es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

ምክር ለወጣቶች

ምክር ለወጣቶች

Ir al canal en Telegram

"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
7 342
Suscriptores
+924 horas
+1057 días
+76230 días
Archivo de publicaciones
የመጅሊሱ ምክትል ሱፊይ ነው እነ ኢብኑ መስኡድ ሴንተር ከእንደዚህ አይነት ሰው ጋር ሆነን ዲንን እንርዳ እያሉ ነው ከባድ ውሸት🙌

ሽርክ እየሰሩ ቢደአ እየሰሩ የሶሻል ሚዲያ ስማቸውን "እገሌ ነኝ የነቢ ወዳጅ " ይላሉ አጂብ!

እህትዋ ሁሉን ነገር ለአላህ መተው ልመጂ።ችግር ይመጣል ይሄዳል። ሶብርሽ ላይ አደራ የነገሮች መክበድ ወይም መጠንከር የሚመጣውኮ ከአላህ ነው ምንአልባት እየተፈተንሽ ቢሆንስ ??? ፈተናውን በአግባቡ
እህትዋ ሁሉን ነገር ለአላህ መተው ልመጂ።ችግር ይመጣል ይሄዳል። ሶብርሽ ላይ አደራ የነገሮች መክበድ ወይም መጠንከር የሚመጣውኮ ከአላህ ነው ምንአልባት እየተፈተንሽ ቢሆንስ ??? ፈተናውን በአግባቡ ለማለፍ ደሞ ከምንም በላይ صبر አስፈላጊ ነው። እናማ ሶብሪ እህትዋ🫰🏽 @yeselefochteketay

