹ በተሻለ እንዲፈጽሙ በማገዝ እና በመርዳት ሥራቸው እንዲቀላጠፍ የበኩላችሁን እንድትወጡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጥሪውን ያቀርባል። ሠ- በዚህ የበጎ አድራጎት ስራ በዘላቂነት በየሰንበት ት/ቤቱ ያለውን የተደራሽነት አቅም በመጠቀም በበጎ አድራጎት ስራው በመላው ወይም በከፊል አዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶችን አገልግሎት መደገፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል ጋር በመገኘት የበጎ አድራጎት ስራውን በሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች መፈጸም የምትችሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እንወዳለን። "ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።" ምሳሌ 19፡17 በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ብድራችንን ብል እና ነቀዝ በማያበላሹት ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት በሰማይ ለናንተ መዝገብ ሰብስቡ ማቴ 6፡20 እንደተባለ እኛም ኑ በሰማያዊ መዝገባችንን እንጻፍ ብለን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
Mostrar todo...
👍 1
“በደለኞች ወደ እርሱ መቅረብ ይችሉ ዘንድ በሥጋ ለተገለጠው ረቂቅ አምላክ ምስጋና ይሁን። ጌታችን ኃጢአተኛዋን ሴት ፈሪሳውያኑ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው እንዳሰቡት ከእርሱ አላረቃትም። ማንም ሊደርስበት ከማይችለው ሰማይ የወረደው እንደ ዘኬዎስ ያሉ አጭር ቀራጮች ይደርሱበት ዘንድ ነው። ሊይዘው የሚችል ምንም ነገር የሌለ አምላክ የሰውን ሥጋ የለበሰው ኃጢአተኛዋ ሴት እንዳደረገችው የተዳደፉ ከንፈሮች ሁሉ እግሮቹን በመሳም ይቀደሱ ዘንድ ነው” ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዲያቆን አቤል ካሳሁን @KaleEgziabeher
Mostrar todo...
👍 14