cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

Join @Rovibook 😎 <|> /\ 👢👢 መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው!! ለማንኛውም ማስታወቂያ ነክ ጉዳዮች @RASNAMRUD ያናግሩን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
29 155
Suscriptores
-3424 horas
-1467 días
-40530 días
Archivo de publicaciones
6) ሁሉንም ልሞክር ይላል ትውልዳችን በአብዛኛው ስንመለከተው ክፉ ፣ ክፉ እንደሆነ የሚያውቀው ሲደርስበት ነው፡፡ እሳት ማቃጠሉን ለመረዳት እሳትን መንካት አያስፈልግም፡፡ እሳትን እንደሚያቃጥል ሲነግረን ተቀብለናል፡፡ የተቃጠሉ ሰዎችንም በማየት እሳትን መጠንቀቅ እንደሚገባን ተምረናል፡፡ ሁሉን በሕይወቴ ላረጋግጥ ፣ ሁሉን ቀምሼ ልወቅ ፣ ሁሉን ሞክሬ ልመለስ ማለት መንገዱን መሔጃ እንጂ መመለሻ የለውም፡፡ ሁሉን በዕድሜያችን ለማረጋገጥ ብንፈልግ ዕድሜያችንም አይበቃም፡፡ ነፃ የትምህርት ዕድልና የክፍያ ትምህርት ልዩነት አላቸው፡፡ ነፃ የትምህርት ዕድልያገኘ ሰው ትምህርቱን በደስታ የሚማር ሲሆን በክፍያ የሚማረው ግን የሚከፍለውን ለማግኘት የሚጥር ነው፡፡ እግዚግብሔር በቃሉ አማካኘነት ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥቶናል፡፡ ትዕዛዙን በመፈፀም በነፃ እንማራለን፡፡ እምቢ ካልን ግን በዋጋ እንማራለን፡፡ በዋጋ መማር በስህተት ፣ በውድቀት መማር በመሆኑ ከባድ ነው፡፡ ትውልዳችን ስናይ ከጥፋት መንገዱ በምክር መቆም አይፈልግም፡፡ ፍሬኑ እንደተበጠሰበት መኪና ሲጋጭ ወይም ሲገለበጥ ለመቆም የሚነጉድ ነው፡፡ በወኅኒ ቤት የሚማቅቁ ፣ በበሽታ የተጎሳቆሉ ብዙ ወጣቶችን ስናይ ምክርን በመናቅ በግትርነት የገብበት ነው፡፡ 7) ደፋር ነው፡፡ ትውልዳችን በአብዛኛውኝ ስንመለከተው ያልሆነውን ለመምሰል ደፋር ነው፡፡ የማያውቀውን አውቃለሁ ለማለት የቴክኖሎጂ እውቀትን እንደሕይወት እውቀት ለመቁጠር ፣ የማይወደውን ሰው እወድሃለሁ ብሎ ለመጥለፍ ፣ ያልገባውን እንደገባው ለመምሰል ፣ የጠራን ነገር ሳይዝ ለአስተማሪነት ለመነሳት ፣ የሚሔድበት ሳይገባው ልምራ ለማለት ፣ በእልፍኘ ሳይሰራ(ሳይታነፅ) በአደባባይ ለመታየት ፣ ትንሹን ብዙ ብሎ ለማውራት ፣ በማጋነን እውቀትን ለማቀጨጭ......ደፋር ነው፡፡ ከእኔ የተሻሉ ሰዎች አሉ ብሎ አይቀበልም፡፡ እነ እገሌ ያርሙኘ ለማለት ፈቃደኛ አይደለም፡፡ በቀዳዳ ያየውን በሰማይ መስክ ላይ እንደታየው አድርጎ ያወራል፡፡ የሞቀ አፍ እንጂ የሞቀ እውነት የለውም፡፡ ትውልዳችን ለመስረቅ ፣ ለመግደል ፣ ራሱን ለማጥፋት ደፋር ነው፡፡ የሰውነቱን ክብር ንቋል፡፡ ሁሉንም አድርጎ ለመደሰት ይፈልጋል፡፡ ያልታየውን እንደታየው አድርጎ የሚተርክ ባለ ራዕይ መሳይ ፣ ያልተሰማውን እንደተሰማው አድርጎ የሚያወራ ሩህሩህ መሳይ ፣ እደርስላችኀለሁ እያለ በተቀመጠበት የሚፎክር ታዳጊ መሳይ ነው፡፡ የሚናገረውን ቃል የማይረዳ ጥሬ ቃል ይዞ የሚሮጥ ፈ ተግዳሮት የሚያደናግር ፣ አፍ እንጂ ጆሮ የሌለው እንደ አመንዝራ በቁንጅናው በርን ሁሉ ለማስከፈት የሚሻ ደፋር ነው፡፡ ቋንቋን እውቀት አድርገው የሚኖሩ ብዙዎችን እየወለድን ነው፡፡ ብዙ አስተዋይ ሰዎች በራቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል፡፡ ሰሚ ያጡ ሊቃውንት እንደ አላዋቂ ዱዳ ሆነዋል፡፡ ትልቅ ድንቁርና አለመማር ሳይሆን መማር አለመፈለግ ነው፡፡ አላዋቂነትን እንደ እውቀት በመቁጠር መንጎማለል ነው፡፡ ለማያፍሩ የሚያፍሩ ፣ ለማይፈሩ የሚፈሩ ብዙ አስተዋዮች ይህንን የሚቸኩል ዘመን ጥግ ይዘው እያዩት ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ችግር ትውልዱ ለዕድገቴ ሌሎች ያስፈልጉኛል ፣ ለዕውቀቴ ስፋት መጠየቅ ያሻኛል ብሎ አለ ማሰቡ ነው፡፡ የዚህ ትውልድ አባላትም የቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ የግዛት አስተዳዳሪዎች እየሆኑ ነውና ችግሩ አሳሳቢ ነው፡፡ 8) በምኞት የሰከረ ነው ትውልዳችን አብዛኛው በምኞት የሰከረ ነው፡፡ ትውልዳችን የምኞት እሳት አንድዶ የሚሞቅ ፣ ትንሽ ፈገግ እያለ ከራሱ ጋር የሚያወጋ ፣ ተግባር የሌለበት ምኞቱ በኩራት የሚናገር ፣ ባልተጨበጠ ነገር ከሰው የሚጣላ ፣ ምኞቱ እየራቀ ሲመጣ ደግሞ ቀቶሎ የሚረበሽ ፣ ተስፋ ለመቁረጥም የሚዳረግ ነው፡፡ ሰው በብዙ ነገሮች ሊያብድ ይችላል፡፡ በቁጣ ያብዳል ፣ በምኞት ያብዳል፡፡ የዕብደት አይነቱ ብዙ ነው፡፡ ሔዋን በምኞት አበደች፡፡ ስለዚህ ያላትን ብዙ ሳይሆን የሌላትን ትንሽ ነገር ነገር መፈለግ ጀመረች፡፡ ውጤቱ ግን የቆጡን አውርድ ብላ እንደሚባለው ተረት ሆነባት፡፡ ትውልዳችን በሰው እጅ ያለው የሚያምረው ፣ የራሱን የማይወድ ፣ በተሰጠው የማይረካ ነው፡፡ ብዙ ትውልዳችን በምኞት አብዷል፡፡ ይህንን ባደርግ ይህ ቢደረግልኘ ፣ ይህ ቢሆንልኘ በሚል መጎምጀዠት ተይዛል፡፡ በሕይወቱ አንድ ትልቅ ነገር ለማድረግ ይመኛል፡፡ በሕይወት ላይ ግን አንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ነገር ማድረግ አይቻልም፡፡ በዙሪያችን የከበበን ትንንሽ ነገር ነው፡፡ በዕየለቱ ትንንሽ ጉዳዮችን ስንፈፅም ትልልቅ ተግባር ይሆናሉ፡፡ መመኘት ክፉ አይደለም፡፡ ምኞት ብቻ ግን ክፉ ነው፡፡ ያልሆኑትን ነገሮች እንደሆኑ አድርጎ መጣላት ከትውልዳችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡ የተዘረጋን ድልድይን መፈለግ ሳይሆን ድልድይን መዘርጋት ፣ ድልድይ መሆን ይገባል፡፡ ትውልዳችን ላይ ግን ያንን አናይም፡፡ 9) ራስ ወዳድ ነው ትውልዳችን በአብዛኛው በዓለም ያለው እርሱ ብቻ ሆኖ የሚታየው ፣ ሁሉንም ሰው ለእርሱ እንዲኖርለት የሚፈልግ ፣ መስዋት መክፈል የማይወድ ፣ እኔን ብቻ ይድላኘ የሚል ራስ ወዳድ ነው፡፡ ራስወዳድነት ዘውድ ጭኖ እየገዛን ነው፡፡ "ከራስ በላይ ንፋስ"እንደሚባለው ለራስ ወዳዶች ከበላያቸው ነፋስ እንጂ እግዚአብሔር መኖሩን የማያምኑ ናቸው፡፡ ራስወዳድ ትውልድ ለክህደት ቅርብ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ለራስ ወዳድነት ፣ በር ዘግቶ ለመኖር ምቹ ሆኗል፡፡ ሁሉም ሰው የራሱ የግል ስልክ ፣ የራሱ የኢሜል አድራሻ ፣ የኣሱ መኖሪያ ቤት...እንዲኖረው የሚጥር ነው፡፡ ስለዚህ ትውልዳችን የእኛ ለሚል ነገር ደስታ የለውም ፣ የእኔ ለሚል ነገር የተሰጠ ነው፡፡ ትውልዳችን ምን አገባኘ ማለት የሚወድ ፣ እኔን ካልነካኘ የፈለገው ነገር ይሁን የሚል ፣ ጓደኛውንም እንደ ባላንጣው የሚያይ ትውልድ ነው፡፡ ራስ ወዳድነት ሌላውን ሰው እንዳናይ ያደርገናል ፣ የጊዜያዊ የፍቅርና የጊዜያዊ ልስላሴ ባለቤቶች ያደርገናል፡፡ ጥቅማችን እስኪሟላ አፍቃሪ መሳይ እንድንሆን ፣ የምንሻውን እስክናገኘ በሰው ፊት ለፊት ያለማቋረጥ እንድንቆም ፣ ጥቅማችን ከተሟላ በኀላ ጀርባችንን እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ ራስ ወዳድነት ይሉኘታን እንኳን የሚያሳጣ ፣ የጥቅም አምልኮ ነው፡፡ ራስ ወዳድ እግዚአብሔር ማምለክና ባለ ራዕይ መሆን አይችልም፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
10) የራሱን አስተሳሰብ መልቀቅ አይፈልግም ትውልዳችን በአብዛኛው ከታሪክ መማር አይፈልግም፡፡ ዛሬ ያለትላንት እንዳልኖረች አይገነዘብም፡፡ ታሪክን ወደኀላ መልሶ ማስተካከል ባይቻልም ከታሪክ ግን መማር ይቻላል፡፡ ውድቀትን ከወደቁት ፣ ተሰጥቷቸው ካላወቁበት ዕድለ ቢሶች መማር ትልቅ ነገር ነው፡፡ አንድ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ሰው በወኅኒ ቤት ሲናገሩ "እኛ ሕያዋን መጽሐፍት ነን ፣ የዛሬው ባለስልጣናት ከእኛ ከእድለቢሶቹ መማር አለባቸው" ብለዋል፡፡ ያለፈው ታሪክ ትለልቅ ትምህርተት አለው፡፡ የታሪክ ዓላማ ለትረካ ፣ ጊዜ ለማሳለፊያ ፣ለተረት መተረቻ ሳይሆን ለትምህርት የሚሆን ነው፡፡ ትውልዳችን ከታሪክ ሊይዘው የሚገባውን መልካም ነገር በዜሮ አባዝቶ ትላንትን ያጣጥላል፡፡ ታሪክ ሲወቅስ እርሱም በታሪክ ፊት መሆኑን ይዘነጋል፡፡ ትውልዳችን አሁንም ትልቁ ችግሩ ፣ ችግሩን መፍታት የሚፈልገው ችግሩ በወለደው አስተሳሰብ ነው፡፡ በአዲስ አስተሳሰብ ውስጥ እስካልሆንን ችግሩን መፍታት አይችልም፡፡ ለዚህ መፍትሔው ቆም ማለት ፣ መፀለይ ፣ ሊቃውንትን መጠየቅና የተቀደሱ ፅሁፎችን ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ትውልዳችን ግን ወይ አይጠይቅም ወይ አይጠየቅም፡፡ ራሱን ዝቅ አድርጎ ሊቃውንትን መጠየቅ ቢጠላ እንኳን ዓይኑን ገልጦ መፅሐፍትን ቢያነብ መልካም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ትውልዳችን ወደማያቀው ግብ እየተጓዘ ፣ መንገድ ሁቹ የሚያደርስ እየመሰለው ወደ ተሰበረ ድልድይ እየነጎደ ነው፡፡ ጠልቆ ባልገባቸው ዘመን ፣ በወለደው ነገር እየተታለሉ ፣ አዲስ ነገር ሁሉ መልካም ነው ብለው የነጎዱ የነቁ ቀን ያዝናሉ፡፡ ስላለፈው እረጅም መንገድ ፣ ስለከንቱ ልፋታቸው ይፀፀታሉ፡፡ ዘመንን ወደሚክሰው አምላክ ካልተመለሱ በቀር ሃዘናቸው ቅጥ የለውም፡፡ ከዓይናማ ሊቃውንትና ከደህና መፅሐፍት የተጣላ ትውልድ ከእውነትና ከእውቀት ብሎም ከእምነት እየራቀ ይመጣል፡፡ የዚያን ጊዜ ሕይወትን አቻችሎ መምራት ያቅተዋል፡፡ የብርሃንና የጨለማን ፈረቃ መታገስ እያቃተው በቶሎ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በአብዛኛው ትውልዳችን ስናየው ምክርን የሚንቅ ፣ በጊዜያዊ ስሜቱ ፣ በገዛ ማስተዋሉ የሚደገፍ ነው፡፡ የራሱን አስተሳሰብ መልቀቅ ስለማይፈልግም ምክርን አይቀበልም፡፡ ከሁለተኛ መፅሐፍ ስምንተኛ ፅሁፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ ምን ተሰማቹ ሃሳቡ እውነት ነው ውሸት?? ደራሲው ትውልዳችንን አልታዘበውም ትላላቹ?? ቤታችን እንሁን አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሌሎች አምስቱን እንቀጥላለን...... እንዲህ ይላል "ትውልዳችን በአብዛኛውኝ ስንመለከተው ያልሆነውን ለመምሰል ደፋር ነው፡፡ የማያውቀውን አውቃለሁ ለማለት የቴክኖሎጂ እውቀትን እንደሕይወት እውቀት ለመቁጠር ፣ የማይወደውን ሰው እወድሃለሁ ብሎ ለመጥለፍ ፣ ያልገባውን እንደገባው ለመምሰል ፣ የጠራን ነገር ሳይዝ ለአስተማሪነት ለመነሳት ፣ የሚሔድበት ሳይገባው ልምራ ለማለት ፣ በእልፍኘ ሳይሰራ(ሳይታነፅ) በአደባባይ ለመታየት ፣ ትንሹን ብዙ ብሎ ለማውራት ፣ በማጋነን እውቀትን ለማቀጨጭ......ደፋር ነው፡፡ እያለ ይቀጥላል......ነገ እንቀጥለዋለን መነበብ አለበት ነገ ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂ አሁንም አስተያየታችሁ አይለየኘ @jahABP @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ያማል """"""" (ከሰለሞን ሳህለ የተወረሰ በዳንኤል ከበደ የታደሰ) ……… እና እንደምነግርሽ ምርመራን ፍራቻ ንጥሻን እንደማፈን ርቀት ሳይጠብቁ ኮሮናን እንደመዝገን በማስክ እጦት ለእስር እንደመጋለጥ ኳራንታይኝ ላለመግባት ከመኪና እንደማምለጥ ሰቆቃ በነገሰባት በዚች ጠፊ ዓለም ከጣና መክሰም በላይ የሚያም ነገር የለም ፌደራል ያስፈራል አዋጁ ያስፈራል በሽታው ያስፈራል እልፍ አዕላፍ ህዝብ ለምርመራ ቀርቧል በሽታው ቀጥሏል ምን ብዬ ልንገርሽ ደግሞ ሌላ ህመም በዚህ በኩል ነግሷል ጣና በእምቦጭ ውኃውን ተወርሷል እና እንደምናቀው እጅን ሳይታጠቡ መዳን ከሌለ ውኃ እየተጠሙ መኖር ከሌለ ነገር ተበላሸ ሞት ተወለደ ፡ የቅጣት በትር ጣና ላይ ወረደ ውኃው ተሟጦ አረሙ ሰፋ ምን ብዬ ልንገርሽ ይኸው ታመናል የሚያየው ሲጠፋ ወጪ ተራማጁ አስመሳይ ሰጋጁ መንግስት ህዝቡ ጆሮውን ደፍኖ ዓይኑን ካዞረ የውኃ ምንጫችን ደርቆ ከቀረ እልፍ አዕላፍ አዕምሮ ተከድኖ ካደረ ለእምቦጭ አረም ተረቶ ከኖረ ፡ ደግሞ ለእምቦጭ ግጥም እናቱን እምቦጭ እናቱን ያ አረም ምን ብዬ ልንገርሽ ያመኛል ጣናዬ ሲታመም ቆይማ ልንገርሽ ድንገት በመንገድ ሳልፍ በጣና ውኃ ኪሱን ያሳበጠ የኃይላንድ ውኃ አስር ብር የሸጠ የቾይዝ ነጋዴ ወደ እኔ አፈጠጠ ውኃ የነካውን ጓንቱን ለብሶ ምን ሁነኃል ይላል ማየቱን ተወርሶ ምን ሁነኃል ይላል እንዴት ዓይን እያለው እኔን ይጠይቃል ጣና ታመመብኝ እምቦጭ ነገሰብኝ አዋጅ ተጣለብኝ እሽ ምን ልበለው ለምንስ ይጠይቀኛ የሚያይ ዓይን እያለው እና እንዳየሁት የጣና ሀይቅ መጠውለግ አመጣ ህዝቡ ገባ ወጣ ኮሮና ቀረት መጣ እምቦጭ ገግሟል … እናቱን ስላልኩት …? ነቅዬ ጥዬ ጉዱን ባሳየሁት እናቱን እናቱን እምቦጭ እናቱን ያ አረም ተይ ዝም አልልም ያመኛል ጣናዬ ሲታመም እናም እኔ ጣናን ስለምወደው እኔ ጣናን ስለምወደው ኮሮናን ተጋፍጬ ነው የምታደገው አለዚያማ ህመሜ ኃያል ነው @Kinchebchabi @kinchebchabi
Mostrar todo...
#በነፃ #mindset የትም ሳትሄዱ በነፃ... በምድር ላይ ብዙ ጥበብ አለ...ብዙ መፅሀፍ እና አዋቂም አለ! ካልመረጥን መጠቀም አንችልም! ብዙ ስለተጠቀምኩበት ላካፍላችሁ እወዳለሁ... ለመነሳት ዝግጁ ናችሁ? # የስታርት ናው(start now) አላማ ህይወትን፡ሊለውጥ የሚችሉ የተለያዩ መማሪያዎችን ማስቀመጥ እና ሰዎችን ወደ ለተሻለ ለውጥ መድረሻ መንገድ መክፈት ነው! ሁላችንም በቀን ውስጥ የተለያዩ የማስታወቂያ እና የመልዕክቶች ውርጅብኝ ሲወርድብን ይውላል ትንሽ ወይም ምንም ጥቅም የሌላቸው ነገር ግን ጊዜያችንን የሚያባክኑ ናቸው! ማህበራዊ ሚዲያ ከሚጠቅሙ እና ለመልካም ነገር ከሚያነሳሱ ሀሳቦች ይልቅ በመርዛማ ሀሳቦች የተሞሉ ሆነዋል! በርግጥ ሁሉም አይደሉም! ቴሌግራም ለተሻለ ነገር የሚያገለግል መድረክ ነው ብዙ ቻናሎች,ግሩፕ እና የመልዕክት ማስተላለፊያዎችን በመያዝ ስኬታማ እና ሰላማዊ ህይወት እንዲኖረን ያደርጋል! ይሄንን ቻናል ስከፍት ሰዎች በማካፍላቸው ጥሩ ፍሬ ያዘሉ መልዕክቶች አዎንታዊ ለውጥ እንደሚያመጡ በማመን በጣም ተነቃቅቼ እና ተደስቼ ነበር። የድምፅ መልዕክቶቹ ደግሞ ዝም ብሎ ማነቃቂያ ብቻ አይደሉም ከራጃጅም ቃለመጠይቆች ውስጥ ጠንካራ መልዕክት የያዙትን ቀድቼ የማስቀምጠው እንጂ:: Join: 👉 @startitupnow
Mostrar todo...
