cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ስብዕናችን #Humanity

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Mostrar más
Advertising posts
30 962Suscriptores
-724 hours
-497 days
-22630 days
Archivo de publicaciones
❤️ነፍሴ ስትመክረኝ … የውስጥ ሰላም ከብር ፣ ከወርቅ ፣ ከአልማዝም ሆነ እንቁ ይልቃል ፤ ስኬታማነት ከውስጥ ሰላም ፣ ደስታና ፍቅር በጥብቅ የተቆራኘ ካልሆነ ትርጉሙ ጎዶሎ ነው። ወደ ሀቅ የምትጠራህ ነፍስህን በድለህ ሺህ ግዜ የምድር ሃብት ብትሰበስብ ሀብትም ሆነ ሌላ ነገርህ የውስጥ ሰላም እስካላስገኘልህ ድረስ ተሳካልህ ተብሎ አይታመንም ፤  በዚህ መልኩ የምታገኘው ነገር " ይዘህ ተገኘህ " እንጂ ተሳካልህ አያሰኝም።. 📍ሰላም የሚያሳጡ ፍጡራኖችን ያየህ እንደሆነ በሌሎች ሰዎች ዋጋና መስዋትነት ማትረፍ የለመዱ ፤ ከራሳቸው ጋር ሰላም መፍጠር ያልቻሉ ስግብግቦችና ወዝጋባዎች እንደሆኑ  ለሰከንድ አትጠራጠር። ከእንደዚህ ዓይነት ስግብግብነት ተጠቆጠብ የሰላም እሴትህን ጠብቅ ፣ ይዘው የተገኙት እየቀደሙህ እየመሰለህ የመልካምነት ጉዞህ መሐል ላይ አትወዛገብ ከመልካምነት እና ከሀቅ በላይ አድካሚና አሸልቺ ግን ደግሞ ፍሬው ጣፋጭ የሆነ እፁብ ድንቅ መታደልና መባረክ የለም። 💡አንዳንድ ጊዜ በራስህ ዓለም ዉስጥ ብቻ ለመኖር ሞክር፡፡፡ ወደ ምድር የመጣኸው ትርጉም ላለው ዓላማ ነውና ሁሉም ቦታ ላይ ጥቀም፡፡ በደረስክበት ቦታ ሀሉ መልካም ዝራ፡፡ 📍እቅድህን በመኖር ሂደት በሚገጥሙህ ፈተናዎች አታማር ከአሁን ቀደም የሆኑ ፣ እየሆኑ ያሉ ፣ ከአሁን በሁዋላ በፈለግከውም ሆነ ባልፈለግከው መንገድ የሚሆኑ ነገሮች ሁሉ በምክንያት ያጋጠሙህ እንደሆኑ እመን። የፈተና መብዛቱ ለበጎ ነው፡፡ አካሄድህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡ በችግሮች ዙሪያ ተጠበብ እንጂ አትጨነቅ ፤ ለመልካምነትና ከሀቅ ጋር ለመታረቅ የረፈደ የሚባል ግዜ የለም ፤ የቻልከዉን ያህል ስራና እረፍ ፤ ቀሪውን ለፈጠረህ ጌታ ተወው። ሀቀኝነትን ድፈር ፤ ሀሜተኝነትንና ዋሾነትን ፍራ 💡ደፋር ይሰማል ፣ ያደምጣል ፣ ይናገራል ፣ ይመረምራል ፣ ይፅፋል ፣ ይወስናል ፤ የሰማውን ሁሉ እንደ ሰነፎችና ፈሪዎች እውነት ብሎ አያምንምም አይፈርጅምም ፤ የሰማኸውን ሁሉ እንደ እውነት አምነህ ደግመህ ደጋግመህ ሳታረጋግጥ አታውራ ፤ ማጣራትን አስቀድም ፤ ሳትጠይቅ እና ሳታመዛዝን አትፍረድ። ስምህን ከምታውቀው በላይ እርግጠኛ ሁን 💡እንዲህ ስታደርግ ሁሉም የሚታየው ጭለማ ፣ የሚያወራው ስለጭለማ ቢሆን ላንተ የሚታይህ ብርሃን እንጂ ሌላ አይሆንም። አትጠራጠር ንስር አሞራ ፈተናዎቿን ከደመናው በላይ ከፍ በማለት እንደምትሻገረው አንተም ፈተናዎችን ከችግሮች በላይ ከፍ ብለህ በማለፍ የውስጥ ሰላምህን ቀጣይነት እያረጋገጥክ ማሳካት ወደ ምትፈልገው ግብ የማትደርስበት ቅንጣት ታክል ምክንያት አይኖርም። 📍እናም እየነዳን ወዳጆቼ ሁሉንም ነገር በንቃት እየታዘብን እስከነዳን ድረስ  ፤ በችግር ውስጥ ሆኖ በመሳቅ ፣ በደስታ እና በውስጥ ሰላማችን እስካልተደራደርን ድረስ የማንሻገረው ፈተናና የማናሳካው  ግብ አይኖርም። ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
27👍 19
👍 1
🔆ከራሱ ጋር የተስማማ ከተፈጥሮው ሁሉ ጋር ይስማማል! (Live in harmony with nature) 📍ተፈጥሮ የሰው አካል ነው፤ ሰውም የተፈጥሮ ውህድ ነው፡፡ ሰው ከተፈጥሮ ውጭ መሆን አይችልም፡፡ ከተፈጥሮው ውጪ ልሁን የሚል ሰው ካለ መጀመሪያ የሚጋጨው ከራሱ ጋር ነው፡፡ ሁለተኛም ከልዕለ የተፈጥሮ ሃይል ጋር ይላተማል፡፡ ብዙ ሰው ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከራሱና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖርን አይደፍርም፡፡ ተፈጥሮው በማይፈቅደው መንገድ የሚተራመሰው ይበዛል፡፡ ያልሆነውን ለመሆን የሚፍጨረጨር የትየለሌ ነው፡፡ ሰው ከተፈጥሮው ከራቀና ከሰውነቱ ካፈነገጠ አደጋ ላይ ነው፡፡ አንድም አዕምሮው ማሰብ አቁማል፤ ሁለትም ጤንነቱ አጠራጣሪ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ 📍ጥንታዊው ሮማዊው ፈላስፋ ሴኔካ ለሚወደው ጓደኛው ለሉሲሊየስ በፃፈው ደብዳቤ ላይ፡- ‹‹ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተህ ከኖርክ በጭራሽ ደሃ አትሆንም፡፡ ነገር ግን እንደሌሎች ሃሳብ መኖር ከፈቀድክ ግን መቼም ቢሆን ሀብታም አትሆንም›› ብሎት ነበር፡፡ ሴኔካ ሀብትን ከቁስ ጋር አያይዞ አይደለም ይሄን የተናገረው፡፡ እሱ ሃብት የሚለው የመንፈስ ሀብትን ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ከተፈጥሮ ጋር በመግባባት የሚገኝ ነው፡፡ ተፈጥሮን ማወቅ፣ መረዳትና ከተፈጥሮው ጋር ተጣጥሞና ተስማምቶ መኖር ሰውን በመንፈሳዊ ሃብት እንዲበለፅግ ያደርገዋል፡፡ ብዙዎቻችን በመንፈሳችን ያጣን የነጣን ደሃ የሆንነው አንድም ተፈጥሮውን ለመረዳት ባለመጣራችን ነው፤ ሁለትም ሰውነታችንን ከተፈጥሮው ጋር እያቃረንን ስለምንኖር ነው፡፡ 💡ብዙ ሰው በራሱ ሃሳብ ሳይሆን በሌሎች ሃሳብ ነው ኑሮውን የሚገፋው፡፡ ሰው ስለእሱ በሚሰጠው ፍረጃና አስተያየት እየተመራ ህይወቱን ሲኦል የሚያደርግ እልፍ ነው፡፡ በርግጥ የሁሉም ሰው አስተያየት ሰውን ገደል ይከታል ማለት አይደለም፡፡ የዛኑ ያህል የተሰጠን አስተያየት ሁሉ የመጨረሻው እውነትም አይደለም፡፡ በሁለቱ መካከል ማሰብና መመርመር የሚባል ነገር አለ፡፡ የትኛውንም መጤ ሃሳብ በአዕምሮ ወንፊትነት ማጣራት ግድ ይላል፡፡ ሳያኝኩ እንደሚውጡ ሳያስቡ የሰውን ሃሳብና አስተያየት የሚተገብሩ ራሳቸውን አደጋ ውስጥ ይከታሉ ለማለት ነው፡፡ 💎ታዋቂውን የግሪኩን ፈላስፋ ዲዮጋንን አንዱ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡- ‹‹በሕይወትና በሞት መሐል ልዩነቱ ምንድነው?›› ዲዮጋንም፡- ‹‹ምንም ልዩነት የለውም›› አለው፡፡ ‹‹ታዲያ አንተ ለምን በሕይወት ትኖራለህ? ራስህን አታጠፋም ነበር?›› ሲለው፤ ዲዮጋንም፡- ‹‹እሱም ቢሆን ምንም ልዩነት የለውም!›› አለው ይባላል፡፡ ዲዮጋን ሞትንም ሕይወትንም አንድ ያደረገው ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡ 📍የብዙዎቻችን አወዳደቅ ራሳችንን አለመሆናችን ነው፡፡ የእኛ የህይወት መስመር ከሌላው ጋር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ብዙዎቻችን ከራሳችን ተፈጥሮ ጋር ተራርቀን ስላለን ደረጃችንን የምንወስነው በሌሎች መለኪያ ነው፡፡ ዋናውና ስሜትን የሚጎዳው አወዳደቅ ደግሞ በትናንት ውድቀታችን ዛሬአችንን ስናወሳስበው ነው፡፡ ሁለቱም አወዳደቆች ከተፈጥሯችን ጋር በመጋጨት የሚመጡ ናቸው፡፡ 💎ወዳጄ ሆይ... ከተፈጥሮው ጋር ተስማምተህ ኑር፡፡ ከራስህ አትራቅ፡፡ የአንተነትህን ተመን ራስህ አውጣ፡፡ ደስታም ይሁን ሀዘን ያለው አዕምሮህ ውስጥ ነውና በሌሎች መለኪያ ሕይወትህን አታወዳድር፡፡ ደረጃህን በራስህ ወስን፡፡ ሌሎች ምንም ብትሆን አቃቂር ከማውጣት አይቦዝኑም፡፡ ሌሎች እንዲያመሰግኑህ ብለህ ራስህን አትጣል፡፡ 📍ለህሊናህ ታመን፡፡ ውስጥህን አድምጥ! ተፈጥሮህን እወቀው፤ እውነትን ተከተል፡፡ አንተነትህን አናግረው፡፡ መንፈስህን አበልጽገው፡፡ ዕለት ዕለት ከራስህ ጋር ትነጋገር ዘንድ ልመድ! ሞት የሕይወትህ ክፋይ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ መሄድህ ላይቀር ጥሩ ነገር ሰርተህ እለፍ! ከተፈጥሮውና ከተፈጥሮህ ተማር! ቀድመህ ከራስህ ጋር ተስማማ፤ ሌላው ቀሊል ነው!! ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
