ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Ir al canal en Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
320
Suscriptores
+124 horas
-47 días
+5530 días
Archivo de publicaciones
አንድም ለፍርሀት፤ አንድም ለተስፋ!ስቃይ በሞላበት የሕይወት ሰማይ ስር ስንከንፍ፣ ሞትን ብንመኝም፣ ልባችን ቢደማም መኖረን መርጠን መብረራችንን የቀጠልነው ለሁለት ነገር ስንል ብቻ ነው። አንድም ለፍርሀት፣ አንድም ለተስፋ። ለፍርሀት ቁጣውንና ቅጣቱን ሸሽተን፤ ለተስፋ ደግሞ እዝነቱንና ውዴታውን ከጅለን። አላህን መፍራት አንዱ ክንፍ ሲሆን፣ እዝነቱን መከጀል ደግሞ ሌላኛው ክንፍ ነው። ቀልባችን በወንጀል ፍላጻ ስትወጋ፣ ፍርሀቱን ጥለን «አብሽር አላህ መሀሪ ነው» ብለን፣ በተስፋ ብቻ ለመብረር ከሞከርን፣ ከሰርን፣ ጣፋንም። በአንድ ክንፍ መብረር የለም። ከፍታ የለም። ሰላም የለም። ነፃነት የለም። ማረፍም የለም። እዝነቱንም ጥለን ቅጥ ባጣ ሰቆቃ ተስፋ ቆርጠን በፍርሀት ከከነፍን፣ አሁንም ውድቀት፣ አሁንም ዝቅጠት ነው። ቀልባችን ብትሞትም፣ በወንጀል የቆሰለውን ልባችን በአላህ ውዴታ እያከምን፣ በተስፋና በፍርሀት ክንፍ ከፍ ብለን መብረራችንን እንቀጥላለን። እንጂማ ድሮ ወድቀን ነበር፤ ድሮም ሞተን ነበር። በስቃዩ ዓለም ስትበሩ አንዳዴ መንገዱ ይረዝማል። የተስፋ ክንፋችሁ ይዝላል። «እንደው መቼ ይሆን ከማረፊያዬ የምደርሰው?! መቼ ይሆን ነፍሴ እርፍ የምትለው?» ትሉ ይሆናል።
ግን አብሽሩ! ዱንያ መቼም የሙስሊም ማረፊያው አይደለችም አይደል? ግድ የለም! በተስፋ፣ በፍርሀትና በላህ ውዴታ መብረራችንን እንቀጥል። ጀነት ላይ እርፍ እስክንል ድረስ!
✍️ ኢብኑ አይደሩስRepost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በአካባቢያችሁ ስም ዲናችሁን መማማሪያ፣ አንገብጋቢ መልእክቶችን መለዋወጫ፣ መሻይኾችን፣ ደረሶችንና አቅመ ደካማ ወገኖችን ማገዣ፣ ጎበዝ ተማሪዎችን ማበረታቻ፣ ... የቴሌግራም ወይም መሰል መሰባሰቢያ ግሩፕ/ ቻናል ይኑራችሁ።
* ከቻላችሁ የራሳችሁን፣ ካልተቻለ ከሌሎች ምንጮች በመውሰድ ጠቃሚ መልእክቶችን ማሰራጨት፣
* ከማህበራዊ ሚዲያ ባለፈ መሬት ላይ ስራ እንዲኖር እንዳቅማችሁ ሞክሩ።
* አካባቢያችሁ ኢስላማዊ እውቀት የራቀው ከሆነ የትምህርት አሰጣጡ የህብረተሰቡን የግንዛቤ መጠን ያገናዘበ ይሁን። በቅድሚያ መሰረታዊ የእስልምና ክፍሎች ማሳወቅ፣ ከከባባድ ወንጀሎች ማስጠንቀቅ፣ መተዛዘንና መተባበር እንዲኖር መስራት ላይ ማተኮር፣
* በተቻለ መጠን ትምህርታችን ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ያተኮረ ይሁን። የመሻይኾች ስም በሌሎች አካላት ቀድሞ የጠለሸ ከሆነ ስም እየጠቀስን ከምናስበረግግ የምንፈልገውን መልእክት ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ተመስርተን ብናስተምር። ካስፈለገ ብዙም ስማቸው ግርታ የማያስነሳ የሆኑ የጥንት ዑለማኦችን ማጣቀስ፣
* ስብስቡ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ የሆኑ ቡድናዊ ጉዳዮችን በማቀንቀን መነታረኪያ እንዳይሆን መጠንቀቅ፣
