🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
Ir al canal en Telegram
Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
1 377
Suscriptores
-124 horas
+3337 días
+63630 días
Archivo de publicaciones
Repost from Abdur-Razzaq|Al-Habeshi
🎯በዒድ ቀን መታረም ያለባቸው ተግባሮች❗️
1. የሜካፕ ማዕበል እና የ"Face ID" ፈተና (ተበሩጅ)
በዒድ ጠዋት አንዳንድ እህቶቻችን ፊታቸው ላይ የሚቀቡት የሜካፕ ብዛት የራሳቸው ስልክ እንኳን በ"Face ID" ሊያውቃቸው እስኪቸገር ድረስ ነው። ከንፈር ደም መስሎ፣ ቅንድብ እንደ ቀስተ ደመና ተስሎ ወደ መስገጃው ሜዳ ሲወጣ፣ የዒድ ሶላት ቦታ የሜክአፕ ውድድር ይመስላል።
ማስረጃው ምን ይላል? እስልምና ሴት ልጅ ለባሏ እና እቤቷ ውስጥ እንድታምር ያበረታታል፤ ነገር ግን ውበቷን አደባባይ ላይ ለባዳ ወንዶች ማሳየት (ተበሩጅ) በጥብቅ ይከለክላል። አላህ በሱረቱል አህዛብ (33:33) ላይ እንዲህ ይላል፡- "በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፤ እንደ ፊተኛው (የአለማወቅ) ዘመን ጌጣችሁንም አትግለጡ..."
2. "ሲኪኒ" አባያ እና የሒጃብ ትርጉም "ሒጃብ ለብሻለሁ" ለማለት ብቻ ፀጉርን ሸፍኖ፣ ነገር ግን ቀሪውን የሰውነት አካል "እኔን እዩኝ" በሚል ጠባብ ልብስ ማጣበቅ የተለመደ ሆኗል። አባያው ከጠባቡ የተነሳ ለመራመድም ሆነ ሱጁድ ለማድረግ ጂምናስቲክ መስራት ይጠይቃል። ሌላው ደግሞ ቀሚሱ ረጅም ሆኖ ከስር በኩል ግን እስከ ጉልበት ተቀዶ የውስጥ ሱሪን የሚያሳይ የ"ዘመናዊ" አባያ ስታይል ነው። ማስረጃው ምን ይላል? ትክክለኛ ሂጃብ ማለት ፀጉርን መሸፈን ብቻ ሳይሆን፡ ሰፊ የሆነ (አካልን የማይገልፅ)፣ የማያሳጭ፣ ጌጠኛ ያልሆነና የካፊሮችን ልብስ የማይመስል መሆን አለበት። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ መጨረሻው ዘመን ሲናገሩ፡- "ለብሰው ያለበሱ (ልብሱ ጠባብ ወይም አሳጭ ከመሆኑ የተነሳ ገላቸውን የሚያሳይ)፣ የሚያማልሉና የተዘነበሉ ሴቶች... ጀነት አይገቡም፣ ጠረኗንም አያገኙም" ብለዋል (ሙስሊም ዘግበውታል)። 3. የሽቶ "GPS" እና የተንቀሳቃሽ እጣን ሱቅ አንዳንድ እህታችን ተቀብታው የምትወጣው ሽቶ፣ መንገዱን በሙሉ አውዳው፣ እሷ አልፋ ከሄደች ከግማሽ ሰዓት በኋላ እንኳን "እከሊት በዚህ አልፋለች" ብሎ ለመናገር ያስችላል። መዓዛው አፍንጫን ሰንጥቆ የሰዎችን ትኩረት በግድ ይስባል። ማስረጃው ምን ይላል? ከላይ እንደተጠቀሰው ይህ ድርጊት በሸሪዓው እጅግ ከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶበታል። "ማንኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ (መዓዛዋን እንዲያሸቱት አስባ) በወንዶች ስብስብ አጠገብ ካለፈች እርሷ አመንዝራ (ዝሙተኛ) ናት።" (አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ)