📌 በሶሃቢያት ዘመን የነበረው የሀያእ (የሀፍረት) ገፅታ ​በሶሃቢያት (ረዲየላሁ አንሁነ) ዘመን የነበረው የሴቶች ጥበቃ እና ሀያእ ሁል ጊዜ የሚያስደንቅ ነው። የነሲባ ቢንት ከዕብ (ኡሙ ዐማራህ) ረዲየላሁ ዐንሃ ንግግር እንዲህ ይላል፦ «በዒድ ቀን እንድንወጣ፣ አልፎ ተርፎም ቢክራ ሴቶችን ከክትክታቸው (ከመጋረጃቸው ጀርባ) እንድናወጣ እንታዘዝ ነበር።» ​«ኽድር» (ክትክታ) ማለት አንዲት ቢክራ ሴት ይበልጥ እንድትከበርና እንድትሸሸግ በቤት ውስጥ የሚደረግላት መጋረጃ ወይም የተለየ ክፍል ነው። እዚያ ውስጥ የምታድግ ሴት ከሴቶች እንኳ ስለምትሸሸግ ሀያእዋ እጅግ የላቀ ይሆናል። በየመንገዱ ከሚወጣና ከሚገባ፣ ከማያውቁት ጋር ከሚቀላቀል ሰው በተቃራኒ ይበልጥ አይን አውጣ አትሆንም። ለዚህም ነው በሀያእ ምሳሌ የምትደረገው። ​በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበው የነቢዩ ﷺ ሀያእ ሲገለፅ የመጣው ሀዲስ ይህንን ያረጋግጣል፦ ​الْحَدِيثُ: «كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَشَدَّ حَيَاءً مِنَ الْعَذْرَاءِ فِي خِدْرِهَا» [صحيح البخاري: 6119، صحيح مسلم: 2320] ​ኡሙ ዐማራህ (ነሲባ) ይህንን ስትናገር ሁሉም ሙስሊም ሳይቀር ለዒድ ሰላት መውጣት እንዳለበት ስታስረዳ፣ እነዚያ ተሸሽገው የሚኖሩት ደናግላን እንኳ እንዲወጡ መታዘዛቸውን በመጥቀስ ነው። እነሱ እንኳ ከወጡ ማንም ሰው ወደ ኋላ ሊቀር እንደማይገባ ታሳያለች፤ ምክንያቱም ክብርና ሀያእን ለመጠበቅ ሲባል ሰላት ላይ ከመገኘት ወደ ኋላ ሊቀሩ የሚችሉት መጀመሪያ እነሱ ነበሩና። ◼️​2ኛ_የኡሙል ሙእሚኒን ዓኢሻ (ረ.ዐ) አስገራሚ ሀያእ ​የነቢዩ ﷺ ውድ ባለቤት፣ የሲዲቅ ልጅ ሲዲቃዋ እናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የነበራትን ሀያእ ስታወራ እንዲህ ትላለች፦ «የአላህ መልክተኛ ﷺ እና አባቴ (አቡበከር) የተቀበሩበት ቤት ውስጥ ልብሴን አውርጄ (ዘና ብዬ) እገባ ነበር፤ "እነሱ እኮ ባሌና አባቴ ናቸው" እል ነበር። ነገር ግን ዑመር አብሯቸው ሲቀበር በአላህ እምላለሁ! ከዑመር በማፈር ልብሴን በደንብ (ሳልሸፈን) ገብቼ አላውቅም።»ትላለች ⚪️​እስኪ አስቡት! እናታችን ዓኢሻ መሬት ስር ከተቀበረ አስከሬን ነው ያፈረችው! ለዚህም ስትል በገዛ ክፍሏ ውስጥ ልብሷን ጠቅልላ ትለብስ ነበር። ሀዲሱ እንዲህ ይላል፦ ​: «كُنْتُ أَدْخُلُ بَيْتِي الَّذِي دُفِنَ فِيهِ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَأَبِي، فَأَضَعُ ثَوْبِي، وَأَقُولُ: إِنَّمَا هُوَ زَوْجِي وَأَبِي، فَلَمَّا دُفِنَ عُمَرُ مَعَهُمْ، فَوَاللَّهِ مَا دَخَلْتُهُ إِلَّا وَأَنَا مَشْدُودَةٌ عَلَيَّ ثِيَابِي؛ حَيَاءً مِنْ عُمَرَ» [مسند أحمد: 25660، المستدرك على الصحيحين للحاكم: 4399 - وقال: صحيح على شرط الشيخين] ◼️​3ኛ_የጀናዛ አልጋ (ነዕሽ) አመጣጥ ታሪክ ​ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ የጀናዛ አልጋ (ሰዎች ሞተው ሲሸከሟቸው ሰውነታቸው እንዳይታይ በላዩ ላይ የሚደረግ ቅርፅ) ታሪክ ነው። ለመሆኑ ይህ ለምን እንደተሰራ ያውቃሉ? ፋጢማ አል-ዘህራእ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ለአስማእ ቢንት ዑመይስ የተናገረችውን ድንቅ ንግግር ላስቀምጥላችሁ፦ ​«አስማእ ሆይ! ነገ እኔ ስሞት በራሴ ላይ ስለሚሆነው ነገር እያስብኩ ነው። በአላህ እምላለሁ! በጠራራ ፀሃይ በወንዶች ፊት በካፈን ብቻ ተጠቅልዬ (የሰውነቴ ቅርፅ ታይቶ) ለመውጣት እጅግ አፍራለሁ!» ስትል አስማእ (ረ.ዐ) በሐበሻ ምድር (ኢትዮጵያ) ስትሰደድ ያየችውን፣ ከእንጨት ተሰርቶ የሴቶችን አስከሬን የሚሸፍነውንና የሰውነት ቅርፅ እንዳይታይ የሚያደርገውን የጀናዛ አልጋ (ነዕሽ) ገለፀችላት። ​ፋጢማ (ረ.ዐ) ስትሞት እንኳ ቅርፅዋ እንዳይታይ ያላትን ጨክኖ የቆመ ሀያእ ተመልከቱ! የሞተች ሴት ማንም ላይ ፈተና አትሆንም፣ ማንም አይመኛትም፣ እሷም ማንንም አታይም፤ በዚያ ላይ ሙሉ በሙሉ በካፈን ተሸፍናለች። ይህ ሆኖ ሳለ ግን የሰውነቷ ውጫዊ ቅርፅ እንኳ ለወንዶች እንዳይታይ ፈቀደች። ​ይህንን አልጋ መጀመሪያ የተጠቀመችው የነቢዩ ﷺ ልጅ ሩቀያህ (ረ.ዐ) እንደነበረችም በሌላ ዘገባ ተጠቅሷል። አስማእ ቢንት ዑመይስ ለነቢዩ ﷺ እንዲህ አለች፦ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሐበሻ እያለሁ ክርስቲያኖቹ ለሴት ልጅ በላዩ ላይ ቅርንጫፎች ያሉት አልጋ (ነዕሽ) ሲሰሩ አይቻለሁ (የሰውነቷ ቅርፅ እንዳይገለጽ ይጠላሉ)፤ ለልጅዎ እንዲህ አይነት አልጋ ልስራላት?» ኣለቻቸው ነቢዩም ﷺ፦ «አዎ ስሪላት» አሉ። ​ عَنْ أَسْمَاءَ بِنْتِ عُمَيْسٍ أَنَّ رُقَيَّةَ بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لَمَّا تُوُفِّيَتْ... قَالَتْ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنِّي رَأَيْتُ بِالْحَبَشَةِ شَيْئًا يَصْنَعُونَهُ لِنِسَائِهِمْ، جَعَلُوا النَّعْشَ فَوْقَهُ الْأَضْلَاعُ، أَفَلَا أَجْعَلُ لِابْنَتِكَ نَعْشًا مِثْلَهُ؟ قَالَ: «اصْنَعِيهِ» [المعجم الأوسط للطبراني: 9127] (ፋጢማህ መጀመሪያ የተጠቀመችበት ዘገባም በሱነን አል-በይሀቂ ቁ. 6916 ላይ በሰፊው ተወርቷል)። ​ ◼️​የሶሃቢያትን ሀያእ እና ሞተው እንኳ ለመሸፈን የነበራቸውን ጉጉት ልብ ይበሉ። ከነቢያት በመቀጠል ምርጥ ፍጡራን በነበሩት ሶሃቦች ፊት እንኳ ለመሸሸግ የነበራቸውን ጥንቃቄ ተመልከቱ። በመሞት ጭንቅ ውስጥ ሆነው እንኳ ያሳሰባቸው የሀያእ እና የሂጃብ ጉዳይ ነበር። ​የሚያስደንቀው ግን በዚያ ዘመን የነበረው ማህበረሰብ በሙሉ የሴቶችን ክብርና ሀያእ ለመጠበቅ የተባበረ ነበር። አንድም ሶሃቢይ የቤተሰቡን ሴቶች ያለ በቂ ምክንያት አጊጠውና ተኳኩለው ከቤት ሲወጡና ሲገቡ ዝም ብሎ የሚመለከት አልነበረም። ሶሃቢያትም ለራሳቸውም ሆነ ለሴት ልጆቻቸው እድሜያቸው ትንሽም ቢሆን ይህንን አይፈቅዱም ነበር። ⚪️​ስለሆነም በዘመናችን ያሉ ወንዶች በሴቶቻቸው፣ በራሳቸውና በማህበረሰቡ ላይ አላህን ሊፈሩ ይገባል። የልጆቻቸውን ክብር ሊጠብቁና ትክክለኛውን ሂጃብ በደረጃው እንዲለብሱ ሊያዟቸው ይገባል። ምክንያቱም በቤት ውስጥ መረጋጋት ከሁሉ የላቀው የሂጃብ መገለጫ ነውና። ሴቶችም ክብራቸውን፣ ሀያአቸውንና ስተራቸውን ሊጠብቁ ይገባል፤ ይህም የኢማንና የتقوى (አላህን የመፍራት) መገለጫ ነውና። ሼር ማድረግ እንዳይረሳ t.me/abduselam_addalochy11 t.me/abduselam_addalochy11

🎈ሁለተኛ ማግባት ማለት ልክ እንደ እስልምና ዳዕዋ ጅማሮ ነው . 🎈በድብቅ ትጀምራል ከዛ ሲሰማ ትሰደዳለህ ከዛ ፊት ለፊት ትጋፈጣለህ ከዛ ወይ ድል ታገኛለህ ወይ ሺሂድ ትሆናለህ Copy

"ያልተጋቡ ወጣቶችን የምመክረው፤ እራሳቸውን ለጋብቻ እንዲያዘጋጁ፣ የትዳር ድንጋጌዎችን (ህጎችን)፣ በወንድና በሴት መካከል ያለውን ግንኙነት ህግጋት፣ ለእሱ የተፈቀደለትንና የተከለከለውን፣ በእሱ ላይ ግዴታ የሚሆነውን፣ የሚወደድለትን (ሱና የሆነውን) እና የመሳሰሉትን እንዲያውቁ ነው። ይህን የሚያደርጉት በትዳር ህይወታቸው በአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ፍርሃት (ተቅዋ) ላይ እና የላቀውና ከፍ ያለው የአላህን ሸሪዓ በመጠበቅ ላይ ለመመስረት እንዲችሉ ነው።"ይላሉ ሸይኽ አል-ሉሀይዳን 📚الأحكام المتعلقة بالزواج በዘመናችን ዑለማኦች ብቻ በዚህ ረገድ የተፃፉ ኪታቦች ከ 100 በላይ መሆኑን ደርሼበታለሁኝ::አሏህ ከሰጠህ ግዜ ቀነሰ አርገህ አጥና t.me/abduselam_addalochy11 t.me/abduselam_addalochy11

🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ

ጣፋጭ ስቃይ ብሎ ማለት በአላህ መንገድ ላይ ስትሆን የሚገጥምህ የሆነ ስቃይ ነው ይህ ስቃይ ዛሬ ላይ ሊመር ነገ ላይ ግን ትላልቅ የዲን ስኬቶች ላይ እንድትነግስ መሰረት ይሆንልሃል
إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
አብሽሩ ሰለፊዮች🙌 https://t.me/Abu_Umer1

የሶሻል ሚዲያ አንበሳ ሳይሆን የተውሂድ የሱና አንበሳ ሁኚ🙌
የሶሻል ሚዲያ አንበሳ ሳይሆን የተውሂድ የሱና አንበሳ ሁኚ🙌

ሁለተኛ ሚስት አገባሁ አትበል እህት አመጣሁልሽ በል

የማዳ ስንቅ ለቀልብዎ🫀🎧 @NasihaLishebab

አላህ ጀነትን የሚያስገባህ ተውሂድህን አይቶጂ በፖለቲካ ላይ ያለህን ብስለት ወይም አቋም አይቶ አይደለም ኢኽዋኒዝም❌

እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ! ይህ ቻናል የሱና ኡለማዎች ለተለያዩ ኢስላማዊ ጥያቄዎች በቁርኣንና በሐዲስ ማስረጃነት የሰጧቸውን ፈትዋዎች(መልሶች) የሚያገኙበት መድረክ ነው። ትክክለኛውን የዲን እውቀት ለማግኘት እና ለጥያቄዎችዎ መልስ ለማግኘት ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ። 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDX7r_ao1Y-79yIOZKj4YFA የቴሌግራም ቻናል 👇 https://t.me/Sunnah_Fatawa https://t.me/Sunnah_Fatawa

#ሸይኽ_ረቢዕ ረሒመሁሏህ።
#ሸይኽ_ረቢዕ ረሒመሁሏህ።

ዋናው ዲና ነው🙌

ውበት አይተህ ታገባ ይሆናል አብሮ የሚያኖርህ ግን አህላቅ [ስነ ምግባር] ነው!

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ🫀

ማነው ተሳዳቢው! ብዙ ጊዜ አስቤ ስንኜን ልቋጥር ፣ ስለ ታላቁ ሸይኽ በኢትዬ ምድር ፣ ወቀሳ ማይፈራ ቆራጥ ጀግና ደፋር፣ ዱኒያን ቺላ ያለ የሚኖር ከገጠር፣ መብራት ውሀ የለ መቀማጠል ነገር፣ ቆርቆሮ ቤት ሳይል በሳርቤት የሚሮር፣ ገጠር ቁጭ ብለው ያዳረሱ ሀገር፣ ለዳእዋ  ለኮርስ ሁሌ ማይበገር ፣ ልበ ሰፊ አሊም ሲያወራ ሲናገር ፣ ውጭ ውስጡ አንድ የሆነ ነገር የማይቋጥር፣ ኡስታዞች ያወጣ የበዙ እንደጠጠር፣ እድሜውንም ለጋሽ ዲኑ እንዳይደፈር፣ የደቡቡ አለኝታ ተንቀሰቃሽ ሞተር  ፣ ሸይኽ አብዱል ሀሚድ ነው ወደሌላ አትዙር። የሂፍዝን ችሎታ አላህ የገጠመው፣ ቁርአን ሀፍዞ ሀድስ የጬመረው፣ ፊቅህን ተምሮ ነህው ሶርፍ ያልቀረው፣ በላጋ መዓኒን ሀፍዞ ያስገባው፣ ኡሱሉን አዳቡን ሁሉን የሸመተው፣ ሀድስ ተፍሲርንም አላምጦ የዋጠው፣ በልጅነት እድሜ ወጣት እያለ ነው። በጥመት አካሎች ቢሆኑም ጠንካራ፣ ለሱና ሰው  ናቼው  ሆዳቼው  የራራ፣ ሌሊት እሚቆሙ ቀን ውሎ ሲያስቀራ፣ ኪታብ ወዳድ ምሁር ተውሂድ የሚዘራ፣ ከሳቼው የቆዬ ስለ ሸይኩ ያውራ። እናም አንድ ነገር ሰሞኑን ተለቆ፣ በስድብ በዝልፊያ እጂጉን ታጪቆ፣ ሸይኹን ዝቅሊያደርግ ምላሱን አዝልቆ፣ የፈተና ሞተር ያልተማረ ታጥቆ፣ ብዙውን ቀርሺቷል በተክፊር ተዘፍቆ። እጂግ የሚገርመው የአይኑ መታወር፣ መረጃ ሲያቅተው ወደ ስድብ መዞር፣ የራስን ሸሽጎ የሰዎችን መቁጥር፣ ሁሌ በባጢል ላይ ሲደነፉ መኖር፣ የተለመዴ ነው ከጦሳዎች መንደር። አንተ ደፋር ስድቡን ተወውና እስኪ መረጃ አምጣ፣ አላህንም ፈርተህ ከውሼትህ ውጣ። ማነው ተሳዳቢው ቆይ ማነው ዘረኛ፣ እናውቃቼዋለን ወሎ ሆነን እኛ ፣ ወላሂ አታቃቼው አይደሉም ዘረኛ፣ አንተ ግን ሆንክና የኢኽዋን ዘበኛ፣ ውጥርጥር ብለህ የተክፊሮች ፊኛ፣ አሊም አሊም መሳይ የኢሞ ጉረኛ፣ ፈግሞ ካንተ በላይ ጉድ አናውቅም እኛ። ጉራጌ ስልጤ እያልክ ያድስ አባዎቹን፣ በዘር ስትከፋፍል ጀማልና አብራንን፣ ወሎዎች ላይ ብቻ ስታረግ ውዳሴን፣ እየሞገታችሁ ባንድ መንሀጅ ላይ ነን፣ ውስጣችሁ ውጭ ወቶ ይሄው ስንቱን አየን። እጂግ ታዋቂ ነህ በተሳዳቢነት፣ እስኪ ትንሽ ላንሳ ትሁን ለአብነት፣ ለራስህ ጉዋደኛ ስንኝ የቋጠርካት፣ ለኢኽዋን ወንድምህ ያው የሞጫጨርካት፣ ይሄንን ይመስላል እስኪ ጉዱን ስሙት፣ የግጥሙ እርእስ ጀናዛው ሰው ሆኖ ይላል አቶ ሙስጤ  እስኪ ስሙት አቦ ነስር ስጂዳችን የድናችን ጮራ፣ በሱንዮች ደምቃ በሂዝብዮች ታፍራ፣ ትኖር የነበረች በሁሉም ተከብራ፣ አለቀሰች አሉ ባጉል ሰው ተደፍራ። በደካማ ጃሂል ያውም በደንባራ፣ ህፃን በማይባል ወይም አባውራ፣ ተንኮል የቀጠነው ያለቀ እንደጪራ፣ ሰው ይቅር ሪጅለይኒ ወገቡ ጎብራራ፣ እግሩ ቅጪጭ ያለች ሀሳቡ ሸውራራ፣ ከዶሮ ከፍ ያለ ያውም ካበሻ አውራ፣ የፈረንጂንማ ምንም ቢንጠራራ፣ እሱን አያክልም ከጃኬቱ ጋራ፣ እንደ አዎ ይመስላል ጀናዛ ይመስላል ጀናዛ ቆሞ የሚያወራ ከቀብር የወጣ በቀን በጠራራ፣ ስጋው እልቅ ያለ አቤት ሲያስፈራራ፣ አይተከው አስተንትን ጉድ ነው ያላህ ስራ። ይገርማል ሰዎች እንዳይኖሩ ጀናዛው አቅራራ፣ ብሎ ተናገረ ሂዱ ከኔ ስፍራ፣ ልቀቁልኝ ቤቴን ሁሉን እንድሰራ። እንደልቤ እንድጮህ ተንኮል እንዳወራ አለ ይህ ጀናዛ ሰው መሳይ ቀብራራ፣ ተላላኪ ምስኪን በሌላ እሚመራ ድሮም ጀናዛ ሰው ስጋ የለው ሞራ፣ በምኑ ያስባል ተሰብሮ እንደንስራ። ይነዳዋል ጀለፍ ይነዳዋል ፋራ፣ አድርጎት አረፈ የሂስድ ሀራራ፣ የተንኮል ኪራይ ቤት የሼር ጎተራ። ይላል አቶ ሙስጤ የተክፊሮች አውራ፣ ይህን ሁሉ ስድብ በግጥም ሲያወራ፣ ስሜቱን ያልገታ ነቄ መስሎ ፋራ፣ ሸይኽን ተሳዳቢ ብሎ ይህ  ቢያወራ፣ ለጤነኛ ሁሉ አላህን ለፈራ፣ ግልፅ ነው ወላሂ ተው አላህን ፍራ። ደግሞ የሚገርመው ወደ ቋንቋ ሄዴ ሸይኹንም ሳላቸው ልክ እንደ ወንበዴ፣ አብዷል ማለት ባንተ ምች ተጀመረና፣ ነብዩስ ከስድብ መቼ ተረፉና፣ አብድ ነው ደጋሚ ሳሂርና ጨምርና፣ በማሉ መች ሲገርም በነብዩ ሱና፣ ብዙም አይገርመንም ፋሽኑ አልፏልና። ደግሞ በመናደድ አቡዘርን ተቼህ ሁሌ መንጠራራት ብቻ ሆኖ ስራህ ልክ እንደ ዝንጆሮ መላጣ አይታይህ፣ ያንተ ብው ማለት ብሎ መናደድህ፣ በወራዳ ድርጊት በእኩይ ደረሶችህ፣ ብው ብያለሁ እኔ ብለህ እያወራህ፣ እራስህን ረስተህ  ሸይኹን ትተቻለህ። ሸይክ አቡዘር ማነው ብለህ ለጠየቅከኝ፣ ስለርሱ ልንገርህ ሀያ ተከተለኝ። በርታ በትንሽ ስንኞች አንድ እውነት ልናገር፣ የወሎው እንቁ ፈርጥ ከኮንቦልቻ ሀገር ሙብተድዑን ሁሉ ድምፁ ሚያንዘረዝር ሙመይዐን ኢኽዋን ያጎረሳት አፈር፣ አንበሳ ታታሪ በሰለፍያ ስም የማይደራደር፣ ሀቅን ማውራት እንጂ ለውሸት የማይኖር፣ ለተቺዎች  ትችት  ወደ  ሇላ ማይዞር፣ በሰፊ  መረጃ  አጭቆ  እሚናገር፣ ሱናን ያራመደ  ከ ወንድሞቹ ጋር፣ አለ ወሎ ምድር  ሸይኻችን አቡዘር፣ እኔም አልኩት ያ ሸይኸና ጠንክር በርታ በአቋምህ                           ብዙ አለ ሚጠብቅህ በሀቅ ላይ የወደደህ                           ለሱና ቁም ሁሌ እስካለህ፣ በጀሊሉ ተመክተህ                         ጀግን በርታ ተውሂድ ይዘህ ሰው ቢጠላህ በአቋምህ                         ቢሰድቡህም ጠላቶችህ እለፋቼው እንዳይገርምህ                           አባት ሆነህ ዱኣ አድርገህ። መልሳቼው በመረጃህ                         ባስገራሚ አንደበትህ፣ ሱንይ ሁሉ ያው ሲወድህ                        ኡለማዎች ሲያወድሱህ፣ በሱና ላይ ስላወቁህ                        ጠንክር በርታ ተመክተህ                        ሀቅ ላይ ኑር በስንፋስህ። እራስ ምታት ለተክፊሮች ፣                     ጣፋጭ ማር ነህ ለሱንዮች አስደማሚ ኪታቦችህ                      ቢያማቼውም ጠላቶችህ ሱናን ጠቅሟል እሪከርድህ                    ተፍሲር ሙሉ እንዲያ አብራርተህ፣ ኪታቦችን አስተምረህ፣ በያይነቱ እረድ አርገህ፣                     ሱናን ጠቅሟል ፅኑ አቋምህ።(2) ለሱና ሁሌ ቁም ሸይኻችን አቡዘር፣ ሙብተዲዑ ሁሉ ወደ ሀቅ እንዲዞር። እንደ ረፋድ ፀሀይ ግልፅ ነው አቋምህ፣ በሀጅር ጉዳይ ላይ በሰፊ መፃፍህ፣   በየፊቅሁ ዘርፍ ሰፋፊው ጥናትህ፣ እጂግ ይማርካል ደርስ አቀራረብህ፣ ምቀኛህ ይመራ ዛሬ የሚሰድብህ፣ ቃላትም የለኝም በምንስ ልግለፅህ፣ ለአላህ ብዬ ነው ወላሂ ስወድህ፣ ባለህበት ምድር አላህ ይጠብቅህ። አወ ያንሳቼዋል ሸይኻችን አቡዘር እረዱ ብርቱ ነው ያስግጥሀል አፈር፣ ጀምሯል አዳምጠው ገብተህ ቻናሉ ስር። ሙስጦፋ ያቼፍችፍ ይሳደብ ልምዱ ነው፣ ጃሂል ስድብ እንጂ እውቀት መች ሲገራው። እናማ አንተ ጀግና ለተሞ  ያለኸው፣ እናማ አንተ ጀግና ኮቻ ላይ ያለኸው፣ ሀቅ ወዳድ ሆነህ ነው ምቀኛህ የበዛው። እንዴ ውሻ ይጩህ በመረጃ አስተፋው፣ ይህን ያክል ካልኩኝ ብእሬ እዚ ትቁም በርቱ የኛ ጀግኖች ወሰላሙአለይኩም። ✍ኢብኑ ኢድሪስ አል–ወሎዊ ibnu_idris_public_chanal @Nikabistuwanigist @nesihetulinisa @yeselefochteketay @Abu_Umer1

🔴 ፈትዋ 🎙 በሸይኽ አ/ሀሚድ አል-ለተሚይ 🟢 ዳሩል-ሁዳ መድረሳ -ወልቂጤ ✍ ከተጠየቁት ጥያቄዎች ውስጥ:- 1 .ሀዲሱል ኢፍቲራቅ:: 2. የወጂዝ ኪታብ ባለቤት ጉዳይ:: 3 . አላህ ወደ ሰማኡ ዱንያ መውረድን በተመለከተ። 📅 ቀን: 02/11/2018 t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ🫀 @NasihaLishebab