* ቁርኣን ለልጆች የምናስተምርበት መንገድ የተሻለ ጥራት እንዲኖረው መጣር፣
* በደረስነት ላይ የተሰማሩ ተወላጆች ካሉ በምንችለው መልኩ ከጎናቸው መቆም። ሁልጊዜ ኡስታዝ ፈልጉልን ከማለት የራስን ልጅ እንደማብቃት ያለ የተሻለ አማራጭ የለም። ሩቅ የመሰለን ነገር ባጭር ጊዜ ይሳካል። ከጎኑ ስንቆም አደራም እያሸከምነው እንደሆነ ይታወቅ።
* ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የዓመቱ መጀመሪያ ላይ ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ ... አስተባብሮ ማቅረብ እና የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን መጨረሻ ላይ በመሸለም ሌሎቹን ማነቃቃት ትልቅ ስራ ነው። ሲታገዝ የነበረ አንድ ተማሪ ተሳክቶለት ቁም ነገር ላይ ቢደርስ አካባቢውን፣ ወገኑን አይረሳም።
* በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መተጋገዝ ለደዕዋ ስራ በጣም አስፈላጊ ነውና በዚህም ላይ መስራት ይገባል። ረዳት የሌላቸው እናቶችንና አባቶችን ማገዝ፣ ያዘመመ ጎጇቸውን ማቃናት፣ እርሻ ካላቸው አስተባብሮ ማረስ፣ የቲሞችን መርዳት፣ ወዘተ.
* ወጣቱን ከሱስ ለማውጣት ከማስተማር ባሻገር ከዲናቸው እንዳይርቁ አድርጎ አማራጮችን መዘርጋት። ለምሳሌ የእግር ኳስ እና የመረብ ኳስ ማመቻቸት፣ የቴኳንዶና መሰል ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣
* በዓመቱ መጨረሻ ላይ የተሰሩ ስራዎችን ለህበረተሰቡ በማቅረብ የተሻለ ትስስርና መነቃቃትን መፍጠር፣
* በተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ተወላጆችን ማስተባበር። ለስራው እገዛ የሚያደርጉ ከሆነ አፈፃፀሞችን በማሳየት ላይ ማስረጃ የሚሆኑ የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ የተሻለ መተማመን እንዲኖር፣ ሌሎች አህለል ኸይሮችን ለማሳየት እና ማህበረሰቡን ለማነሳሳት መጠቀም ዑለማኦች የሚፈቅዱት ነው። ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሱለይማን አር-ሩሐይሊይ፣ ወዘተ.
* በማስተባበር ላይ የሚደክሙ አካላትን ሞራላቸው እንዳይቀዛቀዝ ትርጉም ያለው እገዛ ማድረግ፣
* ወሳኝ እገዛ የሚያደርጉ ወገኖችን ማመስገን እና ኢኽላሳቸውን በማይጎዳ መልኩ እውቅና መስጠት፣
* ባጠቃላይ ሂደቱ ላይ አላህን መፍራት፣ ኢኽላስ፣ ሙታበዐህ፣ ስሜትን መቆጣጠር፣ ስክነት፣ ... እንዳይርቀው አጥብቆ መመካከር ይገባል። እንዲህ አይነት ስራ ላይ ንትርክና መለያየት የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነውና አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
እነዚህ እና መሰል ስራዎች በያካባቢው ቢሰራባቸው ውጤታቸው ቀላል አይደለም። ድንገት አላህ ያለለት ሊሰራው ይችላል በሚል ነው ማስታወስ የፈለግኩት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ታቢዒዩ ሶፍዋን ብኑ ሱለይማን እንዲህ ብለዋል፦
ليأتين على الناس زمان ، تكون هِمّةُ أحدهم فيه : بطنُهُ، ودينُهُ : هواه.
