cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

Join @Rovibook 😎 <|> /\ 👢👢 መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው!! ለማንኛውም ማስታወቂያ ነክ ጉዳዮች @RASNAMRUD ያናግሩን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
29 711
Suscriptores
-1324 horas
-587 días
-32030 días
Archivo de publicaciones
#አዲስ_ቀን_አዲስ_ሰው! የታላቋ ኢትዮጵያ ታላላቅ ህልመኞች የማነቃቂያ እና የስብዕና ልህቀት ስልጠና ፕሮግራም። በአዲስ ዓመት የታደሰ መንፈስ ህይወታችንን በስኬት ሞልተን ወደታላቅነት እንድንሻገር፤ ስመ-ጥርና አንጋፋ የልቦና ውቅርና የስብዕና ዕድገት አሰልጣኞች የሚሳተፉበት ልዩ የማነቃቂያ እና የስብዕና ልህቀት ስልጠና በልዩ ድምቀት ይከናወናል። የትልቅ ህልምና የልቦና ውቅር አሰልጣኝ-ዳዊት ድሪምስ አንጋፋው የስራ ፈጠራ ጥበብ አሰልጣኝ- ዶ/ር ወሮታው በዛብህ የስብዕና እድገትና የስኬት ስነ ልቦና -ከኢንስፓየር ኢትዮጵያ ዳንኤል ወዳጆና ስነወርቅ ታዬ የስኬታማ ቢዝነስ ሚስጥሮች-ከአዲስ እይታ የተግባራዊ ቢዝነስ ስልጠና ማዕከል-ክብረት አካሳ እንዲሁም ተወዳጁ የአነቃቂ ንግግሮችና የስብዕና ዕድገት አሰልጣኝ ማንያዘዋል እሼቱ ...ሌሎችም የስኬታማነትና የታላቅነት ልምዳቸውን ያካፍላሉ: በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የጃዝ ሙዚቃ ቴራፒ በአንጋፋው ሙዚቀኛ ሻለቃ በፍቃዱ ሀይሌ ይቀርባል። ታላቅ ህልም ያለው ዜጋ ታላቅ ሀገር ይገነባል። ስብዕናን የሚያበለፅጉ ስልጠናዎችና የስራ ፈጠራ ጥበቦችን በማካበት ከራሳችን አልፈን ለሀገር: ከሀገርም ከፍ ብለን ለዓለም የምንተርፍ የላቀ ስብዕና ባለቤቶች እንሁን። ይምጡና በአዲስ ዓመት በአዲስ አስተሳሰብ እና በታደሰ ማንነት ወደ ታላቅነት ይሻገሩ። መስከረም 15 ቅዳሜ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በአምባሳደር ትያትር አይቀርም። የመግቢያ ዋጋ vip-300 መደበኛ 200 ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ 0925990099 አዘጋጅ ካሶጵያ ኤቨንትና ዴኮር ከአዲስ እይታ ጋር በመተባበር ሁሉም ቀን አዲስ: ሁሉም ሰው ታላቅ ነው! ኑ አብረን ወደ ታላቅነት እንሻገር! አዲስ ቀን አዲስ ሰው።
Mostrar todo...
ክፍል 2 ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ከወደውጪ ድምፅ ተሰማ፡፡ አስር አለቃ ጎረቤታቸውን በዱላ አናቱን ብለው በሩ ላይ ደፍተውት ነበር፡፡ ሰይጣን አጀንዳውን ይዞ አስር አለቃ ግቢ ሲደርስ ነገር ተደበላልቆ ጠበቀው፡፡ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራና አጀንዳው ላይ እንዲህ ሲል ከተበ "የአስር አለቃው ጉዳይ ከእቅድ በላይ ተፈፅሟል፡፡" ሦስት ፖሊሶች ኮሌታቸው ጨምድደው ወደያዟቸው አስር አለቃ ጆሮ ጠጋ አለና "አንተ ሸፋፋ! ስማ..! አሁን በግድያ ሙከራ ዘብጥያ ትወርዳለህ የተበደረው ጎረቤትህ ተሽሎት ወደ ቤቱ ይመለሳል..፡፡ ያች አንቋራሪ ልጅህም የትም ስታንቋር ር ስለምትውል ቤትህ ሰው የለም፡፡ ሚስትህና ጎረቤትህ ብቻቸውን እዚህ ሰፊ ግቢ ራስህ አልጋ ላይ...ሂሂሂሂሂሂ ቂቂቂቂቂቂ አይ ሸፋፋው!! ይልቅ ሚስትህን ዓይንህ እያየ ከምትወሰድ አንዱን ፖሊስ በካራቴ ድፋውና አምልጥ...ወታደር አይደለህ...? አስር አለቃ አይደለህ?.... ኮማንዶ ነኘ እያልክ በየጠላ ቤቱ ስታወራ አልነበር...? ወይስ ዝም ብለህ ስትወሽክ ነው...፡፡" አስር አለቃ ቀስ ብለው ከጎናቸው የቆመውን ፖሊስ ተመለከቱት፡፡ክስት ያለ ነው...በዛ ላይ የያዘው መሳሪያ የከበደው ይመስላል፡፡ ሁለቱም ፖሊሶች ቢሆኑ ያን ያህል የሚስፈሩ አይደሉም ቀድረ ቀላል ነገር ናቸው፡፡ " ይሔኔንንስ መሣሪያውንም መንጠቅ አያቅተኘ " ሲሉ አሰቡ፡፡ ፖሊሶቹ አስር አለቃን እያጣደፉ ወደ ጣቢያ ወሰዷቸው፡፡ ዷ....! ዷ............መንደርተኛው ከሩቅ የተኩስ ድምፅ ሰማ "ምንድነው....?" "እስረኛ ሊያመልጥ ሞክሮ.....ፖሊሶቹ እግሩን ሰንክለው አቆሙት.....! ሰይጣን በሳቅ ፍርስ አለ፡፡ እናም አጀንዳው ላይ እንዲህ ሲል ፃፈ "የእግሩ ጉዳይ አልቋል አሁን ነፍሱን ማንሻፈፍ ይቀረኛል!!" ከዛም ሰይጣን ቀይ እስኪሪቢቶ አወጣና እየተፍነከነከ እንዲህ ሲል ፃፈ "አስር አለቃ አምሳ አለቃ መቶ አለቃ ሻለቃ ጄነራል ሚኒስተር ...ጠቅላይ ሚኒስተር ሁሉም እግር አላቸው፡፡ እንኳን እነርሱ አገርም እግር አላት ስንፈልግ እናንሻፍፋታለን!!!" ደራሲ #አሌክስ_አብርሃም #ዙቤይዳ ከሚለው መፅሐፍ #እግር_በእግር ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ 😍😍😍🙏🙏🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY r.....for reflection ምስሉን ተጭነው ይመልከቱ 📸📸 ቴክኖ ስፓርክ kb ወንድሜ ስልክህን እንዳነሳበት ስለሰጠኸኘ አመሰግናለሁ😍😍🙏🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN #እግር_በእግር አንድ ቀን ሰይጣን በመንደሩ ወደሚፈሩት እና ወደ ሚከበሩት አስር አለቃ ደባልቄ ግዛው ቤት ሔደና ቀዳሚሚ ተከታይም ሳያደርግ "ደባልቄ!!" ብሎ በስማቸው ጠራቸው፡፡ አስር አለቃ ፊታቸውን በቁጣና በግርምት አኮማትረው ድምፁን ወደሰሙበት ዞር ቢሉ በአካባቢው ሰው የሚባል የለም፡፡ እዚህ ሰፈር አንድም ሰው የአስር አለቅነትን ማዕረጋቸው ሳያስቀድም የአባቻቸውን ስም ሳያስከትል እንዲህ ንፋስ እንዳነሳው ፌስታል ስማቸውን ለብቻው አንጠልጥሎ የሚነሳ ሰው የለም፡፡ እንኳን ሰው የዚህ ሰፈር ሰይጣን ቢሆን ራሱ እንደዚህ አስር አለቃን አቃሎ እና አበሻቅጦ ይጠራቸዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ እንዴት ሆኖ! ምን ሲደረግ...! እንግዲህ አስር አለቃ የተጣሉ ባልና ሚስት አስታርቀው ገና መመለሳቸው ነበር፡፡ ልክ በራቸው ላይ ሲደርሱ ነው ሰይጣን የጠራቸው፡፡ ምን ይጠራቸዋል ያዋረዳቸው እንጂ! ቢሆንም 'ጆሮዬ ነው' ብለው ወደ ቤታቸው ግቢ ሊገቡ ርምጃ ሲጀምሩ፣ "አንተ ደባልቄ ! የሚደባልቅ ይደባልቅህ! ሲጠሩ አትሰማም!? ደንቆሮ!!" ብሏቸው እርፍ፡፡ በዚህ ቢበቃማ ጥሩ ነበር "ምን ያራሩጥሃል? ያቺ መንሽ እግር ሚስትህ እንደሆነች የትም አትሔድብህ ተወዝፋ ነው የምትጠብቅህ" ሲል ዘለፋቸው፡፡ አስር አለቃ መጀመሪያ በተናጋሪው ድፍረት ግርርርርርርርርምምምምምም አላቸው ቀጥሎ የንግግሩ ትርጉም አዕምሮአቸው ውስጥ ሲተረጎም ደማቸው ፈላ፡፡ ላለፉት አርባ ዓመታት እንዲህ ተንቀውም እንዲህ ደማቸው ፈልቶም አያውቅም፡፡ ከዘራቸውን ጠበቅ አድርገው ጨበጡና ድምፁን ወደሰሙበት ፎክረው ዞሩ፡፡ "ያንበሳው ግልገል!" በአካባቢው የሰው ዘር የለም!! "እንኳን ፊቴ ያላገኘሁት ደመ ከልብ አድርጌው ዘብጥያ መውረዴ ነበር፡፡" አሉና ከዘራቸውን ወደ ግራ እጃቸው አጋብቸው ከዘራ በያዙበት እጃቸው አማተቡ፡፡ "ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ..." የሰይጣን የሚያበሳጭ እና የሚሰቀጥጥ ሳቅ ጆሮአቸው ሥር ተቅለጨለጨ....... " ድሮም ከእግዜራችሁ በፊት ዱላችሁ ነው ትዝ የሚላችሁ....ነውጠኛ ሁሉ.... #የምትዠልጠው_ስታጣ_ታማትባለህ? አይሸፋፋው አስር አለቃ....ሂሂሂሂሂ ሁሁሁሁ ቂቂቂቂቂ..." አለ ሰይጣን ግቢ ግቢያቸው ውስጥ ቀድሞ ገብቶ #ካሉበት_አርባ_ክንድ_ርቆ ከቆመ በኀላ፡፡ አስር አለቃ ግራ ተጋቡ፡፡ ንዴታቸውን ዋጥ አድርገው እየተጣደፉ በቁጣ ወደ ቤታቸው በር ገሰገሱ፡፡ አስር አለቃ አቋማቸው እንደሰምበሌጥ ቀጥ ያለ ስፖርተኛ አቋም ነው፡፡ ሰው ሁሉ "አቤት ቁመና!!" ይላቸው፡፡ ሰይጣን ግን ወደ ቤታቸው ሲጣደፉ የሚያበሽቅ ንግግር "ሸፋፋ ..ሸፋፋ ትላለህ! ሲራመዱ አይተህ...ደግሞ ወታደር ነኘ ይላል እንዴ? ይሄን ደጋን የመሰለ እግር ይዞ ሂሂሂሂሂሂ...