4) ከስህተቱ መማር አይፈልግም የስህተት ማካካሻው ትምህርት ነው፡፡ ካለፈው መማር ያለ መበደል ያህል ነው፡፡ ስህተትን እንዳልተሰራ ማድረግ አይቻልም፡፡ የሰውነት ክብር ግን ከትላንቱ መማር ነው፡፡ ትውልዳችን ግን ከትላንቱ የሚማር አይደለም፡፡ ሰው በሁለት ነገር ሊማር ይችላል፡፡ ከስህተት በፊት በመስማት ይማራል ÷ ከስህተት በኋላ ደግሞ ከውድቀት ይማራል፡፡ ትውልዳችን ግን ከስህተት በፊት ለመማር መስማት አይፈልግም፡፡ የቁም ነገር ሃሳብ ሲነሳበት እየሰለቸ ፣ ለፌዝ ተሰጥቶ ይታያል፡፡ ከውድቀት በኋላ ላለመማሩ ምክንያቱ ቶሎ ተስፋ መቁረጡና እግዚአብሔር የእንደገና አምላክ መሆኑን መዘንጋቱ ነው፡፡ ትውልዱ መስማት አይፈልግም፡፡ አክራሪነትን የወለደው ድንቁርና ነው፡፡ ማወቅ የሚመጣው ከመስማት ነው፡፡ አስተማሪዎቻችንን በመጀመሪያ ሰምተናቸዋል፡፡ ከዚያ የዕውቀት ባለቤት ሆነናል፡፡ የማወቅ መሰረቱ መስማት ነው፡፡ ትውልዳችን ግን ማወቅና መፍትሔ ላይ መድረስ አይፈልግም፡፡ ያለበትን ህይወት እንደመጨረሻ መፍትሔ ተቀብሎታል። ችግሩ በፈጠረው አስተሳሰብ ውስጥ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡ አስተሳሰቡ መለወጥ አለበት፡፡ በትውልዳችን ላይ የምናየው ትልቅ ችግር የራሱን አመለካከት አለመኖር የሌሎችን አመለካከት አለማክበር ነው፡፡ ብዙ የተዋቡ ቃላት በቃሉ ያጠናል ፣ የመናገር አምሮት ስላለበት ይናገራል፡፡ በተግባሩ ግን የተበላሸ ነው፡፡ በተግባር የሌለበት የቃላት ኑሮ በመጨረሻም ብቸኛ ያደርጋል ፣ ተስፋ በመቁረጥም ወደ ሞት ያደርሳል፡፡ ስለዚህ ቃል ብቻ ከመሆን መዳን ያስፈልጋል፡፡ አሳባችንን ለመፈፀም በዋናነት የሚያስፈልገን ባለ አደራነት ወይም የቃል ኪዳን ልብ መሆኑን ማሰብ አለብን፡፡ ትውልዳችን ግን ዋናውን ነገር ገንዘብ ነው ብሎ ያስባል፡፡ ከበደ ሚካኤልም እንዲህ ብለዋል:- "በዓለም አይገኝም ቢፈልጉ ዞሮ፣ መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ" 5) ቦታውን ይለቃል ትውልዳችን ተጓዥ ነው፡፡ አንድ ነገር ያልሆነ ከመሰለው ለዘወትር የማይሆን ነው ብሎ ስለሚያስብ እንደገና የመሞከር ትዕግስት የለውም፡፡ ከጓደኛው ጋር ቢጣላ ሌላ ጓደኛ ይፈልጋል እንጂ ከዚህ ውስጥ የምማረው ትምህርት ፣ ክፉ ከመሰለው ነገር ውስጥ የሚወጣው መልካም ነገር ምንድን ነው? ለማለት ፍላጎትም ብስለትም የለውም፡፡ ተጓዥ በመሆኑም ሃይማኖቱን ሳይቀር ሲለዋውጥ ይኖራል፡፡ የአዲስ ሃይማኖት አድናቂ ሆኖ ዘመኑን በቅልውጥና ይጨርሳል፡፡ ኑሮው ሁሉ ወጥ ቀማሽነት እየሆነ ፣ በሰማበት ጣዱኝ እያለ የሚንከራተት ይሆናል፡፡ መሠረት ስለ ሌለው ሁሉንም ነገር የሚሰማው ቦታውን ለቅቆ ነው፡፡ ስለዝሙት ሲያነብ ማመንዘር ይፈልጋል ፤ ስለ ክህደት ሲያነብ ክዶ ይሰነብታል ፤ የቤተክርስቲያን ጉባኤ ሲሰማ አማኝ ይሆናል፡፡ አድራሻ አጥቶ የሚንከራተት ትውልድ እያስተዋልን ነው፡፡ ይህን የምጽፈው ትውልዱን በሙሉ ለመኮነን አይደለም፡፡ ችግሩን ማወቅ በራሱ ግማሽ መፍትሔ መሆኑን በማመን ነው፡፡ በጦር ሜዳ ቦታን አለመልቀቅ ለድል ያበቃል፡፡ ማፈግፈግ ግዛትን ለጠላት በፍቃድ ራስን አሳልፎ እንደ መስጠት ነው፡፡ ትውልዳችን በብዙ መከራዎች የታጀበ ፣ የጀመረውን ነገር ለመፈጸም እልህ የሚያንሰው ነው፡፡ እቅዱ ስለሚበዛም ውጤቱ ያንሳል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን መንገድ መሪ አለማግኘቱ የበለጠ ጉዳት ነው፡፡ ሌሎች አምስት ይቀራሉ ይቀጥላል ከሁለተኛ መፅሐፍ ሰባተኛ ፅሁፍ እኔ ፣ አንተ ፣ አንቺ ፣ የእኛ ትውልድ በትንሽዬ መጽሐፍ ያስገርማል፡፡ አስተያየታችሁን አድርሱኝ @jahABP ነኝ ይቀጥላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ትውልዳችን፡- 1) መዳረሻውን ያላየ ነው ከትውልዳችን አብዛኛውን የመጨረሻ ግቡ ገንዘብ ማግኘት ወይም ዝነኛ መሆን ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች የተጠሉና የማያስፈልጉም ባይሆኑም ራዕይ ግን አይደሉም፡፡ ትውልዳችን የተሻለ ኑሮ እፈልጋለሁ ይላል ፣ ለእርሱ የተሻለው ቤትና መኪና ነው፡፡ ሰውን ለሚያህል ትልቅ ፍጡር ግን እነዚህ ቁሳቁሶች ግብ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ መንገዳችን ላይ ከምናገኛቸው በረከቶች ውስጥ ይመደባሉ። ግባችን ግን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሰው ከበሬ ለተሻለ ነገር መኖር አለበት፡፡ በሬ ቀኑን በሙሉ ላቡን ጠብ አድርጎ ይሰራል ፤ እኛም እንሰራለን ፤ በሬ ከስራ መልስ ላም አለችው እኛም ትዳር አለን፡፡ በሬ ጥጆች አሉት እኛም ልጆች አሉን፡፡ ከዚህ ያለፈ ነገር ከሌለን እየኖርን ያለነው እንደ በሬ ነው ለማለት ነው፡፡ ስለዚህ ደስተኛ ባንሆን ምን ይደንቃል፡፡ ወደላቀው የኑሮ ደረጃ ፣ እግዚአብሔር ወዳየልን ከፍታ መድረስ አለብን፡፡ እርሱም በራዕይ መገለጥ ነው፡፡ ከሕይወት ጥያቄዎች አንዱ "ወዴት ነው የምሄደው?" የሚል ነው፡፡ ሰው መዳረሻውን ካላወቀ በኑሮው ድፍረት አይሰማውም፡፡ ትውልዳችን ላይ በአብዛኛው የምናየው ለዛሬ መሙላት ብቻ መኖር ፣ ለራስ ብቻም ማሰብ ፣ ሁሉንም ሰው የጥቅሙ ገባር አድርጎ መፈለግን ነው፡፡ ለወገኔ የሚል ስሜቱ እየተሟጠጠ ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ችግር በእግዚአብሔር የለሽ አስተሳሰብ መበከሉ ነው፡፡ ፈጣሪ የለሽ ሥርዓት ከአደባባይ ቢወድቅም ከሰው ልብ ግን አልወደቀም፡፡ በየትምህርት ቤቱ ይሰጡ የነበሩ የግብረ ገብ ትምህርቶች በአዋጅ መከልከላቸው ከዚያ በኋላ ያተረፍነው ትውልድ ብኩን ትውልድ ነው፡፡ ትዕግስት የጎደለው ፣ ራዕይ አልባ ፣ መረን ትውልድ ለማፍራት ተገደናል፡፡ 2) ውለታቢስነት ተቆራኝቶታል አይሁዶች:- "ተቀብሎ የማያመሰግን ከቀማኛ ይቆጠራል" ይላሉ አብዛኛው ትውልዳችን ከእግዚአብሔር ፣ ከቤተሰቡ ፣ ከሀገሩ ከመምህራኖቹ ተቀብሎ ፣ እንደ ጩልፊት ነጥቆ የሚሮጥ እንጂ ለምስጋና የሚመለስ አይደለም፡፡ ውለታቢስነት ተቆራኝቶታል፡፡ ሰዎች እንዲያደርጉለት እንጂ እርሱ ለማንም በጎ ለማድረግ አይሻም፡፡ የሚያስፈልገውን ነገር ያደረጉለትን ሰዎች እንደሞኝ ያያል እንጂ ፍቅራቸውን እንኳን መረዳት አይሆንለትም፡፡ ሁሉንም ሰው ወላጆቹን እንኳን ሳይቀር ለጥቅሙ መሟላት ያፈላልጋል፡፡ ጥቅሙን የሚያሟላለት ከመሰለው ምንም ከመሆን ፣ ከመጣመር ወደኋላ አይልም፡፡ ፍላጎቱ ጣዖት ሆኖበታል፡፡ ጥቅሙን የሚያሟሉለት ከሆነ የራሱን ሰዎች እንኳን ይጠላል፡፡ አንዳንዴም ይተናኮላል፡፡ ያስተማረችውን አገሩን ለማገልገል አይፈልግም፡፡ ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት መቀመጥ እንጂ ተግዳሮትን በፍጹም አይፈልግም፡፡ ቀለል ያለውን በመምረጥ ሲጓዝ ቀለል ያለ መስሎ የሚገኝለት ሱስና ሀጢያት ሆኖ ይቀዘፋል፡፡ ትውልዳችን አብዛኛው ወላጆቹን ለመርዳት ፣ ለማመስገን እንኳን ፈቃደኛ አይደለም፡፡ እራሴን መቻሌ የመርዳት ያህል ነው ብሎ በአፉ ይናገራል፡፡ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ስጦታ ሲያጡ "ራሱን መቻሉ ጥሩ ነው" ብለው የሚጽናኑበትን ቃል እርሱ መኩሪያ አድርጎ መጠቀሙ ያሳፍራል፡፡ ገንዘብ ይበትናል እንጂ ጥሩ እርሻ ላይ አይዘራውም፡፡ ለአዝማሪና ለዝሙት ይበትነዋል፡፡ ደስታው ለራሱ ፣ መከራውን ለወላጆቹ መመደቡ በጣም አሳዛኝ አድርጎታል፡፡ ትውልዳችን ያስተማሩትን መምህራኑን የማያከብር ፣ ለራሱ መስፍን ሆኖ ንጉስ አልባ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ የሌሎች ውለታ መመለስ መቻል የሰውነት ክብር ነው፡፡ ውለታን ማሰብ እንኳ አለመፈለግ ግን ከሰውነት ተራ የሚያወጣ ነው፡፡ በፈረንጆች አገር የእናቶች ቀን የመምህራን ቀን እያሉ ፍቅርን በዓል ያደረጉት በትውልዱ ውለታ ቢስነት ነው፡፡ 3) ራሱን የማያከብር ነው ራስን መሆን ለአእምር ጤንነት ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ ራሱን ያልሆነም እራሱንም ያጣል፡፡ ሌሎች ሊያከብሩት የሚችሉት መጀመሪያ እራሳችንን ስናከብር ነው፡፡ ራቁታችንን በራሳችን ሸማ ብንሸፍነውም እንሰወራለን ፤ በሌሎችም ልብስ ግን ሐፍረታችን አይሸፈንም፡፡ ትውልዳችንን ስናየው ገና በአእምሮ ቅኝ ግዛት የተያዘ ፣ እራሱን የማያከብር ፣ ከራሱ መልካም የሌሎችን ክፉ እንደ መልካም የተቀበለ ትውልድ ነው፡፡ ስለዚህ የረጋ ማንነት የለውም፡፡ ሕይወቱን የሚመራው ዘመናዊነት እንጂ ቋሚ እውነት አይደለም ፤ በሳምንቱን ምርጥ ፊልም ሳምንቱን ይመራዋል፡፡ መረጃዎቹን ለመስማት ሳይሆን ለመሆን ስለሚፈልግ በብዙ ጠፍቷል፡፡ ስለ ሌሎች ሲያወራ ስለ ኳስ ተጫዋቾች ደሞዝ ሲጨቃጨቅ ይውላል፡፡ አንድ አባባል አለ፡- "ትልልቅ ጭንቅላቶች ስለ አሳብ ያወራሉ ፣ መካከለኛ ጭንቅላቶቹ ስለ ሁኔታ ያወራሉ ፣ ትንንሽ ጭንቅላቶች ሁሌም ስለ ሰው ያወራሉ" እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የሰጠው ማንነት አለ፡፡ ያ ማንነት የተለያየ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰማይ ወደምድር ሲመለከት የተለያየ ቀለምን የሚያሳይ ኪነ ጥበብ ነው፡፡ ራሳችንን ስንሆን እግዚአብሔር ሊያይ የፈለገውን ሥዕል እናሟላለን፡፡ ከሌሎች መማር አስፈላጊ ቢሆንም የምንቆምበት መሠረት ግን ያስፈልገናል፡፡ መሠረቱን ለቆ ዕቃ ላውርድ የሚል ዕቃውን ይዞ እንደሚወድቅ እንዲሁ ማንነቱን ጥሎ ከሌሎቹ ልማር የሚል ትምህርቱ ለመቆም አይረዳውም፡፡ ትውልዳችን እንደሌሎቹ መናገር ፣ እንደሌሎቹ መራመድ ፣ እንደሌልቹ መልበስ የሚያረካው የራሱ ነገር በጣም የሚያሳፍረው ነው፡፡ የገንዘብ ባሪያ ሆኖም ገንዘብን ለማግኘት ምንም መሆን የማይቆጨው ፣ ሰውነቱን አርክሶ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስደስተው ነው፡፡ ብዙ ወጣት ሴቶች ስናይ ገንዘብ ካዩ ምንም ዓይነት ክፉ ግብዣን እምቢ የማይሉ ፣ በባዕድ አገር ጭምር አገራቸውን የሚሰድቡ ክብር የለሽ ሆነዋል። ትውልዱን ራሱን አለማክበር ብቻ ሳይሆን ታላላቆቹን በመናቅ ትልቅ የሚሆን ይመስለዋል፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN 😊እንዴት ዋላችሁ😍 "ትውልድን ለመታደግ ሁላችንም ግዴታ አለብን:: ምናልባት ለእኛ መለወጥ የደከመልን ላይኖር ይችል ይሆናል፡፡ ፈጣሪንና እራሳችንን ካወቅን ግን ያልተቀበልነውን ለመስጠት መነሳሳት አለብን፡፡ ሰው ወደመልካም ነገር እንዲመጣ ወደ መጥፎ የሚሔደውን መጀመሪያ ማስቆም አለብን፡፡ ወደ መጥፎ የሚሔደውን ካስቆምን በጥፋት ስፍራ ያለው ይለወጣል፡፡በሸለቆ ውስጥ የወደቀ ሰው አለ፡፡ ወደ ሸለቆው የሚወርደው ሰው ከበዛ ለመውጣት መንገዱ ዝግ ነው፡፡ ስለዚሁም ወደ ጥፋት የሚያወርደው መጀመሪያ መገደብ አለብን፡፡ አሊያ ይህ ትውልድ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ዕጣ ያሳስባል፡፡ ወንጀልም በሕግ ከለላ ያገኛል፡፡ ነውሩም ክብር ሆኖ ይፀድቃል፡፡ ትውልዳችን ስናይ የምናስተውላቸው ችግሮች አሉ፡፡ ችግሮቹን የምንጠቅሰው ያለፈውን መልካም ጊዜ ለማወደስ ዛሬን ለመርገም ሳይሆን የተሻለ ቀን ለማየት ነው፡፡ በዚህ ችግር የሚያልፉ ቆም ብለው እንዲያስቡ ፣ ትውልድን ለመታደግ አሳብ ላላቸው ችግሩን እንዲያዩ ለማድረግ ነው፡፡ ትውልዳችን እነዚህ ችግሮች አሉበት ይላል" ፡- ምን ምን ከሁለተኛ መፅሐፍ ሰባተኛ ፅሁፍ ይቀጥላል፡፡ እኔ ይሔን ፅሁፍ ሳነብ ሁሌም እራሴን ከበኩርኩም እንደተመታ ኩም እላለሁ፡፡ የዚህ ትውልድ አካል ነኘና ችግሮቹ በእኔም ህይወት ላይ አሉ ሁሌም እሩጫዬ ከነዚህ ፍላፃዎች እራሴን ማውጣት ነው፡፡ ከዛ ሌሎችንም ለዛም ነው ላካፍላችሁ የወደድኩት፡፡ ሁላችንም ይህንን ፅሁፍ ማንበብ አለብን ከዛ እራሳችንንም ቆም ብለን መመልከት እራሳችንን መለወጥ ከዛ ሌሎች እንዲለወጡ ምክንያት መሆን፡፡ እንቀጥላለን🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ ቆዩልኘ፡፡ @jahABP ነኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB POHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN የሚመስል ነገር የሰው እድሜን በከንቱ የሚጨርስ ፣ ብልጥ ነኝ ብሎ የሚያስበውን ሳይቀር የሚያታልል ፣ አለሁ አለሁ፦እያለ የማይኖር ፣ መጣሁ መጣሁ እያለ የሚቀር ፣ ዝናብ የሌለው ደመና ፣ የሚያስፈራራ የጉም ጋሬጣ ፣ የማይቆይ የአመዳይ ምንጣፍ ቢኖር የሚመስል ነገር ነው፡፡ ፀሀይን የሚጋርዱ ፣ የነጋዴውን ምንጣፍ የሚያሳጥፉ ፣ ገበያተኛውን የሚበትኑ ፣ የደመቀውን ጭር የሚያደርጉ የረጋውን ግብይት የሚደባልቁ መንገደኛውን በማስቸኮል ልቡን የሚያስደልቁ ፣ ውሃ የተጠማውን የሚያጓጉ ፣ ታይተው የሚጠፉ ፣ ድምፅ አሰምተው የሚሞቱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች አሉ፡፡ ሳይዘንቡ ፀሐይን የሚከልሉ ፣ ላያርሱ ጨለማ የሚያለብሱ ፣ ላይደርሱ የቀረበውን የሚያርቁ ፣ ላይወርዱ የተዘረጋውን የሚያጥፉ ፣ ቀስ ብሎ የሚያርሰውን የሚያስጋልቡ ፣ መጣሁ እያሉ የሚቀሩ ፣ የተጠማውን መቅጃ የማይሞሉ ፣ የተማመነባቸውን የሚያሳፍሩ ፣ ቀጠሮ አስይዘው የማይገኙ ፣ ብዙ በሽተኞችን አሳምመው ፣ ስሜትን አጨፍግገው በመዝነብ ያረኩናል ሲባሉ በሩቁ ታይተው የሚቀሩ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች አሉ፡፡ ከጥቁረታቸው ማስፈራራት የተነሳ ሁሉን ትተው ሲጠብቋቸው የሚቀሩ ፣ ፎክረው ሳይዘንቡ የሚመለሱ ፣ ነፋስ የሚበትናቸው ውስጠ ባዶ ደመናዎች አሉ፡፡ የሚመስል ነገር ዝናብ የሌለው ደመና ነው፡፡ በጋውን ክረምት የሚያስመስሉ ፣ በብርሃን መካከል ገብተው የሚያጨልሙ ፣ ሰላማዊ ግብይትን የሚያደፈርሱ ፣ በግርግራቸው ብዙ ንብረት የሚዘርፉ ፣ ዝናብ የሌላቸው ባለራዕዮች አሉ፡፡ ሲያንዣብቡ በረከት ያዘሉ የሚመስሉ ፣ ሲጠቋቁሩ የሚያረኩ የሚመስሉ ፣ ጥቁረታቸውን ታግሶ ዝናብ ለጠበቀባቸው እልም ብለው የሚቀሩ ባለዕራይዎች አሉ፡፡ ፈጣንነታቸውና ፣ ቡድን አሳዳሚነታቸውን ታግሰን መልካም ነገር ይወጣቸዋል ስንል ተስፋችንን አሳፍፈው የሚመልሱ ዛሬም አሉ፡፡ እንደእባብ እየተለሳለሱ አካልን እየዳሰሱ የሚነድፉ ፣ እያሰከሩ የሚሰርቁ ፣ እያደነዘዙ የሚያራግፉ ፣ የመንጋውን ልብ በቅብ ፍቅር የሚያሸፍቱ ዛሬም አሉ፡፡ ጭር ሲል የማይወዱ ፣ ማስመሰል አገልግሎቴ ፣ መበጥበጥ ራዕዬ ያሉ ፣ ያነደዱት እሳት ሌላው ሲያቃጥል እነርሱ ለመሞቅ የሚሹ ፣ ይህንንም አገልግሎት ብለው የያዙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከባል የሚያፋቱ ውሽሞች ፣ ከበግ ጋር የተሰማሩ ተኩላዎች ፣ በበግ እርምጃ እየተራመዱ ራሳቸውን የሚሰውሩ ፣ ሥጋ በል ሳሉ ለዓላማቸው ሣር ለመብላት የጨከኑ ፣ የእረኛው ልብ ከወደቀላቸው