"በሰዎች ላይ ሀሳባቸው ሁሉ ሆዳቸው፣ ሃይማኖታቸው ደግሞ ስሜታቸው የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል።"
[አልጁዕ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ ፡ 261]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
☝️ ዐርብኛ የምትችሉ እህቶችና ወንድሞች ይህን ቻናል ተጠቀሙበት።
📚የመን ላይ ባሉ ታላላቅ ዑለሞችና መሻይኾች ተቀርተው ያለቁ እንድሁም አሁን ላይ እየተቀሩ ያለ ደርሶችን ስብስቦ ይዟል!
Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን
ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ
የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል
🍖በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 🍒
➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች
ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች
ላላቸው
🍯 የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ
👉 @Quran_mylife1
የብዙዎቻችን የውስጥ ስብራት የሚገልጽ "አንድ ሀቅ" አለ።እሱም ሕመም መጀመሪያ ላይ "እንግዳ" ነው፤ በኋላ ግን "መኖርያ" ይሆናል። መድኃኒት መፈለጋችንን የምናቆመው ሕመሙ ጠፍቶ ሳይሆን፣ ሕመሙ የኛ አንድ አካል ሆኖ ስለሚዋሃድህ ነው።
"የሆነ ጊዜ ላይ... ሕመማችንን ማከም እንተዋለን፤ ተሽሎን ሳይሆን ሕመሙን ለምደነው ነው።"
ይህ ንግግር በውስጡ ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮችን ይዟል። መጀመሪያ ላይ ሕመም (የልብ ስብራት፣ህመም ስቃይ የሰው መራቅ፣ ማጣት ወይም ተስፋ መቁረጥ) ሲመጣብን እንታገላለን። እናለቅሳለን፣ መፍትሄ እንፈልጋለን፣ "ለምን እኔ?" ብለን እንጮኻለን። ያኔ ሕመሙ እንደ እሳት ይፋጃል።
ነገር ግን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ፣ ጩኸታችን ወደ ዝምታ ይቀየራል። የቆሰለው ልባችን መድኃኒት መፈለጉን ያቆማል። ይህ ግን "ድኗል" ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ሕመሙ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ሆኗል ማለት ነው። ልክ እንደምንለብሰው ልብስ፣ ልክ እንደምንተነፍሰው አየር... ሕመሙ አብሮን ይውላል፣ አብሮን ያድራል።
✨ ታድያ ሕመምን መልመድ ድክመት ነውን? ✨
በፍጹም! ሕመምን መልመድ ማለት ትልቅ "ጽናት" (Resilience) ማለት ነው።
* ሕመሙ እያለ ፈገግ ማለት መቻል፤
* ልባችን እንደቆሰለ ለሰዎች መልካም መዋል፤
* ውስጣችን እየደማ የሰዎችን እንባ ማበስ... ይህ ትልቅነት ነው።
መልመድ ማለት ሕመሙን "ማሸነፍ" ሳይሆን ከሕመሙ ጋር "መኖር" መቻል ነው። ብዙዎቻችን ዛሬ የምናሳየው ፈገግታ የጤነኝነት ሳይሆን፣ የለመድነው ሕመም ውጤት ነው። በሰዎች ዘንድ "ጠንክሯል" ተብሎ የሚታሰበው ልብ፣ ውስጥ ውስጡን በጠባሳ የተሞላ ሊሆን ይችላል።
🕯️ ሶብር ሊኖረን ይገባል በእስልምናችን "ሶብር" (ትዕግስት) ማለት ሕመሙ እንዲጠፋ መመኘት ብቻ አይደለም። ይልቁንም ሕመሙ ባለበት ሁኔታ አላህን እያመሰገኑ ቀጥ ብሎ መቆም ነው። "አልሐምዱሊላህ" የምንለው ነገር ሁሉ ስለተስተካከለ ሳይሆን፣ በሕመሙ ውስጥም ቢሆን አላህ የሰጠንን ጥንካሬ ስለምናምን ነው።
⚠️ ወዳጆቼ ለቆሰለው ልባችን እንዲህ እንበለው፦ "ሕመሜን ብለምደውም እንኳ፣ አላህ ነገ የተሻለ ነገር እንደሚሰጠኝ ተስፋ አልቆርጥም። ጠባሳዬ የጥንካሬዬ ምልክት ነው እንጂ የሽንፈቴ አይደለም። ዛሬ ከሕመሙ ጋር መኖር የለመድኩት፣ ነገ ደስታን በደንብ እንዳጣጥም ሊያስተምረኝ ይሆናል።"
ባለንበት ሕመም ውስጥ ሆነን ቀጥ ብለን በመቆማችን እኛ ጀግኖች ነን! አላህ ሕመማቸውን ለምደው ሳይሰበሩ ለሚኖሩት ሁሉ ሰላሙንና እረፍቱን ይላክላቸው።
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለሶስቱ "ዝሆኖች"!
~
ትግራዋይ ነኝ ታታሪ - ስራዬን ብቻ የምሰራ
ትብታባችሁ የማይገባኝ - ለፍቶ አዳሪ ነኝ አማራ
ይሁንታችሁ የማያሻኝ - ኦሮሞ ነኝ ዋዠራ
የለት ጉርሴን የማሳድድ - እሩቅ ነኝ ከናንተ ሴራ
ፍጥጫችሁ ማይጥመኝ - ሁሌ የሚሆንብኝ ግራ
ከጫካው አውሬ በላይ - ፍረጃችሁን የምፈራ
አንዱ እንዳይገድለኝ በጨለማ - አንዱ እንዳያስረኝ በጠራራ
ልርቃችሁ የሚከብደኝ - ልቀርባችሁ የምፈራ
ከዝርፊያችሁ የሌለሁኝ - ብጣሽ ያላየሁ ሰባራ
ከፌሽታችሁ ያልታደምኩኝ - ከጭፈራው ከዳንኪራ
ጦሳችሁ ግን የሚተርፈኝ - ባልዋልኩበት የምጠራ
ፍቅራችሁ ለይቶ አግላይ - ጥላችሁ ሁለት ግራ
ምቾት ድሎታችሁ የግል - ሰቀቀናችን የጋራ
የግጭት ጅምላ አቅራቢ - የብሶት የመከራ
ደም መጣጭ እንደ መዥገር - እንብላው ባይ በየተራ
እስቲ አርፋችሁ አሳርፉን - ለሰላም ቁሙ በጋራ።
* አብዛኛው ያገሪቱ ችግር መነሻ የሶስቱ ብሄር #ፖለቲከኞች ስግብግብ ፖለቲካ ነው። ሶስቱም የራሳቸውን ጥለው ወደ ሌላው ጣት ይቀስራሉ። እነሱ ባልተግባቡበት የሃገሪቱ ሰላም የራቀ ነው። በነሱ ጦስ ፍዳቸውን የሚያዩት ከየብሄሮቹ የወጡት ምስኪኖች ናቸው። አላህ ሁሉንም ልቦና ይስጣቸው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 01/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አልሓሪሥ ብኑ ሐቢብ ስምንት ልጆቹን በሞት አጣ። በዚህ መሀል አንድ በጉ በተኩላ የተበላችበት ሰው አዝኖ ሲያለቅስ አየ። በዚህን ጊዜ አልሓሪሥ ለሰውየው አንዲት ግመል ሰጠውና፦ "ይህችን በበግህ ምትክ ውሰድ፤ ማልቀስን ግን ለሚገባው (እውነተኛ ሐዘን ላለበት) ሰው ተወው" አለው።
📚 ዑዩኑል አኽባር — ኢብኑ ቁተይባህ
"እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" ይላል ያገራችን ብሂል። ሆድ የባሰው ሁሉ የከፋ ሁኔታ የገጠማቸውን ቢያስብ አርፎ ይቀመጥ ነበር።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