እንኳን አገር ልትጠብቅ በዚህ ሸፋፋ እግርህ ሚስትህንም አትጠብቅ ተመልከት የእግርህን ክፍተት በልጅነትህ ፀሐይ አላሞቀችልህም ያቺ ጨብራራ እናትህ!!! ኪኪኪኪኪ..." አስር አለቃ ከሳቸው አልፎ እናታቸው ማዋረዱ ቢያንገበግባቸውም የተናጋሪው ማንነት ስለገባቸው እንደገና አማተቡና "የማርያምን ብቅል ፈጭቻለሁ ቱ! ቱ! ቱ! አንተ ፖለቲከኛ ሰይጣን!" ብለው ወደ መሬት አንዴ ወደሰማይ ትፍ! ትፍ! ቀጠል አድርገውም " አንተ ክፋ አውቄኻለው እንዲ አቅልሎ የሚጠራኘ እንዳንተ ያለው ቀላል እንጂ ሌላ እንደማይሆን መች አጣሁት?" ካሉ በኀላ ቆይ ላግኘህ ሚመስል ዛቻ ከዘራቸውን ነቀነቁና ነጠቅ ነጠቅ ብለው በመራመድ ወደቤታቸው ገቡ፡፡ ሰይጣንም አጀንዳውን ከፍቶ "አስር አለቃ ደባልቄ" በሚለው ፊት ለፊት በቀይ እስኪሪቢቶ 'ራይት' አደረገ፡፡ መንገዱንም ቀጠለ! እየሳቀ እና እያፏጨ...! ይሄ ሸፋፋ ለዛሬ ይበቃዋል ሲበሳጭ ይደር፡፡ ነገ ደሞ በተመቸኘ ሰዓት ብቅ ብዬ ነጅሼው እሔዳለሁ፡፡ አለና እየሳቀ መንገዱን ቀጠለ፡፡ አስር አለቃ ቤት ግራና ቀኘ ባሉት ጫት ቤቶች ተኮልኩለው ጫት የሚቅሙትን ወጣቶች በኩራት እየተመለከተ "ርስቴ እየተስፋፋ ነው!" ብሎ እየኮራ ቁልቁቅል ወደ ወንዙ! በእርግጥም ሰይጣን እንዳሰበው አስር አለቃ ሌሊቱን እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር ነበር ያደረው፡፡ እንደዛ ያበሻቀጣቸው ሰይጣን ነው ለማለት ጥርጣሬ ገባቸው "እኔ የትኛው ቅድስና ኖሮኘ ሊፈትነኘ ይመጣል?" አሉ ለራሳቸው፡፡ እንደውም አንዱ ጎረቤታቸው ተደብቆ እንደሰደባቸው ጠረጠሩ፡፡ "ማን ሊሆን ይችላል? ሌሊቱን ሙሉ ተብሰለሰሉ ፡፡ "ይች ጎረቤቴ የትነበርሽ ትሆን እንዴ? የለም ድምፁ የወንድ ነው፡፡ ግንበኛው አሰፋ መሆን አለበት እሱ ለካ ለሥራ ክፍለሃገር ከሄደ ሁለት ወሩ... እና ማናባቱ ነው...፡፡" ወደ ንጋቱ ላይ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላቸው፡፡ አረጋ!! ድንበር እየገፋ የበጠበጣቸው ጎረቤታቸው!! አረጋ! እሱስ ሚስታቸውን በምኞት ዓይኑ የሚቃኘ ጥጋበኛ ነው ድምፁ መጣላቸው ራሱ ነው! "አገኘሁት ብለው ዘለው ከአልጋቸው ተነሱ፡፡ ሚስታቸው እማማ የውብዳር በአስር አለቃ አነሳስ ደንግጠው "በስማም ምን ሆኑ? ሲሉ ጠየቁ "ዝም በይ ሸፋፋ!" ሲሉ ሚስታቸውን ሰደቧቸው ከሰይጣን በተዋሷት ያደረች ስድብ፡፡ አስር አለቃ ከዛ በፊት ሚስታቸው ሰድበው አያውቁም ነበር፡፡ ልብሳቸውን ለባብሰው እየተጣደፉ ሲወጡ ሚስታቸው አልጋው ላይ ሆነው አሰቡ "ይሔን ሁሉ ዘመን ዓይቶት የማያውቀውን የእግሬን መንሻፈፍ ዛሬ እንዴት ታየው? ምናልባት ወጣት ሴት ዓይቶ ይሆን? ማን ያውቃል ...? ባላቸውን ካገቧቸው ጀምሮ ዛሬ ገና ተጠራጠሩ፡፡ ልጃቸው ስንቄ እንደ ሁልጊዜው ከመኘታዋ ተነስታ እያንጎራገረች ነበር፡፡ ለሙዚቃ ከፍተኛ ፍቅር ያላት ስንቄ በተለይ የአስቴርን አወቀን ዘፈኖች ስትዘፍን ታስደምማለች፡፡ ዛሬ ግን እናቷ ድንገት አንባረቁባት "ወዲያ ዝም በይ! ምን በጧቱ ታንቋርሪብኛለሽ!" ስንቄ በእናቷ ንግግር ክፉኛ ተበሳጨች፡፡ እስከዛሬ ሲያንቋርር ነበር "የኔ ልጅ ድምጿ ብቻ የወፍ ዘር የሚያረግፍ..." እያሉ ዛሬ ታዲያ ምን ነካቸው? ስታምሰለስል ድንገት ጓደኛዋ ሊበን ደወለ፡፡ ዛሬ "ሰርፕራይዝ" ሊያደርጋት ጓደኞቹን አዘጋጅቶ እየጠበቃት ነው፡፡ እንድታገባው ሊጠይቃት ወስኗል ጓደኞቹ ጋር ቤቱ ቅልብጭ ያለ ፕሮግራም አዘጋችቶ ድንገት ሊነግራት የቃል ኪዳን ቀለበቱን አዘጋጅቶ በጉጉት እየጠበቃት ነው፡፡ "ሄሎ!" አለች እንደከፋት "ሄሎ...! ምነው ድምፅሽ?" አላት እንባ ተናንቋት ስለተናገረች ድምጿ በእርግጥም ድክም ብሎ ነበር፡፡ "ድምፄ ምን ሆነ? ስትል ጠየቀችው፡፡ "ተንቋረረ ልበል?" አላት ፈገግ ብሎ፡፡ ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችበት፡፡ ዘፋኘነትም ከዚህ በኀላ ዋጋ እንደሌለው ገባት፡፡ አርፋ የፀሀፊነት ሥራዋን ለመስራት ወሰነች፡፡ "አንቋራሪ ድምፅ " ያውም በእናቷና በምቶደው ፍቅረኛዋ የተመሰከረበት...፡፡ እስከዛሬ ሰው ፊት 'ስታንቋርር' ሁሌም ሲታዘባት በሹክሹክታ ሲቀልድባት እነንደኖረች ተሰማትና አፈረች!! ### ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ከወደውጪ ድምፅ ተሰማ........... ክፍል ሁለት ይቀጥላል #ካሉበት_አርባ_ክንድ_ርቆ ከቆመ በኀላ፡፡ እኔ እንደጨመርኩበት ልብ ይሏል @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ 😊😊😊😍😍🙏🙏
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN " #የተበላሸ_ማሞቂያ ጨርሰው የማይሰሩ አሳሳቢ አይደሉም አይሰሩምና ብልሽት ያለባቸው ማሞቂያዎች ግን ሰውየው ሲሞክራቸው ይሰራሉ ልብሱን አውልቆ ሲገባ ያረጥባሉ፡፡ ዓይኑን መግለጥ ከመታጠቢያው መውጣት በማይችልበት ሰዓት ሙቀታቸቅን መስጠት ያቆማሉ፡፡ ሰውየው በአይኑ ሳሙና ገብቷልና ልብሱን ለመልበስ እንኳን ከውሃ ያለፈ ገላውም ሳሙና ብቻ ነውና ማሞቂያው ስለተበላሸ የፈራውን ቅዝቃዜ የፈራውን እንቅጥቅጥ በግድ ይጋፈጣል፡፡ በሙቀት ጀምሮ በቅዝቃዜ በመጨረሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ የተበላሸ ማሞቂያ ሲገጥመን ሁል ጊዜ የወረት ያስታውሰናል በሙቀት ጀምሮ በቅዝቃዜ መጨረስ የዚህ ዓለም መገለጫ ሆኗል፡፡ በኡኡታ ሠርግ በግልግል ማሬ የሚለው ቃል እሬቴ በሚል....ይለወጣል፡፡ ጨርሰው ጨካኘ ፈጽመው ክፉ የሆኑትነ አንሞክራቸውም አንቀርባቸውም ብንቀርባቸውም ተጠንቅቀን ነውና አይጎዱንም፡፡ እነደተበላሸው ማሞቂያ በሙቀት ጀምረው በቅዝቃዜ የሚጨርሱ አረጋግተው ቀጥል የሚያንቀጠቅጡን ስሜት አልባ አድርገው ቀጥለው የሚያሳምሙ አስደስተው ቀጥሎ እትትትትት.....የሚያሰኙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ፍፁም እስክንራቆት ያባበሉን ሌላ ማየት እስከማንችል ያወሩን በማይዘልቀው ሙቀታቸው ያታለሉን የትም መሄድ እንደማንችል ሲረዱ ይለዋወጣሉ፡፡ በረዶአቸውን ማዝነብ ይጀምራሉ፡፡ ስለተለወጡብን ሰዎች ከማሰብ ስለተለወጥንባቸው ማሰብ የተሻለ ነው፡፡ በሞቀው ሰላምታ ጀምረን ያኮረፍናቸው ፍፁም ሚስጥራቸውን ከሰማን በኀላ ገሸሽ ያልናቸው ሌላ ማየት ሲያቅታቸው አውረን የተለየናቸው አውላላ ሜዳ ላይ መሪ ፈልገው ሲንከራተቱ የሳቅንባቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ምናልባት ዛሬ ሰው የማይወጣልን ሰው ገፍተን ሊሆን ይችላል፡፡ የዛሬውን የሚመጥነን ቅጣት ነውና በሚደርስብን ልንደሰት ይገባል፡፡ ትላንትን መልሰን መኖር ቢያቅተን በንሰሐ ማደስ እንችላለን፡፡ እነዚያንም ሰዎች መካስ እንችላለን፡፡ የንሰሐ የይቅርታ ዘመን ዕድል ነውና ሊያልፈን አይገባም፡፡ #ዛሬም_ከተለዋዋጭ_ማንነት_እንጠበቅ፡፡ #ሰው_እንጂ_አካባቢውን_የምንመስል_እስስት_አይደለንም፡፡ ጌታ ሆይ እውነተኛ ፍቅርን እንዳንገፋ እባክህን እርዳን፡፡ " @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ምሽት @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN " #አትድገሙ ክፉ ነገር በማሰብ ይጀምራል፡፡ በማድረግ ይደመደማል፡፡ ማሰብ ለክፋት ፅንሰቱ ማድረግ ልደቱ ነው፡፡ ክፉ ነገር በማድረግ እየተገለጠ ይመጣል፡፡ ክፉ ነገርን የጦር ኀይል የፍርድ ጽናት የቅጣት ብዛት አያስቆመውም፡፡ክፉ ማሰብ ባለቤቱን ይበክላል ክፉ መናገር የጎረቤትን ሰላም ያናጋል አዕምሮን ያቆሽሻል ክፉ ማድረግ ማድረግ ማህበረሰብን ይጎዳል ያፈናቅላል፡፡ ክፉን መድገም ያደነድናል፡፡ #ያለመውደቅን_ያህል_ወድቆ_መነሳት_ክብር_ነው፡፡ የማይወድቅ የለም መልዐክ ካልሆነ የማፀፀት የለም ሰይጣን ካልሆነ፡፡ መድገም ማስተጋባት ነው፡፡ የሌሎችን ክፋት ማወደስ ለክፋት በነፃ ማስታወቂያ መስራት ነው፡፡ ሳይከፍሉን በቅዱስ አደባባይ ርኩስ ማስታወቂያ መስራት ነው፡፡ አንድ ጊዜ ክፉ ነገርን ከሚፈፅሙለት ይልቅ ደግመው በሚያወሩለት ሰይጣን