በኋላ ምልመላ የሚጀምሩ ፣ ባለራዕዩ እስኪጠላ በሌሊት ሳይቀር መንጋው የሚጎበኙ ፣ መንጋውን ከእረኛው ከለዩ በኋላ ትተው የሚሰወሩ ፣ ነገር ግን ባለ ራዕይ የሆኑ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ከራዕይ እንቅፋቶች አንዱ የሚመስል ነገር ነው፡፡ የዘመናችን ሰው እውነተኛ ለመሆን አሳብ እንኳን የሌለው ራሱን በሚመስል ነገር አስሮ የሚኖር ነው፡፡ መልካም ተግባርን በጥሩ ንግግር ተክቶ የሚናገር ከእውነተኛም ጋርም ላለመገናኘት ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው፡፡ እውነት ያልሆኑ ፣ ነገር ግን እውነት እንዲመስሉ የተለፋባቸው ሐሰቶች በዝተዋል፡፡ እውነተኝነትን ደረቅነት ፣ አስመሳይነት ዘመናይነት የሆነበት ዘመን ነው፡፡ "እብድ እውነት ይናገራል" እያልን የጤነኝነት መገለጫው ውሸት ሐሰት መሆኑን ያመንበት ይመስላል፡፡ እኛን የማይገልጡ ቃሎችና አለባበሶች ተግባራችንን ለመሸፈን ብናውላቸውም መሸፈኛዎች ሁሉ የመሸፈን አቅም አጥተዋል፡፡ ጊዜውም ከዋሸህ ከተነቃብህ ጨምርበት ፣ ብዙኃን የተስማማበት ሐሰት ከእውነት ይቆጠራል የሚል ነው፡፡ የዚህ የማስመሰል አብዮት አራማጆች ብዙዎቹ የኃይማኖት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በገንዘብና በሆዳቸው ፍቅር የሰከሩ ሲሆኑ መንገድ በማሳት የአገር መሪዎችን እንኳን ሲያስቱ የሚታዩ ናቸው፡፡ ዘወትር በውዳሴ ከንቱና በመወዳደስ ሕይወት ስለሚኖሩ ብርሃኑ ጨለማ ፣ ጨለማውን ብርሃን በማለት ምድሪቱን በብሩቱ ስቃይ ሲወጓት እየተመለከትን ነው፡፡ በሚመስል ነገር መያዝ ብርቱ እስር ቤት ነው፡፡ በሲኦል ውስጥ ከሚገኙ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት ነፍሶች በሚመስል ነገር ተይዘው ዕድሜያቸውን ያባከኑ ብዙዎቹ በሃይማኖት ካባ ተደብቀው እራሳቸውን ያታልላሉ፡፡ በሕሊናቸው ፊት ሳይሆን በሰው ፊት እውነተኛ ለመሆን ይጥራሉ፡፡ ውሸታምን ያደናቀፈ ዕድሜ የለውምና እነዚህ ሰዎች ውሸታቸውን የነካባቸውን እንደ እርግጠኛ ጠላታቸው በማየት ለማጥፋት እንኳን ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌባ ብርሃን አይወድምና የፈጣሪን ቃል ሲሰሙ ይበሳጫሉ፡፡ሰባኪውን ስም ይሰጡታል፡፡ ቅዱስ የሚሏቸውን የራሳቸውን መምህራን ያከማቻሉ፡፡ በአገር ደረጃም አገር እወዳለሁ እያሉ ህዝብን የሚፈጁ ፣ የወደቀ ዜጋ አልፈው እየሔዱ ሰውዬውን የወከለውን ባንዲራ የሚስሙ ብዙ ግለሰቦች አሉ፡፡ በራዕይ ውስጥ በሚመስል ነገር የተያዙ አያሌ ናቸው፡፡ ራዕይ ማለት ቶሎ ቶሎ መራመድ በተወጠረ ስሜት መስራት ትንፋሽ ለመዋጥ ጊዜ ማጣት የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ራዕይን ለመገምገም ፣ ትርፍና ኪሳራቸውን ለመመልከት ጊዜ የላቸውም፡፡ የሚያባክኑት ኃይል እውነተኞቹ ባለ ራዕዮች የሚያወጡት ሃይል በመሆኑ ያለ ዋጋ እንዳይቀሩ ቆም ቢሉ መልካም ነው፡፡ "ለስሟ ማስጠሪያ ቁና ሰፋች" እንደሚባለው አንዷን ተግባር ለዘለዓለም የሚያወሩ ለመጣ ለሔደው ያችኑ የሚደጋግሙ ከመጠን በላይ አጋነው የሚያወሩ ፣ የሰውን ቀልብ መሳብ ሥራቸው ያደረጉ ሰዎች በሚመስል ነገር የተያዙ ናቸው፡፡ በራዕያችን የምንሰራው የሰራን በማይመስለን ጊዜ ነው፡፡ እንደሰራን ካሰብን ቆመናል ማለት ነው፡፡ የሚሰራ በሰራው ረክቶ አይቀመጥም፡፡ የሚሰራ አይረካም፡፡ ሌሎችም ገድላቸው ተፅፎ እንዲኖር ታሪካቸው በወርቅ ቀለም እንዲሰፍር ይፈልጋሉ፡፡ ለዛሬ ትውልድ ጠቃሚ ሳይሆኑ ለሚቀጥለው ትውልድ ታሪክ ለመሆን ይጨነቃሉ፡፡ ብዙ ነገስታት መሳፍንታት ፣ እንኳን ኖረው ሞተው እንኳን ደምቀው እንዲታዩ ብዙ ለፍተዋል፡፡ ዛሬ ግን ከመደነቅ ይወቀሳሉ፡፡ ሁሉም ነገር እኛ እንዳሰብነው አይሆንም፡፡ ዛሬን ጠቃሚ ሰው ሆነን ለመዋል መጣር ብቻ ህሊናን ነፃ ያደርገዋል፡፡ በራዕይ ውስጥ ትዕግስት ከሚመስል ስንፍና ፣ ትጋት ከሚመስል መክነፍ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ እናስተውል..... ★ ትዕቢተኛ የራሱን ትልቅነት የሚቀበለው የሌሎችን ትንሽነት በማመን ነው፡፡ ★የሚያስፈራውን አምላክ ካልፈራን ፈሪ የሆኑትን የሰው ልጆች መፍራታችን አይቀርም፡፡ ★ እግዚአብሔር ከችሎታችን ጋር ሳይሆን ከእሺታችን ጋር ኅብረት አለው፡፡ ★ ምንም እንሁን ባለንበት ሁኔታ እግዚአብሔር ጠቃሚ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ★እኛም ፍፁም አለመሆናችን መረዳት ለፍፁምነት መነሻ ትልቅ መልስ ነው፡፡ ★ የምንችለውን ማድረግ የማንችለውን ወደ ማድረግ አቅም ይመራናል፡፡ ★ ሥር ያልሰደዱ ሁሉ ቢያምሩም በውበታቸው አይቆዩም፡፡ ★ ራዕይ እየገፋ እንጂ እየጠፋ አይመጣም፡፡ ★ ራዕይ እኛ ብናልፍም የሚቀጥል እንጂ ከእኛ ጋር የሚያልፍ አይደለም፡፡ ከሁለተኛ መጽሐፍ ስድስተኛ ፅሁፍ ቤታችን እንሁን እና ንብብ ለመልካም ነገር የፈጠንን እንሁን ለአስተያየታችሁ @jahABP ነኝ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
ቀጣዩን መፅሐፉ ተፅፎ ያለቀው 1998ዓ.ም ነው ለህትመት የበቃው 2003 ዓ.ም ነው፡፡ መፅሐፉን ስንጀምር ተናግሬ ነበር፡፡ ግን የዛሬውን ሰው ፀባይ ቁጭ አድርጎ ያሳየናል የኔ ያንተ ያንቺ የሁላችንንም የሁላችንንም እኔ ሁሌም ሳነበው እራሴን ደጋግሜ ቆም ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል ከነዚህ ነገሮች መላቀቅ አለብንና፡፡ ታግሳቹ አንብቡትና እናወራበታለን በቆንጅዬው VOICE RECORD አድርጎ ለሚልክ የMB እና የስዕል ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡ @JahABP ነኘ
Mostrar todo...
ሰኔና ሰኞ ትክጓሜ አፈታሪክ እና ሁነት 👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1636059476542246&id=100004146275304
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሁለተኛውን መፅሐፍ ነገ እንቀጥላለን አሪፍ እረፍት ያደረግን ይመስለኛል፡፡ ከዚህ መፅሐፍ የቱን ትቼ የቱን እንደምፅፍ ሁላ ነው ግራ የገባኘ የኡነት ብቻ ያስተምራል ያልኩትን እለቃለሁ፡፡ ግን ካለበት ፈልጋቹ አፈላልጋቹ እንድታነቡት ነው ምክሬ እኔ የምፅፈው በጣም ከብዙ ጥቂቱን ነውና፡፡ በመግቢያዬ ላይ እንዳልኩትም ከራሳችሁም አልፎ የሌሎቹንም ሕይወት ትቀይሩበታላችሁ፡፡ ነገ እንቀጥላለን አዲስ JOIN ያላቹ ቤተሰቦቻችን PIN የተደረገውን ፅሁፍ በማንበብ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ በውስጥ መስመር አስተያየታችሁን የምትሰጡኘ ለሁላችሁም አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያክብርልኘ😍🙏😊 አንብባችሁ ሃሳባችሁን ስለምታጋሩኘ በርታ ስለምትሉኘ ደስተኛ ነኘ እኔም የናንተ ድጋፍ ጥንካሬ ይሆነኛልና፡፡ በድጋሚ አመሰግናለሁ 😃😊🙏 @jahABP አስተያየታችሁን አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሃያሏ አሜሪካ አሁን ላይ ብጥብጥ ላይ ነች፡፡ የሰው ልጅ ላይ የማይሰራ ተግባር በሰራ አንድ ነጫጭባ ድብልቅልቋ ወቷል፡፡ አንድ ወዳጄ ጋር ደወልኩለት እና እህሳ እንዴት ናቹ አልኩ ደና ነን ያው ተቃውሞ በርትቷል ብሎ በጣም ብዙ ነገር አጫወተኘ፡፡ የገረመኘን ያስደነቀኘን አንድ ነገር ነገረኘ፡፡ ይገርምኻል ያልተቃጠለ ነገር የለም ማለት ትችላለህ ይሔ አሁን ደግመህ አሜሪኬ ይሆናል እስክትል ድረስ የተቃጠሉ ቦታዎች አሉ ከባለቤቴም ጋር ትላንት ሔደን አይተነዋል ብዙ ነገሮች ተቃጥለዋል ግን አለኘ......ግን ምን ያህል የተማሩ መሆናቸውን ምታውቀው አለኘ... እ....አልኩት ብዙ ህንፃ ሲቃጠል አዳራሾች ሲነዱ አንድ መስታወት በመስታወት ሆኖ የተሰራ ህንፃ ግን አንድም፡ነገር አልሆነም ፍንጥርጣሪ ድንጋይ እንኳን አልነካውም አለኘ፡፡ ገርሞኘ ምን የባለስልጣን ቤት ነው ስለው ወይ ጉድ እነሱን ቢያገኟቸውማ በምን እድላቸው እና ምንድነው?? ትልቅዬ ላይብረሪ ነው አለኘ፡፡ አይገርሙም አለኘ ማርያምን ቀላል ይገርማለሁ አልኩት ጥሩውንም መጥፎውንም ስትሰማ ከሀገርኸ ሁኔታ ጋር ታገናኘዋለህና እኛ ሃገር ያለውን አሰብኩት ስንት ትውልድ ሚቀረፅባቸው ዩኒቨርስቲ ምናቃጥል ድንቅ ህዝቦች እኮ ነን መፅሐፍቶችን ሰብስበን በአደባባይ ምናቃጥል አስቂኘ ሰዎች እኮ ነን ኧረ ስንቱ ወዳጄ፡፡ ብቻ እራሳችንን ቆም ብለን ብናይ እንዴት ጥሩ ነው፡፡ ፖለቲካን ከትምህርት ጋር ባናገናኘ ምናለ፡፡ ኡነት አስገርመውኛል በአስተሳሰብ በጣም ጥለውን ሔደዋል እኛም ይህን አይተን ልንማርበት ይገባል ባይ ነኘ፡፡ በቀጣይ ከዕረፍት መልስ ሁለተኛውን መፅሐፍ ለመጨረስ አንድ ሁለት እንላለን፡፡ ትንሽ ያዘገየሁት ቶሎ እንዳያልቁ ሰግቼ ነው፡፡ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ እናንብብ እናንብብ አሁንም እናንብብ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
ከሰርጋችን አንደበት ቀን አስቀድሜ የሰጠኘን ስራ በሚገባ የሰራሁለት ሽማግሌው ጆቫኒ እንዲህ አለኘ ፡- "ዩጉ! የበጎቹን ጎረኖ ማፅዳት ሊኖርብን ነው፡፡ ንፁህ ኬሻ ታነጥፍበታለህ፡፡ በጎቹም እዚህ ማደር ከተዉ ከዓመት በላይ ሆኗል፡፡ አንተ እና አይዳ ልትገቡበት ከፈለጋችሁ በደንብ አፅዱት፡፡ እኛም እዚ ውስጥ ኖረን ነበር" አለኘ፡፡ ሀሳቡን በደስታ ተቀብዬ የበጎቹ ጉረኖ እያንጎራጎርኹ ሳፀዳ ቀና ስል አናጢው ኮስታንዙዩን በር ላይ ቆሞ አየሁት፡፡ "ያንተ እና የአይዳ ቤት ነው? ይሁና አልጋችሁ የት አለ? እኔ ጋር ትርፍ አልጋ አለና ማፅዳቱን ስትጨርስ መጥተህ ውሰድ፡፡" አለኘ አልጋውን ላመጣ ስሔድ ማሪያ ባለሱቋ ደግሞ ጮኸችብኘ " እናንተ ጅሎች! በኡነት ልትጋቡ ነው? የናንተ የሆነ አንሶላና ትራስ እንኳን ሳይኖራችሁ? አንድ አይናው! ጅል ናችሁ፡፡ ለማንኛውም እስኪ ግን ሙሽራዋ ወደ እኔ ላካት" ላሜ ኢቶሬ ቪያኖ ከበሩ ላይ እንደቆመ ጮኸባት፡፡ " ምን ያህል ወይን ለእንግዶቹ እንደሚያስቀምጥ ጠይቂው፡፡ ሰዎች እንዴት እንዲህ ያለ አግባብ ግዴለሽ ይሆናሉ?" የሽማግሌው ዓይን እንባ አቀረረ፡፡ ከጭንቅላቱ ዘንበል ብሎ ፈገግ አለ፡፡ "ኦ ሲኞሬ!!" አለ በፈገግታ እጆቹን እያሻሸ፡፡ በሠርጋችኝ ማግስት የፈለግነው ሁሉም ነገር ነበረን፡፡ ሳህኖች ፣ የጠረቤዛ ልብሶችና ሌሎች ቁሳቁሶች ነበሩን፡፡እውነት እላችኀለሁ አይዳ ተፍነከነከች፡፡ አለቀሰችም፡፡ እኔም ሳቅሁ፡፡ የሰፈራችን ሰዎች በሙሉ ሳቁ በሠርግ እለት ማልቀስ ደግ ስላይደለ፡፡ ሲኞሬ! ሰዎችን የራስ አድርጎ የማሰብ መብት መኖሩ እጅግ መልካም ነገር ነው፡፡ የሌላ ሰው ህይወት ቀልድ ፣ ደስታው መሳለቂያው እንዳልሆነ የሚረዱ ሰዎችን መልካም ግንኙነት መፍጠር ጥሩ ነው፡፡ እናም ምን አይነት ሰርግ መሰላችሁ? አቤት እንዴት ያለ እለት ነበር፡፡ የሰፈራችን ሰው በሙሉ ተገኘቷል፡፡ ሁሉም ሰው ወደ ጎረኖዋ ሲመጣ ወዲያው ወደ ሞቀ፡ጎጆነት ተቀየረች፡፡ ሁሉ በእጃችን ሁሉ በደጃችን፡፡ ወይን ፣ ፍራፍሬ ፣፡ሥጋ ፣ ዳቦ....ሁሉም ሰው ተመግቧል፡፡ ሁሉም ተደስቷል፡፡ ሲኞሬ! ለሰዎች ደግ ከመስራት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም፡፡ እመኑኘ! ከዚህ በላይ መልካም ነገር የለም፡፡ በሠርጋችን ላይ ቄሱ መጥተዋል ማለፊያ ንግግርም አደረጉ፡፡ "እዚህ" አሉ፡፡ "እዚህ ለሁላችንም ሲባክኑ የኖሩ ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ እናንተም በተራችሁ ይችህን እለት በልዩ ቀን ለማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኀል ይህ ደግሞ መሆን ያለበት ነው ለእናንተ ብቡ ሰርተዋልና፡፡ እና ሥራ ከመዳብና የብር ሳንቲሞች የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ ስለስራው ከምታገኙት ምንዳ በላይ ስራ ጠቃሚ ነው፡፡ ገንዘብ ጤዛ ነው ይጠፋል ÷ ስራ ግን ዘላቂ ነው፡፡ እኚህ ሰዎች ልበቅንና ድሆች ናቸው፡፡ ኑሮአቸው በመከራ የተውተበተበ ቢሆንም ፣ አማረው ግን አያማሩም፡፡ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ ደግሞ ትረዱአቸዋላችሁ ወርቅ እጆችና ቅን ልብ አላቸውና" ብለው ቄሱ ብዙ አስደሳች ንግግር ለእኔ ፣ ለአይዳ እና ለሰፈሩ ሰው በሙላ አደረጉ፡፡ ሽማግሌው በታደሰ ዓይኖቹ መልሶ ቃኘን እና ሲኞሬ! ስለ ሰዎች ጥቂት ነገርኳችሁ ÷ ጥሩ ነው አይደል? ፀሃፊ:- ማክሲም ጎርኪይ ትርጉም:- መኩሪያ መካሻ ቁም ነገር መፅሔት ቅጽ 15 ቁጥር 301 ሰኔ 2009 ዓ.