es
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

Ir al canal en Telegram

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
1 383
Suscriptores
+624 horas
+3437 días
+63530 días
Archivo de publicaciones
🔖የሒጃብና የኒቃብ ግዴታነትና አንገብጋቢነት ክፍል - 01 (አንድ) 🎙በአቡ ሒበቲላህ ሑሰይን t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

🌴ዑመር ኢብኑ ዐብዱል አዚዝ - አሏህ ይዘንላቸውና - እንዲህ አሉ፡- 📚 ↪️በዱንያ ላይ ወንድም ለውንድሙ አዛኝ- ቸር የሆነ የለም በቂያማ ቀን አሏህ ሊያዝንለት ቢሆን እንጂ። 📚روضة العقل
🌴ዑመር ኢብኑ ዐብዱል አዚዝ - አሏህ ይዘንላቸውና - እንዲህ አሉ፡- 📚 ↪️በዱንያ  ላይ ወንድም ለውንድሙ አዛኝ- ቸር የሆነ የለም በቂያማ ቀን አሏህ ሊያዝንለት ቢሆን እንጂ። 📚روضة العقلاء (صـ١٦٧) 📚↪️ አስታውሊ ውዷ እህቴ እዝነትሽንለምቶቻቼው ሰወች ለምትቀርቢያቸው ጓደኞቸ ለምትያቸው ሰወች ብቻ የተገደበ አታርጊው ይልቁንም ለሁሉም ሰው አዛኚና ረቂቅ ገራገር ለዛባ ሁኚ ለጥላቶችሽ ራሱ ችግርና በደል ላደረሱብሽ ሁሉ ጨካኛና ክፉ ቂመኛ 📚↪️ ከመሆን ይልቅ ለአሏህ ስትይ ይቅር በማለት አጂርሽን ከአሏህ በመተሳሰብ ማለፍን ልመጂ እራስሽን ግን ለችግርና ላደጋ አታጋልጭ ይቅር ማለትን አብዢ አሏህ ካች ይቅር እድልልሽ የምፈልጊ ከሆነ አሏህ እድወድሽ ከፈለግሽ አስታውሽ ያአሏህን ንግግር እንዲህ የሚለውን إنَّ الله يحب التَّوابين) 📚↪️አሏህ ይቅር ባይወችን ተውበተኞችንኮ ይወዳልና።በሌላ አያ ላይ እንዲህ የሚለውን ንግግሩን አስታውሽ وعف وسفح📚 📚↪️ይቅር በሉ አይታችሁ እዳላያችሁ ሰወች መጥፎን ነገር ሲናገሯችሁ አይታችሁ እዳላያችሁ ሁናችሁ አለፉ ይለናል።ይሄ ሲባል ግን መጥፎ 📚↪️ነገር ሸሪአ ያልፈቀደው ነገር ትንሽም ሆነ ትልቅ ነገር ሲሰራ እያዬሽ እለፊ ለማለት አይደለም የተፈለገው።ከልክይ ከናተ መጥፎ ነገርን ያዬ ይከልክል የሚለውን ሀድስ አስታውሽ። https://whatsapp.com/channel/0029VbC9hpU35fLpQT4nLF1h

🛜ሁለተኛው ፕሮግራማችን ▶️ 🎤በአማኞች መካከል መተዛዘን       ተ🎁              ጀ▶️                   መ ▶️                           ረ▶️ ➡️አቡ ፋሩቅ ኑረድን ✅ ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም! ‼  ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘ t.me/tdarna_islam?livestream t.me/tdarna_islam?livestream

Repost from N/a
+3
🔖ርዕስ የሂጃብ አንገብጋቢነት 🎙በኡስታዝ አቡ ሂበቲሊህ https://t.me/abuhureyrahmedresa

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️ 🛜የመጀመሪያው ፕሮግራማችን ▶️ 🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁 🎤ስለ ሒጃብ   ግዴታነት       ተ🎁              ጀ▶️                   መ ▶️                           ረ▶️ ➡️አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ✅ ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም! ‼  ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘ t.me/tdarna_islam?livestream t.me/tdarna_islam?livestream

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ​"ሶስት (ሴት ልጆች) ኖሩት፣ በትዕግስት አሳድጎ፣ አብልቶ፣ አጠጥቶና አልብሶ (ለቁም ነገር) ያበቃ ሰው፣ በቂያማህ ቀን (ከእሳት መጋረጃ) ይሆኑታል። ሱነን ኢብን ማጃህ (3669)