ይደሰታል፡፡ ኃጢያት በተግባር ከሚፈፅሙ በምኞትና በትዝታ የሚጨልጡ ይበዙለታል፡፡ ሰው ነንና ክፉ ነገር እናስብ ይሆናል አለመናገር መልካም ነው፡፡ ሰው ነንና ተናግረን ይሆናል አለማድረግ ግን የተሻለ ነው ሰው ነንና አድርገን ይሆናል አለመድገም ግን መልካም ነው፡፡ መድገም መስራት ብቻ ሳይሆን ማስተዋወቅም ነው፡፡ ነገሩን ደግሞ ማውራት አይገባም፡፡ አዝረከርካለው ያልነውን ጉዳይ አንሰራፍተነው ሊሆን ይችላል፡፡ መድገም ብዙ ደቀመዝሙርትን ያፈራል፡፡ "ክፉ ነገርን አትናገሩ ደግማችሁም አታውሩ" ለምን ስንል፡- ያደረገ ካለ ይደፍራል ያሰበ ካለይፈፅማል የጀመረ ካለ ብቻዬን አይደለሁም ይላል የፈራ ካለ ልብ ያገኛል አደራረጉ የጠፋው ካለ ስልቱን ያገኛል፡፡ ክፋ ነገርን እግዚአብሔር ይገስፅህ በማለት መቅበር ያስፈልጋል፡፡ ዝርዝር ማውራት ለሴጣን ስፖንሰር መሆን ነው፡፡ ይህን ለመገንዘብ መንፈሳዊ ሰው ብቻ ሳይሆን ጨዋ አስተዳደግም በቂ ነው፡፡ #እጅግ_ግልፅነት_እብደት_ነው፡፡ ሰይጣን ዋንኛ ስራ ጆሮን ማስለመድ ነው፡፡ ጆሮን ማስለመድ የፖለቲካ ትልቅ ስልት ነው፡፡ የክፉዎች ትልቅ መንገድ ነው፡፡ ጆሮ ከለመደው አፈፃፀሙ ቀላል ነው፡፡ የምንናገረውን ሰዎች ይለማመዱታል ማስደንበርን ነው የምንፈራው ከዛም የተለየ ነገር አለ፡፡ ብዙ ክፉ ድርጊቶች ሲወሩ ይብሳሉ፡፡ ዝርዝር የሚወራው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ዛሬ ግን አጋንትን እያስለፈለፉ ትምህርት እንሰጣለን እየተባለ ነው፡፡ የሐሰት አባት ከተባለው የእውነት መረጃ እየተፈለገ ነው፡፡ ስብከት ሲያልቅብን ወደዚህ መግባታችን ያሳዝናል፡፡" "መጥፎን ነገር እንደምንጠላ የሚያረጋግጥልን ስራችን ብቻ ነው" እና ከክፉ እንራቅ መልካምነትን እንዝራ እላለሁ @jahABP ነኘ አሰተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ጊዜ ተመኘሁ፡፡ 😍😁👍🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN #ስውር_አይን የመርሐ ግብሩ መሪ እኒያን ሊቅ ሲያስተዋውቅ "በአይነ ሥውር አቅማቸው ይህን ሁሉ ትምህርት ተምረው ይህም ያህል ደቀ መዛሙርት አፍርተው.....እያለ በእርሱ አመለካከት ማድነቅ ያለውን ነገር አወረደው፡፡ ሊቁ ግን ሲነሱ:- "ይህ ወንድሜ ያለውን ሰምቻለሁ ፡፡ በዓይነ ስውር አቅማቸው.......ብሏል፡፡ ወንድሜ #አምፑል ተቃጠለ ማለት መብራት ሄደ ማለት አይደለም ዓይነ ስውር ማለት የሳሎኑን መብራት አጥፍቶ የጓዳውን አብርቶ የተቀመጠ ነው ብለዋል፡፡...."፡፡በእርግጥም ሊቅ ናቸው፡፡ የሚንከባለል ዓይን ያለው አብዛኛው ሰው የጓዳውን አጥፍቶ የሳሎኑን አብርቶ የተቀመጠ ነው፡፡ የላይኛው ዓይን አምፑል ነው፡፡ አምፑል የሚሰራው በራሱ አይደለም ዓይንም ያለ ልብ ከኃይል ምንጩ እንደተለያየ አምፑል ነው፡፡ ማስተዋል ከሌለ የላይኛው ዓይን ከጌጥነት አያልፍም፡፡ እግዚአብሔር የሠራውን ለማድነቅ የወደቁ ሰዎችን ለማንሳት ወዳጆችን በፍቅር ለመመልከት.....የሚያገለግለው የውስጥ ዓይን እንጂ የውጭ አይን አይደለም፡፡ ጌታችን ወደዚህ ዓለም የመጣው እያዩ የማያዩትን እናያለን እያሉ የማያስተውሉትን ሳያዩ እንመራለን የሚሉትን ለመውቀስ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚታየው እውነት የሚገኘው በውስጥ ዓይን እንጂ በላይ ዓይን አይደለም፡፡ ወደ ተመስጦ ስንገባ ዓይናችንን እንጨፍናለን፡፡ የላይኛው ዓይን ባካና ያደርጋል፡፡ ለኅሊና የቤት ስራ እየያዘ ይመጣል፡፡ የቀደሙት አባቶች የቋንቋ እውቀታቸው ይደንቃል፡፡ ሲሰይሙ "ዓይነ ስውር" ብለዋል፡፡ ሥውር አይን ያለው ማለት ነው፡፡ አንዱ የግልፅ አንዱ የውስጥ ዓይን ተደርጎለታል ማለት ነው፡፡ የላይኛው ዓይን ማጣት ሳይከለክላቸው ብዙ ታላላቅ ሥራ የሠሩ ሊቃውንትን ይቺህ ዓለም አስተናግዳለች፡፡ የላይኛውን ብርሃን ማጣት ኃጢያት አይደለም፡፡ በውስጥ ጨለማ ተዝናትቶ መቀመጥ ግን ሀጢያት ነው፡፡ የላይኛው በተዓምራት ይወገዳል የውስጥ ጨለማ ግን ያለትምህርትና እምነት አይወገድም፡፡ ዓይን ተመልሳ እራሷን አይታ አታውቅም፡፡ ሌሎችን ታያለች ራሷን ግን አታይም፡፡ ሌሎች ያጎደሉት ትገመግማለች የራሷን ግን አታውቀውም፡፡ የላኘኛዋ ዓይን ለሌሎች የሆነውን እያየች #ቅንዓትን የሌሎችን ሰላም እያየች #ምቀኘነት የሌሎችን መውደቅ እያየች #ፍርድን የሌሎች ርኩሰት እያየች #ውድቀትን ይዛ ትመጣለች፡፡ #በላይኛው_አይን_ብቻ_ማልቀስ_አይቻልም በመንገድ ላይ እናቶቻችን "እያዩኘ ሰላም ሳችሉኘ አለፉ" ስንላቸው የተለመደ መልስ ይሰጣሉ፡- "አይ ልጄ የሚያየው ልብ እንጂ ዓይን መሰለህ?" ይላሉ፡፡ ትልቁ ብርሃን ያለው ልብ ላይ ነው፡፡ የልብ ብርሃን ከጨለመ የላይኛው አይቶ #መርገጥ አይቶ #መጠንቀቅ አይቶ #ማዘን አይችልም፡፡ ሥውር ዓይን ያስፈልጋል፡፡ ሥውር ዓይን ሲኖረን:- ✿ ያለንን እናውቃለን፡፡ ስለጎደለን የምንጨነቀው ያለንን በትክክል ስላላወቅን ነው፡፡ ✿እግዚአብሔር ዛሬም በሥራ ላይ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ ተስፋችን ይታደሳል፡፡ ✿ በአሁኑ ሁኔታ ሕይወትን አንመዝን፡፡ አሁን ያለው ደግም ይሁን ክፉ እርሱ መጨረሻችን አይደለም፡፡ #የሚመጣው_የሚልቀው_ነው፡፡ ✿ ለጎዱን ሳይቀር በችግራቸው እንገኛለን፡፡ ✿ በተገፉት ላይ አንጨክንም፡፡ ዓለም ተራ መሆኑ ይገባናል፡፡ ✿ ለሌሎች ማካፈል አንረሳም፡፡ ሌሎች እኛ ጋ ድርሻ አላቸው፡፡ ✿ አንደበታችንን እንገዛለን፡፡ መልካሙን ቀን ለማየት አንደበትን መቆጣጠር ያስፈልጋልና፡፡ እርሱ ሥውር አይን ይፍጠርልን🙏🙏🙏😊😊 @jahABP ነኘ ሳነብ ካገኘሁት መልካም ሰዎችን ይገልፃል ብዬ አሰብኩና እንዲህ አቀረብኩት፡፡ 😍ክብር ይስጥልኘ🙏 አስተያየታችሁን አድርሱኘ፡፡ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
እንኳን ለብረሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሰህ በአሉ የሰላም የፍቅር ያንድነት በአል ይሁንልን መልካም በአል!
Mostrar todo...
#የጭቃ_ውስጥ_አበባ የሚለው መፅሀፌን በጃፋር ፣ ሰዓዳ እና አይናለም መፅሀፍ መደብር ያገኙታል። የ90ዎቹ ልጆችን እድገት ፣ ስራ ፣ ፍቅር እና የወሲብ ህይወት ይዳስሳል።
Mostrar todo...
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ
Mostrar todo...
🌼መ🌼 🌾ል🌾 🍃ካ🍃 🍂ም🍂 🌾🌾🌾ገና🌾🌾🌾 💥በ💥 💫አ💫 ✨ሉ✨ 💚የሰላም💚 💛💛የፍቅር💛💛 ❤❤የደስታ❤ይሁንሎት!!
Mostrar todo...
እንደምን አመሻችሁ የመፅሐፍት ዓለም ቤተሰቦች ለትረካ ስራ በአካል ተወዳዳሪዎች የነበራችሁ ስለመጣችሁ ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን አሁን ውጤቶችሁን የምንገለገልበት ስዓት ነው ከዛ በፊት 2ነገሮችን ልበል 1ኛ በሆንላይን(@heny10)ላይ ከአሜን ባሻገር ገፅ 33 እያነባችሁ የላካችሁልኝ ልጆች ውጤት ገና ነው ስለዚህም ይሄ ውጤት እናንተን አያካትትም 2ኛ በአካል ስቱዲዮ መጥታችሁ ድምፃችሁን ወስደን የዛሬው ውጤት ላይ ያላለፋችሁ ግን መተረክ እምትፈልጉ ልጆች ደስ እያለን እንቀበላቸዋለን (ክፍያ ለጊዜው ባይኖረውም የምንቀጥራቸው ልጆች በሌሉበት ሠዓት እናንተ በክፍያ ግን ትሰራላችሁ ) ስለዚህም ከዚ በታች ያላችሁ ልጆች ለቀጣዩ ለመጨረሻ ዙር አልፋችኋል 1ኛ ቤተሌሄም ይመር 2ኛ ሀይለሚካሄል ዳንሄል 3 ዮናስ አይናለም 4ኛ ታደለ ሽመልስ 5ኛ እየሩሳሌም ሰለሞን 6ኛ ምስክር አበራ 7ኛ ሳሙኤል ጌታቸዉ 8ኛ ሱራፌል ሙልዬ 9ኛ ትዕግሥት አበበ 10 ብሩክ ጫላ እናመሰግናለን ሁላችንም ስለዚህ ከላይ ስማችሁ የጠቀስኩት ቀጣይ ፈተና ይኖራል ስለሁሉም ከልብ እናመሰግናለን ። ለማንኛውም ጥያቄ 📞+251938753747 ✍ @heny10
Mostrar todo...
እንደምን አላችሁ ለትረካ የተወዳደራችሁ ውጤት ስላዘገየን ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅን አሀድ ማታ የምናሰማውቅ መሆኑን እንገልፃለን ።
Mostrar todo...
