❝ ዳሩል ቁርአን ❞ የ አጫጭር ኪታቦች መድረሳ
Ir al canal en Telegram
ይኽ ግሩፕ አላማው የ አሏህን ﷻ ሸሪዐ እንዲሁም የነብዩን ﷺ ሱና አጥብቆ የሚይዝ ወንድምና እህቶችን ማፍራት ነው ⌚️የቂራአት ሰዐት ከቀኑ፦ ➜ በኢትዮ 10:20 ➜ በሳዑዲ 4:20
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
736
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
ምርጥ ቤተሰብ ሌሊት በተሀጁድ ላይ የበረታ ነው!
እውነተኛ እና የተዋጣለት ቤተሰብ ማለት በዱንያዊ ኑሮ ብቻ የተሳካለት ሳይሆን ዓለም ፀጥ ባለችበት የሌሊት ክፍለ ጊዜ አላህን ለማውሳትና ለመለመን በአንድነት የሚቆም ነው። ነብያችን (ﷺ) አላህ በሌሊት ተነስቶ ሶላት በሰገደ ሚስቱንም ቀስቅሶ (እንቅልፍ ቢያሸንፋት እንኳ ፊቷ ላይ ውሃ ረጭቶ) ላሰገደ ሰው እንዲሁም በሌሊት ተነስታ ሰግዳ ባሏን ለቀሰቀሰች ሴት እዝነቱን ያውርድላቸው በማለት እንዳስተማሩት በተሀጁድ ሶላት የሚገናኝ ቤተሰብ ትልቁን የአሏህ እዝነት ወደ ቤቱ ያስገባል። ጨለማን አቋርጠው የጣፈጠ እንቅልፋቸውን አሸንፈው የሰማያትና የምድር ጌታ ዱዓን ለመቀበል ወደ ቅርቢቱ ሰማይ በሚወርድበት በዚያ በተባረከ ሰዓት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ የሚዘረጉ ባልና ሚስቶች በቤታቸው ውስጥ የማይጠፋ የሰኪና ብርሃን ያበራሉ። እንዲህ አይነቱ ቤተሰብ በዱንያ ፈተናዎች በቀላሉ የማይናወጥ የውስጥ ሰላሙ የተጠበቀ ፍቅሩ ከሰማይ የተቋጠረ እና የህይወት ጉዞውም ከዚህች አጭር ምድር አልፎ እስከ ጀነት የሚዘልቅ እውነተኛ የምርጥ ቤተሰብ ተምሳሌት ነው።
...............🌹ྀ࿐ ˊˎ-...........