👍 38 22
#ምክር ለወዳጅ 📍ወዳጄ ሆይ ! ያወቅከው እውቀት ቢመስጥህ የመጨረሻ እውቀት አይደለም ። በገዛ ድምፁ ባብቶ የሚያለቅስ እንዳለ ሁሉ ያወቀውም እውቀት ሲያስቀውና ሌላውን ሲያስንቀው የሚውል ሞኝ አለ ። የሞትከው ትምህርት ያቆምክ ቀን ነው ። በዓይኖችህ የምታየው ወዳጅህን በጆሮህ አትመዝነው ። ስለ ወዳጅህ ሐሜትን ይዘህ አትምጣ ፣ የሰማህበት ቦታ መልስ ስጥ ። የወዳጅ ልኩ ለወዳጅ ጠበቃ መሆን ነውና ። ደጋጎች ባይኖሩ ዓለም እንደ ቆሰለች ትቀር ነበር ። አንተም በደግነትህ የዓለምን ቍስል አድርቅ ።ማፍቀርህን እንደ ውለታ አትቍጠረው ፣ እውነተኛ ሰው ሌላውን ከመውደድ ውጭ ምንም አማራጭ የለውምና ። 📍ወዳጄ ሆይ ! የተዳፈነ እሳት አይሞቅም ። ያልተገለጠ ፍቅርም አያስደስትም ። ፍቅር ተግባር ከሌለው ሐሰተኛ ነው ። የሚሠራውን ሰው የማይሠራ ሰው ከነቀፈው ፣ የተማረን ያልተማረ ካረመው ፣ ፊደል ያላጣራ ደራሲውን ሂስ ከሰጠው ያ ዘመን ፣ ዘመኑ ዘመነ ግልብ ነውና በትዕግሥት አሳልፈው  ። 💡ወዳጄ ሆይ ! ተዘቅዝቀህ ስታይ ሁሉም ሰው የተዘቀዘቀ ይመስልሃል ። ስትወድቅ ሁሉም ሰው ውዳቂ ይመስልሃል ፣ ስትረክስም የሰው ሁሉ ርኩሰት ይታይሃል ። በእግርህ ቆመህ በጭንቅላትህ አስብ ። በእግር መቆም ባመኑበት መጽናት ፣ በጭንቅላት ማሰብ ማስተዋል ነው ። 📍ወዳጄ ሆይ ! ገንዘብህን ይውሰዱብህ እንጂ አመልህን እንዲወስዱብህ አትፍቀድላቸው ። ስምህን ባገኙት ጭቃ ሊያቆሽሹት ይችላሉ ፣ አንተነትህን ግን አንተ ብቻ ትለውጠዋለህ ። ከሰረቁህ ይልቅ የምትጥለው እንዳይበዛ ተጠንቀቅ ። 💡ወዳጄ ሆይ ! በወንድምህ እጅ ያለውን ክብር ለእኔ ቢሆን ብለህ አትናፍቅ ። ምኞት ምቀኛ ፣ ምቀኝነትም ክፉ እይታ ፣ ክፉ እይታም ነፍሰ ገዳይ ያደርጉሃልና ።  ዕድሜህ እንዳያጥር ትልቅ አዋራጅ አትሁን ። መኖርህ ለሚያስደስታቸው ቅድሚያ ስጥ ። ለሚጸልዩልህ ምርኮህን አካፍላቸው ። ያልተቀበረ ሬሳ እየገደለህ ይመጣል ። ያልተሻረ ቂምም እየመረዘህ ይመጣል ። ወዳጄ ሆይ ! ተቃውሞን ከፈራህ ሥራ አትጀምር ። ነቀፋን ከሰጋህ ከቤትህ አትውጣ ። ውግረትን ካልጠበቅህ ባለ ራእይ አትሁን ። ለማግኘት ማጣት ፣ ለመክበር መዋረድ አስፈላጊ ነው ። ጸጋ ፈጣሪ የሚበዛልህ በሁለት ነገሮች ነው ። የመጀመሪያው በትሕትና ፣ ሁለተኛው በባለጌዎች በመሰደብ ነው ። 📍እናም ወዳጄ ! ጥቅም ለማግኘት ብለህ የተዋጋኸው ውጊያ በመጨረሻ ባለጠጋ እንጂ ባለ ኒሻን አያደርግህም ። ከገንዘብ ክብር እንደሚበልጥ ተረዳ ። የረዳህን ፈጣሪ አልሰጠኝም ብሎ ማማት ነውና እያለህ ከሌላቸው ጋር አትሻማ፣ የረዳህን ፈጣሪ አልሰጠኝም ብሎ ማማት ነውና እያለህ ከሌላቸው ጋር አትሻማ ። የሌለህን ስትመኝ ያለህን እንደምታጣ ተገንዘብ ። ግማሽ ደግነት የክፋት ያህል ነውና ለጉዳይህ ብለህ ቸር አትሁን ። የጎደለ እንስራና ባዶ አዳራሽ ድምፅ ያበዛሉና በእውቀትና በመንፈስ ሙሉ ሁን ።            ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
61👍 31
👍 6 1
🌗 ቅብጥብጡ ውሻ ✨የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡ 💡በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡ የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡ 💡የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡ 💡ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡ ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . . 💎ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!     ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ ውብ ጊዜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
107👍 56
📍ወዳጄ ሆይ አትድከም፣ አትዘን ማን ያውቃል ሸክምህና ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል። በቀልባቸው ንፅህና ብቻ ሰላማቸው የበዛ ሰዎች አሉ። ቀልባችሁ ንፁህ ሲሆን ሰላማችሁ ይበዛል፣  ለሌሎች መልካም ስትመኙ በረከታችሁ ይሰፋል። ልብህ የተጠራጠረዉን ነገር ተው፤ ልብ ከዐይን በላይ ያያልና።ወደ ፊት የሚሆነውን ሳትበሳጭ ሳትሰለች በትግስት ጠብቅ።የማይረባና ጥቅም የሌለው ነገር በመከተል ጉልበትህን አታባክን። ወዳጄ ሆይ ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ! ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል፡፡ የጨለመው ይበራል ፣ የጠፋዉም ይገኛል ። ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በፈረሰና በተናደ ጊዜ ይህንን ክፋ ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያ ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ።ያለነው የፈተና ምድር ውስጥ ነው። በበሽታ መፈተን አለ። በኀጢአት መፈተን አለ። በዕዳ መፈተን አለ ፣ የምድር ፈተናዎቿ ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም። እናም ወዳጄ ያለህን የሌለህን ገንዘብህን ሁሉ አንድነት አከማችተህ ስትሰራበት ሁሉንም ባንድ ጊዜ ስትከሥር አጣሁ ከሠርኩ ብለህ ቃል ሳትተነፍስ አሁንም ሰርተህ ለማተረፍ ከሥር ጀምረህ እንደ ገና አንድ ብለህ ድከም። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ይበርታ። ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ።             ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
58👍 26
📍በሠዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳ ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው። ሕይወት ጠመዝማዛ ብትሆንም ውብና ተስፋን የተሞላች ናት። 💡በዚህ አለም ሁሉ ነገር አበቃ፣ አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል፣ የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር፣ ዙሪያችን ጭው ያለ በረሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሬያለሁ። 📍ህይወት እንደ ሳንቲም ናት ሁለት ገፅታዎች አሏት ፣ ተቃራኒ ግን ማይነጣጠሉ ገፅታዎች ። በህይወት እስካለን ካአንዱ ገፅ ብቻ ስንኖር ማለፍ የለም፣ እያንዳንዷ ሁኔታ ከጀርባዋ ተቃራኒ ገፅ አላት እናም ሳንቲም ያለ ግልባጭ ገፁ ምሉዕ እንደማይሆነዉ ያለ ሀዘን ደስታ ፣ ያለ ሞት ህይወት ፣ ያለ  ለቅሶ ሳቅ ፣ያለ ድህነት ሀብት ፣ ህይወትን ከነ ህብረ ቀለሟ አምነን መቀበል አለብን ፡፡ 💡እድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! "ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ ያቆጠቁጥ ዘንድ፣ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው" ። ✍አለማየሁ ዋሴ ውብ አሁን♥️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
49👍 20