ም እኔም እንዲህ አልኩኘ "ልብ ይበቃል መቆም ለቃል ቤት ይሞቃል በቃል" እዮባ መልካም እንሁን መልካምነት መልሶ ይከፍላልና ለአስተያየታችሁ @jahABP @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ሀሳብ አለኝ ብዙ ጊዜ ሴቶችን እንዳትደፈሩ እንዲህ አድርጉ በማለት እንመክራለን፡፡ አለባበስሽን አስተካክይ: አጭር ቀሚስ ፡ ሰውነት የሚያሳይ፡ የሚያማልል ልብስ አትልበሺ፡፡ አጉል ወጣ ወጣ አትበይ፡፡ ቆጠብ በይ፡፡ ራስሽን አይን ወስጥ አትክተቺ፡፡ መጠጥ አትጠጪ፡፡ ከ ብዙ ወንዶች ጋር አትውጪ፡፡ አታምሺ፡፡ በምሽት ብቻሽን ስትሄጂ አቋራጭ መንገድ አትምረጪ፡፡ የማታውቂውን ወንድ ቤትሽ አታስገቢ፡፡ የማታውቂው ወንድ ቤት አንቺም አትግቢ፡፡ በ ምሽት ብቻሽን ስትሄጂ እራስሽን መከላከያ መሳሪያ ያዢ፡፡ የመዝናኛ ቦታዎች ብቻሽን አትሂጂ፡፡ የሚሸኝሽ እና የሚጠብቅሽ ወንድ አዘጋጂ፡፡ ግን ይሄ ሁላ ነገር ሴቶችን ከ መደፈር አይታደግም፡፡ ምክንያቱም መደፈር ሁሌም የደፋሪዉ እንጂ የተደፋሪዋ ጥፋት ሆኖ አያውቅም፡፡ስለዚህ ሴቶችን እንዳትደፈሩ ብሎ ከመምከር የድርጊቱን ፈፃሚ ወንዶችን አተድፈሩ ብሎ ማስተማር አይቀልም? ሴቶች የሚደፈሩት ቀሚሳቸው ስላጠረ ወይ ስለረዘመ አይደለም ፡፡ አንገታቸውን ደፍተው ወይ አቅንተው ሰለሄዱ አይደለም፡፡ ከቤት ስለወጡ ወይ ቤት ስለተቀመጡ አይደለም፡፡ ስለጠጡ ወይ ስላልጠጡ አይደለም፡፡ የማያውቁት ሰዉ ቤት ሰለሄዱ ወይም የማያዉቁትን ሰዉ ቤታቸዉ ስላስገቡ አይደለም ፡፡ በምሽት ብቻቸውን ስለሄዱ ወይ ደሞ አቋራጭ መንገድ ስለተጠቀሙ አይደለም ፡፡ ሴቶች የሚደፈሩት በነዚህ ምክንያቶች አይደለም፡፡ ሴቶች የሚደፈሩት ደፋሪ ወንዶች ስላሉ ነው፡፡ ደፋሪ ወንዶች አስካሉ ሴቶች ሁሌም ይደፈራሉ ፡፡ ይህን ማስቆም የምንችለው ወንዶችን ስለድርጊቱ አስከፊነት አስነዋሪነት አስፀያፊነት አንዲሁም ከባድ ወንጀልነት ስናሰተምር ነው ፡፡ ወንዶችን ከልጅነታቸው ጀምሮ ከቤተሰብ ከጎረቤት ከዛም ከፍ ሲሉ በትምህርት ቤት በሀይማኖት ተቋማት ስለድርጊቱ እንዲገነዘቡ ማድረግ፡፡ በተጨማሪም የወንጀለኛ መቅጫችን የእውነት ማስተማሪያ መሆን የሚችል ቅጣት መበየን ሲችል ነው ይህን ቅዠት ማቆም የምንችለው ፡፡ በተጨማሪም ደፋሪ ወንድ ሲባል አንደምናስበው አሳቻ ሰዓት ጠብቆ ጨለማ ውስጥ ተደብቆ የሚጠብቀን ማንነቱን የማናውቀው ወንድ ብቻ አይደለም ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መደፈር የሚፈፀመው የቅርብ በምንላቸዉ በምናውቃቸው በምናምናቸው ሰወች ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተሰቦቻችን ጓደኞቻችን ዘመዶቻችን ጎረቤቶቻችን መምህራኖቻችን የስራ ባልደረቦቻችን ባሎቻችን ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ ሴቶችን አንዳትደፈሩ ተጠንቀቁ ብሎ ከመምከር ወንዶችን አትድፈሩ ብሎ ማስተማር የተሻለ ለዉጠ የሚያመጣ ይመስለኛል፡፡ #ወንዶች_አትድፈሩ!!! HERE'S A THOUGHT INSTEAD OF TEACHING WOMEN NOT TO DRESS PROVOCATIVELY, BE PASSIVE, TO TAKE UP LESS SPACE, DON'T BE DOMINANT, WATCH WHERE YOU WALK, WATCH WHEN YOU WALK, DON'T LEAD MEN ON, DON'T WALK ALONE, DON'T DRINK TOO MUCH, DON'T INVITE ATTENTION, DON'T SLEEP WITH TOO MANY PEOPLE, BE CAREFUL WHO YOU TALK TO,TAKE SELF DEFENSE CLASSES, NEVER WALK HOME ALONE, DON'T WEAR YOUR HAIR IN A PONYTAIL, IT'S EASIER FOR AN ATTACKER TO GRAB, DON'T WALK THROUGH THE SHORT CUT, CARRY YOUR KEYS BETWEEN YOUR FINGERS, DON'T LEAVE YOUR OPEN DRINK ANYWHERE, DON'T GO INTO PUBLIC BATHROOMS ALONE, GET A GUARD DOG, DON'T LET STRANGERS IN TO YOUR HOME, DON'T LET YOURSELF IN IN A STRANGERS HOUSE, DON'T GO OUT AT NIGHT, CARRY A MOBILE PHONE WITH YOU ALWAYS. TEACH MEN NOT TO RAPE!!! RAPE IS NEVER THE FAULT OF THE SURVIVER END RAPE CULTURE!!! @kinchebchabi @kinchebchabi
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሽማግሌው ከሮምና ከጄኖዋ መሃል የሚገኘ አነስተኛ የባቡር ጣቢያ ነው፡፡ አስተናጋጁ የነበርንበት ክፍል በረገደ፡፡ አንድ ዓይናና ድንክዬው ሽማግሌ የመሸከም ያህል ደግፎ አስገባው፡፡ ቆቅ፡የሆነ ሽማግሌ ነው፡፡ የረዳውን ሰው ለማመስገን እጆቹን አውለበለበ ÷ ዘባተሎ ባርኔጣውን አንስቶ እጅ እየነሳ ትህትናን በሚረጭ ጥልቅ ዓይኑ ተሳፋሪውን ቃኘ፡፡ " ትፈቅዱኛላችሁ?! ሲል በእፎይታ እጆቹን ጉልበቶቹን ላይ አሳረፈ፡፡ ጥርስ የለሽ ፈገግታውን ረጨ፡፡ "ሩቅ ነው የሚሔዱት አባቴ?" ሲል ጓደኛዬ ጠየቃቸው፡፡ "አይደለም ÷ ሶስተኛው ጣቢያ ላይ ነው የምወርደው፡፡ ቀጥሎም ቆይት ታሪኩን ይተረትረው ጀመር - ንፋስ እንደሚያወዛውዘው ቅርንጫፍ በቆመበት እየተወዛወዘ፡፡ እኔ ሊንጎሪያዊ ነኘ፡፡ እኛ ሊንጎሪያዊያን ጠንካሮች ነን፡፡ ለምሳሌ ያህል እኔ ውሰደኘ፡፡ 13 ወንዶችና አራት ሴቶች ልጆች አሉኘ፡፡ ምን ያህል የልጅ ልጆች እንዳሉኘ ግን በትክክል አላውቅም፡፡ ዛሬ የሚያገባው ሁለተኛ ልጄ ነው ÷ ሽማግሌው ደግ አይደል ታዲያ?" በኩራት በአንድ አይኑን እየቃኘን "ለንጉሴና ለአገሬ ምን ያህል ሰው እንዳበረከትኩ አስቡ፡፡" "ደግሞም ዓይኔ እንዴት ሊጠፋ እንደቻለ ልንገራችሁ?" ከብዙ ዓመታት በፊት ነው ÷ ገና ህፃን የነበርኩ ብሆንም አባቴን መርዳት ጀምሬ ነበር፡፡ መሬቱ ጠንካራና ድንጋያማ ስለነበር ከባድ ስራን ይጠይቃል፡፡ ታዲያ አባቴ ድንጋዩን ሲፈነቃቅል ፍንጣሬ አይኔ ውስጥ ገባች፡፡ ያኔ ህመም የተሰማኘ ስለመሆኑም አላስታውስም፡፡ መድሃኒት አደረጉልኘ ግና አልፈየደልኘም ይኸው እስከዛሬ አይኔ ታውራለች፡፡ የተጨማደዱ ጉንጮቹን እያሻሸ ፈገግታውን ረጨብንና ትረካውን መልሶ ቀጠለ፡፡ "ያኔ እንደዛሬው ዘመን ብዙ ሃኪሞች ስላልነበሩ ሰዎች በየዋህነት ይኖራሉ፡፡ አዎን! በሞኘነት፡፡ ይሁና ከዛሬ ዘመን ሰዎች ይልቅ ደግ ነበሩ፡፡ "የእኔን ያህል እድሜ የኖረ ሰው ስለሰዎች የሚያስበው መናገር ይቻላል፡፡ አይመስላችሁም ጎበዝ እንግዲያውስ ስለሰዎች ላውጋችሁ፡፡ ልጆቼ አባቴ የሞተው የ13 አመት ልጅ ሆኜ ነው፡፡ የስራ ነገር ከተነሳ ግን ሰርቼ የማልደክም ጠንካራ ሰው ነበርኩ፡፡ ከአባቴ የወረስኩት ይህኑኑ ብቻ ነው፡፡ ቤታችንና የእርሻ መሬታችን የተሸጠው እዳ ለመክፈል ሲባል ነበር፡፡ ስለዚህ በአንድ ዓይኔና በሁለት እጆቼ ስራ በተገኘበት እየማሰንኩ ነው የኖርኩት፡፡ ህይወት ፈተና ነበር፡፡ ነገር ግን ወጣትነት ለችግር አይበገርም አይደለም እንዴ?! "አስራ ዘጠኘ ዓመት ሲሞላኘ አንዲት ጉብል አፈቀርኩ፡፡ ልክ እንደኔው መናጢ ድሃ ነበረች፡፡ ከደከሙ አሮጊት እናትዋ ጋር እየኖረች እንደእኔው የተገኘውን ስራ ሁሉ ትሰራ ነበር ቁንጅናዋ እስከዚህም ቢሆንም ደግና ብሩህ አእምሮ ነበራት የድምፇ ነገርማ አይነሳ! አቤት እንዴት ታንጎራጉር ነበር? መቼም ከዘፋኘ አትተናነስም፡፡ እኔም እኮ ጥሩ ድምፅ ነበረኘ፡፡ እንጋባ! አልኳት በዱብ እዳ፡፡ "ይህ ጅልነት ነው አንድ ዓይናው አለችኘ በንዴት" አንተም እኔም መናጢ ድሆች ነን ፣ እንዴት ነው የምንኖረው? አባባልዋ ትክክል ነው፡፡ ሁለታችንም ምንመም አልነበረንም፡፡ ይሁና ወጣት ፍቅረኛሞች ምን ይፈልጋሉ? የፍቅር ምሱ ምን እንደሆነ እናንተም ራሳችሁ ታውቃላችሁና በእግር በጥፍሯ ገብቼ አገባኀት፡፡ " መልካም ምንአልባትም አንተ ልክ ነህ" አለችኘ ፍቅረኛዬ ኢዳ በመጨረሻም፡፡ ተለያይተን እንዲህ መኖር ከቻልን አንድ ላይ ደግም እንዴት የተሻለ አንኖርም?! ብዬአት ተያይዘን ወደቤተክርስቲያን ሔድን፡፡ "ይሕስ እብደት ነው አለ ቄሱ፡፡...ምስኪኖች ራስ ሳይጠና ጉተና' የሰፈሩም ወጣቶች ተሳለቁብን፡፡ በእድሜ የገፉት ደግሞ አስሟጠጡብን፡፡ እኛ ግን ወይፍንክች! ወጣት ሲባል ግትርና የራሴን መንገድ ቀያሽ ነውና የሰርጉ ቀን ደረሰ፡፡ የሰርጉ እለት የት እንደምናድር እንኳን አናውቅም ነበር፡፡ ሜዳ ላይስ ብናድር ለምን አናድርም፡፡ መሬት አልጋችን ሰማይ ብርድልብሳችን እንዲሆን ወሰንን፡፡ በረዥሙ ዘመኔ ያተረፍኩት ልዩ ታሪክ እነግራችኀለሁ እባካችሁ በትዕግስት ጆሮአችሁን አውሱኘ፡፡ ይቀጥላል🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ትላንት ከውጭ ወደቤት ስገባ አልጋዬ ላይ የሆነ መፅሔት አገኘሁ፡፡ ማን አምጥቶልኘ ነው ስል ያንተ እኮ ነው አሉኘ መፅሔቶችን ስለምሰበስብ አይ የኔ እንኳን አይደለም ካሱ ያመጣልን ይሆናል አልኩኘ፡፡ ካሱ ምጣድና ስቶቩ የሚሰሬ የድሮ አራዳ ነው ቤት ሲመጣ ይደንስልናል🕺🕺 ይዘፍንልናል🎤🎷🎺🎸🎹...የባህል ህክምናንም ይሞክራል ብዙ ነገሮችንም ያወራናል ከትንሹ ወንድሜ ጋር ደግሞ በጣም ይዋደዳሉ፡፡ እና አንባቢ ነው ሲመጣ የድሮ መፅሐፍቶችና መፅሔቶችን ጋዜጦችን ይዞልን ይመጣል፡፡ ደሳስ ሚሉ ፅሁፎች ያሉባቸው እና አያሌ እውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ እኛም እያነበብን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ይህን መፅሔትም እሱ እንዳመጣው ጥርጥር የለኘም፡፡ ምክንያቱም የኔ ዕቃዎች ያሉት እቃ ማስቀምጥበት ቦርሳ ውስጥ ነው ካለኔ ማንም አይነካም እማ እራሱ ብትሆን፡፡ እሱ ነው ያመጣሁ ያልኩበት ምክንያት መፅሔቱ የሰኔ 2009 ዓ.ም ህትመት ቁምነገር የተሰኘ መፅሔት ነው፡፡ ጉስቁል ብሏል አነሳሁት የመፅሔት ገፅ ከዚህ በፊት ቆጥሬ ባላቅም ገፆቹን ቆጠርኳቸው 6 ገፅ ነው ያለው እስከ ስምንት በተራው ይሔድና በመሐል ብዙ ገፆች ጎድለውት ገፅ 29 ድጋሚ ይጀምርና ገፅ32 ላይ ያልቃል፡፡ አነሳሁት የገለጥኩት ገፅ ላይ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደሰ ስለተባሉ የሃገራችን ፕሮፌሰር የህይወት ተሞክሮ ያስቃኛል ግን አይጨርሰውም ተበሳጨው፡፡ ጥቂት ቢሊኒየሮችና ብዙ ምንዱባኖች የሚል ርዕስ አለ ግን ፅሁፉ ተቆርጧል🤦‍♂፡፡ ቀጠልኩ የስፔናዊው የፈርናዶ ቶሬዝ ከፍታ እና ዝቅታ ይላል፡፡ ገርበብ አደረኩት ለካ ቶሬዝ ፊልም ሰርቷል 😂😂😂 ዛሬ ነው ማቀው🤦‍♂👊👊 ገለጥ ሳደርግ ለባለትዳሮች ይልና ወሲብ አልባ ትዳር ይላል ይሔን አንብቤ ቻናል ላይ ማካፈል አለብኘ አልኩና ንባቤን ገታሁ ልብስ ቀያይሬ መፅሔቱን ይዤው ወጣሁ ብና ከጠጣሁ በኀላ ወደ ንባቤ ተመለስኩ ስላነበብኩ አዲስ ነገር አውቄያለሁ ፅሁፏ አጭር ነች መፅሐፍ አለብኘ የለብኘም እያልኩ ወደሌላ ገፅ ተሸጋገርኩ ወደ መጨረሻው ገፅ በትልቁ "ሽማግሌው" ይላል ማክሲም ጎርኪይ ፅፎት መኩሪያ መካሻ ተርጉሞታል ይላል... አነበብኩት በጣም ደስ ይላል በጣም የላይኛውን ፅሁፍ ልዝለላችሁ እና ይሔን ላካፍላቹ ወደድኩ ባለትዳሮች እንዳትቀየሙኘ ይሔም ፅሁፍ ስታነቡም ይቅርታ እንደምታደርጉልኘ አልጠራጠርም ልታገቡ ያሰባችሁ እስኪ ይቺን ፅሁፍ ገርበብ አድርጓት ሲንግል የሆናችሁም እራሳችሁን ታዘጋጁበታላችሁ፡፡ ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂ ለአስተያየታችሁ @jahABP ነኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN አንፃር አባቴ ነው፡፡... .....ቀና ብለህ ከግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ፎቶዬን ተመልከት አለኘ፡፡ አባቴ ከእናቴ ጋር ሲጋቡ የተነሳው ፎቶ ነው፡፡ የአባቴ ፀጉር ከብዛቱ ርዝመቱ ጉድ ያሰኛል፡፡ የገረጣ ጠይም ፊት ነው፡፡ መካከለኛ ቁመና ፣ ሥጋ ያልበዛበት አካል ይታያል፡፡ አባቴ ከሰላሳ አመት በፊት የተነሳው ፎቶ፡፡ ፎቶው ላይ ያለው ምስል የአባቴን ዘመን የአለባበስ ስርዓት ያሳያል ፣ ቬል የረዘመ ሱሪ ፣ ኮሌታው የሰፋ ኮት በነጭ ስፖርት ሸሚዝ ይታያል፡፡ አባቴ በእኔ እድሜ እያለ የተነሳው ፎቶ.. "አየህ አይደል? እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ ንፋሱን እጨብጥ ባህሩር እጨልጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ንፋሱም ከእጄ የለም ፣ ባህሩም ሆዴን አልሞላም፡፡ ከንቱ የወጣትነት ምኞት ነበርና፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ ከአባቴ ምክር ይልቅ የራሴን ስሜት የማዳምጥበት ወቅት ነበር፡፡ ከአያትህ መሬትነት ይልቅ የኔን እሳትነት እመካበት ነበር፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ እያለሁ" አለኘ አባቴ፡፡ ፀጉሬን እየፈተልኩ አባቴ የደረሰባትን የዘመን እውነት በልቤ እያሽሟጠጥኩባት እሰማ ጀመር.. "ታሪክ እራሱን ይደግማል ማለት እንግዲህ ይህ ነው፡፡ የምትመካበት አዲስ ነገር ምንድነው? እኔ ያላደረግሁት አንተ የምታደርገው ምን አለ? ተመልከት ፎቶዬን <ፀጉሬ ጎፈሬ ነበር፡፡ የአንተም ፀጉር አፍሮ ነው፡፡ እኔ ለጎፈሬዬ ከኀላ ኪሴ የእንጨት ሚዶ አይለየኘም ነበር፡፡ አንተም እንደኔው ለአፍሮህ ትጨነቃለህ፡፡ አፍሮህ ሲያድግ ደሞ ትገምደዋለህ፡፡ ሲሻህ ደግሞ ትሾርበዋለህ፡፡ይሔ ሁሉ ግን ከእኔ ከአባትህ የተረፈ ነው፡፡ ከኔ ያላገኘኸው ምንም ነገር የለም፡፡ እኔ በጎፈሬዬ የሀገሬን ጠላት ማጥፋቴን ፣ ማንነቴን መጠበቄን መሰከርኩበት፡፡ አንተ ግን በሹሩባህ መጀመሪያ ራስህን ፣ ቀጥሎ ቆነጃጅቶችኝ ጠለፍክበት፡፡ አንተ በፒያሳ እንደምትሆነው ሁሉ እኔም በውቤ በረኃ ዘምቻለሁ፡፡ <ይኼ ሁሉ የአባቴ ምክር ነበር፡፡ አሁንም እጄ ከፀጉሬ ላይ አልተለየም ÷ ሦስቱ ጣቶቼ ፀጉሬ ላይ ይፈትላሉ አባቴም ያወራል፡፡ <ይሄ ሁሉ ግን ጥላ ነው፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ የሚዳሰስ አካል ይመስለኘ ነበር፡፡ አይደለም፡፡ ወጣትነት ፍቹ እንደሌለው ህልም ነው፡፡ ታየዋለህ ፣ እንደ ነፋስ ሽውታም ያመልጥኻል፡፡ ወጣትነት ፊደል ነው፡፡ ፣ ቃል ግን አይደለም፡፡ ልጄ ሆይ ምክሬን ስማ ወጣትነትና ሕሊና ባዶ ናቸው፡፡ ሕሊና ፀፀትን እንጂ እርምትን አይወድም፣ ወጣትነት እና ሕሊና አንድ ናቸው፡፡ ሕሊና ፀፀት እንጂ እርምትን አይወድም ፣ ወጣትነትም እንደዚያው ነው፡፡ ብዙ ምኞትና ብዙ ከንቱነት፡፡" ቀና ብዬ አይኑን አየሁት...ዓይኔን ወደመሬት መለስኩት፡፡ ቢጨርስና ቤቱን ጥዬው ብወጣ ደስታዬ ነበር፡፡ የአባቴ ምክር ወሬውን ቀጠለ... "እስካሁን ከነገርኩህ በላይ የምነግርህ ቢኖር ዕድሜህ በአንተ ላይ ታዛለች እንጂ ፣አንተ በዕድሜህ ላይ መብት የለህም፡፡ እስካሁን የነገርኩህን ሁሉ ልትቀበለኘ የምትችልበትን ስልጣን በራስህ የለህም ወጣት ነህና፡፡ ወጣትነትህ ደግም እርጅናዬን ታስንቅኃለች ፣ እርጅናዬ ደግሞ ያንተን ወጣትነት በቅናት ትንቀዋለች፡፡ ምናልባት፡- ዛሬ አንተ ከእኔ አባትህ የበለጥክበት ጊዜ እንደሚመስልህ ሁሉ አንተ በተራህ በልጅህ የምትበለጥት ጊዜ ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ልጄ ይበልጠኛል ለማለት አትችልም ÷ ልጅህ ከአባቴ እበልጣለሁ ይላል እንጂ፡፡ ያን ጊዜ የልጄን ልጅ ሰባት እጥፍ እወደዋለሁ ÷ የአያቱ ተበቃይ ነውና፡፡ አባቶች የልጆቻቸውን ልጆች የሚወዱበት ምክንያት ለማወቅ ከፈለግህ ፎቶዬን ተመልከተው ÷ አንተ ስወልድ ዕድሜዬ እንዳንተ ነበር፡፡ አንተ በእኔ ዕድሜ ስትሆን እኔ ወደ አያትህ እየሔድኩ ነው፡፡ ሕይወት ታሳሳለች ÷ አባት ስትሆን ደግሞ ልጅህ እያካለለ ሲያሮጣት ታያለህ ያኔ ለልጅህ ጠላቱ ልጁ ነውና የልጅህን ልጅ ትናፍቃለህ፡፡ የልጅህንም ልጅ ከልጅህ ይልቅ ሰባት እጥፍ ትወደዋለህ፡፡ ተበቃይህ ነውና፡፡" ብሎኘ ሽበት የወረረውን ወጉሩ ላይ ባርኔጣውን ጥሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ወጣ፡፡ እኔም አባቴ ከተናገራቸው ብዙ ቁም ነገሮች መካከል ያስገረመችኘና ያስፈገገችኘ እያሰብኩ ወደ ቀጠሮዬ ተነሳሁ...... "አሁን የነገርኩህን ሁሉ ልትቀበለኘ የምትችልበት ስልጣን በራስህ የለህም፡፡ ወጣት ነህና፡፡ ወጣትነትህ ትሰማለች እነንጂ አታስተውልም፡፡ ጉብዝናህ እርጅናዬን ታስንቅኃለች ÷ እርጅናዬ ደግሞ ያንተን ወጣትነት በቅናት ትንቀዋለች፡፡" የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች ከኤፍሬም ስዩም ህዳር 2007 ቤታችንእንሁን ቤተሰቦቻችን የሚሉንን እናዳምጥ @jahABP ነኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
አባትክ/አባትሽ መክሮሽ ያውቃል?? 😂😂ፈገግ ያስብላል አይደል😂👊 እስኪ እንደዚህ ብሎ መክሮኻል/መክሮሻል ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂😜😜 በዚህ ፅሁፍ ተገርሜበታለሁ...... ብዙ ታተርፉበታላችሁ @jahABP ነኘ
Mostrar todo...
