es
Feedback
Diinii kee Anaakara (Md Ali)

Diinii kee Anaakara (Md Ali)

Ir al canal en Telegram

دروس وفتاوي ومحاضرات باللغة العفرية ★Diini barittooy, fatwaa kee Daqwa Qafar afat Tû mabul=> @Anaakar or @acmadxalol

Mostrar más
1 608
Suscriptores
Sin datos24 horas
+67 días
+1030 días
Archivo de publicaciones
🎞 አፋር በእምነትና ህልውና አደጋ መሐል! 🔖 ይህ በሐኒፍ ኢስላማዊ ድርጅት የተዘጋጀ በአፋር ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኘውን የዲን ትምህርት እጥረትና ይህም ያስከተለውን አደጋ የሚዳስስ ዘጋቢ ሲሆን ፤ በዚህ ቪድዮ ድርጅቱ በክልሉ ተንቀሳቅሶ ባደረጋቸው ቅኝቶችና በጎበኛቸው አከባቢዎች ያስተዋለውን የዲን ትምህርት ተደራሽነት ችግርና ይህም ያስከተለውን መዘዝ በመግለፅ የመፍትሄ ሀሳቦችን አቅርቧል። 🎥 በዩትዩብ ለመመልከት 👇 🔗 https://youtu.be/Jbcqy7OAYbs Hanif Islamic Organaization ∣ مؤسسة حنيف الإسلامية

photo content

ጥቂት ስለ ኢዕቲካፍ! ~ * ትርጓሜው፦ ለአላህ ዒባዳ ለመፈፀም በማሰብ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው። * ብይኑ፦ በቁርኣን በሱና የተረጋገጠ ሙስተሐብ (የተወደደ) ዒባዳ ነው። ለመፈፀም ስለት ለተሳለበት ሰው ግን ግዴታ ይሆናል። አዕቲካፍ ለሴቶችም የተፈቀደ ነው። * አላማው፦ ልብንም አካልንም ስብስብ አድርጎ በዒባዳ መጠመድ ነው። ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ከትርፍ ወሬ፣ ከትርፍ ቅልቅል፣ ከትርፍ እንቅልፍ መቀነስ ይገባል። * ጊዜው፦ አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ በረመዷንም ይሁን ከረመዷን ውጭ መፈፀም ይቻላል። በላጩ ጊዜ ግን ረመዷን ነው። ከረመዷንም የመጨረሻዎቹ አስሮቹ የበለጡ ናቸው። * ቦታው፦ ለወንድም ይሁን ለሴት መስጂድ ውስጥ ብቻ ነው። * የጀመረ ሰው መጨረስ ግዴታ ነውን? የሚያስገድድ ማስረጃ የለም። * ዝቅተኛው ጊዜ ምን ያህል ነው? ገደብ የለውም። ያሰኘውን መጠን ያክል ነይቶ መቀመጥ ይችላል። * ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ለመፀዳዳት መውጣት ይችላል። የታመመን ለመጠየቅ፣ ጀናዛ ለመሸኘትና መሰል ጉዳዮች ግን አይወጣም። የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ ግብይት፣ ስራ መስራት አይቻልም። ኢዕቲካፍ ላይ እያለ የታመመ ሰው መታገስና መቆየት የሚችል ከሆነ መውጣት የለበትም። * የረመዷን የመጨረሻዎቹን አስር መግባት የፈለገ መቼ ይጀምር? የረመዷን 20ኛው ቀን ከመጥለቋ በፊት ቢሆን መልካም ነው። * የሚወጣበት ደግሞ ረመዷን ተጠናቆ የዒድ ሌሊት ሲገባ ነው። ወላሁ አዕለም። = ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

sticker.webp0.44 KB

AnimatedSticker.tgs0.50 KB

sticker.webp0.31 KB

sticker.webp0.31 KB

sticker.webp0.46 KB

sticker.webp0.42 KB

sticker.webp0.44 KB

sticker.webp0.30 KB

AnimatedSticker.tgs0.52 KB

sticker.webp0.31 KB

ጥቂት ስለ ወቅታዊ ጉዳይ ~ መካከለኛው ምስራቅ ላይ ግጭትና ጦርነት በተከሰተ ቁጥር ኢራንን እያንቆለጳጰሱ፣ ሱኒውን ዓለም በማብጠልጠል የሚጠመዱ አካላት አሉ። መለከፍ ነው መቼም። እኮ ሺዐዎች ተሽለው? ለማንኛውም ሺዐዎችን እያወደሰ ሱኒዮችን በማውገዝ ላይ ለተጠመደ አካል የምንለው ቢኖር "እሺ በምን እንድዳኝ?" ነው። በምን እንድዳኝ? 1- በቁርኣን ብንነጋገር ሺዐዎች ለቁርኣን ቦታ የላቸውም። በቁርኣን የተወደሱ ሶሐቦችን የሚያወግዙ ናቸው። እንዲያውም ታላላቅ ሰዎቻቸው ቁርኣን ጎደሎ ነው የሚሉ ናቸው። (ይህንን ነጥብ የሚያስተባብሉ ስላየሁ ሌላ ጊዜ በመረጃ እመለስበታለሁ።) 2- ጉዳዩን በሐዲሥ ለመመዘን ፈቃደኛ የሚሆን ካለ ቡኻሪና ሙስሊምን ጨምሮ አቡ ዳውድን፣ ቲርሚዚይን፣ ነሳኢይን፣ ኢብኑ ማጀህን ጨምሮ በርካታ የሐዲሥ ኪታቦችን ከነጭራሹ አይቀበሉም፣ ሺዐዎች። 3- በአኢማዎች እንዳኝ ካላችሁ እነ ኢማሙ ማሊክ፣ ሻፊዒይ፣ አሕመድ፣ ቡኻሪ በሺ0 ላይ የተናገሩትን ተመልከቱ። መቼም ከነዚህ አኢማዎች በላይ ስለ ኢስላም እናውቃለንም፣ እንቆረቆራለንም የምትሉ አይመስለንም። 4- መመዘኛችሁ ተውሒድ ከሆነ ሺ0 እና ተውሒድ ምስራቅና ምዕራብ ናቸው። በዚያ ላይ በአህለል በይት ላይ ድንበር የሚያልፉ፣ ሶሐቦችን የሚያወግዙ፣ ለኸሊፋው ዑመር 7ዳይ ሀውልት የሰሩ፣ ከነሱ ውጭ ያለውን የሱናውን ዓለም ናሲባ ብለው የሚያብጠለጥሉ ናቸው። 5- ለሙስሊሞች ውግንና ያላቸው መስሏችሁ ከሆነ በሶሪያ፣ በዒራቅ፣ በኢራን፣ በሊባኖስ፣ ... ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሱኒ ሙስሊሞችን የፈጁ ናቸው። በምስሉ ላይ ያያያዝኳቸው ቡድኖች የሱናው ዓለም በመፍጀት ላይ ኢራን ያሰማራቻቸው ቡድኖች ናቸው። ስለ ኢራን ሲነሳ ሶሪያ ላይ ያደረሱት ግፍ እንዳይነሳ የሚፈልጉ እንዳሉ አውቃለሁ። እነሱ ከአንድ ሺህ ሶስት መቶ ዓመት በፊት ለተፈፀመ የሑሴን ሞት እንበቀላለን እያሉ ሱንዮችን እየጨረሱ እኛ ሶሐቦችን ማውገዛቸውን፣ ሙስሊሞችን መጨረሳቸውን እንደ ተራ ነገር ልናልፍ ነው ወይ? ለመረጃ ያክል በኢራን ብዙ ግፍ ያስተናገዱት ሶሪያውያን በኻሚነኢ ሞት አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ሲገልፁ ነበር። የነሱን ቁስልና ህመም የማያውቅ አካል በድርጊታቸው ሊበግን ይችላል። 6- በፖለቲካ ሚዛን ቢታይም እናንተ ጠዋት ማታ የምታወግዟቸው የዓረብ መሪዎች ከኢራን የተሻለ ብስለት አላቸው። የማይችሉትን ሃይል መጋፈጥ ጀግንነት ነውንዴ? እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለሰዳም ሑሴንም፣ ለሙዐመር አልቀዛፊም አላዋጣም። ለኢራንም እንደማያዋጣ እያየን ነው። ዛሬ ኢራን ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ደቋል። አንድ ዶላር በ1,313,789 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሪያል) እየተመነዘረ ነው። በርካታ የጦር መሪዎቿ በገፍ እየተ7ደሉ ነው። "በክብር መሞት ይሻላል" የሚል አጉል መድረቅረቅ ሊኖር ይችላል። በቅድሚያ ተወደደም ተጠላ የሶሐባ ጠላት ክብር የለውም። እውነተኛ የዲን መቆርቆር የሌላቸውን አካላት ቢያንዘረዝርም ደጋግመን እናነሳለን ይህንን ጉዳይ! አቡበክርና ዑመርን፣ ዓኢሻንና ሐፍሷን የሚያብጠለጥል አካል ስንጥር ታክል ክብር የለውም። ወደ ነጥቤ ስመለስ ኢራንን የሚያወድሰው ፕሮፖጋንዲስት የሶሐባ መሰደብ ስለማያሳስበው ይህንን ለሙግት ያህል ብናልፈው እንኳ እየደረሰ ባለው ውጤት ኢራኖች አሜሪካን የሚቋቋሙበት አቅም እንደሌላቸው በተግባር እየታየ ነው። የዓረብ መሪዎች አቅማቸውን አይተው ቢቆሙ ምንድን ነው ጥፋታቸው? አቅምን ማወቅ ሞኝነት ሳይሆን ጀግንነት ነው። በተረፈ ሁሉም የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖ እየተመለከትን ነው። ገብቶት ቢሆን አንድ ነገር ነበር። ስለ ጀናባ አንድ ጥያቄ ቢጠየቅ ከዚህ ሁሉ ፈትፋች ውስጥ ለመልስ የሚቀረው ከጥቂትም ያነሰ እንደሆነ እርግጥ ነው። ፖለቲካው ላይ ግን ማሻአላህi ሁሉም የበቃ የነቃ ተንታኝ ሆኖ ይነሳል። የፖለቲካ ርእስ ከጀናባ ትጥበት ቀሎ ሳይሆን ብዙዎች ዘንድ ስለ ፖለቲካ ማውራት እንደ ንቃት ስለተቆጠረ ነው። ልብ በሉ! የፅሁፌ ትኩረት በዋናነት የሱኒውን ዓለም በማብጠለጠል ላይ ለተጠመዱ አካላት ነው። እንጂ ስለ ጦርነቱ በተለያየ አቅጣጫ ተመልክቶ ጉዳዩ ከኢራን ያለፈ እንደሆነ ስለሚያስቡ አካላት አይደለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 12/1447) የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

AnimatedSticker.tgs0.50 KB

sticker.webp0.31 KB

photo content

خطبة الجمعةد.ر إدريس إسماعل .mp319.44 MB

AnimatedSticker.tgs0.30 KB

sticker.webp0.29 KB