es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Ir al canal en Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
318
Suscriptores
-424 horas
-77 días
+5430 días
Archivo de publicaciones
🌳👌በሉ በደንብ ሸር ይደረግ🌼 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀 🌳አቂደቱል           🌳ዋሲጥያ                        🌳ተጀመረ                                         🌳ተጀመረ    🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 👌ገባ ገባ በሉ 🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ለቀጥታ ስርጭት ይሔን በዚህ በኩል 👇👇👇    https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah?livestream=a63a02480ee1b1feb1

وشهد شاهد من أهلها ይህ እንግዲህ የዚህ ዘመን የኢኽዋን ዓሊምና ኢማም የሆኑት አል-ቀርዳዊ የሰይድ ቁጥብን የ‘ተ‘ክፊዐር አካሄድ (መንሃጅ) የሚያረጋግጡበት ምስክርነት ነው። ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ «አውላውያት አል-ሐረካህ አል-ኢስላሚያህ» በተሰኘወወ  መጽሐፋቸው፤(ገጽ 110) ላይ፦ "በዚህ ደረጃ ላይ የሸሂዱ የሰይድ ቁጥብ መጻሕፍት ብቅ አሉ፤ እነዚህም የመጨረሻውን የሐሳብ እድገት ደረጃውን የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ፡ ማህበረሰቡን በ‘ካ’ፊ’ር’ነት በመፈረጅ፣ ፊቅህን የማደስና የማሻሻል እንዲሁም ኢጅቲሃድን  (የማንቃት) ሐሳብን በመጠቀም ወደ ኢስላማዊ ስርዓት የሚደረገውን ጥሪ በማዘግየት፣ ከማህበረሰቡ የስሜት መገለልን (ዑዝላህ ሹዑሪያህ) ማድረግንና ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥን ጥሪ የሚያደርጉ፣ ሁሉንም ሰዎችን የማጥቃት ጂሃድ ማወጅን እንዲነሳሱ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም የመቻቻልና የለዘብተኝነት ጥሪ አድራጊዎችን የሚያናንቁና በምዕራባውያን ሥልጣኔ ፊት በየዋህነትና በስነ-ልቦና ሽንፈት የሚከተሷቸው ናቸው።" የሚሉ ትችቶቹ የኋላ ኋላ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ይህ አመለካከቱ «ፊ ዚላል አል-ቁርዓን» ሁለተኛው ዕትም ላይ እና «መዓሊም ፊጥ-ጠሪቅ» መጽሐፉ ላይ በጣም በግልጽ ጎልቶ ይታያል።»

የቀልባችንን ድርቀት ለማስወገድ እንታገል ! በዚክር እንዴት እንጠቀማለን ?! " ተውሒድን ፣ አስማእ ወስሲፍትን በአግባቡ ተገንዝበናል " ይባላል ... እውነት ነውን ? ከሰዎች እንደበቃለን - ወንጀሎችን ስንፈፅም ! ... ግን .... እስከመቼ ወደ ሐራም እየተመለከትን ... ከደርስ የተቆረጠ ምክር https://t.me/MerkezulimamiAhmed

