cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

Join @Rovibook 😎 <|> /\ 👢👢 መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው!! ለማንኛውም ማስታወቂያ ነክ ጉዳዮች @RASNAMRUD ያናግሩን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
29 500
Suscriptores
-924 horas
-677 días
-28730 días
Archivo de publicaciones
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሪፖርተር፡- የሠራሀቸውን ሙዚቃዎች በሙሉ በአንድ መጠቅለል ባይቻልም፣ በተደጋጋሚ ከምታነሳቸው ጽንሰ ሐሳቦች መካከል ሰው መሆንን፣ ፍቅርና ጥላቻን፣ አገርንና መንፈሳዊነትን እንዴት ትገልጻቸዋለህ? #ኤልያስ፡- "ሰዎች ስለሆንን አንዳንዴ መሳሳታችን አይቀርም የሚለውን አላምንበትም፡፡ #ለኔ_ሰው_መሆን_ጥሩ_መሆን_ብቻ_ነው፡፡ ሰውነት ለኔ ለመስተካከል፣ እግዚአብሔርን ለመፍራት መሄድ ነው፡፡ መሳሳት አይቀርም በሚል ምክንያት ካልተሳሳትክ አትማርም የሚል ነገር በፍፁም የለኝም፡፡ ፍቅር ብዙ ዓይነት ነው፡፡ #መጥፎ_ነገርን_መውደድ_ፍቅር_ስለሆነ_ብቻ_ጤነኛ_አይደለም፡፡ ሰው መውደድ ያለበትን መምረጥ አለበት፡፡ የራሱን ልብ ብቻ እያዳመጠ መሄድ የለበትም፡፡ ከሱ በላይ አስተማሪ #የእግዚአብሔር #ቃል አለለት፡፡ ልቡን ብቻ ወይም ልቡ የማይታመን ሰውን እያዳመጠ ከሄደ እርስ በርስ መጨራረስ ነው፡፡ #ጥላቻ ደግሞ #ጥሩም ነገር አለው፡፡ ለምሳሌ #መጥፎ_ነገርን_መጥላት፡፡ አገር ለኔ #ኢትዮጵያዊ #ሰው ነው፡፡ ቁሳቁስ ያልፋል፡፡ #አገር_ማለት_ከሌላው_ለራስ_ወገን_ማዳላት_አይደለም፡፡ በመሬት የተነጠፈ ነገር አገር ነው ብዬ አላስብም፡፡ #በእግዚአብሔር_ቃልም_ሰው_ይበልጣል፡፡ መንፈሳዊነት የግድ ስለሆነ ሰው መንፈሳዊ ላይሆን አይችልም፡፡ የጥሩ ወይም የመጥፎ መንፈሳዊነት አለ፡፡ መንፈሳዊነት እግዚአብሔርን መፍራት ከሆነ ጥሩ ነው፡፡" ከሪፖርተር ጋር ያደረገው ቆይታ የዛሬ አራት አመት ህዳር 2009 ቀንጭቤ ያቀረብኩት፡፡ ንግግሩ ሰምተህ ከዛ በፊትም ሆነ በኀላ የሰራቸውን ስራ ስትመለከት ምን ያህል ንግግሩን ህይወቱን በስራዎቹ እንደሚገልጥ ታይበታለህ፡፡ ኤላ አንተ ታላቅ ነህ ሁሌም በልባችን ትኖራለህ 😍😔😢😢😢😍😍😊🙏 ሙዚቃን እንድናውቅ ያደረከን አንተ ትለያለህ፡፡ 😢😭😢ፈጣሪ🤦‍♂🙇🤦‍♂🙇 ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን @jahABP ነኘ😊🙏 የኤላን ራዕይ ለማሳካት አውታርን አፕሊኬሽንን በመጠቀም የኤላ ስራዎችን እንዲሁም የተለያዩ የሀገራችን ድምፃውያንን ዘፈኖች እንድትሰሙት እንድታዳምጡ አደራ እላለሁ፡፡ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN "እግዚአብሔር በፍቅር ኃይሉ ሰዎችን ወደ ራሱ ይስባል፡፡ ሰዎች ግን ፍቅሩን ካልተጠለሉ የቁጣው እሳት ይበላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ማዳንመ መግደልም ይችላል፡፡ የሚጠቀመው ግኅ የማዳን ሀይሉን ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ግን በእንቢተኘነታቸው ሲፀኑ እግብዚአብሔር ይቀጣል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ብቻ እንዲሆንላቸው የሚመኙ ሰዎችን "ይቀጣል" ሲባሉ አይመስላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ግን ፍቅር ነው ፣ ፈራጅም ነው፡፡ ፍቅሩና ፍርዱ አይነጣጠሉም፡፡ ምክንያቱም የፍቅሩም የፍርዱም መሰረቱ እውነት ነውና፡፡ እውነት ደግሞ እራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ባሕሪዩን ስለማይክድ አፍቃሪ ነው፡፡ ፈራጅም ነው፡፡ ፍቅር አካል ነሥታ በመንገድ ብናገኛት ብቻዋን አናገኛትም፡፡ በቀኘና ቀግራ የከበቧት ሁለት ወዳጆች አሏት፡፡ እነርሱም:- #እውነት እና #ፍትህ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ይቆጣል ስንል ትግስት ያጣል ማለታችን አይደለም፡፡ እርሱ ፃድቅ በመሆኑ ኃጢያትን ይቀጣል፡፡ እግዚአብሔር ኃጢያትን ባይቀጣ ኖሮ ጻድቅነቱ ባልታወቀ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሚቀጣው #ኃጢያትን ነው፡፡ #ኃጢያትን_ሲቀጣም_ከኃጢያት_ጋር_የሚያገኘውንም አብሮ ይቀጣል፡፡ 😊 መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ 🙏 @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ ከቅጣቱ ይጠብቀን
Mostrar todo...
🌼2013🌼 🌼እንኳን ለ አዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 2013 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻🌻 አዲሱ አመት የሰላም🌻 የፍቅር 🌻የደስታ🌻የመከባበር🌻የአንድነት🌻የመረዳዳት🌻የመደማመጥ🌻የመቻቻል🌻ተማሪው በትምህርቱ🌻ሰራተኛው በስራው🌻ውጤታማ የሚሆንበት🌻እንዲሆን እመኛለው!!! 🌼ጥላቻን በ - 🌼ያለንን በ ÷ 🌼ይቅርታን × 🌼ፍቅርን + 🌻ቀንን በ ቀናት 🌻ሳምንትን በ ሳምንታት 🌻 ወርን በ ወራት 🌻ዘመንን በዘመናት 🌻የሚለውጥ እርሱ ግን የማይለወጥ ፈጣሪ መልካም ዘመንን ይጨምርልን🌻🌻 🌻በአዲሱ አመት ሀገራችን🌻 ኢትዮጵያ ሰላም የበዛላት ሆና🌻አድጋ 🌻ለምልማ ትበልፅግልን! 🌻ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር❤️🌻
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ለውጡ የአመት ብቻ እንዳይሆን እንጠንቀቅ!! ከሌለን ያለን ይበልጣል ይህን ስል ሁላችንም ጋር ከሌሎች የተሻለ ነገር አለን እያልኩህ ነው በነገሮች ልክ አትለካው አብሶ በጣኸው ነገር ብቻ አትለካው፡፡ እውቀትም ቢሆን አንፃራዊ ነው፡፡ ሁሉም ሰው አንድ ነገር ከኛ በተሻለ ያውቃል ስለዚህ እኛም ከሰዎች በሆነ ነገር የተሻልንን ነን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት እኛ ጋር ሰዎች ሚፈልጉት ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ያ ነገር ደግም ለጥሩ ነገር ስንጠቀምበት ውጤቱ አመርቂ ነው፡፡ ፈገግ በል አንተን ማንም ሊሆኖን አይችልም አንተ የፈጣሪ ስራ ነህ አስበኸዋል አንተን ሰው የሰራህ ቢሆን ያንተ ፊት ስንቴ ሊደገም እንደሚችል😜👊 ስለዚህ በሁሉም ነገር አንተን ሊመስል ሚችል የለምና ቀና ብለህ የላይኛውን አመስግነው፡፡ ያለፈውን ጊዜ ቆም ብለህ አስበው እስኪ በመጀመሪያ ስለራስህ አስብ አንተነትህ ማለቴ ፀባይህ.........እያንዳንዱ የምታደርጋቸው ድርጊቶች ምን ጠቀመህ ምንስ ጎዳህ ቀጥል አብረውህ ያሉትንስ ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ.... ጠቀመ ጎዳ?🤔 ለዚህ መልስ መልሰህ ከዛ ቆም ብለህ እራስህን እየው ምክንያቱም ይህን የሚጎዱህን ፀባዮችህን ካልተውክ የተቀየረው አመተ ምህረቱ እንጂ አንተ አይደለህም ዛሬ 23 ዓመትህ ነበር ቀጣይ ደሞ 24.....ዕድሜ ብቻ ጨመርክ አንተ ግን ያው ነክ እኔ ግን ያው ነኘ አንቺ ግን ያው ነሽ እኛ ግን ያው ነን ይሔ ያናዳል🤦‍♂🤦‍♂ በአዲስ አመት አዲስ ነገርን ፍለጋ ከመጥፎ ፀባያችን ቢያንስ በግማሽ መቀነስ አለብን.....ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለኛ ብለው ለሚጨነቁ ስንል፡፡ የኛን መለወጥ ለሚናፍቁ ስንል ለውጥን ለምን አንሻው ለምን አንይዘውም ለምንያን ያክል እራስ ወዳደድ እንሆናለን?...... ስለመልካምነታችን ምን መባል አያስፈልገውም ይበል ይጠንክር ይበርታ እንጂ፡፡ አዲስን አዲስ ለማድረግ እንትጋ እንጠንክር እንበርታ ሁሌም ይህን እናስብ ከዛሬ ነገ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ እናድርግ የኛ ህይወት በሰው አልተጀመረምና በሰዎች ወሬና ነቀፋ የሚደናቀፍ እና የሚወድቅ አይደለምና፡፡ ያንተ የህይወት ዘዋሪው #ታላቁ_የድንግል_ልጅ ነው እንጂ፡፡ ሰዎች ስላሉህ አይደለም እንዲህ ሆነ ማለት የሰዎች ልማዳቸው ነው፡፡ ያንተ ህይወትህ መሪው አንድ #አላህ ነው፡፡ አንተን ሊጥሉህ ሁሌም ጉድጓድ ይቆፍራሉ ግን በቆፈሩት ጉድጓድ መውደቃቸው አይቀርም ምክንያቱም የአንተ ህይወት መንገድ ጠራጊው #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው፡፡ ተስፋ አለን እንደርሳለን ተስፋ አለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡ እንበርታ እንጠንክር እኛ ለሀገራችን እናስፈልጋለን በኡነት እኛ ለኢትዮጵያ እናስፈልጋታለን ለዚህ ኮትኩቶ ያሳደገን ሚስኪን ህዝብ ከኛ ሚጠብቀው ነገር አለ እና እንበርታ፡፡ NOT I LOVE YOU #አፈቅርኃለሁ NOT SORRY #ይቅርታ NO THANK YOU ፅድት ያለው አማርኛ አቻ ትርጉሙን #አመሰግናለሁን..........#እንልመድ...........................#መረዳዳት......#መተሳሰብ.....እንጠቀምባቸው የህይወት መሪያችን እናድርጋቸው ገነትን ማየት ያለብን ሞተን ሳይሆን ገነትን ምድር ላይ እንስራ፡፡ ከመጥፎ እንሽሽ! መጥፎውን! አንናገር! ግን "የመጥላት #ጥሩ ነገር አለው ለምሳሌ #መጥፎን ነገር መጥላት" ብሎ የለ ታላቁ😍👏 #ኤልያስ_መልካ የተቸገሩትን ረድተን ያስቀየምነውን ይቅር ብለን የተጣላን ታርቀን ቂምን ተንኮልን ጥለን ለተደረገልን ብቻ ሳይይሆን ላልተደረገልንም አመስግነን(ምክንያቱም ሚጠቅመን ቢሆን ለኛ እሱ የላይኛው ያሳካልን ነበርና)....ለሁላችንም መልካም በዓል መልካም አዲስ አመት እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ፡፡ አብይ አንዱአለም(የማርያም ልጅ ነኘ) @jahABP 😊🙏😍 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN አይ ከንቱነት! አይ የህይወትን ትርጉም አለማወቅ ! አይ የመዝናናትን ትርጉም አለማወቅ! ለአብዛኛው ለዘመኑ ወጣት መዝናናት ማለት ዝሙት መፈፀም ፣ ጫት መቃም ፣ መጠጥ መጋት ፣ በስካር መናወዝ ፣ እስከምሽቱ ስድስት ሰዓት መጨፈር ፣ ራስን መርሳት ነው ብለው አብዛኞቹ አምነዋል፡፡ አይ ከንቱነት! ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት እራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ እራስን እና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማነው? መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! በወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኘነት ተሞልቶ በመታወር ፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውንተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሀይል በማይረባ ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ጊዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት ፣ በአሉባልታ ፣ በወሬ ሱስ ፣ በአቃቂር ፣ በተንኳሻነት ፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም! ወጣትነት ይሔንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ አልያም ምርጥ የፀጉር ቁርጥ ተቆርጦ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትም ለመርገጥ እየተፀየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት በተስፋ መቁረጥ! ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድ መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባ በቀበሌኛ አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል ዕውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመፃደቅ ማለት አይደለም....... ወጣትነት ባህር ነው፡፡ ወጣትነት ዕውቂያኖስ ነው፡፡ ወጣትነት ከአድማስ ሰፊነት ነው፡፡ ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰዓት ነው፡፡ ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው፡፡ ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው፡፡ ወጣትነት በዘረኘነት ተሞልቶ አማራ ፣ ትግሬ ፣ ኦሮሞ ፣ ወላይታ....ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም ስለአቀፋዊነት እይታን ማስፋት ነው፡፡ ወጣትነት #ፍቅርና #አንድነት መስበክ ነው፡፡ ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር ነው፡፡ ወጣትነት አንድን ነገር በአንድ ዓይን ሳይሆን በሶስት ዓይን መመልከት ጥበብን ማዳበር መቻል ነው፡፡ ወጣትነት ብርሃን ነው፡፡ ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው፡፡ ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከ መጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው፡፡ ወጣትነት ማንበብ ነው፡፡ ወጣትነት መጠየቅ ነው፡፡ ወጣትነት ስለዓለም ፣ ስለ ህይወት ፣ ስለ ጥበብ ፣ ስለ ዕውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው፡፡ ወጣትነት ለሌሎች ለሌሎች መኖር ነው፡፡ወጣትነት ለዚች ምስኪን ኢትዮጵያ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው፡፡ ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና ዕቅድ መሰነቅ ነው፡፡ ወጣትነት እሳት ነው፡፡ ወጣትነት ቤንዚል ነው፡፡ ወጣትነት ቅጠል ነው፡፡ ወጣትነት ጤዛ ነው፡፡ ወጣትነት ታክሲ ነው፡፡ ወጣትነት ምርጫ ነው፡፡ ወጣትነት ባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው፡፡ ወጣትነት ከፍርሃት ፣ አልችልም እና አይሳካልኘም የሚለው እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው፡፡ ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው.....፡፡ ኤጭ...........! ከሚለው የአዘርግ መፅሐፍ የተቀነጨበ፡፡ ኤጭ.....! (በኢትዮጵያ ምድር የተከናወኑ ዘግናኘ ታሪክ) አዘርግ....2010 ዓ.ም አዲስ አበባ ጃ!.....ይህን መፅሐፍ እንዳነበው ስለጋበዝከኘ አመሰግናለሁ፡፡😍🙏😊 ወጣትነትን በሚገባ ገልፆታል ብዬ አስባለሁ ሁላችንም እራሳችንን እናይበታለን ብዬ አስባለሁ፡፡ #መልካም #በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ እራሳችንን እየጠበቅ በዓሉን ስናከብር በጥንቃቄ ይሁን #መልካም_አዲስ_አመት ወጣትነታችንን ለመልካም ነገሮች እንጠቀምበት ሆነን መታየት ያለብንን ቦታ እስክንደርስ እሩጫችንን ማቆም የለብንም ሩጫችን ከትላንት ማንነታችን የተሻለመሆን አለበት የተሻለ ብቻ ሳይሆን የበለጠን😍🙏😊፡፡ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
#ወጣትነት .............ምንድነው?? ሁላችሁም ይሔን ፅሁፍ እንድታነቡት እፈልጋለሁ ጠብቁኘ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ይድረስ ላልተፀነስከው ልጄ (በ2 pac "letter to my un bornchild ሙዚቃ የነቃ ፅሁፍ) በእናትህ ማህጸን ውውጥ ካለ እንቁላል ፣ ከእኔ አብራክ ውስጥ ካለ ዘረምል ወጥተህ ፅንስ ያልሆንከው ልጄ እንደምን አለህልኘ፡፡ እኔ ካንተ ናፍቆት በስተቀር ደህና ነኘ ያገሬ ሰው ሞኘ ነው "የማያቁት ሀገር አይናፍቅም" የሚል፡ተረት ያምናል፡፡ ይኸው እኔ በማላውቅህ ልጄ ባንተ ናፍቆት እየተብሰለሰልኩ አይደል፡፡ ለነገሩ የማያቁት ሀገር ላዬናፍቅ ይችላል የማያቁት ልጅ ያላፀነሱት ልጅ እንደሚናፍቅ ግን እኔ በአስሩም ጣቴ ፈርሜ እናገራለሁ፡፡ ካስፈለገም ማህተቤን ጨብጬ እምላለሁ፡፡ ማረርያምን፡፡ እናልህ ልጄ እጅጉን ናፍቀኸኛል፡፡ ምን አይነት ሰው ይሆን? ፀባዩ? ባህሪው? መልኩ?? ቁመናው?? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ ግን መልስ የለም፡፡ ደግሞ እንደምታውቀኘ ችኩል ነኘ፡፡ ለነገሩ የትብለህ ታውቀኛለህ፡፡አንተ ገና አልተፈጠርክም! ኧረ መች ተፀነስክና! ብቻ ግን ብታውቀውም አይከፋምና እወቀው እኔ የወደፊት አባትህእጅጉነለ ችኩል ነኘ፡፡ እና ይህ ችኩህነቴ እየገፋፋኘ ቶሎ ላፀንስህና ተወልደህ ላይህ እጓጓለሁ፡፡ ግን ደግሞ ከቀልቤ ሆኜ ሳስበውም #አይሆንም፡፡ ምንም ሳይዘጋጁ ልጅ መውለድ ሃጢያት ነዋ! ይህንን ደሞ ያስተማረኘ አለምን በቃሉ ያፀና ፣ ሰማይን ያለምሶሶ ፣ ምድርን ያለመሰረት ያፀናው ክርስቶስ ነው፡፡ እሱ አዳምን የፈጠረው የሚያስፈልገው ሁሉ ከፈጠረበኀላ አይደል? ሌሎቹ አፈጣጠሮቹንም ተመልከት ሁሉንም የፈጠራቸው መጀመሪያ የሚያስፈልጋቸውን ከፈጠረ በኀላ ነው፡፡ ሰማይን ፈጥሮ ፀሀይን ፣ ፀሀይን ፈጥሮ እፅዋትን ከዛ እንስሳትን ምናምን እያደረገ፡፡ ከፈለክ ጠይቀው ከኔ ይልቅ ላንተ ይቀርብ የለ፡፡ "እኔ የክርስቶስ ተከታይ ነኘ" የሚለው የሀገሬ ህዝብ ግን ምንም ሳይኖረው አንዳች ሳያዘጋጅ ልጅ ያምረዋል፡፡ ልጅ እንዴት ያድጋል? ምን ይበላል? ምን ይጠጣል? ምን ይለብሳል? የት ያድራል?የት ይማራል?የሚሉትን ጥያቄዎች ሳይመልስ ይወልዳል ያስወልዳል፡፡ እሱ ምንጨነቀው "ልጅ በድሉ ያድጋል" የሚል ሰንካላ ተረት አለለት በኩ ይፅናናል፡፡ አን ስንቱ መሰለህቀየመንገዱ ተርቦ ፣ተጠምቶ ፣ ታርዞ...የወደቀው፡፡ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ያልተፀነስከው ልጄ ስንቱን መሰለህ "በክርስቶስ ክርስቲያን የሆናችሁ" ሲባል አቤት እያለ ከዲያቢሎስ የባሰው፡፡ ያልተፀነስከው ልጄ የወደፊት አባትህ መልስ ከሌለው ጥያቄ ከምብሰለሰል ለምን አትነግረኘም ምኅ አይነት ሰው ነህ ልጄ? አባትህ ቀጭንቀት ከምሞት እስኪ ንገረኘ፡፡ ለነገሩ እንኳን ገና ያልተፀነሳችሁት ይቅርና በቅርቡ የሚወለዱትስ መች ላባት ቁብ አላቸው፡፡ እኛስ ቀደም ብለን የተወለድነው #ስላባቶቻችን #አባቶቻችን #ላባቶቻቸው #የሚጨነቁትን ያህል መች ጨንቆን? ልጄ ሁሉንም እንተወው እና አንድ ነገር ልንገርህ፡፡ ስማኘ ተወልደህ ለዚች ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ #ትርፍ ሰው እንዳትሆን፡፡የተሰራ ለመድገም የሚጥር አዲስ ሀሳብ የሚጠላ አልቸገራትም፡፡ ልምራሽ ብሎ ወደ ኀላ የሚወስዳት ፣ አውቅልሽ ብሎ ገደል የሚከታት ተቀያሪ ሳይቀር አላት፡፡ ላልማሽ ብሎ የሚያወድማት ፣ ልሳምሽ ብሎ የሚነክሳት ትርፍ አላት፡፡ ሀገርህ ፣ ሀገሬ ኢትዮጵያ፡፡ የማያውቅ አዋቂ ነኘ ባይ ሞልቷታል፡፡ የማያድን አዳኘነኘ ባይ ተሮፉታል ኧረ ስንቱ .....ኧረ ስንቱ ልጄ....በልቶ ስላደረ ሁቹም የጠገቀ የሚመስለው ገንዘብ በደረቱን አስነፍቶት ሁሉን የሚያውቅ የሚመስለው ስንት አለ መሰለህ እሷም ደግሞ አታውቅበትም፡፡ ለማጀቷ በር አላበጀችም፡፡ ማጀቷን ለሁሉ ከፍታለች፡ የደረሰ ይገባል፡፡ የገባው ግን ደግ አይሰራም፡፡ እሱ ቢወጣም ደግ የሚሰራ አይገባም፡፡ የለማ! ሀገርህ እነዲያ አይነት ሰው አላፈራችም! ሀገሬ በጎ ሰው ጨርሳለች! ኢትዮጵያ....ቢኖሯት እንኳን ጥቂት አረሞች ውጠዋቸዋላ! ተወኘ ባክህ ልጄ ሆድ አታስብሰኘ፡፡ይልቅ ከጭንቄ ገላግለኘ፡፡ አንተ ምን አይነት ሰው ትሆን? ትርፍ? ሃገሬ ያልቸገራትን ሀገርህ የሞላትን? አደራ እንዲህ ከሆንክ አንተን ወደዚህ የማምጣት ጉጉቴ ሁቹ በልቤ ውስጥ ይመክናል፡፡ አንተ ወደምድር እንድትመጣ በማደርገው ጥረት ኮንዶምና መሰሎች እንኳን አያስተማምኑኘም፡፡ ብልቴን ቆርጬእጥለዋለሁ እንጂ፡፡ ስላሴን፡፡ እኔ ለሀገሬ ምንም አልሰራሁላት፡፡ ትርፍ ሰው ሆኜባታለሁ ትርፍ ሰው ግን ልጨምርባት አልፈልግም፡፡ እናም አደርገዋለሁ፡፡ ልጄ ሙት አደርገዋለሁ፡፡ ልጄ ሙት እቆርጠዋለው፡፡ ልጄ እባክህ ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ንገረኘ አልጨነቅ? ሀገሬ የቸገራት ፣ ሀገርህ ያጣችው ኢትዮጵያ የሌላት አይነት ሰው ከሆንክ ዛሬውኑ ልሰናዳ ወደምድር የመምጫ ትኬት ልቁረጥልህ በእናትህ ማህፀን ላሳፍርህ የሚያስፈልግህን ላሟላል ወደምድር ላምጣህ፡፡ ኢትዮጵያን ታደጋት፡፡ ልጄ ባዛኘቱ አታስጨንቁኘ ንገረኘ ምን አይነት ሰው ነህ???????????መልስህን እጠብቃለሁ፡፡ ቻው፡፡ ምናልባት የወደፊት አባትህ እኔ😔😔🤦‍♂🤦‍♂ አዲስ አይን መፅሔት ግንጣይ ገፅ በደቀ ከፈለኘ ወየሻረግ ፀሀፊው ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ሳላደንቅ አላልፍም እቆርጠዋለሁ አለ እኮ😜😜😜😳😳👏👏👏 ታዲያ እኔ አንቺ አንተ እኛ ሁላችንም ለዚች ምስኪን ሀገር ምን አይነት ልጅ ነው ልናወርሳት ያሰብነው 🤔🤔🤔 ቆዩልኘ🙏😊🙏 @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
" ፍቅር የሚገኘው በፍቅር ነው ሰዎች ስንወዳቸው ይወዱናል፡፡ እንዲወዱን ከፈለግን ግን መቼም አይወዱንም፡፡ ፍቅር ሳያዳምጡ መውደድ መቻል ነው፡፡ ፍቅር ዕቁብ ሳይሆን ፍቅር ስጦታ ነው፡፡ ካፈቀርን...... መጠላትንም ለመቀበል መዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡ ለመረገምም ለመነቀፍም ዝግጁ መሆን ያስፈልገናል፡፡ ግን አስታውሱ..... የምንኖረው እግዚአብሔር ስለወደደን እንጂ ሰዎች ስለወደዱን አይደለም፡፡ የህዝብ ፍቅር ሲናፍቀን የአንድ ሰው ፍቅር ሳናገኘ እንቀራለን፡፡ ራሱን መውደድ ካቃተው ሰው እኛን እንዲወደን መፈለግ ተገቢ አይደለም፡፡ የፍቅር ደስታው #ሲሰጡት እንጂ #ሲቀበሉት አይደለም፡፡ ያማለት ሲያፈቅሩት እንጂ ሲፈቀሩ አይደለም፡፡ ልወደድ የሚል ስሜት ያደረባቸው ከንቱ አስተሳሰብ ያደረባቸውና የአእምሮ ድህነት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች ፍቅር ብቻ አይደለም ያላቸው፡፡ ጥላቻም የእነርሱ ናት፡፡ ስለዚህ ደስ ሲላቸው ይወዱናል ደስ ሲላቸው ይጠሉናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ታምኖ የማይከዳ ፣ ወዶ የማይጠላ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ አለሙ ፍቅር አልባ አስፈሪ ሆኗል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅርን ብቻ ስናስብ ያልተሰበረ መንፈስ እናተርፋለን" አፍቃሪ ልብ❤️ ይስጠን 😍🙏🙏 መልካም ጊዜ @jahABP 😊🙏 ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ፡፡ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY የአመቱ የመጨረሻ ቅዳሜ.....በፈገግታ ወዳጄ አንድ ነገር ልምከርህ ልምከርሽ ሁሉም ሚሆነው አንተ ስትኖር ነው አንቺ ስትኖሪ ነው፡፡ ኑርልን😃 ኑሪልን😃 ብዙ ነገር ለዚች አለም ማበርከት ትችላለህና ባንተ የተነሳ ቡዙሀኑ ይደሰታሉ ነገ በቅንነት በታማኘነት ይቺን ሀገር ይጠቅማሉ ከሚባሉት ነህና/ነሽና እባክሽ ጠንክሪልን እባክህ ጠንክርልን፡፡ አንተን ካጣ አንቺን ካጣ ሁሉም ቢያለቅስ ቢያዝን ለጊዜው ነው፡፡ ምክንያቱም መርሳት የሰው የተፈጥሮ ባህሪው ነውና፡፡ ከሔደ ለማይመለሰው ውድ ለሆነው ህይወትሽ ስትይ ስትል ማስክሽን አድርጊ ሳኒታይዘርህን ተጠቀም ከሰዎች ጋር ያለህን ንኪኪህን ቀንስ፡፡ አስገዳጅ ነገር ካልሆነ አቤት አትውጪ፡፡ ነገ አንተን ማየት ያንተን ደስታ ሚፈልጉ ሰዎች በዙሪያህ አሉና ተጠንቀቅ ለሌላው መጎዳት ምክንያት ላለመሆን ጣሪ፡፡ ታስፈልገናለህና ታስፈልጊናለሽና እባክህህ/ሽ እራሳችንን እንጠብቅ፡፡😷😷🤲 @jahABP ነኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ማን ነው ተያቂው? ህይወት? ሰይጣን? አጋጣሚ? ዕጣፋንታ ወይስ ታላቁ ፈጣሪ? ወይስ ሁሉም ተጠያቂዎች አይደሉም? ወይስ ተጠያቂ የሚባል ነገር የለም? ኤልያስ ከፀሀይ በታች ያለው ሁሉ ከንቱ ንፋስን እንደመከተል ነው የተባለው እውነት ይሆን? እውን ከፀሀይ በታች ያለው ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው? የከንቱ ከንቱ ለሆነስ ነገር መጨነቅ አስፈላጊ ነው? የከንቱ ከንቱ ከሆነስ ለምን ከፀሀይ በታች ያለው ሁሉ ተፈጠረ? ለምን የምድር ነዋሪዎች ከእነ ግሳንግሳቸው ተፈጠሩ? ወይስ ከንቱ መሆን እራሱ ከንቱ አለመሆን ነው? ወይስ መሆን አለመሆን! አለመሆን መሆን! መሆን መሆን! አለመሆን አለመሆን!