ሠላም የመፀሀፍት ዓለም ቤተሰቦች ከዚህ በፊት ያወጣነውን የመፅሐፍ ትረካ የስራ ማስታወቂያ ብዙ ሰዎች አመልክታችዋል እናም ለፈተና ያለፋችሁ ነገ ስለሆነ ጠዋት ከ4ሠዓት እስከ 5ሠዓት ድረስ 6ኪሎ መነን ትህምርት አካባቢ መጥታችሁ ፈተናውን መውሰድ ትችላላችሁ ቦታው ላይ ስትደርሱ በዚ ስልክ መደወል ትችላላችሁ +251938753747 ያልተመዘገባችሁ እና በትረካ መስራት እምተፈልጉ ዛሬ የመጨረሻ መመዝገቢያ ነው። አርፋጅ አንቀበልም !!!
Mostrar todo...
የስራ ማስታወቂያ ከመፅሀፋት አለም የቴሌግራም ቻናል ሞባይላችንን በመጠቀም ብቻ መፅሀፍቶችን መገበያያ አፕሊኬሽን ከአዲስ ታግ ሶፍትዌር ዴቨሎፐር ጋር በጋራ መተግበሪያ ሰርተናል ስለዚህም ፕለይ ስቶር ላይ እና አፕ ስቶር ላይ እያወረዳችሁ እንድትጠቀሙ እንጠይቃለን ብርሀን ቡክስ (Birhan Books )ይሰኛል ።ስለዚህም በሰራነው የመጽሐፍ መገበያያ ላይ ለለሚለቀቁት የመፅሀፋት ትረካዎች ወንድ እና ሴት ተራኪዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ሰለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት ከስር ባስቀመጥንላችሁ የቴሌግራም አድራሻ እንድታመለክቱ ይሁን። ቀኑ ካለፈ ቡሀላ የሚመጣ አመልካች ተቀባይነት አይኖረውም። ተራኪ/ተራኪት እድሜ 18-30 ጾታ ወንድ/ሴት የስራ ቦታ አአ የስራ ስዓት በትርፍ ሰዓት (አብዛኛውን ጊዜ ቅዳሜ እና እሁድ) ደሞዝ በተረኩት የመጽሐፍ ብዛት የቅጥር ሁኔታ በኮንትራት የትምህርት ደረጃ ማንበብ እና መጻፍ የሚችል/የምትችል ለመመዝገብ የሚያስችሉ መስፈርቶች ሙሉ ስም እስከ አያት እድሜ ሲያነብ/ስታነብ ጥሩ ድምጽ የለው/የላት የመመዝገቢያ አድራሻ @heny10(0938753747) ላይ ይላኩልን ተጨማሪ ከመፅፈት አለም ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በብዙ አዳዲስና ተወዳጅ ፕሮግራሞች ጋር እንመጣለን እናንተም መሳተፍ ከፈለጋቹ አናግሩኝ @heny10(+251938753747)አብረን ጥሩ እናደርጋለን ። መልካም ጊዜ
Mostrar todo...
የስራ ማስታወቂያ ከመፅሀፋት አለም የቴሌግራም ቻናል ሞባይላችንን በመጠቀም ብቻ መፅሀፍቶችን መገበያያ አፕሊኬሽን ከአዲስ ታግ ሶፍትዌር ዴቨሎፐር ጋር በጋራ መተግበሪያ ሰርተናል ስለዚህም ፕለይ ስቶር ላይ እና አፕ ስቶር ላይ እያወረዳችሁ እንድትጠቀሙ እንጠይቃለን ብርሀን ቡክስ (Birhan Books )ይሰኛል ።ስለዚህም በሰራነው የመጽሐፍ መገበያያ ላይ ለለሚለቀቁት የመፅሀፋት ትረካዎች ወንድ እና ሴት ተራኪዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ሰለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት ከስር ባስቀመጥንላችሁ የቴሌግራም አድራሻ እንድታመለክቱ ይሁን። ቀኑ ካለፈ ቡሀላ የሚመጣ አመልካች ተቀባይነት አይኖረውም። ተራኪ/ተራኪት እድሜ 18-30 ጾታ ወንድ/ሴት የስራ ቦታ አአ የስራ ስዓት በትርፍ ሰዓት (አብዛኛውን ጊዜ ቅዳሜ እና እሁድ) ደሞዝ በተረኩት የመጽሐፍ ብዛት የቅጥር ሁኔታ በኮንትራት የትምህርት ደረጃ ማንበብ እና መጻፍ የሚችል/የምትችል ለመመዝገብ የሚያስችሉ መስፈርቶች ሙሉ ስም እስከ አያት እድሜ ሲያነብ/ስታነብ ጥሩ ድምጽ የለው/የላት የመመዝገቢያ አድራሻ @heny10(0938753747) ላይ ይላኩልን ተጨማሪ ከመፅፈት አለም ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በብዙ አዳዲስና ተወዳጅ ፕሮግራሞች ጋር እንመጣለን እናንተም መሳተፍ ከፈለጋቹ አናግሩኝ @heny10(+251938753747)አብረን ጥሩ እናደርጋለን ። መልካም ጊዜ
Mostrar todo...
ሄሎ ታክሲ - Hello Taxi ያጋሩ ይሸለሙ 🚖 የሄሎ ታክሲ የያጋሩ ይሸለሙ መልዕክት ለሄሎ ታክሲ ተጠቃሚዎችና ለቴሌግራም ተከታዮቻችን የቀረበ ታላቅ ስጦታ በታህሳስ ወር ከቀረጥ ነፃ ከሚገቡ መኪኖቻችን ውስጥ 2019/20 ሞዴል የሆነ ውሊንግባስ ኤስ ባለ 7 መቀመጫ መኪና እና ሌሎች ሥጦታዎችን ለተወዳዳሪዎች ለመሸለም ተዘጋጅተናል። 1ኛ. ለ 1 (አንድ) ባለ እድለኛ 2019/20 ውሊንግ ባስ ባለ 7 መቀመጫ መኪና 2ኛ. ለ 50 ባለ እድለኞች Samsung A10s ሞባይል እና የ ሄሎ ታክሲ ነፃ የጉዞ miles ስጦታ 3ኛ. ለ 50 ባለ እድለኞች የ 500miles ነፃ ጉዞ እንዲሁም የሞባይል ካርድ እና ሌሎች አጓጊ ሥጦታዎች ያስተውሉ በውድድሩ ዕጩ ለመሆን መጀመርያ በጥንቃቄ ያንብቡና፤ መመሪያውን ይከተሉ። ለመሸለም ይህንን መንገድ ይከተሉ፦ 1.መጀመርያ ከታች ባለው ማስፈንጠርያ (link) የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE7dMzPWA9bnFVH0jA (የሄሎ ታክሲ Telegram channel አባል ይሁኑ) 2. ይህንን Post Like 👍 ያድርጉ። 3. በመቀጠል ለ 50 ወዳጅ ዘመድዎ ይህን መልዕክት በፍጥነት ሼር ( Forward) ያድርጉ (ለበርካታ ወዳጅዎ ሼር ሲያደርጉ የማሸነፍ እድልዎ የሰፋ ነው።) 4. እስከ ታህሰስ 1 ድረስ የሽልማቱ አሸናፊ ይሁኑ ! መልካም እድል! አሸናፊዎችን በ ሄሎ ታክሲ @Hello_Taxi የቴሌግራም ቻናላችን ላይ የምንገልፅ ይሆናል። የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን በሰይፉ ሾው ላይ የሚቀርብ ይሆናል። ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ። መልካም ዕድል Hello Taxi A Company with passion! Join us @Hello_Taxi @Hello_taxi
Mostrar todo...
ሰማሺኝ አለሜ ? መሄድ እሚሉት ቃል ፥ ከሀገር የሰፋ የትርጉም ኩታንኩት ፥ ጉንጭን እሚያለፋ መሄድ ሲሉ ሰምተሽ ! እንደ ያሬድ ዜማ ፥ እንደ እግዜር ያለ እረፍት እንደ ቀን ቅዳሴ ፥ እንደ ሌ'ት ማህሌት የ 6 ቀን እድሜ ፥ በ 60 አመት ሀሳብ ያ'ንድ ቅፅበት ቀመር ፥ እንደ ህያው ጥበብ ያነፅነውን ፍቅር ! ባ'ንድ የስልክ ጩኸት ፥ ባ'ልፈልግህም ቃል ፍቅርሽን ገፈሺኝ ፥ እኔነቴ ወልቋል የመውደድ ግርማዬ ፥ በሀፍረት ተራቁቷል ። ሰማሺኝ አለሜ ? መሄድ የሚሉት ቃል ፥ የማጣት ታላቁ የክፋቱ ክፋት ፥ ከኔ አንቺን ማራቁ ባ'ንቺ 1 መሄድ ውስጥ ፥ ሺ ጥሎኝ የሄደ ክንድሽ ያረፈበት ፥ ጎኔ እየነደደ አቅሜ እንዳለልነበርሽ ዛሬ አቅም ቢከዳኝ አካሌ እየራደ መሄድሽን ረግማለሁ ! ደግሞ እጠይቃለሁ ? በቅተኸኛል ያልሺን ፥ በባዶ ሀሳቤ በተጎሳቆለው ፥ በድኩም ምናቤ ቢመላለስብኝ ልክ እንደ እግዚኦታ ፥ እንደ ቤተስኪያን ደውል፥ አንገቴን ደፋለሁ አፍጦ ከሚያየኝ አቧራ መሬት ላይ ፥ መልስ እጠብቃለሁ ሰማሺኝ አለሜ 👂 ባ'ንቺ መሳቅ ቀኔ በርቶ ፥ በሀዘንሽ ሲጠፋብኝ እውር ልቤ ባንቺነትሽ ፥ እንደሚያይ ሰው ሲዘልብኝ ተዚያ ተቤተስኪን ፥ ከመላዕክት መቅደስ ፦ ከእግዜሩ ደጃፍ እነኛን ጥዑም ቀን ፥ በመዋደድ ቅኔ ፥ አብረን ስናሳልፍ እጅሽ እጄን ይዞ ፥ የተባባልነው ቃል የልጆቻችን ስም ፥ ማን ትባል ማን ይባል እንዳልነተረኩሽ ፥ እንዳልጨቀጨቅሺኝ ዛሬ ግን የለሽም ፥ ብቻዬን ከ እግዜር ጋ ፥ ሄደሻል ጥለሺኝ ! ሰማሺኝ አለሜ ? መሄዱንስ ሂጂ ፥ ብርሀን ይነጠፍልሽ ይቃናልሽ መንገድ ፥ ክንፈ መላዕክት ይጠብቅሽ ደግሜ ልሻለሁ ፥ ይቅናልሽ መንገዱ ሊያገኝሽ ይጋደል ፥ ይሙትልሽ ወንዱ ሌሊቱ እንዲረዝም ፥ እያልኩኝ ባልነጋ እኔ ግን አለሁኝ ፥ ተኝቼ እየቃዠሁ በትዝታሽ አልጋ ሰርክ እየደነገጥኩ ፥ ሰርክ እየባነንኩኝ የመሄድሽን ህልም ፥ ልትመጣ ነው በሚል ፥ 😚እየተረጎምኩኝ እኔ ግን አለሁኝ በትዝታሽ አልጋ ፥ ላልነቃ ተኝቼ መሄድሽን ላልወቅስ ፥ ስላ'ንቺ ልሸነፍ ፥ ምዬ ተገዝቼ