⚡️የጨረቃዋን ውበት የሚሻ ጨለማውን አይሸሽም፣ ጽጌረዳዋን ብሎ የሄደ እሾሁን ፈርቶ አይመለስም ፍቅርን ከልቡ የሚፈልግ ሰው ከራሱ አይደበቅም ፣እራሱን ፈጽሞ አይሸሽም ። የምንፈራው ነገር ብዙ ጊዜ የምንመኘውና የሚበጀንን ነገር ነው። ሰዎች ከእውነተኛ ፍላጎታችን የመሸሽ ባህሪ አለን። በምክንያቶች እራሳችንን እያታለንን፤ ሊነቃ የሚታገለውን ድብቅ ምኞታችንን መልሰን እናስተኛዋለን። ✨ፍርሃታችንን ብንከታተለው..ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚባለው። ውብ ነገሮችን ለማግኘት ሰው ፍርሃቱን አልፎ መሄድ አለበት፤ በምንፈግልጋቸው ነገሮችና በእኛ መካከል የቆመው ትልቁ ግድግዳ ካለማውቅ የሚመነጨው ፍርሃት ነው:: ጨለማውን የደፈረ ጨረቃን፤ እሾሁን ያልፈራ ጽጌረዳዋን፤ እራሱን ያወቀ ፍቅርን ማግኘቱ አይቀርም:: 🔑ፍርሃታችንን....እንከተለው ፤ የፍርሃት ዱካ እውነትኛ ምኞታችንን ያሳይን ይሆናል። ያንቀላፋውን ምኞት የሚቀሰቅሰውም ይኸው ለፍርሃት የምንሰጠው ምላሽ ብቻ ነው።              ውብ አሁን♥️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
42👍 34👎 1
🔺“ሰው - ራሱን እንኳ የሚያስደምመውን ተቃርኖ በውስጡ ተሸክሞ የማይፈራ። “ሰው” -ጨክኖ መግደልን ከአፍቅሮ መግደል ጋር አስማምቶ ሲኖር እንቅልፍ የማያጣ። ሰው' -ሰፍሮ ያልጨረሰው መሬት ቢጠበኝ ብሎ የሚሰፋ። “ሰው -የስጋ ደካማነቱን ማካካሻ ከምናቡ ቆርጦ፥ በስራው፣ በሰራው እና በሚሰራው፤ ደካማነቱን የረታ፣ የሚረታ። “ሰው -የማያቋርጥ የተቃርኖ ጅረት፣ የማይጠግ ጥበብ ምንጭ፤ የፍርሀት ልጅ፣ የድፍረት ወላጅ። “ሰው - ምንነቱ ከማንነቱ የተምታታ፤ ምንነቱ ማለቂያ ቢስ፣ በማንነት የሚታሰር። ሰው ፥ ይህ ሰው! እንዴትና በምን ?” ምንስ ሆኖ ?” ራሱን፣ ማንነቱን፣ ሰው-እነቱን ረሳ ?! ከዚህ በላይስ ምን ይገርማል ! 📍ለማንኛውም ካላስታወሳችሁ አይፈረድባችሁም፡፡ ራሱን የረሳ ሰው፥ ሌላ ነገር አስታውስ ተብሎ ሊጠየቅ አይገባም፡፡ ግን ለምን አይገባም ?” ባይገባም፣ ባይገባም ግን ይጠየቃል፤ ይጠይቃል፣ ይመልሳል። የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን፣ የኖረውን ሳይሆን የተነገረውን፣ እውነቱን ሳይሆን የተባለውን ይመልሳል። ሰው መሆን በጣም ይደንቃል። ሰው መሆኑን የረሳ ሰው፥ ወንድ መሆኑን ግን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” ሰው መሆኑን የረሳ ሰው፥ ነጭ ወይም ጥቁር መሆኑን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” መሬት ላይ የተፈጠረ ሰው፥ መሬትን ረስቶ ሀገሩን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” ከሌላው ጋር መግባቢያ ቋንቋ እንዳለውና ይህም ደግሞ ከየትኛውም ፍጡር እንደሚለየው ረስቶ፥ መናገሪያውን ማስታወሱ አይደንቅም ?” ብትረሱም አልፈርድባችሁም። ዞሮ ዞሮ ምንም ነገር እንዳለኝ ወይም እንደነበረኝ ያወቅሁት፥ ሳይኖረኝ ሲቀር ነው። እናትም፣ ቋንቋም፣ ሀገርም፣ አያትም፣ አባትም፣ ሃይማኖትም ሁሉም፡፡ ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
54👍 30
እነዚህ መፅሐፎች ቅፆች ያሉት ሰው የሚሸጥ ካለ እንደው ወይም የምታውቁት ሰው ካለ ብትተባበሩኝ @Nagayta በዚህ ሊንክ ልታገኙኝ ትችላላችሁ
Mostrar todo...
👍 16 5
✨«እናንተ የዓለም ብርሃን ፣ የምድርም ጨው ናችሁ» 🔷ብርሐንና ጨው ከተባልን ዘንዳ፤ እንግዲያውስ እውነተኛው ብርሐንና እውነተኛው ጨው ምንድነው አልን ! ቃሉን ልንተነትን ሳይሆን ቃሉ ያጫረብንን መረዳት ከአኗኗራችን ዘይቤ ጋር አዛምደን፣ በዘመናችን ታይታ ወዳድነት እና የመታየት ልክፍት፥ ሳናውቅ ለገባን እኛ ነገሩን ለማስታወስ ያህል ይህን አልን! 📍ብርሐን ያሳያል እንጅ አይታይም! ብርሐን የማይታየው ጨለማ ውስጥ ስለሆነ አይደለም፣ ይልቁንም ብርሐን ብርሐኑን የሚያበራው ወደራሱ ሳይሆን ወደሌሎች በመሆኑ ነው! ሌላውን ለማሳየት እንጅ ራሱን ለማጉላትና ለማድመቅ የሚታገል ብርሐን በዙሪያው የሚረጨው ጨለማ ብቻ ነው! እዚህ ላይ ብርሐን ስል የብርሃን ምንጩን ጭምር ማለቴ ነው።ብርሃን ተፈጥሮው ማሳየት እንጅ መታየት አይደለም። 🔷ፀሐይ በምትረጨው ብርሃን ዓለም ይነጋል ፤ ፍጥረት ሁሉ ይደምቃል፣ ተክሎች ያድጋሉ፣ አበቦችም ይፈካሉ፣ ቆፈን ይገፈፋል፤ ፀሐይን ራሷን ግን ለሴከንዶች እንኳን ማየት አንችልም።ታሳያለች እንጅ አትታይም! የቤታችንን አንፖል ከነመኖሩ የምናስታውሰው ቤታችን ሲጨልም ብቻ ነው፣ ግን ሁሉን ነገር የምናየው ከአንፖሉ በሚወጣው ብርሃን ነው። አንድ ሰው ሻማ የሚለኩሰው ሻማውን ሲያይ ለማምሸት አይደለም ፣ በሻማው ብርሃን አካባቢውን ሊያደምቅ ነው! መታየትን የምትሳሳ ነብስ ብርሐን አይደለችም፤ ይልቅ ብርሐን ያስፈልጋታል፤ በሌሎች ጨለማ የምትሳለቅ ነፍስ ብርሐን በውስጧ የለም ፣ብርሐን በተገኘበት የሌሎችን ጨለማ ያነጋል እንጅ በጨለማቸው አይዘባበትም። 📍ጨው እና ብርሃን ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፤ ጨው ብቻውን ምግብ ነኝ ብሎ ማዕድ ላይ አይኮፈስም፤ ቢኮፈስም የሚነካው የለም! ጨው ምግቡ ውስጥ አይታይም ግን ምግቡን ያጣፍጣል! በአጭሩ ነፍሳችሁ መታየትን መጉላትን መደነቅን መወደስን ከፈለገች «ሰዋዊ ነው» በሚል ትሁት መታበይ ራሳችሁን አታታሉ። እንደዛ ካሰባችሁ ብርሐንም ጨውም አይደላችሁም! እንደውም ትክክለኛ ጨውነታችሁ የሚታወቀው በእናተ በጎነት ሌሎች ሲወደሱ ነው! በተረት እንዝጋው «በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ» ይሄው ነው! ✍አሌክስ አብርሃም ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
56👍 29
💡ወንድሜ! ራስ ወዳድነት የታወረ የበላይነትን የመሻት መክንያቱ ነው።የወንድምህ የበላይ የመሆን ፍላጎት ጎሳና ነገድ እንዲፈጠር ምክንያቱ ሆነ፤ጎሳና ነገድ ደግሞ እርስ በርስ መጋደልና አንዱን መጨቆን አስከተለ። 📍ፍቅር በእዉቀት ሃይል ታምናለች ፤ ፍትህ ደግሞ በጨለማው አላዋቂነት ላይ ትሰለጥናለች። ታላቋን ባቢሎን ካጠፍ ፣የኢየሩሳሌምን መሰረቶች ካናወጠ፣ሮምን ከፍርስራሿ ጋር ካስቀረዉ ከዚያ ሰልፍ ከሚያቀብል ሥልጣን፣አላዋቂነትና ጭቆናን ከሚያንሰራፋ የሥልጣን ሃይል ጋር ፍፁም ትቃረናለች። ዳሩ ታላላቅ ሰዎች ተብለው ሲጠሩ የኖሩ እንዲህ አይነቶቹ ወንጀለኞች ናቸው። 📍አኔ የምቀበለው ብቸኛ ስልጣን በተፈጥሮ ሕግ ላይ የተመሰረተዉን ፍትሕና እሱን የሚቀበለውን እዉቀት የያዘውን ብቻ ነው። የራሱን ጉዳይ ብቻ የሚያቅፍ ባለሥልጣን ላይ ፍትህ ምን የምታደርግ መስልሃል? አንተ ወንድሜ ነህ፤ስለዚህ እወድሃለሁ! ፍቅር ደግሞ ታላቅ ፍትህ ነው! ከየትኛውም ጎሳ ወይም ነገድ ብትመጣ  ለአንተ የምሰጠው ፍትህ "ፍቅር" ብቻ ነው። ❤️ፍቅር ስለ ራስ ብቻ ማሰብ ሳይሆን ስለሌላውም ማሰብ ነው ። ፍቅር ሲታመም ሁሉም ነገር ይታመማል። ስብእናም አስተሳሰብም  ስሜትም ይታመማል ። ወዳጀ ሆይ አንተም አስተውል ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና!!                     ✍ ካህሊል ጂብራን ውብ አሁን ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
47👍 24
🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። 💛በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ ይሁንልን🎄 ❤️🏑 መልካም የገና  በአል 🏑 @ETHIOHUMANITY @ETHIOHUMANITY
Mostrar todo...
