የቀጠናው ተመልካች
Ir al canal en Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 295
Suscriptores
Sin datos24 horas
-217 días
-9130 días
Archivo de publicaciones
4 292
🇮🇱⚡️🇱🇧 የውጊያ ጨዋታ ቀያሪዎቹ የሂዝቦላ FPV ድሮኖች፣ ዛሬ፣ በጨለማ ማየት በሚያስችላቸው thermal imagery በመጠቀም፣ በደቡብ ሊባኖስ የእስራኤል ወታደሮችን ሲያድኑ ታይተዋል፣ ቡድኑ በለቀቀው ቪዲዮ መሠረት።
የእስራኤል ጦር ቀን ቀን ድሮኖቹን በመፍራት ብዙውን እንቅስቃሴውን በምሽት ገድቦ ነበር የቆየው።
ቡድኑ፣ ባለፈው ሳምንት፣ እንዲሁ፣ በ150 ዶላር FPV ድሮኖች $150 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሦስት የእስራኤል IRON DOME ሲስተሞችን ሲያወድሙ የሚያሳይ ምስል ለቆ ነበር።
በዚህም የተነሳ፣ በእስራኤል ጦር ውስጥ፣ እነዚህ ድሮኖች እያመጡ ያሉትን ለውጦች በተመለከተ ከፍተኛ መደናገጥ አለ።
4 292
🇮🇷 ኢራን ከፍተኛ ደረጃ ያለው ዩራኒየም ከሀገሪቱ ለማውጣት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች፤ በአንድ ቅድመ ሁኔታ፦ ወደ አሜሪካ ሳይሆን ወደ ቻይና መሄድ አለበት። አል ሃዳት ከፍተኛ ምንጮችን በመጥቀስ እንደገለጸው።
4 292
🇮🇷🇺🇸🇮🇱 — የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፦ 'ሌሎቹ ቢፈልጉ ከእስራኤል ጋር ይደመሩ፣ እኛ እንቀነሳለን።'
'የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ 'እስራኤልን' አይቀበልም፣ በጭራሽ አይቀበልም! ምክንያቱም ሕገ-ወጥ እና ወራሪ አካል በመሆኗ።
ስለዚህ፣ በቀጠናው ውስጥ የአለመረጋጋት እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ትልቁ ምንጭ ከሆነ አገዛዝ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መፍጠር አይቻልም።
ለሺዎች ዓመታት የኖረ ሥልጣኔ ባለቤት ለሆነችው ኢራን፣ የዘር ማጥፋት ከምትፈጽም 'ሀገር' ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወይም ሌላ ማንኛውንም ግንኙነት ከመፍጠር ይልቅ በሙሉ ሰውነቷ ሰማዕት መሆን ይሻላታል።'
4 292
+3
🇸🇦 የሳዑዲ ዓረቢያ ያልተገደበ እና እንደልብ የነበረው የገንዘብ ፈሰስ፣ ዛሬ የለም BBC
ከጥንት ጀምሮ አምባገነን መሪዎች ያለ ጠያቂ እና ያለ ተቀናቃኝ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በስማቸው በመቅረጽ ሠርተው ያልፋሉ። በኋላ እነዚህ ግዙፍ ሥራዎች 'እከሌ የሠራቸው' እየተባሉ ይወደሱበታል። እንዲህ ያሉ ከሺ ዓመታት በፊት የተሠሩ ትልልቅ ቅርሶች ዛሬም በመካከለኛው ምሥራቅ ቆመው ይታያሉ፣ እንደ BBC ዘገባ።
በዘመናችን፣ በዚሁ አካባቢ፣ በስማቸው የሚተውት ዘርፈ- ብዙ ዘመናዊ ግንባታዎችን እና ፕሮጀክቶችን፣ ገደብ እና ተቆጣጣሪ በሌለው የገንዘብ ፍሰት እንደሚገነቡ በየጊዜው ከሚያውጁ መሪዎች አንዱ፣ የሳዑዲው ሙሐመድ ቢን ሠልማን ነው።