4. እንደ ጤፍ መቀላቀል (ኢኽቲላጥ) እና የፎቶ ግርግር ሶላት እንዳለቀ ዒድ ዒድ የሚሸተው ፆታን ሳይለዩ እንደ ሰርዲን ታሽጎ ፎቶ በመነሳት ይመስል፣ ወንዱና ሴቱ ትከሻ ለትከሻ ይላፋል። "የአጎቴ ልጅ ነው፣ የሰፈሬ ልጅ ነው፣ አብሮ አደጌ ነው" በሚል ሰበብ ከባዳ (አጅነቢ) ወንዶች ጋር መተቃቀፍና መተራመስ የዘመኑ የዒድ "ፋሽን" ሆኗል። ማስረጃው ምን ይላል? አጅነቢ (ሊያገቧቸው የሚፈቀዱ) ወንዶችን መጨበጥም ሆነ መነካካት ክልክል ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "ከእናንተ አንዳችሁ (የማትፈቀድለትን) ሴት ከሚነካ፣ ጭንቅላቱ ላይ በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል።" (ጦበራኒ ዘግበውታል)።
5. የቲክቶክ ሱስና የዒድ ተክቢራ ድሮ ዒድ ሲመጣ ተክቢራ በማድረግ አላህን በማላቅ ነበር ጊዜው የሚያልፈው። አሁን ግን ሶላቱ ቦታ ላይ እንኳን ሳይቀር በጀርባ ተክቢራ እየተባለ፣ ከፊት ለፊት ለቲክቶክ እና ለስናፕቻት ዳንስ እና የተንሻፈፈ የከንፈር ፖዝ ይሰጣል። ዒዱ ዒባዳ (አምልኮ) መሆኑ ቀርቶ የላይክ እና የቪው (View) ማግኛ ፕሮጀክት ሆኗል። ማስረጃው ምን ይላል? እስልምና "ሐያእ" (አይነ አፋርነት/ክብርን መጠበቅ) የኢማን (የእምነት) አንዱ አካል መሆኑን ያስተምራል። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) "እያንዳንዱ ሃይማኖት የራሱ የሆነ መለያ አለው፤ የእስልምና መለያ ደግሞ ሐያእ (አይነ-አፋርነት) ነው" ብለዋል (ኢብኑ ማጃህ)። ቪዲዮ እየቀረፁ ራስን ለባዳ ወንዶች ማጋለጥ የዚህን ሐያእ ተቃራኒ ነው። 6. የዓይን "ራዳር" (እይታን አለመሰብሰብ) በዒድ ቀን ሁሉም አምሮና አጊጦ ስለሚወጣ፣ ዓይን አላረፍ ይላል። "ያቺ ምን ለበሰች? የሱ ጫማ ያምራል" እያለ አይን እንደ አውሮፕላን ራዳር 360 ዲግሪ ይዞራል። በዚህ መሃል አይን ባልተፈቀዱ (አጅነቢይ) ሰዎች ላይ አፍጥጦ ይውላል። ማስረጃው ምን ይላል? አላህ በሱረቱ-ኑር ለአማኝ ወንዶችም ሆነ ሴቶች እይታቸውን ዝቅ እንዲያደርጉ (አይናቸውን ከሐራም እንዲሰብሩ) በጥብቅ አዟል (24:30-31)። እይታ የሰይጣን መርዛማ ቀስት ነች። ➖➖➖➖➖➖➖ 7. የሒል ጫማ ፈተና (High Heel) በዒድ ጠዋት፣ በተለይ የዒድ መስገጃው ሜዳ ወይም ጎድጓዳ ቦታ ሲሆን፣ አንዳንድ እህቶቻችን 15 ሳንቲ ሜትር የሚረዝም የሒል ጫማ አድርገው የሚገጥማቸው ፈተና ቀላል አይደለም። ጫማው መሬት ውስጥ ሲሰምጥ፣ ወይም እንደ አዲስ ጥጃ ሚዛን ለመጠበቅ ሲንገዳገዱ ማየት የተለመደ ነው። ከዚህም በላይ ደግሞ አስፋልት ላይ ሲራመዱ ጫማው የሚያወጣው ዜማ፣ የሰፈሩን ወንድ ሁሉ አንገት አስጠምዝዞ እንዲያይ ያደርጋል። ማስረጃው ምን ይላል? አላህ በቁርኣን ውስጥ ሴቶች እግራቸውን መሬት ላይ እያጋጩ ድምፅ በማሰማት ትኩረት እንዳይስቡ አዟል። በሱረቱ-ኑር (24:31) ላይ እንዲህ ይላል፡- "ከጌጣቸውም የሚደብቁት እንዲታወቅባቸው በእግሮቻቸው አይምቱ (አያጋጩ)..." ይህ የሚያሳየው ጌጥን (አምባርን) ለማሰማትም ሆነ ትኩረትን ለመሳብ ተብሎ በሚጮህ ጫማ መራመድ ከሸሪዓው ጋር እንደሚጋጭ ነው። በተጨማሪም ጤናን የሚጎዳና ለውድቀት የሚያጋልጥ (አደጋ ያለው) ጫማ ማድረግ እስልምና ከሚያበረታታው ራስን ከመጠበቅ መርህ ጋር ይላተማል። 8. የድምፅ ማለስለስ እና የሳቅ ማዕበል ዒድ በመጣ ቁጥር ከመንገድ ዳር፣ ከካፌዎች እና ከፓርኮች የሚሰማው የሴቶች ከፍተኛ ሳቅ እና ጫጫታ ሌላው ጉዳይ ነው። አንዳንዷ ደግሞ ሱቅ ውስጥም ሆነ መንገድ ላይ፣ ከማይገባት (አጅነቢ) ወንድ ጋር ስታወራ ድምጿን ቀይራ፣ ከወትሮው በተለየ አለስልሳና አስውባ ትናገራለች። በመንገድ ላይ የሚለቀቀው ከፍተኛ ሳቅስ ቢሆን የአካባቢውን ሰው ሁሉ ትኩረት ይስባል። ማስረጃው ምን ይላል? እስልምና የሴት ልጅ ድምፅ ሙሉ በሙሉ ሐራም ነው አይልም (ለአስፈላጊ ጉዳይ ማውራት ይቻላል)፤ ነገር ግን ድምፅን ከባዳ ወንዶች ጋር ሲያወሩ ማለስለስና ማሳመርን በጥብቅ ይከለክላል። አላህ በሱረቱል አህዛብ (33:32) ላይ ለነቢዩ ሚስቶች (እና በነሱ በኩል ለሙስሊም ሴቶች ሁሉ) እንዲህ ይላል፡- "በንግግርም አታለስልሱ፤ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት ሰው ይመኛልና። መልካምንም (የተለመደና ቀጥተኛ) ንግግር ተናገሩ..." በየመንገዱ ከፍ ባለ ድምፅ መሳቅና መጮህም ከሙስሊም ሴት ውበት ከሆነው "ሐያእ" (አይነ አፋርነትና ክብር) ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም።
እነዚህን ሁሉ ስንል ዒድን በሀዘን እናሳልፍ፣ አንደሰት ማለታችን አይደለም። እስልምና የደስታ ሃይማኖት ነው! ነገር ግን የደስታችን ልክ እና ድንበር የጌታችንን ህግ በማይጥስ መልኩ መሆን አለበት። መልካም ልብስ (ነገር ግን ሒጃብ የሆነ)፣ ጥሩ ሽቶ (ነገር ግን እቤት ውስጥና ለሴቶች ብቻ የሚረጭ)፣ ፈገግታ እና ደስታ (ነገር ግን ሐያእን የጠበቀ) መሆን ሲችል ነው የዒድ ደስታችን በረካ የሚኖረው። ✨መልካም፣ ሸሪዓውን የጠበቀና በበረካ የተሞላ ዒድ ይሁንልን!