29👍 14
💡ያለፈ ጥረታችንን ሳስታውስ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ። ሃገር ስትታመም፣ ብርድ ብርድ ሲላት፣ ተስፋና ሥጋት፣ ወኔና ፍርሃት፣ ምርቃትና እርግማን - እንዳሻው ሲንጣት ከሆነብን ይልቅ እየሆነ ያለው ያሳስበኛል ፣ ከእሳቱ በላይ አያያዙ ያሰጋኛል፣ ከጥያቄው በላይ ምላሹ ይስበኛል። 📍ችግር ፈቺነት ከሚጠይቀው ጥበብ ውስጥ ዋነኛው የሚመስለኝ ለሌላ እንከን ገርበብ የማይልን በር የመተው ብልህነት ነው። አንድን ሕመም ስታክም 'ከተጠባቂው' ጎንዮሽ እንከን ውጭ ሌላ ህመም እንዳልፈጠርክ ማረጋገጥ ግዴታህ ነው። በስመ መድኃኒት የተገኘው አይደነጎርም፣ አንድ ችግር ፈትቷል ተብሎ ለሌሎች ችግሮች ሰበብ እንዲሆን አይተውም፣ በእውቀት እንጂ በደመነፍስ አይቃኝም። 💡በእንዲህ ዓይነት ጊዜ ጥሞና ነው የሚያስፈልገን፣ የሰከነ ውይይት ነው የሚያሻን፣ 'ምን ብናደርግ ይበጃል?' መባባል አለብን። ጊዜው እሾህ እያወጣን ጦር የምንተክልበት አይደለም፣ እንቅፋት እየነቀልን ፈንጂ የምንቀብርበት አይደለም፣ ጀግነን አዙሪቱን እኛው ጋ የምናቆምበት እንጂ፣ የክብሪቱን እሳት እፍ በምትልበት ሰዓት ካላጠፋኸው እፍ ብሎ ያጠፋሃል። 📍'ካልደፈረሰ አይጠራም' የሚል አስተሳሰብ የሚያቀነቅኑ ሰዎች ዛሬም በዙሪያችን እንዳሉ ማሰብ ያደክማል፣ ሳይደፈርስ ማጥራት ከተቻለ ለምን ይደፍርስ ብሎ መጠየቅ ግን ግድ ነው። የደፈረሰ ሁሉ ይጠራል ወይ ማለትም ያስፈልጋል፣ ድፍርስ ሲጠራ ዝቃጭ እንደሚተው አለመርሳትም ደግ ነገር ነው። ምንም ብንታገል ልናስቀር የማንችለው አንድ ነገር ለውጥ ብቻ ነው፣ ለበጎ አልያም ለክፉ እንዲሆን የማድረጉ ድርሻ ግን እጃችን ላይ አለ። ችግሩ 'እንዲሆን' የምንፈልገው አለ - ሆነን ግን አንጠብቀውም.. 'እንዲመጣ' የምንሻው አለ - የምናዋጣው ግን የማይገባውን ነው። 💡በእንዲህ ያለ ቀውጢ ጊዜ ወሳኙ ሰው አንተ ነህ፣ ዘረኛ ሳይሆኑ ነው ዘረኝነትን ማረቅ የሚቻለው፣ ሳይሰርቁ ነው ዘራፊነትን ማስቆም የሚቻለው፣ አድማጭ ሆኖ ነው ጫጫታን ማስቆም የሚቻለው፣ ግማሽ መንገድ መጥቶ ነው 'እስኪ እንነጋገር' የሚባለው፣ለውጡን ተለወጠው እንጂ ከሌሎች አትጠብቀው፣ አርዓያ ሁን የሚመለከቱህ አሉ ፣ የሚከተሉህ አሉ። ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ ስህተት በመንቀስ አትሙላው ብሽሽቁ፣ አተካራው፣ መናቆሩ፣ ጎራ ማበጀቱ ፣ አሁን ፈጽሞ አይጠቅምም። እንዲመጣ የምትፈልገው ለውጥ አሁን አንተ ያልሆንከው ወይም የሌለህ ከሆነ ለውጡ መቼም አይመጣም መቼም!! 🔑 የትኛውም የችግር ቁልፍ የፍቅር ስሪት ከሌለው መሰበሩ አይቀርም ፣ ወደድክም ጠላህ እውነተኛውና ዘላቂው ኃይል ፍቅር ብቻ ነው ፣ የረቀቀ ሳይንስም ሆነ የጠለቀ አስተሳሰብ ፍቅርህን አያክልም፣ የገዘፈ ኃይልም ሆነ ልክ የለሽ ስልጣን ፍቅርህን አይተካም፣ የፍልስፍናህ ጥግም ሆነ የልሂቅነትህ ጠገግ አፍቃሪነትህን አይተካከልም። የአብሮ መኖር እንከናችንን የሚደፍን ሕብር እንጂ የመለያየት ግንብ የሚገነባ መዝሙር ሰልችቶናል፣ ከነበርክበት 'የተሻለ' ብርሃን ስትፈልግ ወደ አልነበርክበት ጨለማ አለመግባትህን ማረጋገጥ ብልህነት ነው!!   ✍ ደምስ ሰይፉ ውብ ጊዜ ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
44👍 31👎 1
10
❤️ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነታችን እንደ ወንዝ ይሁን! ሳንመርጥ፣ ለለመነን ሁሉ እጃችንን እንዘርጋ። ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ይመሰክራል፤ የኛም ደግነት እንዲሁ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ፤ ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት የተሞላበት ይሁን። 📍መርዳት ዕድል ነውና እንጠቀምበት! ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የለም  ለፈጣሪ እጅ ሆነን እንደምንሰጥ ልናስብ ይገባናል። እውነተኛ ስጦታ ከትርፍ ሳይሆን ካለን ላይ ነውና ተጎድተን እስክንሰጥ ድረስ ገና እንዳልሰጠን ልንረዳ ይገባል፡፡ እያዩ ፈንገስ በመድረኩ ላይ ሲናገር "ላለመርዳት ኪስህን ሰበብ አታድርግ። ባዶ ኪስ ነህ ማለት የምትሰጠው ምንም ነገር የለህም ማለት አይደለም፤ ቢያንስ የምትሰጠው ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ አለክ ማለት እንጂ። ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ መስጠት ቢያቅትህ፥ በባዶ ኪስህ እጁን እንዲያስገባ ፍቀድለት። ቢያንስ አንድ እጁን ከብርድ ትከላከላለህ'' ይለናል ። ❤️ሰውን እንደራስ ለመውደድ ቅን አዕምሮ፤ ደግ ልብ ይፈልጋል፡፡ ቅንነትም ሆነ ደግነት እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይደለም፡፡ ገንቢ ሕሊና ቀድሞውኑ በመልካም አስተሳሰብ የታነፀ ነው፡፡ አንተ ሕሊናህን በወጉ ካልሰራኸው አንተን እንደአዲስ አይሰራህም፡፡ እንዲሰራህ ልትሰራው ይገባል፡፡ እንዲያውቅህ ልታውቀው ግድ ይላል፡፡ ወደውስጡ ስትጠልቅ ይዘህ የምትወጣው ራስህን ነው፡፡ ወደባህሩ አንተነትህ ስትሰምጥ የምታገኘው ሰውነትህን ነው፡፡ ብልህ ሰው አዕምሮውን ይሠራል፤ በሰራው ሕሊና እየተመራ የሕይወት ኮምፓሱን ያስተካክላል። ፈጣሪ ለሁላችንም ልበ ሰፊና ቅን ልቦና ይስጠን! ውብ አዳር❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
68👍 32
📍#እሮጣለሁ ወደ ጎዳና እየወጡ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ❤️ሁላችንም በትብብር ችግሩን ለመቅረፍ የሚጠበቅብንን እንወጣ። የሜሪጆይ ቤተሰብ እያደረገ ያለውን ጥረት እደግፋለሁ። እኔም ከቤተሰቤ ጋር በሜሪጆይ ሩጫ ላይ እሳተፋለሁ። ታህሳስ 14; 2016 ተመዝግቧል! እሮጣለሁ፤ #ወገኖቼን_ከጎዳና_አነሳለሁ 1) የሩጫው መሪ ቃል፡- አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ወደ ጎዳና የወጡ ወገኖቻችን በተለይም ከልጅ ጋር ጎዳና ያሉትን እናቶች በማሰብ፤ የሩጫው መሪ ቃል “እሮጣለሁ፤ ወገኖቼን ከጎዳና አነሳለሁ!” የሚል ነው፡፡ 2) ሩጫው የሚደረግበት ቀን፡- ታህሳስ 14፤ 2016 3) መነሻና መድረሻ፡- ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ 4) ሩጫው የሚሸፍነው ኪሎ ሜትር፡-               5 ኪሎ ሜትር 5) የቲሸርት ዋጋ፡- 400 ብር ለአዋቂዎች እና 300 ብር ለልጆችና አዋቂዎች 6) ቲሸርት ስርጭት የሚደረግባቸው ቀኖች፡- ከታህሳስ 8 – 13፤ 2016 ዓ. ቲሸርት መግዢያ መንገዶች፤ በሜሪጆይ ቴሌግራም ቦት @MaryJoybot በኩል መመዝገብ ይችላሉ ለበለጠ መረጃ፤ ስልክ 0994535353 | 0983636363 | 0987626262
Mostrar todo...