አለመሆን መሆን ነውን? ለነገሩ አለማሰብ ፣ አለመጨነቅ ፣ አለመብሰልሰል ፣ በዝምታ ያለ አንዳንች ጥያቄ ናዳ መቀመጥስ? ይቻላል ከተቻለስ ይህስ ከንቱ አይደለም? ከንቱ ባይሆን እንኳን ከንቱ አለመሆን ራሱ ከንቱ አይደለም? ለመሆኑ እኔ ማነኘ? ስለምን ይህን ያህል ስለከንቱ መሆንና አለመሆን ተወጥሬ አስባለሁ?ስለምንስ ብቻዬን እቆዝማለሁ? ለመሆኑ እንደው ለአባባል ካልሆነስ ሰው ብቻውን መቀመጥ ይችላልን? አጠገቡ ሴይጣን የለም? አጠገቡ መላዕክት የሉም? አጠገቡ የሚያብሰለስለውስ ሀሳብ የለም? እንኪያስ እኔ ብቻዬን ተቀምጬ እውን ብቸኛ ነኘ ማለት ይቻላልን? ፈጣሪ እንኳን ብቻውን መሆን ይችላል? ፈጣሪ እንኳን ሰማይና ምድርን ሲፈጥር መች ብቻውን ነበር? እውን ከፀሀይ በታች ይሁን ከፀሀይ በላይ ብቸኘኘት የሚባል ነገር አለን? ስለምንስ ውስጤ በአንዳች የባዶነት ስሜት ይናወጣል? ስለምንስ ዘወትር ቀይና ጥቁር በሆነ በማያልቅ ጥያቄ እናጣለሁ? ስለምንስ በግዴለሽነት ወንዝ ጠብዝቼ እንቦጫረቃለሁ? ስለምንስ ስለህይወት ከንቱነት አብዝቼ እውጠነጠናለሁ? ስለምንስ ሁሉ ነገር የከንቱ ከንቱ ነፋስ የመከተል ያህል ነው እላለሁ? ስለምንስ በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ማዕበል ውስጥ እዋዥቃለሁ? ስለምንስ ስለዓለም በግዴለሽነት ማዕበል ተሞልቼ አውጠነጥናለሁ? ስለምንስ የመጀመሪያም የመጨረሻም በሌላቸው የጥያቄ እና ሀሳብ እንቆቅልሾች እያውጠነጠንኩ ራሴን አጀዝባለሁ? ስለምንስ በፍልስፍና መንገድ ለመኳተን እታትራለሁ? እደፋደፋለሁ? ማነኘ? መጨረሻዬ ምንድነው? ለመሆኑ መጨረሻውን የሚያውቅስ አለ? እንኳን እኔ ያለ ፍላጎታቸው ከፀሀይ በታችም ሳይሆን ወይም ከፀሀይ በላይም ሳይሆን "ገነት" በምትባለው የሀሳብ መንደር የተፈጠሩት ሁለቱ ሚስኪኖች ቀዳማይ አባታችን አዳም ሆነ እናታችን ሔዋን መጨረሻቸውን ያውቁ ነበር? መንገዱን ከፈጣሪ ጋር ያደረገው ሙሴ መጨረሻው ያውቅ ነበር? ታላላቅ የዓለማችን ነገስታት መጨረሻቸውን ያውቁ ነበር? አያውቁም!!! እና እኔ አንዲት ሚስኪን እንዴት መጨረሻዬን ላውቅ እችላለሁ? እ ና ም ስለ መጨረሻዬ መናገር አልችልም፡፡ አለመቻሌ ከንቱ ነው፡፡ በእርግጥ መጨረሻዬ መናገር ብችልም እንኳን ከንቱ ነው፡፡ በዚች በከንቱ የተወጠረች ዓለም ውስጥ የሰው ልጅ ከአምስት ደቂቃ በኀላ ስለሚሆነው ነገር በእርግጠኘነት መናገር አይችልም፡፡ መገመት መብቱ ነው፡፡ መመኘት መብቱ ነው፡፡ተስፋ ማድረግ መብቱ ነው፡፡ ሂሳባዊ ቀመር መስራት መብቱ ነው፡፡ ይህን ማን ይከለክለዋል? ለማንኛውም ስለመጨረሻዬ መናገር ባልችልም ስለተወለድኩበት ቀን.....አሁን እስካለሁበት ቀን ድረስ ያለውን መናገር እችላለሁ! መተርተር እችላለሁ መቀባጠር እችላለሁ! በእርግጥ ይህም ከንቱ ነው ንፋስን የመጨበት ያህል ነው፡፡ ኤጭ.......! ከሚለው የአዘርግ መፅሐፍ የተቀነጨበ፡፡ ኤጭ...! (በኢትዮጵያ ምድር የተከናወኑ ዘግናኘ ታሪክ) አዘርግ 2010 ዓ.ም አዲስ አበባ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ😊🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
Watch "Mykey shewa - ፍንዳታ Reaction" on YouTube https://youtu.be/xDHsIQko9Fs ቃሊታዬ የኔ😍😍😍👏👏👏 እባካችሁ SUBSCRIBE አድርጉና ተዝናኑ
Mostrar todo...
"ስለምንም ነገር እርግጠኛ ለመሆን ሰነፍ መሆን ያስፈልጋል" ቮልቴር ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች ኃይለጊዮርጊስ ማሞ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ @jahABP አስተያየታችሁን አድርሱኘ
Mostrar todo...
ቀጣይ ክፍል ለመመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮፕያ የተገጣጠመችው አውሮፕላን! ይህቺው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገጣጠመችው አውሮፕላን! ይህቺው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገጣጠመችው አውሮፕላን:- በማስተርስ ሊድግ ዌበር አማካኘነት በ1928 ዓመተ-ምህረት ነበር፡፡ በኃይለስላሴ ሴት ልጅ በሆነችው በፀሀይ ስም የተሰየመችው ይህቺው አውሮፕላን ተገጣጥማ ካለቀች በኀላ በረራዋን የጀመረችውን ወደ 150 ሜትር በማኮቦኮቦ ነበር፡፡ ሰባት ነጥብ ሁለት ሜትር ርዝመት ያላትና ሁለት መቀመጫ የነበራት ፀሀይ 149 የፈረስ ጉልበት ሲኖራት በሰዓት አንድ መቶ ሃምሳ ኪሎሜትር የመብረር ብቃት ነበራት፡፡ አውሮፕላኗ ማስተማሪያ የነበረች ሲሆን ፋሽሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረራ እስከያዘበት ጊዜ ድረስ ፀሀይ በአጠቃላይ የበረረችበት ሰዓት 30 ሰዓት ወይም አንድ ቀን ከስድስት ሰዓታት ብቻ ሲሆን፡፡ ሀገሪቱ በሞሶሎኒ ጦር ስር ስትወድቅ፡፡ ፀሀይን ከጃንሜዳከሚገኘ ዛፍ ስር ቆማ አገኟት፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ጥቂት ካበረርዋት በኀላ ወደ ሀገራቸው ጭነው የወሰዷት ሲሆን ዛሬም ድረስ በዚያው በኢጣልያን ሀገር በሚገኘ ቪዲ በሚባል ሙዚየም ውስጥ የንጉሱ አውሮፕላን ተብላ በጎብኚዋች እየታየች ትገኛለች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳት ያጋጠማት የሀገራችን አውሮፕላን እና በአደጋው የሞቱት ቀዳሚው ኢትዮፕያዊ! የመጀመሪያው አውሮፕላን ለጉዳት ስትጋለጥ አውሮፕላን ወደሀገራችን ከገባ አንድ ወር እነኳን አልሞላውም፡፡ መስከረም 5 በ1921 በደሴ አካባቢ "ሀጪ ሓጂ ሙሳ አጃይብ" በተባለ ቦታ በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ትንሽ ያለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡ ይሔን ግጭት ለማብረድና ለመዳኘት ደጅአዝማች ወልደስላሴ - ወልደሚካኤል ፣ ደጃዝማች አመዴ ፣ ፀሐፊ-ትዕዛዝ አፈወርቅ ሚሴ ሸሚት......ደብሊው 33 በተባለች አውሮፕላን ወደስፍራው ለማምራት ገና ተነስታ 100 ሜትር ከፍታ ብቻ እንደበረረች ሞተርዋ ይጠፋና በአደጋው የኃይለስላሴ አጎት የነበሩት #ወልደስላሴ #ወልደሚካኤል በተከሰከሰችው አውሮፕላን ህይወታቸው ሲያልፍ........ፓይለቱ ጨምሮ ሌሎች ተሳፋሪዎቹ ሊተርፉ ችለዋል፡፡ የወልደስላሴ ሞት መንስኤ የራሳቸውም ጥፋት ነበረበት የተባለው አውሮፕላኗ ለበረራ ከመነሳቷ በፊት የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶን ይሰሩ ሲባሉ፡- ኧረ ወይግዱልኘ እኔ እንዴት እንደፈሪ ቀበቶ የምታጠቀው!? ብለው ባለማሰራቸው የተነሳ ነው፡፡ በእምቢተኛነታቸው ነው የሞቱት የሚል ወሬ እንደተሰማ አልቃሾች...... ከላይ አልጨበጡ........ከታች አልረገጡ ሓጂ ሙሳ አጃይብ....እንደ እንቧይ ፈረጡ በማለት ገጥመውላቸዋል፡፡ ቃል አምባ መፅሔት 2ኛ አመት ቁጥር 50 ቅዳሜ መጋቢት 2011 ዓ.ም :: ተገንጥሎ ከተገኘ ገፅ ላይ የሰፈረ፡፡ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ፡፡ 😂😂ያስቃልም ያናዳልም😡😡 ሀበሻ ተገንጥላ ያገኛትን የመፅሔቷን ገፅ አንብቦት ለኛ ይዞ በመምጣት ፅሁፉን እንድናነብ ታሪክን እንድናውቅ ላደረገን #ለካሱ በእናንተ ስም ትልቁን አክብሮትና😘 ምስጋናን🙏 ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
#በአውሮፕላን #አደጋ #የሞቱት #የመጀመሪው #ኢትዮፕያዊ #ማናቸው?? የሰው ልጅ ለመገናኛ ከፈጠራቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከ100 ዓመት በላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የኖረው አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን ሰማይ የበረረውና በመሬታችን ላይ ያረፈው ነሀሴ 12 1921 ሲሆን ባለፈው 90ኛ ዓመት የልደት ቀኑ ነበር፡፡ ይኸው የመጀመሪያው አውሮፕላን አዲስ አበባ ከደረሰ በኀላ ልዩ ስፍራው :- ገፈርሳ-ሜዳ ከቀኑ ሰባት 7 ሰዓት ከአስር ላይ ያረፈ ሲሆን እለቱ ዕሁድ ነበር፡፡ይሄ አውሮፕላን ወደ ሀገራችን የገባበት አመት የመጀመሪያ የአውሮፕላን ፈጣሪ የሆኑት የዊልቨር ወንድማማቾች የተሳካ በረራ ካደረጉ ከ26 ዓመት በኀላ ነበር፡፡ አውሮፕላኑ በሀገር ቤት:- ንስረ-ተፈሪ የሚል የዳቦ ስም ወጥቶለታል፡፡ ቀጣዩ አውሮፕላን የንሥረ-ተፈሪ አውሮፕላን ከፈረንሳይ ተገዝቶ ከገባ በኀላ በቀጣይነት ወደሀገራችን የገባው አውሮፕላን ደግሞ ከሌላኛዋ አውሮፓዊት ሀገር ጀርመን ሲሆን አውሮፕላኑን የፈበረከው ጂንከር የተባለ ኩባንኛ ነው፡፡ ነሀሴ 30 1921 አመተ-ምህረት ከድሬዳዋ ተነስቶ ጃንሜዳ ላይ ያረፈው ይሔው አውሮፕላን ከድሬዳዋ ጀርመናዊውን ዶክተር ብሩስን እና አስተርጓሚያቸውን የነበሩትን አቶ አስፋው አንዳርጌን አሳፍሮ የመጣ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ፖስታዎችን ጭምር ይዞ ነው፡፡ አብራሪው ኢግል የተባለ ሲሆን አውሮፕላኑ ጃ# ሜዳ በደረሰ ጊዜ ታላቅ አቀባበል ነበር የተደረገለት፡፡ በቦታው ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ጨምሮ ሚኒስተሮች መኳንቶችና ጥሪ የተደረገላቸው የውጪ ሀገር ዲፕሎማሶች የተገኙ ሲሆን ኃይለስላሴም በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡ አውርፕላኖቹ ቁጥር በአጭር ጊዜ ያበዛችው ሀገር! ነሀሴ 12-19-21 የመጀመሪያው አውሮፕላንን ከፈረንሳይ ገበታዋ ይዞታዋ ያደረገችው ኢትዮጵያ ይሄን የቴክኖሎጂ ውጤት በአየርዋ ላይ በስፋት ለማርመስመስ እምብዛም ጊዜ አልፈጀባትም፡፡ የኢጣሊ ፋሽሽት ጦር እስከወረራት 1928 አመተ-ምህረት ባሉት ሰባት አመታት ብቻ የኢትዮፕያ የ16 አውሮፕላኖች ባለንብረት መሆኗ ሲታይ ምን ያህል ለዚህ ቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥታ እንደነበር ያሳያል፡፡ በተለይ ከዚህ የአውሮፕላን መብዛት ጋር ተያይዞ በወቅቱ በሕዝቡ የተገጠመ ግጥሞች ነበሩ፡፡ አውሮፕላን መጣ........ሰማይ ለሰማይ የተበደለውን...............ድሃውን ሊያይ ነይ እንሳፈር................ነይ እንሳፈር በማይነቀነቀው.............በሰማይ ባቡር! ይቀጥላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
ወይ ጉድ 😂😂😂😡😡😡🤔🤔 ስቄያለሁም ተናድጃለሁም ሂሂሂሂ...ሃሃሃ..ዝም የአንድ የሀገራችንን ማወቅ ያለብንን ታሪክ አስቂኘም ነው አስገራሚም ነው.....ጠቅላላ ዕውቀት ላይ እራሱ ቢጠየቅ አብዛኛው ሰው ያውቀዋል ብዬ አላስብም 😂😂🤔 ፅሁፉን እስክለቀው በመጀመሪያ ለመለሰልኘ ሰው የmb ሽልማት አለኘ፡፡ ፅሁፉን ያገኘሁት ካሱን አወቃችሁት አይደል እሱ ካመጣልን ከአንድ የመፅሔት ቁራጭ ላይ ነው፡፡ በአውሮፕላን አደጋ የሞቱት የጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ማናቸው?? መቼ?? ሰው ያላቸውን ቢሰሙ እኮ አይሞቱም ነበር ምክንያቱም አብረዋቸው ያሉት ሌሎቹ ተርፈዋላ ፓይለቱንም ጨምሮ ፡፡ ሀበሻ ኩራት እኮ😂😂😂😔😔 ኧረ ወግዱልኘ እንደፈሪ......ቀበቶ ልታጠቅ እንዴ አሉ😂😂😂😂 ከነሙሉው ታሪክ እመለሳለሁ ጥያቄው ላይ ሩቡ መልስ አለ ትልቅ ሰው እንደሆኑ ሴት ይሁኑ ወንድ ባታቁትም፡፡ መልካም ቀን ተመኘቻለሁ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ነገ ጠብቁኘ ታሪካችንንማ ማወቅ አለብን 🏃‍♂🏃‍♂ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
Mostrar todo...