استغفرالله العظيم واتوب اليه عدد خلقه ورضا نفسه وزنه عرشه ومداد كلماته
‧ ₊ ˚ ♡ ليبلغ تكبيركم عنان السماء
كبروا فإن الله عظيم يستحق الثناء ‧ ₊ ˚ ♡
الله أكبر لا إله إلا الله
الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
الله أكبر لا إله إلا الله
الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
باركل الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير
አልሀምዱሊላህ ይገባዉ ምስጋና
ለደስታወ ለኒካ እዚህ ደረስንና፡
ዉዱ ኡስታዝአችን እኮን ደስ አላህ፡
ከላጤነት ህይወት አላህ አወጣህ፡
በባከነ ህይወት ደርሰህ ነበር እዚህ ፡
ዉሀ አታጭህን ጌታችን ወፈቀህ፡
የዛሬ ሙሺራ አላህ አድርጎህ በል፡
አልሀምዱሊላህ ምንስ ቃል አለህ፡
ጋብቻ ሱና ነው የሙዕሚን ጎዳና፡
የፍቅር ቃል ኪዳን ማህደር ሰኪና፡
ትዳርህን ያርገው ያማረ ያበበ በነብዩ ፡
ሱና ደምቆ የተዋበ ጋብቻ ጥሩ ነው ፡
ብዙ ጥቅም አለው አዉቆ ለገባበት ፡
አላህ ለወፈቀው ከሀራም መሸሻ አይን፡
አይን መስበሪያ ነው፡በነብዩ ሱና ፡
ይድመቅ ትድርህ የሚስትህን ሀቅ
ጠባቂ ጌታችን ያድርግህ፡ዘላቂ ያድርገዉ
ሞቅ ይበል ጎጆህ ፡
አተውድ ኡስታዜ የዛሬው አበባ፡
የነገ ፍሬ ነህ ሆድህ እንዳይባባ፡
በሱና ካገባህ ይሄንን ከታደልክ፡
የነብዩን መንገድ ሀላሉን ከመረጥክ፡
እኔም መብሩክ አልኩኝ እንኳንም ደስ አለህ፡
ትዳር ሰኪናነው በደንብ ከገባህ ፡
ተግባብተህ በሀሳብ ስትኖር ተቻችለህ፡
ታዳ ከዝህ ሌላ ምንስ ውበት አለህ፡
በሀቅ ላይበርታ አይዞህ ስትልህ፡
ልጆችን በተውሂድ ስታሳድግልህ፡
ከዝህ የበለጠ ምንስ ስጦታ አለህ፡
ቤትህ ፍክት ብሎ መብራቱ ደምቆልህ፡
የሱናዋን ጀግና አላህ ወፍቆህ
ብልህ አስተዋይ ሁን ያዝ ጠበቅ አድርገህ
ዛሬ ጀምራችሁ ከዚሁ ሠአት ፡
በሃላል በኒካ በአሏህ በረከት፡
ሂወታችሁ ይመር በአላህ ራህመት፡
ሙሽራው ሙሽሪት ሰርጋቸው ነው እና
በሉ ባረከሏህ በነብዩ ሱና
አምሮ ይድመቅለት በሃላል ጎዳና
ይስመር ትዳራቸው ፍቅራቸው ይቃና
ውዷ ሙሽራችን እንዲያምርላት ቤቷ
ጎጆውም እንድሞቅ እንድሰምር ሃያቷ
መርቀን እንሸኛት ይህ ነው ፍላጎቷ
ባረከላህ እንበል ይስመር ፍላጎቷ
ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል በሱና
መዳን የሚገኘው በተውሂድ ነውና
ዘላቂ ያድርገው እስከ ዳሩል ጀና
የነብዩን ሡና ያዉ ተከተላችሁ
በዛሬዋ ምሽት እኛም አጀብናችሁ
ከብቸኛዉ አለም ወጣ ሂወታችሁ
አልሀምዱሊላሂ እንኳን ደሥ አላችሁ
ለድኑ ጠቃሚ መልካም ልጅ ይሥጣችሁ
እኛ ደሥ ብሎናል እንኳን ደሥ አላችሁ
መብሩክ ሙሽራችን እንኳንም ደስ አለሽ
ከሀራም አርቆ ለሃላሉ አበቃሽ
ከቢድዓ ኮተት የሌለው ግርግር
ተመኘሁላችሁ የሰመረ ትዳር
ሷሊሆች ውለዱ ድኑን አስከባሪ፡
የማይሾፍራቸ የሂዝብያ ጋሪ፡
በጢልን በሁጃ በጣጥሰው መንጣሪ፡
በሱና ያጌጡ የተውሂድ ተጣሪ፡
ድምቀት ለምድሪቱ አንበሳ ኮከቦች፡
ሽርክን የሚያወግዙ ተወርዋሪ ጀቶች፡
የሙብተዲዕ ጠላት ተናዴዳፊ ንቦች፡
ኩፋርን አሰደንጋጭ ለድን ተሟጋቾች፡
አሏህ ይችራችሁ ውብ ወንድና ሴቶች፡
ግርማ ሞገስ ለብሰው ጥላት አሸባሪ፡
በየደረሱበት የኢስላም ተጣሪ፡
ወሀቡ ይስጣችሁ የሴት አናብስቶች፡
በኒቃብ ያጌጡ የእውቀት እንስቶች፡
አሏህ ይችራችሁ ሪዝቅን በስፋት:
በደስታ ላይ የኑሩ አይንካችሁ ልፋት:
አልሀምዱሊላሂ ምስጋና ይድረሰው
ሀራምን ከልክሎኒካህ ለፈቀደው
ለአለማቱ ጌታ ከአርሽ በላይ ላለው
ባረከሏህብየ በጣም ልባርክልሽ
እጅግደስ ብሎኛል ኒካህ በማሠርሽ
ትዳርም መሰረትሽ ኢማንሽም ሞላ
ምን ያስደስትሻል ታዳ ከዚህ ሊላ
የኛማ ሙሽራ በጣም ተውባለች
ከጅልባቧ በላይ ኒቃብ ደርባለች
የነብዩን ሡና ሀይ አድርጋዋለች
የድነል ኢስላምን መስፈርት አሟልታለች
እናማ እህቴ አደራ ብየ እምነግርሽ
ሀቁን ጠብቂለት ለውዱ ባልሽ
ከሷሊሆች ሁኝ ለትዳርሽ ብቁ
አላህን በመፍራት ሀቁን ከሚጠብቁ
ለባል ታዛዥ መሆን ኢባዳ ነውና
ፍቅርሽን መገቢው በንፁህ ልቦና
ትልቅ ደረጃ አለው ትዳር በስልምና
ወሚን አያቲሂ ብሏል ረበና
በሚያዝሽም ሰአት መረሀባ ብለሽ
በችጉሩ ሁሉ መፍተሄ ሁነሽ
በደስታውም ግዜ አብረሽ ተደስተሽ
ሙሽራው ልንገርህ አድምጥ በጥሞና
ውዷ ባለቤትህ ስጦታህ ናትና
ተከባክበህ ያዛት ዛሬም ትላትና
የረሡል አደራ አማናህ ናትና
ከምነግርህ በላይ በስፋትብታውቅም
ሀቋን ጥብቅላት በምትችለው አቅም
እሷም ባቅምህ እጅ በብዙ አጠይቅም
ሚስትኮ ላተ ሁለ ነገርህ ናት
የፍቅርህ ምርኮኛ የተለየች ከናት
ተዛዝናችሁ ኑሩ ሁለየም ተዋዳችሁ
በኢማን አጊጡ ሞቅ ይበል ቤታችሁ
መቻቻል ነውና የትዳር ሚስጥሩ
ባድነት ፀታችሁ በፍቅራችሁ አብሩ
የደስታ የአለም ይሁን ጋብቻችሁ
ሁለይም ተዋደዱ አላህ ያዋዳችሁ
ማን አለ እደኔ ኡስታዝን የሚወድ፡
ከጅህልና አዉጥቶ ያሳየን ቅን መንገድ
እኔማ ኡስታዜን በጣም ነዉ የምወደዉ
ትናት የነበረው ሂይወቴን ቀየረዉ ፡
በጭፍን ስንጎዝ ገደል ልንገባ
ብረሀን አሳየን መራን ቅን ጎዳና
አድበተ ጣፋጭ ምክሩ ተናፊቂ
ቢድዓን አባሮ ተዉሂድ አሳዋቂ
ምርጡ ኡስታዝአችን ኑርልን ዘላለም
እደ አንተ አስተማሪ ለኛ ማንም የለም
እኔ እዚህ ላይ ላቁም አላብዛ ዛዛታ
ተዘርዝሮ አያልቅም የኡስታዝ ዉለታ
ኡስታዜ
የሱናው ተዋናይ የተውሂዱ ጀግና
ፍርሃት የማያዉቅ ለአቂዳ ቆንቋና
ከቁርአን ከሀዲስ መረጃ ሰፋሪ
የጠላትን ሴራ አድቅቆ ሰባሪ
የተውሂዱ ጀግና የሱናው አንበሳ
ያለውን የሚሰጥ ለምንም ሳይሳሳ
ዉድ ነው ጀግናዬ የሽርክ መርዘኛ
የሱናው ነበልባል የተውሂድ ዘበኛ
መና የሚያስቀረው የባጢልን ነዶ