ራሱን ወቀሰ "ወደማልኩበት እንዴት ተመለስኩ?" ትላንት እርሜን ስጎርስ ለምን አላፈርኩኘም? ሐፍረቴን ለመግለፅ የማይራራልኘ "የሰው ልጅ ያስባል" የሚል ማፈሪያዬን እንዴት እመካበታሁ? አለማሰብ ባይቻልም ማሰብን መመኪያ ለማድረግ የሰው ልጅ እጅግ ብዙ ይቀረዋል፡፡ ይቺህ ውብ አለም እናስባለን በሚሉ ደናቁርቶች ጠፍታለች፡፡ ረሃብ የሰው ልጆችን የተንኮል ቀመር ነው፡፡ ጦርነት የሰው ልጆች ያለማሰብ ውጤት ነው በሽታ በሰው ልጆች ተቦክቶ ይጋገራል... የዋሆች ይመገቡታል ፈጥነውም ይሞታሉ፡፡ ይህ የሰው ልጅ የማሰብ ውጤት ነው ግን፡፡ ይህ ዓይነት ጭካኔ በእንስሳት አልተደረገም፡፡ ስለዚህ ከሚያስበው፡የሰው ልጅ እንስሳቶች በለጡ፡፡ የተበለጠ ጎበዝ የሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡ ያሸነፈ ተሸናፊ፡፡ ድጋሚ ካዘዘው ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ ፉት አለ ጥቁረቱ ደስ ይላል፡፡... ቡና ባይኖር ዓለም ምን ትመስል ነበር? አለ በውስጡ ራሱ ቡናን ትመስል ነበር፡፡ በቡና ጥቁረት ስር የሃሳባዊነት ብርሃን ተሸሽጓል፡፡ እዚህ ቤት ያለው የቡና ጣዕም የሚወደው አይነት የቡና ጣዕም ነው፡፡ ምላሱ ላይ ያለውን ቡና እያሰበ ቀና አለ የቤቱ መግቢያ ላይ በቢጫ ፕላስቲክ ላይ የተለጠፈውን ጥቅስ አየ... ስለቡና ይህንን ጥቅስ አየ... ስለቡና ይህንን ጥቅስ እልፍ ጊዜ አንብቦታል የሚካኤል ባልዛክ "When you drink a cup of coffee, ideas comes marching in your brain" የመጨረሻውን የቡና ጨመቅ ወሰደ ቡናውን ምላሱ ላይ አሽከረከረ፡፡ አሁን አንተ ምን ታስባለህ? አለ ራሱን፡፡ የቡና ጣዕም ለመለየት ከማሰብ ብቻ በመልካም ወይም መጥፎ ጣዕም ሊታወቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አሁን ማሰብ በጣዕም ላይ የምትደረግ ትኩረት ናት እንጂ ሌላ ጨዋታ አይደለችም፡፡ ለምሳሌ... ሰው ያስባል በማሰቡም ተዋርዷል እያልኩ እያሰብኩ ነው እንበል (አሁን) እንስሳው ደግሞ ስለ አለማሰቡ ምንም አያስብም አያውቅምም፡፡ እኔ ስላሰብኩ ምን ይፈጠር?...ይህ ምላሽ ትንሽ ቀላል ሊመስል ይችላል ነገር ግን እኔ ስላሰብኩ ምን ይፈጠር?... የሚለው ምላሽ የጥያቄው ምላሽ ብቻ አይመስለኘም ከጥያቄው በኀላ የመጣ አንድ የሃሳብ መስመር ይመስለኛል፡፡ስለዚህ "ሰው ያስባል ነገር ግን በማሰቡ ተዋርዷል" እነንዲህ ከሆነ ደግሞ አልታሰቀም ማለት ነው(ራሱን)፡፡ ምክንያቱም ከዛ በኀላ የታሰቀው "እኔ ስላሰብኩኘ ምን ይፈጠር ስለሆነ፡፡" ሁለት፡፡... እንስሳው ስለ አላሰበ አይደለም ያላጠፋው፡፡ እንዳያስብ ሆኖ በሆነ (በተፈጠረ) ነገር ላይ እሻላለሁ ይሻላል ፣ እበልጣለሁ ይበልጣል ቅሎ መፃረር አለመሻል ይመስላል፡፡ ምክንያቱም አልሻልም አልችልም አይደለሁም ማለት የማይችል እንደሆነ ከሚኖር ነገር ጋር መሆንን ሲሻ ከማይሆን ከአለመሆን ጋር የሚስማማ የሰው ልጅ ሁኔታውን ከሚኖር እንስሳ ጋር በምን ይለያል? ምክንያቱም እንስሳው የማያጠፋው ስለማያስብ ሳይሆን ሁኔታውን ስለሆነ ነው፡፡ የሚያጠፋውም እንዲያ ስለሆነ ነው፡፡ ማሰብ የምክንያት አይደለም፡፡ መሆን ግን አብዛኛው ጊዜ የማሰብ ሳይሆን የመፈለግ ውጤት ናት...አስበን አንፈልግም የፈለግነውን፡እናስባለን እንጂ፡፡ እውነት ነው የቃላት ጨዋታ ሊመስል ይችላል ግን የምናወራው (የምፅፈው) (የምታነበው) ስለ ማሰብ የምትታሰብ የወረቀት ወሬ ናት፡፡ ቅድም እንዳወራነው ወደ ኀላ ልትተርትና የአፍ ደመና ዝናብ መሆን ባትችል እንኳ ካፍያ እናድርጋት ትንሽ ወሬ፡፡ በብራና ላይ ቅንጣት ብርሃን መሆን ስለምትችል የምናስበው በቃል ስለሆነ የቃል ጨዋታ ብሎ ነገር የለም፡፡ ቅድም ከተናገርኩት ጋር በመጠን የተቃረንኩት ይመስላል... ከዚያ ምልከታ በኀላ ይኼኛውን ከተቀበልኩስ የቃላት ወንዝ በሃሳብ እዚህ ካደረሰኘ የቃል ጨዋታ ያልሆነ ስለሌለ ሁሉም "ንድፍ" የቃል ውጤት ነው፡፡ መስመር እራሱ ሳይቀር...፡፡ ጠረቤዛ ላይ ባዶ ሲኒ... ሲኒው ሲዞር ዜሮ መሳይ የቡና ስኒ ማስቀመጫ ላይ ፣ የስኒ ማስቀመጫው ስኒውን ተሸክሞ ዜሮ ቅርፅ ጠረቤዛ ላይ ይታያል፡፡ አስተናጋጇ መጣች ስኒውን ልታነሳ መስሎኘ ነበር፡፡ ነገር ግን ከአጠገቤ ካለው ጠረጴዛ ላይ ያሉትን ጥንዶች ለመታዘዝ ነበር፡፡ አመጣጧ ለካ የምትንጎራደደው ስራዋ ስለሆነ ነው፡፡ መንጎራደድ ከጠረጴዛ ጠረጴዛ እዚህ ቤት ብዙ ደስ የሚሉ ዜሮ ነገሮች ይበዛሉ...ይህንን ያልኩት የአስተናጋጇ ዳለሰ ስለሚያምር ነው ምርጥ ቅንፍ አላት () እዚህ ቤት ስገባ ይህንን ሃሳብ ራሱ ሳያሳስበኘ አይቀርም፡፡ እንደ ምርጥ ባለ ቅኔ ውብ ስንኞች፡፡ ሳይታሰቡ እንደሚፈሱ ግጥሞች፡፡ እንደ ባለተሰጦዖ ቀልደኛ ቀልዶች፡፡ ተፃፈ፡፡ በድንገት እኔ የዚች ፈገግታ የተለያት የተወዳጇ ኑሮ ወደጎን ያዘመማት ከተማ ነዋሪ ነኘ ከተማችን እንብርት ላይ የተፃፈው ሕግም ተገዢ ነኘ የከተማዋ ቁልፍ ሕግም " ድንገትና ምናልባት" የሚል ነው፡፡ ይህ ሕግ የሕዝቡ ሕይወትና ኑሮ አማክሎ የወጣ እነንደሆነ የከተማዋ "ጭቃ ሹሞች" ይናገራሉ...እንዲህ ሲሉ... "የህዝቡ ሕይወት የሚመራው በምናልባት ነው...ድንገት ተነስቶ የሚኖር ህዝብ ስለሆነ በድንገት ለሚመራ ህዝብ የምናልባት ስርዓት ሊጨመርበት (ለት) ይገባል...ምናልባት ለሚሆነው ነገርም...የድንገት ህግ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ እኔም የዚህ ከተማ ሕግ ተገልጋይ ነኘና እዚህ ካፍቴሪያ ይህን ጽሁፍ ጻፍኩት ድንገት፡፡ መፍሰስ መልካም ነው፡፡ ወደ ሃሳብ ወንዞች ወደ ፍላጎተት ውቅያኖስ የመሆንን ተራራ ባያቅፉትም እየዳሰሱ፡፡ በእውነት ሸለቆ ባይኖሩም እየተሽለኮሎኩ፡፡ ወንዙ ወደሚያደርሰን እየታጠፍንም ቁልቁል እየተወረወርንም በፀጥተኛው ሜዳ ላይ እንደማይጓዝ ለጥ ብለን እነንደ አሸዋ በልባችን እየተሳብን አንዳንዴም በአሸዋማ ሜዳዎች ላይ ውለታ ቢስ ለመሆን ቁልቁል እያደረግን መፍሰስ እስከመዳረሻችን...ለመተኛት መውደቅ ለመውደቅ ማንቀላፋት... ለሕልም ...ለቅዠት ምንምንም ላለማየት ተኘቶ ለመነቃት፡፡ ወድቆ ለመነሳት መውደቅ... መውደቅ...መውደቅ... ቅድም ሆቴሉ ውስጥ ወድቆ ሲነሳ... አንቀላፍቶ ሲነቃ ያሰበውን አሁንም አሰበ፡፡ አንዳንድ ሃሳቦች እነንዲህ ናቸው...አይለቁም...ይኖራሉ...ብቅ...ይላሉ... ድንገት የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች ከኤፍሬም ስዩም ህዳር 2007ዓ.ም ቤታችን እንሁን እናስብ🤔🤔👊 ለአስተያየታችሁ @jahABP @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
አባትክ/አባትሽ መክሮሽ ያውቃል?? 😂😂ፈገግ ያስብላል አይደል😂👊 እስኪ እንደዚህ ብሎ መክሮኻል/መክሮሻል ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂😜😜 በዚህ ፅሁፍ ተገርሜበታለሁ...... ብዙ ታተርፉበታላችሁ @jahABP ነኘ
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ሃሳብ ... ማሰብ ... አሳቢነት ወድቋል ማለት ይቀላል፡፡ አልጋው ላይ የተጣለ እንጂ የተኛ አይመስልም፡፡ ጥልቅ መጥፋት ውስጥ ነበር፡፡ ሕልምም ቅዠትም አላየም፡፡ ተኘቶ ብቻ ነው የተነሳው (ይቅርታ ተኘቶ ነው የነቃው)፡፡ አልጋው ላይ ወድቆ ነበር የተነሳው፡፡ ዓይኖቹን ገለጠ በስተግራ በኩል ካለችው ትንሽ ጠረቤዛ ላይ ከኮንዶም አጠገብ የተቀመጠ አንድ የሮዝማን ሲጋራ አንስቶ ለኮሰ፡፡ አሰበ፡፡ ማሰብ ማፍጠት ከሆነ እያሰበ ነው፡፡ (እዚህ ላይ አሰበ ያልኩት እኔ ነኘ ወይ እርሱ እያሰብኩ ነው አለ) መልካም አለም አላለም...እያሰበ ነው፡፡ :...እኔም ካልኩኘ እያሰብኩት ነው፡፡ በሌላ ሁኔታ ውስጥ በማናሰላሰስላት ነጥብ ላይ መብሰልሰል ማሰብከሆነ (በትላንቱ ሁኔታ ውስጥ መፀፀት ወይ መደነቅ) ማሰብ ከሆነ አድፍጧል ማፍጠጥ ማሰብ ተደርጎ ስለሚወሰደድ፡፡ ምናልባት ማሰብ ከመፃኢ ጊዜ ጋር ቂርኘነት ሊኖራት ይችላል፡፡ ወደኀላ ማሰብ ግን ስላልታሰበበት የማሰብ ያህል ነው፡፡ ማስታወስ የተሆነውን ወደኀላ የመተርተር ውጤት እንጂ በራሱ የአሁንታነት ሁኔታ አይመስለኘም፡፡ ሲጋራውን በረጅሙ ሳበ፡፡ በረጂሙ ተነፈሰ፡፡ ጢሱ ተበተነ ...የጢሱ ሽታ ትላንት ያሳለፈውን ሁኔታ መሰለው ትላንትን እያስታወሰ (እያሰበ) ሌላ ሃሳብ ታሰበው ...ከአንዱ ወደሌላው ሲሸጋገር የሚያውቀው ነገር አልነበረውም፡፡ (ካላወቀው እንዴት እያሰበ ነው፡፡) ማለት እንችላለን... ቢሆንም እያሰበ ነው... .... ለመተኛት ማንቀላፋት ያስፈልጋል፡፡ ካንቀላፉ መውደቅ አለ፡፡ መውደቅ!!! ከወደቁ በኀላ የሞት ልምምድ( በእንቅልፍ) አለ፡፡ እንግዲህ በእንቅልፍ መሃል ነው ሕልም የሚታለመው... ሕልም ከሌለህ ቅዠት ፣ ከምንም ግን የሚሆነው ምንም ነው፡፡ ተኘቶ መንቃት ወድቆ መነሳት ብቻ፡፡ ያለህልም ያለ ቅዠት... ከወደቀበት ተነሳ፡፡ ወጣ የሆቴሉን ደረጃ እየቆረጠ ወረደ፡፡ ሰባት ደረጃ ሥምንተኛው ወለል፡፡ ሰባት ነው አለ፡፡ ለራሱ ስምንተኛውንማ አልቆጥርም ብሎ በልቡ አሰበ፡፡ ሰባትን ስለሚወድ የእድል ቁጥሬ ሰባት ነው ይላል... ሥላሴ በሰባት ናቸው፡፡ ሰው የሰባት ነገሮች ውጤት ነው... የስጋው ክፍል አራት፡፡ ስጋ ጎዶሎ የሚሆነው ደካማ የሆነው ሙሉ ስለሆነ ነው፡፡ ነፍስ የሶስት ባህሪያት ውጤት ናት የማሰብ የመናገር የሕያውነት ÷ እኔ ከነፍስ ወገን ስለሆንኩ በሰባት አምናለሁ አለ... ሰባት ራሱ በራሱ ለራሱ የታመነለት ቁጥር ነው፡፡ ሲወጣ በልቡ እንዲህ ተናገረ.... "ወለሉን ሳይቆጥረው ደረጃው ሰባት ነው" ሲል፡፡ ከተማይቱ በብዙ የተጨነቁ መንፈሶች የተሞላች ናት፡፡ በከተማይቱ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ከህይወትና ከፊደል የተማሩ አዛውንቶች ሳይቀሩ... ሕይወታቸው በእንባና በሀዘን ማህበረሰብንም በማማረር የተሞላ ነው፡፡ ለከተማይቱ ነዋሪዎች ሕላዊ በጣራና በግድግዳ ላይ የተመሰረተ ሆኗል ከዚህ ከፍ እንዳይሉ ግራና ቀኙን አይተው እንዳያስተውሉ እንዳይጠነቀቁ የከተማዋ ድምፅ አልባ ሕግ አይፈቅድም፡፡ በዚህ ትንሽ እድሜ ጠገብ ከተማ ውስጥ ሕይወት በንድፍነት ደረጃ የተቀመጠ ሲሆን ቀለም አልተቀባም፡፡ የትኛውም ነዋሪ የሚጓዙበት ያለበትን አያውቀውም ÷ እዚች ድሃ ነገር ግን ውብ ከተማ ውስጥ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች በድንገተኘነት ላይ የተመሰረቱ ናቸውና የዚህ፡ከተማ የሕግ መፅሐፍ "ድንገትና ምናልባት" የሚል ነው፡፡ አየ፡፡ ሰማዩን ምድሩን የፊቱን የኀላውን ሁሉንም አየ ዓለም እንደከዚህ በፊቱ ናት፡፡ ወያላዎች የጠራሉ ፣ ሴቶች አጊጠዋል ፣ ካፌዎች ቡና መቁላት ጀምረዋል፡፡ እርሱም እንደትላንትጠዋቱ መጀመሪያውን ቡና ለመጠታት ካፍቴሪ ሊቀመጥ ነው...ዛሬ ጠዋት ደግሞ የትላንትናው ምሽት ይወራል ስለድራፍት ፣ ስለቢራ ፣ ስለውስኪ ፣ ስለፐብ ፣ ስለክለብ ፣ መጨረሻ መሐል መጀመሪያ ደግሞ ሴት ስለሴት ስለሴት የአንድ ቀለም ወግ፡፡ ተራ ወሬ ህይወት አልባ ድምፅ...ለነገሩ ምርጥ ሃሳብ ራሱ ወረቀት ላይ ካልሰፈረ ተራ የዓይን ደመና ነው፡፡ ደመናው በቀለም ረጥቦ ወረቀት ሜዳ ላይ ከዘነበ ተራና መናኛው ወሬ ትንሽ ሃሳብ መሆን ይችላል፡፡ ከወሬ ከፍ ያለ፡፡ ዓለም አሁንም በዓይኑ ፊት እንደትላንቱ ናት፡፡ ጠየቀ፡፡.... ትላንት የሞቱ ምን አመለጣቸው? በዛሬው እና በትላንቱ እንቅስቃሴ መሃል ምን፡ለውጥ አለ?? የዛሬው ሰው ከትላንቱ በምን ከፍ ይላል? የአምናው ጣዕም ከዘንድሮ በሚሻልበት ዓለም የዛሬ ምርጥነት ምኑ ላይ ነው? እየቀነሰና እየወረደና እየተዋረደ በሚገኘበት ሁኔታ ውስጥ ከትላንት ወደ ዛሬ የመገኘት በረከትነት ምኑ ላይ ነው? በሕይወት ያሉት ከሞቱት ዝቅ ካሉ በሙታን ቀናቶች ላይ ሕያዋን ቀናቶኞች ላይ ሕያዋን ቀናተኞች ከሆኑ የዛሬ ዛሬነት ምኑ ላይ ነው? እናንተ አምና... ካቻምና... የዛሬ ሃያ አመት የሞታችሁ ሆይ... ቀናቶቻችሁን መልሱልን ቀኖቻችን ከእናንተ ይልቅ ብርሃናማ አይደሉምና፡፡ የሚያየውን ሰው ሁሉ ተፀየፈ፡፡ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ቀለም የተቀባ ብራና መሰለው ያውም ከባድ ቀይ የተቀባ... አስተናጋጇ መጣች፡፡ ቡና አላት እንደወረደ፡፡ ቡና ሲያዝ አፉ በምራቅ ልቡ እንዲህ በማይለው ሐሴት ይሞላል... ቡና ሊጠጣ ነውና ደስተኛ ነው፡፡ ቅድም ስለማሰብ ያሰበው ትዝ አለው፡፡ ማሰብ ምንድን ነው? ሰው በማሰቡ ከእንስሳት ይለያል ሲባልስ እንዴት ነው?... የሰው ልጅ ምንን ስላሰበ ነው ከእንስሳት የሚነጠለው? ወይስ እያሰበ መሆኑን (ማሰብ መቻሉን ማወቁ) ነው? ከእንስሳት ልዩ የሚያደርገው፡፡ እንስሳት ወደ ማይሆን አቅጣጫ ሲጓዙ እረኛቸው እንደሚያግዳቸው ሁሉ ማሰብ እረኛችን ትሆን? እንዲህ ከሆነ የሰው ልጅ መች እረኛውን ሰማ? ከኔ ጀምሮ፡፡ አሁን እኔ ውስጥ እዚህ ካፍቴሪያ የተሰበሰቡ ሰዎች የሉምን? ምክንያቱም ስለራሱ ሙሉ የሆነ ስለእርሱም አይሳሳትም፡፡ Period ውሸት??? ማሰብ ከእንስሳት የተለየንቀት ሳይሆን ከአራዊት ይልቅ አውሬነታችን የተገለጠበት ከትንኘም በታች ቅንጣት ያከልንበት ሁኔታ ነው፡፡ ማሰብ ነውራችንን አደባባይ ያሰጣብን ከእኔነታችን ያጣላን ከእንስሳት ዝቅ ያደረገን ነገር ነው፡፡ ቡናው እስኪቀርብ እነዚህን እያሰበ ነበር... ቡና ቀረበለት፡፡ የመጀመሪያው ቡና፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስራውን በእጅጉ እንደያዘ ከደረሰበት ቀጠለ... "ዘሎ ገደል የገባ እንስሳ የትኛው ነው? የሰው ልጅ ብቻ፡፡ መውደቅ አውቆ ማጥፋት አስቦ ማጥቃት አስቦ መጥፋት የሰው ልጅ ብቸኛ መለያ ነው... የማያስብ እንስሳ ጥፋት ኪሚያስብ የሰው ልጅ አጥፊነት አናሳ ከሆነ የሚያስብ የሰው ልጅ ጥፋት በማያስብ እንስሳ ካልተደረገ ከሁለቱ አናሳው ማን ነው? ያሰበውስ? የደመነ-ነፍስ እውቀት ከነፍሳዊ እውቀት ከተሻለ ሰው ክብሩን ለእንስሳ ሊለቅ ይገባዋል፡፡ በእርሱ የተደረገ ጥፋት በእርያዎች የለምና..." ወደ ራሱ ተመለሰ የቡናውን ስኒ አነሳ...