es
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Ir al canal en Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 321
Suscriptores
+824 horas
-47 días
-7130 días
Archivo de publicaciones
🇮🇷🇺🇸⚡️CENTCOM, 'የአሜሪካ ኃይሎች በኢራን ላይ አዳዲስ ጥቃቶችን ጀምረዋል።' — ይህም በተከታታይ ለ12ኛ ምሽት የቦምብ ጥቃቶች እንደተደረጉ ያመለክታል። ይህ የተባለው፣ ባለፈው ሰዓት በበርካታ የኢራን ከተሞች ፍንዳታዎች ሪፖርት ከተደረጉ በኋላ ነው።

+4
🇷🇺🇺🇦⚡️ሩሲያዊያን፣ እሳቱን መሞቅ ጀምረዋል። መጣላቸው ቤታቸው ድረስ፣ እድሜ ለፑቲን ደካማነትና ሴራ ይሁንና። ይህ ስሜት የብዙ ሩሲያዊያን ስሜት ነው ዛሬ። ፑቲን ለምዕራቡ ዓለም ሩሲያን ሊያስበጣጥስ ይፈልጋል፣ ሩሲያን ሊበታትን ተፈራርሟል፣ ሩሲያን ሊያዳክም እና ሊሰብር ቃል ኪዳን ይዟል፣ ያ ባይሆን በምን ስሌት አንድ መሪ ሀገሩን እና ጦሩን በዚህ መጠን ወደ ኋላ እየጎተተ ጦርነት ያረዝማል? ይላሉ፣ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሩሲያዊያን። መዋጋታ ሲችል፣ ጦሩን በማስተባበር ጦርነት ማወጅ ሲችል፣ ሩሲያን አስበላ፣ አንድ ነገር ይደረግ፣ ይላሉም ናሽናሊስቶች። ፑቲን፣ በዚህ ሁሉ ግድ የሰጠው አይመስል። በዚህ አያያዙ የሚቆይም አይመስልም።

🇺🇸🇮🇷⚡— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማስፋፋት፣ እያሰበ ነው። አሜሪካም፣ ተጨማሪ ኃይሎችን፣ አውሮፕላኖችን እና የሕክምና ሠራተኞችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ
🇺🇸🇮🇷⚡— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማስፋፋት፣ እያሰበ ነው። አሜሪካም፣ ተጨማሪ ኃይሎችን፣ አውሮፕላኖችን እና የሕክምና ሠራተኞችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች ነው፣ በWSJ ጋዜጣ ዘገባ መሠረት። ➡️ እንቅስቃሴው፣ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ በተጠንቀቅ የተቀመጡ ኃይሎችን፣ ተዋጊ ጀት ስኳድራኖችን፣ ከባባድ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ለተጎዱ የአሜሪካ ወታደሮች ሕክምና የሚሰጡ ከ150 በላይ ዶክተሮችን፣ ያካትታል።

🇺🇸🇮🇷⚡— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማስፋፋት እያሰበ ነው፣ ተጨማሪ ኃይሎችን፣ አውሮፕላኖችን እና የሕክምና ሠራተኞችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች ነው
🇺🇸🇮🇷⚡— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማስፋፋት እያሰበ ነው፣ ተጨማሪ ኃይሎችን፣ አውሮፕላኖችን እና የሕክምና ሠራተኞችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች ነው፣ በ WSJ ጋዜጣ ዘገባ መሠረት። ➡️ እንቅስቃሴው፣ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ በተጠንቀቅ የተቀመጡ ኃይሎችን፣ ተዋጊ ጀት ስኳድራኖችን፣ ከባባድ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ለተጎዱ የአሜሪካ ወታደሮች ሕክምና የሚሰጡ ከ150 በላይ ዶክተሮችን ያካትታል።