መረጃዉን ፈርቶ ወደ ኋላ ቯዶ
የጠላትን ሴራ ያስቀራል በባዶ
بَارَكَ اللهُ لَكُمَا، وَبَارَكَ عَلَيْكُمَا، وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ. اللَّهُمَّ اجْعَلْ بَيْنَهُمَا مَوَدَّةً وَرَحْمَةً، وَارْزُقْهُمَا ذُرِّيَّةً صَالِحَةً، وَبَارِكْ لَهُمَا فِي رِزْقِهِمَا، وَاجْعَلْ حَيَاتَهُمَا سَعَادَةً وَطَاعَةً."
"أدعو الله أن يجعل حياتكما مليئة بالحب والسعادة والخير."
መብሩክ ኡስታዙና
ከተማሪህ ኡሙ ሓቲም መኪያ
https://t.me/Multeka_Selefiyin
*➤ሀላሌ ፈልጌሽ ነበረ🙌*
ፍቅሬን የሚጋራኝ ፍፁም ሰው አጥቼ
ፈልጌሽ ነበረ ከደጅሽ መጥቼ
ሰው ተርቤ ሳለሁ ሰው የሚሆንልኝሰው የምሆንለት
ሀገሩን ሰው ሞልቶ ሰው የናፈቀኝ ለት
➤ፈልጌሽ ነበረ
ሰሚ አዳማጭ ጠፍቶ ብቻዬን ሳወራ
ደስታ ሀዘኔን አጥቸ የሚጋራ
በቀልዴ የሚስቅ ስቆ የሚያሳስቅ አንድ ሰው ስጠብቅ
ፈልጌሽ ነበረ________🙌
አለ አፍቃሪው ➤ ኢላሂ _የሚፈላለጉ ልቦችን በእዝነትህ አገናኛቸው💦_
♻ታላቅ የሠርግ ድግስና የዳዕዋ
ፕሮግራም♻
የወንድም ዐጃኢቡ አቡ ዒምራን
እና
የእህት ራህመት ኡሙ ዒምራን
ታዳሚ መሻይኾችና ኡስታዞች
1/ ሸይኽ አወል አህመድ ከኬሚሴ
2/ ሸይኽ ሙሀመድ መኪን ከደሴ
3/ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢይ ከደሴ
4/ ኡስታዝ ኸድር አህመድ ከኬሚሴ
5/ ኡስታዝ አቡ ሱፍያን ከ አ/አበባ
6/ ኡስታዝ አቡ ሙስዐብ ከመርሳ
7/ ኡሰታዝ አቡ ሂበቲላህ ከአ/አበባ
8/ ኡስታዝ ኑረዲን አል_አረቢ ከሳኡዲ
9/ ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ ከኬሚሴ
10/ ኡስታዝ አብደል መሊክ ከኬሚሴ
12/ ኡስታዝ አቡ አብዲ ረህማን ከ ኮቻ
13/ ኡስታዝ አቡ ሉቅማን ከሀርቡ
14/ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ ከ ኮቻ
15/ ኡስታዝ አቡል መዓሊ ከ ኮቻ
16/ ኡስታዝ አቡ ሀኒፋ ከ ኬሚሴ
17/ ኡስታዝ አቡ አዲረዛቅ ከ ኮቻ
18/ ኡስታዝ አቡ ሀሳን ከኮቻ
19/ ኡስታዝ ሙሀመድ መኪን ከሀይቅ
20/ ኡስታዝ አቡ ጁዳና ከ ሀርቡ
🔰ፕሮግራሙ በአቡ ረያን እና
በሙሀመድ አያሌው ይመራል
ፕሮግራሙ የሚተላለፈው
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Multeka_Selefiyin
ህይወቴ ባዶ ናት፣ ትርጉም የላትም፣ እንደበረሀ ደርቃለች ብለሽ ተስፋ ልትቆርጭ ስትይ አንጀት የሚያርስ መልስ የሚሰጥሽ አሏህ አለ።
ወዳጄ የዘገየ ይመስልሻል እንጂ እሱን የሚቀድመው የለም! አንች ብቻ ታገሽ!
