es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

የክብሩ ነፀብራቅ✨

የክብሩ ነፀብራቅ✨

Ir al canal en Telegram

ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
358
Suscriptores
+324 horas
+137 días
+9030 días
Archivo de publicaciones
መንፈሳዊ ጸሎት አንድ አማኝ በእውነት ወደ መንፈሳዊው ዓለም ሲገባ፣ ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ይረዳል፤ ለሌሎች የሚሰጠው የሕይወት በረከት እንደሌለውና በራሱ ውስጥም ጠላትን የሚቃወም አንዳች አቅም እንደሌለው ይገነዘባል። ያኔ በራሱ ተነሳሽነት እግዚአብሔርን የሕይወቱ ምንጭ ያደርገዋል፤ ጸሎትም የማይተው የሕይወቱ ክፍል ይሆናል። እውነተኛ ጸሎት የጸላይውን ባዶነትና የመላሹን (የእግዚአብሔርን) ባለጸግነት የሚገልጽ ነው። አንድ ሰው "ባዶ" እስኪሆን ድረስ ሥጋው በመስቀል ካልተገደለ፣ ጸሎቱ ምን ፋይዳና ዓላማ ይኖረዋል? መንፈሳዊ ጸሎት ማለት ከሥጋ ያልሆነ ጸሎት ማለት ነው። ይህም አማኙ ራሱ የሚያስበው፣ የሚመኘው ወይም ለማድረግ የሚወስነው ነገር አይደለም። ይልቁንም በእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት የሚለማመደው ነው። መንፈሳዊ ጸሎት በመንፈስ የሚጸለይ ጸሎት ነው። ይህም ማለት አንድ ሰው መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመንፈሳዊ ግንዛቤው (Intuition) ይረዳል፣ ከዚያም ስለዚያ ጉዳይ ይጸልያል። መጽሐፍ ቅዱስ
"በጸሎትና በልመና ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ" (ኤፌ. 6፡18)
በማለት ያዝዛል። በመንፈስ ካልጸለይን በሥጋ እየጸለይን ነው። ወደ እግዚአብሔር በምንቀርብበት ቅጽበት አፋችንን መክፈት የለብንም፤ ይልቁንም እንድናውቅ የሚፈልገውን ነገር እንዲያሳየንና እንዴት መጸለይ እንዳለብን እንዲያስተምረን መጀመሪያ እግዚአብሔርን መጠየቅ ይኖርብናል። ለምንፈልገው ነገር ደጋግመን መጸለይን ሞክረነዋል፤ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ስለሚፈልገው ነገር ለምን አንጸልይም? በጸሎት ውስጥ ለሥጋ ስፍራ የለውም። ዋናው አንተ የምትፈልገው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚፈልገው ነው። በእውነት መንፈሳዊ ያልሆኑ ሰዎች፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ጸሎት ሊኖራቸው አይችልም። መንፈሳዊ ጸሎቶች ሁሉ መነሻቸው እግዚአብሔር ነው። ምን መጸለይ እንዳለብን የሚያሳየን እግዚአብሔር ነው። እርሱ ፍላጎቱን ያሳየናል፣ በመንፈሳዊ ግንዛቤያችንም ውስጥ ያንን ጉዳይ እንደ ሸክም እንድንቀበለው ያደርገናል። ይህ የመንፈስ ሸክም ለጸሎት የቀረበልን ጥሪ ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በቸልተኝነት ምክንያት በመንፈሳችን ውስጥ የሚመጡ ጥቃቅን ስሜቶችን እናመልጣለን። በመንፈሳችን ካለን ሸክም በላይ መጸለይ የለብንም። በመንፈሳዊ ግንዛቤ (Intuition) ያልተጀመረና ያልተነሳሳ ማንኛውም ጸሎት፣ ከአማኙ ራሱ የሚመነጭ የሥጋ ጸሎት ነው። ዋችማን ኒ (Watchman Nee) "መንፈሳዊው ሰው" (The Spiritual Man) ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ

Our Generation's Sad truth😭
Our Generation's Sad truth😭

‎       ጉዳዬ 🎯 ‎ ‎እውነቱ ይህ ነው ፦ በዚህ ዘመን ልባችን "በብዙ ነገር" ተይዟል። አእምሯችን በኑሮ ስሌት፣ በነገ ስጋት፣ እና በምድር "ስኬት" ባልናቸው ሩጫ ተወጥሯል። አብዛኛውን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር የምንመጣውም እነዚህን የህይወት "ጉዳዮች" እንዲፈጽምልን፣ የጎደለውን እንዲሞላልን ወይም የተዘጉ በሮች እንዲከፍትልን ብለን ነው። እግዚአብሔርን የምንፈልገው እንደ "መፍትሄ ሰጪ" እንጂ እንደ "ህይወት ምንጭ/ዋና ጉዳይ" መሆኑ እየቀነሰብን መጥቷል 🙌 በቃ Our Motive is deeply Corrupted 🥺። ነገር ግን እውነተኛ የመንፈሳዊ ሰው የብስለት ጥግ የሚለካው፣ የልቡ ትኩረት ከሁኔታዎች (Circumstances) ተነስቶ በክርስቶስ ማንነት ላይ ብቻ‼️ ሲያርፍ ነው። ‎ ‎ይህ ማለት እግዚአብሔር የጉዳዮቻችን ማስፈጸሚያ መሆኑ ቀርቶ፣ እርሱ ራሱ የህይወታችን ብቸኛ እና ዋና "ጉዳይ" ስሆን ማለት ነው። ❤️ 🎯 ‎ ‎ይህንን የተረዳው ልበ አምላክ ንጉሱ ዳዊት፣ በዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉስ ቢሆንም፣ ብዙ የጦርነትና የመንግስት አጀንዳዎች ቢኖሩበትም፣ የልቡን ምት ግን ወደ አንድ "ጉዳይ" ብቻ አጠበበው። ‎
‎📖 “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።” ‎  — መዝሙር 27፥4
‎ ‎ዳዊት "አንድት ነገር" አለ! ይህች "አንድ ነገር" ጠላት እንዲጠፋለት አይደለም፣ እግዚአብሔር እንዲባርከው ወይም ግዛት እንዲሰፋለት አይደለም። እርሱ የፈለገው የእግዚአብሔርን እጅ (ስጦታውን) ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፊት (ማንነቱን) ነው። ‎
‎1. አይንን "ከነገሮች" ወደ "ንጉሱ" መመለስ 👁️
‎ ‎አይናችንን በጉዳያችን ላይ ስናደርግ እንዝላለን፣ እንጨነቃለን። አይናችንን በክርስቶስ ላይ ስንተክል ግን፣ የምንፈልገው ነገር ሁሉ በእርሱ ውስጥ እንዳለ እንረዳለን። እውነተኛ ክርስትና ማለት ብዙ ነገሮችን ከጌታ ተቀብሎ በደስታ መኖር ሳይሆን፣ ጌታን የነገሮች ሁሉ ማዕከል፡ መጀመሪያ እና የመጨረሻ መዳረሻ አድርጎ መያዝ ነው። ክርስቶስ ለሰው ልጅ "የማይጎድል ሙላት" ነው። እርሱን ያገኘ ሰው፣ "ጉዳዬ ተፈፀመ" ይላል፤ ምክንያቱም ከእርሱ በላይ የሚያረካ ሌላ ጉዳይ በሰማይም በምድርም የለምና። ‎
