ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 293
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-217 أيام
-9130 أيام
أرشيف المشاركات
🇮🇷⚡️🇺🇸 ቅድም እንዳልኩት ነው፣ ኢራኖች ሲበዛ ተጠራጣሪ ናቸው፣ መጠራጠራቸው ትክክል ነበር፣ ጠቅሟቸዋል። አሜሪካ ተንሸራታለች። ትናንት ያሉትን፣ አላልንም ብለው አሁን እየሸመጠጡ ነው። **
🇮🇷⚡️🇺🇸 ቅድም እንዳልኩት ነው፣ ኢራኖች ሲበዛ ተጠራጣሪ ናቸው፣ መጠራጠራቸው ትክክል ነበር፣ ጠቅሟቸዋል። አሜሪካ ተንሸራታለች። ትናንት ያሉትን፣ አላልንም ብለው አሁን እየሸመጠጡ ነው። ** — አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለFOX NEWS እንደተናገረው፣ ምንም ስምምነት “ዛሬም ሆነ ነገ” አይፈረምም፣ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጨረሻ ውጤት ለመድረስ ለሂደቱ ተጨማሪ ቀናት ለመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጿል። ባለሥልጣኑ እንደተናገረው፣
የአስተዳደሩ አካሄድ “አቧራ (ዩራኒየም) ከሌለ፣ ዶላር የለም” በሚለው ፖሊሲ እየተመራ ነው፣ ይህም ማለት፣ ኢራን ግዴታዎቿን ሙሉ በሙሉ ካላሟላች የማዕቀብ እፎይታ ወይም የገንዘብ ጥቅማጥቅሞችን አታገኝም ማለት ነው። በተብላላው የዩራኒየም ክምችት እና የሆርሙዝ መተላለፊያ እንደገና መከፈት ላይ፣ መግባባት ተደርሷል፣ የመጨረሻው የቃላት አጻጻፍ ግን አሁንም በድርድር ላይ ነው። ድርድሮች ካልተሳኩ ወይም እንደ “መጥፎ ስምምነት” የሚቆጥሩትን ነገር ካስገኙ፣ አሜሪካ ወታደራዊ ጥቃቶችን ለመቀጠል ዝግጁ ነች።
5,6,7 ቀን ነው ያላቸው፣ ይፍጠኑ!

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 'በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው የመግባቢያ ስምምነት ሊሰረዝ ይችላል።' ይህ የተዘገበው በኢራን የዜና ኤጀንሲ ታስኒም ነው። ከዚህ ቀደም የኢራን ምንጮች በአሜሪካ አቋም ለውጥ ምክንያት በድርድሩ ላይ ከባድ ቀውስ እንደተፈጠረ ዘግበው ነበር። ይህ የተባለው፣ ዛሬ ይፈረማል ተብሎ የነበረውን የመግባቢያ ሰነድ፣ ትራምፕ፣ 'እንደገና በክለሳ ልየው እና እንወስናለን' በማለት ቃሉን ካፈረሰ በኋላ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጨምሮ፣ የእስራኤል መንግሥት፣ የተደረሰበት የመግባቢያ ሰነድ ኢራንን አሸናፊ የሚያስመስል ነው፣ በማለት ከባድ ትችት በዋይት ሃውስ ላይ መሰንዘራቸው ይታወቃል።

🇮🇷 ኢራኖች፣ እንዲያውም በቃ ትተነዋል ብለው ደረሱበት ከተባለው ስምምነት ሊያፈነግጡ ነው። ይህን ያሉት፣ ጥሩ ያልሆነ፣ የመደባበቅ ነገር ከአሜሪካና እስራኤል "እየሸተተን ነው" ካሉ በኋላ ነው።