ስለ ኢኽዋነል ሙፍሲድን የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ 42 አከባቢ ሙሓደራወችኢኽዋነል ሙስሊሚን እና ፓለቲካ ኢኽዋን እነማን ናቸው ኢኽዋን እና ሀድስ ኢኽዋን ይገለሀል ኢኽዋን እና ችግራቸው ኢኽዋን ሙፍሲድን ኢኽዋነል ሙፍሲድ ኢኽዋነል ሙስሊሚን እና አቂዳ ኢኽዋን እና ቡድተኝነት የሀገራችን ኢኽዋኖች ለምንድነው ኢኽዋኖች ኢኽዋን እና ስልጣን ኢኽዋን እና ኡዙር ኢኽዋን እና ኢሀድግ ኢኽዋን እና ኢብኑ ባዝ ኢኽዋን እና ሙብተድእ ኢኽዋን እና ዱአ የኢኽዋን ዱአቶች ኢኽዋኖች እነማን ናቸው ኢኽዋኖች ለምን ተበጣበጡ የኢኽዋኖች መገለጫ ኢኽዋኖች ከተስማሙ ከሸይጣንም ጋር ይሰራሉ ኢኽዋን እና ኡስማን ሰሀባው የኢኽዋን 2ቱ መስራቾች ኢኽዋን እና መውሊድ ኢኽዋን እና ድሞክራሲ ኢኽዋን ሱሩሪያ ኢኽዋን እና ሱፍያ ኢኽዋን ድሮ እና ዘንድሮ ኢኽዋንን ሳታቅ ኢኽዋን ባጭሩ ኢኽዋን እና መሪዎቻቸው ኢኽዋንን ተጠንቀቋቸው ኢኽዋን እና ስልክ ምልልስ ኢኽዋን እና ፖለቲካ ኢኽዋን እና ሽርክ ኢኽዋን ጎጂወች የኢኽዋን ድፍረት ኢኽዋን ጠላቶቻችን ናቸው የኢኽዋኖች ጥመት
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«እናውቃለን»
-------------------
ህይወት ዑደት ውስጥ በመኖር ጎዳና፡
በሰው መሆን አለም ስርዓትና ዳና፡
እጂግ ብዙ ነገር እያየነው ሆኗል፡
የስንት ወጣት እቅድ ስንት ቦታ ባክኗል፡
በሰፊው ጎዳና ጉዞ እየጀመሩ፡
ስኬት ላይ ለመድረስ መስመር ያሰመሩ፡
በፍቅር ጥላ ስር ሰላም የቀመሩ፡
መንገድ ለያይቷቸው ሜዳ ላይ የቀሩ፡
ከባድ ስርቻ ስር የተቀረቀሩ፡
በልብ አዳራሽ ላይ ፍቅር እንደሰሩ፡
እናውቃለን ጥንዶች ለትርፍ የከሰሩ፡
ዛሬ ተለያይተው ይነፋፈቃሉ፡
አልጠፋም ህያው ነው የትዝታው ቃሉ፡
ህይወት እንደዚህ ነች ብለው ይስቃሉ፡
የአሏህ ውሳኔ በዚህ ተፈፅሟል፡
እንደዚህ ነች ዱንያ ሆኖ ተደምድሟል፡
በትዝታ ፀዳል ሁሉም ልቡን ታሟል፡
ግና ተለያዩ የአሏህ ቀደር ቀድሟል፡
.....እንጂማ......!!
