es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Ir al canal en Telegram

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
3 015
Suscriptores
+3324 horas
+1177 días
+28330 días
Archivo de publicaciones
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

photo content

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ሰኔ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ_አቡናፍር ገዳማዊ +"+ =>ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው:: ወቅቱ ሥርዓተ መነኮሳት የሚጠበቅበት:አበው ባሕታውያን እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው የደመቁበት ነበር:: ታላቁ አቡናፍርም ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በሥርዓት አድጎ: መጻሕፍትንም ተምሮ ገና በወጣትነቱ መንኗል:: +ሥርዓተ መነኮሳትን ከአባ ኤስድሮስ ታላቁ አጥንቶ ገዳሙንና መምሕሩን እየረዳ ለብዙ ዓመታት በጾምና በጸሎት ኑሯል:: መነኮሳቱ ስለ ትሕትናውና ስለ ታዛዥነቱ ፈጽመው ያከብሩት ነበር:: +ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋውያን መነኮሳት ጭው ባለ በርሃ ስለሚኖሩ ባሕታውያን ሲጨዋወቱ: ሲያደንቁዋቸውም ሰማ:: እርሱ በዛ ወቅት ባሕታውያን በበርሃ መኖራቸውን አያውቅም ነበርና ሒዶ መምሕሩን አባ_ኤስድሮስን ጠየቃቸው:: እርሳቸውም "አዎ ልጄ! ከዚሕ በጣም ርቅው: ንጽሕናቸውን ጠብቀው: ከሰውና ከኃጢአት ተይለው የሚኖሩ ገዳማውያን አሉ" አሉት:: +ቅዱስ አቡናፍር "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት ማን ይበልጣል?" ቢላቸው "እነርሱ በጣም ይበልጣሉ:: ዓለም እንኩዋ ከነ ክብሯ የእግራቸውን ሰኮና አታህልም" አሉት:: ይሕንን የሰማው ቅዱስ አባ አቡናፍር ጊዜ አላጠፋም:: +ከመምሕሩ ቡራኬ ተቀብሎ ወደ በርሃ ሔደ:: ለብዙ ቀናት ከተጉዋዘ በኋላ አንድ ባሕታዊ አግኝቶ አብሯቸው ተቀመጠ:: ከእርሳቸው ዘንድም ሥርዓተ ባሕታውያንን ተምሮ እንደገና ወደ ዋናው በርሃ ጉዞውን ቀጠለ:: +ከብዙ ቀናት መንገድ በኋላም አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ደረሰ:: አካባቢው የውሃ ጠብታ የማይገኝበት: ይቅርና መጠለያ ዛፍ የሣር ዘር እንኩዋ የሌለበት ወይም በልሳነ አበው "ዋዕየ ፀሐይ የጸናበት: ልምላሜ ሣዕር የሌለበት: ነቅዐ ማይ የማይገኝበት" ቦታ ነበር:: በዚህ ቦታ ይቅርና የሰው ልጅ አራዊትም አይኖሩበትም:: +ለአባ አቡናፍር ግን ተመራጭ ቦታ ነበር:: ቅዱሳኑን ይሕ አያሳስባቸውም:: ምክንያቱም ለእነርሱ ምግባቸውም: ልብሳቸውም ፍቅረ_ክርስቶስ ነውና:: አባ አቡናፍር ወደ ፈጣሪ ጸለዩ:: በእግዚአብሔር ቸርነት ከጎናቸው አንዲት ዘንባባ (በቀልት) በቀለች:: ከእግራቸው ሥርም ጽሩይ ማይ (ንጹሕ ምንጭ) ፈለቀች:: +ጻድቁ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: ዓመታት አለፉ:: ልብሳቸውን ፀሐይና ብርድ ጨርሶት ቅጠል ለበሱ:: በዚያ ቦታም የሰው ዘርን ሳያዩ ለ60 ዓመታት በተጋድሎ ኖሩ:: የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር አባ_በፍኑትዮስን (የባሕታውያንን ዜና የጻፈ አባት ነው) ላከላቸው:: +ቃለ እግዚአብሔርን እየተጨዋወቱ ሳለ የአባ አቡናፍር አካሉ ተለወጠ:: እንደ እሳትም ነደደ:: አባ በፍኑትዮስም ደነገጠ:: ታላቁ ገዳማዊ ግን እጆቻቸውን ዘርግተው ጸለዩ: ሰገዱና አማተቡ:: ነፍሳቸውም ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ቅዱሳን መላዕክትም በዝማሬና በማኅሌት አሳረጉዋት:: የሚገርመው ደግሞ አባ በፍኑትዮስ ይሕን ሲያይ ቆይቶ ዘወር ቢል ዛፏ ወድቃለች: ቅርንጯም ደርቃለች:: =>ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱሳን አበው ባሕታውያን መታሠቢያ ናት:: +ከሰው (ከዓለም) ርቀው: ንጽሕ ጠብቀው: ዕጸበ ገዳሙን: ግርማ አራዊቱን: ጸብዐ አጋንንትን ታግሠው የኖሩ: ስማቸውን የምናውቀውንም ሆነ የማናውቃቸውን እንድናከብራቸው ቤተ_ክርስቲያን ሥርዓትና በዓል ሠርታለች:: =>አምላካችን ከአበው ባሕታውያን ጸጋ በረከት ይክፈለን:: =>ሰኔ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ አቡናፍር ገዳማዊ (ስም አጠራሩ የከበረ: ሽምግልናው ያማረ አባት) 2.አበው ቅዱሳን ባሕታውያን ( ዛሬ የሁሉም ቅዱሳን_ባሕታውያን (በተለይም የስውራኑ) ዓመታዊ በዓል ነው:: ¤ከሰው: ከዓለምና ከኃጢአት ርቀው ¤ንጽሕ ጠብቀው ¤ዕጸበ ገዳሙን ¤ድምጸ አራዊቱን ¤ግርማ ሌሊቱን ¤የሌሊቱን ቁር ¤የመዓልቱን ሐሩር ¤ረሐቡን: ጽሙን: መራቆቱን . . . ሁሉ ስለ ፍቅረ_ክርስቶስ ሲሉ ታግሠውታልና:: << ዛሬም በየበርሃው የወደቁ: ስለ ዓለም ምሕረትን የሚማጸኑ አሉ:: >> << አምላካቸው በረከታቸውን ያድለን >> 3.የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ከግብጽ እንዲመለስ የነገረበት (ተዝካረ ሚጠታ ለእግዝእትነ ማርያም) 4.አፄ ይኩኖ አምላክ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ኪዳነ ምሕረት ማርያም 2፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ 3፡ አባ ዳንኤል ገዳማዊ 4፡ ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሠ ሮሜ 5፡ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 6፡ ቅዱስ ሐርቤ ንጉሠ ኢትዮጵያ =>+"+ . . . ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ: ከዚሕም በላይ በእሥራትና በወኅኒ ተፈተኑ . . . ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:36) <<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ሰኔ 15-ታላቁ ሰማዕት ማር ቅዱስ ሚናስ ታላላቅ ተአምራት ያደረገበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት መርዩጥ በሚባል አገር ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት (ቅዳሴ ቤቱ) ነው፡፡ የቅዱስ ሚናስ አባቱ አውዶክስዮስ ሲሆን ሀሩም አናቅዮስ ይባላል፡፡ እርሱም ሀገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በሐሰት ነገር በመሥራት ከንጉሡ ጋር አጣላው፡፡ ንጉሡም አፍራቅያ ወደምትባል ሌላ ሀገር ልኮት በዚያ ገዥ አድርጎ ሾመው፡፡ አውዶክስዮስ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ደግ ሰው ስለነበር በአፍራቅያ የሚገኙ ሕዝቦችም ደስ አላቸው፡፡ የአውዶክስዮስም ልጅ አልነበረውና ሚስቱ ወደ እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን እየሄደች እመቤታችንን ትለምናት ነበር፡፡ አንድ ቀን ጸሎቷን ስትጨርስ ከእመቤታችን ሥዕሏ ድምፅ ወጣና አነጋገረቻት፡፡ ልጅ እንደምትወልድና ስሙንም ሚናስ እንደምትለው ነገረቻት፡፡ ሚናስም ተወለደና ወላጆቹ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ በ12 ዓመቱ አባቱ ዐረፈ፣ ከ3 ዓመት በኋላ እናቱም ዐረፈችና ሚናስ ብቻውን ቀረ፡፡ መኳንንቱም አባቱን በጣም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ መስፍንነት ሹሙት፡፡ እግዚአብሔርንም መንግሥትንም በትጋትና በቅንነት እያገለገለ እያለ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ነገሠና ክርስቲያኖችን ማረድ ጀመረ፡፡ ቅዱስ ሚናስም ይህን ሲሰማ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባና በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብቻ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡ አንድ ቀን ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታት የብርሃን አክሊል ሲቀዳጁ አየ፡፡ በዚህም ጊዜ ወደ ከተማው ተመለሰና የጌታችን የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ አምላክነት መመስከር ጀመረ፡፡ መኰንኑም የመንግሥት ወገን መሆኑን ዐውቆ በማባበል ብዙ ለመነው፡፡ ‹‹የንጉሡን ትእዘዝ አትተላለፍ›› እያለ ቢለምነው ቅዱስ ሚናስ ግን አልሰማ አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮች ያሠቃየው ጀመር፡፡ ማሠቃየቱም በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘና ቅዱስ ሚናስ ኅዳር 15 ቀን ተሰይፎ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ በእርሱም ምክንያት ብዙዎች በክርስቶስ አምነው ሰማዕት ሆኑ፡፡ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ እሳት አንድደው በዚያ ጨመሩት፡፡ ነገር ግን እሳቱ አልነካውም፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋውን ወስደው የመከራ ዘመን እስኪያልፍ ደብቀው በክብር አኖሩት፡፡ የመርዩጥ አገር ሰዎች ወደ አምስት አገሮች ሲጓዙ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው አብረው ወሰዱት፡፡ በባሕርም ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያሉ አውሬዎች ከባሕር ወጡና የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ይልሱት ዘንድ አንገታቸውን ዘረጉ፡፡ ነገር ግን ከቅዱስ ሚናስን ሥጋ ውስጥ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጥላ ገደለቻቸው፡፡ ሰዎቹም ይህን አይተው እጅግ ተደሰቱ፡፡ ወደ እስክንድርያ አገር ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ይዘው ሊመለሱ ወደው በግመል ላይ ጫኑት፡፡ ነገር ግን ግመሏ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ ሁለተኛም በሌላ ግመል ቢጭኑትም አሁንም