🇮🇱 እስራኤል ለጥቃት የማይሰማት እየሆነች፣ ጫንቃዋ እየደነደነ ነው። ይሄ ስሜት ወደ ዋናው የህብረተሰብ ክፍል እየገባ ነው — ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ 'በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች ላይ በአክራሪዎች ለሚደረግ አስቀያሚ ባሕሪ ተጋላጭ ሆነናል። 'ክርስቲያን እና ሙስሊም ዜጎቻችን በአክራሪዎች ሲጠቁ እያየን፣ ምንም እየመሰለን አይደለም።'

🇮🇷 ኢራናዊያን እጅግ በጣም ተጠራጣሪ ሕዝብ ናቸው። ማንንም አያምኑም። ያሳለፉት ታሪኮቻቸው እና የዛሬ ሕይወታቸው ያስተማራቸው ዋና ቁም ነገር፣ "ማንንም አትመን" የሚል ነው። ይህም ሆኖ፣ መንግሥታቶቻቸው ዛሬም በተደጋጋሚ ሰው ሲያምኑና ከጀርባቸው ሲወጉ አይተናል። የሚነግሯቸውን ያምናሉ፣ በዚህም ምክኒያት ዘወር ከማለታቸው፣ ጦር ሲመዘዝባቸው እና ሲወጉ በቅርብ አስተውለናል። አሁን ግን አመራሮቻቸው "በቃ" ያሉ ይመስላል። ይመስላል? የሕዝቡ ተጠራጣሪነት እና አለማመን ግን እንደ ሁሌውም እንዳለ ነው። መንግሥታቸው የሚያደርገውን ድርድር በዓይነ ቁራኛ እየተከታተሉ እና "ዋ! ምንም እንዳትፈርም፣ ማታለያ ነው" እያሉ ናቸው። አሁን ላይ መንግሥቱ የሆነ ነገር እንዳይፈርም የሕዝቡን ቁጣ ፈርቷል። በተቀናቃኞች እንደሚባለው አይደለም፣ በኢራን ሕዝቡ ነው ሹፌሩ። መንግሥቱ ተሳፋሪ ነው። ይሄ አሁን በዚህ ጦርነት በጎላ ታይቷል። እና አሁን የኢራን መንግሥት የቀረበለትን ይፈርም? ሕዝቡ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል በዚህ ልክ ለጥ ማለት ለተንኮል ነው በሚለው እርግጠኛ ናቸው። "አትመኗቸው" በማለት ላይ ናቸው። ወይ ትልቅ እጅ መስጠት ነው (ከሆነ እናያለን) ወይም ትልቅ ማታለል ነው! ተጠንቀቅ! እያሉት ነው መንግሥታቸውን። ሕዝቡ፣ ጦርነት የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደማይቀር ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ናቸው። አሜሪካ እና እስራኤል መምጣታቸው የማይቀር ነው፣ ይልቅስ ለጦርነት ተዘጋጅ እያሉ መንግሥታቸውን እየወተወቱ ናቸው።

🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረጉ ድርድሮች በሥርዓት እና ገንቢ በሆነ መንገድ እየተካሄዱ መሆናቸውን እና ጊዜ ከአሜሪካ ጎን ስለሆነ ወኪሎቹ ስምምነት ለመድረስ እን
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረጉ ድርድሮች በሥርዓት እና ገንቢ በሆነ መንገድ እየተካሄዱ መሆናቸውን እና ጊዜ ከአሜሪካ ጎን ስለሆነ ወኪሎቹ ስምምነት ለመድረስ እንዳይቸኵሉ መመሪያ እንደሰጣቸው ተናግሯል። አሁን እየተካሄዱ ያሉትን ውይይቶች ከኦባማ ዘመን የኑውክሌር ስምምነት ጋር የማይነጻጸር፣ የያኔው ስምምነት ኢራን የኑውክሌር መሳሪያ እንድታዘጋጅ ቀጥተኛ መንገድ እንደነበር ገልጿል። ስምምነት እስኪደረግ፣ እስኪረጋገጥ እና እስኪፈረም ድረስ የአሜሪካ የባሕር ኃይል እገታ ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ እንደሚቆይ ትራምፕ ገልጿል። ለመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ላደረጉት ድጋፍ አመስኖ ኢራን አንድ ቀን የአብርሃም ማህበርን ልትቀላቀል እንደምትችል ጠቁሟል።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 በመጀመሪያው የትራምፕ የስልጣን ዘመን፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበረው Mike Pompeo፣ ከኢራን ጋር ተደረሰበት የተባለውን ስምምነት የቅዠቶች ቅዠት በማለት አጣጥሎታል። ትራምፕንም፣ አይደረጋትም፣ እንደገና አጢነው ብሎታል። 'ሁኔታውን በጣም ቀላልና ቀጥተኛ ማድረግ ይቻላል፣ ሆርሙዝን ይክፈቱ ይክፈቱ፣ አለቀ! ካልሆነ፣ እንዲያውም ዘግይተናል፣ ኢራንን በምትቆስልበት ቦታ ላይ እንምታ!' ብሏል። የPompeoን እይታ በአሜሪካ የሚገኙ ጦርነት አቀንቃኝ ባለስልጣናት እና የእስራኤል ደላሎች (lobbyists)፣ እንዲሁም የእስራኤል መንግሥት የሚጋሩት ሲሆን፣ ትራምፕ 'በቀላሉ እጅ መስጠቱ' ከፍተኛን መደናገጥ ፈጥሯል። ስምምነቱ ለኢራን ያደላ እና ኢራንን አሸናፊ አድርጎ የሳለ ነው ብለውታል።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 እስራኤላዊያን ባለስልጣናት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ሁሉም በሚባል ደረጃ፣ ከኢራን ጋር ተደረሰ በተባለው ስምምነት ደንግጠዋል። አንዳንዶች በግልፁ፣ ብዙዎች በውስጥ፣ ትራም
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 እስራኤላዊያን ባለስልጣናት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ሁሉም በሚባል ደረጃ፣ ከኢራን ጋር ተደረሰ በተባለው ስምምነት ደንግጠዋል። አንዳንዶች በግልፁ፣ ብዙዎች በውስጥ፣ ትራምፕን በክፉ እየኮነኑት ናቸው። ተሸንፈናል ወይ? በማለት ይጠይቃሉ።

— 🇺🇸/🇮🇷 ኢራናዊ ተንታኝ፦ 'መንግሥታችንን ለመገልበጥ የተከፈተብን ጦርነት፣ አሁን የአሜሪካ ኃይሎች ከክልላችን በመውጣታቸው የሚጠቃለል ይሆናል።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 ስምምነቱ እንደሚባለውና እንደምንሰማው ከሆነ፣ ኢራን አሜሪካንን ጉድ ሠርታታለች ማለት ነው። ወይም እስራኤል አሜሪካንን ጉድ ሠርታታለች ማለት ነው። እስራኤል አሜሪካ ከቀጠናው እና ከመካከለኛው ምሥራቅ ጓዟን ይዛ እንድትወጣላት ትፈልጋለች የሚል ጠንካራ ግላዊ እምነት አለኝ። አሜሪካ በቀጠናው እስካለች እስራኤል ሁሌ ሁለተኛ ናት፣ ተቆጭ አላት። አሜሪካ ከወጣች ግን፣ በአካባቢው አንደኛ ፈላጭ ቆራጭ፣ አዛዥ ናዛዥ መሆን ትፈልጋለች። ይሄንን ተስፋ አድርጋ ነው፣ በቀጠናው የመጨረሻ ተቀናቃኟ ኢራን በአሜሪካ እንድትወገድላት ሌት ተቀን ሥትሰራ የነበረው። ኢራን ወደቀች ማለት፣ አበቃ! እስራኤል ዙፋኑን ትይዛለች። ችግሩ ኢራን አልወደቀችም፣ እንዲያውም ተጠናከረች። ከዓለም ኃያላን አንዷ እንደሆነች አሳይታለች። የብዙዎች ፍራቻ፣ የባሕሩን ወሽመጥ ከመቆጣጠር ጋር፣ እንዲያውም ይብስባታል ነው የሚሉት ኢራን። ይኸው ኢራን በስምምነቱ መሠረት (የመጨረሻ ከሆነ)፣ አሜሪካንን ከአካባቢው ልታስወጣት ነው። ተሳስቼ ነው፣ 'በስምምነት' አይደለም፣ በጡንቻ ነው። አሜሪካ ስትወጣ፣ ሁለቱ ለአካባቢው የበላይነት ይቀራሉ። እውን አሜሪካ ከዚያ ልትወጣ ነው? አይመስለኝም በፍፁም። ግን ይኸው ሊስማሙበት ነው ይሉናል።