ወይ ጉድ 😂😂😂😡😡😡🤔🤔 ስቄያለሁም ተናድጃለሁም ሂሂሂሂ...ሃሃሃ..ዝም የአንድ የሀገራችንን ማወቅ ያለብንን ታሪክ አስቂኘም ነው አስገራሚም ነው.....ጠቅላላ ዕውቀት ላይ እራሱ ቢጠየቅ አብዛኛው ሰው ያውቀዋል ብዬ አላስብም 😂😂🤔 ፅሁፉን እስክለቀው በመጀመሪያ ለመለሰልኘ ሰው የmb ሽልማት አለኘ፡፡ ፅሁፉን ያገኘሁት ካሱን አወቃችሁት አይደል እሱ ካመጣልን ከአንድ የመፅሔት ቁራጭ ላይ ነው፡፡ በአውሮፕላን አደጋ የሞቱት የጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ማናቸው?? መቼ?? ሰው ያላቸውን ቢሰሙ እኮ አይሞቱም ነበር ምክንያቱም አብረዋቸው ያሉት ሌሎቹ ተርፈዋላ ፓይለቱንም ጨምሮ ፡፡ ሀበሻ ኩራት እኮ😂😂😂😔😔 ኧረ ወግዱልኘ እንደፈሪ......ቀበቶ ልታጠቅ እንዴ አሉ😂😂😂😂 ከነሙሉው ታሪክ እመለሳለሁ ጥያቄው ላይ ሩቡ መልስ አለ ትልቅ ሰው እንደሆኑ ሴት ይሁኑ ወንድ ባታቁትም፡፡ መልካም አዳር ተመኘቻለሁ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ነገ ጠብቁኘ ታሪካችንንማ ማወቅ አለብን 🏃‍♂🏃‍♂ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
Mostrar todo...
፡፡፡፡፡፡፡፡፡ በሸንጎ ተጀንኘ ፍቅሬን በግልጥ ፣ በአደባባይ ደስታየን በድንጋይ ሰሌዳ ላይ መናዘዜ ቅሬታዬን በደብዛዛ ርሳስ መከራየን በለሆሳስ ጭንቄን በምስጢር መያዜ ካዘናጋሽ አንድ ቁምነገር ላውራሽ! ተከፍቼ ግና ፊቴ ላይ የብርሃን ዱቄት ነፍቼ ምድር አትችለው ችዬ ፣ ሆዴን ከጠረፍ አስፍቼ ከሾህ አክሊሌ በላይ ፣ ያልማዝ ዘውዴን ደፍቼ በሸንጎ ተጀንኘ ፣ በእልፍኜ ብስለመለም ህመምን አለማወጅ አልታመምኩም ማለት አይደለም፡፡ በዕውቀቱ ስዩም:- አዳምኤል የግጥም መድብል
Mostrar todo...
#ኩርኩም 1 የእግዚአብሔርን ዕርዳታ የረሳን እንደሆነ በእርግጥ እኛ ደካሞች ነን፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሰው ብቻውን አይደለምና፡፡ ሰው በባህርዩ ደካማ ቢሆንም በእግዚአብሔር እርዳታ የማይችለው ነገር የለም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ "ሀይልን በሚሰጠኘ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡" በማለት እንደተናገረው፡፡ የሚፀልይ ሰው ከእግዚአብሔር ሀይልን ለማግኘት ይፀልያልና ደካማ አይደለም :- ፀሎቱም ሃይልን ታደርጋለች፡፡ በህይወቱ ውስጥ በበረከትና በረድኤት ስራውን ይሰራል ይህም በሀጢያት ላይ ኃይልን ይሰጠዋል፡፡ ዳዊት እኔ ደካማ ነኘ- እግዚአብሔር ይረዳኛል ባይል ኖሮ ጎልያድን ባልተዋጋ ነበር፡፡ ጎልያድ ግዙፍ ነው ባለብዙ መሳሪያ ነው ሊፈራው ይችል ነበር፡፡ ዳዊት ማንም እንዲዋጋ አልጠየቀውምየጦር መሪዋች ሳኦልነ ጨምሮ ግልያድን ፈርተውት ነበር፡፡ ስለዚህ ዳዊት እኔ ደካማ እና ትንሽ ነኘ ለማለት በቂ ምክንያት ነበረው፡፡ እግዚአብሔር ግን አደፋፈረው ሁሉም ሰዎች የሁኔታውን ክብደት ተረድተው ነበርዳዊት ግን በእምነት ለድል በቃ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ልንፈፅመው የማንችለውን እንድም ፈፅም አያዝምና የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከባድና አስቸጋሪ እንደሆኑ ማሰብ የለብንም፡፡ ፈጣሪያችን ያዘናል የምንፈፅምበት ሀይል ይሰጠናል፡፡ ከትዕዛዛቱ ጋር ደግሞ ፀጋው አለ፡፡ ያለበለዛ ሊውጠን እንደሚያገሳ አንበሳ ሆኖ የመጣውን ሴጣን መቋቋም ባልተቻለ ነበር፡፡ አባታችን አብርሃምም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከብዶትየታዘዘውን ከመፈፀም አልገታውም፡፡ በእርጅና ያገኘውን ልጁን ለእግዚአብሔር እንዲሰዋ ሲጠየቅ እምቢ አላለም፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ለመፈፀም አልችልም ብሎ አላመካኘም፡፡ ይቀጥላሉ..... ለኃጢያት በምንም መንገድ ቢሆን ሽፋን የሚሆን ስያሜ ሊሰጠው አይገባም፡፡ ኃጢአት በኃጢአትትነቱ ልናውቀውማ ልንሸሸው የሚገባ ጠላታችን ነው እንጂ ለአእምሮአችን እንዲመች የቅድስና ስም እየሰጠነው ራሳችንን የምንሸነግልበት መሆን የለትም፡፡ እውነቱን እንናገር ከተባለ ማንኛውም ኃጢአት በሚሰራው ሰው ዘንድ የመሸፈኛ ሌላ ስያሜ አለው፡፡ በዚህም የተነሳ ኃጢያተኛው ንሰሃ አይገባም በዚህ የመጽናኛና የሽፋን ስያሜ እራሱ እያእያታለለ በኃጢያት ይኖራል እንጂ፡፡ ሲጃራ የሚያጨስ ሰው በማጨሱ የሚደሰትበት መሆኑን እንጂ ኃጢአት እየሰራ መሆኑ ስለማያስብ፡-ማጨስ ደግሞ "የደስታ ምንጭ" የተሰኘ የተሳሳተ ስያሜ ስለጠሰጠው የሚያጨሰው በዚህራሱን እያታለለ ማጨሱን ይቀጥላል እንጂ ንሰሃ አይገባም፡፡ ጭፈራም "ጥበብ" ወይም "አርት" ስለተባለ፡- ዝሙትና ማመንዘር (ፍቅር) ስለተሰኘ፡- የሚፈፅሙት ሁሉም ኃጢያት እንደሰሩ ስለማያስቡ፡ንሰሃ አይገቡም፡፡ ሰዎችን ለማሳሳቅ ብለው አንዳንድ ሰዎች በቀልድ ሽፋን በሌሎች ሰዎች ያሾፋሉ በዚህም የሰው ህሊና ይጎዳሉ ፣ ይዋሻሉ የኃጢአት ቃላትን ይጠቀማሉ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች ኃጢአትን ይሰራሉ፡- በእነዚህ ሰዎች አመለካከት በሃሳባቸው እየቀለዱ እንጂ ኃጢያት እየሰሩ ስላልሆነ ንሰሃ አይገቡም፡፡ ከዚህ ሁሉ በተቃራኒ ደግሞ ጭካኔም "የበግ ልምድ ለብሶ" የሚቀርብበት ወቅት አለ፡፡ ለምሳሌ ጨካኘ አባት ልጅን በሥነ-ስርአት እንደአሳደገ ራሱን ይቆጥራል እንጂ ጭካኔው ሀጢያት መሆኑን አያስብም፡፡ በመፅሐፍ እንደተፃፈውም "በቁጡነቱም ጽድቅን የሰራ ይመስለዋል" ነገር ግን ቅዱስ ዳዊት "አቤቱ በቁጣህ በአትቅሰፈኘ "ያለውን ዘንግቶታልና ይህን ስራውን እንደ ኃጢአት ላይቆጥረው ይችላል፡፡ ሰው የሚወደውን ኃጢአት የተቋቋመ እንደሆነ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ባለድልና አሸናፊ ይሆናል፡፡ ኃጢአትን መቋቋም አሸናፊ የሚያደርግ ከሆነ ብዙውን አጢአት ተቋቁሞ በአንዱ መውደቅ ረብ የሌለውና የማይጠቅም ስለሆነ በኃጢአት ሁሉ ላይ አሸናፊነትን ለመቀዳጀት መጣር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ጠላታችን ሴይጣን ልንቋቋመው ባልቻልነው ኃጢአት ገብቶ በልቦናችን ግዛቱን ካስፋፋ በኀላ ከፈጣሪያችን ሊለየን ይችላልና ነው፡፡ አንዲት የመርፌ ቀዳዳ በምታክል ቀዳዳ ግዙፉ መርከብ ለመስመጥ ታበቃዋለች ፣ አንዲትም ነቁጣ ዕድፍ ያማረውን ሸማ ታቆሽሸዋለች ፣ አንዲጥ ጠብታ ቀለም ብርጭቆ ውስጥ ያለውን ንፅህ ውኃ እንዳይጠጣ ታደርገዋለች በሌሎች ትምህርቶች ሁሉ ጥሩ ውጤት ያመጣ ተማሪ በአንዱ ቢወድቅ ሊመረቅ አይቸልም በመሆኑም የወደቀበት ትምህርት እስኪያልፍና ጥሩ ውጤት እስኪያመጣ ድረስ መማርና ማጥናት አለበት፡፡ የታመመ ሰው ከመላ አካሉ አንዱ በሽታ ቢሆን የታመመው አካሉን ክፍል ተመርምሮ መታከም አለበት፡፡ ኃጢአትም እንዲሁ ነው መንፈሳዊ በሽታ የነፍስ ደዌ ነውና ትንሽም ቢሆን አንድም ቢሆን መታከም ያስፈልጋል፡፡ ጾመኛ ሰው ምግቦች ሁሉ ቢተው ነገር ግን የሚወደውን ምግብ መመገቡ ባያቆም አልጾመም፡- የሚወደውን እያደረገ ነውና፡፡ መፅሐፍም "ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከ ልማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፡፡" በማለት ያስገነዝባል፡፡ ከእግዚአብሔር አብልጠን የምንወደው ነገር መኖር የለበትም፡፡ ለእግዚአብሔር ስላለን ፍቅር ግን ሁሉን መተው ይገባል እንጂ፡፡ ከእግዚአብሔር አብልጠን የምንወደውና ከእግዚአብሔር የምናወዳድረው ነገር ካለ ሀጢአት ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በልባችን ከእርሱ በቀር ማንም እንዳይኖር ስለሚሻ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኘ" ይለናል፡፡ ልባችንን ለእግዚአብሔር የሰጠን እንደሆነ ሀጢአት ከእኛ ይርቃል፡፡ ልባችን ከእግዚአብሔር የራቀ እንደሆነ በእኛና በእርሱ መካከል እንቅፋት የሆነ ፈቃደ ሰይጣን ኃጢአት ይገባል በልባችን ያለውን ፍቅረ እግዚአብሔር ይከፍልብናል ይቀንስብናል ከእግዚአብሔር የበለጠ ኃጢአትን እእድንወድ ያደርገናል ከአምላካችንም ያጣላናል፡፡ የመፅሐፍ ርዕስ :- የንሰሃ ሕይወት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሸኖዳ ፫ኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ፡፡ ውርስ ትርጉም:- ቀሲስ እሸቱ ታደሰ ወንድም አገኘሁ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ፡፡ ታነቡት ዘንድ ግብዣዬ ነው እራሳችንን ቆም ብልን እናይበታለንና እንኮረኮምበታለንና፡፡ ጥፋተኛ እንደሆንን ማመን ጥሩ ነው፡፡ ያንን ካመንን ለይቅርታ እንዘጋጃለን ለጥፋታችንም ቅጣቱን መቀበል የተገባ እንደሆነም እናምናለንና ለጥፋቱም ሌሎችን ሳይሆን እራሳችንን እንወቅሳለንና፡፡ መልካም ቀን😊🙏 @jahABP አስተያየታችሁን አድርሱኘ እቀጥላለሁ.....🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN #ኩርኩም አዎ አጥፍቻለሁ ለጥፋቴም ቅጣት ይገባኛል፡፡ በአለምና በእጄ ባለው ስኩራራ ስለዚህ አለም ስጨነቅ የላይኛውን ፈጣሪ ስረሳ.....ሀጢያትን ሳበዛ ተስፋ ወደ መቁረጥ ስቃረብ የፀሎትን ዋጋ ስረሳ ሀይለኛ ኩርኩም ያስፈልገኛል በእጅ አይደለም ታዲያ ጢኒጢየዋ መፅሐፍ መደርደሪያዬ ላይ የሳቸውን መፅሐፍ አነሳለሁ እገልጣለሁ......እራሴን እወቅስበታለሁ እያነበብኩ ቃላቶቹ በሰውጅ ከምመታው ኩርኩም በላይ ያሙኛል.........ብዙ መፅሐፍትን ፅፈዋል ዕውቀታቸው ጥልቅ ነው ወጣቱን ትውልድ ይታዘቡታል እያንዳንዱ መፅሐፋቸው በተለያየ ቋንቋ ተተርጉሟል ቃላታቸው ሃይል አላቸው ስታነቡት እሳቸው በጆሮ መተው የሚናገሩ ነው ሚመስለው.... በተለይ በዚ ሰዓት እኛ ወጣቶች ኩርኩም ያስፈልገናልና ከሳቸው መፅሐፍ ትንሽ ልቆንጥር🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ በፊት ብዙ ጊዜ አሁን ደግሞ አንዳንዴ በራሴ እታበያለሁ ሁሉንም እችላለሁ እላለሁ እዚጋም እዛጋም መግባት ያምረኛል፡፡ ነፍስ ገዝቼ የሱን ዘፈኖች ሰምቼ ቀጥሎ አዳምጬ ደጋግሜ አዳምጬ ወይ ጉድ እላለሁ የትአባትክንስና ሰው ሁሉንም ነገር አይችልም ብሎ በኩርኩም ይለኛል፡፡ ሬጌ ምት ነው ለመስማት አይቸግርም የኢትዮፕያው የሬጌው ንጉስ ዘፈኑን ቆንጆ አድርጎ ይጫወተዋል #በእዮባ ድምፅ አድርጎ ገጣሚው ይመክረናል....ይገስፀናል እንዲህም ይለናል.....🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ እመለሳለሁ አብረን እንኮሮኮማለን🙇🙇 @jahABP ነኘ😊🙏
