es
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Ir al canal en Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 303
Suscriptores
-624 horas
-247 días
-9030 días
Archivo de publicaciones
— 🇺🇸/🇮🇱 እስራኤልን ለመከላከል የተሰማሩ የአሜሪካ ወታደሮች ስልኮቻቸው በሞሳድ ተጠልፈዋል፣ መረጃዎቻቸው በሚስጥር በተጫኑ መበርበርያ ሶፍትዌሮች ሲሰለሉ ደርሰውበታል – ኒው ዮርክ ታይምስ
— 🇺🇸/🇮🇱 እስራኤልን ለመከላከል የተሰማሩ የአሜሪካ ወታደሮች ስልኮቻቸው በሞሳድ ተጠልፈዋል፣ መረጃዎቻቸው በሚስጥር በተጫኑ መበርበርያ ሶፍትዌሮች ሲሰለሉ ደርሰውበታል – ኒው ዮርክ ታይምስ

🇩🇪🇫🇷🇬🇧 Merz፣ Macron እና Starmer እሁድ፣ ጁን 7 ላይ በለንደን ከዜሌንስኪ ጋር ይገናኛሉ። — DW የስብሰባው አላማ፣ የሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማቆም የሚ
🇩🇪🇫🇷🇬🇧 Merz፣ Macron እና Starmer እሁድ፣ ጁን 7 ላይ በለንደን ከዜሌንስኪ ጋር ይገናኛሉ። — DW የስብሰባው አላማ፣ የሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር ነው። በተጨማሪም፣ ለዩክሬን የገንዘብ እና የመሳሪያ ድጋፍ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ሩሲያ፣ ከዚህም በላይ በጦርነቱ ዋጋ የሚያስከፍላትን መንገዶች ለመዳሰስም ነው። — ፓርቲዎቹ፣ ከሞስኮ ጋር ለአዳዲስ ድርድሮች ያሉትን ተስፋዎች ለመወያየትም አቅደዋል።

🇺🇸 “ስሙ ኔታንያሁ አይደለም። ስሙ ሚሌይኮቭስኪ ነው። የተወለደው በፖላንድ ነው። አንዲት ሚሊ ግራም የሴማዊ ደም እንኳ የለውም።” — ኬኔዝ ኦኬፌ ፍልስጤማውያን እውነተኛ ሴሜቶች እንደሆኑ ይከራከራል እና በእስራኤል ተቺዎች ላይ የሚሰነዘሩ የፀረ-ሴማዊነት ክሶችን ውድቅ ያደርጋል። በአሜሪካ ውስጥ፣ እስራኤልን መተቸት ቀላል ነገር አይደለም፣ ሥራህን ያሳጡሃል፣ ህልውናህን፣ መኖርህን ያሳጡሃል። ሰዎችን ዝም ለማስባል የማያደርጉት ምንም የለም። ኦኬፌ ተቃውሞው በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ልጆቹን ጨምሮ የራሱ ቤተሰብ የሞት ማስፈራሪያዎች እንደሚደርሳቸው ይናገራል። “ብዙዎች ያንን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኞች አይደሉም። ስለዚህ ሰዎች ለምን እንደሚፈሩ እና ለዚህም ምክንያት ዝም እንደሚሉ ግልፅ ይሆንልሃል።”