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN " እውነተኛ ግርዶሽ ሐሰተኛ ኑር ያደክማል ፣ እውነተኛ ኑሮ ከራስ ጋር ሰላም ያደርጋል፡፡ እውነተኛ ኑሮ የምትኖረው እግዚአብሔር እንዳለና ስራህን እንደሚመዝን ስታምን ነው፡፡ ነፃነት ጨዋነት ከሌለው ተዘዋዋሪ ባርነት ነው፡፡ ስጋን ከሚገርፉ ገዢዎች ነጻ አውጥተን ነፍስን በሚገዙ አጋንት እጅ የወደቀን ትውልድ ካፈራን የምናሳዝን ነን፡፡ "ከእባብ ጉድጓድ አምልጦ ዘንዶ ጉድጓድ" እንዲሉ አበው፡፡ ዓላማ የሌለው ጉዞ መንከራተት ነው፡፡ በውስጥህ ያለው የሕሊና ሕግ ፣ በመፅሐፍ ያለው የእግዚአብሔር ሕግ በልብህና በተግባርህ *#እንድትገልጠው የተሰጡህ ናቸው፡፡ ስለእግዚአብሔር ለማወቅ በፈለግህ መጠን ወዳጅነትህ እየጨመረ ይመጣል፡፡ #አምላክ_ላይሆኑ_አምላክህን_ያሳጡህን_አትርሳቸው፡፡ ፍልስፍናዎች ፣ ርዕዮተ አለሞች ፣ የበላይ አለቆች ፣ የጦር መሳሪያዎች ፣ የሀብት ጅልቦች ፣ *#ዘረኘነት እነዚህ ሁሉ አምላክ ላይሆኑ ስንቱን አምላክ እንዳሳጡት እወቅ፡፡ #ሰው_ላይሆኑ_ሰው_ያሳጡህንም_አትርሳ፡፡ አለመርሳት ማለት ማለትም ለቀጣዩ ተጠንቀቅ ማለት ነው፡፡ ኅሊናህን ቸል ብለህ ሰዎችን ወዳጅ ለማድረግ አታስብ፡፡ የጠፋ ማህበረሰብ የሚወለደው ከአሉታዊ ነፃነት ውስጥ ነው፡፡ አሉታዊ ነፃነት ልቅነት ነው፡፡ አዎንታዊ ነጻነትን ግን የመናገር ፣ የመኖር ፣ አሳብን የመግለጥ ፣ የወደዱትን ማመን ፣ የእኩልነት እግዚአብሔር የሰጠውን የፆታና የዕድሜ መብብ የሚያከብር ነው፡፡ #የተፈፀሙ_ነገሮች_የተጀመሩ_ነገሮች_ናቸውና ለመጀመር ተነሳ፡፡ የተጀመሩት ይፈፀማሉና ፍፄሜውን አትፍራ፡፡ ቅዱስ መልዓክ ላንተ ያስፈልግኃል ለደካማውም ሰው አንተ ታስፈልገዋለህ፡፡ ከቆመው መልዓክ የወደቀውን ሰው ሊፈልግ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡ የአምላክ እናትን ባሰብክ ጊዜ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን የላቀ ክብር ትረዳለህ፡፡ የህሊናን ድምፅ ጠንቅቀህ የምትመሰርተው ወዳጅነት ራስን ማጥፋት ነው፡፡ በነፍስህ ዋስትና የሌለበት ሀብት በሬሳ አጠገብ እንደተቀመጠ ጥሩ መዓዛ ያለው ምግብ ነው፡፡ ተገፋን ብለው ወደ አንተ ሚመጡ ሰዎች ምን ሰርተው ወደአንተ እንደ መጡ አጥና፡፡ ጅብ የማያቁት አገር ሂዶ ቁርበት አንጥፋልኘ ይላል" ይባላል፡፡ ከሁሉ ፀያፍ ነገር ሃይማኖትለዋጭነት እንደሆነ እወቅ፡፡ እግዚአብሔር በድንጋይ ጽላት ላይ ቃሉን ቀርጾ የሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ዘመን የማይሽረው መሆኑን ሊያስተምረን ነው፡፡ ስነምግባር ስታጣ የምታሳድበው እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን አሳዳጊዎችንህም ነው፡፡ #የመጨረሻው_ድህነት_እግዚአብሔርን_ማጣት ነው፡፡ #የመጨረሻ_ብልጥግናም_እግዚአብሔርን_ማግኘት_ነው፡፡ እንደገና የቀረ የለምና አትመካ ፣ እንደ መሸ የቀረ ሌሊት የለምና አትሸማቀቅ፡፡ የምትችለውን ማድረግ የማትችለውን ለማድረግ መንደርደሪያ ነው፡፡ እውነተኛ የሀብት ውድድር በማጠራቅ ሳይሆን በመስጠት ከሆነ ደስታ አለው፡፡ #በእግዚአብሔር_መንግስት_ምን_ያህል_አጠቀምክ_ሳይሆን_ምንያህል_ሰጠህ_ትባላለህ፡፡ የማይሰጥ ባለጠጋ ድሃ ነው፡፡ ደሃ ሁለት አይነት ነው፡፡ የገንዘብና የቸርነት ድሃ፡፡ ከቸርነት ድህነት የገንዘብ ድህነት ይሻላል፡፡ ከባድ እስር ቤት በራስ አመለካከት መታጠር ነው፡፡ የሚያቆስለው ሰንሰለትም የመሰስትም እጅ ነው #የጨለማም_ወህኒም_ማፍቀር አለመቻል ነው፡፡ ዓለም ማለት በጎሬህ መጠን በሰፈርህ ልክ ከመሰለህ ዘረኛ ሆነኃል ማለት ነው፡፡ ዘረኘነት ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት መግጠም ነው፡፡ ምክንያቱም ስለ ዘሩ የምትጠላው ያ ሰው ከዚያ ዘር ለመውለድ ያቀረበው አሳብ የለምና፡፡ #እውነተኛ_እውርነት_ፀሀይን_ሳይሆን_የፀሀይን_ጌታ_ማየት_አለመቻል_ነው፡፡" መልካም ምሽት @jahABP ነኘ 😊😍🙏 መልካምነት ደግነት በተግባር እንግለፃቸው ከትላንትናው መፅሐፍ ላይ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት *# ምልክት ያለባቸውን እኔ እንደጨመርኩት ልብ ይሏል @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
1495ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል / መውሊድ/ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል❗️ ⚡️የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በታላቁ አንዋር መስጊድ በመገኘት ለእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ⚡️በዓበሉ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማ የሠላም እና የመቻቻል ከተማ እንድትሆን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሲያደርግ የነበረው ተሣትፎ ከፍተኛ ነው ብለዋል ፡፡ ⚡️በከተማዋ ያሉ የሙስሊሙ ማህበረሰብም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀራረብ መስራት ይገባል ያሉት ወ/ሮ አዳነች ከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ⚡️የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ባስተላለፉት መልእክትም የሰው ልጅ የደስታ ቀኑን በተለያዩ መልኩ ያከብራል፤ እኛም ዛሬ ነብዩ መሃመድ የተወለዱበትን የደስታ ቀን ነው የምናከብረው ብለዋል። ⚡️ነብዩ መሃመድ በምድር ላይ ቆይታቸው በዓለም ዙሪያ በርካቶችን አግኝተዋል ያሉ ሲሆን፥ ረጅም ጊዜ ጦርነት ላይ የነበሩ አካላትም እንዲያቆሙ አድርገዋል ሲሉም ተናግረዋል። ⚡️ነብዩ መሃመድ አንድነትን እንድናጠናክር መክረዋል፣ ሰላምን የሰበኩ ነብይ ናቸው፣ እኩልነት እንዲረጋገጥ አድርገዋል ለዚህም ልንከተላቸው ይገባል ብለዋል። 🦁• @Roviben •🦁
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN " የፍቅር ትንታኔ እንኳን ምድራዊ ሀብትና እውቀት ይቅርና ሰማያዊ ጸጋዎች ያለፍቅር ከባድ ናቸው፡፡ ፍቅርን ስትይዝ ሁሉንም ጸጋ ያዝክ ማለት ነው፡፡ የሃይማኖት ፍቅርና ጉልላት ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ካለህ እግዚአብሔር ባንተ ልብ አለ፡፡ አንተም በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ አለህ፡፡ ፍቅር ድል አለው፡፡ ስለፀጋ ስጦታዎች ብዙ ጭቅጭቅ አለ ስለሚበልጠው ጸጋ ስለፍቅር ግን ስብከት ጠፍቷል፡፡ ስለፈውስ ብዙዎች ይለምናሉ ነፍስን ስለሚፈውሰው ፍቅር ግን አይፀልዩም፡፡ ማንኛውመ መንፈሳዊ ነገር በእውቀት በእምነት በፍቅር ካልተደረገፈ ሀጢያት ነው፡፡ ትንፋሽ ድንገት የሚቋረጥ ሲመስልህ ፣ የልብህ ምቾት የቀዘቀዙ መስሎ ሲሰማህ ፣ ተስፋህ ጭልጥ ሲልብህ የምትድነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ እንጨት በምስጥ ፣ እህል በነቀዝ ፣ ልብስ በብል ይበላል ፣ ሰውን ጥላቻ ይገዘግዘዋል፡፡ ሌሎች በኃይል እንዲሰሩ ሞተሩ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ከሌለ ሰማዕትነት ሊኖር አይችልም፡፡ በየዕለቱ ሰማዕትነት ላይኖር ይችላል፡፡ በየዕለቱ መስዋዕትነት ግን አለ እርሱም ጥላቻን እንቢ ማለት ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም ደረጃ ፣ በሁሉም ፀጋ ውስጥ በሁሉም ዘመን ደግሞም ለዘለዓለም የሚፈለግ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ በፍቅር የማይቃጠሉ ልቦች ወንድማቸውን ለመስቀል ይጨክናሉ፡፡ ቤተክርስቲያን የቆመችበቶ ምሶሶ ፍቅር ነው ፣ ያለፍቅር ትወድቃለች፡፡ ፍቅር ራሳችንን በሰው ውስጥ ሰዎችን በራሳችን ውስጥ የምናይበት መስታወት ነው፡፡ ፍቅር ያላቸው ሌሎችን የማስተካከል አቅም አላቸው፡፡ ፍቅር በቀላሎች ሰፈር ያላት ስያሜ ምስኪንነት ፍርሃት ነው፡፡ መንገዶችን ከመስራት ፍቅርን መገንባት ይቀድማል፡፡ የተሰሩት መንገዶች በጥላቻ ይዘጋሉ፡፡ ትልቁ ርዕዮተ አለም ፣ የማይከሽፍ መሳሪያ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ፍቅር ትልቁ ስጦታ ፣ ትልቁ መንገድ ፣ ትልቁ መሪ ነው፡፡ ዓይን ያለ ፍቅር ምን አገባኘ ይላል፡፡ ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡ ምላስ ያለፍቅር ከወጣ ይሰብራል፡፡ እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል፡፡ እግር ያለ ፍቅር ከሔደ ድልድይ ያፈርሳል፡፡ ፍቅር የሌለው ሰማዕት ክርስቶስን አላወቀምና በከንቱ ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች እንደጎደለን ብንናገርም በዋናነት የጎደለንፍቅር ነው፡፡ ፍቅርበመጨረሻው ዘመን ይቀዘቅዛል እንጂ አይጠፋም፡፡ ያለፍቅር የተሰበኩ ነፍሰ ገዳይ ይሆናሉ፡፡ ለማፍቀር የልብ ፈቃድና የእግዚአብሔር ፍቅር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ፍቅር በግልፅነት የምትከብር ናት ፍፁም የምትሆነውም ፍርሃትን ስታሸንፍ ነው፡፡ #ፍቅር_እራሷ_ጌጥ_ናትና_ጌጥ_አትፈልግም፡፡ #ፍቅር_ጽንፍ_የለሽ_ናትና_ዘረኘነት_አይስማማትም፡፡ #ተብራርቶ_ያላለቀ_ትንታኔ_ፍቅር_ብቻ_ነው፡፡ በፍቅር ያጌጡ በወርቅ ከተኝቆጠቆጡ ይበልጣሉ፡፡ ምኞት ዳርቻ ጥማትም እርካታ የሚያገኘው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ያለፍቅር የተዘረጉ ምፅዋቶች ከዱላ አይተናነሱም፡፡ #ኅሊናውን_አጉድለን_ሆዱን_የሞላንለት_ከሰጠነው_የሰረቅነው_ይበዛል፡፡ ፍቅር ሁሉም የሚሰጠው ምፅዋት ነው፡፡ ፍቅርን የማይሰጥ ድሃ የማይቀበል ሀብታምም የለም፡፡ ጎዶሎዎቾ መልካም የሚሆኑት በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ሩጫህን የጀመርከው ያለ ጭብጨባ ብቻህን መሮጥ የጀመርህ ቀን ነው፡፡ #የታየህን_እይ_እንጂ_የሚያዩህን_አትይ_ትወድቃለህና፡፡" የሆነ መፅሐፍ ሳነብ አገኘሁትና ላካፍላቹ ብዬ አሰብኩኘና እንዲህ ለንባብ እንዲመች አድርጌ ቀነጨብኩት፡፡ መፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡ በፍቅር እንኑር እላለሁ😍😍😍 @jahABP ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ 😍🙏😍 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN መስመር ማሳጠር (በተረት ላሰላስል) የአስፓልት ላይ መስመሮችን የመቀባት ስራ ያገኘ ሰው በመጀመሪያው ቀን 9 ኪ.