⛔️ቆንጆ ባልሆነች ሚስቱ ላይ ለ15 ዓመታት የታገሰው ጀግና!⛔️ ታላቁ ሊቅ ኢብኑ አል-ጀውዚ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ሲሉ ዘግበዋል፦ አቡ ዑስማን አል-ኒሳቡሪ የተባሉ ደግ ሰው ነበሩ። ባለቤታቸው መርየም እንዲህ ትላለች፦ "አንድ ቀን አቡ ዑስማን በብቸኝነት ሲያርፉ አገኘሁትና፦ 'አቡ ዑስማን ሆይ! አላህ ዘንድ ይበልጥ ተስፋ የምታደርግበት (ትልቅ ዋጋ ያገኝልኛል የምትለው) ስራህ የትኛው ነው?' ብዬ ጠየቅኩት።" ●እሱም እንዲህ ሲል አስገራሚ ታሪኩን አጫወታት፦ ●"መርየም ሆይ! በወጣትነቴ አል-ረይ በተባለች ከተማ እኖር ነበር። ሰዎች እንዳገባ ቢወተውቱኝም እኔ ግን እምቢኝ ብዬ ነበር። አንድ ቀን አንዲት ሴት ወደ እኔ መጣችና እንዲህ አለችኝ፦ ● 'አቡ ዑስማን ሆይ! እንቅልፍና እረፍት እስከማጣ ድረስ እጅግ አፍቅሬሃለሁ። ልቦችን በሚገለባብጠው አላህ እለምንሃለሁ፣ ወደ እሱም እማጸንሃለሁ... እባክህ አግባኝ!'* ●እኔም፦ 'አባት አለሽ?' አልኳት። እሷም፦ 'አዎን፣ እገሌ የሚባል ስፌት ሰፊ ነው' አለችኝ። ወደ አባቷ መልእክት ልኬ ፈቃዱን ጠየቅኩ፤ እሱም በደስታ ተቀበለኝ። ምስክሮች ተጠርተው ኒካህ ተደረገና ተጋባን። ● ወደ ቤቷ ገብቼ ሳያት ግን በድንጋጤ ቆምኩ! ሴቲቱ ባለ አንድ ዓይን (ዐውራእ)፣ ሽባ/አንካሳ (ዐርጃእ) እና መልኳ እጅግ የማይስብ (ሾውሃእ) ነበረች። ያኔ ልቤ ደነገጠ፤ ነገር ግን ወዲያውኑ፦ 'አላህ ሆይ! በወሰንክልኝ ነገር ላይ ምስጋና ላንተ ይሁን' አልኩ። ● የቤተሰቦቼ አባላት እንዲህ ያለች ሴት በማግባቴ ክፉኛ ይወቅሱኝና ይተቹኝ ነበር። እኔ ግን በተቃራኒው ለእሷ ያለኝን ደግነትና እንክብካቤ ጨመርኩላት። እሷም እኔን ከመውደዷ የተነሳ ከጎኗ እንድትርቅ አትፈልግም ነበር። የእሷን ልብ ላለመስበርና ደስተኛ ለማድረግ ስል፣ የምወዳቸውን የእውቀት መድረኮችና የዑለሞች ስብሰባዎችን ትቼ አጠገቧ እቀመጥ ነበር። ● በዚህ ሁኔታ አስራ አምስት (15) ዓመታት አብረን ኖርን። መርየም ሆይ! በአላህ እምላለሁ... በውስጤ የሚሰማኝን ስቃይ ለእሷ ፈጽሞ ሳላሳይ፣ አንዳንድ ጊዜ ልክ በፍም እሳት (በከሰል) ላይ የቆምኩ ያህል እየተሰማኝ በትዕግስት አሳለፍኩ። ይህ ሁሉ የሆነው የእሷን ስሜት ለመጠበቅና በእኔ ምክንያት እንዳታዝን በማሰብ ብቻ ነበር። በመጨረሻም ሞተች... ● ስለዚህ አላህ ዘንድ ካሉኝ ስራዎች ሁሉ እጅግ ትልቅ ተስፋ የማደርግበት ተግባሬ፤ ለእሷ የነበረኝን ፍቅር ሳላጎድል፣ ልቧን ሳልሰብርና በእኔ ላይ ያላትን መልካም አመለካከት ሳላበላሽ ለ15 ዓመታት በመቻሌ ነው።" 💡 ከዚህ አስገራሚ ታሪክ የምንማረው ቁምነገር፦ ● እውነተኛ ጀግንነት፦ ጀግንነት ጠላትን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፣ ስሜትን ተቆጣጥሮ ሌላውን ሰው ማስደሰትና የሰውን ልብ መጠገን ነው። ● የአላህ ውሳኔ (ሪዳ)፦ አቡ ዑስማን በመጀመሪያ እይታው ቢደነግጥም፣ አላህ የወሰነውን በጸጋ ተቀብሎ በአመስጋኝነት ኖረ። ● የቤት ውስጥ አደራ፦ ሚስት ምንም ዓይነት የአካል ጉድለት ቢኖርባት እንኳ፣ እርሷን በክብር መያዝ የአላህ አደራ መሆኑን አሳየን። ● መሰዋዕትነት፦ ለእውቀትና ለክብር ያለውን ፍላጎት፣ ለአንዲት ምስኪን ሴት ደስታ ሲል መስዋዕት አደረገ። አላህ እንደ አቡ ዑስማን ያለ ሰፊ ደረትና ትልቅ ስነ-ምግባር ይስጠን። 🌹 ምንጭ፦ *[ ሲፈቱ ሶፍዋ - በኢብኑ አል-ጀውዚ ]* የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