ተዋደው ተላምደው ሊጋቡ ቀጥረው፡
ፕላን አዘጋጅተው ቀን ሰዓቱን ቆጥረው፡
በሞት የተለዩ ስንቶችን አይተናል፡
አሏህ ያለው ሆነ ብለን እንላለን፡
መመኪያ ነውና በሱ እንፅናናለን፡
ያልጠበቅነው ሆኗል ይህን እናውቃለን፡
.....ኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from ስለ ቀልባችን
ወዐለይኩም ሰላም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
ውድ ወንድሜ፣ እንዲሁም በውጤቱ ምክንያት ልባችሁ ለተሰበረ፣ ግራ ለገባችሁ ውድ እህትና ወንድሞቼ በሙሉ፤
በመጀመሪያ ደረጃ ጭንቀታችሁ ይገባኛል። ለወራት ደክማችሁ፣ እንቅልፍ አጥታችሁ ያሰባችሁት ውጤት ሳይሳካ ሲቀር መከፋት ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን እባካችሁ ተረጋጉ፤ ረጋ ብላችሁ አስተውሉ!
💡 የኢንትራንስ ፈተና ውጤት ያላሰባችሁት መሆን ማለት የዱኒያ ስኬታችሁ ተቋረጠ ማለት በፍፁም አይደለም! አላህ ለአንድ ባሪያው አንድን በር ሲዘጋበት ከዚያ የተሻለ ሰፊ በር ሳይከፍትለት አይቀርም።
አላህ ለእናንተ ያሰበው መልካም ነገር እናንተ ዛሬ ከምታስቡትና ከምትመኙት እጅግ የላቀ ነው። እኛ በጠባቡ እይታችን «ይህ ካልሆነ ጠፋሁ» እንላለን፤ አላህ ግን በሰፊው እውቀቱ የተሻለውን መንገድ ያዘጋጅልናል። ስለዚህ በአላህ ውሳኔ ላይ እመኑ፤ «አልሐምዱሊላህ አላ ኩሊ ሐል» በሉ።
✏️ሌላው...በዚህ ዘመን ስለተማሩና ዲግሪ ስለያዙ ብቻ ስኬታማ ይሆናል ማለት አይደለም። በተቃራኒው ዛሬ ላይ በቢዝነሱ፣ በቴክኖሎጂውና በተለያዩ ዘርፎች ትልቅ ደረጃ የደረሱ በርካታ ሰዎች መደበኛውን የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ያላጠናቀቁ ወይም ፈፅሞ ያልተማሩ ናቸው።
ይገርማችኃል...እኔ በኮምፒውተር ሳይንስ ተመርቄ ዛሬ የምሰራው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው። ይህ የሚያሳየው ዩኒቨርሲቲ ገብተህ በተማርክበት ትምህርት ትሰራለህ የሚል ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌለ ነው። የሕይወት ሜዳ ሰፊና ያልተገመተ ነው። ትልቁ ነገር የትምህርት ዲግሪ መያዝ ሳይሆን ራስን ለገበያውና ለዘመኑ ብቁ አድርጎ ማዘጋጀት ነው።
✏️ሐቢቢ ዘመኑ የሙያ እና የ Skill እንጂ የዲግሪ ብቻ አይደለም! ብልህ ሰው ዛሬ ባጣው ነገር ላይ ቁጭ ብሎ አያለቅስም፤ ነገን ለመለወጥ ይነሳል! ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው።
✔️አጫጭርና ጠቃሚ ኮርሶችን በመውሰድ በቤት ውስጥ ሆናችሁ በኢንተርኔት ገቢ የምታገኙባቸውን ሙያዎች ተማሩ።
- Web Development
- Graphic Design
- Video Editing
- ዲጂታል ማርኬቲንግ እና መሰል ዘመናዊ ክህሎቶች ተማሩ።
ወዳጆቼ...ዛሬውኑ ጭንቀቱንና ራስን መውቀሱን አቁሙ። ዛሬ ያጋጠማችሁ ነገር ውድቀት ሳይሆን አቅጣጫ መቀየሪያ
ነው። ወድቆ መቅረት እንጂ መውደቅ ራሱ ውድቀት አይደለም!
አላህ ላይ ተወኩል አድርጉ፣ ወገባችሁን ታጥቃችሁ አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ተነሱ። ዛሬ የተዘጋባችሁ በር ነገ ለሚከፈተው ትልቅ የስኬት በር መነሻ ሊሆን ይችላል።
አላህ ልባችሁን ያረጋጋላችሁ፣ የተሻለውን መንገድ ይምራችሁ፣ በዱኒያም በአኼራም ስኬታማ ያድርጋችሁ!
🪶ወንድምህ አቡ ሱፍያን
➦አስደሳች ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካትሁ ለሚመጡት ተከታታይ ወራቶች የሚደረግ የመጀመሪያ ዙር የኪታብ ትምህርት ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ
በዚህ ትምህርት ላይ ታላላቅ መሻኢኾች እና ኡስታዞች የሚገኙበት ነው
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
የመጀመሪያው ትምህርትም ሰኞ ምሽት
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺
♦️በሳኡዲ10:00
♦️በኢትዮ4:00
♦️ በዱባይ 11:00
ኸዛ በኋላ ያለው ሰዓት በምክክር ይሆናል
ትምህርቱን የሚሠጡት መሻኢኾችና ኡስታዞች 👇👇👇👇👇👇👇
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
👉◀◀1. ሸይኽ ጀማል አዝ-ዘሀቢ▶▶ቀዋዒዱል ሙስላን
◀◀2.ሸይኽ ሙሐመድ غዛል ▶▶አቂደቱል ዋሲጥያ
◀◀3.ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ▶▶ ዶላለቱል አህባሽ
◀◀4.ሸይኽ ሙሐመድ መኪን▶▶ ኡሡሉ ሠላሳ
◀◀5.ሸይኽ ሙሐመድ አሚን▶▶ቀዋዒዱል አርበዕ
◀◀6.ሸይኽ አህመድ አወቀ ▶▶አርበዒን ሐዲስ
◀◀7.ዱክተር ሰዒድ ሙሳ▶▶ሚን ኡሡል አቂደቲ አህሊ ሡነቲ ወል ጀመዓ
◀◀8.ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን▶▶ማሒየ ሠለፍያ ወይንም አሠሩ ተመሡኩ ቢሡና
◀◀9.ኡስታዝ ሙርሠል ሰዒድ ጨፌ▶▶አዱሩሡል ሙሐማ
◀◀10.ኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ ▶▶አል ዑዝር ቢል ጀህል በይነል ጉሉዊ ወል ጀፋ
◀◀11.ኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ ▶▶ሪሳለቱል ሒጃብ
◀◀11.ኡስታዝ አቡ ረያን▶▶ ነዋቂضል ኢስላም
◀◀12.ኡስታዝ አብደል መሊከ▶▶ኑሩ ተውሒድ
ከዛም በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የተለያዩ ኪታቦችን በሌሎች መሻኢኾችና ኡስታዞች የሚቀጥል ይሆናል
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ይሔን ተከታታይ የሆነ ኮርስ በቋሚነት ለመከታተል የምትፈልጉ ከታች ባሉት ዩዘር ኔሞች መመዝገብ ይቻላል
ክፍያ የለውም ነፃ ነው በቋሚነት መከታተል ብቻ ነው የሚያስፈልገው
♦️♦️የሚያስፈልገው 👉👉
ሙሉ ስም_
አድራሻ _ ብቻ ነው
እነዚህን መሻኢኾች እና ኡስታዞች እንጠቀምባቸው
የቻናል እና ግሩፕ ባለቤቶች ደግሞ ሸር እያደረግን እናዳርሰው
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በመጨረሻም ከሁሉም መሻኢኾች እና ኡስታዞች የተውጣጡ ጥያቄዎችን ጥያቄዎችን በጥሩ ሁኔታ የመለሠ ሠርቲፍኬት(የምስክር ወረቀት) ይሠጠዋል
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በቴሌግራም 👇👇👇
@Daruhadi21bot
በኢሞ ለመዝገብ 👇👇👇
https://s.imoim.net/wgqDgb
ወደ ደርስ ቻናል ለመቀላቀል 👇👇👇
https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah
https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah
በኢሞ ቻናል ለመቀላቀል 👇👇👇
https://s.imoim.net/8ODOAu
https://s.imoim.net/8ODOAu