🇮🇷⚡️🇺🇸 “ጠንካራ ናቸው፣ ኩሩ ናቸው” ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ለረጅም ጊዜ የተደረገው ድርድር የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያልደረሰበት ምክኒያት፣ "የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ባለስልጣናት፣ ጠንካራ እና
🇮🇷⚡️🇺🇸 “ጠንካራ ናቸው፣ ኩሩ ናቸው” ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ለረጅም ጊዜ የተደረገው ድርድር የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያልደረሰበት ምክኒያት፣ "የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ባለስልጣናት፣ ጠንካራ እና ኩሩ ስለሆኑ ነው፣" ሲል አብራርቷል። "ጠንካራ ስለሆኑ፣ ኩሩ ስለሆኑ...ትንሽ ጊዜ ይወስዳል" በማለት ለምን ድርድሩ አልተፈታም ለሚለው ምክንያቶቹን ለNBC News በሰጠው ቃለ መጠይቅ ተናግሯል። አንድ የኋይት ሃውስ ኃላፊ በበኩሉ፣ “ኢራኖች ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ በጭራሽ ያላሰቧቸው ነገሮች አሉ፣ ነገር ግን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም ምርጫ የላቸውም" ሲል አክሏል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 “ጠንካራ ናቸው፣ ኩሩ ናቸው” ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ለረጅም ጊዜ የተደረገው ድርድር የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያልደረሰበትን ምክኒያት፣ "የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ባለስልጣናት፣ ጠንካራ እና
🇮🇷⚡️🇺🇸 “ጠንካራ ናቸው፣ ኩሩ ናቸው” ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ለረጅም ጊዜ የተደረገው ድርድር የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያልደረሰበትን ምክኒያት፣ "የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ባለስልጣናት፣ ጠንካራ እና ኩሩ ስለሆኑ ነው፣" ሲል አብራርቷል። "ጠንካራ ስለሆኑ፣ ኩሩ ስለሆኑ...ትንሽ ጊዜ ይወስዳል" በማለት ለምን ድርድሩ አልተፈታም ለሚለው ምክንያቶቹን ለNBC News በሰጠው ቃለ መጠይቅ ተናግሯል። አንድ የኋይት ሃውስ ኃላፊ በበኩሉ፣ “ኢራኖች ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ በጭራሽ ያላሰቧቸው ነገሮች አሉ፣ ነገር ግን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም ምርጫ የላቸውም" ሲል አክሏል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 “ጠንካራ ናቸው፣ ኩሩ ናቸው” ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ለረጅም ጊዜ የተደረገው ድርድር የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያልደረሰበት ምክኒያት፣ የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ባለስል
🇮🇷⚡️🇺🇸 “ጠንካራ ናቸው፣ ኩሩ ናቸው” ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ለረጅም ጊዜ የተደረገው ድርድር የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያልደረሰበት ምክኒያት፣ የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ባለስልጣናት ጠንካራ እና ኩሩ ስለኑ ሲል አብራርቷል። "ጠንካራ ስለሆኑ፣ ኩሩ ስለሆኑ...ትንሽ ጊዜ ይወስዳል" በማለት ለምን ድርድሩ አልተፈታም ለሚለው ምክንያቶቹን ለNBC News በሰጠው ቃለ መጠይቅ ተናግሯል። አንድ የኋይት ሃውስ ኃላፊ በበኩሉ፣ “ኢራኖች ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ በጭራሽ ያላሰቧቸው ነገሮች አሉ፣ ነገር ግን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም ምርጫ የላቸውም" ሲል ተናግሯል።

🇮🇷🇮🇱🇱🇧 አራግቺ ለሊባኖስ ፕሬዝዳንት ምላሽ ሰጥቷል የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ለCNN በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ፣ ሊባኖስ ላይ ለደረሰው ቀውስ ኢራንን ተጠያቂ ያደረጉበትን መንገድ፣
🇮🇷🇮🇱🇱🇧 አራግቺ ለሊባኖስ ፕሬዝዳንት ምላሽ ሰጥቷል የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ለCNN በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ፣ ሊባኖስ ላይ ለደረሰው ቀውስ ኢራንን ተጠያቂ ያደረጉበትን መንገድ፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺ ምላሽ ሰጥቶበታል። “በአቶ አውን አስተያየት መሠረት፣ አንድ ሰው፣ ከሊባኖስ 1/5ኛውን የወረረች፣ 1/4ኛውን ሊባኖሳዊ ከቤቱ ያፈናቀለች እና በየቀኑ ሀገሩን የሚያፈነዳው ኢራን ነው ብሎ ሊያስብ ይችላል። ሊባኖስ ለኢራን የድርድር መጫወቻ ብትሆን ኖሮ፣ ከረጅም ጊዜ በፊት ስምምነት እንደርስ ነበር። አቶ ፕሬዝዳንት፣ በገዛ ሕዝብዎና በኢራን ላይ ጣትዎን ከመጠቆም ይልቅ፣ ሊባኖስን ከእውነተኛው ጠላትዎ ያድኑ።"

🇪🇹 በአሁኑ ሰዓት፣ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት 'የአርሴናል ደጋፊዎች' ዝግጅት የተባለውን ድግስ ለማሳካት፣ የከተማው አስተዳደር እና የመንግሥት ባለስልጣናት እጅ
+3
🇪🇹 በአሁኑ ሰዓት፣ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት 'የአርሴናል ደጋፊዎች' ዝግጅት የተባለውን ድግስ ለማሳካት፣ የከተማው አስተዳደር እና የመንግሥት ባለስልጣናት እጅግ በጣም እየለፉ ባለበት ነው፣ በዓለም መድረክ ላይ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንዲህ ሆና ጥላሸት የተበተነባት። ቢራ ሁሉ ገብቶ ነበር ለጭፈራው፣ ዣንጥላ የያዙ እናቶችም 'የአርሴናል ደጋፊዎች' ተብለው በተንቋቋ ወገባቸው፣ በፀሐይ እንዲገቡ ተደርገው ቦታ ቦታቸውን ይዘው ነበር፣ ድግሱ አልቆ ሊቆረስ ሲል ነው፣ ኢላን ማስክ የተባለ ትሪሊየነር ገብቶ ውሃ የቸለሰበት።