ሜ ቀባ፡፡ ፎርማኑም ተደሰተ፡፡ በሁለትና በሶስተኛው ቀን 3 ኪ.ሜ ብቻ ቀባ፡፡ ፎርማኑ በጥቂቱ አዘነ፡፡ በአራተኛው ቀን ግማሽ ኪሎ ሜትር ብቻ ነበር የቀባው፡፡ ይህን ጊዜ በቀቢው ተግባር የተበሳጨው ፎርማን እንዲህ ሊሆን የቻልንበት ምክንያት እንደዲያስረዳው ቀለም ቀቢውን ጠየቀ፡፡ የቀለም ቀቢው መልስ ከዚህ በታች ይነበባል፡- "ሌሎች ያስጀመሩትንጠማድመቅ ቀላል ነው፡፡ በመጀመሪያው ቀን ሌሎች አስምረው የቀቡትን አደመቅኩ እንጂ አዲስ መስመር ማስመር አይጠበቅብኘም ነበር፡፡ በሁለተኛው ቀንም ያው ነበር፡፡ አንዳንድ የቀድሞ መስመሮች ሙሉ በሙሉ መጥፋታቸው እንቅፋት ሆነውብኘ እያሰመርኩ በመቀባቴ በእርግጥ ዘግይቻለሁ፡፡ አሁን እየቀባሁ ያለሁት ግን ሙሉ በሙሉ አዲስ መስመር እያሰመርኩ ጭምር ነው፡፡ ወደፊት ይህን ተከትለው በፍጥነት ያደምቁ ዘንድ መሰረቱን እየጣልኩ እንደሆነ ግን አምናለሁ፡፡" መስመር ማስመር ይቀጥላል..... "ሳይነኩ ማሳጠር" ውክልና (ሲምቦል) ሃሳብን የማስተላለፊያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ "መስመር" የማንነት መለያ ነው፡፡ ስራ ፣ ዕውቀት ፣ ዝና ሁሉም የራሱ መስመር አለው፡፡ ለምድራችን ጠቃሚ ስራ አበርክተው ያለፉትም ሆነ በእኩይ ምግባራቸውን የሚነሱት ሰዎች የራሳቸውን መስመር አስምረዋል፡፡ አብዛኞች ግን ሌላው የሰመረውን በማጥፋት ተጠምደው ይጠፋሉ፡፡ የራሳቸውን መስመር ይስታሉ፡፡ ነገሩን በምሳሌ እናስደግፈው.... መምህሩ የተማሪዎቻቸውን ግንዛቤ ለመገምገም ጥያቄ ያዘጋጃሉ፡፡ ጥያቄው የመስመር ጥያቄ ነበር፡፡ አንድ ረጅም መስመር አስምረው ሲያበቁ ፡- ይህንን መስመር ምንም ሳትነኩ አሳጥሩት ሲሉ አዘዙ፡፡ "#ሳይነኩ_ማሳጠር" ታላቅ ብቃት ነው፡፡ ከሌሎች ገዝፈው ለመታየት የተሰመረውን የማጥፋት አማራጭ ለሚመስላቸው ግን ቀላል፡፡ ጥያቄው ኢጎ ወለድ እሳቤን ይነቅፋል፡፡ ምክንያቱም ፣ የተሰመረውን ማጥፋት መስመሩን አያሳጥረውም፡፡ አጥፊውን እንጂ፡፡ መምህሩ ለጠየቁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት አንዱ ጎበዝ ተማሪ ተነሳ፡፡ መምህሩ ካሰመሩት ጎን ሌላ ረዥም መስመር አሰመረ፡፡ በእርግጥም የመጀመሪያው መስመር ከሁለተኛው መስመር ያጠረ ነበር፡፡ በትክክልም መምህሩ ሊያስተምሩተ የፈለጉት ይህን ነበር፡፡ ሌላውን ለማሳጠር ረጅም መስመር ከጎኑ ሊኖር የገሸድ ይላል፡፡ ፉክክር በበዛበት ዓለማችን ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ነው፡፡ ጥቂቶች ሌላውን ሳይነኩ የራሳቸውን መስመር ያሰምራሉ፡፡ ሌሎች ያሰመሩትን ረጅም መስመር አጭር የሚያደርግ ረዥም መስመር፡፡ ሌላው ያሰመረው ሳይነኩ ያሳጥራሉ፡፡ አያሌዎች ግን የሌሎችን መስመር ለማሳጠር ይተጋሉ፡፡ አለማችን ሌላው አስምሮ ያለፈውን መስመር አጥፍተው የራሳቸውን መስመር ለማርዘም በሚጥሩ አጥፊዎች ተሞልታለች፡፡ የድንክ ግንዛቤ አጭሩን መስመር አርዝሞ ያሳያል፡፡ የመከነ ግንዛቤ ውጤት ፣ የራስን መስመር ከማስመር ይልቅ ሌላው ያሰመረውን አጥፍቶ ማሳጠርን ያስመርጣል፡፡ ይህ ነው ሐቁ፡፡ እኮ ማነው ሌላው ያሰመረውን ሳይነካ የሚያሳጥር!????? ኄኖክ ስጦታው ሸገር ታይምስ መፅሔት ግንጣይ ገፅ ቅፅ 01 ቁ 21 ታህሳስ 2010ዓ.ም የሌሎችን ሳትነካ የራስህን አርዝመህ አስምር ወዳጄ፡፡ አብሶ ቦለቲከኞቻችን እባካችሁንንንንን የራሳችሁን መልካም ነገር ብቻ እየፃፋችሁ የሌሎችን አሳጥሩ እንጂ በክፋት ከሌሎች አትባሱብን ኧረ መኖር እንፈልጋለን ኧረ የሌሎች መኖርም ነው የኛ መኖር ይቺ ሀገር ያለሰው ምንድነች?? ሁሉን አጥፍተን እንችለዋለን?? ለእኛ እንጂ ለኔ የት ያደርሰናል😔😢 @jahABP ነኘ ቀን ተመኘሁ😔😔🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN "ፍቅር ማለት በምትወደው ነፍስ ውስጥ ራስን መግደል ነው" ለብዙዎቻችን "ምስጢር" የሆነው ፍቅር ከሰው ልጅ የቀሕይወት ልምዶች ውስጥ አስደናቂውና አይረሴው ነገር ቢሆንም ሊያጤኑት የወደዱ ግን እጅግ ጥቂቶች ሆነው ተገኘተዋል፡፡ ለፍቅር አመጣጥና ዕድገት በየሰው ሕይወት ውስጥ በሚደንቅ ስነፅሁፋዊ አገላለፅ ሲቀርብና ሲያስደንቀን ኖሯል፡፡ ፍቅር በታላላቅ ደራስያን ብዕር ተፅፉል ፣ በታላላቅ ድራማዎች ላይ ተሰርቷል ፣ ባለቅኔዎች ተቀኘተውበታል.....ነገር ግን ፍቅር ምንድነው? የሚለው ጥያቄ "መልስ አገኘሁለት" በማለት ለመፃፍም ሆነ ለመናገር የደፈረ "አልተገኘም" አንድ ወንድ አንዲት ሴት ያፈቅራል ይህን የተለመደና በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የሚከሰት ስሜት ተራ ክስተት አድርጎ ማለት የፍቅር ሀያልነት እንደማሳነስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ የፍቅር ሀያልነትን ጠቀሉን የተቋደሱ ሁቹ ሲመሰክሩ፡- "ፍቅር ከህይወት ጡት ውስጥ እንደሚፈልቅ ወተት አድርገን እንውሰደው"ይላሉ የፍልስፍናው ጎራ ሰዎችም በዚያ ይስማማሉ፡፡ ሕፃን ልጅ የእናቱን ጡት ሲመለከት የሚሰማውን ደስታ ያህል በወጣትነት ዘመንም በሴቷ ላይ የሚያየው ቁንጅና እንዲሁ ያደርገዋል፡፡ ዳሩ ቁንጅናዋን የፍቅሩ ምክንያት አድርጎ መውሰድም የሚከብድ ነው፡፡ ምክንያቱም #ቁንጅና_ፍቅርን_ከሚፈጥረው_በላይ #ፍቅር_ቁንጅናን_ይፈጥራልና ፡፡ እንደመሰለው እንደመሰላት እንደመሰለን እንፋቀራለን፡፡ በትክክል የፍቅራችንን ክፋይ ያገኘን መስሎን በፍቅር የደከምንባቸው ጊዜያት መለስ ብለን ተመልክተን ደግሞ መሳሳታችንን ስንረዳ መለያየትን በቦታው ተክተን ወደሌላ የፍለጋ ጉዞ እንሰማራለን፡፡ ፍቅርን በባግህዋን ሽሪ ራጅናሽ(ኦሾ) እይታ ደግሞ ለማየት እንሞክር፡፡ ኦሾ "No Water, No Moon" በተሰኘው መፅሐፉ ፍቅርን እንዲህ አስቀምጦታል:- "ብዙዋች በፍቅርና በወዳጅነት መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው በጎዳናው ላይ ሲዳክሩ ይስተዋላል፡፡ አንድ መስለው ይታዩዋቸዋል ነገር ግን አንድ አይደሉም፡፡ ይመሳሰሉባቸዋል ነገር ግን በእውነታው አይመሳሰሉም፡፡ እንዲያውም ከወዳጅነት ይለቅ ከፍቅር ጋር የሚመሳሰሉ ጥላቻ ነው፡፡ ጥላቻ ተቃራኒውን ነው - ወዳጅነት የጥላቻን እውነታ ደብቆ የፍቅርን መልክ ይይዛል፡፡ ነገር ግን ፍቅርን እየገደለ ነው፡፡ አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ ማሰብ(Possessiveness) መርዘኛ ነገር የለም፡፡ ይህን በሚገባ ከተሰጃችሁ ወደ ቀጣይ ጉዳይ እንዝለቅ....." ይላል፡፡ "ለብዙዎችእንዲህ ሆኗል ለናንተም እንዳይሆንባችሁ ልንገራችሁ ምክንያቱም በፍቅርና በግንኙነት መካከል ያለው ልዩነት ግራ አጋብቷቸዋል፡፡ በተለይም ከውጪ ሆነው ሲመለከቱ የኖሩ ሰዎች ሰለባው ሲሆኑ ኖረዋል ወዳጅነትና የግል ማድረግን እንደፍቅር ወስደውት አይቻለሁ፡፡ በዚህ መንገድም እውነተኛውን ነገር አጥተውታል "ሰውን የግል ለማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ ስሜት ጥላቻ ይሻላል፡፡ #በጥላቻ_ውስጥ_ውሸት_የለም፡፡ ከዚያ በላይ ደግሞ ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል፡፡ የሰውን ልጅ የግል የማድረግ ፍላጎት ግን ፈፅሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም፡፡ "ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው፡፡" ፍቅር ማለት ሞት ነው፡፡ የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው፡፡ ዕለት ዕለት ወደ ጥለቅ የነፍሷም ቦታ ትወስዳለህ ፍቅር ወደ ምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው፡፡ ጉዞውም ማቆሚያ የለውም፡፡ አንዲት ሴት ስታፈቅራት አንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት፡፡ ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ የምናስቀምጥለት ከሆነ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ለራስህ ዋጋ ሰጥተኃል ማለት ነው፡፡ ራስህን ዋነኛ ጉዳይ አድርገህ በፍቅር ውስጥ ስትመለከት ተፈቃሪዋ መጠቀሚያህ ሆነች የፍላጎትህ ማርኪያ አደረግሃት በሌሎች ዘንድ መደነቂያህ ሆነች መነሻውም መድረሻውም አንተ ሆነሃል፡፡ ፍቅር ደግሞ መነሻው አንተ መድረሻው ግን ተፈቃሪው ይሁን ይልሃል፡፡ በተፈቃሪው ውስጥ ትሟሟለህ ትጠፋለህ፡፡ የመሞት ሒደትና ክስተት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ፍቅር የሚፈሩት፡፡ ስለፍቅር ልታወራ ፣ ልትዘፍን ፣ ትችላለህ ነገር ግን የልብህ ጥልቅ ስሜት ቢመረመር ፍቅርን በመፍራት የተሞላ ነው፡፡ "ስለፍቅር የምትቀኘው ቅኔ የምታዜመው ዜማ ሁሉ የፍቅር የምትክ እንጂ በራሳቸው ፍቅር አይደሉም በአጭሩ የምታፈቅረውን ሳታፈቅር ነው፡፡ ፍቅር ደግሞ ያለእሱ መኖር የማትችለውን እጅግ አስፈላጊህ ነገር ነው፡፡ ፍቅርህን እውነተኛ ካልሆነ ደግሞ ምትክ የሚሆነው ነገር ያስፈልግሃል፡፡ የእሱ ምትክ ደግሞ መሻት ሊሆን ይችላል ቢያንስ በመሻትህ በፍቅር ውስጥ ያለህ አድርጎ እንዲሰማህ ያደርጋል፡፡ የውሸት ፍቅርህን እንኳን ደስታን ይፈጥርልሃል፡፡ ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ ግን የውሸት መሆኑን መረዳትህ አይቀርም፡፡ ያን ጊዜ የውሸት ፍቅርህን ወደ እውነተኛ ፍቅርን መለወጥ አትችልም፡፡ አንድ የምትችለው ነገር ቢኖር "ያፈቀርከውን" ሰው መለወጥ ብቻ ይሆናል፡፡ "ሁለቱ መንገዶች እነዚህ ናቸው፡- ያለህበትን ፍቅር የውሸት መሆኑን ስትረዳ ራስህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ይህንን የውሸት ፍቅር ጥለህ ኸደ እውነተኛው አፍቃሪነት ትገባለህ፡፡ ሁለተኛው መንገዶች እነዚህ ናቸው፡- ያለህበትን ፍቅር የውሸት መሆኑን ስትረዳ ራስህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ይኸን የውሸት ፍቅር ጥለህ ወደ እውነተኛው አፍቃሪነት ትገባለህ፡፡ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ያፈቀርካትን ሴት መለወጥ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ደግሞ አእምሮህ የሚሰራው እንደምታታልል ሳይሆን እንደተታለልክ ነው፡፡ "በምታፈቅረው ሰው በኩል ችግር አለመኖሩ ብትረዳ እንኳን ወደ እውነተኛ ፍቅር ለመግባት ትፈራለህ፡፡ ፍቅር እንደሞት ያስፈራሃል፡፡ ሞትን የምትፈራ ከሆንክ ደግሞ ፍቅርን መፍራትህ አይቀርም፡፡ በሞት ውስጥ የሚሞተው ስጋህ ብቻ ነው፡፡ ማንነትህ ግን እንደተጠበቀ ይኖራል፡፡ ለአንተ ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ ሆኖ የኖረው አእምሮሆ ወደ ሌላ ሕይወት ይወስዳል፡፡ ውስጣዊ ማንነትህ ግን አይቀየርም፡፡ ሞት የሚለውጠው የላይኛው ሽፋንህን ብቻ ነው፡፡ "ስለዚህም ሞት ይህን ያህል ጥልቅ ነገር አይደለም ፡፡ እንግዲህ ሞትን የምትፈራ ከሆነ እንዴት ወደፍቅር የመግባቱ ድፍረት ይኖርሃል? ምክንያቱም በፍቅር ውስጥ የሚሞተው የላይኛው ሽፋንህ ብቻ ሳይሆን ውስጥህም ነው፡፡ የሞት ፍርሃት የፍቅር ፍርሃት ሆነ ፣ የፍቅር ፍርሃት ደግሞ የጥልቅ ሀሳብ ወይም የፀሎት ፍርሃትን አመጣ፡፡ እነዚህ ሦስት ነገሮች ተመሳሳይ ናቸው:- ሞት ፣ ፍርሃትና ፣ ጥልቅሃሳብ፡፡ አፍቅረህ የማታውቅ ከሆነ መፀለይ አትችልም ማሰላሰልም አትችልም፡፡ አፍቅረህም ሆነ በጥልቅ ሃሳብ ውስጥ ገብተህ የማታውቅ ከሆነ ደግሞ የሞትን የተዋበ ልምምድ አታውቅም ማለት ነው......." ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች (፩ ፪ ፫ ፬) ከኃይለጊዮርገስ ማሞ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደወሰድኩት 😃እየተፈላሰፋችሁ እደሩ😄 @jahABP ነኘ አስተያየታችሁ አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN የአገራችን ኑሮ ብድር ነው የአገራችን ኑሮ ስጦታ ሳይሆን ብድር ነው፡፡ ፍቅር ስጦታ ነው፡፡ ብድር ግን ሲከፋፈሉ መኖር ነውና አድካሚ ነው፡፡ ሰዎች ያመጡልንን እንመዘግባለን፡፡ በደስታ ከመቀበል ቀን እንጠብቃለን፡፡ አሳንሶ ላመጣ አሳንሶ ለመስጠት ስጦታ መሳዩን በቀል መዝግበን እንኖራለን፡፡ ፍቅር ግን ሲያልፍ ነው፡፡ የእኛ ወደዚያ በደንብ ሲያልፍ የሌሎችም ወደ እኛ በደንብ ሲፈስ ነው፡፡ ፍቅር ስጦታውን ሳይሆን ወዳጁን ያያል፡፡ ፍቅር በቁሳቁስ ከተሰፈረ ዋጋው ያንሳል፡፡ ባለ ራዕይ....መልካም ሰው ምን አድርገውልኘ ነበር ብሎ መዝገብ አያገላብጥም፡፡ ላልሰጡት ለመስጠት ፣ ያላስተማሩትን ለማስተማር ይገሰግሳል፡፡ ብድርን ወይም ምላሹን አያገናዝብም እንደውምየሚጠብቀው ስድብን ነው የሚጠብቀው ነቀፋንና ክዳትን ነው፡፡ በቤት ውስጥ ካሉት ቁሳቁስ ይልቅ በር ላይ ያለው፡፡ የእግር መጥረጊያ ምንጣፍ ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡ ባለቤቶቹ እንድንገባ የሚፈቅዱልን በልባቸው ቆሻሻችንን መጥረጊያ ምንጣፉ እንዳለ ስለሚያስቡ ነው፡፡ እኛም ጠርገን በነፃነት እንገባበታለን የፀዳንቀትን እቃ ግን ለማየት እንኳን አንፈልግም፡፡ አገልግሎቱም አይታየንም፡፡ ከዚያም ይልቅ ንፁህ ካልሆንን የማይወደውን አበባ ምንጣፍ እናደንቃለን፡፡ በህይወት ላይም ንፁህ ስለሆንን የሚወዱን እና ከነማንነታችን የሚቀበሉን አሉ፡፡ ከነማንነታችን የሚቀበሉንን ሰዎችን ግን ዋጋቸውን አላወቅንም፡፡ እንደደጅ ምንጣፍ እየረገጥንባቸው እንኳን አናያቸውም፡፡ ዋጋቸውን ለማሰብ እንኳን አንፈቅድም፡፡ ብዙ መልካም ሰዎች እንደሚተክዙ እናውቃለን፡፡ ለራሳቸውምያለቅሳሉ በሚያገለግላቸው ሰዎች ደንዳናነት ውለታ ቢስነት ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ መልካም ሰዎች እግዚአብሔርን ማየት አቁመው ለራሳቸው እያለቀሱ ይገኛሉ፡፡ ለመልካምነታችን ዋጋውን ከሰው አይጠበቅም፡፡ የመልካምነት ዋጋ ከፋይ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ቢከፍሉንም የሰው እጅ ትንሽ ልቡም ስስታም ነውና የእግዚአብሔር ይሻለናል፡፡ እንዳንዴ በኑሮአችን ምናየው ነው ችግራቸውን በገዛ አፋቸው ይነግሩናል ደስታቸውን ግን ከሰው ተነግሮን እንሰማለን፡፡ ችግራቸውን ሲነግሩን ከዘመዶቼ ደብቄ ነው ይሉናል፡፡ ደስታቸውን ግን ከእኛ ደብቀው ለዘመዶቻቸው ይነግራሉ፡፡ በነዚህ ቀላል ሰዎች መገረም እንኳን የለብንም፡፡ ምክንያቱም መገረም ጉልበት ይጨርሳልና፡፡ እኛም ለእግዚአብሔር እንዲህ ነን እያልን ራሳችንን ግን እንይበታለን፡፡ ዋጋችንን ከነዚህ ከጠበቅን ግን መልካምነታችን አደጋ ላይ ይወድቅብናልና ምላሹን ከእሱ ከባለቤቱ ከፈጣሪ እንጠብቅ፡፡ ራዕይ ያለው ትውልድ ለንባብ እንዲመች አድርጌ የቀነጨብኩት መልካምነት መልካምነት መልካምነት ይለምልም!! ባደረግነው መልካም ነገር ብዙ ጊዜ ጥሩ ምላሽ እንደማናገኘ መገመትን ተምሬበታለሁ፡፡🙏😊 የመልካምነት ከፋዩ ፈጣሪ ስለሆነ ደግሞ ደስታዬ ወደር አልባ ነው🙏ተመስገንልኘ 😊 @jahABP ነኘ መልካም አዳር 🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY GRAPHIC DESIGN 🤔መንገድ ያለው ከውጪ አይደለም🤔 ሁለት ወንድማማቾች እናታቸው ስታርፍ በቤት ውስጥ ያገኙት ትልቅ ገመድ ብቻ ነበር፡፡ ታላቁ ልጅ እጅግ በመበሳጨቱ ገመዱን ጠቅልሎ ጣራ ላዬ ወረወረውና ከቤት ወጥቶ ሔደ ፡፡ ታናሹ ግን ምንም ቢሆን ገመዱ የእናቱ ማስታወሻ ቅርስ ነውና እንደምንም ብሎ ጣራ ላይ ወጥቶ አወረደው፡፡ ከባዱ ጥያቄ ግን ከዚህ በኀላ ያለውን ኑሮ እንዴት ነው መግፋት ይችላል? የሚለው ነው ነበር፡፡ ለብዙ ሰዓታት ተቀምጦ አሰበበት ምንም ነገር ግን ሊታየው አልቻለም መንገዱ ሁሉ በግንብ የታጠረነው አስቦ አስቦ ወደ አንድ ጠቢብ ዘንድ ሔደ፡፡ ጠቢቡ ሰው እንዳገኘውም የጠየቀው ጥያቄ "ምን አለህ" የሚል ነበር፡፡ መልሱም ቀላል ሆነ "ምንም" ጠቢቡም ሰውም "በዓለም ላይ ምንም የሌለው ሰው የለም፡፡ ምናልባት ግን ጥቂት ብቻ ያለው ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ለምሳሌ:- አንተ ከወንድምህ በተለየ ጥበብ አለህ ይህም ጥበብ ነው ወደ ጠቢቡ ያመጣህ አለው" ልጁ ግን በእርግጠኘነት እየማለ ምንም እንደሌለው ተናገረ፡፡ ጠቢቡም "ይህ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው፡፡ ሰው ሆኖ ምንም የሌለው የለም፡፡ ረስተኸው ነው እንጂ አንዳች ነገር አለህ" አለው፡፡ ልጁ ቢያወጣና ቢያወርድ ያለውን ነገር ሊያገኘው አልቻለም፡፡ የሚያውቀው ምንም እንደሌለው ብቻ ነው፡፡ ያን ጊዜ ጠቢቡ ልጁን ይዞት ወደ አንድ ክፍል ገባ፡፡ ክፍሉ ሊዳሰስ በሚችል ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተሞላ ነው፡፡ ጨለማው አይን ሊወጋ ይደርሳል፡፡ ከጠቢቡም ጋር በዚያ ክፍል እንደገቡም "ምን ይታይሃል?"አለና ጠየቀው ልጁም ወዲያውኑ ነው መልሱን ያገኘው "ጨለማ" ጠቢቡ ግን እንደገና ጠየቀው፡፡ "ሌላነገር አለ ፈልገው" ዘወር ዘወር አለ ምንም ግን ምንም የለም ጠቢቡ እንዲህ አለው "ና አብረን ቁጭ እንበልና ጊዜ ወስደህ ተመልከት" ተቀመጡም ልጁ በግራና በቀኘ በፊትና በኀላ ማየት ጀመረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች አየ በመካከልም ላይ "አሃ" የሚል ድምፅ ከልጁ ሲወጣ ተሰማ .............ይቀጥላል ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ ገራሚ ታሪክ ነው🏃‍♂🏃‍♂
