🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
Ir al canal en Telegram
Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
1 383
Suscriptores
+624 horas
+3437 días
+63530 días
Archivo de publicaciones
Repost from []سَكِينَةُ الْقُلُوبِ ሰኪነቱል-ቁሉብ[]
📩 ለእኛ... ለሁላችንም የተላከ መልእክት
ሁላችንም በውስጣችን መልካም ቤተሰብ የመመሥረት ትልቅ ሕልም አለን። ሁላችንም ልባችን በተመሳሳይ ምኞት ይረታል፤ ነገ መልካም ልጆች እንዲኖሩን፣ መልካም ባል ወይም መልካም ሚስት እንድንታደል እንመኛለን። ነገር ግን...
ለአንድ አፍታ ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ! አሁን እኛ ማን ነን? በምንስ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው???
እኛ ወንዶች... ዓይናችንን ከባዕድ ሴቶች (ለእኛ ካልተፈቀዱ) እየከለከልን ነው? ሰላታችንን በወቅቱ እና በጀማዓ በመስጊድ እየሰገድን ነው?እኛ ሴቶች... ከሸሪዓዊ ሂጃብ ጋር ያለን ቁርኝት የት ላይ ነው? ከሰላታችን... በተለይም ከፈጅር ሰላት ጋር ያለን ጥንካሬ ምን ያህል ነው? ከሰዎች ጋር ያለን ሙዓመላ (ግንኙነት)፣ ታማኝነታችን እና ፈተናዎችን የመቋቋም ትዕግሥታችንስ?
እስከ መቼ ነው አላህ የማይወደውን የሐራም ግንኙነት እና ንግግሮች ውስጥ የምንጣደው? እኛ በውስጣችን የምንደብቀውን ምስጢር አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው።
አዎ! ሁላችንም መልካም ቤተሰብ የመመሥረት ሕልም አለን፤ ነገር ግን ለውጡን መጀመሪያ ከራሳችን መጀመር እንዳለብን ለምን ይዘነጋናል?እኛ ሴቶች... ባላችን ወደ ሌላ ሴት እንዳያይ እንመኛለን፤ ነገር ግን እኛ ራሳችን ለሌሎች ወንዶች መፈተኛና የስሜት መነሻ እየሆንን ከሆነ እንዴት ይሆናል? "ምንዳ (ዋጋ) ከሥራው ዓይነት ጋር ተመሳሳይነው" (የዘራነውን ነው የምናጭደው)።
እኛ ወንዶች...ልጆቻችን መልካም እና ሳሊህ እንዲሆኑ እንመኛለን፤ ነገር ግን እኛ ራሳችን ለእነሱ የሚከተሉት ቀጥተኛ አርአያና ምሳሌ ሳንሆንላቸው እንዴት መልካምነታቸውን እንጠብቃለን?
ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ እህቴ ሆይ ...እኛ ሁላችንም የተሻለውን የዲን ቤተሰብ ለመገንባት የለውጡ
መጀመሪያ (ዋናው ዘር) እንሁን።
ጅማሬው እኛው ራሳችን ነን...።
https://t.me/+SpJHRe6JfQQ0NGI0
Repost from ስለ ቀልባችን
የሰዎች ዕዳ ላስጨነቃችሁ፣ እንቅልፍ ለነሳችሁ ሁሉ መፍተሔ!
ወንድም አቡ ሱፍያን
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Repost from هَذِهِ عَقيدَتُنَا
ሷሊህ የሆነቿን አግባ💍
የሷሊህ ሴት ዋና ዋና መገለጫዎች
አላህን ፈሪ መሆን፦ በድብቅም በግልጽም አላህን የምትፈራና የእሱን ትእዛዛት የምታከብር ናት።
መልካም ሥነ-ምግባር፦ ለሰዎች ያላት አቀራረብ፣ ንግግሯና ተግባሯ በትሕትናና በደግነት የተሞላ ነው።
ታማኝነትና ጥንቃቄ፦ ባሏ በሌለበት ወቅት እራሷን፣ የባሏን ንብረትና የልጆቿን ክብር ትጠብቃለች።
t.me/qdemiy_letwuhideፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት / ሀሰት
ቁርዓን በየትኛው ቀን ላይ ነው መውረድ የጀመረው ?