[رسالة إلى كل سني سلفي :ماأشبه الليلة بالبارحه فاثبت ولا تتزعزع والموعد الجنة] الحمد لله وحده والصلاة والسلام على من لانبي وحده وبعد : فإن أهل الظلم والضلال والزيغ والبدع يتوارثون عداوتهم لأهل الحق والسنة لأن الحق الذين يدعوا إليه أهل السنة أزعج أهل الباطل وأفلسهم وهم مساكين مفاليس من الحجة والعلم والبرهان. فما لهم سلاح يحاربون به أهل السنة إلا إثارة العامة الدهماء أو تحريش السلطان واستعمال ألقاب السوء تنفيرا وتحذيرا وفي هذا الزمان سل أهل الأهواء سلاح الماضين اللمز والنبز والتعيير كفعل أسلافهم الماضين تشابهت قلوبهم وأخلاقهم ،فكما وصف أهل البدع السلف الصالحين بأوصاف منفره فكذا قام أشياعهم اليوم بمثل أعمالهم،فاليوم  يسمون السلفيين بالوهابية تارة وبالحماسة تارة وبالمدخلية تارة تنفيرا للناس منهم ،لأن السلفيين كشفوا عورهم وفضحوا ألاعيبهم  وأبرزوا للناس ضحالة علمهم وسوء مقاصدهم وزيف مناهجهم  وانحراف عقائدهم وهم ليس لديهم حجة وبرهان يقابلون بها أهل السنة إلا التعيير والأوصاف المنفره وقد شابهوا أهل البدع الأولين .يقول ابن القيم رحمه الله : |[ فما ذنبُ أهل السُّنَّة والحديث إذا نطقوا بما نطقت به النصوص، وأمسكوا عمَّا أمسكتْ عنه، ووصفوا الله بما وصف به نفسَه ووصفه رسولُه، وردُّوا تأويل الجاهلين، وانتحال المبطلِين الذين عقدوا ألوية الفتنة، وأطلقوا أَعِنَّة المحنة، وقالوا على الله وفي الله بغير علمٍ؛ فردوا باطلهم وبيَّنوا زيفهم، وكشفوا إفكهم، ونافحوا عن الله ورسوله؛ فلم يقدروا على أخذ الثأر منهم إلَّا بأن سمَّوهم مشبِّهةً ممثِّلةً مجسِّمة حشويةً.]| الصواعق المرسلة  (1-88) فيا أيها السني اثبت ولا يزلزلك نباحهم وصياحهم فهم كالذبان!!أتخاف من ذبان والله الله بالصدق مع الله والتوكل عليه فإن الله مع الذين اتقوا والذين هم محسنون والله الموعد اثبت والموعد الجنة مع محمد وصحبه وتسلى بهذا الأبيات السلفيات التي كتبها من لقي الأذى وصبر  ونصره الله ورفعه وأبقى ذكره إلى يومنا هذا شيخ الإسلام  الإمام ابن القيم تلميذ الهمام الشجاع شيخ الإسلام ابن تيمية رحمهما الله وجمعنا وإياهم مع النبيين والصديقين والشهداء والصالحين وحسن أولئك رفيقا يا أيها الرجل المريد نجاته **** اسمع مقالة ناصح معوان كن في أمورك كلها متمسكاً ****بالوحي لا بزخارف الهذيان وانصر كتاب الله والسنن التي ****جاءت عن المبعوث بالفرقان واضرب بسيف الوحي كل معطل ****ضرب المجاهد فوق كل بنان واحمل بعزم الصدق حملة مخلص ****متجرد لله غير جبان واثبت بصبرك تحت ألوية الهدى **** فإذا أصبت ففي رضا الرحمن واجعل كتاب الله والسنن التي **** ثبتت سلاحك ثم صح بجنان من ذا يبارز فليقدم نفسه **** أو من يسابق يبد في الميدان واصدع بما قال الرسول ولا تخف ****من قلة الأنصار والأعوان فالله ناصر دينه وكتابه **** والله كاف عبده بأمان لا تخش من كيد العدو ومكرهم ****فقتالهم بالكذب والبهتان فجنود أتباع الرسول ملائك **** وجنودهم فعساكر الشيطان شتان بين العسكرين فمن يكن ****متحيراً فلينظر الفئتان واثبت وقاتل تحت رايات الهدى ****واصبر فنصر الله ربك دان واذكر مقاتلهم لفرسان الهدى **** لله در مقاتل الفرسان وادرأ بلفظ النص في نحر العدا ****وارجمهم بثواقب الشهبان لا تخش كثرتهم فهم همج الورى ****وذبابه أتخاف من ذبان واشغلهم عند الجدال ببعضهم **** بعضاً فذاك الحزم للفرسان وإذا هم حملوا عليك فلا تكن **** فزعاً لحملتهم ولا بجبان واثبت ولا تحمل بلا جند فما ****هذا بمحمود لدى الشجعان فاذا رأيت عصابة الإسلام قد **** وافت عساكرها مع السلطان فهناك فاخترق الصفوف ولا تكن ****بالعاجز الواني ولا الفزعان وتعر من ثوبين من يلبسهما **** يلقى الردى بمذمة وهوان ثوب من الجهل المركب فوقه ****ثوب التعصب بئست الثوبان وتحل بالإنصاف أفخر حلة ****زينت بهاالأعطاف والكتفان واجعل شعارك خشية الرحمن مع **** نصح الرسول فحبذا الأمران وتمسكن بحبله وبوحيه **** وتوكلن حقيقة التكلان فالحق وصف الرب وهو صراطه الـ **** هادي إليه لصاحب الإيمان وهو الصراط عليه رب العرش أيـ ****ضاً وذا قد جاء في القرآن والحق منصور وممتحن فلا **** تعجب فهذي سنة الرحمن وبذاك يظهر حزبه من حربه **** ولأجل ذاك الناس طائفتان رحم الله علماءنا وجمعنا وإياهم في مستقر رحمته وكتبه العبد الفقير إلى الرحمن عبدالله بن صلفيق القاسمي الظفيري السبت الموافق الثالث والعشرين من شهر ربيع الأول لعام (١٤٤٧)من هجرة المصطفى صلى الله عليه وآله وسلم