👍 27 10
👍 3 2
❤️ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም። ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው። ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው። እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፤ ለሌሊት ቀን አለው። ላንተም ጊዜ አለህ። ጊዜን የሚሰጥ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ እመንና ጠብቅ። ጊዜ ለታጋሾች የማታሳየው የለም። መስበርም መጠገንም ትችላለች ፣ አንተርሳ ትዘቀዝቃለች ፣ ዘቅዝቃ ታቃናለች። ለጊዜ የሚሳናት የለም ። እንዳወጣች ታወርዳለች ። አንተም በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ። ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት ብስለትህን እና ራስ ገዝነትህን አሳይ። ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ። 📍እንደ እንስት ውበት ያጌጠው  ህይወታችን ፣ ቀን ሲገፋ ይደበዝዛል እስከተፈቀደልን አብርተን ጊዜ ሲቋጭ ጭልመት እንላበሳለን። አጥቶ ማግኘት እንዳለው አግኝቶ ማጣት አለ ፣ ብርሀኑ ቢጨልም አንከፋ ለበጎ ነው፣ ጭልመት በብርሃን ሲቀየር አንገረም። ምንም ዘላለም ሊቆይ አልመጣም። ተስፋ ከቤታችን አይጥፋ!              ውብ ምሽት❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
47👍 34
🌗በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ስንት ወርቅ ይዛችሁ እንደመዳብ ካቀለላችሁት ከእጃችሁ ሲወጣ ይቆጫችኋል። ዛሬ እናታችሁ አጠገባችሁ ስላለች አመስግኑ ዛሬ አባታችሁ ስላለ ተመስገን በሉ ዛሬ ጤና ስላላችሁ ፣ ዛሬ ወጥታችሁ መግባት ስለምትችሉ አመስግኑ። 💡ይህ ሁሉ ባይኖራቸሁ እንኳን በህይወት ስላላችሁ ተመስገን በሉ፣ በህይወት ያለ ነውና የተበላሸውን ማስተካከል የሚችለው። በህይወት ከመኖር በላይ ዋጋ ያለው ነገር የለም፤ የምናገኘውም የምናጣውም በህይወት ስላለን ነው። መኖርን ደግሞ በነፃ ነው ያገኘነው፣ ምሬት ዓይንን ያጨልማልና ደስተኛና አመስጋኝ እንሁን። 💡እጅግ ውድ የሆኑ ነገሮች በነፃ ነው የተሰጡን፡፡ ፈጣሪ የአቅማችንን ልክ ስለሚያውቅ የከበሩትን ነገሮች ያለክፍያ አስረከበን፡፡ አየር፣ውሀ፣ ደማችን፣ አካላችን፣ ፀሀይዋ፣ ዝናቡ እና አፈሩ በክፍያ ቢሆኑ ማን መግዛት ይችል ነበር? ህልውናችን በነኝህ ነገሮች እጅግ የመቆራኘቱን ያህል በገንዘብ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ እኔነኝ ያለ የምድር ባለጠጋስ ወጪውን ይችለው ነበር ወይ ? ❤️በነፃ የተሰጡን ባይኖሩ ኖሮ ሰው በውድ የሚራኮትባቸው ቁሶችስ መች ይኖሩ ነበር፡፡ ሰው ርካሹን በውድ ይሸጣል ፈጣሪ ግን ውዱን በነፃ ይሰጣል፣ ማጉረምረሙን ትተን ስለ ፈጣሪ ለጋስነት እናመስግን ከምናስበው በላይ ባለፀጎች ነን፡፡ 🌗ስለ ሁሉ ነገር አመስጋኝ ሁን ማመስገን ስትጀምር አለም ወደአንተ ታዘነብላለች ነገሮች በሙሉ መልካም ይሆናሉ። ካሰብከው በላይ ሁሉ ነገር ሲስተካከል ሲያምር ታየዋለህ በምድር ላይ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሆነ ስታውቅ፣በማመስገን ስትታጀብ ቤትህም ይደምቃል ኑሮህም ይሞቃል በረከት ሁሉ ወዳንተ ይመጣል። ልባችን ሁሌም ለምስጋና ክፍት ይሁን!          ውብ ቅዳሜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
50👍 35👎 1
Mostrar todo...
3
💎እንደ ንስር ወደ ላይ ከፍ በል ወዳጄ ንስር ሁን በቀቀንነት ይቀርብህ። በቀቀን የሌሎችን ሰዎች ሕይወት በመመሰል ውድድር ከፍ ብሎ መብረር አይችልም። ስጦታውን፣ እውቀቱን እና ክህሎቱን ከማዳበር ይልቅ ሌሎችን መስሎ መኖር ይመቸዋል። ሕይወት ደግሞ በተቃራኒው ከበቀቀኖች ይልቅ ለንስሮች ፍሬዋን ትሰጣለች። ተፈጥሮ ብዙ ቀለም ፣ ብዙ ዕድል፣ ብዙ ፈተና ናት። ንስር አሞራ የለውጥ ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው በስራ የዳበረ ከእውነተኛው ዓላም ጋር የተሰናሰለ ስብእና ስለገነባ ነው። 📍ንስር የአእዋፋት ሁሉ ንጉስ ነው ሲባል በዋዛ እንዳይመስላችሁ። ንስር የሃይል ሚዛኑን ለመጠበቅ በቂ የሆነ ልምምድ የሚያደረግ ፣ የሚፈልገውን ነገር ከማድረግ  የማይቆጠብ ቁርጠኛ የስነ ልቦና ተምሳሌት ነው ። ህይወቱን ሙሉ ትኩስ ስጋ እያደነ ነው የሚኖረው ። የሞተ ነገር አይነካም። የእለት ሲሳዩን እያደነ ይበላል እንጅ እንደ ቁራ የሞተ በክት እያሸተተ አይቀላውጥም። ሃይሉን እያደሰ የእንደገና ድልና ስኬቱን እያጣጣመ በንግስናው እስከወዲያኛው ይዘልቃል። ሰማዩ ሲጠቁር ደማናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች እዕዋፋት በየ አለቱና በየጥሻው ችፍርግ ወስጥ ይደበቃሉ በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡ ሲጀምር ንፋሱን በመሞገት የራሱን ጥንካሬ ይላካበታል።  የነፋሱን አቀጣጫ በመከተልም ይበራል። ረሱን ወደላይ ለማምጠቅና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል ፣ በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል። 💎ንስር ወጀብ ከመምጣቱ ብዙ አስቀድሞ ማወቅ ይችላል። እንዳወቀም ከፍታ ቦታ ለይ ይቀመጥና ንፋሱን ይጠብቃል። ወጀቡ ሲመጣ ከተቀመጠበት በመብረር ንፋሱ አግዞት ከወጀቡ በላይ እንዲበር ያደርገዋል። ወጀቡ ከታች ያለውን ዓለም ሲያተራምሰው፣ ንስሩ ከወጀቡ በላይ ይንሳፈፋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል። ንስሩ ወጀቡን አላመለጠውም ፤ ተጠቀመበት እንጂ !! 📍የሕይወት ወጀብ ወደ እኛ ሲመጣ፣ ልክ እንደ ንስሩ ከወጀቡ በላይ መብረር እንችላለን፤ በሽታን፣ አደጋን፣ ውድቀትን፣ እና ሃዘንን ወደ ሕይወታችን የሚያመጣውን ንፋስ ለከፍታችን መወጣጫ ልናደርገውው እንችላለን። 🔑እናም ወዳጄ አንተም መከራንና ፈተናን አትፍራ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥም ቢሆን መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን የአዳዲስ ሐሳቦች መነሻ የጥናካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ፣ አልፎም ወደ ላይ የምትመጥቅበትና ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት ዕድል አድርገው። እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራው አትሽሽ ከችግሩንም አትደበቅ መከራን ለጥንካሬና ለበረከት ተጠቀምበት።           ውብ የስኬት ጊዜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
45👍 30
👍 10
📍የተሻለ አለህ በአውሎ ንፋስ ውስጥ ብትሆን፣ ዶፍ ዝናብ ቢወርድብህ፣ ዋጋህ ያነሰበት፣ መኖርህ የማይቆጠርበት፣ አበርክቶትህ የማይታይበት፣ ስራህ የማያፈራበት፣ ማንነትህ የማይመረጥበት ስፍራ ብትኖር እንኳን ፈጣሪ አብሮህ ካለ ሁሌም የተሻለ ከፍ ያለ ነገር አለህ። 🔷ምንም እንኳን እምነታችን ቢጎድል፣ ክፋታችን ቢበዛ፣ ሃሳባችን ቢያንስ፣ ምግባራችን የወረደ፣ ስራችንም አሳዛኝ ቢሆንም ፈጣሪ ግን ጥሎ አይጥለንም።፣ ትቶ አይተወንም ሁሌም ይመለከተናልና መቼም ችላ አይለንም። የተውን ሰዎች ይኖራሉ፣ ያገለሉን፣ የተጠየፉን እንዲሁ እንደዋዛም የናቁን ሰዎች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን በፈጠረን አለመገፋታችን አለመረሳታችን ነው። ♦️የተሻለ አለህ! ከዛሬው የላቀ፣ ከትናንት የገዘፈ፣ ከአሁንህ ያየለና ከፍ ያለ ስፍራ ይኖርሃል። የማይቀየሩ የሚመስሉ ከባድ ሁኔታዎች ይቀየራሉ፤ ይወርዱ የማይመስሉ ሸክሞች፣ ይፈቱ ያልመሰሉ ችግሮች፣ ይስተካከሉ ያልመሰሉ ውጥንቅጦች ይወርዳሉ፣ ይፈታሉ፣ ይስተካከሉ። እምነትህ ቢፈተን ግራ አትጋባ ይልቅ ለተሻለ ክብር እንደታጨህ አስተውል፤ በፈተናህ ብዛት አትደናገር ይልቅ የድልህ ቀን ቅርብ እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት የማትሸበር፣ ለምድራዊ ፈተና የማትበገር፣ ከፈጣሪህ ውጪ እንዳልሆንክ አስተውል። 🔷አንዳንዴ ማሳለፍ እየቻልን አቅፈናቸው የምንቀጥላቸው ብዙ ኮተቶቻችን ጣእሙን ማየት እንዳንችል ሁሉ ነገራችንን ዘግተንባቸዋል። ለማማረር እንጂ ለማመስገን ስንፈናል ለማዘን እንጂ ለመደሰት ጉልበት አጠተናል። መቆየት በማይገባን ቦታ ላይ በመቆማችን ማሳለፍ የሚገባንን አላፊ ሃሳቦችን እንዳያልፋ መንገድ ዘግተንባቸዋል እሰኪ ነቅነቅ እንበል እናሳልፋቸው የሚመጡት ሁሉ እንደአመጣጣቸው እንሸኛቸው አኛም ከቆምንበት አስተሳሰብ ስናልፍ ሁሉም ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን። ሁሉም ያልፍ የለ ትላንትናም አልፏል ዘሬም ታልፋለች ነገም ትቀጥላለች እኔም አንተም እናልፋለን ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል።ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የያዘ፣ በሁሉ ውስጥ ያለው አምላክህ ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ አትጠራጠር፤ ለተሻለው ስፍራ እንደሚያበቃህ እምነት ይኑርህ። 🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል። ውብ አሁን ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
56👍 29
19👍 1
📍ምን ይዤ ልሔድ ልድከም? ታላቁ እስክንድር እንዲህ አደረገ አሉ። ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው። በክንዱ ስንቱን ያስገበረው ታላቅ፤ "ምንም ይዤ አልሄድም" ሲል ተናገረ። አንዳንዴ የምንኖረው እስከመቼ ነው ብለን እራሳችንን ከምር ብንጠይቅ መልሱ ያስደነግጠናል። 💡 ምክንያቱም የምንጨነቀው ከምንኖረው በላይ ነው። ፈገግታን፤ ሳቅን፤ ደስታን ሳያውቁ የሚሞቱ ሰዎች ሞልተዋል። ኖረው ሳይሆን፤ ሞተው ወደ መቃብር የሚወርዱ ምስኪኖች ብዙ ናቸው። አብዛኛዏቻችን በቁማችን ሞተናል፤ ምክንያቱም መኖር ከመንቀሳቀስ እና ከመተንፈስ የጠለቀ ስሜት አለውና። መኖር ማለት እራስን ከአሁኗ ደቂቃ ጋር አጣምሮ፤ መንፈስን፤ አይምሮን ከተፈጥሮ ጋር አዋህዶ፤ ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው የሚለውን የጠቢቡን መርህ ተከትሎ ህይወትን መምራት ማለት ነው (በጥቂቱ)። ይህ ትርጉም ለእያንዳንዳችን በልካችን መበጀት ይችላል። አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለው፤ የምንጨነቅለት ነገር ሁሉ ከዚህ አለም ስንሄድ ይዘነው የምንሄደው ካልሆነ፤ ምንድን ነው ነጥቡ? የብዙዏቻችን ኑሮ ይዘነው ለማንሄድ ወይም ስማችንን ከመቃብር በላይ ለማያስጠራ፤ ተራ ነገር ተሰውቷል። የቱ መቅደም እንዳለበት አናውቅም፤ እኛ ወይስ ጭንቀታችን? ቤተሰባችን ወይስ ስራችን? ሰብዓዊነት ወይስ ቁሳዊነት? ለምርጫ የምናቀርባቸው ነገሮች እራሱ የሞኝ ሰው ድርድር ነው። ♦️ተጨንቀን የምናጠራቅመው ገንዘብ፤ በጥላቻ የገነባነው ክብር፤ በደም ያገኘነው ስልጣን፤ በስርቆት ያካበትነው ሃብት፤ በውሸት የፈጠርነው ማንነት፤ ሁሉም ስንሞት አብረውን አይሄዱም። ያንን ማስተዋል እንዴት አቃተን? በቃ ሃቁ ይህ ነው፤ ምንም ነገር ከኛ ጋር ወደ መቃብር አብሮ አይወርድም። 💡ይህንን ሳስብ ግርምት ያዘኝ፤ እንዴት እናሳዝናለን ? ምን አልባት ስዎች ሲቀበሩ እጃቸውን ወደላይ አድርገው ቢሆን ኖሮ፤ በጥቂቱም ቢሆን ህይወታችንን እንዴት መኖር እንዳለብን ትምህርት ይሆነን ነበር። በህይውትህ የሚያስጨንቅህ ነገር ሲገጥምህ፤ እስከምን ድረስ እራስህን አሳልፈህ መስጠት እንዳለብህ ለማውቅ ሞክር፤ ምናልባት ከህይወትህ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ሊሆን ይችላልና። ✍ አቤል ብርሀኑ ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
53👍 33👎 2
5👍 2
💚ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። የደካማነት መገለጫ አይደለም ፣ ትህትና የትንሽነት ምልክት አይምሰልህ የዋህነት ደካማነት ሳይሆን የለስስት የመኖር ችሎታ ነው፣ ደግነት የመልካም ሰው የህይወት መምርያ ነው።፡፡ትህትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው፡፡ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ቀና የሚሉት ፍሬ የሌላቸው ናቸው፡፡ትህትና የልብ ነው፡፡ አየህ አንተ ባታስበውም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ ፣ ያንተ መኖር የሚያኖራቸው አያሌ ሰዎች አሉ ። ህይወትም ትርጉሟ የሚጨምረው ለሌሎች መኖር ስንጀምር ነው፣ ምንም የለኘም ምንም መስጠት አልችልም አትበል ያለህን ካሰብከው ብዙ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡ 💛"ሰው ሁሉ በልቡ ያለውን ይሰጣል።" በውስጥህ ያለውን ነው የምትሰጠውን ሁሌም ደግ ሁን።ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ። አንዳንዶች ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው ፤ አንዳንዶች ሰላምታህን ፤ አንዳንዶች ጊዜህን ፤ አንዳንዶች ሃሳብህን ፤ አንዳንዶች ድጋፍህን ፤ አንዳንዶች ጓደኝነትህን ሊሆን ይችላል ። ❤️ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን ፈገግታ እና ደስታችን እንኳን የምናውቀውን ሰው ቀረቶ የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ሃይል አላቸው። ሀብታም ሁን ወይም ደሀ ደግነትህን በዛ ሚዛን አትመዝነው! ዋናው የሚያስፈልግህ ሀብታም የሆነ  ልብ ብቻ ነው"!               ውብ አዳር ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
69👍 25
💡ስሙኒ ይቀራል 📍ከአንድ ሰው በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ ድንች የሚሸጥ ምሲኪን ሰው ነበረ። የቤቱ ባለቤት ሁሌም ወደ ውጪ ሲወጣ ይህንን ምስኪን ሰው ይመለከተው ነበረ። ቀኑን ሙሉ ብርድና ጸሀይ እየተፈራረቀበት ኑሮን ለማሸነፍ መድከሙ ስላሳዘነው በአቅሙ ሊረዳው ወሰነ። 💡ነጋዴው አንዷን ድንች በ50 ሳንቲም ነበር የሚቸረችረው። ታዲያ ይህ ሰው ምስኪኑን ነጋዴ ለመርዳት በማሰብ በየቀኑ የአንድ ድንች ዋጋ እየሰጠው ለመሄድ ወሰነ። በየቀኑ 50 ሳንቲሙን እየሰጠው በአንጻሩ ምንም ድንች ሳይቀበል ይሄዳል። ከብዙ ጊዜ በኋላ ይህ ሰው እንደለመደው 50 ሳንቲሙን አኑሮለት ጉዞውን ቀጠለ። ድንገት ከኋላው “ጌታዬ” የሚል ጥሪ ይሰማል። ዞር ብሎ ሲመለከት ምስኪኑ ነጋዴ ነበር በሩጫ የደረሰበትና የጠራው። ሰውየው በፈገግታ “ከስንት ጊዜ በኋላ ለምን በቀን በቀን 50 ሳንቲም በነጻ እየሰጠሁ እንደማልፍ ልጠይቀኝ ነው ያስቆምከኝ?” አለው ነጋዴው ግን እያለከለከ “አይደለም ኸረ” ሲል መለሰ። ይሄኔ ሰውየው ግራ ገብቶት “እና ለምን አስቆምከኝ?” ቢለው “የድንች ዋጋ 75 መግባቱን ልነግርዎት ነው፤ እናም ስሙኒ ይጎድላል” አለው አሉ። 💡ይህንን ታሪክ የሰማሁኝ ቀን በጣም አስቆኝ ነበር። መለስ ብዬ ሳስበው ግን ከቀልድነቱ በላይ የሰው ልጅን የአልጠግብ ባይነትና ያለማመስገንን ባህሪ የሚያንጸባርቅ መስሎ ታየኝ። ሰዎች አመስጋኝ ፍጡሮች ነን ብዬ አላምንም። ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነጻ በሚሰጠን ነገር ላይ እንኳን እንደራደራለን። የእኛ ባልሆነው ሀብት እንሟገታለን። በቸርነት በተሰጠን ነገር ሁሉ ይበልጥ እንጠይቃለን። ሃምሳ ሳንቲም ለምን በነጻ ተሰጠኝ ሳይሆን ለምን ስሙኒ ጎደለ የሚል አመለካከት ስላለን እኮ ነው አብዛኛዎቻችን ባለን ነገር መደሰት የሚያቅተን። 📍ብዙ ጊዜ ከፈጣሪ ጋርም ሆነ በየእለት ኑሮዋችን በነገሮች ላይ የምንደራደረው ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነው። በነጻ የሚሰጠንን 50 ሳንቲም ሳይሆን የኑሮዋችንን ዋጋ እራሳችን ተምነን ቀሪው ጎደለ ብለን እንሟገታለን። ስዎች የሚሰጡንን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት ዋጋ የማንሰጠው ቀሪውን ስሙኒ ስለምናስብ ነው።እኛ በባህሪያችን ነጻ የሆነን ነገር ዋጋ አንሰጠውም፣ የሚያስደንቀው ግን የሰው ልጅ በምንም ያህል ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው ሀብቶቹ በሙሉ በነጻ የሚያገኛቸው ናቸው። 💡በ50 ሳንቲሙ ያልተደሰተና ያላመሰገነ ሰው ስሙኒ ቢጨመርለት ምን ዋጋ አለው? በየቀኑ የሚቸረን 50 ሳንቲም ከበቂ በላይ ነው፤ አንዳንዴ ስሙኒው ይቀራል ብለን ሰጪውን ባናስቀይም መልካም ነበር፤ ነገር ግን ሰው ነን!!! ብዙ ጊዜ ደስታችንን የሚነጥቀን የ “ስሙኒ ይቀራል” አይነት አመለካከታችን ነው። የተሰጠንስ 50 ሳንቲም? የተሰጠን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት፤ ነጻ ጤንነት፤ ነጻ ተስፋ? ከምንም በላይ ነጻ ህይወትስ? ✍ሚስጥረ አደራው ውብ አሁን❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Mostrar todo...
77👍 41👎 2
📍ወዳጄ ሆይ ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። አንተም እንደዛፉ ስር ስደድ ጠንካራነት እውቀት አለው ፣ በጥበብ ይናገራል ፤ ተግባር አለው ። ጠንካራነት ስሜት ሳይሆን ተግባር ፣ ፉከራ ሳይሆን ድርጊት ነው ። ጠንካራነት ሞራልም ምግባርም ነው። 📍ወዳጄ ሆይ ፊት የልብ አደባባይነውና ሁሉን ቅሬታህን ፊትህ ላይ አታስነብብ፡፡ ጠላቶችህ ፊትህን እንጂ ልብህን እንዲያዩ አትፍቀድ፡፡ ለስድባቸው ስድብን አትመልስ ይህን ሰምቻችኀለሁ ማለት ነውና፡፡ ምንም ቢሆን አሁን የተሰማልን አትናገር፡፡ ከራስህ ጋር ሳትመክር ከሰው ጋር አትመካከር፡፡ ለአንድ ሀሳብ የሶስት ቀን እድሜ ስጠው፡፡ ባዕድ ባለበት ስለቤትህ አታውራ፡፡  ለግቢህ አጥር ፣ለቤትህ በር፣ለህይወትህ ሚስጥር ይኑርህ፡፡ የተሻልክ ሳይሆን የበለጥክ ሁን፡፡ 📍ወዳጄ ሆይ መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ። የሌላው የሆነችውን ሴት ላንተ አትመኝ ። ያንን ጥላ ስትመጣ አንተን ጥላህ መሄድ እንደምትችል እያስተማርሃት ነው ። አንቺም የሌላውን ባለትዳር አትመኚ ። 📍ወዳጄ ሆይ ብትታመም በአገርህ ትታመማለህ ። አገርህ የታመመች ከሆነች ግን ዓለም ዝግ ይሆንብሃል ። ተሰደህም ለመከበር አገር ያስፈልግሃል ። ከሰላም የበለጠ ሀብት ፣ ከማስተዋል የበለጠ ሥልጣኔ ፣ ከፍቅር የበለጠ ደስታ የለም ። ያለ ፈጣሪ እየተስፋፉ ያሉ ሰዎች እየጠበቡ ነው ። ልብስ ጸድቶ ልብ ከቆሸሸ የመንፈስ ነጻነት ገና አልመጣም ። የድሮ ሰው ልቡ ንጹሕ ፣ ልብሱ አዳፋ ነበር ። የዛሬ ልጅ ልብሱ ንጹሕ ፣ ልቡ ሸርታታ ነው 📍ወዳጄ ሆይ የሰብዊነት ሥራ ለሰው ሁሉ የሚደረግ የደግነት ስራ ነው፣ ደግ ለመሆን ጥግ አትያዝ ። ከሥርህ ያለው አንተ የማትችለውን የሚችልልህ ነውና አክብረው ። ቆጥረህ ከሰጠህ ስጦታህ ይረክሳል ። ደብቀህ ከሰጠህ ስጦታህ ሲወራ ይኖራል ። ከፍ ስትል ልታይ ካልክ ሁሉም ሰው ስትወድቅ ያይሃል ። በከፈትክለት መጠን ጠላት ይገባል ። ሰይጣን አስገድዶ ሳይሆን አዘናግቶ የሚገድል ጠላት ነው ። 💡እናም ወዳጄ የታወከ ሌሊት ሲገጥምህ በሰላም ስላደርክባቸው ሌሊቶች አለማመስገንህን አስብ ። ቀኑ መብትህ ሳይሆን ስጦታህ ነውና አመስግንበት ። እሰይ ነጋ ማለት ሲገባህ ደሞ ነጋ አትበል ።ሲያነጋልህ ላላስከፈለህ ጌታ የማለዳ ምስጋና ለማቅረብ አትዘግይ ። ወጥቶ የመግባት ዋጋው ትልቅ ነውና የምሽት ጸሎትህንም አታስታጉል ። እያጣጣርክ ስለ ጤና ከመጸለይ በጤናህ ፈጣሪህን አመስግን ። ውብ ጊዜ❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Mostrar todo...
71👍 27👎 1
👍 1 1
💡የተለያየ ድርሻ መያዛችን ሕይወትን የተሟላች ያደርጋታል፡፡ ሰዎች እንደ እኛ ካላሰቡ የተሳሳቱ ፣እንደ እኛ ካልተናገሩ ቋንቋ ያበላሹ ፣እንደ እኛ ካልኖሩ የሞቱ እንደ እኛ ካልሰሩ ሥራ የፈቱ አይደሉም ሌሎች አስፈላጊያችን የሚሆኑት እኛ የማንችለውን ሲያውቁና ሲያደርጉ ነው፡፡ 📍ሁሉም ሰው ዶክተር ቢሆን ያለገበሬ ምን ይመገባል?? ዶክተሩ በእውቀቱ ተመክቶ ገበሬውን አንተ አታስፈልገኘም ቢለው ይሞኛል፡፡ የላይኛው ከታችኛው የግድ የሚፈላለግ የተለያየ ተሰጦ ተቀብለናል፣ ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኘም ሊለውና ሕይወትን ብቻውን ሊመራ አይቻለውም፡፡ ትልቁ የኑሮ የኑሮ ሚስጢር " እኔ ለአንተ ፣ አንተ ለእኔ" የሚል ነው፡፡ 🔷የጥቁሮች መብት ታጋይ  የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡-  አላባማ እያለሁ ጫማዩን የሚጠርግልኘ አንዲት ሊስትሮ ነበር፡፡ይህን ሊስትሮ ስመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣ ነገር ቢኖር የቱንም ያህል ጫማዬን ብጠርገው እንደእርሱ አድርጌ ላሳምረው አለመቻሌ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ ልጅ በጫማ ማሳመር የዶክትሬት ዲግሪ አለው ብዬ ተቀበልኩ፡፡ ከኔም የተሻለ ስለሆነ አከበርኩት" ብሏል፡፡ 💡የትኛውም እውቀታችን አዋቂ የሚያሰኘን ላላወቁት በምናደርገው መንገድ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ እውቀት የአገልጋይነት እንጂ የጌትነት መንፈስ የለውምና፡፡ የእኛ እውቀት አስፈላጊ የሚሆነው የማያውቁ ስላሉ ነው፡፡ ሁሉም ቢያውቅ እውቀታቸው አለማወቅ ይሆናል ስለዚህ የማያውቁትን አክብረን ማገልገል ይኖርብናል፡፡ 🔷የትኛውም ሀብታችን ባለጠጋ የሚያሰኘን በችግር ለሚያቃስቱት ባፈሰስነው ልክ ነው፡፡ ራሱን የቻለ ባለጠጋ አይባልም፡፡ለሌሎች የተረፈ ግን ባለጠጋ ይባላል፡፡ስኬታችን የሚለካው ራሳችንን በረዳንበት መጠን ሳይሆን በሌሎች በተረፍንበት መጠን ነው፡፡ ♦️ዛሬ ኑሮአችንንና ሕይወታችንን እንዲገዛው የፈቀድንለት ነገር ቢኖር ንቀት ነው፣ ሌሎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን ፣ እኛ ግን ሌሎችን መናቅ እንሻለን፡፡ ሌሎችን መናቅ በአዋጅ የተፈቀደልን ሥልጣን ይመስለናል፡፡ ሌሎችን በንቀት ዝቅ ካላደረግን የተስተካከልናቸው አይመስለንም፡፡ 💡ስለዚህ የበላይነት ስሜታችን የበታችነት መንፈስ የወለደብን ነው፡፡ የምንኖረው ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ነውና ሌሎችን...ማክበር ደግሞም ፈጣሪ የምንሰጠውን አስታቅፎ ወደ ዓለም ልኮናልና አደራችንን ማድረስ ይገባናል፡፡ በቤታችን ፣ በሥራ ቦታችን ፣ በአገልግሎታችን እየሰራን ያለን እኛ ብቻ መስሎ ከተሰማን ሌሎች የሠሩት አይታየንም፡፡ ሌሎችን መውደድ ያቅተናል፡፡ ሥራችንም ከጥቅሙ ኩራቱ እየገነነ ይመጣል፡፡ በሌሎች ላይም እምነት እያጣንም የርክክብን ሥርዓት እናፈርሳለን፡፡ ራሳችን አልሚ ሌሎችን አጥፊ ሆነው እየታዩን ነቃፊ ብቻ እንሆናለን፡፡ 🔷የዓለማችን ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም ፣የሰላም መሰረት ግብረ ገብነት ወይም የሞራል ሕግ ነው፡፡ የሥነምግባር መሰረቱ ሃይማኖት ነውና ሃይማኖትን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ብዙ ባለ ራዕዯች ነን የሚሉ ሃይማኖትን በቀና መንፈስ አያዩትም፡፡ሃይማኖት ግን የልምድ ሳይሆን የተፈጥሮ መሻት ነው፡፡ መስራት ፣ መማር ፣ መልፋት ፣ መትጋት ብቻውን በቂ አይደለም ሃይማኖት ያስፈልጋል፡፡ ♦️ዓለም ድፍርስ ውሃ ነው፡፡ ስለዚህ ማንነትን አያሳይም፡፡ እንደውም እውነትን የሚሸፍን በመሆኑ ምንመ ያልበራለትን የብርሃናት አለቃ፣ ሰነፉን የትጉሃን አለቃ እያለ ያሞካሻል፡፡ ዓለሙ የሽንገላ የመዳለል አለም ነው፡፡ ሰዎች መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚጠሉት እውነት ስላልሆነ ሳይሆን ኃጢአጣቸውን ስለሚነግራቸው ነው፡፡ ዓለሙ የንግግር መክፈቻው "አንተ ለአንተ" ወይም "ሀይልህን አውጣ" የሚል ነው፡፡ ዛሬ የሰው ልጆች ሌላውን እንጂ ራሳቸውን ማየት አልቻሉም፡፡ 🔷የኛ ድርሻ ተራችንን ጠብቀን መቆም ፣ ቀጥሎ መመልከት ከዚያም መጠየቅ በመጨረሻም መጓዝ ነው፡፡ ካልቆምን መመልከት ፣ ካልተመለከትን ማስተዋል ፣ ካላስተዋልን መጠየቅ ፣ ካልጠየቅንም መጓዝ አንችልም፡፡ መቆም ለቀጣዩ ጊዜ ያዘጋጃል ፣ ለቀጣዩ ጉዞም ኃይል ይሰጣል ፡፡ ♦️በክፉ ጎዳና የሚጓዝ መቆም ያስፈልገዋል ፡፡ የመጣበትንና የሚሔድበትን የሚያየው በመቆም ብቻ ነው፡፡ በመቆም በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ራስን መገምገም ፣ ከዚያም መመልከት ቀጥሎም መጠየቅ በመጨረሻም ዕረፍት ወዳለበት ደሴት መጓዝ፡፡              ውብ ቅዳሜ❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Mostrar todo...
37👍 25👎 2
9👍 1
✨የዛሬ ደስታህ የዛሬ ነው። የነገ ደስታህ የነገ ነው። ፈጣሪ አንተን የሚያስደስትህ ነገር ሊሰጥህ ምንም እጥረት የለበትም። አንተ ብቻ በሆነውም ባለህም በሚሆነውም በሁሉም ተደሰት። ውስጥህ የሚያሳምምህን ሳይሆን የሚያስደስትህን እይ። ውስጥህ የሚያሳዝንህን ሳይሆን የሚያዝናናህን እይ። ውስጤ ያለችውን ትንሽዬ ደስታ አስተውዬ ባየሁ ጊዜ ግን የፈጣሪን መልካምነትና ቸርነት አያለሁ። የፈጣሪን ደግነትና ቅንነት አስተውላለው። ከምንም በላይ የፈጣሪን ፍቅር አያለሁ። በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ከስምንት ቢሊዮን የዓለም ሰው ሁሉ እኔንም አለመርሳቱ ይደንቀኛል። ውስጤ በፈጣሪ የተቀመጠችውም ትንሽዬ የደስታ ቅባትም በአካሌ ውስጥ ካሉትና በላዬ ላይ ከተፈጠሩት አሉታዊ ነገሮች ሁሉ ትልቃለች። 💡ውስጤ ያለችው ሚጢጢዬ የደስታ ፍንጣቂ ካጋጠሙኝ የሂወት መሰናክሎች ሁሉ ትገዝፍብኛለች። ያኔ ላለመሳቅ ምክንያት አጣለሁ። ከውስጤ የተፈጠረው ደስታ በፊቴ ላይ ይደገማል። መጀመሪያ ውስጤ ይስቃል በመቀጠል ጥርሴ። ከዛ ደሞ የኔ ደስታ ከኔ አልፎ በዙሪያዬ ያሉት ላይ ይጋባና እነሱም ይስቃሉ። የእውነት ፈጣሪ እንዴት ድንቅ ነው። በሱ ላይ እምነታችንን በጣልን ጊዜ ልባችንን በደስታ ፊታችንን በፈገግታ ይሞላዋል! በእውነት የፈጣሪን ጥበበኝነት መመስከር ከፈለጋችሁ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ውስጠ ውስጣችሁን ተመልከቱ። ያኔ የምታገኙት የደስታ ጨረር ከከበቧችሁ ችግሮች ሁሉ ይበልጡባችኋል። ያኔ ከልባችሁ ትስቃላችሁ። 📍የበለጠ የፈጣሪን የእውቀት ጥግ ደሞ የምታዩት በምንምና በየትኛውም ጊዜ ለእያንዳንዳችን እደግመዋለሁ ለእያንዳንዳችን የሚሆን ደስታ ሰቶናል! እሱ ጋ ስስት የለም። እሱ ጋ ማዳላት የለም። የተወሰኑትን አስደስቶ የተወሰኑትን የሚያስከፋ ሚዛናዊ ያልሆነ አምላክ አይደለም። ውስጣችንን በደንብ ማየት ስንጀምር በገንዘብ ልንገዛው የማንችለውን ደስታ እናገኛለን። ይህም ደስታ ሳቅን ይፈጥርልናል። ጥርሳችንም ከልብ በመነጨ ደስታ ፈገግ ይላል። 💡ዛሬ ይህንን በውስጣችን ያለውን ደስታ የምናይበትና ፊታችንን በሳቅ የምንሞላበት ቀን ነው። አስተውለን ወደ ውስጥ እንይና ውስጣችን ያለውን ደስታ በፊታችን ላይ እንዲንጸባረቅ እንፍቀድለት!ውስጣችንን ስናይና ፈጣሪ ውስጣችን ያስቀመጠውን ድንቅ ስጦታ ስናስተውል ፤ያኔ አለመሳቅ ይከብደናል። አለመደሰት ታሪክ ይሆናል። ከፈገግታችሁ ጀርባ ያሉትን ብዙ ችግሮች መከራዎችና ማጣቶችን ሳይሆን ትንሿን ጥሩ ተአምር እዩ፤ያኔ ትንሿ ብዙ ትሆናለች። ከውስጥ የተጫረችው ሚጢጢዬም የደስታ ፍንጣቂ ከናንተ አልፋ ለዓለም ሁሉ የምትበቃ ትሆናለች። 🔑 ከውስጥህ ያለው ብዙ ነው። ከውስጥሽ ያለው ድንቅ ነው። ፈጣሪንም ለሰጣችሁ ሁሉ አመስግኑ! እውነቴን ነው ውስጠ ውስጣችሁ ያለውን ስታስተውሉ (ማየት ብቻ አይደለም ማየት ወስጥ ማስተዋል ካልተጨመረበት ትርጉም የለውም) ያኔ ባላችሁ ሁሉ ትገረማላችሁ። ✍ብሩክ የሺጥላ ውብ አሁን❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Mostrar todo...
57👍 19
Inicia sesión y accede a información detallada

Te revelaremos estos tesoros después de la autorización. ¡Prometemos que será rápido!