Repost from قناة أبي عمار أمير بن محمد አሚር ሙሐመድ
በኡስታው ዐማር አሚር ሙሐመድ እና የእህታችን ሱመያ ዐበዱልቃዲር የሰርግ
ፕሮግራም ላይ የቀረበ አዲስ ሙሓደራ🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🎙በኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ 💡 እርዕስ ⏮️በባልና በሚስት መካከል ያሉ ማህበራዊ ኑሮ ነብዩ 🤍ከሚስቶቻቸዉጋ እንዴት ነበሩ በምን መልኩ ነበር ያለ ሂደታቸዉ......⏭️ ╭┈──── ••↯↯↯▫️ ╰┈➢//t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED ✰••👈
ረሱል (ﷺ) ጭንቀት ወይም ከባድ ነገር በገጠማቸው ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፦
«ያ ሐዩ ያ ቀዩም! ቢራሕመቲከ አስተጊሥ።
አንተ ህያው የሆንክ፣ ፍጥረታትን ሁሉ የምትቀሰቅስና የምታስተናብር ጌታ ሆይ! በእዝነትህ እታደጋለሁ/እረድኤትን እፈልጋለሁ።
ሶሂህ ሱነን አት-ቲርሚዚ (3524)
ረሱል (ﷺ) አላህን አውስተው እንዲህ አሉ፦
"አላህ እንዲህ ይላል፦ "እኔ ባሪያዬ በእኔ ላይ ባለው (ጥርጣሬ) ዘንድ ነኝ። ሲያስታውሰኝም እኔ ከእሱ ጋር ነኝ። በነፍሱ (በውስጡ) ቢያስታውሰኝ በነፍሴ (በውስጤ) አስታውሰዋለሁ። በሰዎች ስብስብ ውስጥ ቢያስታውሰኝ ከእነሱ በተሻለ ስብስብ (በመላእክት ዘንድ) አስታውሰዋለሁ። በስንዝር ወደ እኔ ቢቃረብ (በክንድ ወደ እሱ እቃረባለሁ)፤ በክንድ ወደ እኔ ቢቃረብ በባንድ (በሁለት እጆች መዘርጋት) ወደ እሱ እቃረባለሁ፤ እየተራመደም ወደ እኔ ቢመጣ እኔ እየሮጥኩ (በፍጥነት) እመጣለታለሁ።"»
ሶሂህ አል-ቡኻሪ (7405) ሶሂህ ሙስሊም (2675)
Repost from قناة أبي عمار أمير بن محمد አሚር ሙሐመድ
የቀጥታ ስረጭት ፕርግራማችን እደቀጠ ነዉ
የሶስተኛዉ ፕሮግራም
🎙️በኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ
ርዕስ⭐️⏮️በባልና በሚስት መሀከል ያለ ማህበራዊ ኑሮ⏭️
🚀https://t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED?livestream=ac590f55a2b4160087
Repost from قناة أبي عمار أمير بن محمد አሚር ሙሐመድ
ቀጠሮ አለን'ኮ አረፈድን አይደል
https://t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED?livestream=ac590f55a2b4160087
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"ሀብታምነት (የንብረት መብዛት) አይደለም፤ ነገር ግን እውነተኛ ሀብታምነት የልብ መበልጸግ (በአላህ ውሳኔ መርካት) ነው።