«ከጀርባዬ አንድ ግዙፍ ተራራ!!» --------------------------- .......✍አባትነት ግዙፍ ተራራ ነው ስሙ የደመቀ፡ ለልጁ ነፍስ ሰጭ ወኔው የታመቀ፡ በህይወት እስካለ ይደምቃል ልጅነት፡ ጋሻ መከታ ነው ማዕረግ ነው ወንድነት፡ የጥበብ መነሻ ይህ ነው አባትነት፡ ልጄ የሚል ጥሪ አባት ሲያስተጋባ፡ አበጥሮ ሲለይ ምርቱን ከገለባ፡ ልጁን እንዳይደፍረው ዱርየና ሌባ፡ አለኝ ማለት ብቻ ማዕረግ ነው አባ። «አባት ሳለ አጊጥ ጀንበር ሳለ ሩጥ» ........ ከኔ የበዙ ደስታዎች ጀርባ አንድ የሆዱን በሆዱ አምቆ የያዘ የኔን ሳቅ ብቻ በጉጉት የሚጠብቅ አንድ ግዙፍ ሰው አለ። ከኔ የወጣትነት ውበትና መሽቀርቀር ጀርባ አንድ የተበሳቆለ፣ የተንከራተተ፣ ያደፈ ልብስ የለበሰ አንድ እምቅ ወኔ ያለው ሰው አለ። ......ከኔ የለሰለሱ እጆች ጀርባ አንድ የሻከሩ መዳፎች ያሉት ሰው አለ። .......ከኔ በሁለት እግር መቆም እና በራስ መተማመን ጀርባ አንድ ጠንካራ ሰው አለ ። ........ከኔ የመኖር ትርጉም እና ሰው የመሆን ማንነት ጀርባ አንድ ብልህ ሰው አለ ። .......ከኔ ዛሬና የተስፋ ነገዎቼ ጀርባ አንድ ለኔ ሲል ትናንቱን ያጣ ሰው አለ ። ......ከኔ ህይዎት መቃናት ጀርባ አንድ የጎበጠ ሰው አለ ። ......➢ከኔ ምርጥ አባወራ የመሆን ምኞት እና ለሰው የመኖር ጥበብ ጀርባ አንድ ለቤተሰቡ እንደ ሻማ እየበራ እራሱን በማቃጠል ለቤቱ ብርሀን ሁኖ የቆመ ሰው አለ። ...ያ አንድ ሁኖ ብዙ የሆነ ጀግና ያ እናትም አባትም በመሆን ፍቅርን ሳይሰስት እየለገሰ ሁሌም እና በምንም ሁኔታ ከጎኔ ሳይለይ የመከታ ክንዱን የሚዘረጋልኝ ድንቅ ሰው #ውድ_አባቴ ነው ። «ሌላውን ተውት ካርድ እንደልብ በማይገኝበት በገጠር ህይወት እየገፋ ለኔ በቀጥታ ስልክ የደወለልኝ ማንም ሳይሆን አባቴ ነው ።» .....ከእማዬ የዘጠኝ ወር ሸክም በኋላ እስከ አሁኗ ጊዜዬ ድረስ አርግዞ አምጦ ወልዶ አዝሎ ልጄ አንቀልባህኮ ዛሬም ከወገቤ አልተፈታም መቼ ይሆን ከሀሳብ የማርፈው እያለ እንባው በአይኑ ሲያቀር አሁን እየፃፍኩ ከሆሄወቹ ጋር ምስሉ የሚታየኝ ይመስለኛል። «የኔ አባት ለማንም ክፉ እንዳልመኝ፣ የማንም ማግኘት እንዳስደስተኝ፣ ምቀኝነትና ክፋት ከውስጤ እንድጠፋ እና የተሰማኝን ነገር ሳልደብቅ በነፃነትና በድፍረት እንድናገር ሳትማር ያስተማርከኝ የኔ ንጉስ አንተ ነህ ዲግር ተሸክመህ ለኔ ድግሪ የምትጨነቅ የገጠር ግዙፍ #ካንፓሴ አባ.....!!! ሁሉም አልፎ በልጅህ ኮርተህ እንደኖርክልኝ እንድኖርልህ አላህ ረጂም ሀያት ይስጥህ አባ ኢንሻ አሏህ ሁሉ ይሳካል አንድ ቀን ሰርፕራይዝ አለህ እሽ የኔ አባት እወድሀለሁ። .....ኑረዲን አል-አረብ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