በአሁኑ ሰዓት፣ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት 'የአርሴናል ደጋፊዎች' ዝግጅት የተባለውን ድግስ ለማሳካት፣ የከተማው አስተዳደር እና የመንግሥት ባለስልጣናት እጅግ በጣም
+3
በአሁኑ ሰዓት፣ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት 'የአርሴናል ደጋፊዎች' ዝግጅት የተባለውን ድግስ ለማሳካት፣ የከተማው አስተዳደር እና የመንግሥት ባለስልጣናት እጅግ በጣም እየለፉ ባለበት ነው፣ በዓለም መድረክ ላይ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንዲህ ሆና ጥላሸት የተበተነባት። ቢራ ሁሉ ገብቶ ነበር ለጭፈራው፣ ዣንጥላ የያዙ እናቶችም 'የአርሴናል ደጋፊዎች' ተብለው በተንቋቋ ወገባቸው፣ በፀሐይ እንዲገቡ ተደርገው ቦታ ቦታቸውን ይዘው ነበር፣ ድግሱ አልቆ ሊቆረስ ሲል ነው፣ ኢላን ማስክ የተባለ ትሪሊየነር ገብቶ ውሃ የቸለሰበት።

🇪🇹⚡️በቅርቡ የመጀመሪያው የዓለም ትሪሊየነር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ኢላን ማስክ፣ 'ኢትዮጵያ የደሃ ደሃ ናት' በሚለው ነጥብ ላይ መስማማቱን ገለጸ። ይህን የገለጸው፣ ዛሬ በ X ገፁ ላይ ባሰፈ
🇪🇹⚡️በቅርቡ የመጀመሪያው የዓለም ትሪሊየነር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ኢላን ማስክ፣ 'ኢትዮጵያ የደሃ ደሃ ናት' በሚለው ነጥብ ላይ መስማማቱን ገለጸ። ይህን የገለጸው፣ ዛሬ በ X ገፁ ላይ ባሰፈረው ልጥፉ ነው። የዚህ ሓሳብ መነሻ ባለቤት እራሱ ኢላን ማስክ አይደለም። የዚህ ሓሳብ ዋና ባለቤት አፍሪካዊቷ ሥራ ፈጣሪ፣ አነቃቂ ተናጋሪና የሴኔጋል ዜግነት ያላት (በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የምትኖረው) ወይዘሮ ማጋቴ ዋዴ (Magatte Wade) ናት። ወይዘሮ ማጋቴ ዋዴ፣ በገጿ ያሰፈረችውና በኢላን ማስክ ታግዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ የሆነው ሙሉ መልዕክት የሚከተለው ነው ።
"ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተገዝታ አታውቅም። በታሪኳ አብዛኛው ዘመን ግን በአህጉሪቱ ካሉ በጣም የደሃ ደሃ ሀገራት አንዷ ነበረች። በሌላ በኩል፣ ቪየትናም በፈረንሳይ የቅኝ ግዛት ሥር ነበረች፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት በዘለቀ ጦርነት ፈራርሳለች፣ አሁን ግን ወደ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ብልጽግና ጎዳና ላይ ትገኛለች። አፍሪካ ለምን ድሃ ሆነች ለሚለው ጥያቄ መልሱ 'የቅኝ ግዛት' ቢሆን ኖሮ፣ ኢትዮጵያ ሀብታም መሆን ነበረባት፤ ቪየትናም ደግሞ መክሰር/ድሃ መሆን ነበረባት። ነገር ግን ሁለቱም እውነት አይደሉም። እባካችሁ ይሄንን ሰበብ አሁን ማቆም (ማረፍ) እንችላለን?"
 ይህ መረጃ፣ ኢትዮጵያ፣ ትልቁ የዓለም መድረክ በሆነው በ X ፊት፣ በአፍሪካ የድህነት ታሪክ ማማ ላይ የምትገኝ ሀገር እንደሆነች ተናግሯል። *-*-*-

🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከእንቅልፉ ተነስቶ ሁሉም ሰው ትራምፕን እንደሚወድ የሚያሳይ በAI የተፈጠረ "የሙዚቃ ቪዲዮ" ለመለጠፍ ወሰነ።

