es
Feedback
هداية القلوب (የልቦች መሪ)

هداية القلوب (የልቦች መሪ)

Ir al canal en Telegram

https://t.me/httpYelbochMeriQuran

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
228
Suscriptores
-124 horas
+197 días
+1430 días
Archivo de publicaciones
እውነቱን ነው! በዚህ ዘመን ገንዘብ ስታበድሩ የመመለስ ዕድሉ ጠባብ ስለሆነ እንደ ሰደቃ አስባችሁ ስጡት።የግድ ማበደር ካስፈለገም፣ በየቀኑ በስራ ለምታገኙትና በቢዝነስ ለተሳሰራችሁት ሰው ብቻ ይሁን። ለዘመድ ወይም ለጓደኛ ማበደር ግን፣ ገንዘቡንም ሰውንም በአንድ ላይ ማጣት ሊሆን ስለሚችል፤ "በሰደቃ" ንያ አስባችሁ ስጡት። ሀቂቃ በዚህ ዘመን ማበደር ማለት በገዛ ገንዘብህ ለማኝ መሆን ማለት ነው! t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

ሞት እድሜ አይመርጥም ተዘጋጅቶ መጠበቅ ግድ ነው https://t.me/MerkezulimamiAhmed

🛡️ጥቂትም ቢሆን በጎ ስራህ ነው ለነገ ዋስትናህ! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا وَسَيُكَلِّمُهُ اللَّهُ يَوْمَ القِيَامَ
🛡️ጥቂትም ቢሆን በጎ ስራህ ነው ለነገ ዋስትናህ! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا وَسَيُكَلِّمُهُ اللَّهُ يَوْمَ القِيَامَةِ، لَيْسَ بَيْنَ اللَّهِ وَبَيْنَهُ تُرْجُمَانٌ، ثُمَّ يَنْظُرُ أَيْمنَ مِنْهُ فَلَا يَرَى إِلَّا مَا قَدَّمَ، وَيَنْظُرُ أشْأَمَ مِنْهُ فَلَا يَرَى إِلَّا مَا قَدَّمَ، وَيَنْظُرُ بَيْنَ يَدَيْهِ فَتَسْتَقْبِلُهُ النَّارُ، فَمَنِ اسْتَطَاعَ مِنْكُمْ أَنْ يَتَّقِيَ النَّارَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ﴾ “ከእናንተ መካከል በቂያማ (በትንሣኤ) ቀን አላህ በእሱና በእሱ መካከል ምንም ዓይነት አስተርጓሚ ሳይኖር የሚያነጋግረው እንጂ ማንም የለም። ከዚያም ወደ ቀኙ ይመለከታል ያስቀደመውን (መልካም) ሥራውን እንጂ ሌላ አያይም፤ ወደ ግራውም ይመለከታል ያስቀደመውን (መጥፎ) ሥራውን እንጂ ሌላ አያይም፤ ወደ ፊቱ ሲመለከትም እሳት ከፊቱ ትጠብቀዋለች። ስለዚህ ከእናንተ መካከል የቴምር (ክፋይ) እንኳን ቢሆን ሰደቃ በመስጠት እሳትን መከላከል (ከሱ መጠበቅ) የቻለ ሰው ይህንን ያድርግ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6539 ➖➖➖➖➖➖➖ 🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok

ነብዩ صلى الله عليه وسلم የተለዱበት ቀን እያሉ ማክበር አድስ ፈጠራ ወይም ቢድአ ስለመሆኑ የተደረገ ወሳኝ ሙሀደራ👂👂👂👂👂👂 በኡስታዝ አቡ አምር ኑርየ ጎቤ አሏህ ይጠብቀው 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/nuruya76

ልዩ የጁሙዓ ኹጥባ ፉርቃን መስጅድ ቢስቲማ https://t.me/sheikhmohamedhussen አቡ አስማእ

«ራስህን ፈትሽ። ወደ ዓላማህ ተመልከት። ዓላማህ ምንድነው? በዚች ህይወት አላማህ ምንድነው? ከሞትክኮ ሁለተኛ አትመለስም። ዕድልህ ካለፈ፣ ጊዜህም ካበቃ፣ መመለስ አትችልም። ተጠንቀቅ። የሚያልፍህ እያንዳንዱ ጊዜ ወደ ሞት፣ ወደ ቀብርና ወደ አኺራ እያቀረበህ ነው። ሕይወትም በእውነቱ የተቆጠሩ ሰከንዶች ብቻ ናቸው። ስለ እድሜህ ስትል አላህ ፍራ። በዋና ወረትህ (በዕድሜህ) አትቀልድ። አላህ የሁላችንም መጨረሻ እንዲያሳምርልን እማፀነዋለሁ።» = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