እህቴ_ሆይ ↬ፊተናዎች በሚሰራጭበት ፈትና በበዛበት ዘመን ልብሽን ጠብቂ!! ↬በዚህ ዘመን ከማንኛውም ሹቡሀት ለመራቅ ሞክሪ!! ↬ከማንኛውም ሙከር ማዕስያ ነገር እራቂ ሀራም ከሆኑ ነገሮች እራስሽን ልታ
እህቴ_ሆይ ↬ፊተናዎች በሚሰራጭበት ፈትና  በበዛበት ዘመን  ልብሽን ጠብቂ!! ↬በዚህ ዘመን  ከማንኛውም   ሹቡሀት  ለመራቅ ሞክሪ!! ↬ከማንኛውም  ሙከር ማዕስያ ነገር  እራቂ  ሀራም ከሆኑ ነገሮች እራስሽን ልታርቂ ይገባል!! «በዚህ ዘመን ከተበላሹት እህቶች  አንዷ እንዳትሆኝ ተጠንቀቂ» ↬ጥንቁቅ  እና  ጥብቅ  ነፍስያዋን  አላህ  ከሚጠላው  ነገር  ሁሉ እራሷን  ያራቀች_ ልቦን ሁሌም  ወደ  አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ያስጠጋች አንስት ሁኚ!! ↬ሷሊህ  የሆኑ ጎደኞችን  ፈልጊ  ከነሱጋም ተቀማመጭ!! ↬ከአላህ እርዳታን ጠይቂ በሀቅ መንገድ ላይ እንድያፀናሽ። ↬እህቴ ጀግና አንስት ሁኝ   ይህን ስልሽ በተግባር እንጅ በወሬ አይደለም!! ↬ስሚኝ እህቴ ከወሬ ምንም አታገኝም  እልቅ ቁጥብ ሁኝ ውድ ትሆኛለሽ እና!!

Repost from N/a
🔖"ርዕስ" የመልካም ሚስት መገለጫ 🎙በኡስታዝ ሙሐመድ አያሌው https://t.me/abuhureyrahmedresa

ወንድ ልጅ ነብስ ሲያቅ ሲበስል ዲኑ ሲገባው ከሴትጋር  ያለውን ጋጋታ ያቆማል

ከመልክ ይልቅ መልካምነት ልዩ ውበት አለው። ​መልክ ዓይንን ይስባል፤ መልካምነት ግን ልብን ያሸንፋል። መልክ በጊዜ ሊቀየር ይችላል፤ መልካም ልብ ግን ሁል ጊዜ ውብ ነው። ​ሰዎች ፊትህን ለእፍታ ሊያ
ከመልክ ይልቅ መልካምነት ልዩ ውበት አለው። ​መልክ ዓይንን ይስባል፤ መልካምነት ግን ልብን ያሸንፋል። መልክ በጊዜ ሊቀየር ይችላል፤ መልካም ልብ ግን ሁል ጊዜ ውብ ነው። ​ሰዎች ፊትህን ለእፍታ ሊያስታውሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ያሳየሃቸውን ፍቅር፣ ክብር፣ ርኅራኄ እና መልካምነት ለረዥም ጊዜ ከልባቸው አይጠፋም። ​ውበትን በመልክ ብቻ አትለካ፤ ሰዎች የሚያስታውሱህ በፊትህ ሳይሆን በልብህ ነው። ምክንያቱም ከመልክ የሚበልጥ ውበት መልካምነት ነውና።

•አጥንቶችን ከበሰበሱ፣ጅማቶች ከደረቁ፣ መሬት ክው ብላ ከደረቀች በኋላ ነፍስ ዘርተህባቸው ሕያው የምታደርግ አምላክ ሆይ! በኢማናችን ላይም ነፍስ ዝራ!ያ ረብ! *አሚንንንያረብ*
•አጥንቶችን ከበሰበሱ፣ጅማቶች ከደረቁ፣ መሬት ክው ብላ ከደረቀች በኋላ ነፍስ ዘርተህባቸው ሕያው የምታደርግ አምላክ ሆይ! በኢማናችን ላይም ነፍስ ዝራ!ያ ረብ! *አሚንንንያረብ*