🇺🇸ነገሩ በቁጥጥር ሥር ውሏል፣ ሁለት ተጠርጣሪዎች በዋይት ሃውስ ጠባቂዎች ተመተዋል።

—❗️🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ፦ የመግባቢያ ስምምነቱ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ከፋርስ ባሕር፣ ከኦማን ባሕር እና ከአረቢያ ባሕር መውጣትን እና ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የኢራን ንብረቶችን መልቀቅን ያካትታል – Al Mayadeen ***

+1

🇺🇸 አስቸኋይ ዜና፡ ከ 20 በላይ የተኩስ ድምፅ ዋይት ሃውስ ላይ ተሰምቷል። ከየት ወይም በማን እንደተተኮሰ አልታወቀም። የዋይት ሃውስ ልዩ ኃይሎች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው። ተኩሱ ሲሰማ ፕሬዝዳንቱ
🇺🇸 አስቸኋይ ዜና፡ ከ 20 በላይ የተኩስ ድምፅ ዋይት ሃውስ ላይ ተሰምቷል። ከየት ወይም በማን እንደተተኮሰ አልታወቀም። የዋይት ሃውስ ልዩ ኃይሎች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው። ተኩሱ ሲሰማ ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሃውስ ነበር --- CNN

🇮🇱🇺🇸 እስራኤል ከ'ረዳት አብራሪ' ወደ ተራ 'ተሳፋሪ' ደረጃ ዝቅ ተደርጋለች — The New York Times ትራምፕ ኔታንያሁን በኢራን ጦርነት ላይ ሙሉ በሙሉ 'ከጨዋታ አስወጥቶታል' 👉'መረጃ እጥረት ያለበት' እና 'ከኮክፒት የተባረረ' ሆኗል። 🇺🇸TRUMP፦ ኔታንያሁ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል።

🇺🇸🇮🇷⚡️ — ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የመግባቢያ ስምምነቱ በአብዛኛው እንደተጠናቀቀ እና የመጨረሻ ዝርዝሮቹ በቅርቡ እንደሚገለጹ ተናግረዋል። እኔ፣ ከሳውዲ ዓረቢያ፣ ከኳታር
🇺🇸🇮🇷⚡️ — ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የመግባቢያ ስምምነቱ በአብዛኛው እንደተጠናቀቀ እና የመጨረሻ ዝርዝሮቹ በቅርቡ እንደሚገለጹ ተናግረዋል።
እኔ፣ ከሳውዲ ዓረቢያ፣ ከኳታር፣ ከዩናይትድ አረብ ኤሜሬት፣ ከባሕሬን፣ ከዮርዳኖስ፣ ከቱርክ፣ ከፓኪስታን እና ከግብፅ መሪዎች ጋር፣ በኢራን ጉዳይ በጣም ጥሩ ስብሰባ አድርጌአለሁ። በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ፣ በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ እና በተዘረዘሩት ሌሎች የተለያዩ ሀገራት መካከል ስምምነት ላይ በአብዛኛው ደርሰናል። የመጨረሻው ደረጃ ላይ ነን። በተለየ መልኩ፣ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢቢ ኔታንያሁ ጋር የስልክ ጥሪ አድርጌ ነበር፣ ይህም በተመሳሳይ በጣም ጥሩ ሆኖ ነበር። የስምምነቱ የመጨረሻ ገጽታዎች እና ዝርዝሮችን በአሁኑ ጊዜ እየተወያየንባቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ ይሆናሉ። ከስምምነቱ ሌሎች በርካታ አካላት በተጨማሪ፣ የሆርሙዝ መተላለፊያ ይከፈታል።


