ch
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

前往频道在 Telegram

显示更多
未指定国家未指定类别
1 383
订阅者
+624 小时
+3437 天
+63530 天
帖子存档
📩 ለእኛ... ለሁላችንም የተላከ መልእክት     ሁላችንም በውስጣችን መልካም ቤተሰብ የመመሥረት ትልቅ ሕልም አለን። ሁላችንም ልባችን በተመሳሳይ ምኞት ይረታል፤ ነገ መልካም ልጆች እንዲኖሩን፣ መልካም ባል ወይም መልካም ሚስት እንድንታደል እንመኛለን። ነገር ግን... ለአንድ አፍታ ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ! አሁን እኛ ማን ነን? በምንስ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው??? እኛ ወንዶች... ዓይናችንን ከባዕድ ሴቶች (ለእኛ ካልተፈቀዱ) እየከለከልን ነው? ሰላታችንን በወቅቱ እና በጀማዓ በመስጊድ እየሰገድን ነው?እኛ ሴቶች... ከሸሪዓዊ ሂጃብ ጋር ያለን ቁርኝት የት ላይ ነው? ከሰላታችን... በተለይም ከፈጅር ሰላት ጋር ያለን ጥንካሬ ምን ያህል ነው? ከሰዎች ጋር ያለን ሙዓመላ (ግንኙነት)፣ ታማኝነታችን እና ፈተናዎችን የመቋቋም ትዕግሥታችንስ? እስከ መቼ ነው አላህ የማይወደውን የሐራም ግንኙነት እና ንግግሮች ውስጥ የምንጣደው? እኛ በውስጣችን የምንደብቀውን ምስጢር አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው። አዎ! ሁላችንም መልካም ቤተሰብ የመመሥረት ሕልም አለን፤ ነገር ግን ለውጡን መጀመሪያ ከራሳችን መጀመር እንዳለብን ለምን ይዘነጋናል?እኛ ሴቶች... ባላችን ወደ ሌላ ሴት እንዳያይ እንመኛለን፤ ነገር ግን እኛ ራሳችን ለሌሎች ወንዶች መፈተኛና የስሜት መነሻ እየሆንን ከሆነ እንዴት ይሆናል? "ምንዳ (ዋጋ) ከሥራው ዓይነት ጋር ተመሳሳይነው" (የዘራነውን ነው የምናጭደው)። እኛ ወንዶች...ልጆቻችን መልካም እና ሳሊህ እንዲሆኑ እንመኛለን፤ ነገር ግን እኛ ራሳችን ለእነሱ የሚከተሉት ቀጥተኛ አርአያና ምሳሌ ሳንሆንላቸው እንዴት መልካምነታቸውን እንጠብቃለን? ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ እህቴ ሆይ ...እኛ ሁላችንም የተሻለውን የዲን ቤተሰብ ለመገንባት የለውጡ መጀመሪያ (ዋናው ዘር) እንሁን። ጅማሬው እኛው ራሳችን ነን...። https://t.me/+SpJHRe6JfQQ0NGI0

የሰዎች ዕዳ ላስጨነቃችሁ፣ እንቅልፍ ለነሳችሁ ሁሉ መፍተሔ! ወንድም አቡ ሱፍያን t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

ሷሊህ የሆነቿን አግባ💍 የሷሊህ ሴት ዋና ዋና መገለጫዎች አላህን ፈሪ መሆን፦ በድብቅም በግልጽም አላህን የምትፈራና የእሱን ትእዛዛት የምታከብር ናት። መልካም ሥነ-ምግባር፦ ለሰዎች ያላት አቀራረብ፣
ሷሊህ የሆነቿን አግባ💍 የሷሊህ ሴት ዋና ዋና መገለጫዎች አላህን ፈሪ መሆን፦ በድብቅም በግልጽም አላህን የምትፈራና የእሱን ትእዛዛት የምታከብር ናት። መልካም ሥነ-ምግባር፦ ለሰዎች ያላት አቀራረብ፣ ንግግሯና ተግባሯ በትሕትናና በደግነት የተሞላ ነው። ታማኝነትና ጥንቃቄ፦ ባሏ በሌለበት ወቅት እራሷን፣ የባሏን ንብረትና የልጆቿን ክብር ትጠብቃለች። t.me/qdemiy_letwuhide

ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️ ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት / ሀሰት ቁርዓን በየትኛው ቀን ላይ ነው መውረድ የጀመረው ?