+1
የሰዎች ዕዳ ላስጨነቃችሁ፣ እንቅልፍ ለነሳችሁ ሁሉ መፍተሔ! ወንድም አቡ ሱፍያን t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

⚠️ይድረስ በላይቭ የደዕዋ ፕሮግራም ለምታዘጋጁ ወንድምና እህቶች⁉️ ውድ የደዕዋ ፕሮግራም አዘጋጅ ወንድምና እህቶች ሆይ! አላህ በዘመናችን የሰጠን የቴክኖሎጂ በረካ ዳዕዋው በየቤቱ እንዲገባ ትልቅ በር ከፍቶልናል። በተለያዩ አጋጣሚዎች (በኒካህ፣ በምረቃ፣ በሽኝትና መሰል ፕሮግራሞች) ላይ ታላላቅ መሻይኾችንና ኡስታዞችን እንዲሁም ወንድሞችን በመጋበዝ የዒልም ድግስ ማዘጋጀታችሁ እጅግ የሚደነቅና አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ ተግባር ነው። ነገር ግን ይህ የተቀደሰ ተግባር ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆንና ለኡማው ትልቅ ፋይዳ እንዲኖረው፣ ሁላችንም ልብ ልንላቸው የሚገቡ እጅግ ወሳኝ ነጥቦች አሉ። ማወቅ ያለብን በዚህ ስራችን ላይ የሚታየው አንድ ትልቅ ስህተት የደዕዋውን ተደራሽነት እየገደለና የኡስታዞችን ጊዜ እያባከነ ይገኛል። ⚠️የታላላቅ መሻይኾችንና የኡስታዞችን እውቀት እንዲህ በዋዛ አታባክኑ! አንድን ታላቅ ዓሊም ወይም ኡስታዝ ጋብዞ፣ እሳቸው ደክመውና ተዘጋጅተው የሚያስተላልፉት ዕንቁ የሆነ እውቀት በ2ሺ በ3ሺ በ4/5 ሺ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ በማዘጋጀታችሁ ምክናያት በ30 እና በ40 ሰው ብቻ ተወስኖ እንዲቀር እያደረጋችሁ ነው። 300 እና 400 ሰው ከዛም በላይ በሚሳተፍበት፣ ከ10 ሺህ ከ20 ሺ ከ30ሺ በላይ ተከታይ ባላቸው ትላልቅ የሰለፊያ ቻናሎች ላይ ፕሮግራሙን ማስተላለፍ እየተቻለ፤ ተደራሽነታቸው በጣም አነስተኛ በሆኑ ቻናሎች ላይ ፕሮግራሙን መገደብ "ደዕዋውን በጭሩ ማስቀረት" ነው። ለምንድነው ትላልቅ ቻናል ያላቸውን ወንድሞች የማታማክሩት? ለምንድነው እንዲተባበሯችሁ የማትጠይቁትና? በነሱ ቻናል ላይ አዘጋጅታችሁ ደዕዋው በሰፊው ተደራሽ እንዲሆን የማናደርገው!!? ⚠️ አደራ በደዕዋ ስም የቻናል ቁጥር ለማሳደግ አትሞክሩ! ይህ እጅግ አደገኛና ኒያን የሚያበላሽ ተግባር ነው። አላማችሁ የሰለፊያ ደዕዋ ለኡማው እንዲደርስ ሳይሆን፣ በደዕዋው ሰበብ የራሳችሁን ቻናል ተከታይ ለመጨመር ከሆነ እወቁ... በዲን እየነገዳችሁ ነው። ኡስታዞች ተጋብዘው የሚቀሩት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው። ጊዜያቸውን ሰጥተው፣ ጉሮሮአቸው እስኪደርቅ ተናግረው መጨረሻ ላይ ውጤቱ ዜሮ ሲሆንና ደዕዋው ለሚገባው ሕዝብ ሳይደርስ ሲቀር፤ ለቀጣይ ፕሮግራሞች ያላቸው መነሳሳት ሞራል ይሞታል።ይሄን ጉዳይ በደንብ ልናስብበት ይገባል። ⚠️ የኡለሞች እውቀትና ጊዜ አማና ነው! የመሻይኾቻችን እውቀት የኡማው ሀብት እንጂ የእናንተ የቻናል ማሳደጊያ መሣሪያ አይደለም። "ይህ የኔ ቻናል ነው፣ እኔ ነኝ ያዘጋጀሁት" የሚለው የ"እኔነት" በሽታና ስስት ከውስጣችሁ ይውጣ። እውነተኛ የሰለፊያ ደዕዋ አገልጋይ ማለት ራሱን ደብቆ ደዕዋው ግን ዳር እስከ ዳር እንዲደርስ የሚተጋው ነው። ደዕዋው ተደራሽነቱ ሰፊ በሆነበት ቦታ እንዲተላለፍ በማድረግ ለኡማው እዘኑ። ⚠️ ከዚህ በኋላ ማንኛውንም የደዕዋ ፕሮግራም ስታዘጋጁ፣ አላማችሁ ለጥቂት ሰዎች ጆሮ ሳይሆን ለሰፊው ኡማ ይሁን። ትላልቅ ቻናል ያላቸውን ወንድሞች "እባካችሁ ደዕዋው ለብዙ ሰው እንዲደርስ በዚህ ቻናል ይተላለፍ" ብላችሁ ጠይቁ፤ ተባበሩ። ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የመሻይኾችንና የኡስታዞችን ጊዜ አታባክኑ። ደዕዋው የአላህ ነው፤ በረካው የሚመጣው ደግሞ በኒያ ጥራትና በመተባበር (በተዓዉን) ብቻ ነው። ⚠️ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተመሳሳይ ሰአትና ቀን በተለያዩ ቻናሎች ላይም ፕሮግራም ለምታዘጋጁ ሁለት ሶስት ፕሮግራሞችን በአንድ ላይ ለማድረግ ሞክሩ ተመካከሩ የሶስት የአራት የኒካህ የሽኝት ፕሮግራም አንድ ላይ በአንድ ቻናል ቢዘጋጅ ሳንከፋፈል በአንድነት በተወሰኑ መሻይኾችና ኡስታዞች ደምቀን ስናመሽ በጣም ደስ የሚልና የማይሰለች ፕሮግራም ይሆናል ። ሁላችን በየቦታው ላይቭ የምንከፍት ከሆነ ግን ብትንትን ብለን ደዕዋውም በሰፊው ሳይደርስ ይቀራል። ⚠️ይሄንን መልዕክት በመልካም እንዲትረዱት አደራ እላለሁ ።⁉️ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

 ibnu munewr ዛሬ ቲክቶክ ላይ የተደረገ ➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️ ➧ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ምን መምሰል አለበት? ➧ እዉን ጊዜአችንን በአግባቡ ተጠቅመንበታልን? አዳምጡ🎧🎧 ◍ ኡስታዝ ibnu munewor🎙🎧

ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️ ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት / ሀሰት ቁርዓን በየትኛው ቀን ላይ ነው መውረድ የጀመረው ?

➧የጀነት ሰወች አላህን የሚያዩበት እለት !! ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➲የአላህ መልዕክተኛ ሙሀመድ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦ የጀነት ሰወች ጀነት ከገቡ ቡሀላ አላህ ለእነርሱ እንዲህ
➧የጀነት ሰወች አላህን የሚያዩበት እለት !! ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➲የአላህ መልዕክተኛ ሙሀመድ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦ የጀነት ሰወች ጀነት ከገቡ ቡሀላ አላህ ለእነርሱ እንዲህ ይላቸዋል።"እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ ! ከሰጠኋችሁ ፀጋወች በላይ ሌላ ተጨማሪ ፀጋ እንድለግሳችሁ ትፈልጋላችሁን? ይላቸዋል።ከዛም እነርሱ እንዲህ ይላሉ "እንዴ ጌታችን ፊታችንን አላበራህልንም? እንዲሁም ጀነትን አላስገባህንም? እንዲሁም ከጀሀነም እሳት ነፃ አላወጣህንም? ይህ ሁሉ አይበቃንም? ይላሉ ፡ከዛም አላህ በእርሱና በነርሱ መሀል ያለውን ግርዶሽ ይገልጠዋል!ከዛም አላህን ይመለከቱታል ! በአላህ ስም እምላለሁ ከተሰጡት ፀጋ ሁሉ እርሱን እንደመመልከት የመሰለ ትልቅና ተወዳጅ ስጦታ አልተሰጡም ። 📝ምንጭ፦ ሶሒሁ ሙስሊም

ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ እና ልጆችህ አስጠሉህ??? እህቴ ሆይ! ባልሽ እና ልጆችሽ አስጠሉሽ??? ልጆች ሆይ! አባት እና እናቶቻችሁ አስጠሏችሁ??? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞች መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ቀጥታ ወደ ነጥቡ እንግባ፡፡ 1) ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ እና ልጆችህ አስጠሉህ??? ምን ነክቶህ ነው ወንድሜ ስንት ሽማግሌ አስልከህ ያገባሃትን፤ የአላህ ቃል ኹጥበቱል ሃጃ የተቀራበትን ሰለዋት ተወርዶ ‹‹ብልቷ›› የተፈቀደልህን ሚስት፤ ብሎም ከሷ ያገኘሃቸውን ምርጥ ልጆች አስጠልተውህ፤ ሰልችተውህ ነው፤ ከነሱ ጋር መጫወቱን ትተህ - ኳስ - ጫት - ፊልም - ከረንቡላ - ፑል - ዜና፤ ታላቅ ፊልም፤ ፖለቲካ እና የመሳሰለውን እያልክ እነሱን ዞር ብለህ እንኳን የማታያቸው፡፡ አረ መጀመሪያ ጀመዐ ሰላት ትተህ፤ ፊልም፤ ዜና፤ ኳስ ላይ አምሽተህ ፈጅር ሰላትን እያሳለፍክ፤ ለሚስትህ እና ለልጆችህ ክብር ትሰጣለህ ተብሎ አይገመትም፡፡ ጌታውን ማውሳት የሰለቸው እና ቀልቡ የደረቀ ብቻ ነው አላህነ ከማውሳት ይልቅ በእንደዚህ አይነት ነገር እራሱን የሚወጥረው፡፡ ልጆች እኮ ሊሳሙ፤ ዲናቸውን ልናስተምራቸው፤ በፍቅር አይን ልናያቸው እንጂ የወለድናቸው፡፡ እነሱን ላለማጫወት እና ከነሱ ጋር ግዜን ላለማሳለፍ ‹‹የአእምሮ ጭንቀት›› እንዳለበት ሰው ካርቶን ፊልም እና ሌላን እያዩ መሳቅ የእብደት ምልክት ይመስላል፡፡ አደለም በእንደዚህ ባለ የማይረባ ነገር፤ አላህን በመገዛት ላይ እንኳን ቢሆን፤ ለቤተሰቦቻችን ግዜ እንድንሰጥ ኢስላም ያስተምራል ‹‹ለነፍስህም ሃቅ አላት፤ ለሚስትህመ ሃቅ አላት፤ …..›› ታድያ ይህንን ታላቅ መርሆ የት እረስተን ነው፤ ሚስት እና ልጆች ያስጠሉት ይመስል፤ ቤቱ ይገባል ጨዋታው ከጌም፤ ከቲሌቭዥን፤ ከኳስ ጋር የሆነ ስንት ሰው ሞልቷል፡፡ እንጠንቀቅ 2) እህቴ ሆይ! ባልሽ እና ልጆችሽ አስጠሉሽ??? - ሙሰልሰል - ሰው ለሰው - MBC እና የመሳሰለውን እያልሽ ባልሽ እና ልጆችሽን የረሳሽዋስ ምን ነው እባክሽ??? ኢስላም ካንቺ ይሄን ነው የሚጠብቀው??? ባልሽ ሚስቴ ብሎ ይጠራሻል፤ አንቼ ሙሰልሰል ላይ ያለው ወንድ ላይ ስታፈጪ ታመሻለሽ፡፡ የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ወንድም ሴትን አይመልከት ሴትም ወንድን አትመልከት›› ታድያ አንቺ ሙሰልሰል ላይ ያለ እንደ ሴት ‹‹ሜክ አፕ›› የሚቀባ ወንድን ስታፈጪበት ታመሻለሽ፡፡ ልብሽ ይደርቃል፡፡ መቼም ኢትዬጵያው ባል አላህ ሲፈጥረው ጠይም፤ ጠቆር ያለ፤ አንዳንድ ቀይ አድርጎ ነው የፈጠረው፤ አንቺ ፊልም ላይ ያለን ‹‹ሜክ አፕ›› የሚቀባ ወንድ ስታይ እያመሸሽ ልብሽ ተሸርሽሯል፡፡ ታድያ ለባልሽ ትክክለኛ ፍቅር መስጠት ያቃተሸ በዚህ አይመስልሽም??? እስቲ ፊልም ላይ የምታሳልፊውን 10/100 አላህን በመገዛት ላይ ታሳልፊዋለሽ????????????????????? ጥያቄውን ላንቺው ልተወው፡፡ እንዳትረሺ የሰው ልጅ ለአላማ ብቻ ነው ወደዚህ አለም የመጣው፡፡ ለሰራውም ይጠየቃል፤ ላጠፋውም ጊዜ እና ወጣትነት ይጠየቃል፡፡ መልስ አዘጋጅተሻል???????????? ልጆችሽ እማዬ ብለው ቢጠሩሽም አትሰሚም፤ ብተሰሚም ወደ ውድ ልጆችሽ መሄድ እና እነሱን ማስተናገድ ዲናቸውን ማስተማር ከብዶሻል፡፡ አረ ተይ አላህን ፍሪ፡፡ ትጠየቂባቸዋለሽ፤ መልስ አዘጋጅተሻል??? አንቺ እንዲ እየራቅሻቸው ይወዱኛል በለሽ ትገምቻለሽ??? እወቂ ዛሬ ባደረግሺላቸው ቅርርብ እና ግንኙነት ነው ፍቅር የሚዳብረው፡፡ 3) ልጆች ሆይ! አባት እና እናቶቻችሁ አስጠሏችሁ??? አባት እና እናት በዘመናቸው ልጅ ሲወልዱ ስንት ነበር ያሉት ‹‹ሙሃመድ አድጎልኝ እሱን ድሬ የልጅ ልጅ አይቼ….››፤ ‹‹ሙኒራ አድጋ አግብታ፤ ወልዳ፤ ከነ ልጆቿ እየመጣች ትጠይቀናለች›› ብለው ተመኝተው ነበር፡፡ ዛሬ አላህ ካዘነላቸው ውጭ አደለም ከእናት ከአባቱ ጋር አብሮ መንገድ ላይ ሊታይ፤ ሊያዋራቸው፤ እነሱ ሊያዋሩት እየፈለጉት እሱ/ እሷ ወይ ፌስቡክ ቻት ወይንም ፊልም እና የመሳሰሉት ላይ ናቸው፡፡ እስቲ ከዚህ ከአርቲፊሻል የማሽን (ቲቪ፤ ዲሽ፤ ጌም…እና የመሳሰሉት) ወጣ ብለን እውነተኛ ህይወትን እንደ ኢስላም እንኑር፡፡ ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ እና ልጆችህ ጋር ተጫወት ፈታ በል፤ ከማሽን ጋር ያለህን ህይወት ቀንሰው፤ ካርቶን እና ሌላ ፊልም እያየህ እራስህን አታታል፤ አንተ ሰው ነህ ከሰዎች ጋር ተጫወት፡፡ ከሚስትህ፤ ከልጆችህ እና ከወላጆችህ ጋር፡፡ ካርቶን ፊልም የጤነኝነት ምልክት አይመስልም፡፡ ሰውን ለሰው ነው የፈጠረው፡፡ እህቴ ሆይ! ፍቅር ማለት ኢስላም ያሳየው፤ ለሰው ልጆች የደነገገው፤ አላህን መፍራት የተሞላበት እንጂ ፊልም ላይ ያለ ‹‹fiction›› አይደለም፡፡ ስለዚህ አጅነቢ ወንድ ላይ ተተክለሽ አምሽተሸ ነገ ሞት ቢመጣ ‹‹አሽሃዱ አላ ኢላሃኢለላህ ወአነ ሙሃመደን ረሱሉላህ›› የሚለው እንዲህ በቀላሉ ይመጣል ብለሽ ትገምቻለሽ????????? አላህ ሆይ! የመጀመሪያው ተውልድ ሰሃባዎች እንዳመኑት እንድናምን ሃቁን ምራን፤ እውቀትን ጨምርልን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Repost from Abu Hayder Aliy
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 ኢንሻአላህ ዛሬ ሳምንታዊ የሴቶችን ሙሃደራ/ የደዕዋ ፕሮግራም ለመከታተል የሚመቸዉ ካለ 11:00_11:40 ድረስ ከታች ባለዉ ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ :  ባረከላሁ ፊኩም 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy