cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

S.A.D.A.S የአእምሮ ጤና ለኢትዮጵያውያን❤

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ጤናማ አእምሮ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ትውልድ መፍጠር ነው።🇪🇹 Contact us @Nebyou_Nigussu

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
499
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የኤለን ዲጀነረስ ሾው ዲጄ የነበረው ትዊች ራሱን አጠፋ =========================== So you think you can dance ውድድር ላይ ከፍተኛ ብቃት በማሳየት ሁለተኛ የወጣው ትዊች ከፍተኛ ታዋቂነት አግኝቶ የሄለን ዲጀነረስ ሾው ላይ ዲጄ ሆኖ ይሰራ ነበር። ትዊች ጨዋታ የሚወድ የደስደስ ያለው ሰዎችን ለማዝናናት የሚጥር የኪነ ጥበብ ሰው ነበር። የሶስት ቆንጅዬ ልጆች አባት የነበረው ትዊች ከሳምንት በፊት ከሚስቱ ጋር ዘጠነኛ የጋብቻ 'አኒቨርሰሪያቸውን' አክብሮ ነበር። ማክሰኞ ምሳ ሰአት ራሱን አጥፍቶ ተገኘ። ሚስቱ የተፈጠረውን ማመን አልቻለችም። "የቤታችን ምሶሶ ነበር፤ ለኔ ምርጥ ባል ለልጆቼም ምርጥ አባት ነበር" አለች እንባዋ እየወረደ። ሰዎች አለባበሳቸውን አይቶ ውስጣቸውን መገመት ከባድ ነው። የሚስቅ ሁሉ ደስተኛ አይደለም። ገንዘብ ደስታን አይገዛም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሺህ ጓደኞች ቢኖርህም ቢጨንቅህ የሚያዳምጥህ ቢቸግርህ የሚያግዝህ በጣም ጥቂት ነው። የአእምሮ ህመም ፆታ፣ ብሄር፣ ሀይማኖት አይለይም። ማን ላይ እንደሚከሰት አይታወቅም። ሰዎች ሲጨንቃቸው በጥሞና የሚያዳምጣቸው ሰው ቢኖር ብዙ አሳዛኝ ነገሮች ሳይከሰቱ ይቀሩ ነበር። ለቅሶ መድረስ፣ ቀብር ማስቀበር ብዙ ሰአታት ይፈጃል ነገር ግን ብዙ ለውጥ አያመጣም። ለጥቂት ደቂቃ ያለ ፍረጃ ማዳመጥና ወደ የአእምሮ ህክምና መውሰድ ብዙ ጊዜ አይፈጅም ነገር ግን እጅግ በጣም ትልቅ ለውጥ ያመጣል። የአእምሮ ጤና ግንዛቤ እንዲስፋፋ ሁላችንም አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን። የአእምሮ ህክምና በጳውሎስ፣ አማኑኤል፣ ዘውዲቱ፣ የካቲት 12፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲሁም በግል ክሊኒኮች ይሰጣል። የመፅናናት አምላክ ለልጆቹ መፅናናትን ይስጣቸው። ነፍስህ በሰላም ትረፍ። ዶ/ር ሰላም ዜናውን ስለላክልኝ አመሰግናለሁ🙏 ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
Mostrar todo...
Mostrar todo...