🇷🇺🇺🇦⚡️— ሩሲያ፣ የዋና ከተማዋን የአየር መከላከያ መረብ ለማጠናከር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች ሲሆን፣ ዛሬ የPantsir-SMD የአየር መቃወሚያ መሳሪያዎችን በMi-26 ሄሊኮፕተሮች በመጠቀም በሞስኮ ባሉ ከፍተኛ ሕንፃ ጣሪያዎች ላይ ስትሰቅል ታይታለች። አሁን ላይ፣ የዩክሬን ድሮኖች እና ሚሳዬሎች በሩሲያ ላይ ከፍተኛን ስጋት የደቀኑሲሆን፣ ሞስኮ ድረስ ዘልቀው በመግባት ጥቃት እየፈጸሙ ናቸው። በዚህም ምክኒያት ዋና ከተማዋን በመከላከል ዙሪያ፣ ሩሲያ ሰፊ ሥራ እንድትሰራ ተገድዳለች።

🇷🇺🇺🇦⚡️— ሩሲያ የዋና ከተማዋን የአየር መከላከያ መረብ ለማጠናከር እያደረገች ባለችው ጥረት፣ የPantsir-SMD የአየር መቃወሚያ መሳሪያዎችን በMi-26 ሄሊኮፕተሮች በመጠቀም በሞስኮ ባሉ ከፍተኛ ሕንፃዎች ጣሪያዎች ላይ እየሰቀለች ነው። ዛሬ ላይ፣ የዩክሬን ድሮኖች እና ሚሳዬሎች፣ ሞስኮ ድረስ ዘልቀው በመግባት ጥቃት እየፈጸሙ ናቸው። በዚህም ዋና ከተማዋን በመከላከል ዙሪያ፣ ሩሲያ ሰፊ ሥራ እንድትሰራ ትገድዳለች።

🇪🇹⚡️አንድ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ በባሕር ዳር ስቴዲየም ምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረገው ንግግር፣ ስቴዲየሙ እንደ ፓሪስ ሴይንት ጀርሜን፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል እና የመሳሰሉት የአውሮፓ ክለቦች ሀገራቸው ሙቀት ሲሆን መጥተው ሊጫወቱበት እንደሚችሉ ተናገረ። ይሄን ያለው፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ አብይ አሕመድ ዓሊ ከፍተኛ አማካሪና የሀገሩ የደህንነት ኃላፊ ነው። ብዙዎች፣ ዛሬ ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት፣ በአእምሮ ቅንጭርና እና ውስንነት የተጎዱ ናቸው ብለው በመክሰስ፣ በሁሉም ዘርፍ ሀገሩ ለገባበት ድቀት ተጠያቂ ሲያደርጓቸው ይሰማሉ። በሌላ በኩል፣ ሌሎች፣ ለዚህ ሁሉ መቀመቅ ሕዝቡን በግንባር ቀደምትነት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ይሞግታሉ። እነዚሁ አካላት፣ "ግን ምን ሆነን ነው?" ሲሉ ራሳቸውን ይጠይቃሉ።

+2
🇺🇦❌🇷🇺— የዩክሬን ድሮኖች ዛሬ ጠዋት ላይ በሩሲያ የሚገኘውን የቲዩመን የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ላይ ጥቃት በመሰንዘር በተቋሙ ላይ ከፍተኛ እሳት እንዲነሳ አድርገዋል።

🇺🇸🇮🇱🇸🇦 ለግል ኩባንያዎ ከሳዑዲ አረቢያ 2 ቢሊዮን ዶላር ለምን ወሰዱ? 🗣 ጃሬድ ኩሽነር (የትራምፕ ሴት ልጅ ባል): የተቀበልኩትን ገንዘብ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ግንኙነት ለመፍጠር እና ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከእስራኤል የመጡ ነጋዴዎችን እርስ በእርስ ለማገናኘት በእስራኤል ውስጥ ኢንቨስት አድርጌዋለሁ።"

🇺🇸🇮🇱🇸🇦 ለግል ኩባንያዎ ከሳዑዲ አረቢያ 2 ቢሊዮን ዶላር ለምን ወሰዱ? 🗣 ጃሬድ ኩሽነር (የትራምፕ ሴት ልጅ ባል): የተቀበልኩትን ገንዘብ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ግንኙነት ለመፍጠር እና ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከእስራኤል የመጡ ነጋዴዎችን እርስ በእርስ ለማገናኘት በእስራኤል ውስጥ ኢንቨስት አድርጌያለሁ።"

🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ስለላ እያደረገች ነው ሲል፣ NBC ዘግቧል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።

🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ሰላይ እያደረገች ነው ሲል NBC ዘግቧል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።

🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ሰላይ እያደረገች ነው ሲል NBC ዘግቧል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።