‎2. ለናፍቆት የሚሆን ጸጋ 🙌
‎ ‎ነገር ግን ይህንን ቅዱስ አቋም ይዞ እስከመጨረሻው መዝለቅ በሰው ተፈጥሮአዊ አቅም የሚቻል አይደለም። ስሜታችን ይዋዥቃል፣ ትኩረታችን ይበተናል፤ ዛሬ የነደደው የፍቅር እሳት ነገ በኑሮ ነፋስ ሊቀዘቅዝ ይችላል። ብዙዎቻችን ጌታን በመከተል ውስጥ "ገባ ወጣ" እያልን እንቸገራለን። ለዚህ ነው ከፍተኛ የሆነ የጸጋ እርዳታ የሚያስፈልገን። ‎ ‎ጸጋ የሚያስፈልገው ለመዳን ብቻ ሳይሆን፣ በፍለጋው ለመቀጠልም ጭምር ነው። ‎ናፍቆታችን እንዳይበርድ፣ ፍቅራችን እንዳይቀዘቅዝ፣ አይናችን ከእርሱ ላይ እንዳይነቀል የሚያደርገው ብቸኛው ጉልበት "ጸጋ" ነው። ጸሎታችን "ጌታ ሆይ ችግሬን ፍታ" ከሚለው ጸሎት ከፍ ብሎ፣ "ጌታ ሆይ፣ አንተን መፈለግ እንዳይሰለቸኝ፣ ናፍቆቴ እንዳይሞት፣ ፍለጋዬ ሳይጎድልብኝ እስከ እድሜዬ ፍጻሜ ድረስ እንድከተልህ ጸጋህ ይብዛልኝ" ወደሚል የህይወት ኪዳን ማደግ አለበት። 🔥🤲 ‎ ‎የህይወት ትልቁ ስኬት ጅምሩ ላይ ሳይሆን ፍጻሜው ላይ ነው። ትልቁ ድል የፈለጉትን አግኝቶ መደሰት ሳይሆን፣ ፈላጊው ከሚፈልገው ጌታ ጋር ተገናኝቶ ማረፍ ነው።🙇‍♂️ ‎ ‎መንፈስ ቅዱስ ሆይ ፣ ዛሬም  ከተተበተብንንበት የኑሮ "ጉዳዮች" አይናችንን አንስተን፣ የዘላለም "ጉዳይ" በሆነው በኢየሱስ ላይ እንድንተክል በሃይልህ አንቃን😭: ከምድር ጉዳዮች አላቅቀን🙏። ‎
‎አይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ ‎ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ ‎ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ ‎ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ ‎እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ ‎ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ ‎ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ ‎ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ✨ ‎
‎✒️ Abenezer Mathewos

መንፈስ ቅዱስ 😭

ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ 🧎🧎‍♂ ከእግሮችህ መድኃኒት ይዤ እንድነሳ 💊 ማርቆስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁰ ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት። ³¹
ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ 🧎🧎‍♂ ከእግሮችህ መድኃኒት ይዤ እንድነሳ 💊 ማርቆስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁰ ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት። ³¹ እናንት ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ አላቸው፤
የሚመጡና የሚሄዱ ብዙዎች ነበሩና፥ ለመብላት እንኳ ጊዜ አጡ።
³² በታንኳውም ብቻቸውን ወደ ምድረ በዳ ሄዱ።

ከግርግሩ ሽሽት... ወደ እረፍቱ ጓዳ! 🌿 ‎ ‎የሰው ልጅ ነፍስ አቅም የምታጣው በስራ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ እረፍት በነሳው የዓለም ሁካታና ግርግር ምክንያት ነው። በዙሪያችን ያለው ትርምስ፣ የሚመጣውና የሚሄደው የሰው ብዛት፣ እንዲሁም የማያቋርጠው የኑሮ ሩጫ የውስጥ ሰላማችንን ይበላዋል። በዚህ ጊዜ ነፍስ የሚሰማት ከፍተኛ ድካም አካላዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነው። ለዚህም ነው ከዚህ ሁሉ ግርግር ተነጥሎ "መጥፋት" ወይም ወደ ፀጥታው ስፍራ ማፈግፈግ ምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ የሚሆነው። ይህንን እውነታ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለይ በማርቆስ ወንጌል ላይ ደቀ መዛሙርቱ በሰዎች ግርግር ተጨንቀው እህል እንኳን ለመብላት ጊዜ ባጡ ሰዓት የሰጣቸው መመሪያ ይህንን  ሀሳብ የሚያጸና ነው። ‎
‎ "ብዙ ሰዎች ይመጡና ይሄዱ ስለ ነበር... እርሱም፦ እናንተ ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት እረፉ አላቸው።" (ማርቆስ 6፥31)
‎ ‎ይህ የጌታ ጥሪ የሚያሳየን፣ ከግርግሩ መራቅና ለብቻ መሰወር የመንፈሳዊ ብርታት ምንጭ መሆኑን ነው። ግርግሩና ትርምሱ ባለበት ስፍራ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ይከብዳል። ስለዚህ ነፍስ ከለመደችው አካባቢ ርቃ፣ ሁሉንም ነገር ረስታ ወደ ጌታ እግር ስር ስትሰደድ፣ ያኔ ትክክለኛውን "መድኃኒት" ታገኛለች። መድኃኒቱ ያለው በሰዎች መካከል በሚደረግ እሩጫ ውስጥ ሳይሆን፣ በጌታ ፊት በሚደረግ ፀጥታ ውስጥ ነው። ሰው ወደ ምድረ በዳ (ወደ ፀጥታው ስፍራ) ወርዶ በጌታ እግር ስር ሲቀመጥ፣ የዓለምን ጫጫታ በሰማያዊ ዜማ ይለውጠዋል። ‎ ‎በዚያ የእግሮች ስር በሚገኝ ቆይታ ውስጥ፣ የተሰበረ ልብ ይጠገናል፣ 💊 የደከመ ጉልበት ይበረታል። ከሁካታው መሸሽ፣ ባዶ እጅን ለመመለስ ሳይሆን፣ ፈውስን ታጥቆ ለመነሳት የሚደረግ ቅዱስ ጉዞ ነው። ማንም ሰው ከግርግሩ ርቆ በጌታ እግር ስር ጊዜን ወስዶ ሲቀመጥ፣ የነፍሱን ቁስል የሚያደርቅለት መድኃኒት ተቀብሎ፣ የቀድሞ ማንነቱን በዚያው ትቶ፣ ኃይልን የተሞላ አዲስ ሰው ሆኖ ወደ ዓለም ይነሳል። ‎ ‎ "ሽፍት" በል መድኃኒትህን ተቀበል 🙌 💊 ✒️ Abi-Kidan

