es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

SU|ኤስዩ

SU|ኤስዩ

Ir al canal en Telegram

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
674
Suscriptores
+124 horas
+67 días
+430 días
Archivo de publicaciones
photo content
+4

photo content
+1

photo content
+8

photo content
+9

photo content
+7

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+3

photo content
+9

photo content
+2

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+1

photo content
+9

photo content
+9

#ከሚሴ_ኃይስኩል_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት ----- ----- ------- ------ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 18 ፥ በሰሜን ምስራቅ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አካባቢያዊ ቢሮ፣ #ለከሚሴ ክርስቲያን ተማ
+8
#ከሚሴ_ኃይስኩል_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት ----- ----- ------- ------ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 18 ፥ በሰሜን ምስራቅ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አካባቢያዊ ቢሮ፣  #ለከሚሴ  ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መሪዎችና አባላት ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው፣ #የእግዚአብሔር_ልብ_ለኃይስኩል (God's Vision for Highschool )፣ #የተማሪ_ህብረትና_የቤተሰብ_ቡድን (School Fellowship and Family Group ) ፣ #የትምህርት_ልህቀትና_የትምህርት ምርጫ (Acedamic Excellence and Choice) እና #እውነተኛ_አምልኮና_ፀሎት (True Worship and Prayer ) ርዕሶች ላይ የተሰጠ ሲሆን፤ በተጨማሪም የተማሪ ህብረትን Reshape እና Repurpose በማደረግ ዙሪያ ምክክርና ፀሎት ተደርጓል። በፕሮግራሙ ላይ የተማሪ ህብረት አገልግሎት ላይ አንድም ጊዜ ተሣትፈው የማያውቁ ተማሪዎች መገኘት የቻሉ ሲሆን፣ በመገኘታቸው እንደተጠቀሙና በቀጣይ በህብረት ታቅፈው ለመቀጠል እንደተበረታቱ ተናገረዋል። ክብር ለጌታ ይሁን እግዚአብሔር አካባቢውን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ የተመሰረቱ ህብረቶች እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ እንፀልይላቸው ========== #ኤስዩ #ሰሜን_ምስራቅ_ክልል #ከሚሴ #ኦሮሞ_ብሔረሰብ_ዞን_አካባቢያዊ_ቢሮ #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

#ምስራቅ_ሐረርጌ_ባቢሌ #ሕብረት_ተደራጅቷል ---- ----- ----- ----- #በምስራቅ_ኢትዮጵያ የቃለ እግዚአብሔር  አንባቢዎች ማህበር (ኤስዩ) ከሚያስተባብራቸው ከተሞች መካከል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የምትገኘው #የባቢሌ ከተማ አንዷ ነች:: በእግዚአብሔር እርዳታ እንዲሁም በከተማው አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ትብብር የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ፌሎሽፕ ድጋሚ የመመስረቻ እና የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናውኗል። በከተማው ከዓስር አመት በፊት የኃይስኩል ተማሪዎች ህብረት አገልግሎት የነበረ ቢሆንም በተፈጠሩ አንዳንድ ችግሮች ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል። በዝግጅቱ በባቢሌ ከተማ የሚገኙ የኃይስኩል ፌሎሽፕ ተማሪዎች እንዲሁም ከአጎራባች ከተሞች፣ #ከሐሮማያ እና #አደሌ ከተማ ጥሪ የተደረገላቸው የተማሪ ህብረት መሪዎች ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ፣ #የእግዚአብሔር_ልብ_ለኃይስኩል ፣ #የቤተሰብ_ቡድን_ስልት እንዲሁም #ዓለምአቀፍ_የእግዚአብሔር_ተልዕኮ የሚሉ ስልጠናዎች በቁጥር 50 ለሚሆኑ ተማሪዎች መስጠት ተችሏል:: ከስልጠናው ጎን ለጎን በከተማው ከሚገኙ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ሰፊ የምክክር እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል። ለቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሤት፣ እና የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። በዝግጅቱ ተማሪዎች ደስተኞች እንደሆኑ ገልፀዋል። የተሰጡት ስልጠናዎችም ለግል ህይወት እና ለአገልግሎት የሚኖራቸውን ቁልፍ ጠቀሜታ አንስተዋል። የቤተክርስቲያን መሪዎች በበኩላቸው፣ በኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎት ደስተኞች እንደሆኑ እና አብረው በትብብር ለመስራት ያላቸውን ሙሉ ፈቃደኝነት ገልፀዋል። አያይዘው፣ ለተማሪዎች ሕብረት የሚደረገው ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የባቢሌ ከተማ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ548 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። በምስራቅ ክልል ለሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶች እንድትፀልዩ እንለምናለን! ከቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) #ተልዕኮ መካከል #ተማሪዎች፣ #ለፀሎት_እና_ለእግዚአብሔር_ቃል_ጥናት የሚሰባሰቡበትን #ሕብረት_ማደራጀት ቀዳሚው ነው። በምስራቅ የኤስዩ ክልላዊ ቢሮ የተማሪዎችን አገልግሎት በትጋት እያከናወኑ ያሉትን ሁሉ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው። ======= #ኤስ_ዩ #ምስራቅ_ክልል #ባቢሌ #ሐሮማያ #አደሌ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content
+8

photo content
+8

#ጂንካ: #የኃይስኩል_ፌሎሽፕ_መሪዎችን_የማስታጠቅ_መርሐ_ግብር ----- ------ ------ ----- #ደቡብ_ኤስዩ_ክልላዊ_ቢሮ፣ በአሪ ዞን፣ በጂንካ ከተማ የኤስ.ዩ አካባቢያዊ ቢሮ ለኃይስኩል የ
+7
#ጂንካ: #የኃይስኩል_ፌሎሽፕ_መሪዎችን_የማስታጠቅ_መርሐ_ግብር ----- ------ ------ ----- #ደቡብ_ኤስዩ_ክልላዊ_ቢሮ፣ በአሪ ዞን፣ በጂንካ ከተማ የኤስ.ዩ አካባቢያዊ ቢሮ ለኃይስኩል የተማሪዎች ሕብረት መሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ የስልጠናው የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረትን ማጠናከር እንዲሁም ስለ ቤተሰብ ቡድን ( Family Group) የአገልግሎት ስልት ግንዛቤ መፈጠርን ዐላማ አድርጎ የተዘጋጀ ነው። በሕይወት ብርሃን አጥቢያ ቤ/ክ በተሰናዳው ፕሮግራም፣ #በጂንካ የሚገኙ የኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪዎች፣ የአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪዎች ፣ እንዲሁም ተተኪ መሪዎች ተሣታፊ ሆነዋል። በዕለቱ #የዘፍጥረት_መጽሐፍ ላይ ያተኮረ መልዕክት ቀርቧል። የቤተሰብ ቡድን አሰራር ( #Family_Group_Strategy) እና ወዳጃዊ ወንጌልን የመመስከር ስልት ( $PCS: Pray-Care-Share) በዞኑ እያገለገሉ በሚገኙ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ስታፎች ተሰጥቷል። በተጨማሪም፣ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) አገልግሎትና አሰራርን በተመለከተ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል። ከስልጠና ባሻገር የእግዚአብሔር መገኘት የነበረበት #የፀሎት_መርሐ_ግብርም ተካሂዷል። ጅንካ ከአዲስ አበባ የ615 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። በአሪ ዞን፣ ጅንካ ከተማ እያገለገሉ የሚገኙት #የኤስዩ_አሶሼት_ስታፎች አስደናቂ አገልግሎት እየሰጡ ነው። አገልግሎታቸውን በታላቅ ትጋት፤በብዙ መሰጠት እያገለግሉ ነው። እግዚአብሔር አብዝቶ ፀጋውን ያብዛላቸው። አካባቢው ከነበረበት የጤና ስጋት ድባብ ወጥቶ ነገሮች በመስተካከላቸው እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። @suethio