የእሱን የአገዛዝ ስልት እና በዚህ በኩል ያለውን የሳዑዲን ትራክ ሬከርድ የሚያውቁ ኤክስፐርቶች እንደሚሉት፣ ሀገሪቱ በአብዛኛው የምታውጃቸው ሕዝባዊ ፕሮጀክቶች፣ ከሚጠራው የገንዘብ ፍሰት አንፃር፣ 'ከቅዠት ያላለፉ' ናቸው ይላሉ።
"ፕሮጀክቶች ከልዩ ፌሽታና ድምቀት ጋር ይታወጃሉ፣ በመነጋታው የሉም"
"ለዚህ ምክኒያቱ" ይላሉ እኒህ ኤክስፐርቶች፣ "ሳዑዲ እንዳለፉት ጊዚያት ዛሬ ላይ እንደ ልቧ የምታወጣው ገንዘብ የላትም።"
4 292
🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ በለጠፈው ረጅም ጽሑፉ፣ ከትናንት በስትያ በስልክ ያዋራቸው የአረብ ሀገሮች፣ የፖኪስታን እና የቱርክ መሪዎች ሳያቅማሙ በፍጥነት ከእስራኤል ጋር በአብርሃም ጎጆ (Abraham Accord) ውስጥ እንዲጠቃለሉ እና እንዲደመሩ አሳስቧል።
በዚህ ጉዳይ 'ወገቤን ማለት' የለም፣ ብሎ የዛተው ትራምፕ፣ እነዚህ ሀገሮች ይህን ነገር እንደ ትንሹ ግዴታቸው ወስደው ሊወጡት የሚገባ ኃላፊነት ነው ብሏል።
4 292
🇸🇦🤝🇮🇱 ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሳዑዲ ንጉሥ መሐመድ ቢን ሠልማንን ሳዑዲ ዓረቢያ ከእስራኤል ጋር "ቀለበት እንድታስር" እና ወደ አብርሃም ጎጆ (Abraham Accord) እንድትገባ መጠየቁ ተሰማ።
ትራምፕ፣ ሳዑዲን ጨምሮ፣ የገልፍ አረብ ሀገሮች በአብርሃም ማህበር ጥላ ሥር (Abraham Accord) ከእስራኤል ጋር እንዲደመሩ እና የሚሽኮረመሙትን ነገር እንዲተው ትናንት በዋይት ሃውስ በነበረው የስልክ ስብሰባ እንደነገራቸው ተዘግቧል።
ከኢራን ጋር ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ለማግኘትና፣ ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ ለመወያየት የመጡት የአረብ ሀገሮች፣ በትራምፕ ምክረ-ሐሳብ ደርቀው እንደቀሩና አፍረውም እንደነበር Axios ዘግቧል።
4 292
🇮🇷 PressTV፦ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ ሊባኖስ እንደ ሞባይል ስልኮች፣ GPS ሲስተሞች እና የቼሪ ቲማቲሞች ላሉ ፈጠራዎች እስራኤልን ማመስገን አለባት በማለቱ መሳቂያ ሆነ። በውነቱ፣ እስራኤል በተሰረቁ የፍልስጤም መሬቶች ላይ ከመመስረቷ ከ 1,200 ዓመታት በፊት የቼሪ ቲማቲሞችን ያለሙት ቀደምት የአሜሪካ ተወላጆች (Native Americans) ነበሩ።
4 292
🇪🇹⚡️ በወለጋ ክፍለ ሀገር፣ ምሥራቅ ወለጋ በሚባለው ክፍል፣ ኪረሙ አጋምሳ አካባቢ፣ ዛሬ ቀኑን ሙሉ፣ በአምሃራ ታጣቂዎች (ፋኖ) እና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ ነበር ሲሉ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በዚህም፣ የማዕከላዊ እዝ አመራርን ጨምሮ ከ100 በላይ የመንግሥት ወታደሮች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተሰምቷል።
ውጊያው፣ እስከዛሬ በቀጠናው ከተደረጉ ውጊያዎች የከፋ ነበር ተብሏል።
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸 ቅድም እንዳልኩት ነው፣ ኢራኖች ሲበዛ ተጠራጣሪ ናቸው፣ መጠራጠራቸው ትክክል ነበር፣ ጠቅሟቸዋል። አሜሪካ ተንሸራታለች። ትናንት ያሉትን፣ አላልንም ብለው አሁን እየሸመጠጡ ነው።
**
— አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለFOX NEWS እንደተናገረው፣ ምንም ስምምነት “ዛሬም ሆነ ነገ” አይፈረምም፣ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጨረሻ ውጤት ለመድረስ ለሂደቱ ተጨማሪ ቀናት ለመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጿል።
ባለሥልጣኑ እንደተናገረው፣
የአስተዳደሩ አካሄድ “አቧራ (ዩራኒየም) ከሌለ፣ ዶላር የለም” በሚለው ፖሊሲ እየተመራ ነው፣ ይህም ማለት፣ ኢራን ግዴታዎቿን ሙሉ በሙሉ ካላሟላች የማዕቀብ እፎይታ ወይም የገንዘብ ጥቅማጥቅሞችን አታገኝም ማለት ነው። በተብላላው የዩራኒየም ክምችት እና የሆርሙዝ መተላለፊያ እንደገና መከፈት ላይ፣ መግባባት ተደርሷል፣ የመጨረሻው የቃላት አጻጻፍ ግን አሁንም በድርድር ላይ ነው። ድርድሮች ካልተሳኩ ወይም እንደ “መጥፎ ስምምነት” የሚቆጥሩትን ነገር ካስገኙ፣ አሜሪካ ወታደራዊ ጥቃቶችን ለመቀጠል ዝግጁ ነች።5,6,7 ቀን ነው ያላቸው፣ ይፍጠኑ!
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 'በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው የመግባቢያ ስምምነት ሊሰረዝ ይችላል።'
ይህ የተዘገበው በኢራን የዜና ኤጀንሲ ታስኒም ነው።
ከዚህ ቀደም የኢራን ምንጮች በአሜሪካ አቋም ለውጥ ምክንያት በድርድሩ ላይ ከባድ ቀውስ እንደተፈጠረ ዘግበው ነበር።
ይህ የተባለው፣ ዛሬ ይፈረማል ተብሎ የነበረውን የመግባቢያ ሰነድ፣ ትራምፕ፣ 'እንደገና በክለሳ ልየው እና እንወስናለን' በማለት ቃሉን ካፈረሰ በኋላ ነው።
የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጨምሮ፣ የእስራኤል መንግሥት፣ የተደረሰበት የመግባቢያ ሰነድ ኢራንን አሸናፊ የሚያስመስል ነው፣ በማለት ከባድ ትችት በዋይት ሃውስ ላይ መሰንዘራቸው ይታወቃል።
4 292
🇮🇷 ኢራኖች፣ እንዲያውም በቃ ትተነዋል ብለው ደረሱበት ከተባለው ስምምነት ሊያፈነግጡ ነው።
ይህን ያሉት፣ ጥሩ ያልሆነ፣ የመደባበቅ ነገር ከአሜሪካና እስራኤል "እየሸተተን ነው" ካሉ በኋላ ነው።
4 292
🇮🇱 እስራኤል ለጥቃት የማይሰማት እየሆነች፣ ጫንቃዋ እየደነደነ ነው። ይሄ ስሜት ወደ ዋናው የህብረተሰብ ክፍል እየገባ ነው — ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ
'በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች ላይ በአክራሪዎች ለሚደረግ አስቀያሚ ባሕሪ ተጋላጭ ሆነናል።
'ክርስቲያን እና ሙስሊም ዜጎቻችን በአክራሪዎች ሲጠቁ እያየን፣ ምንም እየመሰለን አይደለም።'
4 292
🇮🇷 ኢራናዊያን እጅግ በጣም ተጠራጣሪ ሕዝብ ናቸው። ማንንም አያምኑም። ያሳለፉት ታሪኮቻቸው እና የዛሬ ሕይወታቸው ያስተማራቸው ዋና ቁም ነገር፣ "ማንንም አትመን" የሚል ነው።
ይህም ሆኖ፣ መንግሥታቶቻቸው ዛሬም በተደጋጋሚ ሰው ሲያምኑና ከጀርባቸው ሲወጉ አይተናል። የሚነግሯቸውን ያምናሉ፣ በዚህም ምክኒያት ዘወር ከማለታቸው፣ ጦር ሲመዘዝባቸው እና ሲወጉ በቅርብ አስተውለናል።
አሁን ግን አመራሮቻቸው "በቃ" ያሉ ይመስላል። ይመስላል?