አልቋል ስኒው ውስጥ የዕድፍ መስመር አየ.....የአቧራ መንገድ የሚመስል ብዙ አቋራጭ መንገድ መሳይ ነገር ከንፈሩ በነካበት የስኒው የውስጠኛ ክፍል ደግሞ ሰፊ የአቧራ ሜዳ ወይም የሸርተቴ መጫወቻ መሳይ ነገር ይታያል... ይቀጥላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN አስታውሳለሁ ምኒልክ 12 ክፍል እያለን ከትምህርት ቤታችን ዝቅ ብሎ በቢኒያም ፎቶ ቤት ወደቀኘ ታጥፎ ባለች ባለች የራሳችን በምትመስል ትንሽዬ ምግቤት እርጥብ ልንበላ ተቀምጠን ሳለ.......አንድ ጓደኛዬ አንዴ አብያ ብሎ ጮኸ ምንድነው አልነው ሁላችንም አንድ ላይ....የገጣሚ ስም ጠራ አትቀልድ አልኩት በኡነት እሱ ነው፡፡ ሔደ ብሎ እየሮጠ ወጣ........ተከተልኩት ኡነትም እሱ ነው የገጣሚ ወግ የሆነችውን ስካርፑን ጣል አድርጎ ገና ከእንቅልፉ መነሳቱ ነው መሰል አይኖቹ ትንንሽ ሆነዋል ፊቱን የወረረው ፂሙ ላይ የውሃ ጠብታዎች ይታያሉ በኢንቬሎፕ የታሸገ ዶክመንት ይዟል ሰላምታ ተለዋውጠን አድናቆታችንን ገልፀን ማስታወሻ ፎቶ ተነሳን ደስ ብሎን ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን እናደዳለሁ ለምን ታክሲ ድረስ አብሬው አልሔድኩም ለምን ትንሽ እንኳን አላወራሁትም በጣም እበሽቃለሁ🤦‍♂🤦‍♂፡፡ ይህን እንዳነሳላችሁ ያስገደደኘ የዚህን ገጣሚ አጫጭር ልቦለዶች ትንሹ ወንድሜ እያነበበ አየሁት ሲያስቀምጠው አነሳሁና ርዕሱን አየሁ ፈገግ አስባለኘ ከጀርባ የደራሲው ቀደምት ስራዎች ተፅፈዋል ማውጫውን ስመለከት አይኔ አንድ ርዕስ ላይ አረፈ አስገረመኘ፡፡ የጋሽ ስብሃት አባባል ፊቴ ድቅን አለ " አንዳንዴ የምታስበውን ነገር የሆነ ቦታ ተፅፎ ታገኘዋለህ የምትለዋን"፡፡ ገለጥኩና ማንበብ ጀመርኩ ተደነኩ የኔ ያንተ ያንቺ የኛ የሁላችንም ሃሳብ ይጋራል ብዬ አሰብኩና ስለወደድኩት ይኸው ላካፍላቹ ወደድኩ፡፡ ነገ ጠብቁኘ ለማንኛውም አስተያየታችሁ @jahABP @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ⚡️🔥ተቃጠለ🔥⚡️ ተቃጠለ ቢሉኝ ጎጆየን ነው ብዬ፣ ተቃጠለ ቢሉኝ ታዛየን ነው ብዬ፣ ለካስ ሰማይ ኖሯል ኧረ እናንተ ሆዬ! እሱማ እሳት ነው የእሳተ መለኮት የጌታ መኖሪያ፣ በውሃና ነፋስ የተጠቀለለ የእግዜር የጥበቡ ትንሹ ማሳያ። ከላይ ያለው እሳት ዝቅ ብሎ ከሆን ኋጥያቴ ሲበዛ፣ ነነዌ እንደሆነው ዮናሴ ሰብኮኝ እኔም ልብ ብገዛ፣ ፊቱን ይመልሳል ፈጣሪ ደግ ነው ምህረቱ የበዛ። የተ.አ.ኢ (አል አይን) 24/09/ 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2:25 ትዝታ © °°°°° አብያችን ያነሳውን ፎቶ ካየሁ በኋላ የተጻፈ... @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ባለፈው ነው ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ ሰፈር ንፋስ እየተቀበልን እየተጫወትን እየተሳሳቅን ነበር በመሐል እኔ አመሌ ተነሳና ፎቶ ማንሳት ጀመርኩ፡፡ እነሱ ደቂቃ ይይዛሉ ወይኔ አመለጠህ አሁንስ አገኘኸው እስኪ አሳየን አሁን አመለጠህ ለጥቂት ይሉኛል፡፡ 324 ፎቶዎችን አነሳሁ አንድም የተሳካ ፎቶ ሳላገኝ ቀረሁ፡፡ ሁላችንም በጣም ብናዝንም እየተሳሳቅን ወደቤት ተመለስን፡፡ ማርያምን እላችኋለሁ ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር የሆነ ቀን ሚገርም ፎቶ ከሰማዩ ላይ እንደማስቀር አውቅ ነበር፡፡ እና ዛሬ ማታ ምን ሆነላችሁ ወደ ሰማይ አንጋጥቼ 180 ፎቶዎችን አነሳሁ አንገቴን እስኪያመኝ ድረስ... የእውነት ግን አሞኛል..... ከዛማ ፎቶዎቹን ስታዩ እራሳችሁ ትፈርዳላችሁ....ሚገርመው አስተያየት እንዲሰጡኝ ጓደኞቼ ጋር ልኬላቸዋለሁ ሸጋ የሆነ አስተያየታቸውን ለገሱኝ፣ አበረታቱኝም ፎቶዎቹን ካዩት ሰዎች መካከል አንዲት ወዳጄ😍🙏የምወዳት😘 ከመቼው እንደጻፈችው ባላውቅም ገራሚ ግጥም ጻፈችለት በጣም ደስ ሚል ግጥም ነገ ከፎቶው ጋር ይለቀቃል፡፡ እባክህ ወዳጄ ሞክር ሞክር ሙከራዎች ወደ ትክክለኛው ቦታ ያደርሱሀል፡፡ ሩጫችን ከትላንት የተሻለ መሆን አለበት ከትላንት የተሻልን ብቻ ሳይሆን የበለጥን!!! @jahABP ነኝ ማንኛውንም አስተያየታችሁን አድርሱኝ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
በጎ ነገር ማድረግን የመሰለ ምን ነገር አለ ሰውንም አንተ ባደረከው መልካም ነገር ሰው ሲድን ማየት ደግሞ ደስታህን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡ ምን መሰለህ ወዳጄ ማንም አስታዋሽ ባይኖርህ ደም መለገስ ጀምርማ፡፡ ደምህን ከለገስክ ልክ ሶስት ወር ሲሞላህ የሚገርመ ሰላም ያለው ድምፅ ወዳጃችን እንዴት ነህ ሁሉ ሰላም ነው የዛሬ ሦስት ወር ደምህን ለወገኖችህ ለግሰህ ነበር ጤኔኘነት የሚሰማህና ብቁ ነኘ ብለህ ካሰብክ ዛሬ ሶስት ወር ስለሞላህ ለመስጠት የምትችል መሆኑን ልንገልፅልህ እኖዳለን ይሉኻል፡፡ አቤት ትህትና🙏😍 አየህ አንተ ባታስበውም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ ያንተ መኖር የሚያኖራቸው አያሌ ሰዎች አሉ፡፡ ምንም የለኘም ምንም መስጠት አልችልም አትበል ያለህን ካሰብከው ብዙ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡ በዚ አስፈሪ ጊዜ ደግሞ የደም እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል አቅማችን የሚፈቅድ ሰዎች ሔደን የዚህ መልካም እና ቅዱስ ሐሳብ ተካፋይ እንሁን እላለሁ፡፡ ይኽን ክፉ ጊዜ በፍቅር በመተሳሰብ በጋራ ተባብረን እንለፈው፡፡😍🙏😍 @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ምሽት
Mostrar todo...
ማንም ስልክ ላይ ባይደውልል አንድ ስልክ ግን እንዲደወልልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ማን ለሚለው ተመልሼ እመጣለሁ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂😀
Mostrar todo...
የፊልም ስክሪፕት ያላችሁና ስክሪፕቱን መሸጥ ወይም ፕሮዲውሰር የምትፈልጉ በ @bcrazykid አግኙኝ።
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN እናንተ ሰዎች ነው ያልከው?? አዎ ኡነቴን እኮ ነው ትገርሙኛላችሁ?? ለምሳሌ ይህን መስመር እየው አለኘ ወደ ወለሉ እያመለከተ ወለሉ ላይ ብዙ ቀጥ ያሉ መስመሮች አሉት፡፡ አየኻቸው አይደል ማንኛውም ሰው በህይወቱ እንደዚህ አይነት መስመሮች አሉት ግን ማንም ይሔን መስመር ጠብቆ መሔድ አይፈልግም በዚ መስመር ተጉዞ የፈለገበት መድረስ ይችላል፡፡ ግን የሌላው ያምረዋል ሌላውን ከመስመር አስወጥቶ እሱ ባቋራጭ ለመክበር ይፈልጋል የሱን መስመር ትቶ የሌላው መስመር ውስጥ ይገባል ሌላውን ከተሳካ አሽቀንጥሮ መጣል ካልሆነ ይዞ ማስቀረት ማዘግየት ይፈልጋል ጉልበት ያለው የሌለውን ይጨቁነዋል.....ታዲያ ሰው አይገርምም ትላለህ?? ሰው አይደለሁም ልልህ አይደለም ነኘ ያውም በሙሉ ጤነኘነት የተወለድኩ ግን አብዛኞቻችን እንደሰው መኖር አቅቶናል ልልክ ነው፡፡ ይኼማ ምንም ጥያቄ የለውም የሁላችንም ትልቅ ችግር ነው፡፡ አልኩት በቀጣይ ስለማቀርብላችሁ መፅሐፍ አነሳሁለት ደራሲውን በጣም እንደሚወደው ነገረኘ ግን አህያዋን መፅሐፉ ላይ ማድረጉ ቅር እንዳለው ነገረኘ ለምነ?? ስለው፡፡ አህያ እወዳለሁ አሁን እያወራንበት ባለንበት ሰዓት አህያ ሆኜ ባወራህ ደስ ይለኛል፡፡ እኔ ከhigh school ጀምሮ አህያን ፕሮሞት እያረኩ ነው የመጣሁት፡፡ አንዴ ጅማ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ጊዜ አንድ ሰውዬ አህያውን በሆነ በር ሊያስገባው እየሞከረ አህያው አልቻለም በሀይለኛው መታው ሊያልፍ አልቻለም በድጋሚ ሌላ ዱላ አሳረፈበት አሁንም ሊያልፍ አልቻለም ሰውየው ዝቅ ብሎ ሲያይ ለኬ አንድ ብረት ነው አግዶ የያዘው ከዛ በኀላ ስለአህያ አብዝቼ ማሰብ ጀመርኩ አያሳዝንም?? አለኘ፡፡ ስለመፅሐፉም ብዙ ተባባልን፡፡ ቀላል ያሳዝናል አልኩትና በውስጤ የሀገራችንን አህዮች ስቃይ ሽው አለብኘ ከጥንት እስከ አሁን ፡፡ የምኞት ማደሪያ እያደር ሲለጠጥ ግድግዳና ጣሪያው ለበር የታሰበው ሽንቁር ሆነ ቀረ....ምትል የበውቄን ግጥም አለልኘ ስንኙን ተሳስቼ ይሆናል አለኘ ኡነት ገብቶት ነው የፃፈው ብዬ ሁሌ አስባለሁ፡፡ ከሆነ HE IS GREAT አለኘ፡፡ አያ ሙሌን ሳያውቀው በሱ ታሪክ ለመክበር የሚፈልጉ ሰዎች አሉ እንደጅብራ እላዩ ላይ ለመጣበቅ የሚፈልጉ አያ ሙሌን እወደዋለሀው ይሉኃል መከራውን ችግሩን ሳያውቅ ደቡብ ላይ አንድ ፍሬ አለ በጣም ይጣፍጣል ያን ለማግኘት ግን መተህ መስበር አለብህ ውስጡ ያለውን ጣፋጭ ነገር ምታገኘው ስለዚህ ስለ አያሙሌ በደንብ ልናውቅ ይገባናል መጎርጎር አለበት አለኘ፡፡....ግን ለወደቀ ልጁ አንድ ነገር ማድረግ አልቻለም😡(ስለአያሙሌ ህይወት በሰፊው እመለስበታለሁ) የሀገራችን አስተሳሰብ ተበላሽቷል ሁሉም ነገር ተዛብቷል እኛ ሀገር አምልኮ በዝቶል የሀይማኖት ሳይሆን የሰው አምልኮ ሔዶ የሆነ ሰው እግር ላይ አዳኜ ፈጣሪዬ ታዳጊዬ መውደቅ አንተ የፈጠረህ አምላክ አለህ የብርሃን አምላክ ስለዚህ ለምን ሰውን ትለምናለህ እሱጋር የጎደለ ነገር አለ አንተ ማሳየት ምትችለው አላስተዋልነውም እንጂ፡፡ ሰብአዊ ግንኙነት የተዛባው ለዛ ነው ይሔ የገዢና ተገዢ አካሔድ.... ፂምህን አሳድገህ ስካርፕ ማድረግ ፋሽን ነው ፓሽን?? ወይስ ሌሎቹ ስላደረጉት?? በወጉ የማይንቅ በወጉ አያከብርም ይላል በዕውቀቱ የሆነ ቦታ ላይ፡፡ በኡነት ነው ምልህ እዛ ፀሀዩ ላይ ሔጄ እንዲ ጠብታ እስክሆን ድረስ ብቀልጥ ደስ ይለኛል ግን አይሆንም ኬሚካል ሪአክሽን አይሰራም🤦‍♂🤷‍♂ አለኘ ከጃንቦ ብርጭቆው ላይ ላይ ጠብታ እያፈሰሰ ተስፋ ቆርጬ ምናምን አይደለም ሀገራችን ወደማይሆን ደረጃ እየሔደች ነው፡፡ ስብሃት ስለአማርኛ ቆንጅዬ ንግግር ተናግሯል እንደ አማርኛ ሀሳብን ለመግለፅ የሚሆን የለም ይላል፡፡ ወደፊት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም ይህን ፖለቲከኛ ይተቹታል አለኘ አው የሆነ መፅሐፋቸው ላይ ይህ ትውልድ የስልጣን ጥመኛ ነው ይሉታል አልኩት፡፡ በትክክል አለኘ መፍትሔው ምንድነው ትላለህ አልኩት እንደራስህ ምታስቀምጠው ስህተት ይፈልጋል የሰው ልጅ እንደእሳት እስኪሰራ ድረስ ደግሞ እስኪሳሳት፡፡ የምትል የሆነ ሰው ግጥም አለልኘ የበውቄም ሊሆን ይችላል አላቅም🤷‍♂ ከሰራ በኀላ መሳሳቱን ያምንልሃል ካልሰራ ግን መቼምምምምም አያምንልህም ስለዚህ መስራት አለብን መሞከር መጣር አለብን ያ ወደ ምንፈልገው ቦታ ያደርሰናልና፡፡ አዲስ ነገር በሀይማኖታችን በባህላችን እንዴት አስማምተን ነው መጠቀም ያለብን የሚለው ላይ ትልቅ ስራ ሊሰራ ይገባል፡፡ ምን እየሰራህ ነው ግጥም እፅፋለሁ የተለያዩ ሀሳቦችን እየፈጠርኩ ሰዎችን አማክራለሁ ለሚሰሩት ነገር በዛ ጥሩ ገቢ አገኘበታለሁ ለምሳሌ ፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ጋር አዲስ የሚሰራ ቤት አለ ለዛ ስም ማወጣው እኔ ነኘ አሁን አልነግርህም ሲከፈት ሔደህ እየው አለኘ፡፡ እሺ በደስታ አልኩት እንዳነበው ምጠቁመኘ መፅሐፍ?? ሁሉንም መፅሀፍ ግን ይኸ ትውልድ የብላታ ወልደጊዮርጊስ ስነምግባር ሚለውን መፅሐፍ ቢያነብ በጣም ተጠቃሚ ይሆናል ብዬ አስባለሁ አለኘ፡፡ መፅሐፉ እንዳጋጣሚ አንድሽ ስጦታ ተሰጥቶት በትንሹ የማንበብ አጋጣሚ ነበረኘየተወሰነ በፎቶም ያስቀረሁት ነበር አሳየሁት ሸጋ ነው አንብበው ብዙ ነገር ታተርፍበታለህ አለኘ እሺታዬን ገለፅኩኘ፡፡ ሰርገኞቹ መጡ እዚህ ነህ ስለው አዎ አለኘ መጣሁ ብዬው ወደሰርጉ ሔድኩ አጃቢ ነና ሞቅ ለማድረግ...🕺🕺🕺 ግን አሳዛኙ ነገር ግን ስመለስ ላገኘሁ አልቻልኩም የለም😢😢😔😳በራሴ በጣም ተናደድኩ ስልክ እንኳን ሳልቀበለሁ በጣም በሸኩኘ ግን ተመልሼ መጥቼ እንደማገኘሁ ለራሴ ቃል ገብቼ Final ፈተና ነበረብኘና ወደዛ ሔድኹኘ፡፡ "ተማሪ ካለ አስተማሪማ የትም አለ" @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ምሽት ሀሳቡ የተቆራረጠ የሆነው እንደሰውየው አካሔድ እንደሆነ ልብ ይባልልኘ፡፡ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN አንድ ልምድ አለኘ ይቅርታ ግን ይህ የኔ ልምድ ነው ለብዙ ሰው ላይመች ይችላል👊👊...ሊመችም ይችላል 😍🙏ብቻ አላቅም🤷‍♂ ምን መሰላችሁ አዲስ ነገር በጣም ደስ ይለኛል፡፡ 😃እና አዲስ ሰው ስተዋወቅ በተለይ ውይይት ከሆነ በሆነ አጋጣሚ ክርክር ከተነሳ አብሶ እኔ ስለማላቀው አዲስ ነገር ከሆነ🕺🕺....ደስታዬ ነው፡፡ ለነገሩ የማቀውም ነገር ቢሆን ከኔ የተሻለ ዕውቀት አላቸው ብዬ ካሰብኩ ያን ማድረጌ አይቀርም፡፡ ቲያትር እና ፊልሞች ሳይስ ብትሉ አይፋታኘም እኮ.....😂😂ለማየት ነው ለመፃፍ ምገባው አትሉኘም😝 ይህ ልምዴ ምን መሰላችሁ ከሰው ጋር ያወራነውን ቶሎ ብሎ መፃፍ ነው እና voice record ማድረግ ነው፡፡😂😜👊 የሆነ ሰዓት ላይ በምን እንደሆን አላቅም ድብር ሲለኘ ወይ ስለዛ ስላወራነው ነገር ደግሜ ሳስብ ወይም ማወቅ ስፈልግ ለሰው መናገር ስፈልግ ማስታወስ ካለብኘ ወደፃፍኩበት ማስታወሻ ስልኬ ላይ ሊሆን ይችላል ወይም openvoice🏃‍♂🏃‍♂........