የሶሻል ሚዲያ ተፅእኖ እና አሳሳቢው የአእምሮ ጤና../ስለጤናዎ/ /በእሁድን በኢቢኤስ//

An infotainment program on Sunday afternoon with EBS’ own Asfaw Meshesha ,Nafkot Tigistu, Mekdes Debesay & Tinsae Berhane . It includes multiple segments depending on the number of stories following the topical discussion. The program is engaging which keeps viewer right at the other side for the whole three hours. It is a magazine format; small updates of the talk of the town, guest appearance, Wello, live music, cooking and many more. #EhudenBeEBS #SundayAfternoonShow_EBSTV #InfotainmentShow_EBSTV #AsfawMeshesha_EBSTV

የንግግር ህክምና (Psychotherapy) ለተለያዩ የስነ ልቦናና የስነ አእምሮ ህመሞች ውጤታማ የሆነ የህክምና መንገድ ነው፥፥ በህክምናውም የተዛቡ አስተሳሰቦችን፣ ጠቃሚ ያልሆኑ ባህሪያትን እንዲሁም የስሜት መዛባትንና ከሱስ ጋር ተያይዞ የሚመጡ የስሜት አለመቆጣጠርን ያግዛል፥፥ የንግግር ህክምና በሚደረግበት ጊዜ ምስጢርነቱ ተጠብቆ እርሶና ባለሙያው ብቻ የሚነጋገሩበትና የሚመካከሩበት ቦታን ይከፍታል፥፥ የንግግር ህክምና በየጊዜው እያደገ የመጣ ህክምና አይነት ሲሆን ህክምናውን ለማድረግ በአካል ወይም ኢንተርኔትን ተጠቅሞ በ ማድረግ ይቻላል፥፥ የንግግር ህክምና ብዙ አይነቶች አሉት፥፥ - እንድ ለአንድ ህክምና - የጥንዶች ንግግር ህክምና - የቡድኖች ህክምና እንዲሁም የቤተሰብ የንግግር ህክምና የሚጠቀሱት ናቸው፥፥ የንግግር ህክምና ወይም Counseling ጥሩ ውጤቶችን እንዲያመጣ የሚያስፈልጉን ነጥቦች አሉ፥፥ - ከባለምያው ጋር ፍፁም እምነትን ጥለህ ሃሳብን በግልፅ መናገር ያስፈልጋል፥፥ - ባለሙያን ማመን ያስፈልጋል፥፥ ከንግግር ህክምናው በኳላ የቤት ስራ የሚሰጥባቸው ጊዜያት ኣሉ፥፥ እነዛን የቤት ስራዎች ትኩረት አድርጎ መከታተል ያስፈልጋል፥፥ ብዙ ጊዜ ወደ ንግ ግር ህክምና ሰዎች ሲመጡ ችግሩ ለብዙ ጊዜ የቆየ በመሆኑ ውጤት እስከሚታይ ትእግስት ይፈልጋል፥፥ በህክምናው ምን ማግኘት እንደሚፈልጉ ትኩረት ማድረግ ይፈልጋል፥፥ የንግግር ህክምና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለጭንቀት፣ ለፍርሃት፣ ለሱስ ጋር ለተገናኘ የአእምሮ ህመም እንዲሁም ለድብርት ጥሩ የሆነ የህክምና ውጤት አሳይቷል፥፥ For Counseling, consuktations and inquiries, call us on 0966111111/0116662966 Lebeza Specialty Psychiatry Clinic Website: Lebeza.org
Mostrar todo...
Which Holistic Services to Mental Health Are Most Beneficial? Each individual’s struggles and hopes are unique. If you need mental health services such as anxiety treatment, depression treatment, bipolar disorder treatment, ADHD treatment, PTSD treatment, and more, holistic treatment may help you find relief and recovery. Treatment centers that take a holistic approach recognize mental health conditions as biological, physiological, and spiritual conditions. At Lebeza Specialty Psychiatry Clinic, our holistic approach to recovery is Central to our support. The Common holistic services include: Acupuncture Massage Fitness Nutrition Yoga Mindfulness meditation These holistic services can be powerful individually, but more so in combination, and Lebeza has organized a group seminar. We will share the details soon. Stay tuned. For consultation, counseling and inquiries, please call us on 0966111111/0116662966. Address: around St. Urael Church, 22 behind old Plaza hotel @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
Photo unavailableShow in Telegram
በግሬስ የህሙማን እና የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል የአስታማሚዎች ጭንቀት ይገባናል ፡ - ካላቸው ጊዜ ላይ ቀንሰው ቤተሰቤን ብለው ስራ ሲያቆሙ እንረዳለን ፡ - በማያቁት ሙያ ገብተው የወንድም የእህታቸውን ቁስል ሲያጥቡ ሲቀይሩ ይሰማናል ፡ - እናት አባት ታሞ ለሊቱን ሙሉ አብረው ቁጭ ብለው ሲታመሙ እናቀዋለን ፡ - ስሙን እንኳን በቅጡ የማያቁትን በሽታ ስለባህሪው ፈልገው ለማጥናት ሲሞክሩ እናያለን ፡ ለዚህም ነው አንደኛው አላማችን አስታማሚዎችን ማሳረፍ ጭንቀታቸውን መቀነስ ነው የምንለው ። በግሬስ የህሙማን እና የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል የምንሰራውን ማወቅ ከፈለጉ ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/gracenursinghome ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0967-03-42-42 / 0954-99-11-90.