🇮🇷 | ከIRGC የአየር ላይ ኃይል አዛዥ Seyed Majid Musawi (H) የተሰጠ ወሳኝ ማስጠንቀቂያ፦ "የእኛ ድልድዮች እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ጥቃት ከደረሰባቸው፣ በሕፃናት ገዳይ አጋ
🇮🇷 | ከIRGC የአየር ላይ ኃይል አዛዥ Seyed Majid Musawi (H) የተሰጠ ወሳኝ ማስጠንቀቂያ፦ "የእኛ ድልድዮች እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ጥቃት ከደረሰባቸው፣ በሕፃናት ገዳይ አጋሮች እና አስተናጋጅ ግዛቶች (አረብ ሀገራት) ውስጥም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚቋረጥ እርግጠኛ ሊሆኑ ይገባል። እኛም፣ መሠረተ-ልማቶቻቸውን እናቃጥለዋለን።

🇺🇦🇷🇺⚡️ዩክሬን 310 የድሮን መንጋዎችን ወደ ምዕራብ ሩሲያ እና ክራይሚያ ግዛት ምሽቱን አስወንጭፋለች።
🇺🇦🇷🇺⚡️ዩክሬን 310 የድሮን መንጋዎችን ወደ ምዕራብ ሩሲያ እና ክራይሚያ ግዛት ምሽቱን አስወንጭፋለች።

🇺🇸🇮🇷🇷🇺⚡- የአሜሪካ የስለላ ባለሥልጣናት፣ ሩሲያ ለኢራን የስለላ መረጃ፣ የዒላማዎችን መገኛ እና የተሻሻለ የድሮን ቴክኖሎጂ በማቅረብ በባሕር ወሽመጡ እና በባሕረ ሰላጤው ሀገሮች ውስጥ የ
🇺🇸🇮🇷🇷🇺⚡- የአሜሪካ የስለላ ባለሥልጣናት፣ ሩሲያ ለኢራን የስለላ መረጃ፣ የዒላማዎችን መገኛ እና የተሻሻለ የድሮን ቴክኖሎጂ በማቅረብ በባሕር ወሽመጡ እና በባሕረ ሰላጤው ሀገሮች ውስጥ የሚገኙ የCIA ተቋማትን ዒላማ እንድታደርግ መርዳቷን እየመረመሩ ነው፣ ምንም እንኳን እስካሁን ጠንካራ ድምዳሜዎች ላይ ባይደርሱም። ኢራን፣ ሪያድ ውስጥ የነበረውን ጨምሮ፣ በቀጠናው ባሉ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የCIA ድብቅ ቤቶችን እና ማዘዣ ጣቢያዎችን መምታቷ እና ፔንታገንም ቦታዎቹን ለቅቆ እንዲወጣ ማስገደዷ፣ የወታደራዊ አመራሮችን እስከ አሁን ያስደነገጠ ክስተት ሆኗል -- ሮይተርስ። *-*-*- አሜሪካ፣ የደረሰባትን ሕመም ለማስታመምና ለኢራን ሙሉ የጥቃቱን ክሬዲት ላለመስጠት፣ አንዴ ሩሲያ አንዴ ቻይና፣ በማለት እያሳበበች ነው። በኢራን ነው የተመታነው ላለማለት፣ አቀበት እየቧጠጡ ናቸው። ነገር ግን ጋዜጣው እንዳለው፣ እነዚህን ሀገሮች ለመክሰስ በተጨባጭ ያገኙት መረጃ የለም። ይህም ማለት፣ ጥቃቱን ሙሉ በሙሉ አቀነባብራ የፈፀመችው ኢራን ናት ማለት ነው። ይሄ የኢራን አቅም ነው ያስደነገጣቸው።

+7
🇪🇹⚡️በተመሳሳይ፣ በአማራ ግዛት የሚገኙ የፋኖ ታጣቂዎች፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የገዢውን ፓርቲ ብልጽግና ሰራዊት አባላት መማረካቸውን፣ እንዲሁም ብዙውን መግደላቸውን ዛሬ ከወጡ ምስሎች ለማየት ተችሏል።

🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ፣ በገዢው ፓርቲ ብልጽግና ሰራዊት እና በሕዝባዊ ሰራዊቶች መካከል የሚደረገው ጦርነት ተፋፍሞ የቀጠለ ሲሆን፣ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ለትግራይ ተዋጊዎች የላኳቸው FPV ድሮኖች፣ በቦታው ደርሰው በተዋጊዎች እጅ ሲከፈቱ የሚያሳይ ምስል፣ ሲዘዋወር ታይቷል። በዩክሬን፣ በስፋት በሩሲያ ጦር ላይ የሚውሉት እነዚህ ጨዋታውን የቀየሩት ድሮኖች፣ አብዛኞቹ፣ በተመሳሳይ በውጭ በሚኖሩ የሀገሩ ተወላጆች ተገዝተው ወደ ዩክሬን የሚገቡ ናቸው። ከ$100-$1500 ዶላር በሚያወጣ ወጪ የሚገዙት እነዚህ ድሮኖች፣ ካሜራ የተገጠመላቸው ሲሆን የተለያዩ ዓይነት ፈንጂዎችን፣ እና እንዸ ሞርታር ቅንቡላ ያሉ ተተኳሾችን መታጠቅ የሚችሉ ናቸው።

🇺🇸🇻🇪⚡️— የተባረረው የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤቱ ሲሊያ ፍሎሬስ፣ የፍርድ ሂደታቸው ዛሬ በኒው ዮርክ ዳኛ ትዕዛዝ መሠረት፣ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በጁን 1፣ 2027 እንዲ
🇺🇸🇻🇪⚡️— የተባረረው የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤቱ ሲሊያ ፍሎሬስ፣ የፍርድ ሂደታቸው ዛሬ በኒው ዮርክ ዳኛ ትዕዛዝ መሠረት፣ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በጁን 1፣ 2027 እንዲጀመር ታቅዷል። *-*-*- አስባችሁታል አሜሪካ በኢራን ቢሳካላት ኖሮ? አያቶላውን እንዲህ ሊያሳዩን ነበር። ጨቃኝ እኮ ናት አሜሪካን፣ ዊ! ኢራኖችን ላቲን አርጋ አስባቸው።

+3
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ ጦር፣ በኢርቢል ኢራቅ፣ የኢራንን ድሮኖች ለማውረድ፣ C-RAM አየር መቃወሚያ መሳሪያን በመጠቀም ላይ ነው።

🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼— የሳተላይት ምስሎች፣ በቅርቡ የተካሄደው የኢራን ጥቃት በኩዌት በሚገኘው አህመድ አል-ጃበር አየር ኃይል ማእከል የAN/FPS-117 ረጅም ርቀት ያለው የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ራዳር
🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼— የሳተላይት ምስሎች፣ በቅርቡ የተካሄደው የኢራን ጥቃት በኩዌት በሚገኘው አህመድ አል-ጃበር አየር ኃይል ማእከል የAN/FPS-117 ረጅም ርቀት ያለው የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ራዳርን እንዳወደመ ያሳያሉ። ➡️በ Lockheed Martin የተመረተው AN/FPS-117፣ በግምት 470 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው የ3D የአየር ክትትል ራዳር ሲሆን፣ ከአሜሪካ እና ከጥምረት የአየር መከላከያ አውታረ መረቦች ጋር በመዋሃድ በኩዌት ሲሰራ ነበር።

🇮🇷⚡️የኢራን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ሼካርቺ፦ እንድንገባ በተገደድንበት በሦስተኛው ዙር የጠላት ጦርነት፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ የሚገኘውን፣ ግዙፍ የጠላት የዳታ ማዕከልን አውድመናል። ይህ ማዕከል፣ በአረብ ኤምሬትስ ውስጥ ተሠርቶ ለመጠናቀቅ 20 ዓመታት የወሰደበት ሲሆን፣ የተቋቋመው፣ በአውሮፓውያን፣ በጽዮናዊው አካላት እና በአሜሪካ እርዳታ እና ኢንቨስትመንት ቀጠናውን ለመቆጣጠር ነበር። የዳታ ማዕከሉን በመምታታችን ዓይናቸውን አውጥተነዋል።

🇮🇷 🔻🇸🇦|  የኢራን ጥቃት በሳዑዲ አረቢያ የኪንግ አብዱል አዚዝ አየር ኃይል ማእከልን ዒላማ አድርጎ የተወሰደ ሲሆን፣ በአካባቢው ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ ተዘግቧል።

🇮🇷 🔻🇸🇦|  በሳውዲ አረቢያ ኮባር ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። በኪንግ ፋሐድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚካሄዱ ተግባራት እንደተቋረጡ ተዘግቧል። በኪንግ ፋሐድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያም፣ ተጨማሪ ፍንዳታዎች ሪፖርት ተደርገዋል።

🇸🇦 | የሳዑዲ ተቃዋሚ ሚዲያ እንደዘገበው፡ በየመን ጦር ሃይሎች የተሰጠውን እና በብሪጋዲየር ጄኔራል ያህያ ሳሪ የተገለጸውን መግለጫ ተከትሎ፣ እና በመባባስ ላይ ባለው የቀጠናው ክስተቶች ምክኒያት፣ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ወደ Bunker (ጥብቅ ዋሻ) በመሸሽ ተደብቋል።

+2
🇮🇷⚡️🇺🇸 በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ በኢራን ላይ ከባድ ድብደባ እየፈጸመች ትገኛለች። ድብደባው፣ ከሌላው ጊዜ በበለጠ መጠኑ እና ስፋት ከፍተኛ ነው። በዚህ ሰዓት የሚሰሙ ፍንዳታዎች፣ ከጥቃቱ ቦታ ሩቅ አካባቢ ያሉ ቤቶችን መስኮቶች እያንቀጠቀጠ ነው ይላሉ፣ ነዋሪዎች።

🇺🇸🇮🇷⚡️— The Atlantic ጋዜጣ የጠቀሰው ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን እንደተናገረው፣ የመጀመሪያ የአሜሪካ የስለላ ግምገማዎች እንደሚያመለክቱት፣ የቅርብ ጊዜው የአሜሪካ ጥቃቶች የኢራንን
🇺🇸🇮🇷⚡️— The Atlantic ጋዜጣ የጠቀሰው ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን እንደተናገረው፣ የመጀመሪያ የአሜሪካ የስለላ ግምገማዎች እንደሚያመለክቱት፣ የቅርብ ጊዜው የአሜሪካ ጥቃቶች የኢራንን ባሕሪ ለመለወጥ ብዙም አልረዱም፣ ሲል ተናግሯል። "ጥቃቶቹ ኢራንን ተስፋ እንዳደረግነው፣ መንገዳቸውን እንዲለውጡ አላደረጋቸውም፣ እንዲያውም አባብሷቸዋል።" ➡️ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ቅርብ የሆኑ ሁለት ሰዎች በመጪው ምርጫ የሪፐብሊካን ተስፋዎችን ለማጠናከር በመጨረሻው ደቂቃ ትራምፕ ጦርነቱን ለማቆም ሊያስብ እንደሚችል ተናግረዋል። ➡️ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለThe Atlantic እንደተናገሩት፣ ኢራን የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከቦችን ዒላማ ማድረጓን አጠናክራለች፣ ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን አባብሰውት ቀጥለዋል፣ ብለዋል።

🇷🇺⚡️የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር፣ ማራት በርድዬቭ፣ ለTASS እንደተናገሩት፣ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ፑቲን በነሐሴ 2026 በማያሚ በሚካሄደው የG20 ጉባኤ ላይ እንዲገኙ እንደምትፈልግ
🇷🇺⚡️የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር፣ ማራት በርድዬቭ፣ ለTASS እንደተናገሩት፣ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ፑቲን በነሐሴ 2026 በማያሚ በሚካሄደው የG20 ጉባኤ ላይ እንዲገኙ እንደምትፈልግ ምልክት እያሳየች ነው። ዲፕሎማቱ እንደተናገሩት፣ ትራምፕ ተሳትፎውን፣ "ጠቃሚ" ብሎ በይፋ ገልጾታል፣ ይህም "የፖለቲካ መስተንግዶ ሳይሆን ምክንያታዊ አመክንዮ ነው"፣ ምክንያቱም በመሪዎች መካከል የሚደረግ ውይይት ወሳኝ ነው እና "ያለ ሩሲያ አደጋዎችን እና ቀውሶችን መቆጣጠር አይቻልም።" *-*-*- አይገርማችሁም? የዛሬ 5 ዓመት ሩሲያ የG8 አባል ነበረች። G7 ቡድን፣ ሩሲያን ለመጨመር ሲል በ1997 G8 ተብሏል። ከዚያ በኋላ፣ አሁን በመሪዎቿ እንዝህላልነት የተነሳ በጦርነቱ ስትንደፋደፍ፣ ከG8 ስብስብ አባረሯት። ዛሬ G20፣ እነ ሕንድ፣ እነ ኢንዶኒዢያ፣ እነ ሜክሲኮ፣ እነ ቱርክ እና ቻይና …… ያሉበት ስብስብ ለመካተት "አሜሪካ ምልክት" እያሳየችን ነው ይላሉ። በዚህ ደረጃ ነው መሪዎቿ የፈጠፈጧት ሩሲያን። ይታያችሁ፣ ለG20ም የሉበትም፣ እንደው ብጋበዝ ብላ ነው የፑቲን ሩሲያ ከውጭ የምትቀላውጠው። አሁንም ለሩሲያ ጊዜው አልረፈደም፣ ይሄን ጦርነት ባለ በሌለ ኃይል ማሸነፍና ማጠናቀቅ ይገባል። ሌሎች ኃይሏን እንዲያዩ እና እንዲያከብሯት ይገባል። በዚህ ዓለም ላይ፣ በጥንካሬና በጥንካሬ ብቻ ነው፣ ደረጃ ማግኘት የምትችለው! ፑቲን ዩክሬን ላይ እንደሚልፈሰፈሰው፣ G50 የሚባል ስብስብ ቢኖርም እንኳ፣ የሚጋብዘው አይኖርም። ስለተልፈሰፈሰ፣ አይመጥነውም።

🇸🇾🇱🇧🇮🇱 ሶሪያ ከእስራኤል ጎን በመሆን እሷን ለመከላከል ትመጣለች፣ በካን ኒውስ ዘገባ መሠረት። የሶሪያ የደህንነት ተቋም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በሂዝቦላ ላይ ለሚደረጉ ክንዋኔዎች የአደጋ
🇸🇾🇱🇧🇮🇱 ሶሪያ ከእስራኤል ጎን በመሆን እሷን ለመከላከል ትመጣለች፣ በካን ኒውስ ዘገባ መሠረት። የሶሪያ የደህንነት ተቋም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በሂዝቦላ ላይ ለሚደረጉ ክንዋኔዎች የአደጋ ጊዜ ዕቅዶችን፣ ከእስራኤል አመራሮች ጋር በትብብር እያዘጋጀ ነው። ለመንግሥት ቅርብ የሆነ የሶሪያ የደህንነት ምንጭ እንደተናገረው፣ በደማስቆ ይፋዊ መልእክት እና ከመድረክ በስተጀርባ በሚደረገው እቅድ መካከል፣ ልዩነት አለ። የሶሪያ የፀጥታ ኃይሎች፣ በሶሪያ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም የሂዝቦላ መገኘት እንዲገጥሙ ታዝዘዋል። ትራምፕ በሊባኖስ ከሂዝቦላ ጋር ያለውን ሥራ እንዲጨርስ የሶሪያውን ፕሬዝዳንት አሕመድ አል- ሻርን እንደላከው በተደጋጋሚ ገልጿል። *-*-*-*-