በኡስታው ዐማር አሚር ሙሐመድ  እና  የእህታችን ሱመያ ዐበዱልቃዲር የሰርግ 
ፕሮግራም ላይ የቀረበ አዲስ ሙሓደራ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🎙በኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ            💡  እርዕስ    ⏮️በባልና በሚስት መካከል ያሉ ማህበራዊ ኑሮ ነብዩ 🤍ከሚስቶቻቸዉጋ  እንዴት ነበሩ በምን መልኩ ነበር ያለ ሂደታቸዉ......⏭️ ╭┈──── ••↯↯↯▫️ ╰┈➢//t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED ✰••👈

ረሱል (ﷺ) ጭንቀት ወይም ከባድ ነገር በገጠማቸው ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፦ «ያ ሐዩ ያ ቀዩም! ቢራሕመቲከ አስተጊሥ። አንተ ህያው የሆንክ፣ ፍጥረታትን ሁሉ የምትቀሰቅስና የምታስተናብር ጌታ ሆይ! በእዝነትህ እታደጋለሁ/እረድኤትን እፈልጋለሁ። ሶሂህ ሱነን አት-ቲርሚዚ (3524)

ረሱል (ﷺ) አላህን አውስተው እንዲህ አሉ፦ "አላህ እንዲህ ይላል፦ "እኔ ባሪያዬ በእኔ ላይ ባለው (ጥርጣሬ) ዘንድ ነኝ። ሲያስታውሰኝም እኔ ከእሱ ጋር ነኝ። በነፍሱ (በውስጡ) ቢያስታውሰኝ በነፍሴ (በውስጤ) አስታውሰዋለሁ። በሰዎች ስብስብ ውስጥ ቢያስታውሰኝ ከእነሱ በተሻለ ስብስብ (በመላእክት ዘንድ) አስታውሰዋለሁ። በስንዝር ወደ እኔ ቢቃረብ (በክንድ ወደ እሱ እቃረባለሁ)፤ በክንድ ወደ እኔ ቢቃረብ በባንድ (በሁለት እጆች መዘርጋት) ወደ እሱ እቃረባለሁ፤ እየተራመደም ወደ እኔ ቢመጣ እኔ እየሮጥኩ (በፍጥነት) እመጣለታለሁ።"» ሶሂህ አል-ቡኻሪ (7405) ሶሂህ ሙስሊም (2675)

Telebirr ±251 911 678 186 Sheh Mohamedamin CBE: 1000680622543

የቀጥታ ስረጭት ፕርግራማችን እደቀጠ ነዉ የሶስተኛዉ ፕሮግራም 🎙️በኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ ርዕስ⭐️⏮️በባልና በሚስት መሀከል ያለ ማህበራዊ ኑሮ⏭️ 🚀https://t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED?livestream=ac590f55a2b4160087

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ሀብታምነት (የንብረት መብዛት) አይደለም፤ ነገር ግን እውነተኛ ሀብታምነት የልብ መበልጸግ (በአላህ ውሳኔ መርካት) ነው። ሶሂህ አል-ቡኻሪ (6446) ሶሂህ ሙስሊም (1051)

እያወቁ እንዳላወቁ እያዩ እንዳላዩ መሆን ብዙን እንድናውቅ ብዙን እንድናይ የሚጠቅመን ሲሆን ሳያውቁ እንዳወቁ ሳያው እንዳዩ መሆን ደግሞ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ፡፡
እያወቁ እንዳላወቁ እያዩ እንዳላዩ መሆን ብዙን እንድናውቅ ብዙን እንድናይ የሚጠቅመን ሲሆን ሳያውቁ እንዳወቁ ሳያው እንዳዩ መሆን ደግሞ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ፡፡

አሥግቶኛልና የአፊያችን ነገር፣ እስኪ ስለፈውሱ  ትንሽ እንማከር፣ አንች ውዷ ጓደ እደት ነሽ ጤናሽን፣ ከሳምንቱ ዛሬ  ንገሪኝ ለውጥሽን፣ እኔሥ እደዛውነኝ አፊያው እደራቀኝ፣ ውስጤ እደተከፋ ደሥታ እደናፈቀኝ፣ እንማከር ብዬ መጣሁኝ ቢጨቀኝ፣ ሰላምን ፈልጌ ቢለቅሽ ቢለቀኝ፣ መፍትሄ እንፈልግ  ይብቃና ዝምታው፣ እህቴ አንዘንጋ ከባድ ነው በሽታው፣ ታይ ብለው መክረውኝ ከልክለውኝ ልተው፣ ዛሬ እያልኩ ነገ ስቀጥር ቆይቸ፣ አሁን በነን ስል ከጛፍላ ነቅቸ፣ ልቤ ርቆ ሂዷል አላገኘሁትም፣ መመለሥ አልቻልኩም አላወኩበትም፣ ምን ይሆን መፍትሄው እንፈልግ መላ፣ ነፍሳችን ደርቃለች ሁናለች ተላላ ፣ ጎዳናውን ለቃ  ዙራለች በሌላ፣ ዟሂሯን አስውባ ለሠው ደህና መሥላ፣ በወንጀል እስር ቤት ተጠፍራ ነፍሴ፣ ስለውጭ ውበቴ ስለ አለባበሴ፣ ስጨነቅ ገረመኝ አጀብ ሞኝነቴ፣ አሁን በዚህ ሀሌ ቢመጣብኝ ሞቴ፣ ምን አስቀድመሻል ብሎ ሲጠይቀኝ፣ ምን ልመልስ ይሆን ወላሂ ጨነቀኝ፣ እገዥኝ ውዷዬ በዱንያ ላይ ዛሬ፣ ልዳን ከበሽታው ለስበቡ ጥሬ፣ ለአለም ጠቢቦች ባማክር ዘርዝሬ፣ የህመሜን  ጉዳይ ሁሉን ተናገሬ፣ አላገኝም ፈውሱን የትም ቦታ ዙሬ፣ በሽታው ልቤን ነው ስበቡ መእሲያ: እደተረዳሁት  ከቀራሁት ዓያ: የመውጫውን ነገር ከሱ መዳኒያችን፣ እስኪ እንመካከር ምን ይሆን ፈውሳችን፣ ✍

ከሙሽራው ቤት ምሳችንን በላንና የተወሰነ መመካከር አስበን አንድ ሁለት እየተባባልን ነው https://t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED?livestream=72c3296e0a772b1a22

​ረሱል (ﷺ) ከሳሪ ማለት ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን? አሉ። ሰሃቦችም "ከሳሪ ማለት እኮ ገንዘብና ንብረት የሌለው ነው አሉ። ረሱልም (ﷺ) እንዲህ አሉ፦ "ከኡመቴ እውነተኛው ከሳሪ ማለት በቂያማ ቀን በሶላት፣ በጾምና በዘካት (በብዙ መልካም ስራ) መጥቶ፣ ነገር ግን ይህንን ሰድቦ፣ ይህንን አምቶ (ስሙን አጥፍቶ)፣ የዚህን ገንዘብ በልቶ፣ የዚህን ደም አፍስሶ የሚመጣው ሰው ነው። ከዚያም ለመልካም ስራው (ለተበደሉት ሰዎች) ይሰጣቸዋል። በእሱ ላይ ያለባትን እዳ ሳይከፍል መልካም ስራው ካለቀቀ፣ "ከተበዳዮቹ ወንጀል" ተወስዶ በእሱ ላይ (ይጫናል)፤ ከዚያም ወደ ወደ ጀሀነም ይጣላል። ሶሂህ ሙስሊም (2581)