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
قُل🪄
يـارب ابنِ لي عندك بيتاً في الجنة
يظلهُ ظلّك وينيره وجهك وتجمعني
فيه بمن أحب يـارب ازرع في قلبي
حبّــك اشغلني بـك وحدك قربني
إليك أكثر كي لا أبكي إلا من شوقي
لنور وجهك اللهم حبّــك وعونـك
ورضــاك اللهّـم لطفــك اللهّــم
الحـــاجه وكــل الحــاجـة إليـك
Repost from ፍቅር እስከ ጀነት | ራማስ አል ሀናኒ
ይህን ያውቁ ኖሯል⁉️
🔖 ከጀነት ጓዳ
➊ ሑር ፦ የጀነት ውስጥ ምርጥ ሴቶቾ
➋ አዕራፍ ፦ በጀነት እና በጀሀነም መካከል ያለ ተራራ
➌ ፊርደውስ ፦ የጀነት የላይኛው ክፍል
➍ ረያን ፦ ጾመኞች ብቻ የሚጠሩበት የጀነት በር
➎ ሐሪር ፦ የጀነት ሰዎች ልብስ
➏ ሚስክ ፦ የጀነት ውስጥ ሽቶ
➐ ትልቁ ጸጋ ፦ በጀነት ውስጥ የአላህን ፊት ማየት
➑ ከውሰር ፦ ጀነት ውስጥ ያለ ወንዝ
➒ ድሆች ፦ አብዛኛዎቹ የጀነት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች
┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
= t.me/FKR_ESKE_JENET
🔖 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጥዎ!
ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል።
✅ ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ!
ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫኑ 👇
👉 t.me/FKR_ESKE_JENET
Repost from ስለ ቀልባችን
ክፍል--5--
📚 የኪታቡ ስም፦
❞ذَمُّ قَسْوَةِ الْقَلْب❝
(የቀልብ መድረቅ አደገኝነት፣ መንስኤውና መፍትሔው)
🎙 በኡስታዝ፦ ዐብዱ ረዛቅ አል-ባጂ (ሐፊዘሁላህ)
➡️ t.me/Sle_qelbachn1
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ብቸኝነት ደስ ይላል። ከሰው መራቅ ጤና ነው በተደጋጋሚ አይቸዋለሁ።ጓደኛም ማብዛትም ጥሩ አይደለም።
መገለል ትኩረት ለመሰብሰብ፣ አቅምን ለመሳደግ፣ ኢማንንም ለማደስ ያግዛል። አንዳንዴ ስራህ ላይ እና ዒባዳህ ላይ ብቻ ትኩረት ስታደርግ የምታሳካው ብዙ ነው።
እናማ…ብቸኝነት ሲበዛ ከሰው መቀላቀል... ከሰው መቀላቀል ሲበዛ ብቸኝነትን መምረጥ፣ በጥሩ መንፈስ ለመቆየት አንዱ የኑሮ ስልት ነው። ሞክሩት¡