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሁለት ወንድ "ፍቅረኛዬን ለምን አናገርካት" ገጭ! "ፍቅረኛዬ ላይ ምን ታፈጣለህ" ገጭ.....ገጭ!! ማንንም አይፈራም፡፡ እሷ ግን ትሸማቀቃለች፡፡ እሷን አቅፎ አይኑ ወደሷ የሚወሰልተውን ይፈልጋል ገጭ!...ገጭ!..ገጭ! አንዳንዱ ጎረምሳ ዱቄት ተነፍቶበት ከወደ ሽንትቤት ከመጣ እንደታሸ ታውቃለች፡፡ አንዳንዱ የፊቱ ሚዛን ተዛብቶ ብቅ ይላል፡፡ የመጨረሻውን ወንድ እፊቷ ሲመታው እሷ ብሳ ቱግ አለች፡፡ "አየሽ!" "አላየኘም" "አይቶሻል እኮ!" "ቢያየኘስ" የተመታው ይገላግላቸው ጀመር፡፡ "ካየኹም ይቅርታ ብሎ" ጉልበት ሊስም አጎበደደ አንዳንዱ ወንድ ምኑ ታይቶ ነው ወንድ የሚባለው? አንድ አይኑ ተለስኗል፡፡ ይህን ስትመለከት ቅልብሽ አላት፡፡ "አሳፈርከኘ" በፍቅረኛዋ እየተለመነች እንቢ ብላ ስትሔድ.... የተደበደበው ለመናት "በእኔ ሰበብ አትጣሉ" እንቢ ብላ ሔደች የአንዳንዱ ሰው ፍርሃት እየገረማት፡፡ ጠዋት ፍቅረኛዋ ደወለላት፡፡ "ምንድነው??" "እስኪ ነይ" "የት ነህ" "እቤቴ" "ስራህስ" "ቀረሁ" "ለምን" ኦ!.....ኦ!...ነይ" ንዴቷን ለመበቀል ጭምር ሔደች ተኘቷል፡፡ ሁለት አይኖቹ አብጠዋል፡፡ ግራ እጁ ከክርኑከፍ ብሎ ፋሻ ተጠምጥሟል፡፡ "ምንድነው??" "እ!" "አንቺ ስትሔጂ እሷ ፊት አላዋርድህም ብዬ ነው፡፡ በልና ይዋጣልን.....ብሎ ወንድ ነው!! መላልሼ ብገጥመውም መላልሶ አሸነፈኘ፡፡ወንድ ነው!! አጋጣሚ ከመሰለህ ሲሻልህ ደውልልኘ ብሎ ስልኩን ሰጥቶኘ ታክሲ አሳፈረኘ፡፡ እ....በህይወቴ ሁለት ወንድ አውቃለሁ፡፡ #እሱ እና #እኔ፡፡ አለማየሁ ገላጋይ :- ውልብታ 🙏😂😂መልካም ቀን 😂😂🙏 አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ😊🙏
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY መልካም ልደት ንጉሱ😍💪💪👑🌕🌎✨💥🎂🎂🍭🍮🍩🏹🏇🏇🏆🥇🥈🎼🚗🚞🚉🚦🏠🏗☎️📺📻📡💡🕯🔧🔨⚖⚖⚖⛓🏺⚱🔬🚪🗝📈🗒📚📖🔓🔓🔓🔓🔓🔓 "ሚኒልክን ልትጠላው ትችላለህ፤ ደግሞም ልትወደው ትችላለህ። ነገር ግን ሚኒልክ ተራ ስብዕና እንዳልነበረ ለመረዳት አይከብድም። ሚኒልክ ውስብስብ ሰው ነው። ረቂቅ ነው። ደግሞ አድማጭ ነው። ሚኒልክ እንደ ገሞራ እሳት የሚፋጅ ነው። ደግሞ እንደ ምንጭ ውኃ ገር ነው። ሚኒልክ ሀገር መመስረት፣ ግዛት ማስተዳደር ያውቃል። ተራ የታሪክ ሰው አይደለም። ጉልህ ነው። የሚኒልክን ነገር ለማጉላት ብዬ ከሌሎች ማወዳደር አልፈልግም። ዳግሞም ማሳነስ ሊሆን ይችላል። " @jahABP ነኘ #፲፪-፲፪-፲፪
Mostrar todo...
ይህ ቻናል #የተዓምረኛዋ #ወይንየ ጌቴ ሴማኒ #ቅድስት #አርሴማ አንድነት ገዳም መረጃ የሚቀርብበት ነው:: ስለ ገዳሙ አመሰራረትና በገዳሙ ስለተፈፀሙ ተዓምራት ለመከታተል ይቀላቀሉን https://t.me/WeynyeArsema
Mostrar todo...
"ሰይጣን ኃጢያት እስክንሰራ ጎበዝ ይለናል፡፡ ከሰራን በኀላ የማትረባ ውዳቂ ነህ ይለናል፡፡ እስክንሰራው ያበረታታንና መልሶ ይከሰናል፡፡ ከኃጢአት በፊትና ከኃጢአት በኀላ ሰይጣን ሁለት ጠባይ አሉት፡፡ ከኃጢአት በፊት ኃጢአትን ቀባብቶ የሚያቆነጅ ማታለል ፣ ከኃጢአት በኀላ ደግሞ ምህረት የማይገባህ ስለሆንኩ እኖራለሁ አትበል ይለናል፡፡ ሁለቱንም ጊዜ ጠላትችን ሴጣንን እናምነዋለን፡፡ ሁለቴም ሰይጣንን ስናምን አንድም ጊዜ ግን #እግዚአብሔርን አንሰማም፡፡ " ማስተዋሉን ያድለን🤦‍♂ መልካም አዳር🙏 @jahABP ነኘ😊
Mostrar todo...
" ሰዎች ለማለት ነው የሚኖሩት፡፡ ትልቁ ነገር ሆኖ አለመገኘት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሉትን መስማት ጥሩ ነው፡፡ እንደጨረስነው አድርገው የሚያወሩትን ወሬ ገና በህሊናችን ውስጥ ሲተራመስ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ ነገሩን ብንፈፅመው እንዲህ ነው የምንባለውና የሚሆነው ለማለት ይረዳናል፡፡ ስጋ የሚወዱ ሰዎች ስለ ስጋ ያውቃሉ፡፡ ሐሜተኞችም የሚያሙን ሲፈሩን እንጂ ሲንቁን አይደለም፡፡ እነዚህ ሐሜተኞች የሞቱትን አያሙም፡፡ ያበዱትን በአፋቸው አያነሱም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ካሙንና ከነቀፉን #አለን ማለት ነው፡፡ " 🙏 መልካም አዳር🙏 @jahABP ነኘ😊😊😊
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN እመጣለሁ!!! ሐኪም ቤት ቁጭ ብለናል ዶክተሩ እስኪወጣ እየጠበቅን ነው፡፡ የሐኪም ቤቱ ንፋስ በየት በኩል እንደሚነፍስ አናቀውም እየበረደን ነው......እግሬን ይበርደኛል ጆሮዬን ይበርደኛል...እጄ ወደመደንዘዝ ጀምሯል "ጠንካራ መሆን አለባችሁ" አለችኘ..... ከገባሁበት እራሴን የማሞቅ ሰመመን ነቅቼ እ አው...ልክ ነው አልኩኘ፡፡ አንድ ታሪክ ላጫውትህ የአሁን ወጣቶች መጠንከር አለባችሁ በጣም ጠንካራ መሆን አለባችሁ ይህን ስልህ እኔ ከሷ ጠንካራ መሆንን ተምሬያለሁ....እሷን አወካት አይደል አንዴ ምን እንዳደረገች ታውቃለህ.....ሐኪም ቤት ሰው እያስታመመች ነው ለሊት ላይ ሰውየው ሞተባት እእእ🤦‍♂😱😱😳.....እሺ ቀወጠችው ስል ወይ አንተ........ብላ....... "አለማየሁ ዋሴ ሰበዝ በሚለው መፅሐፉ አስገርሞናል....ከሱም እንመዛለን የኔ ፕሮፌሰር ብሎ ይጀምርና ዝም ብለህ ተናገር ይለናል ለሀገራችን ቦለቲካ እኔ ከሞትኩም ሰርዶ ይብቀል ይለናል አማርኛ ቋንቋ በክብር አስጨብጭቦ አመጣኘ ይለናል ብዙ ብዙ ይመክረንና አልጨረስክልኘም ብሎ በቁጭት በንዴት ይዘጋብናል..... " ከሩቅ ከሬዲዮ ይሁን ከቴሌቪዥን " ኢትዮፕያ ለዘለዓለም ትኑር" የሚል ድምፅ ይሰማኛል ምን የሚሉት የቂል ወሬ እንደሆነ ሁሌም ይገርመኛል ሁሌም ዘለዓለም ማንም እንደማይኖር እየታወቀ እያወቁት ያውም ኢትዮፕያ....ለዘለዓለም ሃሃሃሃሂሂሂሂሂሂሂ 😂😂😂 በዚ ካልሳኩማ በምን ልስቅ ነው ሃሃሃሃሃ ይሔ ሞኘ ህዝብ መቼ ይሆን ሚነቃው ኤዲያ.............አጭሩ ወግ ይቀጥላል....🏃‍♂ እዚ ማዶ አኔ እና እሱ እያወጋን ነው፡፡ ኡነቴን ነው ምልህ አብያ ይሔ ጨለማ አይንጋልኘ ብሎ ይምልልኛል፡፡ እዛ ማዶ ያለው ደሞ ኧረ ለኛ ሲል ይንጋ.....ይላል በማስክ የተወራው ወሬ ለኔ በቅጡ ያልተሰማኘ እዛ ማዶ ተሰማ፡፡ መጀመሪያ ሳቄ ነው ያመለጠኘ ኧረ ለኛ ሲል ይንጋ😂🤔🤔ተፈላሰፈ እንዴ😳 ኡነትም ግን እንደ አንዳዳችን ፍላጎት ቢሆን እኮ ይቺ አለም አትነጋም ማለት ነው🤔🤷‍♂፡፡ ይህንን አዝናኘ ወግ እንመለስበታለን፡፡ ብዙ ሰው እኮ አንተ ጎበዝ ነህ ማለት አይፈልግም ለአንተ ሊልህ አይፈልግም ስራዎችህን አይቶ ድንቅ እንደሆነ እያወቀ ስህተቱን ለማውጣት ይሮጣል ይህ የኔ በምትላቸው ሰዎች ይብሳል ይህንን ሁሌም አትርሳ ምርጥ እንደሆንክ ያቁታል እነሱ ስላሉህ ስላላሉህ ብለህ አንድም ደቂቃ ከአላማህ እንዳታዛነብል....ይሔ የሁል ጊዜ ምክሬ ነው፡፡ PEOPLE ALWAYS GO AWAY DON'T FORGE THAT.👊 ከራሴ ከምለው ሰው ጋር ያደረኩት አስደናቂ ቆይታ.....ቃለምልልስ ልለው እችላለሁ ረጅም ሰዓት አውርተናል እኔም እጠይቃለሁ እሱም አይሰለቸውም ይመልስልኛል....... እኔ፡- እስኪ ስለሴቶች አውራኘ አብሶ ስለዘመኑ ሴቶች? እሱ፡- በመጀመሪያ ሁለታችንም ምንስማማው አንድ ነገር አለ ...አይደል🤔 እኔ:- አዎ አዎ በአሁን ሰዓት ሴት ልጅ መውለድ አያስፈልግም የሚል አስተሳሰብ እንዳለን አውቃለሁ፡፡ እሱ፡- በኡነት101% ልክ ነን መቼም መቀየር የለብህም ይህን አስተሳሰብ፡፡ ፈጣሪን እንለምነዋለን ወደፊት ካገባሁ ካገባሁ ነው ያልኩት አግብቼም ከወለድኩ ሴት ልጅ አትስጠኘ ብዬ እማፀነዋለሁ ኧረ ሴትነት ፈተና ውስጥ ገብቷል ወንድሜ ለአብለጭላጩ ዘመን እጃቸውን ሰጥተዋል የቤተሰብ እልህ አይታያቸውም ሀሳባቸው ቅንጡነትን ነው ቅንጡ እቃ ነው ቤተሰብ ኖረው አልኖረው ፍቅረኛዬ ኖረው አልኖረው አይታሰብም አንተ ካላመጣህ ስንት ያልኩትን ሚያመጣ ወንድ ሞልቷል ሚሉ ይመስለኛል በልባቸው ደሞም ይላሉም እንጂ ሂሂሂሂሂ በትንሽ ብርም ተገዝቶ የተገዛበትን ማዋደድ ነው ሆኗል ስራቸው ተገላልጦ ለመታየት ጡትና ቂጥን ለማሳየት የሚደረግ ሩጫ ነው መላ ሰውነትን ለማሳየት እከሌን ለመሆን የሚደረግ ሩጫ ነው በአሁን ሰዓት ሴትነት.......እያለ ይቀጥልና ይህን ማድረግ ግን መብታቸው አይደለም አላልኩም ግን ልኩ ምንድነው?? እሱ እራስን መጠየቅ ነው፡፡ ግን ይሔ የኔ የአንድ ተራ ሰው አሳብ ነው ሴቶች ላይ ያለኘ.....ለራሴ ልክ ነኘ እና ደግሞ የኔም ያንተም አብዛኛው ጀለሶቻችን ሴቶች መሆናቸውን መዘንጋት የለበትም፡፡ ግን የአንተን የተወሰኑ ሴት ጓደኞችህን ሳላደንቅ ማለፍ አልፈልግም ከነገርከኘ አንፃር ወይም የዋህ ስለሆንክ እነሱ አሳምነው ነግረውኸም ሊሆን ይችላል፡፡ ማለቴ ዋሽተውህ😂😂👊👊 እኔ፡- አይ ውሸት አይደለም እኔም ምኮራባቸው አሉ እንኳንም አወኳቸው እንኳንም ጓደኞቼ ሆኑ ምላቸው፡፡ እሱ፡- በነገራችን ላይ.............አለች?? አንተ እኮ ምትገርም ሰው ነህ እኔ፡- አይ እሱን ተወው ሌላ ጥያቄዬን ልቀጥል እሱ፡- ጎበዝ ወዳጅ ነህ ለማለት እደፍራለሁ አፍቃሪ ለመሆን አትችልም አፍቃሪ ሚባል ነገር የለም፡፡ ይቅርታና አንድ ምኞት ልመኘ??😃 እኔ፡- እሺ እሱ፡- ሁሌም ለራሴ እንደራሴ አይነት ጓደኛ ባገኘ እመኛለሁ.......ይህን ምኞቴ ላንም ጨምሬ መመኘት ጀምሬያለሁ እንደ አንተ አይነት ሰው እንድታገኘ እመኛለሁ፡፡ እኔ ፡- እሺ አመስግኛለሁ😍🙏 በጋዝ ተከቦ ትንንሽዬ ነጠብጣቦች ከታች ወደ ላይ ከሚፈነዳው ስፕራይቱ ተጎነጨ.... ምንም አይደል የሚል ፈገግታን ለገሰኘ እኔ፡- ስለ ውሸት እናውራ እሱ፡- ዛሬ ስለሴቶች ነው እንዴ ልናወራ የመጣነው.................😂😂😂😂😂ረጅም ሳቅ በሁለታችንም መካከል😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂 ha ha ሂሂሂሂሂሂ ሃሃሃሃሃሃ....ኧረ ልታስገድለኘ አይደል ሃሃሃሃሃሃሃ አንተ እራሱ አንድ አባባል እኮ አለህ አይደል......ሂሂሂሂሂሂ ልጀምረው፡ጨርሰው በናትህ.....ሂሂሂሂሂ 😂😂በ ጣቱን ወደኔ እየጠቆመ አይ አንተ ይለኛል ሴቶች ውሸት ስለሚወዱ.......እ ቀጥለው እኔ:- ወንዶች ውሸታም ሆኑ ነዋ፡፡ ረጅም ሳቅ😂😂😂😂😂😂😂 ውሸት ስለሚወዱ ወንዶች ቆንጅዬ ውሸቶችን እየፈጠሩ በጠረባ እየጣሏቸው ነው፡፡ እንዲህ እያልን ቀጥለነዋል ሙሉውን እቀጥለዋለሁ...🏃‍♂🏃‍♂ ግራጫ ቃጭሎችን አስታወሳችሁት አዳም ረታ ..........መዝገቡ.........መዝጌ......እሱን እኮ በአካል አገኘሁት🙈 እንዴት? የት? መቼ?...🏃‍♂🏃‍♂ ከመዝገቡ ጋር ያደረኩት አጭር ቆይታ እኔ እእ እና አባቴን እጠላቸዋለሁ እጠላቸዋለሁ ይለናል.....፡፡ ሌሎችም አሉ እንቀጥላለን ማንበብ ማንበብ መፅሐፍን ብቻ ሳይሆን ሰዎችንም ተፈጥሮንም ስሜትንም ንግግርንም ፊትንም ሳቅንም ሀዘንንም ድምፅንም ዝምታንም ጫጫታን ሁሉንን ማንበብ..ከዛ ከራስ ስሜት አንፃር መገምገም አንዱን መጣል አንዱን ማንሳት እንደሚጠቅመን አድርገን መስራት ለኛ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰባችን እንዲጠቅም አድርገን ጭምር እንጂ ፡፡ @jahABP ነኘ ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኘ፡፡ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ #ጠባቂ!? ? ! ደሮ እንደጮኸ… ጭፍኑ ዳመና ብርሃን ይለብሳል በፀሐይ ጨረሮች አካሉ ይበሳል ቁኑ እንዲህ ያልፋል… ዳመናው ተባዝቶ ፀሐይዋን ሳያሳይ ንጋቷን ከቀትር ካመሻሿ ሳይለይ ቀኑ እንዲህ ያልፋል… ዳመናው ሆድ ብሶት እንባዉን ሲያወርደው የፀሐይና ጨረቃን ተፈራርቆ መቆም ከእቁብ ሳይቆጥረው ሌተ ቀን ሳይመርጥ መሬት ይደልቃል መከር ከተስፋ ጋር ርቆ ይታየኛል ቀኑ እንዲህ ይሄዳል… መንገድ ዳር ቁጭ ብየ ሁሉን እየታዘብኩኝ ብርዱን አለምድ ብየ ጥጥ እየባዘትኩኝ ዝናብ ያጠፋዉን እሳት እየሞኩኝ ጊዜው እንዲህ ይሄዳል… ቀኑ ከምሽቱ በጋ ከክረምቱ ከ'ቶ' ሳታወቅ የኩታ እዳይቱ ተስገብግቦ ይነጉዳል ሁሉን ጠርጎ ሊወስድ ክሩ ላይበጠስ። እዲጠነክር ሳይፈቅድ ጨለማው እንዲህ ያልፋል… የመንገድ መጀመሪያ መቋጫው እንዳይሆን!! የወሰደ መንገድ መመለሻ እንዲሆን!! ቁጭ ብየ እመኛለሁ በሰለለ አንደበት በደከመ ገላ፣ ብርድ በመታው ልብ በለባሽ ነጠላ!? ዘመኑ እንዲህ ያልፋል… ነሐሴ01/2012 ዓ.ም ✍Aman😑 YTZ @aman116🖤 @kinchebchabi @kinchebchabi
Mostrar todo...
🖤 24
👎 7
Watch "ብራና ( BIRANA)" on YouTube https://www.youtube.com/channel/UCgIPQrC6h-e2c7LCDHEu0jg
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY ግድቡ የኔ ያንተ ያንቺ የሁላችንም ነው!!!፡፡ 🇲🇱🇲🇱🇲🇱 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ #ድምፃችንለግድባችን #ግድቡየኔነው! #ግድቡየኛነው! #ItsMyDam #OneVoiceForOurDam #CongratulationsEthiopia
Mostrar todo...
🇪🇹 35
እንድታነቡት ጋበዝኩዋችሁ
Mostrar todo...
አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ
Mostrar todo...
አትክልትና ፍራፍሬዎች
የታሸጉ ምግቦች
የንፅሕና መጠበቂያዎች
ሙሉ የቤት አስቤዛ ጥቅል
ቅዳሜ ገበያ ድረ-ገፅ ለመጎብኘት
አትክልትና ፍራፍሬዎች
የታሸጉ ምግቦች
የንፅሕና መጠበቂያዎች
ሙሉ የቤት አስቤዛ ጥቅል
ቅዳሜ ገበያ ድረ-ገፅ ለመጎብኘት
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN የሳምንቱ የመጀሪያ ቀን የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ለብዙዎቻችን ከዕረፍት ማግስት በመሆኑ የረሳናቸው ጉዳዮች የሚታወሱበት ፀጥ ያሉ ስልኮች የሚጮሁበት ያልተቆጩ ሩጫዎች ድቅን የሚሉበት የሰዓት ተቆጣጣሪዎችና ቁጠኞች አለቆች ትውስ የሚሉበት ነው የረሳናቸው ነገሮች መቀስቀስ የሚጀምሩበት ቀን በመሆኑ የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን "ጨለማው ቀን" እንለዋለን በዚህ የመጀመሪያ ቀን ጌታችንን ካልፈለግን ስሜታችን የጨገገ ነው፡፡ አንድ ሰው በየዕለቱ ሲያገኘኝ፡- "እንኳን አደረሰህ" ይለኘ ነበር፡፡ እንዲህ ሲለኘ ከሰሞኑ ያለፈ በዓል እፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን ዓመት ሙሉ "እንኳን አደረሰህ" የሚለኘ እያንዳንዱ ቀን ልዩ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ወጣት እግዚአብሔር አስተማረኘ ፡፡ ለካ ትልቁ በዓል መኖር ነው! 🤔😍 አንድ አባት ሲፀልዩ፡- "ሰላማዊ ቀን እዘዝልን" ይሉ ነበር፡፡ ሰላምንና ቀን የሚያዝዝልን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ሁለቱ የሚገጥሙት በስንት ጊዜ አንዴ ነው፡፡ በፀሎት መንፈስ ግን ሰላማዊ ቀን ይታዘዝልናል፡፡ "ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትዕዛዝህ ይኖራል" መዝ. 118÷91 ይላል፡፡ ቀን እንኳን ሳይቀር የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡ ዕድሜ ስለተጨመረልን በጣም ልናመሰግን የሚገባን ቀን ቢኖር ፣ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ነው፡፡ ከዕረፍት አንስቶ ያሰማራን የኑሮ ጉድለት ነው፡፡ ይህ የኑሮ ጉድለት በሥላሴ ጥበብ የጎደለ ነው ሲሆን እኛን የሚያተጋን በመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ጉድለት ከቤታችን የምንወጣበት ምክንያትና ኃይል ባልኖረን ነበር፡፡ ባይኖር የመሙላት ደስታ ባልኖረን ነበር፡፡ ሲሞላልን ደስ የሚለን ታላቅ ሐሴት ከጉድለት በኀላ የተገኘ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ዘመኑ እየፈጠነ ፣ ወሩ በዓመት ለመተካት እየቸኮለ በመሆኑም ብዙ ጊዜ እናዝንበታለን፡፡ "ቀኑ ይበራል" እንላለን፡፡ ቀኑ አልገፋ ያላቸው ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ለእኛ ቀኑ ሳናስበው የሚሔድ ከሆነ ጣፍጦልናል ማለት ነው፡፡ ያልጣፈጠ ቀን የዓመት ያህል ይረዝማልና፡፡ ሌሊቱ አልፎ ብርሃን ሲመጣ እግዚአብሔር ዛሬን እንድንኖር የዕድሜ ኮንትራቱን አራዝሞልናል አድሶልናል ማለት ነው፡፡ ስለታደሰልን ዕድሜ ልናመሰግን ይገባል፡፡ በህይወት ከሌለን የማንኖረው ለጉድለታችንም ለሙላታችንም ነው፡፡ የሚከብደው የኑሮ ጉዳይ ሳይሆን የሚከብደው እድሜ ነው፡፡ ፍላጎታችን አንድ ባለጠጋ ሊሞላው የሚችል ይሆናል፡፡ ዕድሜ ግን በእርዳታ የምናገኘው ሳይሆን የአምላክ ጸጋ ነው፡፡ ጌታ ሆይ ብዙዎች መኖር እየፈለጉ ይችህን ቀን ሳያዩ አልፈዋል፡፡ ማለፋቸውን በማለዳ ሰምቻለሁ፡፡ እኔ ግን አኑረኘ ብዬ በመፀለዬ ሳይሆን ኑር ብለህ በመፍቀድህ ለዚህ ደርሻለሁና አመሰግንሃለሁ፡፡ ሳምንቱን ከአንተ ጋር እንዳሳልፈው ፣ ያቀድኩት ሳይሆን ያቀድክልኘ እንዲሆን እማፀንሃለሁ፡፡ የማይኖሩበት ቀን እንደተቀበሉ ሰዎች ሳይሆን ካንተ ጋር ዕድሜያቸውን እንደሚያጣፍጡ ሰዎች አድርገኘ፡፡ የምኖር ያልመሰሉኘ የፈተና ቀኖችን አሳልፌያለሁ፡፡ ስታኖረኘ ደግሞ ደስ እንዲለኘ እርዳኘ፡፡ ያለኘን ነገር የማከብረው ከእጄ ሳጣው አይሁንብኘ፡፡ ጌታሆይ! በዚህ ቀን አንተ ቅደም ፣ እኔ በጽድቅ በቅዱስ ፍርሃት ልከተልህ፡፡ ሰላምን በዚህ ቀንና ሳምንት እዘዝልኘ፡፡ ዲ/ን አሸናፊ መኮንን ረቡኒ ከሚለው ትንሽዬ መፅሐፉ ላይ እንዳሰፈረው፡፡ መልካም ቀን መልካም ሳምንት ተመኘሁ አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