➡️ዱንያ ኡስማን ቢን አፋን ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላሉ፦ "አላህ ዱንያን የሰጣቹህ አኼራን ልትፈልጉበት ነው በእሷ ልትደገፉ ልትመቻቹ አደለም።!! 📖 البدايــة والنهايــة (٢٤١/٧). ⚡️سبحان الله وبحمده ⚡️سبحان الله العظيم https://whatsapp.com/channel/0029VbCISkjA2pLBBlySHC29/1025

+1
ሶለዋት ማውረድ እናብዛ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ‏ (أكثروا الصلاة عليَّ يوم الجمعة وليلة الجمع فمن صلى عليَّ صلاة صلى الله عليه عشراً) ‏ 🌺اللهم صل وسلم على نبينا محمدﷺ 🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ 🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ ፏያለችጁሙዓ ይሁንላችሁ 🌸🌸

ሱረቱ'ል ከህፍ سورة الكهف خليفة الطنيجي https://t.me/httpYelbochMeriQuran

​📢 ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም በመርከዝ ኢብኑ አባስ የቴሌግራም ግሩፕ ​የእውቀት ጥማታችሁን የሚቆርጥ፣ መንፈስን የሚያድስና ለበጎ ስራ የሚያነሳሳ ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። የሁላችሁም መ
​📢 ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም በመርከዝ ኢብኑ አባስ የቴሌግራም ግሩፕ ​የእውቀት ጥማታችሁን የሚቆርጥ፣ መንፈስን የሚያድስና ለበጎ ስራ የሚያነሳሳ ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። የሁላችሁም መገኘት ለፕሮግራሙ ድምቀት ነው። ​ቀን፦ ጁመአ ​ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ​ቦታ፦ መርከዝ ኢብኑ አባስ ​🎙️ የክብር እንግዶቻችን (ተጋባዥ ኡስታዞች) ​በዕለቱ በዕውቀታቸውና በምክራቸው የሚያንጹን ታዋቂ ኡስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ፡ ⓵ ​ሸይኽ አወል አሕመድ አልኬሚሴ ⓶ ​ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አልኬሚሴ ⓷ ​ወንድም አቡ ኡበይዳ ሰኢድ አል ኬሚሴ ⓸ ወንድም ሙሐመድ ሲራጅ አል ኬሚሴ ​የፕሮግራም መሪ፦ አቡ ዑበይዳ or ማሒ ​"ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪው አይነት ምንዳ አለውና  መልእክቱን ለሌሎች በማድረስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!" ሼር ሼር አድርጉ https://t.me/+lmLw2jJXwF45Zjdk

አንጡ ባይ እና ሞት ሁለቱ አንድ አንድ ናቸው ሁሌም ይኖራሉ ሰው እንደጠላቸው

Mensaje de voz02:28

• ዝሆን ሁለት ጥርሶቹ ጎልተው ስለሚታዩ ሌሎች ጥርሶች የሉትም ማለት አይደለም። እነዚህ ጎልተው የሚታዩት ጥርሶች ውበቱ ወይም ግርማ ሞገሱ ናቸው። ፈገግታችንን ብቻ ስለሚያዩ የማይከፋን ለሚመስላቸው፣
• ዝሆን ሁለት ጥርሶቹ ጎልተው ስለሚታዩ ሌሎች ጥርሶች የሉትም ማለት አይደለም። እነዚህ ጎልተው የሚታዩት ጥርሶች ውበቱ ወይም ግርማ ሞገሱ ናቸው። ፈገግታችንን ብቻ ስለሚያዩ የማይከፋን ለሚመስላቸው፣ ስለማንጨናነቅ ቁም ነገር የማናውቅ ለሚመስላቸው፣ መልካም ብለው ባሉት ቦታ ስለማያገኙን እርባና ቢስ ለምንመስላቸው ሰዎች አቅል ይስጥልን። ሁለት ጥርስ ብቻ  ሁሌ አትመልከቱ ሌሎች ከ20 በላይ ጥርሶች አሉ። ሳቆቻችን የሚሸሽጉትንን ለመመልከት ሰፋ በሉ። ከምናሳያችሁ የበለጠ የምናሳይበትን ምክንያት ተረዱ። ⇄ t.me/AbuSufiyan_Albenan

ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥ
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኢስላም የሃገር እና የዘር ድንበር የማይገድበው ዓለማቀፋዊ እምነት ነው። ኢስላም ከሃገር፣ ከብሄር በላይ ነው። መካ ከየትኛውም የዓለም ሃገራት በተለየ ልዩ ከተማ ነች። ይሁን እንጂ ከእምነት በላይ ስ
ኢስላም የሃገር እና የዘር ድንበር የማይገድበው ዓለማቀፋዊ እምነት ነው። ኢስላም ከሃገር፣ ከብሄር በላይ ነው። መካ ከየትኛውም የዓለም ሃገራት በተለየ ልዩ ከተማ ነች። ይሁን እንጂ ከእምነት በላይ ስላልሆነች ነው ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እትብታቸው የተቀበረባትን ልዩ ሃገር ጥለው የተሰደዱት። ኢስላም ከዘርና ከጎሳ በላይ ስለሆነም ነው ከቁረይሽ ጋር የተዋጉት፣ ከአጎታቸው አቡ ለሀብ ጋር የተፋጠጡት፣ ከሐበሻው ባሪያ ቢላል ብኑ ረባሕ ጋር በኢማን የተሳሰሩት። የማንም ብሄር ከኢስላም በላይ አይደለም። ብሄርና ጎሳ ለቀብር ጥያቄ አይሆንም፣ ሲራጥ አያሻግርም፣ ከጀሀነም አያስጥልም። ነገ ዘርና ቋንቋ ሊጠቅም ቀርቶ እናት ከልጇ፣ ወንድም ከወንድሙ፣ ባል ከሚስቱ፣ ... የሚሸሹበት ቀን ነው። የብሄርና የዘር ጉዳይ ወላእና በራእ የሚቋጠርበት ጉዳይ አይደለም። የኢማንን መለኪያ ገፍቶ ሰዎችን በዘራቸው ብቻ የሚወድና በዘራቸው ብቻ የሚጠላ ሰው እራሱን ነው ያረከሰው። ላኢላሀኢለላህን ገሸሽ አድርጎ ቋንቋ እያየ የሚሰለፍ ሰው በዘረኝነት ናላው ዞረ ሰው ነው። እንዲህ አይነት ችግር በተንሰራፋበት ዘመን እየኖረ ከዘር ልክፍት ወጥቶ መለኪያውን ላኢላሀኢለላህ ያደረገ ሰው በጣም የታደለ ነውና ደጋግሞ ጌታውን ሊያመሰግን ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የማለዳ መልእክት (43) ~ ለዒልም እንቅፋት ከሚሆኑ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ቀሪ ማብዛት ነው። ተደጋጋሚ ቀሪ፦ * የዒልምን ጣእም ያሳጣል። * ባለፈን ትምህርት እንዳንቆጭ ይልቁንም መቅረትን እንድንላመ
የማለዳ መልእክት (43) ~ ለዒልም እንቅፋት ከሚሆኑ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ቀሪ ማብዛት ነው። ተደጋጋሚ ቀሪ፦ * የዒልምን ጣእም ያሳጣል። * ባለፈን ትምህርት እንዳንቆጭ ይልቁንም መቅረትን እንድንላመድ /'ኖርማል' አድርገን እንድንወስድ/ ያደርጋል። * ከነ ጭራሹ ከዒልም ሰፈር የመራቅን በር ይከፍታል። ስለዚህ ስንፍናችን ጋር ጊዜያዊ እንኳን ቢሆን ወዳጅነት ከመመስረት እንጠንቀቅ። ልማድ ይሆናል። በጊዜ ድክመታችንን እናስተካክል። ዒልምን በመከታተል ላይ ቆራጥ እንሁን። ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ፈፅሞ ከዒልም ማእዶች ያለን ተሳትፎ አይቆራረጥ። ዛሬ ቆራጥ ከሆንን የየቀኑ የተጠራቀመች ዒልም በዓመቱ መጨረሻ ትልቅ ክምችት ይወጣታል። ጠብታ ተጠራቅሞ ብዙ ያቁራል። ጠብታ ውሃ ድንጋይ ይበሳል። ፅናት ኖሮን ጥረታችን ዓመታትን ከተሻገረ በርግጠኝነት በአላህ ፈቃድ ጉልህ ለውጥ ይኖረናል። በዚህ አብዛኛው ሰው - አስተማሪውን ጨምሮ - በስሜት፣ በቡድንተኝነት፣ በአስመሳይነት፣ በእልህ፣ በቢድዐ፣ በሞራል ዝቅጠት፣ ... በተለከፈበት ዘመን ከአላህ ጋር እንደ ዒልም ያለ ዋስትና የለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 26 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