አልንቀሳቀስ አለች፡፡ አብዝተውም ቢደበድቧት እምቢ አለች፡፡ አሁንም ሌላ ሦስተኛ ግመል ቢሞክሩ እርሷም እምቢ አለች፡፡ ከዚያም ‹‹ይህ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት ቦታ ነው›› ብለው ቦታውን አዘጋጅተው በዚያ ቀብረውት ሄዱ፡፡ ማር ሚናስ ሰማዕትነቱን ፈጽሞ ካረፈ በኋላ ቅዱስ ሥጋው ተሰውሮ ለብዙ ዘመን ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ለምእመናን ጥቅም ቅዱስ ሥጋው የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ በእግዚአብሔር ፈቃድ በአንድ በግ ጠባቂ እረኛ አማካኝነት ያለበት ታወቀ፡፡ ይኸውም አንድ የታመመች በግ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ተደብቆ በሚኖርበት ኮረብታ አካባቢ ባለው ውኃ ውስጥ ገብታ ስትወጣ ዳነች፡፡ እረኛውም መዳኗን አይቶ ሌሎች የታመሙ በጎቹንም በውኃው ውስጥ እየከተተ ሲሞክራቸው ፍጹም ጤነኛ ሆኑለት፡፡ ቦታውም የታወቀ ሆነና ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ሁሉም እየመጣ በውኃው እየተጠመቁና አፈሩን በውኃው እየለወሱ እየተቀቡ ይፈወሱበት ጀመር፡፡ ወሬውም እስከ ሮሙ ንጉሥ ድረስ ደረሰ፡፡ ንጉሡም የታመመች ሴት ልጅ ነበርችውና ወደ እረኛው ዘንድ ላካትና እርሷም ፍጹም ተፈወሰች፡፡ የንጉሡም ልጅ ይህ ፈውስ የሚደረግበት ነገር ምን እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ወደደች፡፡ ቅዱስ ሚናስም በሕልሟ ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋውን አስቆፍራ እንድታወጣ እግዚአብሔር ያዘዛት መሆኑን ነገራት፡፡ እንደታዘዘችውን ቅዱስ ሥጋውን አስወጥታ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን አሠራችለት፡፡ ንጉሡም በቦታው ላይ ታላቅ ከተማ እንዲሠራ አዘዘና ከተማ ሆነች፣ ስሟንም መርዩጥ አሏት፡፡ እግዚአብሔርም በቅዱስ ሚናስ ሥጋ እስከዛሬ ድረስ እጅግ አስገራሚ ተአምራት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለመናገር የሚከብዱ እጅግ ብዙ ተአምራት ይሠራሉ፡፡ ይህችም ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ሰኔ 15 ነው፡፡ ዳግመኛም ይኸች ዕለት ታላላቅ ተአምራት ያደረገባት ዕለት ናት፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ ሚናስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡

💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞ ✞ እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ✞
=> #4ቱ_ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ ስማቸው #አባ_አክራ : #አባ_ዮሐንስ : #አባ_አብጥልማ እና #አባ_ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት (ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው) ካህናትና ሃብታሞች ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው:: +ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ እየተቀበሉ: ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ:: +በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ:: የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ: ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ:: +በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና: የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ:: +አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) አደረጉ:: +በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ:: በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ ድፍረት ነበር:: +መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም: በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ:: በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን ተቀብለዋል:: =>የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን:: =>ሰኔ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን አበው ሰማዕታት (አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ አብጥልማ: አባ ፊልዾስ) =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት =>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE