cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

"ቃለ እግዚአብሔር "

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16 "ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Mostrar más
Advertising posts
8 303Suscriptores
Sin datos24 hours
-97 days
-2430 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) #የዘንባባ_ዝንጣፊ፡- ☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ #የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡
Mostrar todo...
👍 22
ተጨማሪ
Mostrar todo...
Henok: መንፈሳዊ ጉባኤ: ❖ ❖ ❖ የዐቢይ ፆም ስምንተኛ ሳምንት። 💦💦💦💦💦"ሆሣዕና" ❖ ❖ ❖ ሆሣዕና ማለት በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ መድኃኒት ማለትም ነው፡፡ ከጌታችን ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ሆሣዕና፡-- የተባለበት ምክንያት ጌታ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት የሚታሰብበትና የሚዘመርበት በመሆኑ ነው፡፡ የሆሣዕና ሥርዓት ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዕለቱ ፍጻሜ ድረስ የተለየ አገልግሎት አለው፡፡ ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ“ አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡ አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸው፡፡ የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች- ዘሁል22+28 ፤ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል ፣ የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል፡፡ ለምን የተዋረዱትን አህያዎች መረጠ ? 1. ትሕትናን ለማስተማር የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው ለሰው ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ 2. ትንቢቱን ለመፈጸም ትንቢት- ‹‹ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ በእህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል›› ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው ዘካ 9+1 3. ምሳሌውን ለመግለጽ ምሳሌ- ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል፡፡ 4. ምሥጢሩን ለመግለጽ ምሥጢር- በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል √ አህያ የእስራኤል ምሳሌ ፤ ውርንጫላይቱ የአሕዛብ ምሳሌ አህያይቱ ቀንበር መሸከም የለመደች ናት እስራኤልም ሕግ መጠበቅ ለምደዋልና ፤ ውርንጫላይቱ መሸከም አለመደችም አሕዛብም ሕግ መጠበቅ አለመዱምና √ አህያ የኦሪት ምሳሌ ፤ ውርንጫይቱ የወንጌል ምሳሌ አህያ ቀንበር መሸከም እንደለመደች ኦሪትም የተለመደች ሕግናትና ውርንጫላይቱ ቀንበር መሸከም አለመደችም ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና √ በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው √ በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል:: ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ √ በአህያዋ ላይ ኳርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ሕግ ሠራህልን ሲሉ ነው። √ ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ ልማድ ነው፡፡ እዩ የተባለው ሰው በእስራኤል ላይ ሲነግሥ እስራኤል ልብሳቸውን አንጥፈውለት ነበረና በዚያ ልማድ አንጥፈውለታል √ እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ። * ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፦ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤ አንድም ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡ * የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦ ቴምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ ቴምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የቴምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አንተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡ * የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡ * ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፦ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ “የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡ ኢየሱስ ኢየሩሳሌምን ሲያያት አለቀሰላት፡፡ “አንቺ ኢየሩሳሌም ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው አውቀሽ ቢሆን ኖሮ አሁን ግን ይህ ነገር ከዓይንሽ ተሰውሮብሻል ጠላቶችሽ በዙሪያሽ እንደ አጥር ከብበው በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል… ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽና ሊጐበኝሽ የመጣበትን ጊዜ
Mostrar todo...
👍 4
ባለማወቅሽ ነው” እያለ ረገማት፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ሰለ ደኅንተቷ ሊያሳስባት ፈልጐ ነው፡፡ በማያወላዳ መንገድ ንጉሧና መድኃኒቷ እንደሆነ ገለጸላት፡፡ ወደ ራሷ ተመልሳ ጸጋዋን እንድትቀበል የልቧን ድንዳኔ ትታ እርሱን እንድትሰማ አስጠነጠቃት፡፡ ግን አልተጠነቀቀችም፡፡ ለጊዜው በክብር ተቀበለችው፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ግን ተወችው፤ በመስቀል ላይ ሰቀለችው፡፡ የደኅንነቷን ቀን ማወቅ ተሳናት፡፡ በዚህም ደግሞ ከብዙ ዓመታት በኋላ መዓት ወረደባት፡፡ ይህ የሚያሳዝን የኢየሩሳሌም ሥራ የእኛም ሥራ ነው፡፡ ኢየሱስን መድኃኒታችንን መቀበል አንፈልግም ወይም ተቀብለን በኃጢአታችን ከእኛ እንዲርቅ እናደርገዋለን፡፡ በቅዱስ ቁርባን ወደ እኛ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ትንሽ ቆየት ብለን ደግሞ እናዋርደዋለን፡፡ ከእርሱ ጋር እንጣላለን፡፡ ከኃጢአት ጋር ጓደኝነት እንይዛለን፡፡ በኃጢአት ስንወድቅ እርሱን እንደገና እንሰቅለዋለን፡፡ ኢየሱስ እኛን “አቤት በዚህ ቀን ለደኅንነትህ የሚደረገውን ብታውቅ ኖሮ …፣ ይህ ሁሉ ከዓይንህ ተሰውሮብሃል ማወቅን አልፈለግህም፡፡ ይህን እወቅ ግን አንድ ቀን …” እያለ አዝኖ ይፈርድብናል፡፡ ይህንን በማሰብ ሲመጣና ሲናገረን እምቢ አንበለው አናባርረው፡፡ በኋላ እርሱ ቂም ይዞ እምቢ እንዳይለና እንዳያባርረን ደኅንነታችንን ራሳችን አናጥፋት፡፡ በዚህ ዕለት ፀበርት /ዘንባባ/ እየተባረከ ለሕዝብ ይታደላል ይኽንን በመያዝ ዕለቱ የፀበርት እሑድ ይባላል፡፡ታሪኩ በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡ √ማቴ.21፡4 √ ማር.11፡1-10 √ሉቃ.19፡28-40 √ዮሐ.12፤15 • የሆሣዕና መዝሙር፡- - ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ • የሆሳዕና የቅዳሴ ምንባባት ( ዕብ.8÷1-ፍጻ. ) ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (1ኛ ጴጥ.1÷13 ) ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ ( ሐዋ.8÷26-ፍጻ. ) የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡ • የሆሣዕና ምስባክ የቅዳሴ ( መዝ.80÷3 ) ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ“ ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡ (ወይም መዝ.80÷2 ) እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡“ ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡ • የሆሣዕና ወንጌል የቅዳሴ ( ዮሐ.12÷1-11 ) ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ...... • የሆሣዕና ቅዳሴ - ቅዳሴ ዘጐርጐርዮስ
Mostrar todo...
👍 5
ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለበዓለ ትንሣኤ የነድያን ማስፈሰኪያ መርሐ ግብርን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል።" ምሳሌ 19፦17 የሰንበት ት/ቤቶች ላለፉት ረጅም ዓመታት ዋነኛ የሆነውን ህጻናት እና ወጣቶች የተምሮ ማስተማር ሥራ በተጨማሪ ህጻናት ወጣቶች እና ጎልማሶች የተማሩትን በሕይወት እንዲተገብሩ የተለያዩ ክፍላትን በማደራጀት ወንጌልን በተግባር እንዲተረጉሙ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህን አገልግሎት ከሚያከናውኑባቸው አበይት ክፍሎች አንድ የበጎ አድራጎት ክፍል ተጠቃሽ ነው። ዛሬ ይህን መግለጫ ለመስጠት ያነሳሳን በአዲስ አበባ ብቻ የሚገኙ ከ250 በላይ ሰንበት ት/ቤቶች በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እና ትንሳኤ በዓል ሰንበት ት/ቤቶች በተናጠል በየ አጥቢያቸው ከ 200 እስከ 3000 ነደያንን በአንድ ቀን በመመገብ በድምር በአንድ በዓል በአማካይ 125,000 በላይ ነደያንን እና አቅመ ደካሞችን የመመገብ አገልግሎት ላለፉት አሥርት ዓመታት ሲተገብሩ ቆይተዋል ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎታቸውን በማስፋት የአበይት በዓላት የነበረውን አገልገሎት ወደ nሚነት በመቀየር ላይ ይገኛሉ ከአገልገሎቶቹም መሃል ምሳሌ ለመጥቀስ 1. የነደያን የሳምንታዊ እና ወርሃዊ ምገባ እና ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩ ማድረግ እና ለስጋ ወደሙ እነዲበቁ ማድረግ 2. የነደያን ልጆችን ከመዋዕለ ህጻናት ከፍቶ ከማስተማር ጀምሮ ዘላቂ ድጋፍ በመስጠት እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ እና በዘላቂ ፕሮጀቸቶች ራስን የማስቻል ተግባራት 3. መድኃኒት መግዣ ያጡ ህሙማንን የመድኃኒት መግዣ በመደገፍ ከሥጋዊ መከራ በመታደግ 4. የጎዳና ተዳዳሪ ወንድሞች እና እኅቶችን በምገባ እና ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማር 5. ደጋፊ የሌላቸውን ጸበልተኞች በመደገፍ 6. ለአለአስፈላጊ ሥራ የተደረጉ እህቶችን ካሉበት ሕይወት በማውጣት ቃለ እግዚአብሔር በማስተማር እና በመደገፍ 7. በቤታቸው ሆነው ዝቅተኛ ገቢ ኖሯቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች እና ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው ቤተሰቦች ከወር የቤት ወጪ ጀምሮ እስከ በዓላት ማስፈሰክ እነዚህ እና እነዚህን የመሰሉ አያሌ ሥራዎች በሰንበት ት/ቤቶች እየተሠሩ ይገኛሉ። በመሆኑም ዛሬ ከፊታችን በሚከበረው የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ሰንበት ት/ቤቶች ምዕመናንን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ በማስተባበር እና በማሳተፍ ከዚህ ቀድሞ ከምታደርጉት የበጎ አድራጎት አገልግሎት በስፋት በማስተባበር የድርሻችንን እንድንወጣ እያሳሰብን ተርቤ አብልታችሁኛል ፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል ታርዤ አልብሳችሁኛል ታምሜ ጠይቃችሁኛል የሚለውን የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ጥያቄ ሁላችንም ለመፈጸም እንችል ዘንድ ሀ- ምእመናን በጉልበታችሁ በገንዘባችሁ በእውቀታችሁ በቅርባችሁ በሚገኙ አድባራት እና ገዳማት ሰንበት ት/ቤቶች ጋር በመገኘት ከበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ እና የዘላቂ በጎ አድራጎት ስራቸውንም በመረዳት ከጎናችው በመሆን እነድትደግፉ፡፡ ለ- የዚህን በጎ አድራጎት ስራ ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆናችው የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በቀሪዎቹ ቀናት ውስጥ ሀሳቡ ብዙሃን ጋር እንዲደረስ የበኩላችሁን በቅስቀሳ እነድታግዙን ሐ- የሰንበት ት/ቤትን ፍሬ በህይወታችሁ የቀመሳችሁ ቀደምት አባላት እንዲሁም አሁንም በማገልገል ላይ የምትገኙ ካህናት ፤ መምህራነ ወንጌል ፤የኪነ ጥብብ ባለሙያዎች፤ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ፤ በየሙያ ዘርፉ የምትገኙ ሁላችሁም ምእመናን የበጎ አድራጎቱ በረከት ተሳታፊ እንዲሆኑ እግዚአብሔር የሰጣችውን ፀጋ በመጠቀም በቅስቀሳ እንድታግዙ፡፡ እናንተም በጉለበታችሁ ፤በገንዘባችሁ እና በእውቀታችሁ ያሳደገቻችሁ ሰንበት ት/ቤት በመገኘት በአገልገሎት ላይ ያሉ ወንዲሞች እና እህቶችን በማገዝ እንድታበረቱ ሰንበት ት/ቤታችሁ ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡ መ- የገዳማት እና አድባራት አስተዳደር አካላት የሰበካ ጉባኤ እንዲሁም የምግባረ ሠናይ ክፍሎች ይህን የተቀደሰ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሰንበት ት/ቤቶቹ በተሻለ እንዲፈጽሙ በማገዝ እና በመርዳት ሥራቸው እንዲቀላጠፍ የበኩላችሁን እንድትወጡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጥሪውን ያቀርባል። ሠ- በዚህ የበጎ አድራጎት ስራ በዘላቂነት በየሰንበት ት/ቤቱ ያለውን የተደራሽነት አቅም በመጠቀም በበጎ አድራጎት ስራው በመላው ወይም በከፊል አዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶችን አገልግሎት መደገፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል ጋር በመገኘት የበጎ አድራጎት ስራውን በሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች መፈጸም የምትችሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እንወዳለን። "ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።" ምሳሌ 19፡17 በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ብድራችንን ብል እና ነቀዝ በማያበላሹት ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት በሰማይ ለናንተ መዝገብ ሰብስቡ ማቴ 6፡20 እንደተባለ እኛም ኑ በሰማያዊ መዝገባችንን እንጻፍ ብለን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
Mostrar todo...
“በደለኞች ወደ እርሱ መቅረብ ይችሉ ዘንድ በሥጋ ለተገለጠው ረቂቅ አምላክ ምስጋና ይሁን። ጌታችን ኃጢአተኛዋን ሴት ፈሪሳውያኑ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው እንዳሰቡት ከእርሱ አላረቃትም። ማንም ሊደርስበት ከማይችለው ሰማይ የወረደው እንደ ዘኬዎስ ያሉ አጭር ቀራጮች ይደርሱበት ዘንድ ነው። ሊይዘው የሚችል ምንም ነገር የሌለ አምላክ የሰውን ሥጋ የለበሰው ኃጢአተኛዋ ሴት እንዳደረገችው የተዳደፉ ከንፈሮች ሁሉ እግሮቹን በመሳም ይቀደሱ ዘንድ ነው” ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዲያቆን አቤል ካሳሁን @KaleEgziabeher
Mostrar todo...
👍 13