1 035
Suscriptores
Sin datos24 horas
+57 días
+430 días
Archivo de publicaciones
1 035
በውቅሮ አካባቢ 51 ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች ከማስወንጨፊያቸው ጋር በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውለዋል
በትግራይ ክልል ከውቅሮ ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ፅጌረዳ አካባቢ 51 ዘመናዊ ፀረ-ታንክ ሚሳኤል ሮኬቶች ከማስወንጨፊያቸው ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
መሣሪያዎቹ በተለያዩ ቦታዎች ተደብቀው እንደነበሩና በሕብረተሰቡ ጥቆማ እና በመከላከያ ሠራዊት በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ መገኘታቸው ተገልጿል።
ዘገባው መሣሪያዎቹ ከውቅሮ አካባቢ ተይዘው በሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ከመግለጽ ባለፈ፣ በአካባቢው ተደብቀው የነበሩ ሌሎች ትጥቆችንና ተተኳሾችን ለማፈላለግ ፍተሻው እንደቀጠለ ነው።
1 035
ከ15 ሺህ በላይ የህወሓት ታጣቂዎች በDDR ፕሮግራም ለመመዝገብ ተዘጋጅተዋል
በትግራይ ክልል ታጣቂዎችን ወደ ሰላማዊ ሕይወት የማሸጋገር ሂደት አዲስ ምዕራፍ መጀመሩ ተዘገበ።
በመቀሌ እና አካባቢዋ ከ15 ሺህ በላይ የህወሓት (TPLF) ታጣቂዎች ትጥቅ በመፍታት ከውትድርና ተሰናብተው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ በተዘጋጀው የትጥቅ ማስፈታት፣ የቀድሞ ታጣቂዎችን መቀበልና መልሶ ማቋቋም (DDR) ፕሮግራም መመዝገባቸው ተገልጿል።
የDDR ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ ከተተገበረ፣ ታጣቂዎቹ ከጦርነት ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ፣ ትጥቅን ትተው ወደ ሥራና ማህበራዊ ኑሮ እንዲቀላቀሉ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።
ይህ ሂደት በትግራይ ሰላምን ለማጠናከርና ወጣቶች ከግጭት ወጥተው ወደ ትምህርት፣ ሥራ እና ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ለማስቻል የሚያግዝ ሂደት መሆኑ ተጠቁሟል።
1 035
ጠ/ሚ/ዶ/ር/ ዐቢይ አህመድ ወደ አመራር ከመጡ ወዲህ ባለፉት ስምንት የለውጥ አመታት በሀገራችን በጤና በትምህርት በግብርና በዲፕሎማሲ በኢንቨስትመንት በቱሪዝምና በሌሎች የልማት ዘርፎች የተለያዩ የለውጥ ስራዎችና የልማት ተነሳሽነቶች ተከናውነዋል። እነዚህ ጥረቶች የሀገራችንን የልማት አቅም ለማሳደግ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከርና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ሀገራችን በእነዚህ የስራ ዘርፎች ያከናወነቻቸው የልማት ጥረቶችና የተጀመሩ የለውጥ እርምጃዎች የወደፊት እድገቷን ለማፋጠን ወሳኝ መሰረት ይጥላሉ።
የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታትና የልማት ጥረቶችን በማስቀጠል ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የብልፅግና ደረጃ ማሸጋገር የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት ነው።
1 035
በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የመደመር መንግስት እየተመራች የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በተለያዩ ዘርፎች በማስፋፋት ወደ ዘመናዊ የዲጂታል ሽግግር እየተሸጋገረች ትገኛለች።
ይህ ሽግግር የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የንግድ ስራዎችን ለማቀላጠፍ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማስፋፋትና አዳዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።
በዚህም ሀገራችን የቴክኖሎጂ አቅሟን በማጠናከር ምርታማነቷን በማሳደግና የኢኮኖሚ ትስስሯን በማስፋት ለዘላቂ ልማት የሚያግዝ መሰረት እየገነባች ትገኛለች።
ዲጂታል ቴክኖሎጂ የዘመናዊ ልማት መሳሪያ የኢኮኖሚ እድገት ማፋጠኛና ለተሻለ የወደፊት ብልፅግና ወሳኝ መሰረት ነው።