እናም ደጋግሜ እሰማዋለሁ record እንኳን ባላደርግ ደጋግሜ አነበዋለሁ አስበዋለሁ፡፡ ህግ ይፈቅዳል?? እኔንጃ አላቅም ብቻ እኔን ጠቅሞኛል ጥሩ ስለሆነም ሌሎችን ለማስተማር እጠቀምበታለሁ በመሐልም ሚጎዳ ያለ አይመስለኘም፡፡የህግ ሰዎች🙈🙈🙊🙊ምን ትላላቹ?? እናም ሁለተኛውን መፅሐፍ ከመጨረሳችን በፊት ከነዚህ አንዱን ላጋራቹ ወደድኩ...ኤጭ አበዛኸው እንዳትሉኘ፡፡😔😔🙏🙏 አንድ የሰፈራችን አብሮ አደጋችን ሰርግ👫 💑 ላይ በነገራችን ላይ ሶስት ሰርጎች በክብር የተጠራሁ ሰው ነኘ🤟🤘📱✉️✉️ከራሳቸው ከሙሽሮች፡፡ እና እዛ ሰርግ ላይ ሱፌን ለብሼ ዝንጥ ብዬ ሔድኩላችሁ🎀፡፡ ያው በሀገራችን ሙሽራ....ማርፈድ ልማዱ አይደል እስኪመጣ ብለን አንድ ሁለት🍻🍺🍻 ልንል እዛው በነበረ የቀበሌ መዝናኛ ጎራ አልን በነገራችን ላይ የመጠጥ አድናቂ አይደለሁም ግን ያው ወጣት አደለሁ እጠጣለሁ፡፡ወጣት ሁሉ ግን ይጠጣል ማለቴ አይደለም🙏 ከዛ ቁጭ ብለን እየጠጣን አጠገባችን ካለ በሌላ ጠረቤዛ ላይ የተቀመጠ ወጣት ልጅ እናንተ ሰዎች ትገርሙኛላችሁ ብሎ ወሬውን ጀመረ፡፡ ሳናውቀው ከማንአጠገብ ነው የተቀመጥነው ደሞ😳🤔 እናንተ ሰዎች😂😂 ሃሃሃሃሂሂሂሂ ምን ማለት ነው፡፡ ምንስ ለማለት ፈልጎ ነው እሱ ምንድንነው??🤔 ይሔንማ በደንብ፡ማወቅ አለብኘ ተገኘቶ ነው፡፡ ሰርገኞች በናታቹ ቆዩ ስል በልቤ ተመኘሁ ታዲያ እኔስ ምኔ ሞኘ ነው voice record ክፍት ወንበሬን ስቤ ምን ለማለት ፈልገህ ነው ብዬ ወሬውን ጀመርኩ ......ምን አለኘ ምን አወራን😃🤔🤔ነገ ነገ ነገ እጨርስላችኀለው፡፡ ዝናብ እየመጣ🏃‍♂ነው፡፡ እደሩልኘ😍🙏 አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN ምርጦች እንኳን ለ1ሺህ አራት መቶ አርባ አንድጀኛው ኢድ አልፈር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ በዓሉን ስናከብር ፍፁም ጥንቃቄ በተሞላበት ይሁን!! @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1441ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! Eid Mubarak
Mostrar todo...
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1441ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! Eid Mubarak. Sheger ™ @ShegerGebeta
Mostrar todo...
በእያንዳንዷ ምሽት በፍፁም ለስላሳና ለጆሮ በሚስብ ድምፅ የሚጀመረው መዝሙር ወይም ቅዳሴ በየዋሻውና ቀየቋጥኙ ስር ፣ በየጥሻው ውስጥ ያለው በመቶሺህ የሚቆጠረው ሸካራው የወንዶች ድምፅ ይቀበልና ሲደግመው ፣ ከነሱ ተቀብሎ የገደል ማሚቶው በጣም ሩቅ ላሉት ሲያስተጋባው ፣ ይህ ነው ተብሎ መግለፅ የማይቻል ፍፁም ልብን የሚነካ ፣ ሰውነት የሚያንቀጠቅጥ ስሜት ይሰማል፡፡ የሀበሻ ጀብዱ፡- አዶልፍ ፓርስለሳክ ተርጓሚ:- ተጫኔ ጆብሬ መኮንን @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD VOICE BY @jahABP
Mostrar todo...
4.45 KB
Register on this site and make money online https://zbemoney.xyz/382116499356926/
Mostrar todo...
Register on this site and make money online https://zbemoney.xyz/382116499356926/
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ወዴት ነህ? በአሜሪካ አገር አንዲት ወጣት በደረሰባት የሞተር ሳይክል አደጋ እግሯን አጣች፡፡ እጅግ ውብ አስተዋይ የነበረችው እና በቤተሰቧ ትልቅ ተስፋ የተጣለባት ልጅ በዐሥራ ሰባት ዓመቷ የደረሰባትን ጉዳት ረስታ ትኖራለች ብሎ ማንም አልገመተም ነበር፡፡ ወደ በመንፈሳዊው ዓለም ያነቋት ቤተሰቦቿም ከእንባቸው ወጥተው የልጃቸውን ጉዳት ለእግዚአብሔር ክብር ይሆናል ብለው አልገመቱም ነበር፡፡ ያች ልጅ ግን ከጉዳቷ በፊት የሰማችው የእግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን አስረሳት፡፡ ልጅነቷ እንዴት እንደሚሄዱ በሚጨነቁ ወጣቶች ቄንጥ የተሳበ ነበር፡፡ አሁን ግን ወዴት እንደምትሄድ ያለው ተስፋዋ ብቻ ቀረላት ፤ በማንጎራጎር ጉዳቷን መለወጥ እንደማትችል ገባት፡፡ የቀናት መለዋወጥ ፣ የሁኔታዎች መደፍረስ የማይቀንሰው በሸክላ ልቧ ውስጥ የተቀመጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ለትልቅ ዓላማ ቀሰቀሳት፡፡ አንድ ቀን ሰዎች ልዩ ችሎታቸውን በሚያሳዩበት መድረክ ላይ እርሷም በድንገት ተነስታ ቆመች፡፡ ምን ታሳየናለች? ብለው ሲጠብቁ እርሷም ከሁሉም ስለሚበልጠውን ችሎታ መናገር ጀመረች፡፡ "ከሁሉ የሚበልጠው ችሎታ ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም ግን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድ ነገር ልነግራችሁ ፈለግሁ፡፡ በደረሰብኝ የሞተር ሳይክል አደጋ አንድ እግሬን ባጣም ዶክተሮች ለሰባት ወራት ባደረጉልኝ ልዩ እንክብካቤ ልተርፍ ችያለሁ፡፡ በዚህ እድሜዬ የተማርኩት አንድ ልዩ ችሎታ አለኝ፡፡ አደጋው በደረሰብኝ ጊዜ እምነቴ በይበልጥ እየጨመረ ሄደ፡፡ ብዙዎቻችሁ በነፃነት ስትራመዱ አያችኋለሁ፡፡ እኔም እንደ እናንተ ልራመድ ብችል ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ሁኔታዎች ተቀይረዋል። ዋናው ነገር እንዴት እንደምትራመዱ ማወቅ አይደለም፡፡ ከማን ጋር እንደምትራመዱና ማን አብሯችሁ እንዳለ ማወቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው ፤ አብሮኝ ይራመዳል ፣ ያወራኛል ፣ እኔም የእርሱ እንደሆንኩ ይነግረኛል፡፡ ወዴት እንደምትሄዱ ባወቃችሁ ጊዜ እግር ምንም ማለት እንዳልሆነ ትረዱታላችሁ" በማለት ስትናገር ሁሉም በእንባ ማዕበል ተመቱ። እንዴት እንደሚራመዱ የሚጨነቁ ሁሉም ወዴት እንደሚሄዱ ማሰብ ጀመሩ፡፡ "ትልቁን ችሎታ ተረዱ"፡፡ ዘመናዊነት ሁሉ እንዴት እንደምንራመድ የሚያግዝ ነው፡፡ ወዴት እንደምንሄድ የሚያሳውቀን ራዕይ ግን እየጠፋ ነው። እንዴት እንደሚራመዱ ይጨነቁ የነበሩ ዛሬ በትልቅ የሕይወት ኪሳራ ውስጥ ናቸው ፤ ደስታቸው ጊዜያዊ ፣ ዓለምን ያልጠገቡ ፣ ታሪክን ያልተመራመሩ ፣ አዲስ ግልብጦች ናቸው፡፡ ልጅ እንደ ልጅ ሲያስብ ወጉ ቢሆንም አዋቂ ግን እንደልጅ ሲያስብ ውርደቱ ነው፡፡ "ከአካሄድ ቄንጥ ያማረ ፍፃሜ የተሻለ ነው"፡፡ ትልቁ ችሎታ የአለባበስ ፣ የአነጋገር ፣ የአረማመድ ቄንጥ አይደለም፡፡ ትልቁ ችሎታ መድረሻን ተምኖ ጉዞን መጀመር ነው፡፡ ሰዎች ስለ ቁንጅና ፣ ስለ ልብስ ፣ ስለስፖርት ፣ *ስለዝሙት ለመናገር በሚጣደፉበት ዓለም ላይ ከጥበብ የሚበልጠውን ጥበብ ክርስቶስን እና ራዕይን የሚገልጥ ማን ይሆን? ዓላማውን አይቶ ዓላማን የሚያሳይ የታደለ ነው፡፡ መልካም ነገር እና እውነተኛ አኗኗር ዋጋ የረከሰበት በሚመስልበት በዚህ ዘመን ራዕይን ማስተማር ትውልድን እንደገና መፍጠር ነው፡፡ የተፈጠሩ ጫካዎች ለማረፊያነት ማስተካከልና ማስዋብ እንደገና መፍጠር እንደሆነ ሁሉ እንደ ሰው ተፈጥሮ እደሰው መኖር ያልቻለውን ፣ ለሆድ ደሞዝ ብቻ እንደ ውሻ የሚኖረውን ትውልድ ባለ ራዕይ ማድረግ ትልቅ አባትነት ነው፡፡ ዓላማን ለማወቅ ግን ሁልጊዜ ከጉዳት እና ከኪሳራ መማር አያስፈልገንም፡፡ የእግዚአብሔር ቀጥተኛ የማስተማሪያው ዘዴው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ቢሆንም እግራችንን አጥተን እንኳን ዓላማን ማግኘት የተሻለ ነው፡፡ ከባለ እግር ይልቅ ባለ ራዕይ ያደርሳልና፡፡ እግር ማድረስ እንጂ መድረሻውን መወሰን የእርሱ ስልጣን አይደለም፡፡ ሎሌው እግር በመራን መራመድ ለአሽከር መገዛት ነው፡፡ ያሰብነው ጋር መራመድና ፣ የተራመድነበትን ማሰብ የተለያየ ነገር ነው፡፡ ያሰቡት ጋር መሄድ ባለ ራዕይነት ነው፡፡ የሄዱትን ማሰብ ግን መባነን ነው፡፡ የሕይወትን ሩጫ ያስጀመረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር የሕይወት ባለቤትም ነው፡፡ እውነተኛው የሕይወት መምህር እርሱ ነው፡፡ እርሱ በቃሉ የእርሱ መሆናችንን ነግሮናል። በሕይወት በረሃ አብሮን የሚጓዝ የምድር በዳ ጓደኛችን ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ጥቂት ነገሮች ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በኑሮ ውስጥ ብዙ ነገሮችን ያስተምረናል፡፡ የእርሱ ትምህርት በልብ እንጂ በጆሮ የምንሰማው ስላልሆነ ማስተዋል ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር በየዕለቱ እያስተማረ የክፉ ነገርን ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ ግን የሚያስተውል የለም፡፡ በሕይወት መንገድ ላይ እግዚአብሔር አብሮን አለ፡፡ እርሱ ይመራናል፡፡ መልካም ፍፃሜም ከእርሱ ነውና ይሰጠናል፡፡ እንዴት እንደምንሄድ ያለን ጭንቀት ሲያበቃ ወዴት እንደምንሄድ ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ማድረግ የማንችለው ነገር ሲገጥመን ማድረግ የምንችለውን ማሰብ ትልቅ ነገር ነው። ሰዎች ከሚተርኩልን ታሪክ ይልቅ መልካም ውሳኔያችን የበለጠ እርካታ አለው፡፡ ትልቁ ችሎታ ሕይወትን በራዕይ መምራት ነው፡፡ ለሚማር ሰው ሕይወት በትምህርት ቤቶች የተሞላች ናት፡፡ ከጉዳታችን ውስጥ ወደ መጎዳት የሚሄዱትን የሚመልስ ብርሃን ሊወጣ ይገባዋል፡፡ ሰዎች ወድቀው ይማሩ ማለት ትልቅ ጭካኔ ነው፡፡ በእኔ ይብቃ ማለት የዓለምን ስቃይ ይቀንሳል፡፡ ደስታችን የግላችን ሊሆን ይችላል ፣ መከራችን ግን የጋራ ነው፡፡ የሌላው ጉዳት በግድ ሳይነካን አይቀርምና መምከር ይገባናል፡፡ ሰው ስለገደልን ብቻ ሳይሆን ሲገደል ስላየንም በየፍርድ ቤቱ እንከረተታለን፡፡ በታወሰን ቁጥር እናዝናለን፡፡ ከጉዳታችን ስንማር፡- "ከደረሰብኝ ነገር የደረሰልኝ እግዚአብሔር ይበልጣል" ማለት እንጀምራለን፡፡ የላይ ችሎታዎቻችን ሲወሰዱ ፣ ሀብታችንና ጉልበታችን ሲያልቅ ፣ የውስጡ ሰውነታችን እየጠነከረ ይመጣል፡፡ መከራዎች መካሪ ሆነው ራዕይ ያስጨብጡናል፡፡ ተምሮ መቅረት ብቻ ሳይሆን ተምሮ ለተግባር መነሣትን ያድሉናል፡፡ ስለ እውነት የሚመጣ መከራ ዕውነተኛ ማንነትን ያጎናፅፈናል፡፡ ከጎኔ ያለው ማነው ማለት ተገቢ ነው። እግዚአብሔር ነው ብለን ለራሳችን መመለስ ከቻልን ሺህ ሠራዊት ከከበበን በላይ ድፍረት ይሰጠናል፡፡ እኔስ ከማን ጋር ነኝ? ማለት ትልቅ ምርምር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መሆናችንን ለራሳችን መናገር ከቻልን ራዕይ ይታየናል፡፡ ያየነውንም እንወርሳለን፡፡ ★ ትልቁ ችሎታ የቀና አካሄድ ሳይሆን የቀና ፍፃሜ ነው፡፡ ★ትልቁ ችሎታ የቁንጅና አሸናፊነት ሳይሆን የግብረገብ ውበት ነው፡፡ ★ትልቁ ችሎታ የገመድ ዝላይ ፣ የጦር ውርወራ ሳይሆን ከእኔ የሚጠበቀው ምንድነው ማለት ነው፡፡ ★ትልቁ ችሎታ ማስተማር ሳይሆን የተናገሩትን መኖር ነው፡፡ ★ትልቁ ችሎታ ሌሎች ማጋለጥ ሳይሆን ራስን መመርመር ነው፡፡ ★ትልቁ ችሎታ የሌሎችን ታሪክ መቁጠር ሳይሆን ታሪክ መሥራት ነው፡፡ ከሁለተኛ መፅሐፍ አምስተኛ ጽሁፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ እናንብብ እንለወጥ ለሌሎች መለወጥ ምክንያት እንሁን! @jahABP ነኝ ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኝ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ?????? ሰዎች ራዕያቸውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት አንድ ምሳሌ ይነገራል፡፡ በአሁኗ ሰዓት ልክ እንደሞትን አድርገን ራሳችንን እንቁጠረው፡፡ የቀብር ሥርዓታችን ሊፈፀም የቀረው ጥቂት ሰዓት ነው፡፡ ባለጠጎች ሞትን በቅርበት ማሰብ አይፈልጉምና ራቅ ራቅ ብለው ቆመዋል፡፡ ቆንጆዎች የለቅሶ ፉሽን የሆነው ጥቁር ልብሳቸውን ለብሰው ፣ አስለቃሽ ሰዎች እንባቸውን ካስመጡት ለመገደብ በተጠንቀቅ መሐረብ ይዘዋል፡፡ ዋዘኞች እያለቀሱ የለቅሶ ቄንጥ ያወጣሉ፡፡ ወረኞች ለመንደሩ ሪፖርት ይዞ ለመመለስ እያንዳንዷን ነገር በጥንቃቄ ይመለከታሉ ጓዴ ጓዴ ምትለዋን የድሮ ሚስቱ ትሆን?... እያሉ የሰውን ልብ በወሬ ያጠፋሉ፡፡ ሊቃውንቱም፡- ስለ ሞታችን ሳይሆን ስለ አኗኗራችን ብላሽነት ያዝናሉ፡፡ ቤተሰቦቻችኝ የሚሆኑት ጠፍቷቸዋል፡፡ ስርዓተ ቀብራችን ተፈፅሞ ቀባሪው ወደ ዐውደ ምህረቱ ሰበሰብ ስራ የበዛባቸው ቀሳውስት ቆም ቆም እንዳሉ አንድ ሰው የህይወት ታሪካችንን ሊናገር ድምፁን ሞረደ ፣ ሁሉም ሰው ፀጥ ረጭ አለ፡፡ የራቀውም ለመስማት ቀረበ የህይወት ታሪካችን መናገር ጀመረ፡፡ ታዲያ በዚህ ሰዓት እንዲነገርልን የምንፈልገው የህይወት ታሪክ ምንድነው?? "ቅንነት የተሞላበት ፣ ሁሉን ወዳጅ የነበረ ፣ ለሙት ልጆች ወላጅ የሆነ ፣ *ለሰፈር ሰው ታዛዥ የነበረ ፣ ለሰው ችግር ቶሎ ደራሽ የነበረ ፣ በፍቅር የሚያምን ትህትና የሞላው ፣ ሰው ላይ ደርሶ የማያውቅ፡፡ ሁሉን በፍቅር የሚያሸንፍ ሀይማኖቱን ፣ ልጆቹንና ቤተሰቡን አክባሪ ፣ አክብሮም የሚያስከብር ፣ ሀገር ወዳድ ፣ ስራ ፈጣሪ ፣ ባለው ነገር ደስተኛ*.....ወይስ በተቃራኒው *ቲክቶክ ተጠቃሚ ነበር instagram ላይ ብዙ ተከታይ ነበረው ብዙ የዘመኑን ወጣት የሚስብ ብዙ ፎቶዎች ነበሩት.......