ሪዝቅ ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ ማን ነው? || - ዶር ደጘሽ ብኑ ሸቢብ አልዐጅሚ = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/MohamedAljawi

​✨ የመርከዝ መናሩ ሱና ታላቅ የደስታ እና የምረቃ ጥሪ! ✨ ​📖 "ቁርኣንን የተማረና ያስተማረ ከሁሉ በላጭ ሰው ነው! ​ተማሪዎችን ከቃዒዳ ጀምሮ ቁርኣንን በነዞር የሚያስተምረው መርከዝ መናሩ ሱና
​✨ የመርከዝ መናሩ ሱና ታላቅ የደስታ እና የምረቃ ጥሪ! ✨ ​📖 "ቁርኣንን የተማረና ያስተማረ ከሁሉ በላጭ ሰው ነው! ​ተማሪዎችን ከቃዒዳ ጀምሮ  ቁርኣንን በነዞር የሚያስተምረው መርከዝ መናሩ ሱና፤ ለረጅም ጊዜያት በፅናትና በትጋት ሲማሩ የቆዩ፣ ቃዒዳ ኑራኒያን በአግባቡ ያጠናቀቁ እና ቁርኣንን በነዞር ያኸተሙ ውድ ተማሪዎቹን ለመጀመሪያ ጊዜ (#1) በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል። ​በዚህ ታላቅ የኸይር እና የደስታ መድረክ ላይ እርሶም የክብር ተጋባዣችን ነዎት! ​🎙 በዕለቱ በዳዕዋ እና በሙሀደራ የሚያደምቁን ውድ ኡስታዞቻችን፦ ❶❶ ​ሸይኽ አወል ቢን አሕመድ (ከተመቻቸው) ❶ ​ኡስታዝ ኸዲር ቢን አሕመድ ➋ ​ኡስታዝ አሚር ቢን ሙሀመድ ➌ ​ኡስታዝ አብዱል መሊክ ➍​ ኡስታዝ አቡ አዩብ ➎ ​ኡስታዝ አቡ ኢምራን ➏ ​ኡስታዝ አቡ ረያን ➐ ​ኡስታዝ አቡ ሉቅማን ➑ ​ኡስታዝ አቡ ሂባ ➒ ​ኡስታዝ አቡ ሀፍሷ ➓ ​ወንድም አቡ ማሒ 11,ወንድም አቡ ሹራ (እንዲሁም ሌሎች በርካታ ድንቅ ወንድሞቻችን የዕለቱ ድምቀቶች ይሆናሉ!) ​🌟 የዕለቱ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች፦ ●​በተማሪዎች የሚቀርቡ ልብ የሚነኩ የቁርኣን ቂርኣቶችና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ●​በኡስታዞች የሚሰጡ ጠቃሚና አነቃቂ የዳዕዋ መልእክቶች ●​የተማሪዎች የምረቃና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ​📍 ቦታ፦ ከሚሴ በኢማሙ ሻፊዒይ መስጅድ 📅 ቀን፦ 01/ ነገ/ እሑድ ⏰ ሰዓት፦ ጠዋት 2፡30 ጀምሮ
​🧕 ማስታወሻ፦ ለእናቶችና ለ እህቶች በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።
​ኧረ ምን ምን ይቀርባል ካሉን! ቤተሰብዎንና ወዳጅ ዘመድዎን ይዘው ይምጡ እና እዚያው ያዩታል ። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