🇺🇸🇮🇷🇮🇱⚡- "በአሜሪካ-ኢራን ስምምነት ላይ ያለው ትልቁ ችግር፦ ኢራን ወደፊት ጥቃት እንዳይደርስባት የምትቀበለው ዋስትና ነው፣" - የእስራኤል ቻናል 12 አሚቻይ ስቴይን።

🇮🇷 የኢራን አክቲቪስቶች ለሕዝባቸው፡ አሜሪካን ማመን ቀብሮ ነው፣ መቼም መቼም መቼም እንዳታምኗቸው።

⚡️🇺🇸🇮🇷 Axios፦ የትራምፕ አስተዳደር እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት ሊያደርጉ ተቃርበዋል፣ የቀሩት ክፍተቶች ደግሞ በበርካታ ነጥቦች አጻጻፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል፣ በድርድሩ ላይ
⚡️🇺🇸🇮🇷 Axios፦ የትራምፕ አስተዳደር እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት ሊያደርጉ ተቃርበዋል፣ የቀሩት ክፍተቶች ደግሞ በበርካታ ነጥቦች አጻጻፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል፣ በድርድሩ ላይ መረጃ የሰጠ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን። ባለሥልጣኑ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን በተመለከተ ምንም የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልወሰነ አፅንዖት ሰጥቷል። ይህ፣ ወደ ሦስት ወር የሚጠጋ ዕድሜ ያለው ጦርነት ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ሊሆን እንደሚችል እስካሁን ከተሰጡት ጠንካራ ምልክቶች፣ አንዱ ነው።

🇺🇸⚡️🇮🇷 ኢራን፣ Strait Of Hormuz የተባለ የባሕር ወሽመጥን አንቃ ይዛ፣ ዓለምን እያስለፈለፈች ነው። ኃያላን የተባሉ ሀገሮች ባሕሩን ከኢራን ነቅለው ቢያዟውሩት ይመርጡ ነበር፣ ነገር ግን ተፈጥሮ ሆነና የሚቻል አይደለም። ወሽመጥ ሸለቆ ውስጥ እንደገቡ ያወቁት ከገቡበት በኋላ ነው። በተለይ ፈጣሪ ኢራንን የሀብታም አረብ ሀገሮች መተላለፊያ ትቦ ጫፍ ላይ አስቀምጧት፣ ይኸው፣ ከፋችና ዘጊ ሆና፣ ቀረጥ እየሰበሰበች የባንቧ ተቆጣጣሪ ሆናለች። ከዚህ በፊት አልማው የማታውቀውን ገንዘብ ነው ባሕር ላይ ኬላ ዘርጋታ እያገኘች ያለችው። የጨነቀ ነገር ነው። እናም የገልፍ አረቦች ሳይላቸው አሜሪካና እስራኤልን ሆይሆይ ብለው ያስጀመሩትን ጦርነት፣ ዛሬ እንዲያቆሙላቸው በእንብርክክ እየለመኗቸው ነው። አሁን ትራምፕ ከኢራን ጋር ከምንግዜውም በላይ ስምምነት ልንፈራረም ጫፍ ደርሰናል ብሏል። ይሄ ለአረቦች እፎይታ የሚሰጥ ዜና ይመስለኛል፣ ለጊዜው። ፕሬዝዳንቱ በዚህ ሰዓት በዋይት ሃውስ ከሙስሊም ሀገሮች ጋር በስልክ እየተነጋገረ ነው። ውጤቱን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንሰማለን።