🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹
Ir al canal en Telegram
ሰላም ለእነዛ 🕊 በዱኣቸው ለሚያስታውሱን...ስማችንን ጠርተው ያ ረቢ ላሉ ሁሉ ይሁን። 💐 ለበጎነት በር ከስር ያለውን ይጫኑ @ALIFCHARITY123 ሃሳብ ካለ @HASHI41
Mostrar más1 043
Suscriptores
+324 horas
+27 días
+330 días
Archivo de publicaciones
1 043
"እንዴት በደንብ መተኛት ትችላለህ" የሚለውን መጽሐፍ አንብባ ይኸው በደንብ አድርጋ እየተኛች ነው፡፡
.
ማንበብ ጠቃሚ ነው።
ማንበብ መድኃኒት ነው።
ማንበብ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው።
1 043
🌾አሺራዚ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ቀን ከአባቴ ጋር ሆነን እየሰገድን፣ ዚክር እያደረግን እና ቁርኣን እየቀራን ሌሊቱን ሙሉ አሳለፍን። ቤቱ ዉስጥ ያሉ ሰዎች በሙሉ ተኝተው ነበር። ለአባቴ
"አንድም ሰው ተነስቶ ለይልን አልሰገደም እኮ።" አልኩት።
" ልጄ ሆይ! የሌሎችን ሥም ከማንሳት እንደነርሱ ተኝቶ ማደሩ ይመረጣል።" አለኝ።
መልካም ሠርቶ ከመመፃደቅ፣ አልፎም ሌሎችን ከማነወር አለመሥራቱ ይሻላል።
መልካም ምሽት💐
@ychanut
1 043
ጀነት ፈጽሞ ስህተት ሰርተው ለማያውቁ 'ለፍጹማን' ብቻ የተዘጋጀች አይደለችም፤ ይልቁንም ተሳስተው የተጸጸቱ፣ አምነውና መልካም ሰርተው የታገሉ የብርቱዎች መድረሻ እንጂ።
إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا
فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ شَيْئًا
@ychanut
1 043
ከአላህ ስም የላቀ አይገኝም ። ሲጠሩት መድኃኒት ፣ ሲያወሱት መረጋጊያ የስኬትም የከፍታም ምንጭ ነው ስሙ ። እንዘክረው እናውሳው ። አላህን ( ሱ.ወ ) ማውሳት የህይወታችን አንድ አካል ይሁን !
@ychanut
1 043
🌾ፈትዋ የተጠየቀ ጥያቄ 😍
እኔ 2 ሚስቶች አሉኝ 4 አመታቸው ነው 3ኛም አግብቼ 1 አመቷ ነው አሁን 4ኛ ለማግባት ጨርሻለሁ ለነሱም አማክሪያቸው እሽ ብለው ተሰስማምተዋል ሰሞኑን አገባለሁ ሚስቶቼ ልክ እንደ እህቶቼም ጭምር ናቸው በጣም ያስቡልኛል ያን ያክል ሀብታም አይደለሁም ግን አላስርባቸውም የሚጠበቅብኝ መስፈርት ካለ ምከሩኝ ኡስታዝ
የኡስታዝ መልስ ....ምኑን እመክርሀለሁ አንተ ምከረን እንጂ....😁
@ychanut
1 043
የላቀ ሐዲስ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿اتَّقِ اللهَ حيثُ كنتَ وأتبِعِ السيئةَ الحسنةَ تَمْحُها وخالِقِ الناسَ بخُلُقٍ حسنٍ﴾
“የትም ብትሆኑ አላህን ፍራ፣ ከወንጀል በኋላ መልካም ስራን አስከትል ታጠፋዋለችና። ከሰዎች ጋር ደግሞ በመልካም ስነምግባር ተኗኗር።”
📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 1987
@ychanut
1 043
ጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር ስለ እስልምና ምን አለ?!
(አንብበው ለሌሎችም ያካፍሉ!)