እስኪ ምን ተብሎ እንዲነገርልን ነው የምንፈልገው ይኼን አስበነው እናውቃለን??.......በየትኛው ነው ህይወታችን እየሔደ ያለው??* የትኛው ነው እንዲነገርልን የምንፈልገው????? ይህ ምሳሌ ራዕይን ለማግኘት የሁል ጊዜ መለኪያ አይደለም፡፡ ራዕዬ ምንድነው? ለሚለውና ጭልም ላለበት አእምሮ ትንሽ ብርሃን ይሰጣል፡፡ በቀብራችን ሰዓት ብቻ አይደለም በቁማችንም እንዲነገርልን የምንፈልገው መልካም ነገር አይደለምን?? መልካም ናቸው እንዲባልልን እንሻለን፡፡ ነገር ግን መልካም ናቸው ከመባል መልካም መስራት ይሻላል ፣ ይቀላል ያስደስታልም፡፡ ራዕይ ምንድነው? ራዕይ ያልሆነው አይተናል፡፡ ራዕይ የሆነው ምንድነው? ጠቅለል ባለ ቋንቋ ብንገልጠው ራዕይ ግብ ነው፡፡ ግብ ሁሉ ራዕይ ላይሆን ይችላል፡፡ የተጠበቀ ግብ ግን ራዕይ ነው፡፡ ያለ ራዕይ ብዙ ስኬቶች ሊመጡ ይችላሉ፡፡በኑሮ ውስጥ የሚሰጠን መኖር በቅቶኛል ብለን እንድንረካ የሚያደርገን ራዕይ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ "ሰው የሚፈልገውን ካየ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ይሉ ነበር፡፡ ሰው መኖር ከብዶት ምቱን ሊመን ይችላል፡፡ ረክቶና ሰማይ ናፍቆትም ሞቱን ሊመኝ ይችላል፡፡ መኖርና መሔድን ዋጋውን እኩል የሚያደርግልን ራዕይ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚኖርበት በቂ ምክንያት ከሌለው መኖሩ ጣፋጭ አይሆንለትም መኖርን ጣፋጭ ከሚያደርጉት አንዱ ራዕይ ነው፡፡ እውነተኛ ራዕይ ግብ አለው፡፡ ራዕይ ግብ ከሆነ ደርሰን የምናውቀው ሳይሆን በእምነት መነፅር አይተን የምንጓዘው ነው፡፡ በመጀመሪያው እና በመጨረሻው መካከል ብዙ ሸለቆዎች/ጉድለቶች/ ብዙ ተራራዎች (ተገዳዳሪዎች) ቢኖሩም ባለ ራዕዩ ግን ወዳየው ፍጻሜ ይገሰግሳል፡፡ የሰው ልጅ "መጨረሻዬን አሳምርልኝ" ብሎ ይፀልያል፡፡ መጨረሻችን ከሚያምርበት ነገር አንዱ ራዕይ ነው፡፡ ሰለሞን እንደ ገለጠው ከመጀመሪያው የመጨረሻው ይሻላል፡፡ የተሻለው መጨረሻ ግን በራዕይ ስንጓዝ ነው፡ አንድ ሰው መጨረሻዬ እንዲህ ነው ብሎ የወሰነው ነገር ራዕዩ ይሆናል፡፡ እኛም እንደ ውሳኔያችን ነን፡፡ የምንሆነው ያሰብነውን ነው፡፡ ውጫዊ ኑሮአችን የውስጣዊ ትራፊክ ነው፡፡ የሚታዩ ተግባሮቻችን የአስተሳሰባችን ውጤቶች ናቸው፡፡ ራሳችንን እንዳዘጋጀነው ነን፡፡ ብንፈልግ አስጨናቂ ሰዎች መሆን እንችላለን ብንፈልግ አሳራፊ ሰዎች መሆን እንችላለን፡፡ ብንፈልግ ብዙዎችን ለማጥፋት የሚችል ማንነት አለን፡፡ ብንፈልግ ብዙዎችን ለማዳን ኃይል ተሰቶናል፡፡ በአንድ ኦሳማን ቢላደን አለም ተጨንቋል ፣ በአንዲት እማሆይ ትሬዛ ብዙዎች ድነዋል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን ነገር አለ ፣ ነፃ ፈቃዱ ግን የእኛ ነው፡፡ የአስተሳሰብ ኃይል በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ካልዋለ የጥፋት ፎርሙላ ነው፡፡ ልብ የተባለው ግዙፉ ተፈጥሮ ሳይሆን የሰው የሕይወቱ ማዕከል የሆነው አስተሳሰቡ ነው፡፡ ምነጩ ከደፈረሰ ወራጁ እንደማይጠራ አስተሳሰቡ የተበላሸም ከተግባሩ አይፀዳም፡፡ ልብ በደከመት ነገር አካል ሳይሰራ እንደሚደክመው ሁሉ ልብ ደስ ባለው ነገርም ሥጋ አይደክመውም፡፡ አስተሳሰባችን ቅዱስ ከሆነ መልካም ጌታ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ያሉን ነገሮች ሁሉም መልካም ሎሌዎች ይሆናሉ፡፡ ወታደር የራሱ ጠብ የለውም፡፡ራሱን ለማስከበር ጦር አያንቀሳቅስም፡፡ የመንግስቱ ጠብ የእርሱ ጠብ ነው፡፡ መንግስቱ የወደደውን ይቀበላል፡፡ አስተሳሰባችንም እንዲሁ ለአካላችን ለንብረታችን መንግስት ነው፡፡ አካላችን ንብረታችን ውስጣችን የገፋውን ይገፋል ፣ የተቀበለውንም ያገለግላል፡፡ ኒውክለር ቦንብ ለመስራት ኒውክለር ቦንቡን ማግኘት አይጠቅምም፡፡ ረቂቁን ፎርሙላ ግን ኒውክለር ቦንቡን ይሰራል፡፡ ረቂቁ የአለም መሰረት ፣ ረቂቁ የግዙፉ ነገር ገዢ ፣ ረቂቁ የታመቀ ሀይል ነው፡፡ መኖር የሚለካው ኖረን ካበቃን በኋላ አይደለም፡፡ የምንኖራት ሕይወት ምንነቷ የማይታወቅ ስንደርስ ብቻ እንድናውቃት ሆና የተዋቀረች አይደለችም፡፡ የምትለካ ሕይወትን ተቀብለናል፡፡ አውሮፕላን ማረፊያ ሔደን አንዱን መንገደኛ የት ነው የምትሔደው?? ብንለው:-"አላውቀውም ስደርስ ነው ማውቀው" ይለናል? በፍፁም አይለንም፡፡ መድረሻውን ካላወቀ መነሳት አይችልም፡፡ መድረሻውን የማያውቅ መንገደኛ ሳይሆን ተንከራታች ነው፡፡ መንገደኛ ሁሉ "የምሔደው እዚህ ሀገር ነው ፣ እግዚአብሔር ከፈቀደ በዚህ ሰዓት እደርሳለሁ" ብሎ ቦታውን ጠቅሶ ፣ ሰዓቱን ቆርጦ የሚናገር ነው፡፡ ሕይወት መንገድ ናት፡፡ የሕይወት መንገደኛም መድረሻውን ወይም ግቡን ወስኖ የሚናገር ነው፡፡ ወስኖ የሚያናግረንም ራዕይ ነው፡፡ ከቤት ስንወጣ የት እንደምንሔድ ወስነን ነው የምንወጣው ስለዚህ ጊዜአችንን ፣ ገንዘባችንን ፣ ጉልበታችንን ሳናባክን ካሰብንበት በቀላሉ እንደርሳለን የት እንደምንሔድ ሳንወስን ብንወጣ ግን በመንቀዋለል ሰዓቱ ያልቃል ፣ ገንዘብ ይባክናል ፣ ጉልበት ይዝላል፡፡ የት ልሒድ? ብሎ እንደመንቀዋለል የሚያስጨንቅ ነገር የለም፡፡ ራዕዬም ግቤም ይህ ነው ብለን የምናስቀምጠው መዳረሻ ነው፡፡በጉዞ፡መጀመሪያ ላይም አይታይም ጉዞአችንን በገፋን ቁጥር ግን የታየን ነገር መግዘፍ ይጀምራል፡፡ ይቀጥላል...... ከሁለተኛ መጽሐፍ አራተኛ ፅሁፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ መልካም ሰዎች እንሁን እኛን አይተው ሌሎችም መልካም ይሆናሉና! ቤታችን እንሁን እናንብብ!!! * ምልክት ያለበት እኔው እንደጨመርኩት ልብ ይባልልኝ @jahABP ነኝ ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ........በአጋጣሚ የምናገኛቸው ነገሮች አባካኝ ወይንም ደስታ የለሽ ፣ አሊያም እብዶች ያደርጉና፡፡ እንዲሁም ራዕይ የሌለበት ስኬት እርካታ የለውም፡፡ ሕይወት በመለኮታዊ እቅድ ያገኘናት በመሆኗ እንዲሁ የምንገፋት አይደለችም፡፡ እንኳን ያለ ራዕይ በራሳችን እቅድ እንኳን የምትገፋ አይደለችም፡፡ በመለኮታዊ እቅድ የተገኘች ሕይወት የምትመራውም በመለኮታዊ እቅድ ነው፡፡ ስለዚህ በአጋጣሚ ያልተገኘውን ህይወት በአጋጣሚ መኖር ከባድና ውስብስብ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ላይ አላማ አለው፡፡ የዓለም መሪዎች አላማቸው በሕዝቡ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ግን በእያንዳችን ላይ ዓላማ አለው፡፡ መንግስታት በብዙኀኑ ላይ ያላቸው አላማ ግለሰቦችን ላያይና ላይነካ ይችላል። ተዋረዱም/ፍሰቱም/ ከታች ወደላይ ነው። እግዚአብሔር ግን በእያንዳችን ላይ ያለው አላማ በህዝቡ ላይ ያለውን አላማ ይገልጣል፡፡ ተዋረዱም ከታች ወደላይ ነው፡፡ የእኛ ማንነትና የእኛ አቅም ግን ይህን አይ'ረዳውም፡፡ አጥንቱ የተሰበረ ሰው ለመጠገን አቅሙን ትቶ ለጠጋኙ ሐኪም ራሱን ማላላት አለበት፡፡ ከአሁን ሀይሉ ይልቅ ከመዳን በኋላ ያለው ብርታቱ ጠቃሚ ነው። እግዚአብሔርም ሕፃናትን ፣ ድሆችንና ስም የሌላቸውን ይጠራቸዋል፡፡ ከዛሬው አቅማችን እግዚአብሔር ባለ ዓላማ ሲያደርገን ያለን አቅም ይበልጣል፡፡ አንድ እቃ ስንገዛ አጠቃቀሙን የሚገልጥ ጽሁፍ ይሰጠናል፡፡ ጽሁፉን እያነበብን ዕቃውን በተሳካ ሁኔታ መጠቀም እንችላለን፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ሕይወትን ሲሰጠን ለአጠቃቀሙ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል። የእግዚአብሔር ቃል ያለው ህይወትን አቻችሎ መኖር ይችላል፡፡ ለብዙ ሰዎች ለምን እኖራለሁ? የሚለው ጥያቄ ከባድ ጥያቄ ነው፡፡ የምንኖርበት ምክንያት እግዚአብሔር ሲመልስልን ብቻ መኖር እንችላለን፡፡ አንድ ሰው፡- "ዓላማን በመፈለግ ዓላማ አይገኝም፡፡ እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለው አላማ ምንድነው? በማለት ግን ዓላማን ማግኘት ይቻላል" ብሏል፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሚሰጠው ስጦታ አንዱ ራዕይ ነው፡፡ እርሱ የራዕይ አምላክ ነው፡፡ ራዕይ በእግዚአብሔር ይጀመራል ፣ በእግዚአብሔር ይከናወናል ፣ በእግዚአብሔር ፣ ይፈፀማል፡፡ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በናይን አንድ ለእናቱ የነበረውንና የሞተውን ሬሳ አገኘ፡፡ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው አፈር ሊጭኑበት እየተጓዙ ነው፡፡ እናቲቱም እንዲቀበር ወስናለች፡፡ እምቢ የምትለው ለማልቀስ እንጂ እንዳይቀበር አልነበረም፡፡ ከዚህ በኋላ መውለድ የማትችል መበለት ናት፡፡ ከእርሷ በኋላ የተገኘው ልጅ ከእርሷ በፊት ሲሔድ አይታ አዝናለች፡፡ ጌታ ግን በመንገድ ላይ አገኛቸው፡፡ አብሮ አላለቀሰም፡፡ የሞት መድኃኒትነቱን መግለጥ ፈለገ፡፡ ቃሬዛውን የተሸከሙትን ቁሙ አላቸው፡፡ እናቲቱንም አታልቅሺ አላት፡፡ ለሞተውም ሰው በፍቅር ቃና "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ" አለው፡፡ የሞተውም ቀና አለ ለመጀመሪያ ጊዜ ሬሳ ለቅሶውን ሳይሰማ፡- "አንተ ጎበዝ" የሚለውን ድምፅ ሰማ፡፡ ሙትን ጎበዝ በሚል ስም መጥራት ያልተለመደ ነው፡፡ የሞተ ሰው ወዲያውኑ ስሙ ይሻራል ፤ ሬሳ ይባላል፡፡ ጌታ ግን በመቃብር አፋፍ ላይ፡- "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ" አለው፡፡ አሁን ላይ ብዙ ወጣቶች ተስፋ በመቁረጥ ውስጣቸው ሞቷል፡፡ ሳይቀበሩ ጉዞ አቁመዋል፡፡ ቤተሰብ ያዝናል፡፡ አካባቢው ቃሬዛ አሰናድቶ ሊቀብራቸው ይፈልጋል፡፡ ጌታ ግን በእነርሱ ውስጥ ያየው ነገር ስላለ፡- "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ" ይላቸዋል፡፡ እነርሱን በዛሬ ሳኦልነታቸው ሳይሆን በነገ ጳውሎስነታቸው የሚያይ ወዳጃችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በአለቀ ነገር መጀመር የሚችል ጉልበታም ፣ ከብሮም የሚያስከብር ንጉሥ ነው፡፡ ሰዎችን ከተኙበት ነገር የመቀስቀሻ ዘዴዎች በዘመናት የተለያየ ቅርፅ አላቸው፡፡ ይህንን በሦስት ዘመን ብናየው፡፡ 1) ባለፉት ዘመናት አንድ መንፈሰ ደካማን ወጣት ለመቀስቀስ ደደብ ፣ የማትረባ.....የሚለው ቃል ያነቃው ነበር፡፡ 2) በቅርብ ዘመናት እነ እገሌን አታይም የሚለው ማወዳደሪያ ቃል ያነቃዋል ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡ 3) አሁን ግን ገና ነው ፣ ትችላለህ ፣ በርታ የሚለው ድምጽ ያነቃዋል፡፡ ይባላል ስለዚህ ጌታ ያለው የዚህንም ዘመን ማንቂያ ነው፡፡ "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ"፡፡ ሚካኤል አንጀሎ አናጢዎች የጣሉትን ድንጋይ አንስቶ ሲቀጠቅጥ ጓደኛው ተመልክቶ ምን ይወጣዋል? ብለህ ነው የምትጠርበው ቢለው፡- "ውብ መልአክ አያለሁ" አለው፡፡ በብዙ ድካም ከቀረፀ በኋላ ያማረ መልአክ ቅርፅ ወጣ፡፡ ከመጥረብ በፊት ማየት ያስፈልጋል፡፡ ትልቁ ዋጋ ያለውም በማየት ውስጥ ነው፡፡ ያየ ሰው ድካሙን አይቆጥርም፡፡ ያየው ጋር እስኪደርስ ዕረፍት የለውም፡፡ ያየውን ለማየት ከሚደክመው ድካም ፣ ያየውን ታግሶ የሚቀመጠው ይከብድበታል፡፡ በመንገድ ስንሄድ ከሚታይ ቅርብ መንገድ ይልቅ የሚታየን ሩቁ መንገድ አጭር ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ወጣቶች ኃይል አላቸው ራዕይ ግን የላቸውም፡፡ ኃይል ከአራዊትም ብዙዎቹ አላቸው፡፡ ራዕይ ግን ስለሌላቸው በቀጣይ ዘመን አይታወሱም፡፡ የጋራ ስም እንጂ የተለየ የዝና ስም የላቸውም፡፡ ታሪክ በተጠና ቁጥር በዚያ ዘመን እነማን ነበሩ ለሚለው መልስ የሚሰጡ የዚያ ዘመን ባለ ራዕዮች ናቸው፡፡ ብዙ ወጣቶች መጀመር ይፈራሉ፡፡ ያለቀ ነገር ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ የድል ደስታን ስለማያገኙ ሕይወትን ይሰለቻሉ፡፡ ያለ ትግል ድልን ይመኛሉ መንፈሳቸውን ቀዝቃዛ ያደርጉታል በጅምሩም ፍፁም ነገርን በመፈለግ ራሳቸውን ከተፈጥሮ ግጭት ውስት ይከቱታል፡፡ ብዙ ወጣቶች ከትልቅ ቤተሰብ መወለድን ዳግመኛም ከጥበብ ጋር መወለድን ይመኛሉ ለራዕይ ግን የሚመቸው ከተስተካከለው የተዘበራረቀው ነው፡፡ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ፡- "ከትንሽ ወይም ከትልቅ መወለድ ሙያ አይደለም፡፡ ራስን ከትልቅ ሙያ መውለድ ግን እውነተኛ ሙያ ነው" ብለዋል፡፡ "ጎበዞቻችሁም ራዕይ ያያሉ" የሚለው ቃል ማራኪ ነው፡፡ ለጎበዝ የሚያስፈልገው ኃይል ሳይሆን ራዕይ ነው፡፡ ራዕይ የሌለበት ጉብዝና ከንቱ ጉብዝና ነው፡፡ መኪና ሀይል አለው፡፡ ኃይሉ ጠቃሚ የሚያደርገው መሪው ነው፡፡ ለትልቁ መኪና ፍፃሜውን የሚወስንለት መሪው እንጂ ኃይሉ አይደለም፡፡ ዛሬም ለትውልዳችን መልካም ግብ ከኃይል ይልቅ ራዕይ አስፈላጊ ነው፡፡ ከሁለተኛ መፅሐፍ ሦስተኛ ፅሁፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ ሁሌም ይሔን ፅሁፍ ሳነብ አንዳች ኃይል ውስጤ ይሞላል፡፡ ቤታችን እንሁን እናንብብ ያነበብነውን ተግባር ላይ አውለን እራሳችንን ብሎም ሌሎችን እንለውጥ፡፡ @jahABP ነኝ ማንኛውንም አስተያየታችሁን አድርሱኝ፡፡ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...