ሁሌም አንድ ነገር አስታውስ ★ እግዚአብሔር አምላክህን ቁርስ ፣ ምሳ ፣ እራት ስጠኝ ብለህ ልትለምነው ትችላለህ ግን መክሰስ ስጠኝ ብለህ ልትጠይቀው አይገባም ይሄ ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ ★ ወንድሜ አንድ ነገር አስተውል ገመድ ሶስት ሆኖ ይቋጠራል ጠንካራ ይሆናል ዋናው ሚና ሚጫወተው መሐል ላይ ያለው ገመድ ነው፡፡ አንተም ለቤተሰቦችህ እንደዛ ገመድ ሁሉንም ጠንከር አድርገህ ይዘህ ጠንካራ ለማድረግ መጣር አለብህ፡፡ ★ የምሬን እኮ ነው ምልህ ምን እንዳልኳት ታቃለህ እኛ ሰዎች እኮ አስጠሊታ ፍጡሮች ነን እስኪ ልብስሽን አወላልቂና መስታወት ፊት ቆመሽ እራስሽን እይው የኡነት አስጠሊታዎች ነን አስቢው በዛ ላይ እድሜ ሲጨምር ሁሉም ነገር እንደነበረ አይሆንም በውበት ልትመኪ አይገባም፡፡ አልኳት አጠፋሁ?? ★ እኔ:- የኔ ቆንጆ😍...የኛ ቤት ድመት እኮ ምንም አይልም አትፍሪው እሺ..... ★ እሷ፡- የኛም ቤት ውሻ እኮ ምንም አይልም አትፍራው እሺ (አታምኑኝም የነሱን ቤት ውሻ ሁሉም የሚፈራው ነው) ስለዚህ የኔ የናንተን ድመት መፍራት አያስገርምህ ነው🤔🤔 የ3አመት ህፃን ልጅ ነች እንዲህ ያለችኝ ★ለመኖር ተጨንቄ አላውቅም ለማወቅ ግን እጨነቃለሁ ★ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአዳም ልጆች ሩቅ መስለኃቸው ክፉ መስራታቸው እያለች በተደጋጋሚ ጮክ ብላ ትናገራለች....በግፍ የተነጠቀችውን መልሳ ያገኘች ሴት ጩኸት ነበር፡፡ እውነትም አንተ እሩቅ መስለኸን ስንቱን በድለናል ስንተ ፍትህ አጓድለናል🤦‍♂🤦‍♂ ★ እግዚአብሔር ቅጣቱን ከኛ ቢጀምርስ ኖሮ ካንተ ቢጀምርስ ኖሮ ካንቺስ ቢጀምርስ ኖሮ ★ አንተ እኔን በፍቅር ሳይሆን በእህትነት ምታስብልኝ ይመስለኝ ነበር.........ትላለች ትንሽ ቆይታ ደሞ እንደዛ አብረን አድረን ስንት ነገር አሳልፈን😂😂😂😂 እህትነት አብሮ ማደር🤔🤔😳 ★ዛሬ አላሸክምም እራሴው ነኝ ማመጣው.. ★ ሀብታም ነህ ገንዘብህን ለሌሎችም አካፍል እንጂ ሸክምን ስራ አድርገው ስንት ቤተሰብ ሚያስተዳድሩ አሉ እኮ ያንን አትዘንጋ ወዳጄ.....አለው ★በዚህ በኩል ብትሄድ አይሻልም🤔?? ★ ሰውዬ ዝም ብለህ ተቀመጥ እንጂ እንዴት ወዴት መሄድ እንዳለብኝ አውቃለው ወይስ መሪውን ለሁለት ነው የያዝነው?😏 ★ አስታውስ ንግግርህን በማይረባ ነገር የምትጀምር ከሆነ አዳማጭ ታጣለህ ★ እንዴ አእምሮማ ዝም ብሎ አይወስንም የሆነ ምክንያት ይፈልጋል፡፡ ★ አትሸወድ አይን ሁልጊዜም ፈሪ ነው፡፡ ልብነው ደፋር እጨርሰዋለሁ ብለህ ስትጀምረው በጥቂት ደቂቃዎች ታጠናቅቀዋለህ የዛኔ ደስታህን አስበኸዋል..... ★ ወንድሜ ድሮ እኛ ኢትዮያዊያን እኮ ኑሯችን ባያምር ብንጎሳቆልም ማንም ባይረዳንም ቀብራችን ግን የደመቀ ነበር በኮሮና ምክንያት አሁን ላይ ይህም ነው የቀረብን ታዲያ ይህ አያሳዝንም ትላለህ? 🤔 ቆዩልኘ ሌላጊዜ እንጨምራለን @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሁለተኛውን መጽሐፍ እንዴት አገኛችሁት?? እንደአስተያየታችሁ ከሆነ እንደወደዳችሁት ተረድቻለሁ አመስግኛለሁ😍🙏😊 ፡፡ ረጃጅም ፅሁፎችን ሳትሰለች አርማ እናንተ ጋር እንዲደርስ ለምታደርገው ትዙዬ😍🙏በእናንተ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ፡፡ ሦስተኛውን መጽሐፍ ከመጀመራችን በፊት እረፍት እናደርጋለን፡፡ እስኪ ከዚህም ከዚያም ከአዲስ ሰዎች ጋር ስነጋገር ከጓደኞቼ ጋር ስንከራከር በተለያየ አጋጣሚ ሰዎች ሲመክሩኝ ሌሎቹን ሲያስረዱ ከኔጋርም ባይሆን እርስ በእርስ ሲያወሩ በተለያየ አጋጣሚ መንገድ ላይ ታክሲ ላይ የሰማኋቸውን አባባሎች ወይም ፍልስፍናዎች ማለትም ይቻላል ማስታወሻዬ ላይ(በስልኬ ፣ ደብተር ፣ በጭንቅላቴ አለፍ ሲልም በVOICE RECORD) ካስቀረኋቸው ድንቅ ድንቅ ሃሳቦች ላካፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡ እዮባ😍 በዘፈኑ ሲመክረን "ዝምታ ይከብዳል ከማውራት ማድመጥ ሚዛን ይደፋል" ይለናል ትክክለኛ አባባል ነው፡፡ እኔ መስማት አመሌ ነው፡፡ ሰዎች ሲያወሩ... እኔ፡- ሚስቶች🙆‍♂ ባሎቻቸውን ስልክ📱 ሲያወሩ እንደሚሆኑት ሁሉ ነገሬ ጆሮ👂 ይሆናል ለጨዋታው ድምቀት ነው እንዳትቀየሙኝ🙏😜 እና በማድመጤ እነዚህን ላካፍላችሁ ነው፡፡ በህይወትህ በጥሩ ነገር ካሰብነው እንቅፋትም ጠቃሚ እንደሆነ ከላይ ባለው መጽሐፍ በደንብ ተመክረናል ታዲያ ዝም ብለን እያደመጥን በነፃ መመከር ተገኝቶ😊😃 ነው፡፡ እናደምጣለን የሚጠቅመንን እንይዛለን ህይወታችንን ከትላንት የተሻለ እናደርጋለን የተሻለ ብቻ ሳይሆን የበለጠ፡፡ ሳዳምጥ ምንም አልንቅም ሁሉንም አደምጣለሁ አብዛኞቹ ደግሞ ይህ ነገር ከእነሱ መስማት ለኔ ትልቅ ነገር ይሆንብኛል እደነቃለሁ ከህፃናት እስከ አዛውንቶች የሰበሰብኳቸውን እነሆ ልላችሁ እወዳለሁ....ትወዱታላችሁ 🏃‍♂ ቆዩልኝ🏃‍♂ @jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN እንቅፋት 2 እንቅፋትን ከመንገድ ማስወገድ ለቀጣዩ መንገደኛም መንገዱን ማጽዳት ነው፡፡ ባለ ራዕይ ልንሆን የምንችለው ሰው ሁሉ እንደ እኔ ከውድቀቱ ይማር ከሚል አስተሳሰብ ስንወጣ ነው፡፡ ችግሮች በእኛ አልቀው ለቀጣዩ ትውልድ መልካምነት ማቆየት ስንችል ባለ ራዕይ እንሆናለን። በራዕያችን ውስጥ የሚገጥሙን ብዙ እንቅፋቶች ናቸው፡፡ የገዛ ቤተሰቦቻችን ፍርሃት ይዘሩብናል፡፡ እኛን እየወደዱ ራዕያችንን የሚጠሉ አፍቃሪዎች ይገጥሙናል፡፡ እኛንና ቤተሰቦቻችንን በረሃብ የሚቀጡ ብዙ ክፉ ቀኖች ይደቀኑብናል፡፡ አንዳንዶቹ እንቅፋቶች ልናርቃቸው የምንችላቸው ናቸው፡፡ ተጠንቅቀን የማናልፋቸው እንቅፋቶችም ይገጥሙናል፡፡ በትላንት ስህተቶቻችን ላይ ውሳኔ ካላደረግን መድገማችን የማይቀር ነው፡፡ ስህተትን ትላንት ላይ ብቻ ሳይሆን ነገ ላይ የሚጠብቀን እንቅፋት ነው፡፡ በራዕያችን ላይ የሚገጥመን እንቅፋት የያዝነውን አላማ እንድንጥል የሚያስደነግጠን ነው፡፡ ከዚያም ሲያልፍ ደግሞ ህይወታችንን ለመቅጨት የሚመኝ ነው፡፡ ራዕያችንን አንጥል ስንል ጠላቶቻችን እኛን በማጥፋት ራዕዩን ለማጥፋት ይመኛሉ፡፡ ራዕይ ግን በሰው ሕይወት ላይ ሳይሆን በእውነት ዘላለማዊነት ላይ እንደ ቆመች ባላጋራዎች አያውቁም፡፡ እንቅፋቱ ይበልጥ የሚጎዳው እጆቹን በኪሶቹ ከትቶ የሚሄደውን መንገደኛን ነው፡፡ ሁለቱን እጆቻችን- መቅዘፊያዎች ፣ ስንወድቅ ደግሞ ከአካላችን በፊት የሚዘረጉ ነፍስን አድን ሰራተኞች ናቸው፡፡ በራዕይ ጎዳና ላይ ትዕቢት ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ትዕቢተኛ በራሱ ኃይል ለመግነን ስለሚፈልግ በሚወድቅ ጊዜ ለመነሳት ረዳት አያገኝም፡፡ ኑሯችን እየተደላደለ ቢመጣም ከማህበረሰቡ በጣም የራቀ ኑሮ ዘይቤ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ ተመልሰን ስንወርድ እንዳንረሳው ወይም ገደሉ እንዳይርቅብን ብዙም መራቅ ተገቢ አይደለም፡፡ በሊፍት የወጣ ሰው በዚያው ፍጥነት በሊፍ ሲወርድ እንደምናየው የዚህ ዘመን ትልቅነትም ከፍታውና ዝቅታው ፈጣን ነው፡፡ ስለዚህ በትሕትና ፣ ትላንትን በማይረሳ ማንነት ፣ ባለጠጎችን በማያመልክ ፣ ድሆችን በማያረክስ ስብእና በመመላለስ ከእንቅፋት ይጠብቃል ፤ በእንቅፋት ወድቆ ከመቅረት ይጋርዳል፡፡ ሁሉም እንቅፋቶች አላሳልፍም የሚሉ አይደሉም፡፡ በራዕያችን ላይም ቀላል የሆኑ እንቅፋቶች ንቀን የምናልፋቸው ሐሜትና ነቀፋዎች አሉ፡፡ ባለራዕይ እንዲህ ተባልኩ እያለ መደነቅ የለበትም፡፡ መባሉ ወደ መሆን እንዳይለወጥ መጸለይ አለበት ሰዎች ብዙ የሚሉት ጥቂት ማድረግ ስላልቻሉ መሆኑን መረዳት አለበት፡፡ አንዳንድ እንቅፋቶች ዞረን የምናልፋቸው በእኛ አቅምም ሊነሱ የማይችሉ ናቸው፡፡ የዘመናት እዳዎች የነገስታት አዋጆች የሚፈጥኑ ደምሳሽ ቀኖችን ባለራዕዩ በጸሎት ማሳለፍ አለበት፡፡ ሞቱን በእግዚአብሔር ፈቃድ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ የማይችለውን በማንሳት ወገቡ እንዳይበጠስ ማሰብ አለበት፡፡ የሚበልጠውን ችግር አስቀምጦ በትንንሽ ችግሮች ዘመኑን እንዳያልቅ አቋሙን መገምገም አለበት፡፡ ባለ ራዕይም ሁሉንም እንዲያከናውን ሳይሆን አንዱን እንዲያከናውን ለሚበልጠውም ቅድሚያ እንዲሰጥ ተልኳል፡፡ እንቅፋት ሲገጥመን ማዘን ፣ መቁሰል ፣ መዘግየት ይገጥመናል፡፡ ብዙዎች እንዳዘኑ ቀርተዋል፡፡ ከሰዎች ጋርም ሲካሰሱ ራዕያቸውን ጥለዋል፡፡ የሳቱ ሰዎች አስተዋቸው፡፡ ሳያስቡት የክፋት ደቀመዝሙር ሆነዋል፡፡ የሚያገኙትን ዕድል ሁሉ የሚጠቅሙት ራሳቸውን ለማስተዋወቅና ሌሎችን ለመንቀፍ ነው፡፡ ስለራሳችን ማንነት መናገር ክፉ ባይሆንም ሥራችን ሲናገር ግን የበለጠ ተአማኒ እንሆናለን። የራዕይ አልባዎች ትልቁ ግብ ራዕይ አልባዎችን ማብዛት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ነገር ግን በራዕያችን እኛን የማይፈልጉ ሰዎችን ሳይሆን እኛ የምናስፈልጋቸው ሰዎችን ማየት መቻል አለብን፡፡ ራዕያችንን ከግብ ለማድረስ ስንነሳ የሰዎች ነቀፋ ብቻ ሳይሆን የጤና ፣ የገንዘብ ችግርም ይፈታተነናል፡፡ ሁሉም ከሚሰማና ለሁሉ ለመስጠት ቸር ከሆነው አምላክ እየለመንን ወደፊት መገስገስ ይገባናል፡፡ በራዕያችንም ዝም ብለን ተስፋ የምንቆርጥበት የጠላትን ሹክሹክታ በመስማት ፍሬ አልባ ነኝ የምንልበት የምናየውን እንደ ሕመም የምንቆጥርበት ፣ በደከምንለት ህዝብ የማንረካበት ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ ሥራችንን በመተው ጥፋት እንዲገዛን የምንፈቅድበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ለብዙ ጥረቶቻችን ጥቂት ምስጋና እንኳ ስናጣ ፤ ከጊዜ የተነሳ ራዕያችን ሊረከቡ ሲገባቸው ገና ዳዴ የሚሉትን ስናይ ፤ በገንዘብ እጥረት ራዕዩ ለመቆም ሲዳዳ ረጂዎች የሚባሉ ሃሰተኞችን በደስታ ሲረዱ ለእኛ ግን እጃቸው ሲታሰር ስናይ ፤ ከድሆች እየተቀበልን ባለጠጎችን ስናገለግል ሰዎችን ለማሳተፍ ስንነሳ ሁሉም ሲንሸራተቱብን ፤ ስህተታችንን ሲነቅፉ መልካምነታችንን ግን እንዳላየ ሲያልፉብን ፤ በስራው እየጠፉ ለመብሉ የማያራፍዱ ሲገጥሙን ፤ ለአንድነት ጸሎት ብን የሚሉ ለአድማ ሌሊት ሲሰበሰቡብን ፤ ተስፋ ለመቁረጥ እንቃረባለን ለእነዚህ ክፉዎች መልካምነታችንን ለመጣል ማሰብ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ ሰይጣን የበጎ ነገር ተቃዋሚ ሆኖ ቆሟል፡፡ የእሱ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት ሰዎችም ራዕይን ማሰናከል አይተውም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአገልግሎት ዘመኑ ሰይጣን በአካል የፈተነው አንድ ጊዜ ነው፡፡ በሰዎች ግን ዘመኑን በሙሉ ተፈትኗል፡፡ እርሱ እራሱ እባብና ጊንጡን ትረግጣላቹ በማለት በክፋ ላይ ስልጣን ሲሰጠን ከሰዎች ግን ተጠበቁ በማለት አስጠንቅቆናል፡፡ ሁሉም ነገር ፀጥ ካለ እኛም እየሞትን ነው ማለት ነው፡፡ ከሰራን ግን ጫጫታ አለ፡፡ እነዚህ የህይወት ትግሎች ራዕዩ ግቡን ከመምታቱ በፊት ተሰርተን እንድናልቅ ይረዱናል፡፡ የነጠረ ማንነት የምንቀዳጀው ልንገፋ ባቃተን ነገር ራሳችንን ተሰርተን ስናገኘው ነው፡፡ እግዚአብሔር እንድንገፋው ያስቀመጠው ተራራ ለዘመናት እልፍ የማይል ይሆናል፡፡ ተራራው እንደቀድሞው ቢሆንም እኛ ግን እንደቀድሞ አንሆንም፡፡ ጡንቻችን ይጠነክራል፡፡ ሰውነታችን ይዳብራል፡፡ እግዚአብሔር የለውጥ ስራውን የሚሰራው በሦስት ነገር ነው ★ ችግሩን በመለወጥ ★ እኛ እንድንለወጥ በማድረግ እና ★ ችግሩ እንዳለ እኛን እንዳይጎዳን በማድረግ ነው፡፡ በእነዚህ ሶስት ነገሮች ይሰራል ፣ ጸሎታችንን ይመልሳል፡፡ በመንገዳችን ላይ የሚገጥሙን እንቅፋቶች ምንም ነገር የማይደንቀን ጠንካራ ሰዎች እንድንሆን ያደርጉናል፡፡ እንቅፋቶቹ በራሳቸው አያጠነክሩም ፣ ሰይጣንም እንድንጠነክር ብሎ የሚያመጣው እንቅፋት የለም፡፡ እግዚአብሔር ግን እንቅፋቶችና ፈተናዎቹን እኛን ለማነፅ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ችግሮች እንደቀድሞው ቢሆኑም እኛ ግን እንደቀድሞው አንሆንም፡፡ መኖርን የሚያጣፍጡና ሕይወትን እንግዳ የሚያደርጉ ያልተመለሱ ጥያቄዎችና ሩጫዎችን የሚጠይቁ ራዕዮች መቀመጣቸው ነው፡፡ የህይወት ማሳያው ግራፍ ከፍና ዝቅ የሚል ነው፡፡ ቀጥ ብሎ የሚጓዝ በሕይወት ውስጥ ምንም የለም፡፡ በማንኛውም መንገድ እንደትላንቱ አይደለንም። #ወይ #ከፍ ብለናል ወይም #ወርደናል፡፡ #ቤታችን እንሁን እናንብብ #አስተሳሰባችንን እናስፋ እንቅፋቶች ዝም ብለው አይመጡም ከትላንት ችግሮቻችን ተምረን ዛሬን እናሳምር። ለማንኛውም አስተያየታችሁ @jahABP አድርሱኝ ዲ/ን አሸናፊ መኮንን የመጽሐፉ ርዕስ:- ራዕይ ያለው ትውልድ ሁላችንም ልናነበው የሚገባ መጽሀፍ @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN እንቅፋት እንቅፋት ያለንን አቅም የምንመዝንበት ነው፡፡ በመንገዱም የዛለው እንቅፋቱ በኃይል ሲያዘልለው ዛሬም ጉልበታም ነኘ ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ እያለን የለሁም የሚል እንጉሮሮ እናሰማለን፡፡ ያረጀው መንፈሳችነ እንጂ ጉልበታችን አለመሆኑ የምናውቀው እነቅፋቱ መነቃቃት ሲፈጥርልን ነው፡፡ በሰላም ዘመን የተሟሟቱ ሰዎች በመከራ ዘመን ሲታደሱ እናያለን፡፡ ብዙ ተሻዋሚዎቻችንን እግዚአብሔር ማንቂያ አድርጎ እንደ ሰጠን የምንገነዘበው ቆይቶ ነው፡፡ እንቅፋት ያቆስላል፡፡ እንቅፋቱም ስስ የሆነውን የሰውነታችንን ክፍል የሚጎዳ ስለሆነ አእምሮን የሚለውጥ ህመም አለው፡፡ በራዕያችን የሚገጥመን ጋሬጣም የመጀመሪያ አላማው እርምጃችንን መግታት ነው፡፡ በህይወታችን ውስጥ የማንቋቋመው ስር ነገራችንን በመጉዳት ያዘገየናል፡፡ የአንዳዶች ስስ ነገር ስምና ክብራቸው የሌሎች ሀብትና ንብረታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በራዕያቸው ምክንያት ትዳራቸውን ብቻ ሳይሆን አካላቸውንና ጤንነታቸውንም ያጡ ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ነገር ሕመሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ የራዕይ ሕመም ግን ይነዘንዛል ግን አይገድልም፡፡ ራስ ያሳምማል ግን አያሳብድም፡፡ የቁጣውም ትንታግ ለሌላ በሽታ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ እግዚአብሔር በትካዜውና ባለ ራዕዩ መካከል ጣልቃ ይገባል፡፡ እንቅፋት ያዘገያል፡፡ ልብ ወደ ደረሰበት ቦታ እግር መድረስ ያቅተዋል፡፡ የመነሻውና የመዳረሻውርቀቱ እኩል እየሆነ ለመመለስ ሆነ ወደፊት ለማለት ወመወሰን እስኪያቅት ያዘገያል፡፡ እንቅፋት ማሳመም ብቻ ሳይሆን ማመንታትንም ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የተከናወኑ ራዕዮች ሁሉ ፍፃሜአቸው እንጂ ጅማሬአቸው አወዳሽ አላገኘም፡፡ ጉዞ ያልጀመረ ሰው እንቅፋት የለበትም፡፡ ስለዚህ እንቅፋት የመነሳታችንና እልፍ የማለታችን ምስክር ነው፡፡ በመነሻችንና በመድረሻችን መካከልም ያለተግዳሮት ነው፡፡ በወደብ ማዕበል የለም፡፡ ብርቱ ማዕበል ያለው በመሃሉ ላይነው፡፡ ማዕበል ስላለ ግን የመርከብ አገልግሎት አልቆመም፡፡ ቢዘገዩም ይደርሳሉ፡፡ አንድ ወዳጄን አንድ ሰው እንዴት ነህ? ቢለው"ዔሊ አትፈጥንም ግን አታቋርጥም ፣ የዔሊ ጉዞ ብንጓዝም አለን" አለው፡፡ እንቅፋት ቆም እንድንል ያደርጋል፡፡ እንቅፋት ክፉ ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ቆም እንድንል ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ በስሜት ስንነጉድ ፣ የገዛ ራእያችንን የሚቃወም ምቾት ውስጥ ስንሆን ፣ ነጻነታችን በዝቶ ሌሎችን መጉዳት ሲጀመር ቆም የምንለው በእንቅፋቶች ነው፡፡ የት እንዳለ እንኳን ማወቅ እስኪሳነን በደመ-ነፍስ የምንጓዝ ጊዜ አለ፡፡ እንቅፋት ግን ያለንበትን ቦታ እንድናውቅ ያደርገናል፡፡ እንቅፋት ከእንቅልፍ ያድናል፡፡ በተመቻቹ መንገዶች ላይ በጥበብ የተሰሩ እንቅፋቶች ወይም ማንቂያዎች አሉ፡፡ ከመንገዱ ልስላሴ የተነሳ ሾፌር ሊተኛ ይችላል ፣ እነዚህ ሸካራ መንገዶች ወይም አንስተው የሚያፈርጡ እንቅፋቶች ሾፌሩን ያነቁታል፡፡ ትልልቅ ችግሮች የሚከሰቱት በምቾት ውስጥ ነው፡፡ ምቾት ወደ ሞት ሊወስድ ይችላል፡፡እግዒአብሔር ለሞት እንዳንተኛ ዓይናችንን የሚያበራው በእንቅፋት ነው፡፡ እንቅልፍ መልካም የሚሆነው እየተጓዙ ሳይሆን በአልጋ ላይ ብቻ ነው፡፡ እየተጓዙ መተኛት ወደ ቀለጠው እንቅልፍ ወደ ሞት የሚወስድ ቅርብ መንገድ ነው፡፡ በራዕይ ላይም ማንቀላፋት መደንዘዝ ገዳይ ነው፡፡እንቅፋት ግን ያነቃናል፡፡ የሚተኛመ ሰው የምናነቃው በማችመቹ ነገሮች ነው፡፡ ውሃ በመርጨት ፣ በመነቅነቅ ፣ በመምታት...ነው፡፡ እግዚአብሔርም ከከባድ ችግር በሚያንስ ችግር ያድነናል፡፡ እንቅፋት ለምስጋና ያበቃናል፡፡ ያለፋትን ሰላማዊ ጊዜዎች የምናመሰግነው ፣ እግዚአብሔር ዕረፍትን ሰጥቶን እንደ ነበረ የምንገነዘበው እንቅፋት ሲገጥመን ነው፡፡ የሰላም ጊዜ ቢረዝምም አጭር ነው፡፡ የመከራ ጊዜ አጭር ቢሆንም ከባድ ነው፡፡ የመከራ ዘመን መልሶ መላልሶ ሰላማዊ ዘመን ያሳስባል፡፡ በመከራችን ስንመረር በሰላማችን ጊዜ እንዳላመሰገንን እናስባለን፡፡ በነፃ የተሰጡን ነገሮች ከሄዱ በኀላ በዋጋ እንኳን ለመመለስ እንደሚከብዱ እንገነዘባለን፡፡ እነቅፋት ለምስጋና ያበቃናል፡፡ ያ ምቹ ጊዜ የእኛ እንዳልነበር ይነግረናል፡፡ እንቅፋት የምንከላከለው የመጀመሪያው እንቅፋት እንደሚኖር በመጠበቅ ነው፡፡ ያልተጠበቁ ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን ያልጠበቁት መልካም ነገር ያስደነግጣል፡፡ ለጠበቅነው ነገር ግን የአእምሮ ፣ የአካልና የንብረት ዝግጅት ስለምናደርግ ጉዳቱ ይቀንሳል፡፡ ያልተዘጋጀንበት ነገር ድንጋጤው ብዙ ስለሆነ መፍትሔው ትንሽ ቢሆንም እንኳን ማከናወን ይከብደናል፡፡ ሰው በጉዳት ውስጥ አካሉና ንብረቱን ማጣቱ ትንሽ ጉዳት ነው፡፡ የሚከብደው ጉዳታችን የሚያስከትለው የኅሊና ስብራተት ነው፡፡ ህሊና እንደ አካል በመረቅ የማይጠገን ነው፡፡ የአለም ባህሪይና የሰዎች አካሔድ ፣ የራዕይን እንቅፋት የመንገዱ መሰናክል መጠበቅ ግን ከህሊና ጉዳት ያድናል፡፡ ስለዚህ እንቅፋትን ለመከላከል የመጀመሪያው መፍትሔ እንቅፋት እንዳለ መጠበቅ ነው፡፡ የእንቅፋት ሁለተኛው መፍትሔ እያዩ መሔድ ነው፡፡ አይን ባላየበት እግር ከረገጠ እንቅፋት ፣ ገደልና ወጥመድ ሊገጥመው ይችላል፡፡ የረገጡትን ማየት ሳይሆን የምናየውን መርገጥ ግድ ነው፡፡ ብዙ ረዎች ከረገጡ በኀላ ስለሚያዩ የሚያዩት ስብራታቸውን ፣ ቆሻሻቸውንና ጠላታቸውን ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ የነፃ የትምህርት ዕድልና በዋጋ የሚሰጥ ትምህርት አለ፡፡ የነፃ ትምህርት ዕድሉ እያስተዋሉ መጓዝ ፣ ምክርን ምክርን መጠየቅና መተግበር ፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል መኖር ነው፡፡ ለምንቀቀለው መከራ ኅሊናችን የማይመሰክርልን ከሆነ መከራውን ድርብ ያደርገዋል፡፡ ያመንበትን ነገር መቀበል ግን ደስታን ይሰጠል፡፡ እያየን ማንጓዝ ከሆነ ክብር የሌለው መከራን እንቀበላለን፡፡ መከራ ወዳጅን ያሳጣል፡፡ ባለማስተዋል የሚመጣ መከራ ደግሞ ህሊናንም ያሳጣል፡፡ ጠዎ እንቅፋትን ለመከላከል ሁለተኛው መፍትሔው እያዩ መጓዝ ነው፡፡ እንቅፋት የመታው ሰውሰው ሊያደርገው የሚገባው መከላከያ እንቅፋትን ከመንገድ ማስወገድ ነው፡፡ እንቅፋትን ከመንከዱ ያላስወገደ ለዚህ ሲገርመው ለቀጣይ ቁስለትም ራሱን ያዘጋጃል፡፡ እንቅፋትን ከመንገዳችን ካላስወገድን በመዘናጋት እንደገና ልንመታ እንችላለን፡፡ እንደገና በእንቅፋት ስንመታ ከሚያዝንልን የሚነቅፈን ይበዛል፡፡ የትላንቱን ምት የትላንቱን መውደቅና መዘግየት በማሰብ በጥንቃቄ መጓዝ ይገባናል፡፡ ያለፉ ቀኖችን መልሰን መኖር አንችልም ካለፉት ቀኖች መማር ግን መልሰን መኖር ያህል ካሣ ነው፡፡ የተበላሹ ቀኖችን የምንክሰው በመማር ብቻ ነው፡፡ ይቀጥላል ከሁለተኛ መፅሐፍ ዘጠነኛ ፅሁፍ እንበርታ እንጠንክር ነገ የተሻለን ይሆናልና፡፡ አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...