…
① "ኢስላም ሀይማኖት ከቆሻሻ መንፃት ነዉ…በቀን አምስት ግዜ የሚታጠብ ማንም የለም። እናንተ ሙስሊሞች ግን በዉሀ ትጥበት አምስት ግዜ ትነፃላችሁ…ከዛ ደግሞ በሰላት ልብና ህሊናችሁን በመንፈሰ ዉሀ ታጥባላችሁ…መስጊዳችሁ በሽቶና በጥሩ ማአዛ ይታወዳል… ነጭ ሽንኩርት የበላ፣ ካልሲዉ ሚገማ ሙስሊም መንፈሳዊዉን ኔቶርክ እንዳያዉክ ሲባል …አይደለም መስጂድ ዉስጥ ሊሰግድ ደጃፉ ላይም አይደርስም። ግሙን ራሱ ይጠጣት ተብሎ ተፈርዶበታል።
እና የሱን ግም ማን እንዲጠጣለት ይፈልጋል?!"
…
② "ሌላዉ አንድ ሰዉ እስላም ለመሆን ከፈለገ መጀመሪያ ሻሀዳ ማለት አለበት። በፍጡር ክዶ ለፈጣሪ እገዛለሁ ማለት አለበት። ሼኪ ፍጡር ነዉ፣ነብዩ መሀመድም ፍጡር ነዉ፣ ጅብሪል ፍጡር ነዉ፣ ፈጣሪ አላህ ብቻ ነዉ፣ እሱን ካወክ.. በመቀጠል ለሰላት ከመቆምክ በፊት ግምህን ሁሉ ትታጠባለህ …ከዛ ለሰላት ትቆማለህ።
ፈስህን ካንዛረጥክ ድጋሚ ትታጠባታለህ .…በቃ እስላም ጋር ግም ነገር ጥዩፍ ነዉ።
ጥርስ መፋቅ እንደስግደቱ ሁሉ ግዴታ ነዉ!"
…
③ "እስላም ጋር ግብረስጋ ግንኙነት ነዉር አይደለም። ነዉሩ ዝሙት ነዉ እንዲያዉም ሚስትህን ስትገናኝ ላንተም ለሚስትህም የፅድቅ ምንዳ ይሰጥካል …ሰላት ስትሰግድ ምፅዋት፣ለነዳያን ስትመፀዉት እንደምትፀድቀዉ ሚስትህ ጋር ስትገናኝም ትፀድቃለህ …ለምን ካልክ ዝሙት ብትሰራ ወንጀል ይፃፍብካልም አይደል …'ለጨዋ ጉርሻ ለባለጌ አለንጋ' ይገባዋል ይላል ኢስላም…"
…
④ "አንድ ሀብታም እስላም ለደሀ ቤት ሰርቶ ቢፀድቅ…ደሀዉ ደሞ ሙዝ ልጣጭ ከመሬት ላይ አንስቶ ሰዉ እንዳይጥል በማድረጉ ይፀድቃል …።
በእስላም ደሀዉም ሀብታሙም ፅድቅ ስራ ለማፃፍ ሁለቱም እኩል እድል አላቸዉ።
አንደኛዉ ከአንደኛዉ የተሻለ አድቫንቴጅ የለዉም ሀብታሙ ለሚስቱ ወርቅ ገዝቶ ቢያስደስታት ፃድቅ ተብሎ ይፃፍለታል።
ደሀዉ ምን አናደደዉ ሚስቱን ግንባሯን ስሞ አንድ ጉርሻ ጠቅልሎ ቢያጎርሳት እሱም እንደሀብታሙ ፃድቅ ተብሎ ይፃፍለታል…"
…
⑤ "የመፅሀፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ምዕራፍ ዘፍጥረት ነዉ።
የቁርዐን ደግሞ መጀመሪያ ለሰዉ ልጆች የቀረበዉ ጥሪ አንብብ! አንብብ ! አንብብ !