“የቆንጆ” ቢድዐ ቁርኣናዊ “ማስረጃ” ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ በኢስላም የዒባዳ ፈጠራ የተወገዘ እንጂ የተወደሰ ምግባር አይደለም። ነብዩ ﷺ ቢድዐን በተደጋጋሚ ሲያወግዙም “ይሄ ሲቀር” ብለው ነጥለው ያስቀሩት የለም። “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ውድቅ ነው” አሉ እንጂ “በራሳችሁ መደንገግ ትችላላችሁ” አላሉም። “በዚህ (የዲን) ጉዳያችን ላይ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ እሱ ተመላሽ ነው” አሉ እንጂ “የሚያስመነዳ ቢድዐ አለ” አላሉም። “ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ”፣ “የሐጅ አፈፃፀሞቻችሁን ከኔ ውሰዱ”፣ “በኔ ላይ ለእናንተ መልካም ተምሳሌት አለ” አሉ እንጂ “አትጨናነቁ በራሳችሁም መጨመር የምትችሉት ዒባዳ አለ” አላሉም። የሶሐቦችም አካሄድ ይህንን ነው የሚያጠናክረው። ለቢድዐ ቀዳዳና መፈናፈኛ የማይሰጡ በርካታ ከባባድ ንግግሮችን ጥለው አልፈዋል። ይህም ሆኖ ግን ለሚፈፅሙት ቢድዐ “ጥሩ” የሚል ጭምብል የሚያለብሱ አካላት በየዘመኑ ያጋጥማሉ። ለዚህም ምንም እንኳን አዋጭ ባይሆኑም የሚጠቀሟቸው ብዥታዎች አሏቸው። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ተከታዩዋ አንቀፅ ነች፦ (تُدَمِّرُ كُلَّ شَيۡءِۭ بِأَمۡرِ رَبِّهَا فَأَصۡبَحُواْ لَا يُرَىٰٓ إِلَّا مَسَٰكِنُهُمۡۚ) [الأحقاف: 25] {በጌታዋ ትእዛዝ ሁሉን ነገር ታጠፋለች። ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ሆኑ።} [አልአሕቃፍ፡ 25] አንቀጿ የነብዩ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ህዝቦች ባስተባበሉ ጊዜ ስለተላከችባቸው የቅጣት ነፋስ ነው የምታወራው። የቢድዐ ደጋፊዎች ግን “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው” የሚለውን ሐዲሥ ለመገደብ ይህቺን አንቀፅ እንዴት እንደሚተነትኗት ተመልከቱ፡- “ሁሉም ነገር ከሚለው ገለፃ ውስጥ ሰማይና ምድር፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፀሀይ፣ ጀነትና እሳት፣ መላኢካ፣ ጂን፣ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች፣ እፅዋት፣ እንስሳት፣ ግኡዛን… ሁሉ ይጠቃለላሉ። በተግባር ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች አልወደሙም። አህቃፍ የተባለችው የከሃዲዎች መንደር ብቻ ናት የጠፋችው። የአንቀጿ ገለፃ ዐሙን መኽሱስ ይሰኛል። ገለፃው አጠቃላይ ቢሆንም በተጨባጭ እውነታ የተገደበ ነው። ቢድዐህ ሁሉ ጥመት ነው የምትለዋ ሀዲስም እንደዚሁ ገለፃዋ አጠቃላይና ሁሉንም አዲስ ነገሮች (ቢድዐዎች) የሚያካትት ቢመስልም በሌሎች ሀዲሶችና በሸሪዐው መርሆዎች የተገደበች ናት።” ምላሽ:- ==== 1. በአንቀጿ ውስጥ “ሁሉ” የሚለው ቃል የቢድዐ አጋፋሪዎች የሚዘረዝሩትን ሁሉ የሚያካትት አይደለም። ነፋሷ የተላከችው ወደ አሕቃፍ ነው፣ ወደ ነብዩ ሁድ ሰዎች። በሌላ ቦታ አላህ እንዲህ ይላል፡- (وَفِي عَادٍ إِذۡ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلرِّيحَ ٱلۡعَقِيمَ ٤١ مَا تَذَرُ مِن شَيۡءٍ أَتَتۡ عَلَيۡهِ إِلَّا جَعَلَتۡهُ كَٱلرَّمِيمِ) [الذاريات: 41-42] {በዓድም ህዝብ ላይ አጥፊ የሆነችን ነፋስ በላክን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ።) በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወውም።} [አዛሪያት፡ 41-42] ስለዚህ ነፋሷ ወደ አሕቃፍ መንደር ነው የተላከችው። ሰማይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፀሀይ፣ ጀነትና እሳት፣ … በአሕቃፍ መንደር አይደለም ያሉት። 2. በዚያ ላይ {በጌታዋ ፈቃድ} የሚል ቃል አለ። ስለዚህ እንድታጠፋ የተፈቀደላትን ብቻ ነው “ሁሉ” ሲል የገለፀው። 3. {ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ሆኑ} ማለቱን አስተውሉ። 4. ከ21ኛዋ አንቀፅ ጀምራችሁ እያነበባችሁ ብትወርዱ እየተረከ ያለው ስለ ዓድ ህዝቦች እንደሆነ ግልፅ ነው። በዚህ አገባብ ውስጥ “ሁሉ” የሚለው ቃል ፍንትው ያለ ሆኖ ሳለ ሰማይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፀሀይ፣ ጀነት፣ እሳት፣ መላኢካ፣ ጂን፣ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች፣ እፅዋት፣ እንስሳት፣… እያሉ ማተራመስ እጅግ የሚደንቅ ነው። “አስራ ሰባት ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደብረ-ብርሃን ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተገልብጦ በውስጡ የነበሩት ሁሉም ተሳፋሪዎች አለቁ” በሚለው ዜና ውስጥ “ሁሉ” የሚለው ቃል እንደሱፍዮች አረዳድ ከአለም ህዝብም ተሻግሮ ጂንና መላእክትን ሁሉ ይገልፃል ማለት ነው። ከንዲህ አይነት የዛገ አረዳድ አላህ ይጠብቀን። ለማንኛውም የቁርኣን ተንታኞች ስለ አንቀጿ ምን እንደሚሉ እንመልከት፡- 1. ኢብኑ ጀሪር አጦበሪ (310 ዓ.ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- وإنما عنى بقوله (تُدَمِّرُ كُلَّ شَيْءٍ بِأَمْرِ رَبِّهَا) مما أرسلت بهلاكه “{በጌታዋ ትእዛዝ ሁሉንም ነገር ታጠፋለች} ሲል ማለት የፈለገው እንድታጠፋው የተፈለገውን ማለት ነው።” [ተፍሲር ኢብኒ ጀሪር፡ 22/129] 2. ቁርጡቢም (671 ዓ. ሂ.) እንዲህ ይላሉ፡- كُلُّ شَيْءٍ مَرَّتْ عَلَيْهِ مِنْ رِجالِ عَادٍ وَأَمْوَالِهَا. قَالَ ابْنُ عَبَّاسٍ: أَيْ كُلُّ شَيْءٍ بُعِثَتْ إِلَيْهِ “ያለፈችባቸውን የዓድ ሰዎችና ንብረቶቻቸውን ለማለት ነው። ኢብኑ ዐባስ፡ ‘የተላከችበትን ሁሉ ማለት ነው’ ብሏል።” [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 16/206] ሲጠቃለል በየትኛውም ሁኔታ “ሁሉ” የሚለው ቃል አገባቡን የሚከተል እንጂ የቢድዐ ልክፍተኞች እንደሚሉት ጀነትና እሳት ሳይቀር ከፈጣሪ ውጭ ያለን ነገር በሙሉ የሚያጠቃልል አይደለም። “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው” የሚለው ጥቅላይ ሐዲሣዊ መልእክት ደግሞ በእንዲህ አይነት አጉል ፍልስፍና ትርጉሙን መገደብ አይቻልም። ሁሉም ቢድዐኮ ለባለቤቱ ቆንጆ ነው። እንዲህ አይነት በር የምንከፍት ከሆነ የትኛውንም የቢድዐ ባለቤት መቃወም አይቻልም። በስሜት የተለከፈ ሁሉ የራሱን ቢድዐ አሾልኮ ለማሳለፍ በዚህ መልኩ አጉል ቢጋጋጥ እራሱን ነው የሚጎዳው። የቢድዐ ፍቅር የማገናዘብ አቅማቸውን ያሽመደመደባቸውን ወገኖቻችንን አላህ ዐቅላቸውን ይመልስላቸው። ኢብኑ ሙነወር የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/IbnuMunewor