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN " "እኔ ለአንተአንተ ለእኔ" የተለያየ ድርሻ መያዛችን ሕይወትን የተሟላች ያደርጋታል፡፡ ሰዎች እንደ እኛ ካላሰቡ የተሳሳቱ ፣ እንደ እኛ ካልተናገሩ ቋንቋ ያበላሹ ፣ እንደ እኛ ካልኖሩ የሞቱ ፣ እንደ እኛ ካልሰሩ ሥራ የፈቱ አይደሉም፡፡ ሌሎች አስፈላጊያችን የሚሆኑት እኛ የማንችለውን ሲያውቁና ሲያደርጉ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ዶክተር ቢሆን ያለገበሬ ምን ይመገባል?? ዶክተሩ በእውቀቱ ተመክቶ ገበሬውን አንተ አታስፈልገኘም ቢለው ይሞኛል፡፡ የላይኛው ከታችኛው የግድ የሚፈላለግ የተለያየ ተሰጦ ተቀብለናል፡፡ ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኘም ሊለውና ሕይወትን ብቻውን ሊመራ አይቻለውም፡፡ ትልቁ የኑሮ የኑሮ ሚስጢር " እኔ ለአንተ ፣ አንተ ለእኔ" የሚል ነው፡፡ የጥቁሮች መብት ታጋይ የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡- "በአላባማ እያለሁ ጫማዩን የሚጠርግልኘ አንዲት ሊስትሮ ነበር፡፡ ይህን ሊስትሮ ስመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣ ነገር ቢኖር የቱንም ያህል ጫማዬን ብጠርገው እንደእርሱ አድርጌ ላሳምረው አለመቻሌ ነው፡፡ ስለዚህምይህ ልጅ በጫማ ማሳመር የዶክትሬት ዲግሪ አለው ብዬ ተቀበልኩ፡፡ ከኔም የተሻለ ስለሆነ አከበርኩት" ብሏል፡፡ የትኛውም እውቀታችን አዋቂ የሚያሰኘን ላላወቁት በምናደርገው መንገድ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ እውቀት የአገልጋይነት እንጂ የጌትነት መንፈስ የለውምና፡፡ የእኛ እውቀት አስፈላጊ የሚሆነው የማያውቁ ስላሉ ነው፡፡ ሁሉም ቢያውቅ እውቀታቸው አለማወቅ ይሆናል ስለዚህ የማያውቁትን አክብረን ማገልገል ይኖርብናል፡፡ የትኛውም ሀብታችን ባለጠጋ የሚያሰኘን በችግር ለሚያቃስቱት ባፈሰስነው ልክ ነው፡፡ ራሱን የቻለ ባለጠጋ አይባልም፡፡ ለሌሎች የተረፈ ግን ባለጠጋ ይባላል፡፡ ስኬታችን የሚለካው ራሳችንን በረዳንበት መጠን ሳይሆን በሌሎች በተረፍንበት መጠን ነው፡፡ ዛሬ ኑሮአችንንና ሕይወታችንን እንዲገዛው የፈቀድንለት ነገር ቢኖር ንቀት ነው፡፡ ሌሎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን ፣ እኛ ግን ሌሎችን መናቅ እንሻለን፡፡ ሌሎችን መናቅ በአዋጅ የተፈቀደልን ሥልጣን ይመስለናል፡፡ ሌሎችን በንቀት ዝቅ ካላደረግን የተስተካከልናቸው አይመስለንም፡፡ ስለዚህ የበላይነት ስሜታችን የበታችነት መንፈስ የወለደብን ነው፡፡ የምንኖረው ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ነውና ሌሎችን...ማክበር ደግሞም ፈጣሪ የምንሰጠውን አስታቅፎ ወደ ዓለም ልኮናልና አደራችንን ማድረስ ይገባናል፡፡ በቤታችን ፣ በሥራ ቦታችን ፣ በአገልግሎታችን እየሰራን ያለን እኛ ብቻ መስሎ ከተሰማን ሌሎች የሠሩት አይታየንም፡፡ ሌሎችን መውደድ ያቅተናል፡፡ ሥራችንም ከጥቅሙ ኩራቱ እየገነነ ይመጣል፡፡ በሌሎች ላይም እምነት እያጣንም የርክክብን ሥርዓት እናፈርሳለን፡፡ ራሳችን አልሚ ሌሎችን አጥፊ ሆነው እየታዩን ነቃፊ ብቻ እንሆናለን፡፡ የዓለማችን ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም ፣ የሰላም መሰረት ግብረ ገብነት ወይም የሞራል ሕግ ነው፡፡ የሥነምግባር መሰረቱ ሃይማኖት ነውና ሃይማኖትን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ ሰዎችን ከሕግ ፣ ከፍልስፍና ይልቅ ሃይማኖት የመግዛት አቅም አለው፡፡ ብዙ ባለ ራዕዯች ነን የሚሉ ሃይማኖትን በቀና መንፈስ አያዩትም፡፡ ሃይማኖት ግን የልምድ ሳይሆን የተፈጥሮ መሻት ነው፡፡ መስራት ፣ መማር ፣ መልፋት ፣ መትጋት ብቻውን በቂ አይደለም ሃይማኖት ያስፈልጋል፡፡ ዓለም ድፍርስ ውሃ ነው፡፡ ስለዚህ ማንነትን አያሳይም፡፡ እንደውም እውነትን የሚሸፍን በመሆኑ ምንመ ያልበራለትን የብርሃናት አለቃ ፣ ሰነፉን የትጉሃን አለቃ እያለ ያሞካሻል፡፡ ዓለሙ የሽንገላ ፣ የመዳለል አለም ነው፡፡ ሰዎች መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚጠሉት እውነት ስላልሆነ ሳይሆን ኃጢአጣቸውን ስለሚነግራቸው ነው፡፡ ዓለሙ የንግግር መክፈቻው "አንተ ለአንተ" ወይም "ሀይልህን አውጣ" የሚል ነው፡፡ ዛሬ የሰው ልጆች ሌላውን እንጂ ራሳቸውን ማየት አልቻሉም፡፡ ተራችንን ጠብቀን መቆም ፣ ቀጥሎ መመልከት ከዚያም መጠየቅ በመጨረሻም መጓዝ ነው፡፡ ካልቆምን መመልከት ፣ ካልተመለከትን መጠየቅ ፣ ካልጠየቅንም መጓዝ አንችልም፡፡ መቆም ለቀጣዩ ጊዜ ያዘጋጃል ፣ ለቀጣዩ ጉዞም ኃይል ይሰጣል፡፡ በክፉ ጎዳና የሚጓዝ መቆም ያስፈልገዋል፡፡ የመጣበትንና የሚሔድበትን የሚያየው በመቆም ብቻ ነው፡፡ በመቆም በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ራስን መገምገም ፣ ከዚያም መመልከት ቀጥሎም መጠየቅ በመጨረሻም ዕረፍት ወዳለበት ደሴት መጓዝ፡፡" ራዕይ ያለው ትውልድ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት መቆም.... ራስን ማየት ...ከኛ የተሻሉ ሰዎች እንዳሉ ማመን፡፡ ከትላንት የተሻልን ብቻ ሳይሆን የበለጠ ለመሆን መሞከር፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ ግን ሳሚሻን(DOC SHOESHINE) አስታውሶኛል 11-12 እስካሁንም ድረስ ሚኒልክ ትምህርትቤት ደጅ😍🙏😊 ሳሚሾዬ ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየትም ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡ 😍መልካም አዳር😊 @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPIC DESIGN እሌኒ ንግስት መስቀሉን አስገኘች፡፡ ምን አይነት መታደል ነው ባካቹ እሌኒ ተስፋ መቁረጥ ትችል ነበር፡፡ እሌኒ አይ ይሔን ሚያክል ተራራ ላስቆፍር ኧረ ይቅር አድካሚ ነው ማለት ወጪ ይበዛብኛል ብላ ምክንያት መደርደር ትችል ነበር፡፡ ንግስት ነች ሁሉም በሷ እጅ ነውና! ግን አላማ ነበራት ዋና አላሟዋም አምላኳ ነበር በቁጭት ነበር የተነሳችሁ ትልቅ ተስፋና እምነት ነበራትና አላማዋን ወጥታ ወርዳ አሳካች፡፡ ለኛም ድህነት የሆነውን መስቀሉ ተገኘልን ስሟም ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሲጠራ ይኖራል....... ከመስቀሉ በጣም ብዙ ነገር መማር እንችላለን ይህ ትልቅ በዓል ነው፡፡ ይህ የማንነታችን መገለጫ በዓል ነው፡፡ ይህ ለፍቅር ሲባል የተደረገልንን ሁሉ ምናስታውስበት በዓላችን ነው፡፡ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ትልቁን ፍቅር ያየነው #በመስቀሉ ላይ ነው፡፡ @jahABP ነኘ 😊🙏😍 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN "ወገኔ ልብ በል እነ ቄሳር ፣ እነ እስክንድር ፣ እነ ናፖልዮን ፣ እነ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ያልኖሩበትን አለም አንተ ምስኪኑ ዘላለም ምትኖርበት ይመስልኃልን?? ዓለሙ ሲያዩት ውበቱ በእየዕለቱ እየጨመረ የሚያሳሳ ይመስላል፡፡ ነገር ግን አበባ ሊረግፍም ሲል ያምራል የሚባለው ለሁሉሞ ይሰራል፡፡ የበረዶ መጥለቅም እንበለው ፣ ሱናሚም እንበለው ፣ ኒውክለርም እንበለው ፣ "ኮሮናም" እንበለው ዓለም እንደምታልፍ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ አሁን እየጎላ ነው፡፡ ስለዚህ፡- 👉በሚያልፍ ዓለም የማያልፍ በጎ ሥራ ሥራበት፡፡ 👉በሚያልፍ ዓለም የማያልፍ የነፍስ ውሴኔ ወስንበት፡፡ 👉በሚያልፍ ገንዘብ የማያልፍ ዘመድ አፍራበት፡፡ ማለት ድሆችን ጎብኘበት የእግዚአብሔር ስራን ስራበት፡፡ 👉በሚያልፍ ዓለም ለሚተካው ትውልድ መሠረት ጣልበት፡፡ " መልካሙን መልካሙን እናስብ ገነትን ሞተን ሳይሆን ምድር ላይ እንስራ፡፡ መልካም ቀን ተመኘሁ @jahABP ነኘ 😊🙏 @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Mostrar todo...