es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Ir al canal en Telegram

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 981
Suscriptores
-224 horas
+507 días
+18430 días
Archivo de publicaciones
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0

🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

††† እንኳን ለቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ ††† ††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው አሥራ አራት መልእክታት መካከል አንዷ የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኳ ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል:: ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው? ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን እስያ ውስጥ: ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው:: የዘር ሐረጉ ከእሥራኤልም: ከጽርእም (ግሪክ ለማለት ነው::) ይወለዳል:: አካባቢው አምልኮተ እግዚአብሔር የጠፋበት ስለሆነ እሱም: ቤተሰቦቹም የሚያመልኩት ከዋክብትን ነበር:: መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ:: ቅዱሱ በወቅቱ ምንም እውነተኛውን ፈጣሪ አያምልክ እንጂ በጠባዩ እጅግ ቅንና ደግ ነበር:: ምክንያቱን ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ: ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን በራዕይ ተገለጠለት:: በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ! ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው::" ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ:: የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም ሊገባቸው አልቻለም:: ለተወሰነ ጊዜም ለጉዳዩ ምላሽ ሳያገኝለት በልቡ እየተመላለሰ ኖረ:: ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው::" ሲሉ ለቲቶ ነገሩት:: "ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን ይፈወሳሉ:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ለምጻሞች ይነጻሉ:: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው::" አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ:: እርሱ መሔድ ስላልተቻለው "ብልህ ጥበበኛ ሰው ፈልጉልኝ::" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን "ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ::" ብሎ ላከው:: ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ:: ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው:: 1.ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ: አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ:: 2.ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: የግሪክ ፍልሥፍና መነሻውም ሆነ መድረሻው ሥጋዊ ነው:: ጌታ ግን በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ ዘላለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ ተጋደል::" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት:: በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ደመረው:: የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ከጌታችን እግር ለሦስት ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ: በመላው እስያ ለስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል:: ቅዱስ ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለሃያ አምስት ዓመታት አስተምሯል:: ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ደግሞ ወደ አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኳቸውም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ††† አምላከ ቅዱስ ቲቶ መልካሙን የሕይወት ምሥጢር ይግለጽልን:: ከሐዋርያውም በረከቱን ያድለን:: ††† ጳጉሜን 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት) ††† ወርኀዊ በዓላት (የለም) ††† "የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ. . . መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ: ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ: በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ለሚሆን ልጄ ቲቶ:: ከእግዚአብሔርም አብ: ከመድኃኒታችንም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን::" ††† (ቲቶ. ፩፥፩) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

፨፨፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚችም ዕለት የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም አመታዊ የዕረፍት በዓሏ መታሰቢያ ነው፨፨፨ ✝✞✝ ቅድስት ዜና ማርያም ✝✞✝ ፨  በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት ግንቦት 30 ቀን በጎጃም ክፍለ ሀገር ተወለደች። የአባቷ ስም ገብረ ክርስቶስ የእናቷ ስም አመተ ማርያም ይባላሉ። እጅግ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፡ ቅዲስ ጋብቻቸውን በንጽሕና የሚጠብቁ፡ ለሰው የሚራሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ። እንዲህ ባለ መልካም ግብር ከኖሩ በኀላ በፈቃደ እግዚአብሔር 3 ወንዶች ልጆች እናት አንዲት ሴት ልጅ ወለዱ። ይህችም ሴት ልጅ ተወዳጇ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ናት። ፨ ቅድስት ዜና ማርያም እናት እና አባቷን እያገለገለች፡ ፈርሐ እግዚአብሔን፡ በጎ ምግባርን ከወለጆቿ እየተማረች አደገች። ለአቅመ ሔዋንም በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ  ወጣት አጯት። ታላቅ ግብዣ ተደረጎ በተክሊል ተዳረች። በዚያው ወራት ግን የዜና ማርያም እናት አመተ ማርያም አምስተኛ ልጅ ወልዳ ተኝታ ሳለች በአካባቢው ሕማመ ብድብድ (ተላላፊ በሽታ) በመነሳቱ የዜና ማርያም እናት ታማ ነበር፡ በመጨረሻም ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈች። ፨ ከዚህ በኋላ የታመመውን ወንድሟንና ሌሎቹንም በመያዝ ከተላላፊው በሽታ ለመትረፍ ሲሉ አካባቢውን ለቀው ወደ በረሃ ወጡ። በዚያም ሌሊት የዱር አራዊት መጥተው ከበቧቸው ሁሉንም ሊበሏቸው ሞከሩ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ስመ እግዚአብሔርን ስትጠራ አራዊቱ ወደኋላ በመሸሽ ከአካባቢው ራቁ። እርሷም ከክፉ ሁሉ የጠበቃቸውን፡ ከአራዊት መበላት የሰወራቸውን እግዚአብሔርን አመሰገነች። በነጋም ጊዜ የታመመውን ወንድሟን እና ሌሎችን በመያዝ መንገድን ቀጠሉ አንዲት ባዶ ቤት አግኝተው ከእርሷ ተጠጉ። በፀሐዩ ንዳድና ታናሽ ወንድሟን በማዘል እጅግ ስለደከመች ከባድ እንቅልፍ ጣላት። ጠዋት ስትነሳ ግን የታመመው ወንድሟ ከአጠገቧ አላገኘችውም ሌሊት የዱር አራዊት በልተውታልና። አጅም አዘነች የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብላ አራሷን አፅናናች የወንድሟን ተረፈ ሥጋ አጠራቅሟ ቀበረች። በመቀጠልም በአካባቢው ካለ ገዳም ሔዳ ምንኩስናን ተቀበለች። ፨ ከዚህ በኋላ ባሏ አባቷን ሚስቴን አምጣ እያለ ስለጨቀጨቀው ከብዙ ልፋት እና ድካም ፈልጎ አገኛት ወደ ሀገሯም ወሰዳት። በዚያም ወደ ጉባኤ ቀርባ ለምን ወደ ገዳመ እንደሄደች እና ባሏን አንደከዳች ተጠየቀች። እርሷም እግዚአብሔር ከብዙ መከራ አድኖኛል እና እራሴን ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ አለች። የጉባኤው ተሰብሳቢ በሏ ሀብቷን ወርሶ እንዲያሰናብታት ፈረዱ። እርሷም በዚህ ነገር በመስማማት የነበራትን ላም እና በሮች አስረከበች። ፨ ከዚህ በኋላ በአባቷ ቤት ለአንድ ዓመት ያህል በመቀመጥ የእናቷን ተዝካር አውጥታ ወደ ገዳሙ ተመለሰች በዛም ለጥቂት አመታት የተለያዩ ገድላትን ስትፈጽም ከቆየች በኋሏ ከነፍስ አባቷ ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል ጋር ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ እንፍራንዝ (ጣራ ገዳም) አካባቢ ዋሻ እንድርያስ በተባለው ለ25 ዓመት በብሕትውና ኖረች። አሁንም ድረስ በዚያ ዋሻ እናታችን ዜና ማርያም በፀሎት ጊዜዋ እንቅልፍ እንዳይጥላት ስትጠቀምበት የነበረ ዘንግ ፣ የምተቆምበት ዙሪያውን በገመድ የታሰረ የተቦረቦረ ግንድ አሁንም ድረስ ተአምር እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም በመቀጠል ዛሬ ዜና ማርያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ዋሻ ሔደች በዚያም በጾምና በጸሎት በልዩ ልዩ ተጋድሎ እስከ እለተ እረፍቷ ድረስ በዚያ ኖራለች። +++ የገድል ዓይነቶች +++ ፨ በየሰዓቱ ከ 100-300 ትሰግድ ነበር ፨ ሁለት ቀን እየፆመች በሶስተኛ ቀን ጥቂት ጥሬ ቀምሳ ሳምንቱን ታሳልፈው ነበር ፨ 150ን መዝሙረ ዳዊት እና ወንጌል በየቀኑ ትጸልይ ነበር ፨ በብሕትውና ወራት ማር፣ ቅቤን፣ ወተትን ፈጽሞ አትቀምስም ነበር ፨  የጌታችን መከራ መስቀል እና ስትየ ሐሞት በማሰብ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ኮሶ የሚባል ቅጠል እየበጠበጠች ከቅል ውስጥ ከሚገኘው መራራ ፍሬ ጋር በማዋሐድ ትጠጣ ነበር ፨ ከጸሎት እና ከስግደት በምታርፍበት ጊዜ አትክልት በመትከል እና በመኮትኮት ጊዜዋን ታሳልፍ ነበር ፨ የጌታችንን ግርፋቱን በማሰብ 100 ጊዜ ጀርባዋን ስለምትገረፍ እና ደም ስለሚፈሳት  ጀርባዋ ይቆስል እና ይተላ ነበር። +++ተአምራት+++ ፨ ዓይናቸውን በተለያየ በሽታ የታመሙ ሰውዎች ሁሉ ከህመማቸው ተፈውሰዋል ፨ የራስ በሽታ ( የራስ ፍልጠት፣ ጭንቀት፣ ማዞር) የታመሙ ጸበሉን በመቀባት ድነዋል፡፡ ፨ ጸበሉን በመጠመቅ፤ የጻድቋን ተአምር በማዘል፤ ስዕለት በመሳል መካኖች ወላድ ሆነዋል።  ሌሎች በየቀኑ ብዙ ተአምራትን እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ታደርጋለች። +++ቃል ኪዳን+++ ቅድስት ዜና ማርያም ከዚህ ዓለም የምታርፍበት ጊዜ እንደደረሰ በመንፈስ ቅዱስ በአወቀች ጊዜ ከታላቅ ዛፍ ወጥታ ስትፀልይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ጋር፣ ከነቢያት፣ ከሐዋርያት፣ ከሰማዕታት፣ ከጻድቃን፣ ከደናግል መነኮሳት ጋር በመሆን ተገልጾ ከአረጋጋት በኋላ ቃል ኪዳንን ሰጧታል። ፨ በፀሎትሽ ያመነውን ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ፨ በስምሽ የተራበውን ያበላ በመንግስተ ሰማያት ኅብስተ ሕይወት አበላዋለሁ፤ የተጠማውን ያጠጣ ጽዋዓ ሕይወትን አጠጣዋለሁ ፨ መጽሐፈ ገድልሽን የጻፈውን፡ ያጻፈውን፡ የሰማውን፡ ያሰማውን ስሙን በዓምደ ወርቅ እጽፈዋለሁ ፨ ከሕፃንነትሽ እስከ አሁን ድረስ ስለ እኔ ብለሽ ብዙ መከራ ተቀብለሻል፦ ደጅሽን የረገጠ የሦስት ጭነት ጤፍ ያህል ነፍሳትን እንደሚምርላት፡ እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት ጌታችን በማይታበል ቃሉ ቃልኪዳን ገብቶላታል። እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት፡፡ +++ ገዳሟ እና መገኛው+++ ፨ የቅድስት ዜና ማርያም መካነ መቃብሯ ( ጸበሏ) በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ከም ከም ወረዳ ይገኛል ቦታውም አዲስ ዘመን ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከከተማው በስተሰሜን በኩል "ደሪጣ" ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ይገኛል። "ደሪጣ" ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜው ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ (ገዳም) ተብሎ እስከ አሁን ድረስ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በቅድስት ዜና ማርያም ገድል ውስጥ " ወትሰቲ ሲካር (ኮሶ) ደሪፃ" የሚል ቃል ይገኛል። ይህም ማለት ኮሶ የተባለውን እንጨት (ቅጠል) ቀጥቅጣ (አልማ) ከቅል ውስጥ ከሚገኘው ፍሬ ጋር በማደባለቅ ትጠጣለች ማለት ነው። ስለዚህ ቦታው "ደሪፃ" ተብሎ ተሰየመ በማለት በአካባቢው የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ። በመጨረሻም ተጋድሎዋን በመፈጸም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን ከዚህ አለም ድካም ዐርፋለች። የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም በረከቷ ቸርነቷ ይደርብን። አሜንን!! +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎታ፡፡ ወበረከታ ለቅድስት ዜና ማርያም የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን!!! +++

✝️✝️✝️††† እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† †††✝️✝️ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር †††✝️✝️ ††† በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ #አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም:: እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም:: በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም " #ዮሐንስ_ሐጺር- አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል:: ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:- "ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ: ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል:: ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር:: ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል:: #አባ_ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ:: አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል:: ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው:: ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ:: በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም:: ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው:- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው::" ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል:: መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል:: #መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር:: ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር:: አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ (ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን #ሊቃነ_መላእክት #ሚካኤል እና #ገብርኤል በግርማ በጌታ ፊት ቆመው ተመለከተ:: "እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ #ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ #ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል:: በ825 ዓ/ም ግን በአባ #ዮሐንስ_ፓትርያርክ ዘመን ክቡር ሥጋው ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ #ቅዱስ_መቃርስ ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል:: ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ:: ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን:: ††† ነሐሴ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት 3.ቅዱሳን ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ (ሰማዕታት) 4.አባ ባስልዮስ ጻድቅ (ዘትግራይ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት 2.ቅድስት አርሴማ ድንግል 3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ 5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት 6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት) ††† "እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ::" ††† (ሉቃ. 17:10) †††✝️✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር✝️✝️ †††