የሕዝቡ ተጠራጣሪነት እና አለማመን ግን እንደ ሁሌውም እንዳለ ነው። መንግሥታቸው የሚያደርገውን ድርድር በዓይነ ቁራኛ እየተከታተሉ እና "ዋ! ምንም እንዳትፈርም፣ ማታለያ ነው" እያሉ ናቸው።
አሁን ላይ መንግሥቱ የሆነ ነገር እንዳይፈርም የሕዝቡን ቁጣ ፈርቷል። በተቀናቃኞች እንደሚባለው አይደለም፣ በኢራን ሕዝቡ ነው ሹፌሩ። መንግሥቱ ተሳፋሪ ነው። ይሄ አሁን በዚህ ጦርነት በጎላ ታይቷል።
እና አሁን የኢራን መንግሥት የቀረበለትን ይፈርም?
ሕዝቡ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል በዚህ ልክ ለጥ ማለት ለተንኮል ነው በሚለው እርግጠኛ ናቸው። "አትመኗቸው" በማለት ላይ ናቸው። ወይ ትልቅ እጅ መስጠት ነው (ከሆነ እናያለን) ወይም ትልቅ ማታለል ነው! ተጠንቀቅ! እያሉት ነው መንግሥታቸውን።
ሕዝቡ፣ ጦርነት የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደማይቀር ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ናቸው። አሜሪካ እና እስራኤል መምጣታቸው የማይቀር ነው፣ ይልቅስ ለጦርነት ተዘጋጅ እያሉ መንግሥታቸውን እየወተወቱ ናቸው።
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረጉ ድርድሮች በሥርዓት እና ገንቢ በሆነ መንገድ እየተካሄዱ መሆናቸውን እና ጊዜ ከአሜሪካ ጎን ስለሆነ ወኪሎቹ ስምምነት ለመድረስ እንዳይቸኵሉ መመሪያ እንደሰጣቸው ተናግሯል።
አሁን እየተካሄዱ ያሉትን ውይይቶች ከኦባማ ዘመን የኑውክሌር ስምምነት ጋር የማይነጻጸር፣ የያኔው ስምምነት ኢራን የኑውክሌር መሳሪያ እንድታዘጋጅ ቀጥተኛ መንገድ እንደነበር ገልጿል።
ስምምነት እስኪደረግ፣ እስኪረጋገጥ እና እስኪፈረም ድረስ የአሜሪካ የባሕር ኃይል እገታ ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ እንደሚቆይ ትራምፕ ገልጿል።
ለመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ላደረጉት ድጋፍ አመስኖ ኢራን አንድ ቀን የአብርሃም ማህበርን ልትቀላቀል እንደምትችል ጠቁሟል።
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 በመጀመሪያው የትራምፕ የስልጣን ዘመን፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበረው Mike Pompeo፣ ከኢራን ጋር ተደረሰበት የተባለውን ስምምነት የቅዠቶች ቅዠት በማለት አጣጥሎታል። ትራምፕንም፣ አይደረጋትም፣ እንደገና አጢነው ብሎታል። 'ሁኔታውን በጣም ቀላልና ቀጥተኛ ማድረግ ይቻላል፣ ሆርሙዝን ይክፈቱ ይክፈቱ፣ አለቀ! ካልሆነ፣ እንዲያውም ዘግይተናል፣ ኢራንን በምትቆስልበት ቦታ ላይ እንምታ!' ብሏል።
የPompeoን እይታ በአሜሪካ የሚገኙ ጦርነት አቀንቃኝ ባለስልጣናት እና የእስራኤል ደላሎች (lobbyists)፣ እንዲሁም የእስራኤል መንግሥት የሚጋሩት ሲሆን፣ ትራምፕ 'በቀላሉ እጅ መስጠቱ' ከፍተኛን መደናገጥ ፈጥሯል።
ስምምነቱ ለኢራን ያደላ እና ኢራንን አሸናፊ አድርጎ የሳለ ነው ብለውታል።
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 እስራኤላዊያን ባለስልጣናት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ሁሉም በሚባል ደረጃ፣ ከኢራን ጋር ተደረሰ በተባለው ስምምነት ደንግጠዋል። አንዳንዶች በግልፁ፣ ብዙዎች በውስጥ፣ ትራምፕን በክፉ እየኮነኑት ናቸው። ተሸንፈናል ወይ? በማለት ይጠይቃሉ።
4 292
— 🇺🇸/🇮🇷 ኢራናዊ ተንታኝ፦ 'መንግሥታችንን ለመገልበጥ የተከፈተብን ጦርነት፣ አሁን የአሜሪካ ኃይሎች ከክልላችን በመውጣታቸው የሚጠቃለል ይሆናል።
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 ስምምነቱ እንደሚባለውና እንደምንሰማው ከሆነ፣ ኢራን አሜሪካንን ጉድ ሠርታታለች ማለት ነው። ወይም እስራኤል አሜሪካንን ጉድ ሠርታታለች ማለት ነው።
እስራኤል አሜሪካ ከቀጠናው እና ከመካከለኛው ምሥራቅ ጓዟን ይዛ እንድትወጣላት ትፈልጋለች የሚል ጠንካራ ግላዊ እምነት አለኝ።
አሜሪካ በቀጠናው እስካለች እስራኤል ሁሌ ሁለተኛ ናት፣ ተቆጭ አላት።
አሜሪካ ከወጣች ግን፣ በአካባቢው አንደኛ ፈላጭ ቆራጭ፣ አዛዥ ናዛዥ መሆን ትፈልጋለች።
ይሄንን ተስፋ አድርጋ ነው፣ በቀጠናው የመጨረሻ ተቀናቃኟ ኢራን በአሜሪካ እንድትወገድላት ሌት ተቀን ሥትሰራ የነበረው። ኢራን ወደቀች ማለት፣ አበቃ! እስራኤል ዙፋኑን ትይዛለች።
ችግሩ ኢራን አልወደቀችም፣ እንዲያውም ተጠናከረች። ከዓለም ኃያላን አንዷ እንደሆነች አሳይታለች።
የብዙዎች ፍራቻ፣ የባሕሩን ወሽመጥ ከመቆጣጠር ጋር፣ እንዲያውም ይብስባታል ነው የሚሉት ኢራን።
ይኸው ኢራን በስምምነቱ መሠረት (የመጨረሻ ከሆነ)፣ አሜሪካንን ከአካባቢው ልታስወጣት ነው።
ተሳስቼ ነው፣ 'በስምምነት' አይደለም፣ በጡንቻ ነው።
አሜሪካ ስትወጣ፣ ሁለቱ ለአካባቢው የበላይነት ይቀራሉ።
እውን አሜሪካ ከዚያ ልትወጣ ነው? አይመስለኝም በፍፁም። ግን ይኸው ሊስማሙበት ነው ይሉናል።
