የቀጠናው ተመልካች
Ir al canal en Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 301
Suscriptores
Sin datos24 horas
-137 días
-8030 días
Archivo de publicaciones
4 301
🇺🇸❌🇮🇷 - አሁን እንደወጣው የአሜሪካ አስተዳደር ኦፊሴላዊ መረጃ ከሆነ፣ ሲባል እንደቆየው UAE ኢራንን አላጠቃችም ማለት ነው። አሜሪካ ነበረች ከፍተኛ ቅጥቀጣ በተጠቀሱት የኢራን ወደቦች ላይ የፈፀመችው።
4 301
🇺🇸❌🇮🇷 - ሰበር፡ የአሜሪካ ጦር በኢራን Qeshm Island እና Bandar Abbas ላይ ጥቃት ፈጽሟል፣ ምንም እንኳን አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን፣ ይህ ጦርነቱን እንደገና ማስጀመር አይደለም ቢልም፣ ሲል FOX NEWS ዘግቧል።
4 301
🇮🇷🇺🇸| አሜሪካ 3 የባሕር ኃይል ደምሳሽ መርከቦች ሾልከው ወደ ሆርሙዝ የባሕር ዳርቻ ለመግባት ሞክረው ነበር፣ ነገር ግን ከኢራን ጦር ኃይሎች ምላሽ አግኝተዋል፣ ሲል የኢራን ጋዜጠኛ ዘግቧል።
4 301
🇺🇸 ❌ 🇮🇷 ⚡️ - የኢራን መንግሥት ቲቪ "የአሜሪካን የባሕር ኃይል ጦር እና የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መትተናል፣ በዚህም የአሜሪካ ጦር ወደ ኋላ አፈግፍጓል።"
4 301
IRIB:
የኢራን ታንከር (ነዳጅ ጫኝ መርከብ) በአሜሪካ ጥቃት የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ፣ የኢራን ጦር ሠራዊት የጠላትን ጦር በሚሳዬል አጥቅቷል። ጠላት ከቀመሰ በኋላ ፈርጥጦ ሄዷል።
4 301
🇮🇷🇺🇸⚡️ - የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ ደህንነት ኮሚሽን ኃላፊ ኢብራሂም አዚዚ - ተመሳሳይ ስህተት ደጋግሞ መሥራት የተለየ መ
ውጤት አያስገኝም! ካስገኘ የሚያስገኘው ጠንካራ ቅጣትን ብቻ ነው።
አዲሱን የኢራን የባሕር ኃይል አገዛዝ አክብሩ!
4 301
🇺🇸🇦🇪⚡️ — 5 የአሜሪካ አየር ሐይል ግዙፎቹ KC-135 Stratotankers ወታደራዊ አይሮፕላኖች ከኤሜሬት ተነስተው ሲበሩ ተስተውለዋል።
ምናልባት ከዛሬው ምሽት የኢራን ፍንዳታዎች ጋር የተያያዘ ነገር ይኖራቸዋል? የሚታወቅ ነገር እስካሁን የለም።
4 301
🇮🇷⚡️ በኢራን ከፍተኛ ፍንዳታዎች ዛሬ ምሽቱን በተለያዩ የሀገሩ ክፍሎች ተሰምተዋል።
በ Qeshm Island፣ በደቡብ ኢራን ክፍሎች እና በሆርሙዝ ዳርቻ ባለው በBandar Abbas ፍንዳታዎቹ የተሰሙባቸው ናቸው።
IRGC የእነዚህን ፍንዳታዎች ምንጭ ለማጣራት እየሞከርኩኝ ነው፣ ከ UAE የመነጩ ከሆነ፣ ኤሜሬት ከፍተኛ ዋጋ ትከፍላለች ብሏል።
እስራኤል በፍንዳታዎቹ እጇ እንደሌለበት ተናግራለች።
4 301
🇺🇸🇮🇷 - Washington Post በCIA ውስጥ ያሉ ምንጮቼ አሹልከው ባወጡት ባለው መረጃ መሠረት፣ ኤጀንሲው ኢራን 70% የሚሆነውን ሚሳኤሎቿን ይዛለች፣ ወታደራዊ አቅሟም እምብዛም አልተነካም ብሎ ያስባል ብሏል።
4 301
🇸🇦🇰🇼🇺🇸 ሳዑዲ እና ኩዌት ጦር ሰፈሮቻቸውን ለአሜሪካን "ወታደራዊ ተደራሽነት ለሆርሙዝ ተልዕኮ" ወደነበረበት ይመልሳሉ።
ሳውዲ ዓረቢያ እና ኩዌት፣ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮቻቸው እና የአየር ክልላቸው ላይ የጣሉትን ገደቦች በማንሳት፣ ዋሽንግተን በሆርሙዝ ባሕር ውስጥ ያሉ መርከቦችን ለመጠበቅ ሥራዎችን ዳግም እንድትጀምር መንገድ ጠርገዋል።
ገደቦቹ የተጣሉት የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ስለ ኢራን የበቀል እርምጃ ስጋት ካነሱ እና በቅርቡ በክልሉ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ የአሜሪካን የደህንነት ዋስትናዎች ከጠየቁ በኋላ ነው።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ቁልፍ የሆነው፣ የነዳጅ ማጓጓዣ መንገድን እንደገና ለመክፈት ያለመ የባሕር ኃይል አጃቢ ተልዕኮ፣ በዚህ ሳምንት ሊቀጥል ይችላል ብለዋል።
4 301
- 🇮🇱 /🇱🇧/ 🇮🇷 ትኩስ ዜና፡ እስራኤል ትናንት በቤሩት ያደረገችው የግድያ ሙከራ አልተሳካም ወይም 'ዒላማውን አልመታም' ስትል ተናግራለች። ይህን ያለችው የRedwan ክፍለ ጦር አዛዥን በቤሩት በድሮን መግደሏን ትናንት ከገለፀች በኋላ ነው። አሁን እንደወጣ መረጃ ግን፣ አመራሩ በሕይወት እንዳለ ያሳያል።
እስካሁን ድረስ እስራኤል በዚህ ጦርነት ወቅት ምንም የተሳካ ከፍተኛ ግድያ አልፈፀመችም። ሂዝቦላህ ከፈረንጆች 2024 ጀምሮ ደህንነቱን እና ሰኪውሪቲውን ያስተካከለ ይመስላል።
4 301
- 🇺🇸 / 🇮🇷 IRGC ሜጀር ጄኔራል ሙህሲን ረዛ፡ "አሜሪካ ኢራን ዘገምተኛ ሀገር እንደሆነች አድርጋ ነው የምታስበው። በወታደራዊ ዛቻ ወይም በማስገደድ መብቷን የምትሰጥ ዘገምተኛ ሀገር ነች ብላ ታስባለች። ይህ የምኞት አስተሳሰብ ነው፣ የኢራን ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ነገር ፈጽሞ አይቀበልም።
'መገዛት' የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ ከመዝገበ-ቃላታችን ውጪ ነው፣ የለም!
በአእምሮ ያልተረጋጋ እና በሥነ ምግባር ብልሹ ፕሬዝዳንት ያላቸው አሜሪካውያን ናቸው።"
