الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Ir al canal en Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 158
Suscriptores
Sin datos24 horas
+1817 días
+41530 días
Archivo de publicaciones
ወድሜ ?! ነብዩሏህ ዩሱፍን አስታውስ ?! ለዝሙት ራሳቸውን አዘጋጁላቸው ): የሳቸው ወደአሏህ ያደረጉት ልመና ያሱበሀን አሏህ⤵️
قَالَ رَبِّ ٱلسِّجۡنُ أَحَبُّ إِلَيَّ مِمَّا يَدۡعُونَنِيٓ إِلَيۡهِۖ وَإِلَّا تَصۡرِفۡ عَنِّي كَيۡدَهُنَّ أَصۡبُ إِلَيۡهِنَّ وَأَكُن مِّنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ
ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው፡፡ ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ? አለ፡፡↩️
የመጀመሪያው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
ኡስታዝ አህመድ አማን
https://t.me/Mf11q?livestream=e146c6f1f438b9c6f5
https://t.me/Mf11q?livestream=e146c6f1f438b9c6f5
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
.📣🎤 🚨አስደሳች ዜና 🚨
💘 የእስላማዊ ትላልቅየቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 3 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉 5k Subscribers
👉 8k subscribers
👉12k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
Repost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
ቀጥታ ስርጪት ተጀምሯል
ሱረቱ ዩኑስ ከቁጥር ( "15" )
የገባችዉ አተዉጡ ተከታተሉ ትጠቀማላቹህ ታተርፋላቹህ ?!✅
ተ
ጀ
ም
ሯል
☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️🍫🍫🍫
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
.📣🎤 🚨አስደሳች ዜና 🚨
💘 የእስላማዊ ትላልቅየቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 3 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉 5k Subscribers
👉 8k subscribers
👉12k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
በጊዜ መጨዋት እና ወደኋላ መንጓደድ ወንጀል ነው
አላህ ጊዜ ሰቶት ያልተጠቀመበት ሰው ወንጀለኛ ነው ውጀል የግድ ሰውን መስደብ ገንዘብ መቀማት ዝሙት መስራት ብቻ አደለም
ጊዜን በዋዛ ፈዛዛ ማሳለፍ ማባከን እራሱ ወንጀል ነው
ፀፀቱ ደሞ በሁለቱም አገር ነው
የመጀመሪያው ፀፀት ዱኒያ ላይ ነው እድሜ ከሄደ እና እርጂና ላይ ባለን ሰአት ወይይይ ምናለ በወጣትነቴ ተምሬ በሆነ በማለት መፀፀት ግን ዋጋ የለውም እንዳውም ዋጋ እድንከፍል ያደርገናል እንጂ✅
ትልቁ ፀፀት ደግሞ አኼራ ላይ ነው ዋ ጥፋቴ ወደ ዱኒያ በተመለስኩኝ ብሎ መከጀል💧💦አላህ ይጠብቀን
ዛሬን ተጠቀሙበት ተማሩ መልካምን ስሩ
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
! ፈጥኖ የመለስ Add የሚለውን በመንካት ምርጥ ቻናል ይሸለም
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
ጥያቄ
በቀን ዉስጥ ስንት ዋጅብ ሶላት አለ ❓
ሁሉም ሰው ባቀመሰው ልክ ይቀምሳታል ለበቀል እራስህን አታዘጋጅ ጊዜ በራሱ ይበቀልልሃልእያንዳንዱ ሰው በሰዎች ላይ ላደረገው በጎም ሆነ መጥፎ ነገር ተገቢውን ምላሽ በጊዜ ሂደት ማግኘቱ አይቀሬ ነው። ለበቀል ብሎ ራስን ማዘጋጀት እና ጉልበትን ማባከን የራስን ሰላም መረበሽ ነውና ጊዜን ለፍርድ መተው ሁልጊዜም ጥበብ ነው። ።ጊዜ ሀሰተኛውን ይለያል እያንዳንዱንም ሥራ በሰፈረበት ይለካል።
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
💘 የእስላማዊ ትላልቅ የቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 1 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉12k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_ስምንት (⓲)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #አይከል ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
የራጎው መርዝና የቃሉ መፍረስ
የሙሐመድ ልጅ አገር ገብታ የአባቷን ሕይወት አኼራ መሸኘት ዜና እንኳን ሳይነግረኝ፣ በሰው በኩል ሰማሁት። "በሐዘን ተሰብራ ይሆናል" ብዬ በቅንነት ቴክስት እያደረግኩ ዐሥራ አምስት ቀናት አለፉ። ያኔ ግን... ያ በሳዑዲ በረሃ ድራማ ስትሰራብኝ የነበረው መርዝ፣ ዛሬ በገዛ አገሯ ላይ ሊረጭብኝ ሰዓቱ ደርሶ ነበር። እናቴ "ልጄ አግባ" እያለች ስትማጸነኝ፣ እምቢኝ ብዬ ተስፋ ያደረግኳት ያቺ "የሙሐመድ ልጅ" ዛሬ ሌላ ገጽታዋን አሳየችኝ።
እኔ በሰላም አገር ይችልጅ "ሀዘኑ በርትቶባት ነው በብዙ አመት ተለይታው የነበረው አባታ ሳትጠግበው ወደ አኼራ ሄደባት ብዬ ስለሷ በእርምጃዬ ልክ አስባለሁ።!!
ያኔ .... ነበር አንግዲህ አንድ ቀን ደወልኩኝ ልጠይቃት
በጉጉትና በሥጋት ደወልኩ። ስልኩ ተነሳ፤ ነገር ግን ድምጯ አልነበረም። አንድ ባዕድ ወንድ ስልኩን ነጥቆ "ምን ፈልገህ ነው?" ብሎ በቁጣ ዘጋብኝ። "ወንድሟ ይሆን? ወይስ ዘመዷ?" ብዬ በሞኝነት ራሴን እያታለልኩ ደግሜ ደወልኩ። ያ ሰው ግን ዳግም አንስቶ "ደህና ነች፣ አትረብሽ!" ብሎ ሲዘጋብኝ፣ የልቤ ትርታ መፋጠን ጀመረ።
ማመን አቃተኝ
"አንደበቷ ማር ነው - ልቧ ግን መርዝ ሰንቋል፣
ተስፋዬን ሰብራ - ዛሬ ተለውጣለች፤
በስልክ ሽቦ ላይ - የሌላ ወንድ ድምፅ፣
ልቤን አደማው - እንደ ሾርጣ ጅራፍ።"--------------------
ያ ሌሊት ለኔ እንደ ሺህ ዘመን ረዘመብኝ። ዱባይ ሆኜ በሐሳብ ማዕበል ስዋኝ፣ እንቅልፍ ከዓይኔ ርቆ አደረ። ጠዋት ወደ ሥራ ስገባ ፊቴ አብጦ፣ ዓይኖቼ በእንባ ተሞልተው፣ ነፍሴ በጭንቀት ታውካ ነበር። ቀኑ አልፎ መሸ። ያንን አስፈሪ ምስጢር የአባታን ሞት የነገረኝን ዘመዷን ደወልኩለት።
ያኔ ነው እንግዲህ... ሰማይ ወደታች መጥታ" የረገጠችኝ፣ ምድርም ተከፍታ የዋጠችኝ የመሰለኝ! ጆሮዬ የሰማው ቃል የሞት ያህል ከበደኝ።
አንባቢያን ሆይ! ተመልከቱ። እኔ በየመን በረሃ፣ በጅቡቲ ባሕር፣ በሳዑዲ እስር ቤት ያለፍኩት፣ ዛሬ ላይ እንዲህ ልሰበር ነበር? "አላህ ሆይ! በማልችለው አትፈትነኝ" ብዬ ጮኽኩ። ያ የሙሐመድ ልጅ የደበቀችው ምስጢር፣ ያ ከሳዑዲ ጀምሮ ሲከረፋኝ የነበረው ሽታ... ዛሬ እውነቱ ሲገለጥ፣ ነፍሴ በቁሟ ተቀበረች።
"ጆሮዬ የሰማው - መርዶ ሆኖ መጣ፣
ተስፋዬ ነጎደ - እንደ ደመና ሽታ፤
የሙሐመድ ልጅ ሆይ - መርዝሽን ረጨሽው፣
ያለፍኩትን መከራ - ሁሉንም ረሳሽው።"
ስሟን ላስተዋውቃችሁ፤ እስካሁን የተደበቀው ስሟን ለማወቅ ጓጉታችኋል አይደል?
አይከል ትባላለች። ቆንጅዬ ስም ያላት፣ እንደ ሚዳቋ ቀልጣፋ፣ እንደ ጸደይ ዝናብ ትሁት የሆነች ልጅ ነች። ያኔ... ነበር እንግዲህ የወደድኳት፤ 'አይን ካልመረጠ ልብ አይፈርድም' እንዲሉ፣ እውነቱን ለመናገር የመረጥኳት ያኔ ነበር።
በእኔ ልብ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ክብር ያላትና የነገሰች ሴት ነበረች። ለመንገስ ዘውድ፣ ለመከበር ግርማ ሳይኖራት በልቤ ዙፋን ላይ ተቀመጠች። ማፍቀር የሚለው ቃል ለራሱ እስከማይገልፀው ድረስ አፈቅራታለሁ።
ይህ ግን ማፍቀር ብቻ አይደለም፤ ለእኔ ከመውደድ በላይ መውደድ፣ ዓለም የሆነ ፍቅር ነው። አንዳንዴ ወደ ሰማይ ቀጥ ብዬ፣ ጨረቃን የአይከል ጥላ እያልኩ፣ ከጨረቃ ጋር የማወራበትና በብቸኝነት የምተክዝበት ሌሊት ሁሉ ያልፍ ነበር።
'ጨረቃ ምስክሬ፣ ሌሊቱ አዝመራዬ' ሆኖ ስለ እሷ ውበት ስቀኝ ነጋሪ ሳይኖረኝ ይነጋል።በጣም አምናት ነበርና... እሷ ለኔ ዓለሜ ነበረች፤ 'ጨረቃን ከሰማይ፣ እሷን ከመሬት' አወዳድሬ እኩል የማያቸው ስጦታዬ ነበረች።
አይከል
ስሟ አይከል... የነፍስ ስንቅ፣
ትህትናዋ... የልብ ምርቅ።
ቀልጣፋ ናት... እንደ ሚዳቋ፣
ለእኔ ግን ነች... የዓለም ጓቋ።
ያኔ መርጬ... በልብ አነገስኳት፣
ከመውደድ በላይ... በነፍሴ ቀደስኳት።
"አፈቅርሻለሁ" ... ቃሉ ምን ሊረባ?
ውቅያኖስ ታክሎ... በቁንጥጫ እምባ።
ሌሊቱን ለጨረቃ... ምስጢሬን አውጋለሁ፣
በእሷ ትዝታ... ብቸኝነቴን እረሳለሁ።
መውደድማ ቀለለ... ስሙም ረከሰብኝ፣
አይከል ማለትማ... "ሕይወት" ሆነብኝ።
የአይከል ክህደትና የሕሊና ስብርባሪ
በስልክ ሽቦ ላይ የሚንቀጠቀጠው የዘመዷ ድምፅ፣ ልክ እንደ መርዛም ጦር የልቤን ግድግዳ ሰነጠቀው። ጆሮዬ ለማመን የከበደውን፣ ሕሊናዬ ሊሸከመው የማይችለውን ያንን መራራ መርዶ እንዲህ ሲል ተፋው፦ "አይከል... አይከል እኮ አገባች!"አለኝ
ያኔ... ሰማዩ በላዬ ላይ የተደፋ፣ ምድሪቱም እግሬ ስር የራደች መሰለኝ። አባት ገና ተቀብሮ፣ ዐፈሩ ሳይደርቅ፣ ሐዘኗን በሐዘን ልጋራ በተቆራረጠ ቴክስት ስማጸናት፤ እሷ ግን በበረሃው ዓለም "እንዳትጎዳኝ አደራ" እያለች በአላህ ስም የለመነችኝን ያንን ቅዱስ ቃል በጭቃ ላይ ረገጠችው። ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ የሁለት ዓመት ቃል ኪዳናችንን እንደ ቆሻሻ ጨርቅ ወርውራ፣ የሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ገብታ የደስታዋን ድግስ ትቆርጣለች።
ስልኬን አውርጄ ወረወርኩት።
ተሸነፍኩ! በእራጎ ሰቆቃ ያልተንበረከከው፣ በየመን በረሃ ጥም ያልታከተው፣ በሳዑዲ ድንበር የጥይት እሩምታ ያልፈራው ነፍሴ፤ ዛሬ በአይከል የክህደት ጩቤ በቁሜ ተቀበረ። ባዶ እግሬን ተራራ ስወጣ፣ በባሕር ማዕበል ስናወጥ፣ በሳቢያ ዱላ ስገረፍ... "ያልፋል" እያልኩ ራሴን ያጽናናሁት ለእሷ ብዬ ነበር። እንዲህ አልኩ፦
"በረሃው አላሸነፈኝ - ጥይቱ አልገደለኝ፣
የአይከል ክህደት ግን - በቁሜ ቀበረኝ።
ባሕሩን ተሻግሬ - ድንበሩን አልፌ፣
ዛሬ እቤትሽ ደረስኩ - በሐዘን ተመትቼ።
አቤት ውርደት! "እንዳትጎዳኝ" የሚለው ቃሏ በልቤ ላይ እንደ ማኅተም ታትሞ፣ ከአገር ከአገር እየቀየርኩ ለታማኝነት ስገላዘዝ እሷ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሊቶች ያወራናቸውን ምስጢሮች በአንዲት ጀምበር ክዳ ሌላ ጎጆ ቀለሰች። ከሥራ ራቅኩ፣ ከቂርዓቴ ተለየሁ። ዓለም በዓይኔ ላይ ጠበበች። ያቺ የነገርኳት እራቢያ በጆሮዬ ያንሾካሸከችው "የወንድ በቀል" ዜማ ትዝ አለኝ። ሴት ልጅን፣ በተለይም "የሰለፍያ እንስት" የምትለውን ማንነቷን ጠላሁት።
ምሬቱ አንጀቴን በላው። "አልፈልግህም፣ ሌላ አግብቻለሁ" ብላ በግልጽ ብትነግረኝ ኖሮ እንዲህ አልሰበርም ነበር።እኮ አልኩኝ" ግን ምስጢሯን አጭቃ፣ ስልኳን በባላ አስነስታ፣ የሁለት ዓመት የሕይወት ጉዞአችንን በመከራ ጽዋ ስትደፋው... ልቤ ተቦጫጨቀ።ደም አለቀስኩ ሀቂቃ
አይከል ሆይ
"አንተ የኔ ነህ" ያልሽው፣ ያ ያንደበቴ ማር፣
ዛሬ መርዝ ሆኖብኝ፣ ልቤን ሲሰባብር።
በሰው አገር ምድር፣ ብቸኝነት ሲወጥረኝ፣
"እንዳትጎዳኝ አደራ" ብለሽ፣ በቃልሽ ስታስረኝ፤
እኔ ተይዤ ስገባ፣ ስጋትሽ የነበረው፣
ዛሬ ሌላ ወንድ አቅፈሽ፣ በሰከንድ ረሳሽው?
አባትሽ ገና ሞቶ፣ ዐፈሩ ሳይመለስ፣
እንባሽ ሳይታበስ፣ ሐዘንሽ ሳይለሰልስ፤
እንዴት ወር ባልሞላ፣ የደስታ ድግስ ደገስሽ?
ያለፍንበትን ቃል፣ በእሳት አቃጠልሽው።
እኔ የሙሐመድ ልጅ፣ በክህደትሽ አልጠፋሁም፣
በቆሰለ ልቤም ቢሆን፣ ተስፋን አልቆረጥኩም፤
አንቺ ግን...
የባልሽን ሐቅ ጠብቂ፣ በበቀል የታወርሽ፣
የእኔን የነፍስ ቁስል፣ በሠርግሽ ድግስ ቀየርሽ።
ክፍል⓳ ይቀጥላል
Repost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
ቀጥታ ስርጪት ተጀምሯል
ሱረቱ ዩኑስ ከቁጥር ( "15" )
የገባችዉ አተዉጡ ተከታተሉ ትጠቀማላቹህ ታተርፋላቹህ ?!✅
ተ
ጀ
ም
ሯል
☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️🍫🍫🍫
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
🌺በየቀኑ በእስላማዊ ጥያቄ እና ምልስ በመሳተፍ ሁሌም የካርድ ተሸላሚ ይሁኑ 🎁
ዛሬ 2 ሰዓት 50 ብር ካርድ ሽልማት አለ
ወላሂ እውነተኛ ማስተወቂያ ነዉ🤌