Mostrar todo...
Mostrar todo...
DREAM LIGHT INTERIOR DESIGN

Interior designers in Addis Ababa

Mostrar todo...
DREAM LIGHT INTERIOR DESIGN

Interior designers in Addis Ababa

መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼💚💛❤️
Mostrar todo...
ስለ Depression... ድንገት ከመሬት ተነስቶ መደበር፣ መከፋት፣ ሁሉንም ነገር ማስጠላት፣ የሚያስደስትህ ነገር ማጣት አጋጥሞህ አያቅም? አጋጥሞሽ አያቅም?! "ሰሞኑን ምን እንደነካኝ እንጃ! የምትልበት፣ በቃ ከአልጋ አትነሳ፣ ባትተኛም ተጋድመህ ዋል የሚል ስሜት፣ መማር፣ መስራት፣ መኖር አለመቻል፤ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ አርቆ ብቻህን የሚያስቀምጥ፣ መላ የጠፉው ነገር ገጥሞህ አያውቅም። አሞኛል ብለህ ሃኪም ጋር አትሄድ ይሄ ነው የምትለው ምልክት አይታይብህም፤ ለሰው አትናገረው አይረዳህም፤ በቃ ዝም ብሎ መብሰልሰል ብቻ! መነጫነጭ! መብሰክሰክ! መፍትሄ ያገኘህ መስሎህ መጠጥ ስትጋት፣ እረፍት የሰጠህ መስሎህ ሱስ ውስጥ ስትነከር፣ አንዳቸውም ለችግርህ አልደርስልህ ብለውህ የገባህበት በር ጠፍቶብህ፣ መውጫ ስትቸገር። የባሰ ተጨማሪ ችግር ውስጥ ራስህን ስታገኘው። ባስ ሲል ደግሞ ሰይጣን ይሆን እንዴ ብለህ ሃይማኖታዊ መላ ፍለጋ መሄድ፣ ወይም መንፈሳዊ ህይወትክን መፈተሽ፣ መፀለይ፣ ከእግዜሩ መታረቅ ሞክረህ አታቅም። አንተም ካልሆንክ... አንቺም ካላገጠመሽ... ፀባዩዋን የምትወድላት ሚስትህ፣ ድንገት ተለውጣ፣ ሁለንተናዋ ተቀያይሮ፣ ሁሌ ሲከፋት፣ ያለምክንያት ስትንጫነጭ፣ በረባ ባልረባው ስትናደድ፣ "ምን አድርጊያት ይሆን? ምን ባደርግላት ይሻላል?!" እያልክ ተጨንቀህ ታውቃለህ?! የሚወድሽ ባልሽ፣ ያ ተጫዋች የልጆችሽ አባት፣ በብዙ አመት የማታውቂውን አዲስ ፀባይ አምጥቶ፣ ከመጠን በላይ ዝምታ አብዝቶ፣ እንቅልፍ አጥቶ፣ ከበፊት የሌለበትን እየጠጣ፣ እያመሸ፣ ሱስ ውስጥ ገብቶ፣ ሌላ ሰው እስኪመስልሽ ተለውጦብሽ፣ ጭንቅ ጥብብ ብሎሽ ያቃል?! ያ ጎረምሳ ልጃቹህ፣ ድሮ ተጫዋች፣ ቤቱን አድማቂ የነበረው ልጃችሁ ወይም ከስርሽ የማትጠፋው ሳቂታዋ ልጅሽ፣ ከእቅፍህ የማትለየው ሚስጥረኛ ልጅህ፣ ድንገት ሃይ ስኩል ሲደርሱ ወይም ዩኒቨርስቲ ደርሰው ሲመለሱ፣ ፀባያቸው ተለውጦ፣ ግልፍተኛ እና መከረኛ ሆነው፣ ያለ ዕድሜያቸው ህይወትን ጠልተው፣ ቤት ውስጥ እየኖሩ ከቤተሰብ ተለይተው፣ የሌላ ሰው ልጅ እክኪመስሉ ማወቅ ተስኗችሁ፣ እንደ ወላጅ መምከር እና መፍትሄ መፈለግ አቅቷችሁ፣ ምኝታ ቤታቸውን ዘግተው በብቸኝነት ሲማቅቁ፣ አንዳች ለማድረግ አቅም አንሷችሁ የምታውቁ ወላጆች የላቸሁም?! ይህ ሁሉ በራሱ ወይም በቅርብ ሰው ላይ የደረሰበት የማወራውይገባዋል። "አንተ እኮ ከድሮም ሰው አትቀርብም፤ እሱ እኮ መዝናናት አያስደስተውም፤ እሷ እኮ መነጫነጭ ፀባይዋ ነው፤ እሱ ሁሌሞ ፊቱ ተፈቶ አያቅም፤ እሷ ሰነፍ ስለሆነች ነው፤ እሱ ስራ ስለማይወድ ነው፤ እሱ ከንቱ ስለሆነ ነው ሱስ ያጠቃው፤ እናቱን ካጣ ነው እንደዚህ የሆነው፤ አባቷ ሲለያት ነው የተለወጠችው፤ ከተደፈረች በኋላ ነው እንዲህ የሆነችው..." "ሰው መድኃኒት አድርጎባት ነው፤ አጋንንት ነው፤ መንፈስ ነው...እንዲህ ነው....እንዲያ ነው!" ብቻ ብዙ ብዙ እየተባለ ስንት ሰው በየጓዳው ቀርቦ የሚረዳው እና በመፍትሄ የሚረዳው አጥቶ እየተሰቃዬ እንደሚገኝ ቤት ይቁጠረው። ዋናው ጥያቄ፦ ይህ ሁሉ ባይሆንስ?! ምናልባትም የገመትነው በሙሉ ስህተት ቢሆንስ?! አዎ! እነዚህ ሁሉ ሰዎች እንደማንኛውም በሽታ (እንደ ወባ፣ ቲቢ፣ ደም ግፊት...) በድብርት በሽታ (Depression Disorders) ወይም በተመሳሳይ የአዕምሮ በሽታ ተጠቅተው ቢሆንስ?! እንዲህ ብለው ራስዎን ጠይቀው ያቃሉ?! ታድያ የድብርት ስሜታችን በሽታ ሊሆን እንደሚችል እና ሊያሳስበን እንደሚገባ እንዴት ማወቅ እንችላለን?! እስኪ ይህን አብረን እንመልከት... Depression (ድብርት/መደበት) የሚለው ቃል ለብዙ አገልግሎት ሊውል ይችላል። እነርሱም፦ 1. የድብርት ሙድን/ስሜትን (state of mood) ይገልፃል፣ 2. በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የሚመጡ የድብርትና ተያያዥ ምልክቶች ስብስብን (depression syndrome) ይወክላል፣ 3. የድብርት በሽታን (Depression Disorders) ይጠቁማል። ድብርት ራሱን የቻለ በሽታ ሊሆን የሚችል፣ ከMood Disorders አንዱ የሆነ፣ ብዙ አይነት subtypes ያሉት disorder (በሽታ) ነው። ለዛሬ ግን ከሁሉም የከፋውን፣ ለተጠቂዎች አሳሳቢ የሆነውን፣ በአለማችን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን የDepression አይነት እንመልከት። ይህም Major depressive disorder(MDD) ወይም Unipolar Major Depression ይባላል። MDD በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ ሊከሰት የሚችል፣ አንዴ ከተከሰተ ደግሞ በተጠቂው ግለሰብ ላይ አስከፊ ስነ-ልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች የሚያስከትል፣ የግለሰቦችን የዕለት ተዕለት ኑሮ በማቃወስ እና ምርታማነታቸውን በመቀነስ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብ እንዲሁም በሃገር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር በሽታ ነው። የበሽታው ተጠቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ፣ ዕድሜያቸው እያነሰ የመጣ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ አለምን በወረርሽኝነት እያጠቃ፣ ብዙ ሰዎች ራስን በማጥፋት ህይወታቸውን እንዲነጥቁ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ይገኛል። በሽታው ለተጠቂው ብቻ ሳይሆን፣ ለባለሙያውም ከባድ ፈተና ነው። ይህም የሆነው በሽታውን በትክክል ለመለየት እና በሚገባው መጠን ለማከም የበሽታው ፀባይ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው። በሽታው በምን ምክንያት እንደሚከሰት እስካሁን በውል ባይታወቅም፣ Genetical (ዘር)፣ Environmental (አካባቢ)፣ Biology (አካላዊ) እና Psychosocial (ስነ ልቦናዊና ማህበረሰባዊ) ተፅዕኖዎች የራሳቸውን ድርሻ በመወጣት፣ በጋራ ለበሽታው ምክንያት እንደሚሆኑ ይታወቃል። ስለዚህ እያንዳንዳችን የDepression Disorders ተጠቂ መሆናችንን ሊጠቁሙን የሚችሉትን ነገሮች ለዛሬ እንመልከት። አንድ ሰው የMajor Depressive Disorder ተጠቂ ነው ለማለት በህይወቱ ቢያንስ አንዴ Major depression episode ሊኖረው ይገባል። ለተወሰነ ጊዜ የምናሳልፈው አንድ የህይወታችን አጋጣሚ እውነተኛ Major depression episode ነው ለማለት ደግሞ ባለሙያዎች የሚጠቀሙት መስፈርት (Criteria) አለ። ይህም DSM - V Criteria በመባል የሚታወቅ ሲሆን እንደሚከተለው ያትታል። በመጀመሪያ በመስፈርቱ ውስጥ የተካተቱትን 9 ምልክቶች እንመልከት። 1. የድብርት ስሜት፣ ዝም ብሎ መከፋት፣ ያለ በቂ ምክንያት መጨነቅ፣ መነጫነጭ፣ መብሰክሰክ (በየቀኑ፣ በቀን ውስጥ ለብዙ ሰዓት) 2. የደስታ ስሜት ማጣት ወይም የምንም ነገር ፍላጎት አለመኖር 3. የእንቅልፍ ማጣት ወይም የእንቅልፍ መብዛት 4. ከፍተኛ የአካላዊ ድካም ስሜት ወይም አቅም ማጣት 5. የውፍረት መቀነስ ወይም መጨመር ፤ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጨመር 6. ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ዝግመት ወይም እረፍት ማጣት 7. ትኩረት ማድረግ አለመቻል፣ ነገሮችን መርሳት፣ ማስተዋል መቸገር 8. ራስን መጥላት፣ ለራስ ያለን ግምት ማነስ፣ ከፍተኛ ፀፀት ወይም ራስ ወቀሳ፣ "ለምንም/ለማንም አልጠቅምም" ብሎ ማሰብ 9. በተደጋጋሚ ሞትን መመኘት፣ ከዚህ አለም መለየትን በብርቱ መፈለግ፣ ራስን ለማጥፋት ማሰብ፣ ማውጠንጠን፣ ማቀድ ወይም መሞከር
Mostrar todo...
የDepression ዋና ዋና ምልክቶቹ እነዚህ ሲሆኑ፣ አንድ ሰው Depression Episode አጋጥሞታል ወይም የMajor Depressive Disorde ተጠቂ ነው ለማለት የሚከተሉትን ማሟላት አለበት። 1. ከላይ ከተዘረዘሩት 9 ምልክቶች ውስጥ 5 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑት ሊከሰቱ ይገባል (ከ5ቱ አንዱ ምልክት ተራ ቁጥር 1 ወይም 2 ላይ የተጠቀሰው መሆን አለበት) 2. ምልክቶቹ በተከታታይ ለ2 ሳምንታት ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ መቆየት ይኖረባቸዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥም almost በየቀኑ እና በ24 ሰዓት ውስጥ ለብዙ ሰዓታት ሊቆዩ ይገባል። 3. እነዚሄ ምልክቶች በሰውዬው የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ (significant distress) ማድረስ አለባቸው። (ለምሳሌ፣ መማር፣ ስራ መስራት፣ ቤተሰብ ማስተዳደር አለመቻል...) 4. እነዚህ ምልክቶች በሌላ ማንኛውም አካላዊ ህመም፣ በተለያዩ ሱሶች (ዕፆች) ወይም በሚታዘዙ መድሃኒቶች ምክንያት የተከሰቱ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል። N.B. (ማሳሰቢያ)፦ 👉 በተለያየ ችግር ምክንያት የመጣ ከባድ ሃዘን ተጠቂ የሆነ ሰው (ለምሳሌ፣ ቤተሰብን በሞት በመነጠቅ) እነዚህ ምልክቶች ሊያሳይ ቢችልም፣ ሃዘኑ ምክንያት ስለሆነው ብቻ የMajor Depression Disorder ተጠቂ አይደለም ማለት አይቻልም። 👉 እነዚህ ምልክቶች በሌሎች በተለያዩ ምክንያቶች እና ህመሞች ምክንያት ሊከሰቱ ስለሚችሉ፣ የDepression መለያዎች ብቻ አድረጎ መውሰድ ተገቢ አይደለም።ስለዚህ እነዚህን ምልክቶች በራሳችን ላይ በማስተዋል፣ የDepression Disorder ተጠቂ መሆናችን በከፊል ልንጠርጥር እንችላለን። በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ካሟላን ወደ ተገቢው ባለሙያ ወይም የስነ-አዕምሮ ሃኪም (Psychiatrist Doctor) ጋር በመሄድ በበቂ ሁኔታ መመርመር፣ ማረጋገጥ እና ተገቢውን ህክምና ማግኘት ይኖርብናል። ስለ ህከምናው ስናስብ በጣም ጥሩ የሆነው ዜና፣ በባለሙያ ተገቢው ህክምና ከተደረገለት፣ በዚህ አስከፊ በሽታ የተጠቃ ሰው፣ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ወደ ቀደመው ጤንነቱ መመለስ እና በሰላም ህይወቱን መምራት ይችላል። ትክክለኛውን ህክምና ያገኙ የDepression ተጠቂዎች ከ80-90% ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ከህክምናዎቹ መካከል፦ 1. በባለሙያ የሚደረግ የምክር ህክምና (Psychotherapy ) 2. የተለያዩ Anti-depressant መድሃኒቶች (Pharmacological) 3. በኤሌክትሪክ የታገዘ ህክምና (Elctro-convulsive Therapy/ECT) ሊሆኑ ይችላሉ። #ጥብቅ_ማሳሰቢያ፦ 👉 ይህ ፅሁፍ ራሳችንን ወይም ሌላ ሰው የDepression Disorders ተጠቂ አድርገን እንድንወስድ ወይም Diagnose እንድናደርግ የታሰበ አይደለም። 👉 ማንኛውም ሰው ራሱን ሙሉ በሙሉ ማወቅ ወይም መመርመር አይቻልም። 👉 በተገቢው መንገድ በባለሙያ ታይቶ ሳይመረመር በራስ መወሰን እና መጨነቅ አይገባም። P.S. በአማርኛ አጠቃቀሜ ላይ ስለሚኖረው ማንኛውም ድክመት ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሰላም ለእናንተ ይሁን። ዶ/ር ሱራፌል አየለ (GP) (የዘረፉ ባለሙያ ባልሆንም በዚህ ጉዳይ እኔን ለማዋራት ወይም የጓደኛ እርዳታ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጆሮዬም፣ ልቤም ክፍት ነው።) Feel free to contact me for anything: @Nicodemus on Facebook @dr_nicodemus on Telegram
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.