በፈጠረህ ጌታ ስም ይሁንብህ። የሚል ለሰዉ ልጆች የቀረበ ልመና ነዉ…የጌታህን የአንብብ ተማፅኖ ተቀብለህ ካነበብክ ባያንዳንዷ ቃል ሳይሆን ያነበብከዉ ፊደል ተቆጥሮልህ የፅድቅ ምንዳ ትንበሻበሻለህ።"
…
⑥ "እስላም ለዕዉቀት ሲል ማይታመን ድርድር ዉስጥ ይገባል። በርካታ ሙስሊሞችን የገደሉ አይሁዶችን ማርኮ የቀጣዉ ቅጣት ምን ይመስልካል…?? መፃፍና ማንበብ ማይችሉ ሙስሊሞችን አስተምሮ ከምርኮ ነፃ መዉጣት።
የጌታ ሰላምና ምህረት በረከት ከንፁህ ሙስሊሞች ጋር ይሁን አሜን!!"
ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር
የእስልምና ሁለንተናዊነት እኛ ከምንረዳው በላይ ተረድተው ከእኛ በላይ ለሚገልፁት ሂዳያውን ይስጥልን።
እስልምናን በውርስ ይዘን ብቻ ለምንኖር መንቃቱን ይስጠን። እናም ነቃ እንበል! ጁሙዓችሁ ይዋብ
#ከአኽላቅ ቤት
@ychanut
1 043
🗣መልካም የሆነ ንግግር ተናገሩ ታተርፉበታላችሁ።
መጥፎ ከሆነ ንግግር ዝም በሉ ሰላም ትሆናላችሁ። አሉን ረሱሉል ሁዳ ﷺ
ሶሂህ አል ጃሚዕ፡4419
@ychanut
1 043
ፈጣሪ አንዳች ጸጋ ሲያድለን ለፈተናም እንደሆነ ማወቅ አለብን ! በችግር ከምናየው ፈተና እኩል ማግኘትም የፈጣሪ ሙከራ እንደሆነ ማሰብ አለብን
መልካም ቀን 👐
@ychanut
1 043
🎈ከሰዎች ሁሉ በላጩ፣
ለሰዎች ጠቃሚው ነው🕸
🎈ከሰዎች ሁሉ በላጩ፣ መልካሙን
የሚከጅሉት መጥፎውን የሚጠነቀቁት ነው🌴
🎈ከሰዎች ሁሉ በላጩ፣ እድሜው
ረዝሞ መልካም የሰራ ነው 🪴
🎈 ከሰዎች ሁሉ በላጩ፣ የተራበን
ያበላ እና ሰላምታን የመለሰ ነው🌷
@ychanut
1 043
እውነተኛ ጥንካሬ የሚለካው ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ሲሆኑልህ ሳይሆን፣ ህይወት ፈታኝ በምትሆንበት ጊዜም ተስፋ ሳትቆርጥ ወደፊት መጓዝ ስትቀጥል ነው።
ውስጥህ ያለውን አቅም አትናቀው። ዛሬውኑ ሰበቡን አድርሰህ፣ ጠንክረህ ስራ፤ የቀረውን ደግሞ ለፈጣሪህ ስጥ። አንተ ካልቆምክ በስተቀር ማንም ሊያስቆምህ አይችልም!
💪 መልካም እና ስኬታማ ቀን ይሁንላችሁ!
@ychanut
1 043
እውነተኛ ጥንካሬ የሚለካው ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ሲሆኑልህ ሳይሆን፣ ህይወት ፈታኝ በምትሆንበት ጊዜም ተስፋ ሳትቆርጥ ወደፊት መጓዝ ስትቀጥል ነው።
ውስጥህ ያለውን አቅም አትናቀው። ዛሬውኑ ሰበቡን አድርሰህ፣ ጠንክረህ ስራ፤ የቀረውን ደግሞ ለፈጣሪህ ስጥ። አንተ ካልቆምክ በስተቀር ማንም ሊያስቆምህ አይችልም!
💪 መልካም እና ስኬታማ ቀን ይሁንላችሁ!
1 043
ለራህማን ንገረው ! የውስጥህን የጓዳህን ፣ የማትናገረው ለሰውና ለሀገር የማታዋየውን ጭንቅህን አካፍለው ። ከአላህ ( ሱ.ወ ) የሚልቅ የልብን ህመም አድማጭ ፣ የነፍስን ቁስለት ተመልካች ፣ የውስጥ ጉዳይን የሚጋራ የለምና ! ለራህማን ንገረው !
@ychanut