~ ሃኪም እና ታማኝነት ~ ~ አንድ ሃኪም / ሃኪም ቤት ሊታከም ለመጣ ሰው ታማኝ መሆን አለበት። * የታካሚውን ሚስጥር ሊያወጣ አይፈቀድም። የታካሚውን ምስል ያለ ፈቃዱ ለሚዲያ ሊያቀርብ አይገባም።
~ ሃኪም እና ታማኝነት ~ ~ አንድ ሃኪም / ሃኪም ቤት ሊታከም ለመጣ ሰው ታማኝ መሆን አለበት። * የታካሚውን ሚስጥር ሊያወጣ አይፈቀድም። የታካሚውን ምስል ያለ ፈቃዱ ለሚዲያ ሊያቀርብ አይገባም። * ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገር ከገጠመው ወደተሻለ ቦታ መጠቆም እንጂ የሰውን ልጅ መለማመጃ ሊያደርግ አይፈቀድም። ከባድ ወንጀል ነው። * ገንዘቡን ያላግባብ ሊያስወጣው አይፈቀድም። የሰው ገንዘብ ሐራም የሚሆነው በስርቆትና በዝርፊያ ብቻ አይደለም። ምርመራና መድሃኒት በማዘዝ፣ አስተኝቶ በማከም፣ በቀዶ ህክምና፣ በየትኛውም መንገድ ባልተገባ መልኩ የታካሚውን ገንዘብ ያስወጣ ሰው የሰው ገንዘብ እየዘረፈ ነው። ይህን ያደረገ ሰው እያንዳንዱ ሰው ገንዘቡን እንዴት እንዳመጣው እና በምን እንዳወጣው በሚጠየቅበት አስፈሪው የቂያማ ቀን ወዮለት። ዛሬ ያላግባብ ለተወሰደ ገንዘብ ሁሉ ነገ ጥብቅ ሂሳብ አለ። ብር በብር አይመለስም። ከመልካም ስራህ ነው ተላልፎ የሚሰጠው። እሱ ካልበቃ የተበዳይ ወንጀል ነው ባንተ ላይ የሚጣለው። ለማይረባ አላፊ ዱንያ ዘላለማዊ ህይወትን ከማጨለም መጠንቀቅ ይገባል። (ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 30/2014) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

يجتمع في أهل البدع الجهل والهوى والتعصّب لباطلهم. الشيخ عبدالله النجمي حفظه الله تعالى

Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል 🍖በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 🍒       ➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች ላላቸው  🍯 የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

📣📣📣አስደሳች ዜና ለአናራት ማህበረሰብ በሙሉ ሳምንታዊ ፕሮግራማችን አሁንም እደቀጠለ ነው የነገው ጁመዕ ደሞ በደገር ከተማ አናራት 🌹🌹 ተጋበዥ ኡስታዞች 🌹 🥇ሸይኽ ዑስማን 🥈ኡስታዝ አረ
📣📣📣አስደሳች ዜና ለአናራት ማህበረሰብ በሙሉ ሳምንታዊ ፕሮግራማችን አሁንም እደቀጠለ ነው የነገው ጁመዕ ደሞ            በደገር ከተማ አናራት   🌹🌹 ተጋበዥ ኡስታዞች 🌹 🥇ሸይኽ ዑስማን 🥈ኡስታዝ አረቡ ሰዒድ 🥉ወንድም ጀማልሙህድን
መቅረት ቀርቶ ማርፈድ ያስቆጫል
በአካል መገኘት ለማችሉ 👇👇 https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea

መድ'ኸሊይ እንዳትሆን! ~ ሸይኽ ረቢዕ አልመድ'ኸሊይ - ረሒመሁላህ - እንደማንኛውም ዓሊም ናቸው። ይሄ ደረጃቸውን ዝቅ ማድረግ አይደለም። ከሳቸው የሚበልጡ ታላላቅ ዑለማኦችን በጭፍን መከተል አይፈቀድም ስንል ደረጃቸውን ዝቅ ማድረግ እንደማይሆነው ማለት ነው። ረቢዕ ልክ እንደሌሎቹ ዓሊሞች በየትኛውም ርእስ ላይ ቢሆን ፍፁም አይደሉም። በትንሽ በትልቁ በሸይኽ ረቢዕ ንግግር የሚያስፈራራ ቢኖር ራሱን ነው የሚሸውደው። ሱናን እከተላለሁ የሚል አካል በየትኛውም ዓሊም ላይ ያለው ምልከታ ለከት ሊኖረው ይገባል። አንድን ዓሊም መለኪያም፣ መስፈሪያም፣ መቁረጫም ማድረግ አይገባም። ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ - ሐፊዞሁላህ - የሌሎች ዓሊሞችን ንግግር ገሸሽ በማድረግ የሸይኽ ረቢዕን ንግግር በተለዬ የሚይዙ ስለሆኑ ሰዎች ሲጠየቁ እንዲህ ነበር ያሉት፦ يعني جعلوه رسولا، جعلوا ربيع رسولا، جعلوه رسولا، وهذا باطل، هذا باطل، ربيع ... يخطيء و يصيب و لا هو المييزان، الميزان: كلام الله و كلام الرسول، فمن قال: الميزان ربيع، هذا باطل. "መልእክተኛ አደረጉት ማለት ነው?! ረቢዕን መልእክተኛ አደረጉት?! ይሄ ውድቅ ነው። ይሄ ውድቅ ነው። ረቢዕ ... ይስታል፣ ያገኛል። ሚዛን አይደለም። ሚዛኑ የአላህ ንግግር እና የመልእክተኛው ንግግር ነው። ሚዛኑ ረቢዕ ነው የሚል ይሄ ውድቅ ንግግር ነው።" [ከድምፅ ቅጅ የተወሰደ ነው።] ስለዚህ የአልባኒይ፣ የኢብኑ ባዝ፣ የኢብኑ ዑሠይሚን፣ ወዘተ ንግግር በጭፍን እንደማይወሰደው የረቢዕ ንግግርም በጭፍን አይወሰድም። ረቢዕ በሌሎች መሻይኾች ላይ የሚናገሩትም በማስረጃ የተደገፈ ሲሆን ይወሰዳል፣ ካልሆነ ይጣላል። እንጂ ተናጋሪው ረቢዕ በመሆናቸው ብቻ ይወሰዳል ማለት አይደለም። አልባኒያ፣ ባዚያ፣ ዑሠይሚኒያ፣ ፈውዛኒያ፣ ... የሚባል መዝሀብ እንደሌለው መድ'ኸሊያ የሚባል መዝሀብም የለም። ስለዚህ አኢማዎችን በጭፍን የሚከተል ሐነፊይ፣ ማሊኪይ፣ ሻፊዒይ፣ ሐንበሊይ፣ ... መሆን እንደሌለብህ ሁሉ ረቢዕን በጭፍን የሚከተል መድ'ኸሊይ ልትሆንም አይገባም። እዚህ ላይ በቃል ደረጃ ችግር የለም። በተግባር ግን በተለያዩ መሻይኾች ላይ ድንበር ማለፍ ስላለ ጥንቃቄ እንዲኖረን ማስታወስ ነው የፈለግኩት። (ለጥጠው ሌላ ትርጉም ከሰጡ በኋላ በራሳቸው ምናብ ላይ ነብር ሆነው ለረድ የሚነሱ እንደሚኖሩ እጠብቃለሁ።) በተረፈ የኢኽ'ዋን ጀሌዎች እዚህ እንዳትመጡ። የዚህ ፅሑፍ ጭብጥ በቅርብም በሩቅም ከናንተ ጋር የሚገናኝ አይደለም። የኢኽ'ዋን ቡድን ዘንድ የአንጃቸውን ጥመት ከተናገርክ፣ የነ ሐሰን አልበና፣ ሰይድ ቁጥብ፣ ቀርዷዊይ፣ ... ጥፉ አካሄዶች ካስጠነቀቅክ፣ ... በኢኽ'ዋን ቫይረስ በተጠቁ አካላት ዘንድ አንተ መድ'ኸሊይ ወይም ጃ'ሚይ ነህ። ልክ የሙታን አምልኮን፣ በአላህ ሲፋት ላይ ማራቆትን ስታወግዝ "ወሃ'ቢይ" እንደምትባለው ማለት ነው። ለነዚህ ሸይኽ ዒምራን ዐሊይ ሪድዋን አልፋሪሲይ - ረሒመሁላህ - እንዳሉት እንላለን፦ قُـلْ لِلَّذِي اتَّـخَـذَ الـتَّـجَـهُّـمَ مَـرْكَـبًـا وَ رَآهُ دِيـنًـا و ارْتَــضَـاهُ مَـذْهَــــبًـا وَ لِـمَـذهَبِ الأَبـــرَارِ صَارَ مُـكَـذِّبـًـا إنْ كَانَ تَـابِـعُ أَحـمَــــدٍ مُـتَـوَهِّــبًـا *** فَـأَنـا الـمُــــقِـرُّ بِـأَ نَّـنِـي وَهَّـــابِي (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 17/2016) = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