ሰልፉን ለባለቤቱ ! 🛡
2 ዜና 20 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ እዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፦ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። … ¹⁷ እናንተ በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥ ነገም ውጡባቸው።
🛡️ በህይወታችን ብዙ ጊዜ የምንዝለው፣ የምንደክመውና ተስፋ የምንቆርጠው ጠላት ስለበረታብን ብቻ ሳይሆን፤ «የእኔ» እና «የእግዚአብሔር» የሆነውን የትግል ሜዳ ለይተን ባለማወቃችን ነው። የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- 📖 «ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ከታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡ።» (2ኛ ዜና 20፥15) 🔥 ጣልቃ አትግባ! እግዚአብሔር «ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው» ሲል፣ ይህ የባለቤትነት ጥያቄ ነው። እርሱ ጉዳዩን «የእኔ ነው» ካለ በኋላ፣ እኛ በጭንቀትና በሰውኛ ጥበብ ያንን ጉዳይ ለመፍታት ስንሞክር፣ በእግዚአብሔር ክልል ውስጥ ያለ ፈቃድ እንደመግባት ይቆጠራል። እግዚአብሔር ኃላፊነት በወሰደበት ጉዳይ ላይ እጅን ዘርግቶ ለመርዳት መሞከር፣ እግዚአብሔርን አለማመን ብቻ ሳይሆን፣ ክብርን የመጋፋት ያህል ከባድ «መንፈሳዊ ቅሚያ» ነው። እግዚአብሔር ኃላፊነት በወሰደበት ጉዳይ እጅህን አትክተት! ቀጥሎም ቃሉ እንዲህ ያዛል፡- 📖 «እናንተ በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ... ተሰለፉ፥ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ።» (2ኛ ዜና 20፥17) 🛑 መቆም «ቁሙ፥ የእግዚአብሔርንም መድኃኒት እዩ» የሚለው ቃል የሽንፈት ምልክት አይደለም። መቆም ማለት፡- • ፍርሃት ሲያርበደበደን እምነት ግን እግሮቻችንን በምስጋና እንዲቸነከሩ እና እንዲፀኑ ሲያደርግ ነው። • ሰልፉ ከእኛ አቅም በላይ ሲሆን፣ ሰይፍ ከመምዘዝ ይልቅ እጅን ወደ ላይ አንስቶ ማምለክ፣ ጦር ከመወርወር ይልቅ በዝማሬ መውጣት፣ ጠላትን ግራ የሚያጋባና ሰማይን የሚያንቀሳቅስ የላቀ የጦር ስልት ነው። [Olay Xoosaaga] ✨ «ተወው» ሲልህ ደስ ይበልህ የማይመለከተንን ጦርነት ስንዋጋ ውጤቱ ሁሌም ቁስልና ድካም ነው። እግዚአብሔር ግን «እናንተ በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም» ሲለን፣ «አንተ አቅም የለህምና አረፍ በል፤ ሸክሙ ለትከሻህ አይመጥንም፤ እኔ ግን ለጠላትህ እመጥነዋለሁ» እያለን ነው። ስለዚህ #_እጅን_መሰብሰብ ሽንፈት ወይም የእግዚአብሔር ዝምታ ሳይሆን፣ ኃያሉን አምላክ ወደ መድረክ መጋበዝ ነው። Brother በህይወትህ እጅግ እያስጨነቀህ፣ እንቅልፍ እየነሳህና አቅም እያሳጣህ ያለ ጉዳይ ካለ፣ ቆም ብለህ ራስህን ጠይቅ፡- «ይህ ሰልፍ የእኔ ነው ወይስ የእግዚአብሔር?» በል🙌 አቅምህን አትባክነው! ሰልፉ ከአቅምህ በላይ ከሆነ፣ በተፈጥሮ ሕግ የማይፈታ ከሆነ እና አንተ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርገህ ምንም ካልተለወጠ፣ በእርግጥም ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው። በቃ ልቀቅለት ምን አለፋህ፡ ብዙ ሳትቆስል፡ ሳትደማ የባሰው ሳይመጣ ሰልፉን ለባለቤቱ ለቀህ ራስህ አድን🙌! 🙌 🧎‍♂️🧎‍♂️ «እግዚአብሔር ሆይ፣ ጣልቃ በመግባቴ ያበላሸሁትን ይቅር በለኝ፤ አሁን ግን ከመንገድህ ላይ ዘወር እላለሁ፤ መድረኩን ላንተ እለቃለሁ፤ አንተ ተዋጋ፣ እኔ ልይ፣ እኔ ልመስክር!» ብለህ ልቀቅለት። ድሉ እንድረጋገጥልህ ፡ሰልፉን ለባለቤቱ ለእግዚአብሔር ልቀቅ !🙌 © አቤንኤዘር ማቴዎስ

‎“እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፤ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።” ‎  — 2ኛ ሳሙኤል 22፥35 ‎ ‎ዳዊት "እጆቼን ያስተምራል ክንዶቼም የናስ ቀስት ይገትራሉ"። ይህ የናስ ቀስት ምሳሌያዊ ነው፡ ናስ አይታጠፍም፡ በሰው ጉልበት የናስ ቀስት መግተር አይቻልም። ዳዊት እያለ ያለው፦ " እግዚአብሔር ሲያስተምረኝ ፣ ተፈጥሮአዊ አቅሜ (My Limit) ይሰበራል፣ አንድ ተራ ሰው ሊያደርገው የማይችለውን ነገር የማድረግ ልዕለ-ተፈጥሮአዊ ጉልበት (Supernatural Strength) ይሰጠኛል " ነው። ‎ ‎እግዚአብሔር ሰልፍ አስተማሪዬ ነው! ‎

አንገብጋቢ ጉዳዬ🥺

ዝም ብዬ እቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ እለቃለሁ 🙌

በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ስም ያለው ምስጢር ልንገርህማ ከዋክብት እንዴት እንደሚበሩ ከመማራቸው በፊት በብርሃን የነበረ፤ ጊዜ ራሱን መቁጠር ከመጀመሩ በፊት እንዴት መጀመር እንዳለበት የተማረበትን መቁጠሪያ ያ ግርማዊ በተውሶ ማህፀን ውስጥ ገብቶ፣ እርሱ ራሱ የፈጠረውን አየር እየተነፈሰ በጸጥታ ወደ ምድር ደረሰ፣ መለኮትን በድክመት ውስጥ፣ ዘላለማዊነትን በልብ ምት ውስጥ አየነው። ያ ዘመንና ክብር የጠገበ ግርማዊ ኦሜጋ ሊፈስ በሚችል አካል ውስጥ ማለቂያ የሌለውን ክብሩን ደበቀ። እርሱ ስራመድ፣ ፍጥረት አወቀውት ነፋሳት ታዘዙለት፣ ውሆች እንኳ እነሆኝ አሉት። አጋንንት ነገረ ጥንትን አስተውሰው በእንቅጥቅጥ ተንዘፈዘፉለት። ጥቂት ሲናገር ቃሎቹ ከፍጥረት በላይ የሸመገለ ፣ ከተራሮች የገዘፈ ነው። ሀሳቦች ከመወለዳቸው ቀድሞ ያውቃል። የፍጥረት አስታውሎት እርሱን ልገነዘበው አይችልም። ያልተከፈተ ልብ ያያል ፣ማንም ድምፅ አውጥቶ ለመጠየቅ ያልደፈረውን ድብቅ የፍጥረት እንቆቅልሽ ይመልሳል። ለስሪቱ ያልበጀ ለርሱ እንደ ትሁት ይታዘዝለታል። ውሃ ልሸከምህ ይለዋል፣ ደመናም ወለል ከልሆንኩልህ ብሎ ይታዘዘዋል፣ ፀሀይም በቀን ይጠልቅለታል። ብዙ ሰዎች ለምን እንደሆነ ሳያውቁ ተከተሉት። ነፍሳቸው አስታውሳ አእምሯቸው ትውስታውን እንደዘነገ ሆነው ለቀው ተከተሉት። ፍጥረት በትስጉቱ ስደነቅ ውሎ እያደረ ያንን መድን ዓለም መስቀል ላይ አንደ የሞተ ሰው ተመለከተ። ነገር ግን በማይታየው ዓለም፣ የሞት በሮች ተሰነጠቁ፣ እርግማን ተሰበሮ፣ መለኮት ሰውን ታረቀ ሦስተኛው ቀን እስክመጣ አጽናፈ ዓለሙ ትንፋሹን ቆጥሮ በጥልቅ ጸጥታ የመስቀል ወግ ተደመ። እናም ከዚያ ጸጥታ… ንጉስ ከመኝታ እንደምነቃ ሆኖ ከመቃብሩ በእርጋታ ወጣ። በነጎድጓድ ድምፅ ሳይሆን፣ እጁ ላይ የበደሌን ጠባሳ ማህተም ይዞ— ይህ ማህተም ለሚፈልጉት ብቻ የሚበራ ለበደሌ አብ በልጁ ያተመው የስቃይ ንቅሳት ነው። ይህ ምስጥር ኢየሱስ ነው። ቸል እንዳይባል እጅግ ግልጥ፤ ለመግለጽም እንዳይሞከር በጣም መለኮታዊ ነው። ሙሉ በሙሉ ለመረዳትም የማይገባ ሚስጥራዊ ነው። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና። ዮሐንስ 3:16 🖊️ Melkamu Asfaw

Repost from ተስፋ
ለእግዚአብሔር የሚከብድ ልብ የለም! ❤️ አንዳንዴ ራሳችንን ለመለወጥ ታግለን ሲያቅተን፣ ባሕሪያችንን ለማስተካከል ሞክረን ሲደክመን... ተስፋ የምንቆርጥበት ጊዜ አለ። ነገር ግን... እግዚአብሔር "
ለእግዚአብሔር የሚከብድ ልብ የለም! ❤️ አንዳንዴ ራሳችንን ለመለወጥ ታግለን ሲያቅተን፣ ባሕሪያችንን ለማስተካከል ሞክረን ሲደክመን... ተስፋ የምንቆርጥበት ጊዜ አለ።
ነገር ግን... እግዚአብሔር "የማይቻለውን" የሚችል አምላክ ነው። 💯
እርሱ፡- የተሰበረውን የሚጠግን፣ 🤲 የጠመመውን የሚያቀና፣ 🙌 የደነደነውን ልብ በፍቅሩ የሚያለሰልስ ጌታ ነው።❤️ ብቻ ልብህን ክፈትለት። 🙏 @hope_words

ኢየሱስ ይመጣል

Repost from ተስፋ
ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። መዝሙር 9:10 good night ❤️

ዘላለም ግርምቴ 🙌

ማቴዎስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³¹ እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ³² ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታች
ማቴዎስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³¹ እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ³² ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ³³ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።