ሶሂህ አል-ቡኻሪ (6446) ሶሂህ ሙስሊም (1051)
እያወቁ እንዳላወቁ እያዩ እንዳላዩ መሆን ብዙን እንድናውቅ ብዙን እንድናይ የሚጠቅመን ሲሆን
ሳያውቁ እንዳወቁ ሳያው እንዳዩ መሆን ደግሞ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ፡፡
አሥግቶኛልና የአፊያችን ነገር፣
እስኪ ስለፈውሱ ትንሽ እንማከር፣
አንች ውዷ ጓደ እደት ነሽ ጤናሽን፣
ከሳምንቱ ዛሬ ንገሪኝ ለውጥሽን፣
እኔሥ እደዛውነኝ አፊያው እደራቀኝ፣
ውስጤ እደተከፋ ደሥታ እደናፈቀኝ፣
እንማከር ብዬ መጣሁኝ ቢጨቀኝ፣
ሰላምን ፈልጌ ቢለቅሽ ቢለቀኝ፣
መፍትሄ እንፈልግ ይብቃና ዝምታው፣
እህቴ አንዘንጋ ከባድ ነው በሽታው፣
ታይ ብለው መክረውኝ ከልክለውኝ ልተው፣
ዛሬ እያልኩ ነገ ስቀጥር ቆይቸ፣
አሁን በነን ስል ከጛፍላ ነቅቸ፣
ልቤ ርቆ ሂዷል አላገኘሁትም፣
መመለሥ አልቻልኩም አላወኩበትም፣
ምን ይሆን መፍትሄው እንፈልግ መላ፣
ነፍሳችን ደርቃለች ሁናለች ተላላ ፣
ጎዳናውን ለቃ ዙራለች በሌላ፣
ዟሂሯን አስውባ ለሠው ደህና መሥላ፣
በወንጀል እስር ቤት ተጠፍራ ነፍሴ፣
ስለውጭ ውበቴ ስለ አለባበሴ፣
ስጨነቅ ገረመኝ አጀብ ሞኝነቴ፣
አሁን በዚህ ሀሌ ቢመጣብኝ ሞቴ፣
ምን አስቀድመሻል ብሎ ሲጠይቀኝ፣
ምን ልመልስ ይሆን ወላሂ ጨነቀኝ፣
እገዥኝ ውዷዬ በዱንያ ላይ ዛሬ፣
ልዳን ከበሽታው ለስበቡ ጥሬ፣
ለአለም ጠቢቦች ባማክር ዘርዝሬ፣
የህመሜን ጉዳይ ሁሉን ተናገሬ፣
አላገኝም ፈውሱን የትም ቦታ ዙሬ፣
በሽታው ልቤን ነው ስበቡ መእሲያ:
እደተረዳሁት ከቀራሁት ዓያ:
የመውጫውን ነገር ከሱ መዳኒያችን፣
እስኪ እንመካከር ምን ይሆን ፈውሳችን፣
✍
Repost from قناة أبي عمار أمير بن محمد አሚር ሙሐመድ
ከሙሽራው ቤት ምሳችንን በላንና የተወሰነ መመካከር አስበን አንድ ሁለት እየተባባልን ነው
https://t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED?livestream=72c3296e0a772b1a22
ረሱል (ﷺ) ከሳሪ ማለት ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን? አሉ። ሰሃቦችም "ከሳሪ ማለት እኮ ገንዘብና ንብረት የሌለው ነው አሉ።
ረሱልም (ﷺ) እንዲህ አሉ፦
"ከኡመቴ እውነተኛው ከሳሪ ማለት በቂያማ ቀን በሶላት፣ በጾምና በዘካት (በብዙ መልካም ስራ) መጥቶ፣ ነገር ግን ይህንን ሰድቦ፣ ይህንን አምቶ (ስሙን አጥፍቶ)፣ የዚህን ገንዘብ በልቶ፣ የዚህን ደም አፍስሶ የሚመጣው ሰው ነው። ከዚያም ለመልካም ስራው (ለተበደሉት ሰዎች) ይሰጣቸዋል። በእሱ ላይ ያለባትን እዳ ሳይከፍል መልካም ስራው ካለቀቀ፣ "ከተበዳዮቹ ወንጀል" ተወስዶ በእሱ ላይ (ይጫናል)፤ ከዚያም ወደ ወደ ጀሀነም ይጣላል።
ሶሂህ ሙስሊም (2581)