🍀ዛሬ ጁሙዓ ነው 🍀 👇 *ሶሉ አለ ነቢይ ﷺ* *አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድ ﷺ * اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ
🍀ዛሬ ጁሙዓ ነው 🍀             👇               *ሶሉ አለ ነቢይ  ﷺ* *አላሁመ ሶሊ  ወሰሊም   አላ  ነቢይና  ሙሀመድ ﷺ * اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ 🖊خطبتنا اليوم
في التحذير من السحر والشعوذة

​أُمَّاهُ... ፡ እናቴ ሆይ... ​لَوْ كَانَ عُمْرُكِ بِيَدِي لَزِدْتُهُ ​፡ እድሜሽ በእኔ እጅ ቢሆን ኖሮ እጨምርልሽ ነበር። ​وَلَكِنَّهُ بِيَدِ رَبِّي
​أُمَّاهُ... ፡ እናቴ ሆይ... ​لَوْ كَانَ عُمْرُكِ بِيَدِي لَزِدْتُهُ ​፡ እድሜሽ በእኔ እጅ ቢሆን ኖሮ እጨምርልሽ ነበር። ​وَلَكِنَّهُ بِيَدِ رَبِّي ​፡ ነገር ግን (እድሜሽ) በጌታዬ እጅ ነው። ​يا الله اِحمِ أُمِّي يا الله ​፡ አላህ ሆይ! እናቴን ጠብቅልኝ አላህ ሆይ። ​أُمَّاهُ... ​፡ እናቴ ሆይ... ​خُذِي مِنْ صِحَّتِي وَلاَ تَمْرَضِي ​፡ ከጤናዬ ወስደሽ አትታመሚ። ​خُذِي مِنْ رَاحَتِي وَلاَ تَتْعَبِي ​፡ ከእረፍቴ ወስደሽ አትደክሚ። ​خُذِي مِنْ بَسْمَتِي وَلاَ تَبْكِي ​፡ ከሳቄ/ከፈገግታዬ ወስደሽ አታልቅሺ። ​خُذِي مِنْ فَرْحَتِي وَلاَ تَحْزَنِي ​፡ ከደስታዬ ወስደሽ አትዘኚ

ብናገኝም ብናጣም ጤና ብንሆንም ብንታመምም ከማመስገን ወደኋላ አንልም። ما فعله الجليل فهو جميل الحمد لله
ብናገኝም ብናጣም ጤና ብንሆንም ብንታመምም ከማመስገን ወደኋላ አንልም። ما فعله الجليل فهو جميل
الحمد لله

تلاوة صباحيَّة محبَّرة لسورة الكهف. 🎙الشيخ: بندر بليلة. t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie